Telegram Web
ሐዋሳ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሐዋሳ ከተማ እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቀዋል፡፡ ቀን 9:00 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ለሐዋሳ ከተማ ናትናኤል ዘለቀ እንዲሁም ለወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እስራኤል እሸቱ ግቦቹን አስቆጥረዋል። የሊጉ መርሐ-ግብር…

https://www.fanabc.com/archives/279766
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከዋንኮ ኢታሊ ኩባንያ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከጣሊያኑ ዋንኮ ኢታሊ ኩባንያ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ስምምነቱ ኮርፖሬሽኑን ሕንጻዎችን በፍጥነትና በጥራት ለመገንባት የሚያስችል የግንባታ ቴክኖሎጂ ባለቤት ያደርገዋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡ በተጨማሪም የመኖሪያ ቤት አሰራር ስልትን የሚያዘምን ግዙፍ የተገጣጣሚ ቤቶች ፋብሪካ ተከላን ለማከናወን የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል፡፡ የግንባታ ቴክኖሎጂው የፌዴራል ቤቶች…

https://www.fanabc.com/archives/279770
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ ከሩሲያ አቻቸው ጋር በዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ እና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ጉዳዮች የጋራ ጥቅም አስመልክተው በበይነ-መረብ ተወያይተዋል፡፡ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በላከው መግለጫ÷ ፑቲንና ዢንፒንግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አንስቷል፡፡ ሁለቱ ሀገራት በፈረንጆቹ 2024 75ኛውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ማክበራቸውን ያመላከተው መግለጫ÷ ፕሬዚዳንት ሺ…

https://www.fanabc.com/archives/279774
በሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የጎላ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ለውጭ ኢንቨስትመንት ባንኮች እና ኢንቨስተሮች ክፍት መደረጉ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ድርሻው የጎላ መሆኑን የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥላሁን እስማኤል (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ሙዓለ ንዋይ (ሃብት) የሚፈስባቸውን ሰነዶች ወይም ኢንቨስትመንቶችን እንደ ባለቤትነት የሚረጋገጥበት የሰነዶች ገበያ ሲሆን፤ በአብዛኛው አክሲዮን፣ የመንግስት…

https://www.fanabc.com/archives/279777
የብሄራዊ ታክስ ሪፎርም ግብረ ሀይል የግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ገመገመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሄራዊ ታክስ ሪፎርም ግብረ ሀይል የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል፡፡ በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያው 6ወራት የገቢ አሰባሰብ በእቅዱ መሰረት በተሳካ ሁኔታ የተፈፀመ መሆኑን እና በቀሪ ስድስት ወራት በእቅድ የተያዘውን የገቢ እቅድ ለማሳካት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ግብረሀይሉ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ በተጨማሪም ለገቢ አሰባሰቡ…

https://www.fanabc.com/archives/279780
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
-የ480 ሚሊየን ብር ፕሮጀክት
-የኢትዮጵያ አየር ኃይል ድጋፍ
በአማራ ክልል ከ12 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የመስኖ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ከ12 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመስኖ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ መሆኑን የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው ኃላፊ ዳኝነት ፈንታ (ዶ/ር ኢ/ር) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደተናገሩት ÷በክልሉ 12 ቢሊየን ብር ወጪ የሚደረግባቸው 158 ፕሮጀክቶች እየተሰሩ ነው። በዚህ አመት 95 ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ…

https://www.fanabc.com/archives/279787
በአፋር ክልል በ783 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል ሎጊያና ሚሌ ከተሞች በ783 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡና ከ160 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሁለት የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል። ፕሮጀክቶቹ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ፤ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ርኢ/ር) እና የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢያሱ ኤልያስ(ፕ/ር)ን ጨምሮ…

https://www.fanabc.com/archives/279786
አየር ኃይሉን ከአፍሪካ ቀዳሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው – ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አየር ኃይሉን ከአፍሪካ አየር ኃይሎች ቀዳሚ ለማድረግ በከፍተኛ ንቅናቄ እየተሰራ መሆኑን የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ፡፡ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በመከላከያ አዛዥነት እና ስታፍ ኮሌጅ ከ15ኛ ዙር መደበኛ ተማሪ ከፍተኛ መኮንኖች ጋር ተወያይተዋል፡፡ ዋና አዛዡ በዚህ ወቅት÷ አየር ኃይል የሀገር…

https://www.fanabc.com/archives/279794
የኢትዮጵያ መንግስት በቱርክ በእሳት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት በቱርክ ቦሉ ግዛት በተከሰተ የእሳት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው የሀዘን መግለጫ በአደጋው ህይወታቸውን ስላጡት ዜጎች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ፤ ጉዳት የደረሰባቸውም በቶሎ እንዲያገግሙ መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ወቅትም ኢትዮጵያ ከቱርክ መንግሥት እና ህዝብ ጎን እንደምትቆም…

https://www.fanabc.com/archives/279798
Live stream finished (1 hour)
በቤት ልማት ፕሮግራም 1 ሚሊየን 500 ሺህ ቤቶች ተገንብተዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ሦስት ዓመታት በቤት ልማት ፕሮግራም 1 ሚሊየን 500 ሺህ ቤቶች መገንባታቸውን የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ገለጹ። ሚኒስትሯ ከ1996 እስከ 2012 ዓ.ም 380 ሺህ ቤቶች ብቻ መገንባታቸውን አስታውሰው፤ ከለውጡ በኋላ በቤት ልማት ፕሮግራም ስኬታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።…

https://www.fanabc.com/archives/279801
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጉዞ ወደ ልህቀት
ረቡዕ ምሽት ይጠብቁን
የዕለቱ የምንዛሪ ዋጋ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
አንድ ሩጫ ሁለት ክብረ በዓላት – ዘላቂ ክብር የ5ኪሎ ሜትር ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አንድ ሩጫ ሁለት ክብረ በዓላት – ዘላቂ ክብር በሚል የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ በጎንደር ከተማ ተካሂዷል። ሩጫው የተካሄደው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 70ኛ ዓመትና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ነው፡፡ እስከ 2 ሺህ ሰዎችን ባሳተፈው ሩጫ ላይ 40 ያህል የጎንደር ከተማና…

https://www.fanabc.com/archives/279805
ሕብረቱ የአህጉሪቱን ተሰሚነት ለማሳደግ የፋይናንስ አቅሙን ማጠናከር አለበት ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ሕብረት የአህጉሪቱን ተሰሚነት ለማሳደግ የፋይናንስ አቅሙን ማጠናከር ይጠበቅበታል ሲሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ፡፡ የአባል ሀገራቱ ብቁ የፋይናንስ ምንጭ አለመሆን ለሕብረቱ ሉዓላዊነት መጣስ ምክንያት እየሆነ መምጣቱን ምሁራኑ አመላክተዋል፡፡ ይህም ሕብረቱ በተለያዩ ጊዜያት አጀንዳዎችን ቀርፆና አደራጅቶ ይወያይባቸው እንጂ መሬት እንዳይወርዱ ማድረጉን ነው የሕግ ባለሙያና ተማራማሪ የሆኑት ማሩ…

https://www.fanabc.com/archives/279809
2025/01/22 06:31:08
Back to Top
HTML Embed Code: