የት ነኝ?
""""""""""
ከማን ነው የተጣላሁ?
ከማነው የተኳረፍሁ?
ከህይወት መስመር ላይ
መንገዴን ያዛነፍሁ?
ከፍቅር፣ከአለም ራሴን ያሸሸሁ
በብቻዬ ለቅሶ ሀዘን የተቀመጥሁ፥
ማን ገሎ ጥሎኝ ነው ወድቄ የተገኘሁ?
ህዝብነቴ የታል? ያለግንብ ያለ አጥር፣
ወዴት ነው መንገዱ?
የት ነው የሰው ሀገር?
አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
""""""""""
ከማን ነው የተጣላሁ?
ከማነው የተኳረፍሁ?
ከህይወት መስመር ላይ
መንገዴን ያዛነፍሁ?
ከፍቅር፣ከአለም ራሴን ያሸሸሁ
በብቻዬ ለቅሶ ሀዘን የተቀመጥሁ፥
ማን ገሎ ጥሎኝ ነው ወድቄ የተገኘሁ?
ህዝብነቴ የታል? ያለግንብ ያለ አጥር፣
ወዴት ነው መንገዱ?
የት ነው የሰው ሀገር?
አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
የጠፋ ማንነት
""""""""""""""""""
ከሌሎች ጋር መስሎ ማደር፣
ያልሆንኩትን ሆኜ ስኖር፥
እኔነቴን ትቼ ሌላ ልሆን ስጥር
ባልተገባኝ ኑሮ ከኔ ስቆራረጥ፣
ቀና ከሌለበት ምራጭ ስመራርጥ
እኔን መሆን ስተው ሌላ ሲናፍቀኝ፥
እንኳንስ እነሱ እኔ ራሴ ጠፋኝ!
ቤተልሔም አባይ(ሰንፔር) ፋና ብዕር
""""""""""""""""""
ከሌሎች ጋር መስሎ ማደር፣
ያልሆንኩትን ሆኜ ስኖር፥
እኔነቴን ትቼ ሌላ ልሆን ስጥር
ባልተገባኝ ኑሮ ከኔ ስቆራረጥ፣
ቀና ከሌለበት ምራጭ ስመራርጥ
እኔን መሆን ስተው ሌላ ሲናፍቀኝ፥
እንኳንስ እነሱ እኔ ራሴ ጠፋኝ!
ቤተልሔም አባይ(ሰንፔር) ፋና ብዕር
ሰላም የምንወዳችሁ የኛ ቤተሰቦች እንደምን አደራችሁ? በያላችሁበት ሆናችሁ ለዛሬ ብታነቡት በጎ ነው ብለን የወደድነውን መፀሀፍ እናስተዋውቃችሁ
የመፀሀፉ ርዕስ = ብቻዬን እቆማለሁ
የመፀሀፉ ደራሲ =ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
የመፀሀፉ የገፅ ብዛት =216
መፀሀፉ የአጫጭር ታሪኮች ስብስብ ሲሆን በውስጡ =16 ታሪኮች ተሰድረዋል
የታተመበት ዓ.ም=ጥር 2012 አ.አ
የመፀሀፉ ዋጋ =150 ብር
ብቻዬን እቆማለው ወቅታዊ እና ተለምዶአዊ አኗኗራችንን አሰደናቂ እና አዝናኝ በሆነ መልኩ ለንባብ በቅቷል
በተለይ"ደሀ ወርቅ አይግዛ" ፈገግ ታሰኛለች
መፀሀፉቶቹንገዝቶም ሆነ በኪራይ ለማንበብ ዝዋይ/ባቱ/ የምትገኙ አንባብያን ራያ መጸሀፍት መደብርን ጎብኘት አድርጉ በፍቃድ ሆቴል አጠገብ ይገኛል
"ደግ ደጉን እናስብ በጎ በጎውን እንስራ"
መልካም ንባብ
ፋና ብዕር
የመፀሀፉ ርዕስ = ብቻዬን እቆማለሁ
የመፀሀፉ ደራሲ =ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
የመፀሀፉ የገፅ ብዛት =216
መፀሀፉ የአጫጭር ታሪኮች ስብስብ ሲሆን በውስጡ =16 ታሪኮች ተሰድረዋል
የታተመበት ዓ.ም=ጥር 2012 አ.አ
የመፀሀፉ ዋጋ =150 ብር
ብቻዬን እቆማለው ወቅታዊ እና ተለምዶአዊ አኗኗራችንን አሰደናቂ እና አዝናኝ በሆነ መልኩ ለንባብ በቅቷል
በተለይ"ደሀ ወርቅ አይግዛ" ፈገግ ታሰኛለች
መፀሀፉቶቹንገዝቶም ሆነ በኪራይ ለማንበብ ዝዋይ/ባቱ/ የምትገኙ አንባብያን ራያ መጸሀፍት መደብርን ጎብኘት አድርጉ በፍቃድ ሆቴል አጠገብ ይገኛል
"ደግ ደጉን እናስብ በጎ በጎውን እንስራ"
መልካም ንባብ
ፋና ብዕር
አይቀያየርም
""""""""""""""""
እንደ ጥቅምት ውርጭ
እንደ ግንቦት ንዳድ፣
እንደ ሀምሌ ዝናብ
እንደ ነሀሴ ብርድ፣
እውነት ወቅት አይደለም፣
ሲያሻው እየመጣ ሲያሰኘው የሚሄድ!!
አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
""""""""""""""""
እንደ ጥቅምት ውርጭ
እንደ ግንቦት ንዳድ፣
እንደ ሀምሌ ዝናብ
እንደ ነሀሴ ብርድ፣
እውነት ወቅት አይደለም፣
ሲያሻው እየመጣ ሲያሰኘው የሚሄድ!!
አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
ፍቅር ማለት ላንቺ
ፍቅር ማለት ለእኔ
ፍቅር ማለት ለኛ
""""""""""""""""""""""""""""""""""
ፍቅር ማለት ላንቺ......
"ታድላ"በሚሉ ሸንጋይና አስመሳይ
ኳኳቴያም ሴቶች ሙገሳ መደነቅ
አንቺ ማለት ፀሀይ የጨረቃ እኩያ
በሚል ማታለያ ከእውነት መደበቅ
ፍቅር ማለት ላንቺ...
ነጭ ቬሎ መልበስ አሸርጋጅን ማብዛት
ለሰው ይምሰል መኖር ያለሀሳብ ማግባት
ድግስ እያሞቁ የልቦናን መሻት
በሆታ'ሚያስቀሩ
ጥቁር ልብን ይዘው በነጭ ፈገግታ
ሰውን በሚድሩ
ነገር አዳራሾች ወረኞች መከበብ
ይህ ነው ላንቺ ፍቅር
ከመኖርሽ በላይ ኑሮሽን ሚረታ
ነገር ሰምቶ መኖር
ይህ ነው ላንቺ ፍቅር
*********************
ፍቅር ማለት ለእኔ
ከጨለማ ምድር አንቺን ፀሀይ ማየት
ውብ አለምን ይዞ ሰማይን መመኘት
አንቺን እያሰቡ ምድሩን ሁሉ መርሳት
ካንቺ ጋር ሲሆኑ ተፈጥሮን ማዛባት
ከእውነት ሆነ ብልሀት ከጥበብ መጣላት
ከልብሽ ለመኖር ከእግዜር ፍቅር መውጣት
ከረቂቁ ድርሰት ከረቂቁ ቅኔ
አንቺን ብቻ ማፍቀር
አንቺን ለወደድኩሽ መልሼ መልሼ
ደሞ አንቺኑ ማፈር
ይህ ነው ለኔ ፍቅር
*************************
ፍቅር ማለት ለእኛ
በጥልቅ ዝምታ ብዙ እንደመግባባት
በሺ ሞት ተከቦ መኖር እንደመፍራት
በሽንቁር ፈገግታ ያለም ደስታን መግዛት
በዝምታ ቅኝት ውድ ልብን መርታት
ፍቅር ማለት ለእኛ
አለሙን ረስቶ ከህይወት መርገፍ ስር
ስጋን ጥሎ መሄድ ነብስን ብቻ መስፈር
ከውድ ስሜት ጋር ዘላለም መጋመድ
ምክኒያት ሳያበጁ ዝም ብሎ መዋደድ
ፍቅር ማለት ለኛ
ሞትን ድል ለመንሳት ፍቅርሽ ስር መደበቅ
አንቺን እየወደድኩ ከእግዜር ጋር መታረቅ
ይህ ነው ፍቅር ማለት!
ቤተልሔም አባይ(ሰንፔር)ፋና ብዕር
ፍቅር ማለት ለእኔ
ፍቅር ማለት ለኛ
""""""""""""""""""""""""""""""""""
ፍቅር ማለት ላንቺ......
"ታድላ"በሚሉ ሸንጋይና አስመሳይ
ኳኳቴያም ሴቶች ሙገሳ መደነቅ
አንቺ ማለት ፀሀይ የጨረቃ እኩያ
በሚል ማታለያ ከእውነት መደበቅ
ፍቅር ማለት ላንቺ...
ነጭ ቬሎ መልበስ አሸርጋጅን ማብዛት
ለሰው ይምሰል መኖር ያለሀሳብ ማግባት
ድግስ እያሞቁ የልቦናን መሻት
በሆታ'ሚያስቀሩ
ጥቁር ልብን ይዘው በነጭ ፈገግታ
ሰውን በሚድሩ
ነገር አዳራሾች ወረኞች መከበብ
ይህ ነው ላንቺ ፍቅር
ከመኖርሽ በላይ ኑሮሽን ሚረታ
ነገር ሰምቶ መኖር
ይህ ነው ላንቺ ፍቅር
*********************
ፍቅር ማለት ለእኔ
ከጨለማ ምድር አንቺን ፀሀይ ማየት
ውብ አለምን ይዞ ሰማይን መመኘት
አንቺን እያሰቡ ምድሩን ሁሉ መርሳት
ካንቺ ጋር ሲሆኑ ተፈጥሮን ማዛባት
ከእውነት ሆነ ብልሀት ከጥበብ መጣላት
ከልብሽ ለመኖር ከእግዜር ፍቅር መውጣት
ከረቂቁ ድርሰት ከረቂቁ ቅኔ
አንቺን ብቻ ማፍቀር
አንቺን ለወደድኩሽ መልሼ መልሼ
ደሞ አንቺኑ ማፈር
ይህ ነው ለኔ ፍቅር
*************************
ፍቅር ማለት ለእኛ
በጥልቅ ዝምታ ብዙ እንደመግባባት
በሺ ሞት ተከቦ መኖር እንደመፍራት
በሽንቁር ፈገግታ ያለም ደስታን መግዛት
በዝምታ ቅኝት ውድ ልብን መርታት
ፍቅር ማለት ለእኛ
አለሙን ረስቶ ከህይወት መርገፍ ስር
ስጋን ጥሎ መሄድ ነብስን ብቻ መስፈር
ከውድ ስሜት ጋር ዘላለም መጋመድ
ምክኒያት ሳያበጁ ዝም ብሎ መዋደድ
ፍቅር ማለት ለኛ
ሞትን ድል ለመንሳት ፍቅርሽ ስር መደበቅ
አንቺን እየወደድኩ ከእግዜር ጋር መታረቅ
ይህ ነው ፍቅር ማለት!
ቤተልሔም አባይ(ሰንፔር)ፋና ብዕር
አትመነኝ
"""""""""""
ተወኝ ብልህ እንኳን
ማጣትን ፈርቼ፣
ስታቅፈኝ ብሸሽህ
ፍቅርህን ገፍቼ፥
ያለአንተ ሙሉ ነኝ
መኖር እችላለሁ፣
ብትሄድ መች ልጎዳ
እኔም እሄዳለሁ።
ብዬ ብልህ እንኳን
እንዳታምነኝ ፍቅሬ፣
ያለአንተ ብቻዬን
አልቆም ነበር ዛሬ።
ከመላመድ አልፎ
ነፍስና ስጋችን፣
ተጣብቆ ተሰፍቷል
ሁለቱ ልባችን።
አልችልም ያለአንተ
መኖር በደስታ፣
እንዳታምነኝ የአፌን
እባክህ የኔ ጌታ።
የማታወርቅ ከበደ(ፋና ብዕር)
"""""""""""
ተወኝ ብልህ እንኳን
ማጣትን ፈርቼ፣
ስታቅፈኝ ብሸሽህ
ፍቅርህን ገፍቼ፥
ያለአንተ ሙሉ ነኝ
መኖር እችላለሁ፣
ብትሄድ መች ልጎዳ
እኔም እሄዳለሁ።
ብዬ ብልህ እንኳን
እንዳታምነኝ ፍቅሬ፣
ያለአንተ ብቻዬን
አልቆም ነበር ዛሬ።
ከመላመድ አልፎ
ነፍስና ስጋችን፣
ተጣብቆ ተሰፍቷል
ሁለቱ ልባችን።
አልችልም ያለአንተ
መኖር በደስታ፣
እንዳታምነኝ የአፌን
እባክህ የኔ ጌታ።
የማታወርቅ ከበደ(ፋና ብዕር)
ብቻዬን መጣሁኝ
************
ከልቤ ዙፋን ላይ
በሰጠዋት ሞገስ፣
አምራና ተውባ
በኑሮዬ ብትነግስ፥
ብዬ በተውኩላት
ሕይወት ማንነቴን፣
ታሾፍበት ጀመር
የልጅነት ፍቅሬን።
እኔ ብከፋባት
ስታረገኝ ከንቱ፣
እንደኔ ሚያፈቅራት
የለምና ብርቱ፥
ሌላ ሰው ያጋጥምሽ ፦
ኑሮሽም ይሙላልሽ
ብዬ አየረገምኳት ፣
ብቻዬን መጣሁኝ ፡
እስከዘላለሙ እሷን
መንገድ ትቻት።
ቤተልሔም አባይ(ሰንፔር) ፋና ብዕር
************
ከልቤ ዙፋን ላይ
በሰጠዋት ሞገስ፣
አምራና ተውባ
በኑሮዬ ብትነግስ፥
ብዬ በተውኩላት
ሕይወት ማንነቴን፣
ታሾፍበት ጀመር
የልጅነት ፍቅሬን።
እኔ ብከፋባት
ስታረገኝ ከንቱ፣
እንደኔ ሚያፈቅራት
የለምና ብርቱ፥
ሌላ ሰው ያጋጥምሽ ፦
ኑሮሽም ይሙላልሽ
ብዬ አየረገምኳት ፣
ብቻዬን መጣሁኝ ፡
እስከዘላለሙ እሷን
መንገድ ትቻት።
ቤተልሔም አባይ(ሰንፔር) ፋና ብዕር
ግድ የለም
አይንህ ሲናፍቀኝ የጨዋታህ ለዛ፣
እስኪ ቶሎ ናልኝ አደብ እንድገዛ።
አደራ ብያለው አንድያ ህይወቴን፣
ታውቀዋለህና ህመም መዳኒቴን።
ፍቅርህ ክንደ ብርቱ የለው መሸሸጊያ፣
የማያልቅ ጦርነት የማይሰለች ውጊያ።
መሸነፍ ማሸነፍ በሆነባት አለም፣
ልረታልህ እኔ ልሸነፍ ግድ የለም።
የማታወርቅ ከበደ(ፋና ብዕር)
አይንህ ሲናፍቀኝ የጨዋታህ ለዛ፣
እስኪ ቶሎ ናልኝ አደብ እንድገዛ።
አደራ ብያለው አንድያ ህይወቴን፣
ታውቀዋለህና ህመም መዳኒቴን።
ፍቅርህ ክንደ ብርቱ የለው መሸሸጊያ፣
የማያልቅ ጦርነት የማይሰለች ውጊያ።
መሸነፍ ማሸነፍ በሆነባት አለም፣
ልረታልህ እኔ ልሸነፍ ግድ የለም።
የማታወርቅ ከበደ(ፋና ብዕር)
* ሀ እና በ *
-------------
መንገድ ሊመርቁ ፥
"እሳቸው" ሊመጡ ፥ መንገዶች ሲዘጉ
መራቂም ፥ ረጋሚም ፥
ሟችም ፥ ገዳዮችም ሊያገኟቸው ጓጉ!
A.P.N.K. -- የሜሮን
-------------
መንገድ ሊመርቁ ፥
"እሳቸው" ሊመጡ ፥ መንገዶች ሲዘጉ
መራቂም ፥ ረጋሚም ፥
ሟችም ፥ ገዳዮችም ሊያገኟቸው ጓጉ!
A.P.N.K. -- የሜሮን
ጌታ ሆይ
""""""""""""
መቼም ተውከኝ አልልህም፥
አንተ መተው አትችልበት
ረሳኸኝ አልልህም፥
ልጅን መርሳት አታውቅበት
አቅሙም የለኝ ፥ ልኬም አይደል
አፌ አይጎብዝ ለወቀሳ
ግን አምላኬ ብርታት ስጠኝ፥
እኔ ራሴን እንዳልረሳ!
አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
""""""""""""
መቼም ተውከኝ አልልህም፥
አንተ መተው አትችልበት
ረሳኸኝ አልልህም፥
ልጅን መርሳት አታውቅበት
አቅሙም የለኝ ፥ ልኬም አይደል
አፌ አይጎብዝ ለወቀሳ
ግን አምላኬ ብርታት ስጠኝ፥
እኔ ራሴን እንዳልረሳ!
አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
የፍቅር ጥግ
""""""""""""""""""
ሀገሬ እናቴ የሚስጥሬ ጓዳ
የችግሬ ሙዳይ፣
መች አለኝ ያላንቺ የሚያንሰፈስፈኝ
ሚያስጨንቀኝ ጉዳይ።
ባይሞላልኝ ባልደርስ ከጀግኖቹ ስፍራ፣
ያቅሜን ልቸርሽ ባለኝ ልደግፍሽ
አለብኝ አደራ።
ካፌ የማይጠፋው የመውደዴ ቃል ልክ፣
ምን ያህል ብትይኝ ምሳሌ ሚሆነኝ አጣሁልሽ ምትክ።
ሰንደቅሽ ከፍ እንዲል ባለም አደባባይ፣
ጎልቶ አንፀባርቆ በኩራት እንዲታይ።
የብዙሀን አንገት ከመሬት ተደፍቷል፣
ስንቱ ባለተስፋ ከመንገድ ዳር ቀርቷል፣
ዕልፍ አዕላፍ ጀግና ለስምሽ ሲል ሞቷል።
ካንዱ ጥግ ቁጭ ብላ እየደጋገመች
ሀገሬን የምትል፣
አይኗን ሀዘን ወሮት አንዱን እያነሳች
አንዱን የምትጥል።
የእንባ ቋቷ ደርቆ እ ብትለው ላይል ጠብ፣
ከአይኖቿ ወርዶ ጉንጮቿን ላያረጥብ፣
የሀዘኗን ቁስል በፈውስ ፀበል ላያጥብ።
ብቻ መኖር ባይሉት እንኳ አለሁኝ ትላለች፣
በድን አካል ይዛ በመሞት ኖራለች።
ከሞቀ ጎጆዋ ብርሀን በፅልመት
ሳይተካ በፊት፣
እንዳገሬው ልማድ ባህልና ትውፊት።
እንኳን ፀሀይ ሳጠልቅ ደጃፉ ሊዘጋ፣
ክፍቱን ነው የሚያድር ቅርቃርም አያውቀው መሽቶ እስኪነጋ።
አባወራዋ ከርሻው ልጆች ከቀዬ ጨዋታ
እንደተመለሱ፣
የቡናው ሽርጉድ የጣን ወይራ ጢሱ፣
ከገበታ ቀርበው ባንድ ሲቋደሱ፣
ነበሩ በጊዜው የደከመ ጉልበት መንፈስ
የሚያድሱ።
ግና ሀገር ተደፈረች ብለው ያሏት ለታ፣
ወደኋላ ሳትል ደጋግማ ሳታስብ
ቁጭ ብላ ላንዳፍታ፣
በኩር ልጇን ላከች ከጉያዋ አውጥታ።
በሔደበት ቢቀር የውሀ ሽታ ሆኖ
መምጫው ቢናፍቃት፣
ስለደንነቱ እንዲ ነው የሚላት
ብታጣ ቢጨንቃት።
ሀገር ትበልጣለች ድል አድርጎ ይመጣል
በሚል ግዙፍ ተስፋ፣
ስጠብቀው ነበር ጠረኑ የቀረበት መሀረቡን ታቅፋ።
ነገር ተባብሶ በሩቅ የሰማችው
ከደጃፏ ደርሶ፣
የጠላቷ በትር የቤቷን ወጋግራ
ቢጥለው አፍርሶ ።
የደም ጎርፍ ብታይ ስትወጣ ከደጇ፣
በላቧ ገንብታ ራሷን ሰውታ ያቆመችው ልጇ፣
ከመሬት ተንጋሎ ብታይ አላመነች
እስክትነካው በጇ።
እንባዋ ደረቀ ሀዘኗ ቅጥ አጣ፣
ልጇን ያስተማረች ነበር ክብሯን ሽጣ፣
ለማን አቤት ትበል ከየት ሸንጎ ቱጣ።
በድን አካሉላይ በደረቷ ወድቃ፣
ተነስ ብትለውም ከሞቱ እንዲነቃ፣
የሱ ነገር እቴ ቆይቷል ካበቃ።
አቅፋ ልታነሳው ብትሞክር ብትለፋ
አቅሙ ተሳናት፣
እንኳንስ ለመጦር እሬሳ ለመቅበር
እድል ያጣች እናት።
ሆዷ ስፍስፍ አለ አንጀቷ ታሰረ፣
ምን የታደለ ነው አፈር ያለበሰ
አልቅሶ የቀበረ።
ይህ አልበቃ ብሎ
በውድቅት ለሊት ባልታሰበ ሰአት፣
ምንም በሌለበት ሳይታወቅ ድንገት ፣
በላያቸው ቢወርድ የጭካኔ መአት።
አይኖቿ እያዩ ባሏ ተጠፍሮ
ተሳስሮ በገመድ፣
ቢላ ሲሳልለት እንደበግ ሊታረድ።
ሰው ይሁኑ አውሬ መለየት ተሰኗት
አይኗ እንደቦዘዘ፣
አካሏ በጭንቅ ምጥ ብርክ እንደተያዘ።
ከሴትነቷ ላይ አይናቸው ከጅሎ
መሬት ሲያሳርፏት፣
በባለቤቷ ፊት ካንዴም ሁለት ሶስቴ
ልባሷን ሲገፋት።
አቅም ባጣ ወኔ ስለእግዜር ብላ
ብትገባም ልመና፣
ማስቆም አልቻለችም አንዴ ሆኗልና።
የሞተች መስሏቸው ስትወድቅ ከመሬት፣
ትንፋሿ ሲጠፋ ቢሄዱ ጥለዋት፣
ከሰመመን ነቅታ ቀና ብትል ድንገት።
የባሏ እሬሳ ከበር ተጋድሞ በእርቃነ ስጋ፣
ጉልበት አጣች ወኔ ልትመለከተው
ጎኑ ልትጠጋ።
መፈጠሯን ጠላች ሞቷን ናፈቀችው፣
አብራው ልትቀበር ቀዝቃዛ አካሉን
አጥብቃ አቀፈችው።
ጎህ እንደቀደደ ጮሀ ብትጣራ ቀባሪ ፍለጋ፣
ሰው አላገኘችም ተከበበች እንጂ
በአሞራ መንጋ።
ይህም ሁሉ አልፎ ዛሬም ስትጠየቅ፣
ዋጋ ነው ትላለች ሀገር ለመጠበቅ።
ሀዘንን አምቆ ችሎ እየታለፈ ሁሉን
በዝምታ፣
መሠዋትነት ነው ለሀገር ውለታ።
ነገን እያሰቡ ለቀጣዩ ትውልድ
ለተተኪው ዜጋ፣
መሠረቷ ጠብቆ እስከሙሉነቷ
ውሏ ሳይናጋ፣
በክብር ለማኖር ያስከፍላል ዋጋ።
ክብሯን ላጎደፈ ልጆቿን ለበላ የዘመን
እዳሪ፣
ታሪክ ላቆሸሸ ክፉ ስም ላሰጣት
የሀሰት መስካሪ።
ዝምታን ሞኝነት ዝቅማለት ውርደት፣
መቻቻል ቂልነት ይሁን ማለት ሽንፈት።
ለመሠለው ጠላት የናቱን ጡት ነካሽ፣
ባከበሩት መጠን ለሚሆን ርካሽ።
አልገባውም እንጂ
ለመቆሟ ካስማ መደገፊያ ማገር፣
የጀግኖቿ ደምነው መሰዋት ለሀገር።
እየሞቱ ማኖር እየጠፉ ማልማት፣
ይህነው የፍቅር ጥግ ሀገር ወዳድ ማለት።
የማታወርቅ ከበደ(ፋና ብዕር)
""""""""""""""""""
ሀገሬ እናቴ የሚስጥሬ ጓዳ
የችግሬ ሙዳይ፣
መች አለኝ ያላንቺ የሚያንሰፈስፈኝ
ሚያስጨንቀኝ ጉዳይ።
ባይሞላልኝ ባልደርስ ከጀግኖቹ ስፍራ፣
ያቅሜን ልቸርሽ ባለኝ ልደግፍሽ
አለብኝ አደራ።
ካፌ የማይጠፋው የመውደዴ ቃል ልክ፣
ምን ያህል ብትይኝ ምሳሌ ሚሆነኝ አጣሁልሽ ምትክ።
ሰንደቅሽ ከፍ እንዲል ባለም አደባባይ፣
ጎልቶ አንፀባርቆ በኩራት እንዲታይ።
የብዙሀን አንገት ከመሬት ተደፍቷል፣
ስንቱ ባለተስፋ ከመንገድ ዳር ቀርቷል፣
ዕልፍ አዕላፍ ጀግና ለስምሽ ሲል ሞቷል።
ካንዱ ጥግ ቁጭ ብላ እየደጋገመች
ሀገሬን የምትል፣
አይኗን ሀዘን ወሮት አንዱን እያነሳች
አንዱን የምትጥል።
የእንባ ቋቷ ደርቆ እ ብትለው ላይል ጠብ፣
ከአይኖቿ ወርዶ ጉንጮቿን ላያረጥብ፣
የሀዘኗን ቁስል በፈውስ ፀበል ላያጥብ።
ብቻ መኖር ባይሉት እንኳ አለሁኝ ትላለች፣
በድን አካል ይዛ በመሞት ኖራለች።
ከሞቀ ጎጆዋ ብርሀን በፅልመት
ሳይተካ በፊት፣
እንዳገሬው ልማድ ባህልና ትውፊት።
እንኳን ፀሀይ ሳጠልቅ ደጃፉ ሊዘጋ፣
ክፍቱን ነው የሚያድር ቅርቃርም አያውቀው መሽቶ እስኪነጋ።
አባወራዋ ከርሻው ልጆች ከቀዬ ጨዋታ
እንደተመለሱ፣
የቡናው ሽርጉድ የጣን ወይራ ጢሱ፣
ከገበታ ቀርበው ባንድ ሲቋደሱ፣
ነበሩ በጊዜው የደከመ ጉልበት መንፈስ
የሚያድሱ።
ግና ሀገር ተደፈረች ብለው ያሏት ለታ፣
ወደኋላ ሳትል ደጋግማ ሳታስብ
ቁጭ ብላ ላንዳፍታ፣
በኩር ልጇን ላከች ከጉያዋ አውጥታ።
በሔደበት ቢቀር የውሀ ሽታ ሆኖ
መምጫው ቢናፍቃት፣
ስለደንነቱ እንዲ ነው የሚላት
ብታጣ ቢጨንቃት።
ሀገር ትበልጣለች ድል አድርጎ ይመጣል
በሚል ግዙፍ ተስፋ፣
ስጠብቀው ነበር ጠረኑ የቀረበት መሀረቡን ታቅፋ።
ነገር ተባብሶ በሩቅ የሰማችው
ከደጃፏ ደርሶ፣
የጠላቷ በትር የቤቷን ወጋግራ
ቢጥለው አፍርሶ ።
የደም ጎርፍ ብታይ ስትወጣ ከደጇ፣
በላቧ ገንብታ ራሷን ሰውታ ያቆመችው ልጇ፣
ከመሬት ተንጋሎ ብታይ አላመነች
እስክትነካው በጇ።
እንባዋ ደረቀ ሀዘኗ ቅጥ አጣ፣
ልጇን ያስተማረች ነበር ክብሯን ሽጣ፣
ለማን አቤት ትበል ከየት ሸንጎ ቱጣ።
በድን አካሉላይ በደረቷ ወድቃ፣
ተነስ ብትለውም ከሞቱ እንዲነቃ፣
የሱ ነገር እቴ ቆይቷል ካበቃ።
አቅፋ ልታነሳው ብትሞክር ብትለፋ
አቅሙ ተሳናት፣
እንኳንስ ለመጦር እሬሳ ለመቅበር
እድል ያጣች እናት።
ሆዷ ስፍስፍ አለ አንጀቷ ታሰረ፣
ምን የታደለ ነው አፈር ያለበሰ
አልቅሶ የቀበረ።
ይህ አልበቃ ብሎ
በውድቅት ለሊት ባልታሰበ ሰአት፣
ምንም በሌለበት ሳይታወቅ ድንገት ፣
በላያቸው ቢወርድ የጭካኔ መአት።
አይኖቿ እያዩ ባሏ ተጠፍሮ
ተሳስሮ በገመድ፣
ቢላ ሲሳልለት እንደበግ ሊታረድ።
ሰው ይሁኑ አውሬ መለየት ተሰኗት
አይኗ እንደቦዘዘ፣
አካሏ በጭንቅ ምጥ ብርክ እንደተያዘ።
ከሴትነቷ ላይ አይናቸው ከጅሎ
መሬት ሲያሳርፏት፣
በባለቤቷ ፊት ካንዴም ሁለት ሶስቴ
ልባሷን ሲገፋት።
አቅም ባጣ ወኔ ስለእግዜር ብላ
ብትገባም ልመና፣
ማስቆም አልቻለችም አንዴ ሆኗልና።
የሞተች መስሏቸው ስትወድቅ ከመሬት፣
ትንፋሿ ሲጠፋ ቢሄዱ ጥለዋት፣
ከሰመመን ነቅታ ቀና ብትል ድንገት።
የባሏ እሬሳ ከበር ተጋድሞ በእርቃነ ስጋ፣
ጉልበት አጣች ወኔ ልትመለከተው
ጎኑ ልትጠጋ።
መፈጠሯን ጠላች ሞቷን ናፈቀችው፣
አብራው ልትቀበር ቀዝቃዛ አካሉን
አጥብቃ አቀፈችው።
ጎህ እንደቀደደ ጮሀ ብትጣራ ቀባሪ ፍለጋ፣
ሰው አላገኘችም ተከበበች እንጂ
በአሞራ መንጋ።
ይህም ሁሉ አልፎ ዛሬም ስትጠየቅ፣
ዋጋ ነው ትላለች ሀገር ለመጠበቅ።
ሀዘንን አምቆ ችሎ እየታለፈ ሁሉን
በዝምታ፣
መሠዋትነት ነው ለሀገር ውለታ።
ነገን እያሰቡ ለቀጣዩ ትውልድ
ለተተኪው ዜጋ፣
መሠረቷ ጠብቆ እስከሙሉነቷ
ውሏ ሳይናጋ፣
በክብር ለማኖር ያስከፍላል ዋጋ።
ክብሯን ላጎደፈ ልጆቿን ለበላ የዘመን
እዳሪ፣
ታሪክ ላቆሸሸ ክፉ ስም ላሰጣት
የሀሰት መስካሪ።
ዝምታን ሞኝነት ዝቅማለት ውርደት፣
መቻቻል ቂልነት ይሁን ማለት ሽንፈት።
ለመሠለው ጠላት የናቱን ጡት ነካሽ፣
ባከበሩት መጠን ለሚሆን ርካሽ።
አልገባውም እንጂ
ለመቆሟ ካስማ መደገፊያ ማገር፣
የጀግኖቿ ደምነው መሰዋት ለሀገር።
እየሞቱ ማኖር እየጠፉ ማልማት፣
ይህነው የፍቅር ጥግ ሀገር ወዳድ ማለት።
የማታወርቅ ከበደ(ፋና ብዕር)
ፍዳ
"""""
ሌቱን አነጋሁት ፥ ብዬ ፈራ ተባ
ቀኑን አባበልኹት ፥ አዝዬ ባንቀልባ፤
በዘበት ነጠፈች ፥ የተስፋ ጥገቴ
ኑሮ ቢደቁሳት ፥ አዘመመች ቤቴ፤
ነብሴም ትርድ ጀመር፥
ከመፍራት ተዋቅራ
ተጭኖ ቢያፍናት፥
የጊዜው መከራ!
አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
"""""
ሌቱን አነጋሁት ፥ ብዬ ፈራ ተባ
ቀኑን አባበልኹት ፥ አዝዬ ባንቀልባ፤
በዘበት ነጠፈች ፥ የተስፋ ጥገቴ
ኑሮ ቢደቁሳት ፥ አዘመመች ቤቴ፤
ነብሴም ትርድ ጀመር፥
ከመፍራት ተዋቅራ
ተጭኖ ቢያፍናት፥
የጊዜው መከራ!
አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
ይሁና
ልቤ ሞኙ ቃል ጠባቂ
ያንተ ምስል አሳባቂ
እኔም አማኝ የታወርኩኝ
እያየውህ እያወኩኝ
በሴት ውበት ስትደመም
በክደትህ የምታመም
ሞኝ አርገኸኝ አላዋቂ
ድንገት ሳይህ ብትል ሳቂ
እስቃለሁ ደጋግሜ
ባንተው ስራ ተገርሜ
የሰው ፍፁም በርግጥ የለም
ከቀን አንዴ ሌላ ማየት ብርቅ አይደለም
ይሁን ብዬ ቻለ ሆዴ
ስንትስ ይቻል አይደል እንዴ?
የማታወርቅ ከበደ(ፋና ብዕር)
ልቤ ሞኙ ቃል ጠባቂ
ያንተ ምስል አሳባቂ
እኔም አማኝ የታወርኩኝ
እያየውህ እያወኩኝ
በሴት ውበት ስትደመም
በክደትህ የምታመም
ሞኝ አርገኸኝ አላዋቂ
ድንገት ሳይህ ብትል ሳቂ
እስቃለሁ ደጋግሜ
ባንተው ስራ ተገርሜ
የሰው ፍፁም በርግጥ የለም
ከቀን አንዴ ሌላ ማየት ብርቅ አይደለም
ይሁን ብዬ ቻለ ሆዴ
ስንትስ ይቻል አይደል እንዴ?
የማታወርቅ ከበደ(ፋና ብዕር)
ደህና!
""""""""""""""""""""
አንቺዬ.....
ጉዳቴ ለገባው ለሚያውቀኝ በሙሉ
"ተሽሎታል እንዴ?" እያልሽ ነው አሉ።
ሰው አታስቸግሪ እኔ ነግርሻለሁ
ተሽሎኛል ስልሽ እቆስልብሻለሁ።
እውነቱን ልንገርሽ?......
ከሄድሽ ጀምሮ ከሳቅ ተኳርፌ
አላዝናለሁኝ ቂም በቀል ታቅፌ።
አንቺ የምታውቂው ጠይም ገፄ ጠቁሯል
የፊት ወዜ ጠፎ አይመስሉትን መስሏል።
ልልሽ ከጅላለሁ........
እንደውም እንደውም በጣም ተሽሎኛል
የወጣው ተክቶ ጎዶሎዬም ሞልቷል።
ወና ቤቴ ሞቋል
እኔነቴ ደምቋል።
ልልሽም እሻለሁ.....
ደህና ነኝ አትምጪ ሌላም አግኝቻለሁ
የለም በቶሎ ነይ እሞትብሻለሁ።
ልልሽም እሻለሁ.....
አየሽ....
እንዴት ነው ከሆነ የጥያቄሽ ውሉ
"ደህና"ሚል ብቻ ነው የምላሼ ቃሉ።
ለምን ብትይ?...
ደህና ነኝ እንዳልል ደህናም አይደለሁም
ይኸው እንዳየሽው የማወራው ሁሉ አይታወቀኝም ።
ቤተልሔም አባይ(ሰንፔር)ፋና ብዕር
""""""""""""""""""""
አንቺዬ.....
ጉዳቴ ለገባው ለሚያውቀኝ በሙሉ
"ተሽሎታል እንዴ?" እያልሽ ነው አሉ።
ሰው አታስቸግሪ እኔ ነግርሻለሁ
ተሽሎኛል ስልሽ እቆስልብሻለሁ።
እውነቱን ልንገርሽ?......
ከሄድሽ ጀምሮ ከሳቅ ተኳርፌ
አላዝናለሁኝ ቂም በቀል ታቅፌ።
አንቺ የምታውቂው ጠይም ገፄ ጠቁሯል
የፊት ወዜ ጠፎ አይመስሉትን መስሏል።
ልልሽ ከጅላለሁ........
እንደውም እንደውም በጣም ተሽሎኛል
የወጣው ተክቶ ጎዶሎዬም ሞልቷል።
ወና ቤቴ ሞቋል
እኔነቴ ደምቋል።
ልልሽም እሻለሁ.....
ደህና ነኝ አትምጪ ሌላም አግኝቻለሁ
የለም በቶሎ ነይ እሞትብሻለሁ።
ልልሽም እሻለሁ.....
አየሽ....
እንዴት ነው ከሆነ የጥያቄሽ ውሉ
"ደህና"ሚል ብቻ ነው የምላሼ ቃሉ።
ለምን ብትይ?...
ደህና ነኝ እንዳልል ደህናም አይደለሁም
ይኸው እንዳየሽው የማወራው ሁሉ አይታወቀኝም ።
ቤተልሔም አባይ(ሰንፔር)ፋና ብዕር
አንዳንዴ...
"""""''''''''''''''''''
ነብስህን ሰው ያሰኛታል
አልባሽ አጉራሽ የልብ አውቃ፥
እንደከፋት ወጥታ እንዳትቀር
እንዳትገኝ የትም ወድቃ፤
ግን...
የሰው ፊቱ የ'ግር እሳት
ወላፈኑ የሚጋረፍ፥
አንደበቱም ተናዳፊ
የልቡ እብሪት የሚሰይፍ፤
ነውና...
ብትነጠል፤
ብትገለል፤
ብትገፋ፤
ብትተፋ፤
ምን ቢርብህ ብትታረዝ
ቁልቁል ብትወድቅ ከከፍታ፥
ከሰው ጠፍታ ፥ ከሰው ሸሽታ
ነብስህ ብትከርም ይበጃታል
የእግዜርን ደጅ ተጠግታ።
አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
"""""''''''''''''''''''
ነብስህን ሰው ያሰኛታል
አልባሽ አጉራሽ የልብ አውቃ፥
እንደከፋት ወጥታ እንዳትቀር
እንዳትገኝ የትም ወድቃ፤
ግን...
የሰው ፊቱ የ'ግር እሳት
ወላፈኑ የሚጋረፍ፥
አንደበቱም ተናዳፊ
የልቡ እብሪት የሚሰይፍ፤
ነውና...
ብትነጠል፤
ብትገለል፤
ብትገፋ፤
ብትተፋ፤
ምን ቢርብህ ብትታረዝ
ቁልቁል ብትወድቅ ከከፍታ፥
ከሰው ጠፍታ ፥ ከሰው ሸሽታ
ነብስህ ብትከርም ይበጃታል
የእግዜርን ደጅ ተጠግታ።
አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
አይፈታም!
"""""""""""""
የሰው ደስታና ሳቅ ፥
መቅጠፍ እንደ በለስ
ከወዴት አንስቶ
ወደምንነው ሚያደርስ?
በፊተኞች መንገድ እግር እየኳተነ፥
ትሁት ማንነት ላይ አፍ እየጀገነ፤
ካንጀት ጠብ የማይል ፥
የይምሰል ይቅርታ
እንኳን ቂምን ቀርቶ
ግንባር እያስፈታ!
አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
"""""""""""""
የሰው ደስታና ሳቅ ፥
መቅጠፍ እንደ በለስ
ከወዴት አንስቶ
ወደምንነው ሚያደርስ?
በፊተኞች መንገድ እግር እየኳተነ፥
ትሁት ማንነት ላይ አፍ እየጀገነ፤
ካንጀት ጠብ የማይል ፥
የይምሰል ይቅርታ
እንኳን ቂምን ቀርቶ
ግንባር እያስፈታ!
አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
አለሜዋ.......
ምን ብታስነኪኝ ነው በምንሽ ብረታ፣
የተውኩትን አለም በፀሎት በግዚኦታ፣
አምና የቋጠርኩትን ዘንድሮ ምፈታ።
ኮብልዬ ካገሩ ካለሽበት ስፍራ፣
መሸሸጊያ ባጣ ህመሜን ሚጋራ፣
አሁንስ ከበደኝ እንጃ ውስጤ ፈራ።
ተውኳት ብዬ ነበር ፍቅሬም አከተመ፣
ማይታክተው ልቤ አቅም አጣ ደከመ፣
ላያገኛት ነገር ስንት አመት ታመመ።
እንዳመረርኩ አውቃ ልረሳት ስወስን፣
ትዝታዋን ስፍቅ ከሆዴ ስጨክን፣
በህልሜ እየመጣች ትለኛለች ለምን።
የማታወርቅ ከበደ(ፋና ብዕር)
ምን ብታስነኪኝ ነው በምንሽ ብረታ፣
የተውኩትን አለም በፀሎት በግዚኦታ፣
አምና የቋጠርኩትን ዘንድሮ ምፈታ።
ኮብልዬ ካገሩ ካለሽበት ስፍራ፣
መሸሸጊያ ባጣ ህመሜን ሚጋራ፣
አሁንስ ከበደኝ እንጃ ውስጤ ፈራ።
ተውኳት ብዬ ነበር ፍቅሬም አከተመ፣
ማይታክተው ልቤ አቅም አጣ ደከመ፣
ላያገኛት ነገር ስንት አመት ታመመ።
እንዳመረርኩ አውቃ ልረሳት ስወስን፣
ትዝታዋን ስፍቅ ከሆዴ ስጨክን፣
በህልሜ እየመጣች ትለኛለች ለምን።
የማታወርቅ ከበደ(ፋና ብዕር)
አልወድሽም
ዘመን ዘመነና ፍቅር ተተመነ
ከገበያ ወጣ፣
የምስኪን ደሀ ልብ የሚታመንበት
ጊዜ ና ቦታ አጣ።
አዎ አልወድሽም ምን አቅም አለኝና፣
ዛሬዬን ምታገል ለፍቶ አዳሪ ገና።
ፍቅሬን ከለካሽው በቁስ አርቲቡርቲ፣
መልሴን እያወቅሽው አጠይቂኝ እስቲ።
ከገንዘቤ በፊት እኔን አስቀድሜ
ሰጥቼሽ ነበረ፣
አልወድሽም በቃ ሳይገባሽ ከቀረ።
የማታወርቅ ከበደ(ፋና ብዕር)
ዘመን ዘመነና ፍቅር ተተመነ
ከገበያ ወጣ፣
የምስኪን ደሀ ልብ የሚታመንበት
ጊዜ ና ቦታ አጣ።
አዎ አልወድሽም ምን አቅም አለኝና፣
ዛሬዬን ምታገል ለፍቶ አዳሪ ገና።
ፍቅሬን ከለካሽው በቁስ አርቲቡርቲ፣
መልሴን እያወቅሽው አጠይቂኝ እስቲ።
ከገንዘቤ በፊት እኔን አስቀድሜ
ሰጥቼሽ ነበረ፣
አልወድሽም በቃ ሳይገባሽ ከቀረ።
የማታወርቅ ከበደ(ፋና ብዕር)
ማነው?
""""""""""
ነገ ሚሉት ህመም ፥ ነገ ሚሉት ውጋት
ቁስል ሆኖ አመርቅዞ ፥ በዛሬና ትላንት
ሲያቃጥለኝ ያድራል
እንደ ውሃ ጥማት
መዝምዞኝ ያነጋል
እንደ እግር ቁርጥማት!
ተሰቅሎ መሰለኝ ርቆ ከሰማይ
ለመንፈሴ ቀርቦ ፥ ላይኖቼ ማይታይ፤
ብጓዝ የማልደርሰው
በእጄ ማልዳድሰው፤
ኧረ ለመሆኑ
ነገ ግን መቼ ነው?
ኧረ ቆይ እንደውም
ነገ ራሱ ማነው?
ማነው?
አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
""""""""""
ነገ ሚሉት ህመም ፥ ነገ ሚሉት ውጋት
ቁስል ሆኖ አመርቅዞ ፥ በዛሬና ትላንት
ሲያቃጥለኝ ያድራል
እንደ ውሃ ጥማት
መዝምዞኝ ያነጋል
እንደ እግር ቁርጥማት!
ተሰቅሎ መሰለኝ ርቆ ከሰማይ
ለመንፈሴ ቀርቦ ፥ ላይኖቼ ማይታይ፤
ብጓዝ የማልደርሰው
በእጄ ማልዳድሰው፤
ኧረ ለመሆኑ
ነገ ግን መቼ ነው?
ኧረ ቆይ እንደውም
ነገ ራሱ ማነው?
ማነው?
አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
ተነሽ ምንአባቱ
"""""""""""""""""""
እናት አለም ሆዴ
የምስጢሬ ጓዳ፣
ዘውትር ህመምተኛ
በልጆችሽ ዕዳ፥
በቤት፣በማጀትሽ
ቀን ከሌት እንግዳ።
በምን ዕዳሽ አንቺ
ከቶ ምን በወጣሽ፣
በሌሎች እስራት
መርዶ ስሚና አልቃሽ።
ተይ እንጁ እማማ
ይህ አይደለም እኮ፣
እግዜሩ ሲፈጥርሽ
የሰጠሽ ተልዕኮ።
መቀነትሽ ይጥበቅ
አንጀትሽ አይባባ፣
ክብርሽን ረግጦ
ገፍትሮሽ ለገባ።
ሀሞትሽ ይኮስትር
ልክ እንደ በፊቱ፣
ክብርሽን አትጣይ
እንድትባይ አንቱ፥
የውዶች ውድ እንጁ
አይደለሽም ከንቱ፣
ጠላትሽ ይደንግጥ
ተነሽ ምን አባቱ።
የማታወርቅ ከበደ(ፋና ብዕር)
"""""""""""""""""""
እናት አለም ሆዴ
የምስጢሬ ጓዳ፣
ዘውትር ህመምተኛ
በልጆችሽ ዕዳ፥
በቤት፣በማጀትሽ
ቀን ከሌት እንግዳ።
በምን ዕዳሽ አንቺ
ከቶ ምን በወጣሽ፣
በሌሎች እስራት
መርዶ ስሚና አልቃሽ።
ተይ እንጁ እማማ
ይህ አይደለም እኮ፣
እግዜሩ ሲፈጥርሽ
የሰጠሽ ተልዕኮ።
መቀነትሽ ይጥበቅ
አንጀትሽ አይባባ፣
ክብርሽን ረግጦ
ገፍትሮሽ ለገባ።
ሀሞትሽ ይኮስትር
ልክ እንደ በፊቱ፣
ክብርሽን አትጣይ
እንድትባይ አንቱ፥
የውዶች ውድ እንጁ
አይደለሽም ከንቱ፣
ጠላትሽ ይደንግጥ
ተነሽ ምን አባቱ።
የማታወርቅ ከበደ(ፋና ብዕር)