💞የእናት ዋጋ ሲተመን💞
❤️ትንሹልጅ እናቱ ወዳለችበት ማብሰያ ክፍል ሲገባ እናቱ እራት እየሰራች አገኛትና የያዘውን ብጣሽ ወረቀት ሰጣት፡፡ እናት እጆቿን አደራርቃ ተቀበለችውና አነበበችው፡፡
💞 እንዲህ ይላል፡፡የግቢውን ሳር ላጨድኩበት 5 ብር የመኝታ ክፍሌን ሳምንቱን ሙሉ ላጸዳሁበት 1 ብር ከማብሰያ ቤት እቃ ላመጣሁበት ሃምሳ ሳንቲም አንች ገበያ ስትሄጅ ትንሹን ወንድሜን እያጫወትኩ ያቆየሁበትን ሃያ አምስት ሳንቲም ቆሻሻ የደፋሁትን 1 ብር
የአገልግሎት ክፍያ ደረሰኝ ያመጣሁበት 5 ብር ግቢውን ያጸዳሁበትን 2 ብር
በአጠቃላይ 14.75 ሲል ያገልግሎት ክፍያየን ስጭኝ ሲል ጠየቀ፡፡
❤️አናት ጥሩ አለችውና እያስተዋለችው ትንሽ አሰብ አድርጋ ወረቀትና እስክብሪቶ አዘጋጅታ መመዝገብ ጀመረች፡፡
ዘጠኝ ወር ሙሉ እስክታድግ ድረስ በሆዴ የተሸከምኩህ… ያለምንም ክፍያ፡፡
ለሊቱን ሙሉ እንቅልፍ ሳልተኛ እየተንከባከብኩ የሳደኩህ… ያለምንም ክፍያ፡፡
💞አንተን አሁን እስከደረስክብት ዕድሜ በማሳደግ ለደከምኩት ድካም… ያለመንም ክፍያ፡፡ትንሽ እንኳን ሲያምህ ያለ እንቅልፍ በጭንቀት ላለፉት ሌሊቶች… ያለምንም ክፍያ፡፡ ላሻንጉሊትህ፣ለምግብህ፣ለልብስህ ያወጣው ወጭ…ያለምንም ክፍያ፡፡
❤️ውዱ ልጄ ከሁሉም የላቀው ደግሞ ይሄን ሁሉ ደምረህ ብትመዝነው የእኔ ፍቅር ላንተ የሚተመን ዋጋ የለውም፡፡ እንዲህ ብላ ጽፋ አቀበለቸው፡፡ልጁ ይሄን አንብቦ እንደጨረሰ እንባ በዓይኖቹ ሞልተው ይታየ ነበር፡፡ እናቱን እየተመለከተም እንዲህ አላት “እናቴ እንደምወድሽ አረጋግጥልሻሁ!” አለና እስክብሪቶውን አንስቶ በትልቁ በደማቁ “በሚገባ ተከፍሏል!” ሲል ጻፈበት፡፡
ግንዛቤ፡
💞የወላጅነትን ስሜት፤የወላጅነትን ዋጋ ወላጅ እስክንሆን ድረስ ለማወቅ የበቃን አይደለንም፡፡ሰጭ እንጅ ጠያቂ መሆን ተመራጭ አይደለም፡፡ በተለይም ደግሞ ለወላጆቻችን፡፡ ከገንዘብ በሻገር ገና ልንሰጣቸው የሚገባ ብዙ ብዙ ነገር ስላለ፡፡ ከሁሉም በላይ እናት የሚተመንላት ዋጋ የላትም፡፡ ከዋጋ በላይ ናትና፡፡
🗞ምንጭ፡ valuing Mother love
@fikren

የምንወደው እና የሚወደን ቼ ልደቱ ነው!❤️✌️✌️
ከቼ ጉቬራ ጋር ሞተር ላይ ተፈናጦ መላ ላቲን አሜሪካን የዞረው አልቤርቶ ግራናዶስ "ቼ ዘወትር መሞገስን የሚሻ ጌታ አይደለም። እርሱ ሰው ነበር! ዳናው ያማረ፤ ፈለጉን የሚከተሉት አይነት።" ይላል! በርግጥ ልክ ነው። ሙገሳን የማይሻ ስለ ሰው ልጅ ኖሮ፤ ለታገለልት መርህ የሞተ መሲህ ነው! መሲህ ደግሞ አሞግሱኝ ሲል የማይመፃደቅ፤ በሰዎች ውዳሴ ጠንካራ ልቡ የማይሸረሸር ብርቱ ሰው ነው። አሞግሱኝ ባይልም በዘመናት መቀያየር ሳይዘነጋ፤ በቀናት መንጎድ ሳይሻር ዛሬ ድረስ፤ ነገን ጨምሮ እስከ ዘላለም ቼ በአለም ዙርያ ስለፍትህ ለሚያስቡ፤ ስለ እኩልነት ለሚጨነቁ ሁሉ አርኣያ ነው።
ቼ ጎምርቶ የከሰመ የመሰለው አላማው እንደረመጥ እየተንቀለቀለ መላው አለምን እያነቃቃ ነው። በበዝባዥ ስርአት ላይ የከረረ ጥላቻ፤ በመደብ ብዝበዛ ላይ የጠነከረ ስል ትችት እየመጣ ነው። ዛሬ የተረሳ ቢመስልም የቼ አላማ ፍሬው እያበበ ነው፤ ቀጣዩ ትውልድ በመርሁ እየተገራ ነው። ብዛቱ ሳይሆን ጥራቱ ከድል ደጃፍ ያደርሰዋል።
ዛሬ ድረስ በኩባ የትምህርት ተቋምት ህፃናት “Pioneers for Communism: we will be like Che,” ሲሉ አዲስ ቀን በጠባ ቁጥር ስሙን ያነሱታል። መርህህን፣ ጎዳናህን፣ ፈለግህን፣ ዳናህን እንከተላለን ሲሉ በአክብሮት እጃቸውን ከፍ አርገው ደጋግመው በልቅና ዙፋኑ ላይ ያነግሱታል።
ቼ ከሰውነት ህላዌ በላይ ሰው የመሆን ምሳሌ ነው። ቼ ካስተሳሰረን ደም ይልቅ ለሰው ልጆች ያለን ፍቅር ተራራን ማንቀጥቀጥ እንደሚችል ያሳየን መልኣክ ነው። ቼ የነገስታት ሁሉ አለቃ፤ የታጋዮች ሁሉ ቁንጮ፤ የአርነት አርማ፤ የነፃነት ቀንዲል ነው። ቼ በግዜውም፣ ዛሬም እስከ ዘላለም ምሉዕ የሆነ ሰው ነው።
ቼ "If you tremble with indignation at every injustice, then you are a comrade of mine." እንዲል በመንገዱ ባልመንን፤ ፈለጉን ተከትዬ ብረት ባላነሳ በየትኛውም ጥግ ማንም ቢሆን ሲበደል ሳይ ስሜቴ ስለሚነካ ጓዱ ነኝ ብዬ በክብር አወራለው።
#ቼ የሰው ልጅ! #ቼ የፍህትህ ሰንደቅ!❤
@fikren
@fikren
@Rasyisak

የሰውነት ሰንደቅ!ቼ!❤
<<እሱ በየቀኑ የተወለደበት ቀን እንጂ የሞተበት ቀን የለም>>
ሁሉም ነፍስ የየራሱ መክሊት አላት። የሰው ልጅ ከራሱ "ነፍስ" ....... ከነፍሱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸውን ነፍሶች ያጠቃልላል .....በላይ የሚወደው የሚያስበልጠው ነገር ከሌለው ያሰው ለእሄ ተራ ሰው ከሚባሉት ውስጥ ነው።
ግን አንድ ሰው ከነፍሱ በላይ አሻግሮ ማየት ከተቻለው እና ማረግ በሚችልበት አቅሙ ማረግ ከቻለ ያ ሰው ነው ጀግና።
ጀግና እንደመንጋ አይመስለኝም ለራሱ እሚነግረው ታሪክ ሳይለይ አይቀርም ለጀግና መሞት ማለት ላመኑበት ነገር መውለሽለሽ ነው ።ለጀግና ላመኑበት ታግሎ ለፍቶ መሞት ህያው መሆን አይነት ነው። ስለዛም ነው ወኔው ሳየከዳው ወደ ሞት የሚጋልበው #ለነብሱ አይሳሳላትም ዛሬ በተአምር ከተረፈው የሞት ክስተት ነገ ተመልሶ እዛው በዛው ወኔ ይከሰታል። ጀግና ሰው እንደተራ ሰው ሞት አያበረግገውም አስፈላጊ ከሆነ ሞት ወደሱ ሳይመጣ እሱ ወደ ሞት ሄዶ በወኔ ይታገለዋል !!!!
በየቀኑ ይወለዳል በብዙዎች ልብ ውስጥ!❤ቼ

አንተነህ አባቴ!!!!!!!!!!
የህይወትን ቅኔ፤ በታዛቢ አይኖችህ፤
በገራገር ልብህ፤ በፅሞና ገርተህ፤
ጎርባጣውን ኑሮ፤
ሳቅ በሚሉት ምትሃት፤ ቋጠሮውን ፈተህ፤
ለልጆች ብርሃን፤
ያንተን ቀለም ሽረህ፤ ያንተን ጎህ አጥፍተህ፤
ለልጅህ ንግስና፤
ሰፍነግ ተጎንጭተህ፤ የእሾህ አክሊል ደፍተህ፤ አንተ ግን ብፁእ ነህ፤
ሃውልት አቁመሃል፤
ለዘንባላው ልጅህ፤ ከሙላትህ ጎድለህ።
በዝቅታ ጎራ፤ በመውረድ ንግስና፤
ከራስ እያጠሩ፤
በወኔ መከምከም፤ የልጅን ቁመና፤
ሲሰልጥህ አየሁኝ፤
የተመረቀልህ፤ መንገድህ ነውና።
ከራስ ቁራሽ ነጥቆ፤
ከራስ ወኔ ሰርቆ፤
የልጅ ወግ አድምቆ፤ በድል ቃል መሸለም
ልንገርህ አባቴ፤
በአንተ ልቡና እንጅ፤ በሌላ ዘንድ የለም።
በሽንፈት መሃከል፤
በውድቀት መሃከል፤
ጎተራ የሚሞላ፤ ተስፋ እየመገብከኝ፤
በማጣት መሃከል፤
በንጣት መሃከል፤
ከእጄ ሞልቶ ሚፈስ፤ ወኔ እየቀለብከኝ፤
ልጄ በሚል ድምፅህ፤
እንደ ዋልያ እግሮችህ፤
መንፈሴ እየፀና፤
ከህይወት ተራራ፤ ከአናቱ አደረስከኝ።
አንተ እኮ ታምር ነህ፤
አንተ እኮ ግሩም ነህ፤
በፍቅርቅር ቀልብህ፤
በስስት አይኖችህ፤ በእንባ እያጠብከኝ፤
ዛሬም በእስከ ማታ፤
ልጄ ማሙሽ ብለህ፤ ባንቀልባ እያዘልከኝ፤
በእስትንፋስህ ቁጥር፤
ባይንህ ጥቅሻ ቁጥር ዛሬም እያሰብከኝ፤
በጉድለት እርካብ ላይ፤
ያንተን ቀናት ሸርፈህ፤
ቀኔን ያበጀኸው፤
የህልሜ መተርጉም፤ ህያው ምልክቴ፤
የአልፎ መሄድ ሰንደቅ፤ የድል ክትባቴ፤
አንተ ነህ ሰው ማለት፤ አንተ ነህ አባቴ፤
((( ይሳቅ))) ïsçø
እንኳን ለአባቶች ቀን አደረሳቹ!❤️❤️

"ከራስህ በላይ ለሌሎች ማሰብ የዕድሜ ሳይሆን
የሰውነት
መገለጫ ነው
ብርሃን ብርሃን የሚሆነው ብርሃኑን ምንም ወደ ራሱ ሳይቆጥብ ወደ ውጭ በመርጨቱ ነው። ያ ባይሆን ብርሃን ብርሃን ባልሆነ ነበር።
ወንዝ የመፍለቅንና የማያቋርጥ ፍሰት የሚያከናውነው ወደ ራሱ ሳይቀለበስ ሙሉ በሙሉ ወደ ውስጥ ስለሚፈስ ነው። እኛም ለጨለማው አለም ብርሃን ፣ ለተጠማው አለም እርካታ ሆነን ለማለፍ ከራሳችን ለሌሎች ማሰብ ፣ የግላዊነት ሙቀት መተው ያስፈልገናል።
ራስን ብቻ በማዳመጥ እርካታ ያለው ኑሮ መኖር አይቻልምና።
"እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ" እንዳለ መፅሐፍ ብርሃናችንን ለሌሎች እናካፍል።
ውብ አሁን 💚
.

በዘመናችን ብሔርተኝነት ማለት የሌሎችን የድካም ውጤት መቀማት መሆኑን አውቃለሁ። አንድ ሰው በግሉ ስኬት መቀዳጀት ሲያቅተው በጥረታቸው ብልጫ ያስመዘገቡ ሰዎችን ስኬት ወደ ብሔር ስኮት ለውጦ ባዶነቱን ለመሙላት ይሞክራል። ሌላው ህልም ያለ ፈሪ ሆኖ ሳለ "የበላይ ዘር" እያለ ይፎክራል። ብብቱውስጥ ገብተው ካልደገፉት በቀር አልጋ ላይ መውጣት የማይችል ሰውዬ አበበ ቢቂላ በተነሳ ቁጥር "አበበ ኬኛ" እያለ ይኩራራል። በላይና አበበ ያስመዘገቡት ድል በላብና በደም የተገኘ የግለሰብ ጥረት ውጤት ነው። ድል በዘር አይተላለፍም። የአባቶች ታላቅነት በዘር ወደ ልጆች የሚተላለፍ ቢሆን ኖሮ ግሪኮች በዛሬይቱ የአውሮፓ እግር ስር እንደ ጉድፍ ወድቀው ባልተገኙ ነበር። ብሔርተኝነት የግለሰብ ጥረትን ሰርቆ የራስን ድክመት ለመሙላት የሚደረግ የመሰሪ እንቅስቃሴ ነው።
ምንጭ ፦ ከአሜን ባሻገር
በእውቀቱ ስዩም
@fikren
@fikren
@Rasyisak
ምንጭ ፦ ከአሜን ባሻገር
በእውቀቱ ስዩም
@fikren
@fikren
@Rasyisak
#የራስ_ሃሳብ
.
.
.
ጡት እንዳጣ ህጻን ፣ መራር እንዳጠቡት
እንደተከፋ አንጀት ፣ ከራስ እንዳፋጩት
ሆዷ እንደጮኸ ሴት፣ርሃብ እንደጠናት
ባሏ እንደቀረባት ፣ እንደ ልጅ አልባ እናት
እንደ ወጥመድ አይጥ ፣ እንደ መረብ አሳ
እንደ እረኛ ዋሽንት ፣ እንዳዘለው ገሳ
መውጫ እንዳጣ ትንፋሽ ፣ ውስጤን እንዳመቀ
በ'ምባ ታጥቦ ሆዴ ፣ ላይፈስ በፈለቀ
ቆሻሻው ጸድቶለት ፣ ንጹህ ነገር ቢያጣ
ባር ባር ይለው ጀመር ፣ ወዳጁን እንዳጣ...
ሃገር ምን ይለኛል? ባልተናገረኝ ሰው ባልሰደቡኝ ስድብ
ቁዝም አቅበዝዝዞኝ በሃዘን ድባት ውስጥ ከደስታዬ ሳድብ?
ምንይለኛል ቀየው ባልከፋብኝ ኑሮ ባልተጫነኝ በደል
አይኔ እንባን አርግዞ ለማማጥ ሲታደል ለመውለድ ሲጋደል?
መሃጸነ አፌ እንደ አይኔ ሁሉ ምናለ ቢነጥፍ?
ያረገዘን ሃሳብ በመውለድ እሳቤ ሳይምጥ ከሚለፍፍ?
ፈልቆ ያልፈሰሰ ተምጦ የቀረው የሃሳብ ልጅ ልጄ
ያንተከትከኛል ለሱ ባልኩት እሳት በእንባዬ ምትክ ትኩስ ደሜን ጥጄ
ይተናነቀኛል ህቅ ስቅ እያለ
ወደ ውስጤ ፈሶ ሞልቶ እያጎደለ
ሃሴት ከኔ አርቆ ድባት እያደለ....
አልበደለኝ በደል ፣ አልተናገረኝ ሰው
የራሴው ሃሳብ ነው ፣ ውስጤን የሚወቅሰው
ቃሌን ማሰልሰሌ ፣ ሆዴን የሚብሰው
አልበደለኝ በደል ፣ አልተናገረኝ ሰው
ወደፊቴ ያልኩት ፣ ዛሬን የሚያምሰው
ሃሳቤ ቢሰድበኝ ፣ ሽፍን የማለቅሰው
አልበደለኝ በደል አልተናገረኝ ሰው።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የራስ ሃሳብ የጭንቅላት
እየኳለ እያቀላት
ልጇን ወልዳ ልጇ በላት
አይመለስ አይገባላት
እንኳን ሰቡ አዘነለት ሃዘን ልቤን
ይቅር በለኝ ያወጋሁህ ክፉ ሃሳቤን
✍Tomi

❤️ፍቅር ያሸንፋል
አወይ የኔ እድል አወይ የኔ ኑሮ፣
ተለዋወጠብኝ ካምናው ይልቅ ዘንድሮ።
ምግብ አልበላህ አልጠጣህ አለኝ፣
እንቅልፍ አላስተኛ አላስቀምጥ አለኝ፣
ከሰው ጋር መግባባት ተራራ ሆነብኝ፣
ቀርበው ሲያወሩኝም ነጭናጫ አረገኝ፣
እውን ይሁን ቅዠት መለየት አቃተኝ፣
ብቻየን ለመኖር በጣምም ከበደኝ።
አወይ ሞኝነቴ አወይ ጅልነቴ፤
ተው ይቅርብህ ሲሉኝ እኔ አለመስማቴ፣
ሁሉንም ነግሬ ስለማንነቴ ፣
ይሄው ተቃጠልኩኝ በሰበሰ አንጀቴ፣
ተለዋወጠብኝ ሁሉም ሰውነቴ፣
ጎዳና ወጣሁኝ ደፈረሰ ቤቴ።
ከዚሁሉ ነገር አንች ብትረጂኝ፣
ፍቅሬን እንዳስረዳሽ ልብሽን ብሰጭኝ፣
ለጥቂት ሰከንዶች ቆመሽ ብታደምጭኝ፣
እነግርሽ ነበረ የማፍቀርን ሚስጥር፣
በዛ በመከራ ተይዤ በፍቅር፣
እንዲ ብየ አሰብኩ እራሴን ስከምር፤
'ማፍቀር መታደል ነው
መፈቀር ፀጋ ነው'
የሚል አባባል ጠቀስ አረኩና፣
ራሴን አፅናናው ከብዙ መከራ።
✍ @Eyoba88
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@fikren
@fikren
አወይ የኔ እድል አወይ የኔ ኑሮ፣
ተለዋወጠብኝ ካምናው ይልቅ ዘንድሮ።
ምግብ አልበላህ አልጠጣህ አለኝ፣
እንቅልፍ አላስተኛ አላስቀምጥ አለኝ፣
ከሰው ጋር መግባባት ተራራ ሆነብኝ፣
ቀርበው ሲያወሩኝም ነጭናጫ አረገኝ፣
እውን ይሁን ቅዠት መለየት አቃተኝ፣
ብቻየን ለመኖር በጣምም ከበደኝ።
አወይ ሞኝነቴ አወይ ጅልነቴ፤
ተው ይቅርብህ ሲሉኝ እኔ አለመስማቴ፣
ሁሉንም ነግሬ ስለማንነቴ ፣
ይሄው ተቃጠልኩኝ በሰበሰ አንጀቴ፣
ተለዋወጠብኝ ሁሉም ሰውነቴ፣
ጎዳና ወጣሁኝ ደፈረሰ ቤቴ።
ከዚሁሉ ነገር አንች ብትረጂኝ፣
ፍቅሬን እንዳስረዳሽ ልብሽን ብሰጭኝ፣
ለጥቂት ሰከንዶች ቆመሽ ብታደምጭኝ፣
እነግርሽ ነበረ የማፍቀርን ሚስጥር፣
በዛ በመከራ ተይዤ በፍቅር፣
እንዲ ብየ አሰብኩ እራሴን ስከምር፤
'ማፍቀር መታደል ነው
መፈቀር ፀጋ ነው'
የሚል አባባል ጠቀስ አረኩና፣
ራሴን አፅናናው ከብዙ መከራ።
✍ @Eyoba88
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@fikren
@fikren