Telegram Web
Live stream started
Live stream finished (11 seconds)
Live stream started


    
                       ❤️ እናቴ ❤️      

ፀጉርሽን አይቼ የኔን ፀጉር ሳየው
እንደ ወንድ ፀጉር ገባ ገባ ያለው
እሳት እንደነካው የተኮማተረው
----ለካ ለፍቅር ነው
የፊትሽ ላይ ቆዳ የተሸበሸበው
እንደ ወየበ ልብስ እንዲህ የገረጣው
እንደ ቼዙ ሜዳ የተዥጎረጎረው
--ለካ ለፍቅር ነው
በጉብዝናሽ ወራት በወጣትነትሽ
እነዚያ ውብ አይንሽ
ጎላ ጎላ ያሉት
ከለሊት ጨረቃ ደምቀው የሚታዩት
አሁን ደም ለብሰዋል
አንቺ ለእኔ ብለሽ በጪስና አቧራ
ሰውተሻቸዋል
---ይሄም ለፍቅር ነው
አንቺ የፍቅር አምድ
ተምሳሌት የመውደድ
አንቺ የፍቅር ማዕድ
ልክ እንደከዘራ ጀርባሽ የጎበጠው
አሁን ነው የገባኝ እኔ ቀና እንድል ነው
------አንቺ እንዲህ የሆንሺው ለካ
ለፍቅር ነው
መዳፍሽን ሳየው
አሻራ እንኳን የለው
ድህነት በልቶታል
ሸክም አጥፍቶታል
-----እናም ውዷ እናቴ
ዝምብየ ሳስበው
ምን አይነት ፍቅር ነው
ይሄን ሁሉ የሆንሺው
አንዴት በትወጂኝ ነው።
እማ ዛሬ ፍቅርሽ ገባኝ!!!

━━━━━━━━✦❤️✦━━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን  👍

           Join us 👇👇👇

https://www.tgoop.com/fekr_bicha
               ባንቺ ጨከንኩኝ

እንደ አዳም ከገነት ማለዳ ልባረር፣
ጨርቄን ማቄን ሳልል ከጎዳና ልደር፣
ባንቺ ከጨከንኩኝ
የተስፋይቱን ምድር ይኑርብኝ ከልካይ፣
ልቅር ከመንገዱ እንደሙሴ ሳላይ።

ባንቺ ከጨከንኩኝ

ጎልያድ ክብደቴ የጀግንነት ደሜ፣
በነዳዊት ጠጠር ይጣለኝ ባ'ፍጢሜ።
የት አባቱ ክብር ይደፋ ከገደል፣
አንቺ እንኳን ቀርተሻል ልከሽብኝ ፊደል።

ባንቺ ከጨከንኩኝ

እንደ ዘማዊቷ ያንሳብኝ ድንጋይ ሰው፣
ገላጋይ ሳይኖረኝ ደሜን ውሻ ይላሰው።
ባንቺ ከጨከንኩኝ
እዉነተኛ ዳኛ ካለ በሠማይ ላይ ይፃፈው በፊደል፣
ይውጣ ባደባባይ የኔና ያንቺ በደል፣
እኔ እንዳንቺ አይደለው አልችልም መጨከን፣
መቁጠር አልተሰጠኝ የሰውን ልጅ እንከን።
የሰው ልጅ ይስታል ስቻለው ባ'ንዱ ዕለት፣
አውቃለው በደሌን ማሪኝ ምን አለበት?

አልጨክንም ባንቺ

ባንቺ ከጨከንኩኝ ይዘዝብኝ ጨካኝ፣
የበደሌ ፅዋ መላ አካሌን ይንካኝ።
ከጨከንሽብኝም ፥ጨካኝ ይዘዝብሽ አልልም ደፍሬ፤
መኖር ስለማልችል
ራሴን ራሴ ልቅበር መቃብር ቆፍሬ

Join us 👇👇👇
https://www.tgoop.com/fekr_bicha
#አሜን_በይ_ልመርቅሽ☺️

ካልሽ እንግዲህ አቦል ጀባ
ያብብ መልክሽ እንደአበባ
ያውድ ጥሩ ቴሌግራም ቤትሽ
በ Hi  ይሙላ Inbox ደጅሽ 😅
እንዳማረው ሸክላ ጋቻ
ጀንጃኝ አትጭ አግኝ አቻ 😘

በይ አሜን በይ ልመርቅሽ,,,,

ካርድ አትጪ ዳትሽ ይብራ 😄
ላይክ አድራጊሽ ይበል ጎራ
ሼር ፣ ኮሜንትሽ አያባራ 😜

በይ አሜን በይ ልመርቅሽ

ይሰውርሽ ከጂል ፍሬንድ ከዘረኛ
የሰው እምነት ከሚሳደብ በሽተኛ
በፖሰትሽው ከሚናደድ ቀናተኛ
ከአዲስ ጀንጃኝ ከሆነ አዛ 🤏
ማሬ ፣ ማሬ ከሚያበዛ
ይጠብቅሽ ከሞዛዛ 🤔

በይ አሜን በይ ልመርቅሽ

ስልክ ቁጥር ላኪ ከሚል 😟
ቢሰጡትም ከማይደውል 😩
በባዶ አንጀት ከሚያደርቅሽ 😕
ልብ ጠቢ ይጠብቅሽ 🤲

በይ አሜን በይ ልመርቅሽ,,,,

እንደፈላው ቆንጆ ቡና 😍
የኔ አይነት ልጅ መልከ ቀና 😌
ላግባሽ ብሎ ይላክልሽ ሽምግልና
አቦ እፎይ በይ በቃ አግብተሽ 😀
ስልክሽ አርፎ አንችም አርፈሽ
ቶሎ ተኝ ዳታ አጥፍተሽ 😗
በባልሽ ክንድ ብሎክ ሁነሽ 😂

            😁 አሜን በል 😂


   ❤️
        ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

               Join us 👇👇👇

https://www.tgoop.com/fekr_bicha
ከምር እወድሻለሁ

ከ  = ከልቤ ሠሌዳ በደም ስሬ ብዕር
ም = ምስልሽ ታትሞበት መከረኛው ፍቀር
ር   = ርቀት ሳይገድበው ልቤ አንቺን ሽቶ
እ   = እትቱ በረደኝ ናፍቆትሽ በርትቶ
ወ  = ወኔዬ ተሟጦ ከጎንሽ ባለቆምም
ሻ   = ሻክሮ መንገዳችን ለየቅል ብንሆንም
ለ   = ለቅፅበት ይህ ልቤ ሊረሳሽ አልቻለም
ው  = ውሎ አድሮ ትዝታሽ አለ እስካሁንም

 
Channel photo updated
                     😒 ህልሜ  😒      


በባዶ ሰመመን ሩቁን ተጉዤ
ያለምንም ነገር ምስኪን ልቤን ይዤ
ዳገት ተራራውን ሽቅብ ቁልቁለቱን በቅጡ ተጉዤ
ልቤ ተሰበረ ይህን ሁሉ አድርጌ ። 💔

      ህልሜን ሚፈታልኝ ማነው የኔ ንጉስ👑
       አድኑኝ ባካቹ ራሴን ከመውቀስ።🙏

ህልም እንደቺው ነው ሲባል ሰምቻለው
ግን እኔ አልገባኝም አስተሳሰባቸው። 🤏

         በህልሜ እያየሁህ በእውኔ ካጣሁህ
         እውነት መሞቴ ነው አንተን ካላገኘሁህ።

የኔ ህልም ማየት ለልቤ ፈተና ከሆነበት
ለማያገኘው ነገር መንገድ ከረዘመበት። 🏃‍♀️

         ቢቀርስ ማለሜ ለምን እጎዳለው
       ድካም ብቻ እንጂ ሌላ ምን ትርፍ አለው። 😱

ብተኛ ብነሳ ቁጭ እንኳን ብልበት
ህልሜ ስላንተ ነው ጥቅም በሌለበት። 😳

          ቢሳካልኝና አንተም የኔ ብትሆን
          ህልሜ ተሳክቶ በእውኔ ቢሆን።
        ሌላ ምን ፈልጌ እንዲ ሚያስደስተኝ 🆗

ህልም ህልም ስል ህልመኛ ተባልኩ
ማለም ውሸት እንደሆነ በራሴ ተማርኩ። 😎

By hanita❤️

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

Join us  👇👇👇

https://www.tgoop.com/fekr_bicha
❤️


                ጨረቃ 🌕

ጨረቃዋ ሆና የልቤ ጓደኛ
እጠብቃታለሁ እንቅልፌን ሳልተኛ
ደሞ ነግራታለሁ አንደናፈቀቺኝ
አዘነች መሰለኝ አቀርቅራ አየቺኝ
ቀና ብዬ አይቻት
ስላንቺ ነገርኳት
ተከፍች መሰለኝ አንባ አመለጣት
አይ የኔ ጨረቃ የዋህ ደግ እኳ ናት

ለብዙ ደቂቃ ስናወራ ቆየን
እኔ ጨረቃ በጣም ተወያየን
ለካ አሷም አፍቅራለች
ፀሀይን ለማግኘት በጣም ናፍቃዋለች
ነገርኳት ብታዝንም አንደማታገኘው
ፀሀይ ቀን ቀን እንጂ ለሊት ምን ስራ አለው
አዘነች ትዘና ተከፋች ትከፋ
አኔን አታይም ወይ ስጠብቅ በተስፍ 

የኔም ፍቅር ሆኖ ልክ እንደጨረቃ
ላገኝሽ አልቻልኩም አቅቶኛል በቃ
ጨረቃዬን ቃኘሁ ብድግ አልኩኝ ቀና
አይዞሽ አትከፊ ለኛም ቀን አለና
ምን አልባት ፈጣሪ ፀሀይን በለሊት
ወይ አንቺን ቀንአርጎ ለቀናችን ድምቀት
ያሳካው ይሆናል ያንቺን ፍቅር አውነት
ብዬ ነገርኳት ዋሸኋት

ፈገግ አለች ጨረቃዬ ሳቀች ጥርሷ ፈካ
ደና ዋል አለቺኝ ሊነጋ ነው ላካ
አይ ጨረቃ አምናኛለች መሰል
ክፋቱን ሳታውቀው በፀሀይ መቃጠል
ደስ ብሏት ሄደች
ክብ ሆና እየበራች
አኔ ግን ተከፋሁ
የሚያፅናናኝ ፍጡር መካሪ ስላጣሁ

        🌕🌖 ❤️

       Join us 👇👇👇

https://www.tgoop.com/fekr_bicha
Live stream finished (17 days)
🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟

           #ፍለጋ_ላይ .....

ከልብ የገባን ሰው እንዴት ነው 'ሚወጣው?
የእውነተኛ አፍቃሪ ምን ነበረ ዕጣው?
ተፈቃሪ የለም ደግሜ ገበየኹ
ዓለም ውሸታም ናት ብዙውን ሰው አየኹ!

አገኘኹ ይልና ልቤ የልቤን ሰው
ግና...
እምነቴን ጨለማ ወረሰው
አጣኹ የልኬን ሰው
ሚዛኔ ላይ ቆሞ እንባዬን 'ሚያብሰው
የለም ለእኔ ያ ሰው!

ክፉ ነኝ እንዳልል...
እውነተኛ ፍቅር ከልቤ ይፈልቃል
ታድያ?
ፍቅርማ ከክፋት ይልቃል!
ከሽንገላ ያርቃል
ግን የሆዴን ማን ያውቃል?
ሞኛ ሞኝ አጫውቶኝ፥ ሕጻን አዋቂውን በእኔ ይሳለቃል
ይዝናናል ይስቃል
መንስኤው በእኔ ያሳብቃል
ሕጻኑም ይስቃል!

ይኸውልሽ ሔዋኔ...
ካለሽበት መንደር በጊዜ ካልመጣሽ
ቆሞ ቀርነት ነው የወደፊት ዕጣሽ
ይሄም ካላሳጣሽ!

ነይ ነይ እያልኩሽ ነው፤ ነይ ቶሎ ድረሺ
ጊዜ ከወርቅ በላይ፤ መሆኑን አትርሺ!
አትሽሺ በይ "እሺ"

አንቺ የእኔ ሴት...
እኔ ላይ ምታደርጊ ሐሴት
ደርሶሽ ካነበብሺው በዪኝ "መጥቻለው!"
ከእንግዲህ አልጠይቅሽ ዕርሜን ጨርሻለው!
አቅሜን አጥቻለው!
ነይ 'ፈልጌሻለው!
ላውቅሽ አውቄያለው!

አንቺ የእኔ ሚስት አትመጪም? 😂
ወይስ ጭራሽ ከቤትሽ አትወጪም 😜
ከኔ አታመልጪም! 🆗
🔵

Join us 👇👇👇
https://www.tgoop.com/fekr_bicha
🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟🚟

              🧐 አጣብቂኝ 🧐

የውልህ አንተዬ
የኛ ነገር ሆኖ ፥  ከድጥ ወደ ማጡ
ክርያላይሶ ብለን ፥ ሰግደን ሳንነሳ ፥ ዳሌ ላይ ማፍጠጡ
ነብሰ በላን ውህድ ፥ በጨለማ ተገን ፥ ለሊት የቀየጡ
ነብስ ማር እያሉ...በፀአዳ ልባስ ፥ ወዳንተ ሲመጡ
ግዝትን ተላልፈው ...
እንደ እስጢፋኖስ ፥ በድንጋይ ውርጅብኝ ፥ ሰው የቀጠቀጡ

ሌላ ሌላም ብዙ ...በደልና ጥፋት
እየተላለፍን በየነጋው...ንጋት...
አፈፃዲቅ እኛ...አንተም ባረምሞ
አይተህ እንዳላየህ ....አፍህ ተከርችሞ...
አልፈህ ስታስገባን ....ሳይቆለፍ ደጅህ
እስከ ትላንትና...እጅ በላን በእጅህ ።
ክፋት ተሸክሞም
የሆዳችን...ነገር
በሆድ እንደዋለ...
ጭንቅ ቀን አስማጠን...በሩቅ አስዋዋለ
አፀድህ ርቆ...አዳፋ ነብሳችን...ከቤት ዘግቶ ዋለ

ይህኔ ......
#ጨነቀን
በተራራ በደል...ቤት ውሎ ...ቤት ማደር
መተንፈሻ ቅጥር...ሲጠፋን እንዳገር
ላለፈው እንለምን....ወይስ ለበፊቱ ?
ማረን ነው የሚባል ?
አውጣን ነው ፀሎቱ ?
በንዲህ ያለ ዘመን...በጠፋ ብልሀቱ
ኋላና ፊት ሆነው ፥ ሀጥያት እና ጥፋት ፥ በመሳ ሲመጡ
ካልጋላይ ሳይወርዱ...ከጎጆም ሳይወጡ
በቀን ይጨልማል ፥ በደል ጎርፍ ሰርቶ ፥ ሜዳ ላይ ሲሰምጡ ።

                     ህሊና ደሳለኝ

Join us 👇👇👇
https://www.tgoop.com/fekr_bicha
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

👱‍♀👫አንቺን እያፈቀሩኩ…💝👫
                ቃል
👨👩👱‍♀👱👴👵👳‍♀👳👮‍♀👮

አንቺን እያፈቀርኩ ከማህፀን ወጣሁ፡
አንቺን እያፈቀርኩ ብዙ ነገር አጣሁ
አንቺን እያፈቀርኩ እየመሸ ይንጋ
አንቺን እያፈቀርኩ ይለፍ ክረምት ና በጋ
አንቺን እያፈቀርኩይለፍም እድሜዬ
አንቺን እያፈቀርኩ ልቅርም ብቻዬን
💚💛❤️💙💜🖤💝💖💞💝
ለአንቺ እየኖርኩ እኔን ይክፋኝ
አንቺን ደስ ብሎሽ እኔን ይጭነቀኝ
ልሁን እማይጠቅም ልሁን እርካሽ
አንቺን እያፈቀርኩ ለ አፍታ ሳረሳሽ
ልኑር በድር በድር ልኑር በጨለማ፡
ምን ንብረት አለኝ ለአንቺ እማይሆንማ
ዉሰጂው ልቤን ውሰጂው ደሜን
ይምቱኝ ይቀጥቅጡኝ ስለ አንቺ እኔን
አንቺን ከቶ አይክፋሽ እኔ እያለሁኝ
አንቺን እያፈቀርኩ አለም ተለፈኝ
አንቺ ላይ እሚሆነው ይሁን እኔ ላይ
ምድርም ከፍ ዝቅ ትበል እኔን ታሰቃይ
ባዶም ቢሆን ይህ ዐለም ያለአንቺ
መውደዴን አትወቂው አትረጂው አንቺ
💚💛❤️💙💜🖤💝💖💜💙
አንቺን እያፈቀርኩ ልክሳም ልጥቆር
አንቺን እያፈቀርኩ ልምሰልም አፈር
አንቺን እያፈቀርኩ አልሳቅ አልጫወት
አንቺን እያፈቀርኩ ትለፍም የኔ ህይወት
አንቺን እያፈቀርኩ አልብላ አልጠጣ
አንቺን እያፈቀርኩ ከቤቴም አልውጣ

ከወደኩበት ቦታ አንድ ቀን ብቅ ብለሽ
አፃናነተሺኝ ሂጂ አለሁልህ ብለሽ
አግቢ ውለጂ ከብደሽም ኑሪ
ይክፋኝ ግድ የለሽም እኔ የአንቺ አፍቃሪ
💝💘💖💚💛❤️💝❤️💛💚
አደራ ግን ነይ በህልሜ ማታ
አንቺን አይቼ ላንባ መንታ መንታ
እመጣለው የሰርግሽ ለታ
እንቺን እያፉቀርኩ ሉኑር በትዛታ
ፅልይልኝ እንዳልሞትብሽ
አልቻልኩም አቃተኝ እኔ አፍቃሪሽ…
.
@fekr_bicha
2️⃣0️⃣2️⃣5️⃣
መልካም ገና
​​🍃🍂​​✟በፍቅሩ አሸንፏል  ✟🍂

ምን አይነት ፍቅር ነው ምን አይነት መውደድ
ንጉሱን ከሰማይ ከዙፋን የሚያወርድ
እስኪ የትኛው ነው የትኛው ስራችን
እስከሞት ውለታ የሚከፈልልን
ፍፁም ይገርመኛል ከአይምሮ በላይ ነው
ስለአንዱ በግ ብሎ መንጋውን የተወው
ፍፁም ፍቅር አየን ፍፁም ትህትና
አምላክ ስለ ሰው ልጅ ከላይ ወርዷልና
እንዲ ለዋለልን ለታላቁ ጌታ ለፍቅር ባለቤት
ሞትን ደገስንለት  በአይሁዶች እጅ ተሰቃይቶ እንዲሞት
አምላክና ወንበዴ አንድላይ አቁመን
ወንበዴውን ፈታን ከአምላክ አስበለጠን
ይህን ክፋት አይቶ ከቶ መች እራቀን
እሱ አቀርቅሮ እኛን ቀና አረገን
ድንጋዩ ልባችንን መች ፍቅሩ ሰበረው
ገንዘብ አስበልጠን በ 30 ዲናር ለጠላት ሰጠነው
ንፁህ ሆኖ ሳለ ሀጥያት የሌለበት
በሀሰት ተከሶ ሞት ተፈረደበት
አኛ እየሸጥነው ወዳጄ ይለናል
የፍቅር አምላክ መሆኑን በግልፅ አሳይቷል
መስቀል አሸክመን ቀራኒዮ ሰደድነው
እራሱ ፍቅር በሀሰት ልንሰቅለው
እሁንም ፍቅር ነው አሁንም ዝምታ
ለጠላቶቹ ነው የሚያዝነው ጌታ
እንዲህ እየወደደን እኛ መች ወደድነው
ቀትር 6 ሰዓት ከመስቀል አኖርነው
አሁንስ ይገርማ በእውነት ድንቅ ነው
መስቀል ላይም ሆኖ ማራቸው ነው ሚለው
ቁስላችንን ሊያድን ስለኛ ቆሰለ
ከሞት ሊያነሳን  ሞቶ ተቀበረ
እጅግ ቢበረታም የኛ በደላችን
በፍቅሩ አሸንፏል ኢየሱስ ጌታችን


   ዮዳሄ
አዘጋጅ : ስለ ፍቅር
​​​​​​┄┄┉┉✽‌»‌‌✿»🌺‌‌✽‌┉┉┄┄
                   
                @fekr_bicha
2025/01/10 12:31:41
Back to Top
HTML Embed Code: