Telegram Web
ሰዎችን በምታዝበት መልካም ነገር ተግባሪ ወይም ከምትከለክልበት መጥፎ ነገር የምትቆጠብ ሁን። አለበለዚያ ግን…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿يُجَاءُ بِالرَّجُلِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، فَيُلْقَى فِي النَّارِ، فَتَنْدَلِقُ أَقْتَابُهُ فِي النَّارِ، فَيَدُورُ كَمَا يَدُورُ الْحِمَارُ بِرَحَاهُ، فَيَجْتَمِعُ أَهْلُ النَّارِ عَلَيْهِ، فَيَقُولُونَ : أَيْ فُلَانُ، مَا شَأْنُكَ ؟ أَلَيْسَ كُنْتَ تَأْمُرُنَا بِالْمَعْرُوفِ، وَتَنْهَى عَنِ الْمُنْكَرِ ؟ قَالَ : كُنْتُ آمُرُكُمْ بِالْمَعْرُوفِ وَلَا آتِيهِ، وَأَنْهَاكُمْ عَنِ الْمُنْكَرِ وَآتِيهِ﴾

“በቂያማ ቀን አንድ ሰው ይቀረብና እሳት ውስጥ ይጣላል። ከዚያም ሆድ እቃው ይዘረገፍና ልክ አህያ ወፍጮውን ይዞ እንደሚዞረው ይዞት ይዞራል። የእሳት ሰዎች ከሱ ዘንድ ይሰበሰቡና እከሌ ሆይ! ምን ነካህ በመልካም ታዘን፣ ከመጥፎ ትከለክለን አልነበረምን ሲሉት እንዴታ! ነገር ግን በመልካም እያዘዝኩ አልፈፅመውም ነበር። ከመጥፎ እየከለከልኩ እፈፅመው ነበር ይላል።”

📚 ቡኻሪ (3268) ሙስሊም (2989) ዘግበውታል



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆#በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልኽሚስ 1⃣5⃣ #ሙሐረም 1⃣4⃣4⃣7⃣
የዓሊሞች ሞት!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إِنَّ اللَّهَ لَا يَقْبِضُ الْعِلْمَ انْتِزَاعًا يَنْتَزِعُهُ مِنَ الْعِبَادِ، وَلَكِنْ يَقْبِضُ الْعِلْمَ بِقَبْضِ الْعُلَمَاءِ، حَتَّى إِذَا لَمْ يُبْقِ عَالِمًا اتَّخَذَ النَّاسُ رُءُوسًا جُهَّالًا، فَسُئِلُوا فَأَفْتَوْا بِغَيْرِ عِلْمٍ، فَضَلُّوا وَأَضَلُّوا﴾

“አላህ ዒልምን ‘እውቀትን’ ከሰዎች ልብ ውስጥ መንጭቆ አይወሰደውም። ነገር ግን ዓሊሞችን ‘አዋቂዎችን’ በማንሳት ‘በሞት በመውሰድ’ ዕውቀትን ይወስደዋል። ዓሊም ‘አዋቂ’ የሚባል እስከማይኖር ድረስ። ሰዎች ጃሂል ‘መሀይም’ የሆኑ አላዋቂዎችን መሪ አድርገው ይይዛሉ። ይጠየቃሉ ያለ እውቀት መልስ ይሰጣሉ። ለራሳቸው ጠመው ሌሎችንም ያጠማሉ።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 100



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
Audio
#ኪታብ ዑምደቱል አህካም
#በፈትህ አባቦራ መስጂድ
#ዘወትር ረቡዕ እና ጁመዓ ከመግሪብ- ዒሻ #በኡስታዝ ካሚል ጣሃ   ደርስ በድምፅ ክፍል #59 መከታተልና መቅራት ትችላላችሁ። #እንዳያመልጥዎ
👍1
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ጁምዓ 1⃣6⃣ #ሙሐረም 1⃣4⃣4⃣7⃣
ወሳኝ ዱዓእ!

ከአቡበከር ሲዲቅ (رضي الله عنه) ተይዞ፡ የአላህ መልዕክተኛን (ﷺ) እንዲህ በማለት ጠየኳቸው፦

﴿عَلِّمْنِي دُعَاءً أَدْعُو بِهِ فِي صَلَاتِي قَالَ : " قُلِ : اللَّهُمَّ إِنِّي ظَلَمْتُ نَفْسِي ظُلْمًا كَثِيرًا، وَلَا يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا أَنْتَ فَاغْفِرْ لِي مَغْفِرَةً مِنْ عِنْدِكَ، وَارْحَمْنِي إِنَّكَ أَنْتَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ﴾

“በሶላት ውስጥ ስሆን የምለውን ዱዓእ ያስተምሩኝ። እንዲህ በል አሉኝ፦ ‘አላህ ሆይ! እኔ ነፍሴን በጣም ብዙ በድያታለሁ። ካንተ በስተቀር ወንጀልን የሚምር የለምና፤ ካንተ ዘንድ የሆነ ምሕረትን ለግሰኝ። አንተ መሐሪና አዛኝ ነህና እዘንልኝም።’”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 834



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#ሰብት 1⃣7⃣ #ሙሐረም 1⃣4⃣4⃣7⃣
የሰላሟ ሐገር መካ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿فَإِنَّ هَذَا بَلَدٌ حَرَّمَ اللَّهُ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ، وَهُوَ حَرَامٌ بِحُرْمَةِ اللَّهِ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ، وَإِنَّهُ لَمْ يَحِلَّ الْقِتَالُ فِيهِ لِأَحَدٍ قَبْلِي،﴾

“ይህን ሐገር (መካ) አላህ ምድርንና ሰማያትን የፈጠረ ቀን አከበረው። እስከ እለት ትንሳዔ ቀን ድረስም የተከበረ አድረጎታል። በውስጡ ለኔም ከኔም በፊት ለነበረ አንድም ሰው ውጊያ አልተፈቀደለትም።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 1834



https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
https://www.tgoop.com/fethababora
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ
#አልአሃድ 1⃣8⃣ #ሙሐረም 1⃣4⃣4⃣7⃣
2025/07/13 12:19:28
Back to Top
HTML Embed Code: