Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
1268 - Telegram Web
Telegram Web
አኑረን እንዳንል ኑረን ምን አፈራን፤
ግደለን እንዳንል እሣትህን ፈራን፤
ጸሎቱ ጠፍቶናል በፈለገው ምራን።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

https://www.tgoop.com/eyorkis
ሰማዩ መጅ
ምድሩ ወፍጮ
አተር ነፍሴ፣ እማህል ላይ ተንገርጭጮ
ቅጤ ቅርሴ ሲፈራርስ፣
"ኅጢያቴ ነው " ?፣ ልበል ላልቅስ?
"እቅዱ ነው"፣ ልበል ወይስ
እርዳኝ ብዬ ፀሎት ላድርስ?
በላይ በታች፣ መንትያ ጥርስ
አተር ነፍሴ፣ ሲፈራርስ
"አሜን" ልበል ወይ "አያድርስ"?
 
    ㅤ     ㅤ                

ረድኤት አሰፋ

@eyorkis
መንገድ ጠፍቶን ስንደናበር ላረጋጉን ፣ ወደቅን ስንላቸው ላልፈረዱብን ። በድለናቸው ይቅርታን ለሰጡን ፦

ሚስጥራቸውን ላጋሩን፣  ደስታችን ለተካፈሉ፣ ሃዘናችንን ቦታ ለሰጡት ፣ ለተጠነቀቁልን ፣አጋርነታቸው ወረት ለሌለበት ፣ በቆሚነት የኛ ለሆኑ ።

እንድናምናቸው ለሆኑ ፣ ደግነታቸው ለማይስተን ፣ ለሚወዱን ፣  ሊረዱን ግማሽ መንገድ ለሚመጡ ፣  ለሚያበረቱን

ችርስ ለነሱ 🙏

ኑሩልን

   @getmnaleloch

https://www.tgoop.com/eyorkis
Forwarded from ኤልዳን
የህይወቴን ድቅድቅ ጽልመት ለመተንፈስ ምስልሽ ፊት እቆማለሁ። ከአንቺ ውጭ ወጋገን ሚያስፈነጥቅልኝ ያለ አይመስለኝም። የታወረ ሚመስል አይኔ እንኳ አጥርቶ ሚያየው አንቺን ነው።

የችግሬን መአት ማዥጎደጉደው ለአንቺ ነው። ቀላሉንም ከባዱንም። ከአንቺ ውጭ ማን እህ ብሎ ይሰማኛልና። ለፍልፌልሽ ስጨርስ ውስጤም ችግሩም ቀሎ ሀይቅ ላይ እንደተንሳፈፈ እቃ ይታየኛል። ለካ እራሴ ነኝ አክብጄ ሳሰምጠው የምውል እላለሁ።

የዕለት ተዕለት ፈተናዬን በምሬት ስተነፍስልሽ ይገርመኛል። አንዳንዴ ቀድመሽ ተገኝተሽ ብታነሺልኝ ብታርቂልኝ ሁሉ እመኛለሁ። አንዳንዴ እኔን አዝለሽ እንድታሻግሪኝ እፈልጋለሁ። ከአንቺ ውጭ አዳኝ ያለኝ መስሎ አይሰማኝም። እየተደናቀፍኩ፣ እየወደቅኩ አንቺን መጠበቅ ወይ ላንቺ መጥቶ መናገር ነው ማስብ።

አንቺ ከእኔ በላይ እንደተፈተንሽ፣ እንደተቸገርሽ፣ ህይወትሽ ጨልሞ እንደነበር ስሰማ ይገርመኛል። ሐኪም ራሱ ይታመማል ቢባል ዘበት እንደሚመስለኝ ነው ማስብ።

ልጅሽን አዝለሽ ተሰድደሽ ነበር።
ልጅሽ ጠፍቶ አንብተሽ ነበር
ልጅሽ ተሰቅሎ አዝነሽ ነበር

ድንግል ማርያም እኔማ ምን ሆንኩ። ደግሞስ ለአንቺ ሳወራ ሁሉ ተቀርፎልኝ የለ። ግን ምሬቴ አይጣል ነው። በአንቺ ትከሻ ታዝዬ እያለፍኩ። በአንቺ እቅፍ መሽጌ እያመለጥኩ እንኳ አለመፈተንን ነው ምማጸን። ብርሃንን ብቻ ነው ምለምን። ድሎትን ብቻ ነው ምጠይቅ።

ሳሳዝን!!!
ያንተ ጓደኛ ይሄ ነው?!
🚢🚢🚢
ጦርነቱ ጋብ ካለ በኋላ አንድ ወታደር በውጊያ ሜዳ የወደቀውን ጓደኛውን ለመፈለግ አለቃውን ያስፈቅዳል፡፡

አለቃውም 'መሞቱ ለማያጠራጥር ሰው ብለህ ህይወትህን አደጋ ላይ እንድትጥል አልፈቅድልህም' በማለት ፍቃድ ይነፍገዋል፡፡

ወታደሩ ግን አሻፈረኝ ብሎ ፍለጋውን ይቀጥላል፡፡ከፍለጋ በኋላ እሱም ሞት አፋፍ ላይ ባደረሰው ሁኔታ ቆስሎ የሞተ ጓደኛውን አስክሬን ተሸክሞ ይመጣል፤አለቃውም 'ይሞታል ብዬህ አልነበረም? ለሚሞት ሠው ብለህ ይህን ሁሉ መስዋዕትነት መክፈል ነበረብህ፤' በማለት ይወቅሰዋል፡፡
🚢🚢🚢

ወታደሩ ግን በስራው ደስተኛ ነበር ፡፡
አለቃዬ ይህኮ ምንም ማለት አይደለም ጓደኛዬ በሞት አፋፍ ላይ ደርሸበት ያለኝን ብነግርህ ትረዳኝ ነበር ፣ አለቃውም 'ምን አለህ?' ሲለው
ወታደሩም

#እንደምትመጣ_እርግጠኛ_ነበርኩ'፡፡
❖ እውነተኛ ጓደኛ ማለት ሁሉም ሠው ሲሸሽህ እሱ ግን የሚፈልግህ ነው!


@eyorkis
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጨለማ ውጦት ስጋ ነፍሴን
እድሜ ዘመኔን ብርሃን ያጣው
ለመዳን ሳይሆን ለመጠመቅ
ስንኩልኩል እያልኩ ደጅሽ መጣው

ቤትሽ ግን ስደርስ ስለት ገባው
ተዓምር ካረገ ኪዳን ቃልሽ
በምህረት እጅሽ አይኔን ዳብሰሽ
ቀሪ ዘመኔን  ላገልግልሽ
ብዬ ገባሁኝ 
ከአጥማቂው ስር
እንዴት ይበርዳል ወየው ወየው
እምነት ከአይኔ ላይ አረኩና
አረፍ እንዳልኩኝ አንቺን አየው

ስዕልሽ አለ ግርዳው ላይ
ልቤ አላመነም ሀቅ ይሸሻል
ትልቅ ዙፋን ላይ ተቀምጠሽ
መድህነ አለም ታቅፈሻል
እንዴት ልካደው ተንተባተብኩ
ፊደል ለጎመ የአፌ መፍቻ
አምላኬን በእጅሽ እያየሁት
የወጣኝ ነገር እምባ ብቻ

የልቤን መቃን ፍቅር ያንኳኳው
ተውጬ ሳለው በሰመመን
እደጅሽ ቆሞ ማሪኝ የሚል
በርጠሚዎስ ነኝ የዚህ ዘመን
የፍቅር እናት የአዶናይ
የጭንቅ ደራሽ የብዙሃን
ድፍኑን አይኔን ገለጥሺልኝ
በልጅሽ በኩል እመብርሃን?

ከህርያቆስ ልዋስ ቅዳሴሽን
ላዚመው ይድረስ ከአርያም
ድቅድቁን ሚገፍ ሀይል ያለው
ፀሀይ ነው ስምሽ ድንግል ማርያም!

@mikiyas_feyisa
አንዳንዱ ጋር ቸኩዬ አንዳንዱ ጋ ፈጥኜ ዋጋ ከፍያለሁ ።
አንዳንዱ ጋር ጥጋቤ አንዳንዱ ጋ ትህትናዬ አስገምቶኛል።
አንዳንዱ ጋር መጠየቄ አንዳንዱ ጋ ዝምታዬ ጥያቄ አስነስቷል። አንዳንዱ ጋር ጥንቃቄ አንዳንዱ ጋ ግዴለሽነቴ አስመርምሮኛል ።
አንዳንዱ ጋር ጨዋነቴ አንዳንዱ ጋ ብልግናዬ ረብሿል።
አንዳንዱ ጋር አማኝነቴ አንዳንዱ ጋ አህዛብነቴ አጠያይቋል።
አንዳንዱ ጋር ቸርነቴ አንዳንዱ ጋ ስስቴ አስገርሟል !!

Adhanom Mitiku
@Kinebook
ውይ ወንዶች!

ባል ነገረኛ ሚስቱ በነገር ስትለበልበው እስኪ በረድ ቀዝቀዝ ብትል ይልና  ለጉብኝት ወደኢየሩሳሌም ይወስዳታል ይላል የሰማሁት  ቀልድ! ያው ምላሷን ቻል አድርጎ ብዙ ነገር ጎበኙ። በመጨረሻ ኢየሱስ በሶስተኛው ቀን ከሞት የተነሳበትን መቃብር ጎብኝተው ከተመለሱ በኋላ ምሳ ሲበሉ ሚስት ትን ይላታል። (ስንጠረጥር እየበላችም ንዝንዝ ላይ ነበረች 😀) ብቻ ትንታው አጓጉል ስለነበር ትሞታለች። በኋላ የአካባቢው ሰወች ባልን በገጠመው ድንገተኛ ሀዘን ሊያፅናኑት ሞከሩ  "በደረሰብህ ነገር እናዝናለን  ግን እዚህ የተቀደሰ ስፍራ መሞቷ እድለኛ መሆኗን ያሳያል...በአጋጣሚ ደግሞ እዚሁ ከተቀበረች ለዚህ ወር ብቻ  ለቀብር ምንም አትከፍልም ነፃ ነው፤ ወደአገርህ ለመውሰድ ከፈለክ ግን በትንሹ ለማጓጓዣ አስር ሽ ዶላር ያስወጣሀል ይሉታል! ባል"ግዴለም የፈጀውን ይፍጅ ወደአገሬ  ጫኑልኝ" ... አለና በሆዱ " እዚህ ልማደኛ ቦታ በሶስተኛው ቀን ብትነሳ የማን ያለህ ይባላል?" 😀 ጮክ ብሎ ደግሞ "እኔን ያስቀድመኝ የኔ ፍቅር... ህህህህህህ"

ከsocial media የተገኘ

https://www.tgoop.com/eyorkis
ለስንቱ አዲስ ቀን ፣በወጣበት እለት
      ለምን ለኔ ብቻ ፣ጨልሞ ቀረበት?

ስንቱ ተስፋን አስሮ ፣በሚራመድበት
    ለምን በመንገዴ ፣እሾህ ጣይ በዛበት?

ለምን እርምጃዬ ፣የሰዉ...
........ አይን አቀላ
  ደረቅ እንጀራዬን ፣አዩብኝ በተድላ?

ብዬ ወደ አምላኬ ምሬቴን....
........ሳሰማ ፣ሔጄ ከደጃፉ
ከታገሱት ፣ሁሉም ያልፋል....
......ይላል ለካ ፣መፅሀፉ


እንግዲማ.......

ልታገሰዉ ቢያቆስለኝም ፣....
........ ቢሰለችም ያለዉ ነገር
የአምላክ ቃል አይሻርም ፣....
.......ያልፋል ሁሉም አንድም ሳይቀር


ይሔም ያልፋል......
.............ግን ያለፋል
??????

ባህር ቢሆን የመከራዉ አበዛዙ
ታንኳ ተስፋን ከአምላክ.....
.......... ዘንድ ሂዱ ያዙ
::
@eyorkis
Forwarded from ሰው


መጀመሪያ 100
ሣጥናኤል አጥፍቶ
ዘጠኝ ዘጠኝ ቀርቶ
አዳም ተተክቶ
ምግብ ሰው አስቶ
ሔኖክ ጥበብ ሰ’ጥቶ
በኖኅ ውሃ ከፍቶ

የምድ’ር ፍጥረት ጠፍቶ
ካም ለ’አፍሪካ በቅቶ
ኩሽ ኢትዮጵያ መ’ጥቶ
ዮ‘ቶ’ር ተመልክቶ
ሳባ ንግስተ ‘ቶ’
ጽዮን ታቦት ገብቶ
አይዙር 600

በዮዲት ጉድ ፈልቶ
ለ3 ሰዎች ታይቶ
ስጋ አምላኩን ሞልቶ
ከነፍሷ ነፍስ’ ነስቶ
አባት ቃል አውጥቶ
መንፈስ ከላይ ዓይቶ

ጌታ ምራቅ ተፍቶ
ዓይን ለሰው ሰርቶ
እጆቹን ዘርግቶ
እውሩን አብርቶ
ጎባጣን አቅንቶ
ዓለም ይህ’ን ጉድ ሰምቶ

12ቱን ጠርቶ
ስጋውን አብልቶ
ደሙን አጠጥቶ
አንዱ ከእር’ሱ ሸሽቶ
ፍቅሩን በጦር ወግቶ
ዲናር ከቃል ጎልቶ
ስሞ አምላኩን ከድቶ
ንጉሥ አንገት ደፍቶ
የማይሞተው ሞቶ
ጨለማን አንግቶ
ነፍሳትን አንስቶ

ትል ያሬድን መርቶ
ዜማን አሰምቶ
ተከታትሎ ዐርብቶ
አራት 40 ገዝቶ
ናኦድ ጥበብ ቀድቶ
ከስምንት ተጣልቶ

ፋሲል ኖኅን ሽቶ
ግንብን አሰርቶ
ምስጢር ቁጥር ፈቶ
ከዘመን ተጋፍቶ
ታሪክ መርማሪ አጥቶ
ጥበብ በሩን ዘግቶ
መጀመሪያው 100
መጨረሻው ጠፍቶ

እንባ ደጅ ጠንቶ
ሙሴን አስነስቶ
ውሃን ከፍሎ በ‘ቶ’
ግብፅን ባህር ከ‘ቶ’
የቆረጣት ለፍቶ
አስማታሟ በትር
የት ገባች ያች ቶ
አሃሎ አሐዱ ኖላዊ
© ፋሲካው ጌታቸው ገሰሰ
እረኛ ነበርኩኝ!
እንስስሳት ጠባቂ ምስለ ክራር ዜማ፡፡
በነ ራሔል ርስት በዳዊት ከተማ

ከለታት በአንዱ ለት
ፍርሐት ሲወጅበኝ ፤
ኸብጤዎቼ ጋር ሰምቼ ብርህ ቃል
አምላኬን አየሁት
በጉረኖዬ ውስጥ በላሞቼ መሃል፡፡

ለካስ የወጀበኝ ያነ የመፍርህ ቃል
የገብርዔል ነበር ለእረኞች ይረቃል፡፡
ለንዲህ ያለው ምስጥር ምንተ ልብ ይበቃል?
እንጃ ብቻ!

እኔን የደነቀኝ
እኔን ያሳፈረኝ ልቤ ቢጠነሰስ
ደመ ነፍስ ካሌኳቸው ከላሞቼ ማነስ፡፡

እሱስ ቢሆን!
ምን እግዜር ቢሆን ነው
ምን ኪዳን ቢያጠልቀው
ምን ምስጢር ቢያረቀው
ዙፋኑን ረስቶ
የሰው እቅፍና በረት የናፈቀው?

እስኪ ተመልከቱ!
የሳት መንጦላይት ግርማ ቤቱን ንቆ
በበረት ውስጥ ሲያድር በላም ትንፋሽ ሙቆ

እስኪ ተመልከቱት
በቤቱ ዝማሬ ሃሌ ሳይታጎል
ከሰለስት ነገስቶች አምሃ ሲቀበል

ግና እረኝነት መና !
ስማና ግብራችን ትርጉሙ ሲገበር
መግቦ ሚያሳድር!
ለወደዱት መሞት እንደ እግዜር ማን ነበር፡፡

መልካም ገና ❤️😘

©ፋሲካው ጌታቸው ገሰሰ
www.tgoop.com/lomi_teratera
🌺🌺🌹💐💐
@Tobiya_Kinet
@eyorkis
Forwarded from ጦቢያ ኪነት
"እነሆ፥ድንግል ትጸንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ስሙንም አማኑኤል ይሉታል።"(ማቴ፦፩፥፳፫)የተባለው ይፈጸም ዘንድ "ኢየሱስም በይሁዳ ቤተልሔም በንጉስ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥እነሆ ሰብዓ ሠገል የተወለደው የአይሁድ ንጉስ ወዴት ነው? ኮከቡን በምስራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናል እያሉ ከምስራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።"
(ማቴ፦፪፥፩-፪)
እንኳን ለ፳፻፲፯ ዓ.ም ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት "ገና" በሠላም አደረሳችው አደረሰን!
መልካም በዓል ከነቤተሰቦቻችሁ ይሁን!
"ቤዛ ኹሉ ዓለም ዮም ተወልደ"

@tobiya_kinet
በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ!

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

የልደትና የጥምቀት ዘመን በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋኒ፣ በግእዝ ዘመነ አስተርእዮ፣ በአማርኛ የመገለጥ ዘመን ይባላል። ጥምቀት የሚለው ቃል “አጥመቀ” ከሚለው የግእዝ ቃል/ግሥ የተገኘ ሲሆን በቀጥታ ሲተረጎም በውኃ ውስጥ ገብቶ መውጣት፣ መጠመቅ ማለት ነው። በምሥጢራዊ ትርጉሙ ግን ጥምቀት ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ሲሆን ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ተወልደን የሥላሴን ልጅነት የምናገኝበት፣ መንግሥተ ሰማያት የምንገባበት፣ ኀጢአታችን የሚደመሰስበትና ድኅነትን የምናገኝበት ዐቢይ ምሥጢር ነው። (ዮሐ. ፫፥፭)
ከእግዚአብሔር ያልመጣ ሲሄድ በረከት ነው🥰🥰

@eyorkis
የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት (ፓርላማ)

አዲስ አበባ ፤ ጥር -- 1952 ዓ.ም

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

@eyorkis
( ዛሬም እንጉርጉሮ )
================

ይህ ልባችን
እስከ ስሩ እስከ ጥጉ ቢበረበር
ኩራታችን የገደለው ስንት ፍቅር
ውስጡ ነበር ....

ህይወታችን
በቅን ዳኛ በጥቂቱ ቢመረመር
ማፈራችን ያሳለፈው ስንት ጸጋ
ገጥሞት ነበር ...

በትነነው ስናበቃ
የሰጠንን ቁና ሰፍሮ
አይከብድም ወይ
አምጣ እያሉ ዛሬም ለእግዜር እንጉርጉሮ ??

@getmnaleloch
@tobiya_kinet
@eyorkis
ፍቅረኛ ለመያዝ ቀና ልብ ይፈልጋል። ከዛ ደግሞ አስተዋይ መሆን አለብን። ምክንያቱም ዘው ብለን የምንገባው የሰው ህይወት ውስጥ ነው።

ስንወጣ ደግሞ የሰውን ልብ እና ቅስሙን ሰባብረን... ህይወቱን አመሰቃቅለን ... ስሜቱን ጎድተን ተስፋ አስቆርጠን ነው የምንወጣው።

ይህን ሁሉ በደል ከማድረሳችን በፊት እስክንበስል ፍቅረኛ አንያዝ።

- ይኸውልሽ <አርግዣለሁ > ብለሽ ፍቅረኛሽን የመፈተን እድሜ ላይ ካለሽ ፍቅረኛ ይቅርብሽ።

ምን አድርጌ ላስደስተው ብሎ ከመጨነቅ ይልቅ ምን ብዬ ላስጨንቀው የምትይበት እድሜ ላይ ከሆንሽ ይቅርብሽ።

የእንትና ባል ለሷ እንዲ ያደርጋል አንተ ግን... ምናምን የሚል አስተሳሰብ ላይ ከሆንሽ ገና አልበሰልሽም።

ፍቅር ማለት ካፌ ለካፌ ሬስቶራንት ለሬስቶራንት መንከራተት መስሎ የሚሰማሽ ከሆነ በቃ ይቅርብሽ።

ፍቅሩን የገለፀልሽን ቴክስቶች ለሴት ጓደኞችሽ በማሳየት <እኔ እኮ እስከዚህም ነኝ .. > ብለሽ የማውራት ሞራል ላይ ከሆንሽ ይቅርብሽ።

- ይኸውልህ። ስለፍቅረኛህ ለጓደኞችህ መናገር የምታፍርበት ጊዜ ላይ ከሆንክ ተወው ፍቅረኛ አትያዝ።

<እኔ እኮ ለሷ እስከዚህም ነኝ ስለምታሳዝነኝ ነው ወይ ደግሞ እሷ ናት በደንብ የምታፈቅረኝ > ብለህ የምታወራበት እድሜ ላይ ካለህ አታፍቅር።

አውቀህ ስልክ አለማንሳት ... ሚስኮሎቿን ለጓደኞችህ ለማሳየት የምትጣጣር እድሜ ላይ ካለህ ይቅርብህ። ጊዜ ያለመስጠት ...

የማስቀናት... ሌላ ሴት የመደረብ ሞራል ላይ ከሆንክ ገና ስለሆንክ ፍቅረኛ አትያዝ።

ስንት ልቦች የተሰበሩት... ስንት ተስፋዎች የተቆረጡት ...ስንት ቤቶች የተዘጉት ... ስንት ህይወቶች የጠፉት በግዴለሽ ፍቅር ነው።

ፍቅርን ሁሉም ሰው ይፈልገዋል። የሰው ልጅ ሁሉ ይፈልገዋል። ግን በግዴለሽ አፍቃሪ ነን ባዮች አጥተውታል።


ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን

ምንጭ ከሀሽማል ወመዘክር የtg Chanel

@eyorkis
"ባሌም ልጄም ሞቱ ፤እንደሁ ደህንነቱ።"

አለች
እኛ ደህና😊😊😊👌👌👌

@tobiya_kinet
@eyorkis
አንንዳንዴ ሁሉንም ነገር ጥላችሁ መጥፋት አምሯችሁ ያውቃል ? ከችግራችሁ፣ከሀሳባችሁ ፣ከሸክማችሁ፣ከኑሯችሁ፣ካስጨነቃችሁ፣ ከሚወዷችሁ፣ ከሚጠሏችሁ፣ ከሚያሟችሁ፣ ከሚያስቡላችሁ፣ከሚያሳምሟችሁ ብቻ ከሁሉም ነገር ብን ብላችሁ መጥፋት አምሯችሁ አያቅም? እኔ ያምረኛል ርቄ በማያቀኝ ማህበረሰብ ውስጥ ስለማንም ሳላስብ ፣ሳላስታውስ፣ተረጋግቼ፣ሰላሜን አጊንቼ መኖር አስቤ አውቃለሁ።



አንዳንዴ በጣም ብዙ ሰው ስታውቁ ጭንቀት ይጨምራል የምሬን ነው።አንዳንዴ አዲስ ሆኜ የምወጣበት ውሃ ባገኘሁ ብየ አስባለሁ ልክ እንደ ሞኝ።ግንኮ ሞኝ ሆኜ አይደለም የምር በጣም ስለደከመኝ ነው የማቃቸው ሰወች ሁሉ ስላቃቱኝ ነው።ራሴን ለመፈለግ ጊዜ ስላጣሁኝ ነው።ስለራሴ ለማሰብ ጊዜ ስላላገኘሁ ነው።ብቻ ያ ውሀ ብየ ያሰብኩት ውስጥ ሔጄ ወደውስጥ እንደ ክርስቶስ 3 ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያልኩ ብወጣ እና ከዚህ ሁሉ ተፈውሼ በ40/80 ቀን ክርስትና እንደተነሳች ጨቅላ ህፃን ንፁህ ብሆን ብየ ተመኘሁ።ራሴን ከክርስቶስ ጋር ማወዳደሬ ወይ እንደሱ ንፁህ ነኝ ማለቴ አይደለም።መንፃት መፈለጌ እንጅ......አንድ ቀን ግን ስኬታማ የሆነ ማንነቴን በመስታወት ፊት ለፊት ቆሜ አይ ይሆን ? እኔ እንጃ ብቻ ያስፈራኛል ካላገኘሁት ግን ሁሉንም ነገር ጥየ ብን ብየ መጥፋቴ አይቀርም
(መሰለኝ🙄)።


@nibab_lehiwot
@eyorkis
2025/02/25 03:08:28
Back to Top
HTML Embed Code: