Telegram Web
🍇🌱🌱

እያንዳንዱ ቀንህን መመዘን ያለብህ በሰበሰብከው ፍሬ ሳይሆን በዘራኸውና በተከልከው ዘር ነው።

@fikrhn
@fikrhn
😪🤷‍♂
...
የውሸት ቅጣቱ በሰዎች ያለመታመን ብቻ አይደለም።ከዚያም የከፋው ቅጣቱ እርሱ ለራሱ ማንንም ለማመን አለመቻሉ ነው።

@fikrhn
@fikrhn
🏃🚶❤️

...የኑሮ ጥበብ ያለው አንዳንድ ነገሮችን በመያዝና በመልቀቅ መካከል ሚዛናዊ አድርጎ በመኖር ውስጥ ነው።

@fikrhn
@fikrhn
🌿የህልም እንጀራ!

ሆንግኮንግ/አሜሪካዊው ብሩስ ሊ (Bruce Lee) ታዋቂ አክተር፣ ብቁ የማርሻል አርት ባለሞያና አስተማሪ፣ እንዲሁም ስመ-ጥር ፈላስፋ ነበር፡፡ ይህ ሰው አንድ ጊዜ ስለስኬቱ ምስጢር እንዲህ ሲል ተደመጠ፣ “አስር ሺህ አይነት የተለያዩ የካራቴ ምቶችን በአንድ ቀን ከተለማመደ ሰው ይልቅ እኔ የምፈራው አንድን አይነት የካራቴ ምት አስር ሺህ ጊዜ ደጋግሞ የተለማመደን ሰው ነው”፡፡

አንድ ቀን ተነስተን የተለያዩ ነገሮችን ስለሞከርን ብቻ የትም እንደማንደርስ አመልካች የሆነ ሃሳብ ነው፡፡ አስር ሺ አይነት ነገሮችን ከመሞካከር፣ ዓላማችንንና ግባችንን ከለየን በኋላ ያንን አንድን ነገር አስር ሺህ ጊዜ አድምተን ብንደጋግመውና ብንለማመደው ለምነገባበት ስኬት ወሰን አይኖረውም፡፡

የዚህ እውነታ ምስጢር ያለው በመነሳሳት (Motivation) እና በዲሲፕሊን (Discipline) መካከል ያለውን ልዩነት በማወቅ ነው፡፡ የተነሳሳን አንድ ቀን ከምናደርጋቸው አስር ሺህ የዘመቻ ስራዎች ይልቅ የያዝነውን አንድ ነገር በዲሲፐልን አስር ሺህ ጊዜ ብንደጋግመው የተሸለ ውጤትን እናገኛል፡፡

በመነሳሳት የጀመርነውን ነገር በዲሲፕሊን መቀጠልን እስከምንለምድ ድረስ ስኬት የህልም እንጀራ እንደሆነ ይቀራል!!!


••●◉Join us share◉●•• @fikrhn
@fikrhn
@fikrhn
❤️🌹🚶
የቀረበን ሁሉ ወዶን አይደለም፤ የራቀን ሁሉም ጠልቶን አይምሰለን። ቀርበው ደካማ ጎናችንን አጥንተው የሚጎዱን እንዳሉ ሁሉ በአብሮነታቸው እየጎዱን ስለመሰላቸው ብቻ በአካል እርቀውን ሌት ከቀን ስለእኛ መልካም እያሰቡና እየተመኙ የሚወዱንም አይጠፉም።



••●◉Join us share◉●•• @fikrhn
@fikrhn
#የታየህን_ያህል_ተንቀሳቀስ

አንድ ምሽት ላይ አባት ልጁን ወደ ሲኒማ ቤት ሊወስደው ውጪ መንገድ ላይ መኪና ውስጥ እየጠበቀው ነው፡፡ ልጅ ከቤት እንደወጣ በጣም ስለጨለመበት ስልኩን አውጥቶ አባቱ ጋር ደወለ፡፡

• ልጅ፡- “አባዬ እንዴት ልምጣ? ጨለማ ስለሆነ አይታይም”፡፡
• አባት፡- “ምን ያህል ይታይሃል?”
• ልጅ፡- “አምስት እርምጃ ያህል ብቻ ነው የሚታየኝ”
• አባት፡- “አምስት እርምጃ ተራመድ”
• ልጅ፡- “እሺ” (አምስት እርምጃ ተራመደ)
• አባት፡- “አሁንስ ምን ያህል ይታይሃል?”
• ልጅ፡- “አሁንም ሌላ አምስት እርምጃ ያህል ርቀት ይታየኛል”
• አባት፡- “በፊትህ የሚታይህን አምስት አምስት እርምጃ እያልክ ከመጣህ እኔ ጋ ትደርሳለህና የታየህን ያህል ተንቀሳቀስ”

ልጅ ብዙም ሳይቆይ አባቱ ጋር ደረሰ፡፡

ሁሉም ነገር ጥጉ ድረስ እስኪታይህ አትጠብቅ፡፡ በሚታይህ መጠን ተራመድ፡፡ የሚታይህን ያህል ስትራመድ፣ ከመራመድህ በፊት ያልታየህን ማየት ትጀምራለህ፡፡

ሁሉንም ነገር እስከምታውቅ አትጠብቅ፡፡ በምታውቀው ልክ ስራን ጀምር፡፡ በምታውቀው እውቀት መጠን ስራን ስትጀምር፣ ያንን ከመጀመርህ በፊት ያልነበረህ ልምድና እውቀት ወደ አንተ ይመጣል፡፡

ሁሉም ሰው እስኪቀበልህ አትጠብቅ፡፡ የሚቀበሉህ ላይ በማተኮር ተሰማራ፡፡ በሚቀበሉህ ላይ ስታተኩርና ደስተኛ ስትሆን፣ ቀድሞ የማይቀበሉህ ሁሉ አንተን ከመቀበል ውጪ ምርጫ አይኖራቸውም፡፡

የጠየከው ነገር ሙሉ በሙሉ እስኪሰጥህ አትጠብቅ፡፡ የተሰጠህን ተቀበልና በዚያ በመጀመር የምትችለውን አድርግ፡፡ በተሰጠህ በጥቂቱ የምታደርገው ጥረትና የምታከናውነው ነገር የቀረው እንዲለቀቅልህ መንገድ መክፈቱ አይቀርም፡፡

አትቀመጥ! የታየህን ያህል ተንቀሳቀስ!

@fikrhn
@fikrhn
@fikrhn
🚶🚶🌹📚🏃🏃


" የምትናገሩት ከሀሳቦቻችሁ ጋር ሰላም መፍጠር ሲያቅታችሁ ነው ። በልባችሁ ውስጥ ባለው ጭር ያለ ስፍራ መኖር ሳትችሉ ስትቀሩ፣ በከናፍሮቻችሁ ውስጥ ትኖራላችሁ
ንግግርም አቅጣጫን የሚያዛንፍ ጊዜ ማሳለፊያ እና መደሰቻ ነው ...እናም በአብዛኛው ንግግራችሁ(ወሬያችሁ) ውስጥ የማሰብ ችሎታችሁ በከፊል ይሞታል ። ሃሳብስ በህዋ ላይ እንደምትበር ወፍ አይደለምን ?
በፍርግርግ ብረት በተሰራ የቃላት መረብ ውስጥ ከተዘጋባትስ ክንፎቿን ትዘረጋ እንደሆን እንጂ ልትበር ትችላለችን...?
በእናንተ መካከል ለብቻቸው መሆንን በመፍራት ወሬኞችን የሚፈልጉ አሉ ። ምክንያቱም የብቸኝነት ፀጥታ ለአይኖቻቸው እርቃኑን የቀረውን ራሳቸውን አጋልጦ ያሳያቸዋልና ሁሌ ከእሱ ለመሸሽ ይፈልጋሉ...ደግሞም ሳያውቁት ወይም ቀደም ብለው ሳያስቡበት የሚያወሩ እና በዚህ ንግግራቸው ራሳቸው እንኳን የማያውቁትን እውነት ገልጠው የሚያሳዩም አሉ...
በውስጣቸው እውነትን የያዙ ፣ ነገር ግን በቃላት የማይናገሩትም አሉ ። እንደዚህ ባሉት ሰዎች ልብ ውስጥ የእውነት መንፈስ ዜማ በሚደረድር ትርታዊ ፀጥታ ውስጥ ይኖራል...
ጓደኞቻችሁን በመንገድ ዳር ወይም በገበያ ቦታ ስታገኙዋቸው በውስጣችሁ ያለው መንፈስ ፣ ከናፍራችሁን ያንቀሳቅስ ፤ ምላሳችሁንም ይምራ ። የጽምፆቻችሁ ድምፅም ለጆሮዋቸው ጆሮ ይናገር..የወይንን ጣዕም ሁሌ እንደሚያስታውስ ሁሉ ፣ የጓደኞቻችሁ ነፍስ የልባችሁን እውነት ጠብቆ ያቆያል አይደለምን? ቀለሙ(ጣዕሙ) በተረሳ ጊዜ ግን ዕቃውም አይታወስም ። "

ካህሊል ጂብራን -
••●◉Join us share◉●••

@fikrhn
@fikrhn
@fikrhn
🌿#Morning_Motivation

ፅናት!

"በዓለም ላይ የፅናትን ቦታ የሚተካ ምንም ነገር የለም። ብቃትም አይደለም። እንደውም ብቃት ያላቸው ስኬታማ እንዳልሆኑ ብዙ ቁጥር ያለው የለም። የረቀቀ ዕውቀትም አይደለም እንደውም ሰዎች እንደማወቃቸው ስኬታማ አለመሆናቸው ቢታይ አስገራሚ ትዕይንት ነው። መማርም አይደለም። ዓለማችን በተማሩና በማይሰሩ ሰዎች የተሞላች ናት። ጽናትና ቁርጠኝነት ግን ሁሉንም ነገሮች ናቸው። የአላማ ፅናት ያላቸው ሰዎች ከየትኛውም ቦታ ተነስተው ያሰቡት ቦታ ለመድረስ ሊያቆማቸው የሚችል ምንም ነገር የለም።" -ካልቬን ኮሌጅ

"እያንዳንዱ ታላላቅ የስኬት ታሪክ የትልልቅ ውድቀቶች ውጤት ነው ። ልዩነቱ ተሸናፊዎች በወደቁበት ተኝተው ሲቀሩ አሸናፊዎች ግን ከያንዳንዱ ውድቀታቸው በኀላ ዳግመኛ በታላቅ ብርታት መነሳተቸው ነው" -ፊዮዶር ዶስቶቭስኪ

መልካም ቀን!
════❥━━━❥═════
@fikrhn
@fikrhn
@fikrhn
🌿#ግራ_የሚያጋባ_ግን_እውነት_የሆነ_አንድ_ታሪክ_ልንገርህ

ታላቁ አስማተኛ (Magician) ሃሪ ሁዲኒ፤ በሆነ ወቅት ላይ ከየትኛውም እስርቤት ማምለጥ እንደሚችል ምሎ ተናገረ። ማድረግ የሚጠበቅበትም ሱፉን እንደለበሰ መታሰርና በአንድ ሰዓት ውስጥ ያለምንም ችግር ከእስርቤት ማምለጥ ብቻ ነው።

እናም ብዙ አመታትን ያስቆጠረ አንድ በምዕራብ የሚገኝ እስርቤት የሁዲኒን ጥያቄ ተቀበለ። ሁዲኒ በሚታሰርበት እለት ሰዎች መጨረሻውን ለማየት በእስርቤቱ ቅጥር ማዶ ተሰበሰቡ። ሁዲኒ በራስ በመተማመን ስሜት እንደተሞላ ወደ እስር ቤቱ ገባ። የእስር ቤት ጠባቂዎችም በብረት በር በተዘጋ ክፍል ውስጥ አስቀመጡት።

ሁዲኒ ኮቶን አወለቀ። ቀበቶውንም ፈታ።

በሁዲኒ ቀበቶ ውስጥ የተሸሸገ፤ እንደ ሽቦ የሚተጣጠፍ እና ሃያ ሳንቲ ሜትር የሚሆን ብረት ነበር። ሁዲኒ ስራውን ጀመረ።

ለሰላሳ ደቂቃዎች ያህል በሩን በያዘው ብረት ለመክፈት ታገለ። ይዞት የመጣው በራስ መተማመን አሁን ላይ ከእርሱ የለም።

አንድ ሰዓት ሆነው። በላብ ተጠምቋል …

ሁለት ሰዓታትን ከበሩ የቁልፍ ሽንቁር ጋር ሲታገል አሳለፈ። ደከመው … ሁዲኒ በተሸናፊነት ስሜት ጭንቅላቱን በበሩ ላይ አስደገፈው… በሩ በቀስታ ወደ ውጪ ተገፋ… ተከፈተ። ይህ በር በጭራሽ አልተቆለፈም።

ሆኖም በአንድ ሰው አእምሮ ውስጥ ይህ በር ተቆልፎ ነበር። በሁዲኒ ጭንቅላት ውስጥ ከአለም ካሉ ሁሉ ጋኖች በሚበረታ ጋን ተቆልፏል። ማንም ቁልፍ ሰሪ እንደዚህ አይነት ጠንካራ ቁልፍ አልሰራም።

አእምሮ ሃይል አለው! ምን ያህል በሮችን በራስህ ላይ ቆልፈሃል?

ምን ያህል ጊዜስ ራስህ በሰራኸው የአእምሮ እስርቤት ታስረሃል?

በቀላሉ የሚፈቱ ግን አንተ በራስህ ላይ ያወሳሰብካቸው ምን ያህል ችግሮች አሉብህ?

አንድ የአፍሪካውያን አባባል አለ

"በውስጥህ ጠላት ከሌለ፤ ከውጭ የሚመጣ ጠላት አንተን መጉዳት አይችልም።"

በአለም ሁሉ ካሉ ውሸታሞች በላይ የአንተ አእምሮ አንተን ይዋሽሃል። ይህን ማድረግ አትችልም… እንዲህ መሆን አትችልም… አቅሙም ብቃቱም የለህም…

ምክንያቱም ልክ እንደ ሁዲኒ የተቆለፈውን በር ብቻ ነው የሚያሳየን። ከፍተህ ውጣ… አእምሮህ የሚልህን አትመነው።

@fikrhn
@fikrhn
@fikrhn
...🌸🌸🌼

.....ራስህን ለሚመጡት አሳልፈህ አትስጥ ለሚሄዱትም አብዝተህ አትጨነቅ ነገር ግን በሁለቱ መሃል ሚዛናዊ ሁኖ መኖርን ልመድ

@fikrhn
@fikrhn
🪨🪨🍁


.....ሁሌም ዝግጁ ሁነህ ጠብቃት ህይወት ብዙ ታስተምርሃለች።እስከዛሬ የኖራችሁበትን ያለፉ አመታትን አስቡ.......... በቅጽበት አእምሮአቹ የኋሊት ይገሰግስና ጥሩውንም መጥፎውንም ጊዜያት ያሳያችኋል።
መምረጥም መማርም ትችላላችሁ መልሱን በልባችሁ ሙሉት

ሁሌም ቢሆን ጥሩ ሰው ከመሆን እንዳትቆጠቡ

@fikrhn
@fikrhn
እኔና አንቺ pinned «🌿#ግራ_የሚያጋባ_ግን_እውነት_የሆነ_አንድ_ታሪክ_ልንገርህ። ታላቁ አስማተኛ (Magician) ሃሪ ሁዲኒ፤ በሆነ ወቅት ላይ ከየትኛውም እስርቤት ማምለጥ እንደሚችል ምሎ ተናገረ። ማድረግ የሚጠበቅበትም ሱፉን እንደለበሰ መታሰርና በአንድ ሰዓት ውስጥ ያለምንም ችግር ከእስርቤት ማምለጥ ብቻ ነው። እናም ብዙ አመታትን ያስቆጠረ አንድ በምዕራብ የሚገኝ እስርቤት የሁዲኒን ጥያቄ ተቀበለ። ሁዲኒ በሚታሰርበት…»
Forwarded from እኔና አንቺ (🎸🇯 $€6ɐʇ€W Brìght)
♥️ የናፈቅሽኝ እለት 📝

💌💌🌹💌💌


ንፍቅ ያልሽኝ እለት
ትገኛለሽ ብዬ…
በፍለጋ ጉዞ ምድርን አካልዬ፤
ስማስን በዱሩ፣
ሳስስ በባህሩ…በሜዳ ገደሉ
ሲመሽ እየነጋ ሲነጋ ቢመሽም
ያለሽበት የለም አንቺ አልተገኘሽም!
አየሽ…

እንደ ዘንዶ ስሳብ… እንደጥንቸል ስዘል… እንደ አሞራ ስበር
👨‍❤️‍💋‍👨ልቤ ውስጥ እንዳለሽ ልብ አላልኩም ነበር።

🌹🌹 🌹🌹🌹🌹🌹
Join👇👇
@fikrhn
@fikrhn
("#ካልተኖረው ጸጋ" ላይ የተወሰደ)

'ተሰጥቶን ያልኖርነው ብዙ በረከት አለ::'

ከዚያ ሁሉ በረዶ ከተከናነበው አመታት በኋላ ስላገኘዋት ደስታ ቢጤ ውስጤን ተሰምቶታል።እርግጥ አዎ እወዳት ነበር ነገር ግን በኔ አለመኖርና በሷ ጊዜያዊ ፍላጎት ያለ ምርጫዬ ሸንጎ ተቀምጬ ነበር የፍርድ ቅጣቴን ፍቅርና ናፍቆቴ ሳይቆጠሩ ንጹህነቴን ለትዝታና ጥላቻ ሰጥታ የተለየችኝ.....ለካስ ይመስለናል እንጂ የራቀብን ሁሉ ቅርብ ነው።ህይወትንም በአግባቡ ካልኖርናት ታሪክና የትዝታ አካል ለመሆን ጥድፊያዋ ሃያል ነው።

"እባክሽ ሰሊ ጊዜ ካለሽ ያቺ የምትወጃትን ነጭማ ማኪያቶ ልጋብዝሽና ተቀምጠን እናውራ ? "መቼም አሁን ድረስ እንደማትረሻት እምነቴ ነው።
"እሺ"አለች ዙርያዋን ቃኘት ቃኘት አደረገችና
"ምነው ሰላም አይደለም:?"
"አረ ሰላም ነው::" ባለቤቴ ከአዳም ዘር ጋር ቆሜ ሊያየኝ ስለማይፈልግ ነው።
"ኢሄን ያህል"
' አዎ አለች'.... ግንኮ ጥሩ ጥሩ የስራና እንደዚህም የድሮ ጓደኞች ይኖርሻል።
"አዎ ይኖረኛል" እሱ ግን እንደዛ አይደለም።በቃ እንግድያውስ በጣም ስለሚወድሽ ይሆናል።ብዙዎቻችን በጣም የምንሳሳለትን ነገር የማጣት ፍርሃታችን ነው እንደዛ አይነት ስሜትን የሚፈጥርብን

ታዲያ
ግን ያ የምታስቢውን አይነት ሰው ነው ያገባሽው? አለ አይደል ቁመቱ መለሎ የሆነ ደረቱ ሰፊ አለባበሱ የሚማርክ የሚንከባከብሽ የራሱ የሆነ በቂ ሀብት ያለው ትዝ ይልሻል በፊት እንደዚህ ነበር የምትፈልጊው።

በሃሳቧ እሩቅ ነጎደች።በትዝታ ማእበል ውስጥ በዝምታ ለደቂቃዎች ተናወጠች።ገጽታዋ አንድ ጊዜ ሀዘን አንድ ጊዜ ደግሞ ደስታ ይላበሳል።ላነቃት አልፈለኩም።ከቆይታዎች በኋላ ፈገግ አለች እቺን ፈገግታ በደንብ አውቃታለው
የስብራት ፈገግታ....🥲

አብ ዛሬ ከምኖረው ህይወት ይልቅ ትናንት ያሳለፍኩት ያ ጊዜ ነው የሚያኖረኝ።
ምንም ነገርን እንደጠበኩት ሁኖ አላገኘውትም
ቆንጆ ሀብታም ገንዘብ ያለው ባል ምናምን ምናምን ውሸት ነው።ማንም ሁሉን የታደለ የለም ዘግይቶም ቢሆን የሚገባህ ነገር ያ ነው።በትዳር ውስጥ ከዲናር ብልጭልጭ ነገር በላይ ጊዜና ፍቅር ለሰው ልጅ ምን ያህል ዋጋቸው ትልቅ እንደሆነ ተረድቻለው።እርግጥ ባለቤቴ ገንዘብ አለው ለኔ ግን ምንምና ተራ ነው።

በጭራሽ መልክ ቁንጅና ገንዘብ ምናምን ለኑሮህ ዋስትና አይሆኑም።ምንም ሳይጎድልብህ ለብሰህ በልተህ ሆድህ ቢሞላ ልብና አዕምሮህ ከተራቡ ግን ሁሉም ነገር ባዶና ወና ነው።

"እሺ ሰሊ በኑረትሽ ደስተኛ አይደለሽም?"

አንዲት ሴት ልጅ አለችኝ።በሷ ደስተኛ ነኝ አለች ጣር በሚመስል ንግግር ለሷ ስል ነው የምኖረው ምክንያቴም እሷ ናት።ከአለመኖር የምታነቃኝና ሁሉን የምረሳባት አለሜ ናት

"ሰሊ ተጎድታለች" በፍጹም ጭንቅላቷ ተቀይሯል በስላለች ነገሮችን በደንብ ተረድታለች አስገረመችኝ ህይወት በትክክል ገብታታለች

" #መቅደም_ያልነበረበትን_አንዱን_ፍለጋ_ ሄጄ_ነው_መቅደም_የነበረበት_ሌላውን_ ያጣውት" አለች 😞

ለሱ ፍቅር ከሌለሽ ለምን አትፈቺውም አልኳት
ልጄ ለሱ ፍቅር አላታ እንዴት አድርጌ... ያለ እሷ መኖር ከባድ ነው
አንዳንድ ጊዜ እናትነት የሚያስተምርህ ነገር አለ።ምን መሰለህ ምንም ቢሆን ውስጥህ ከራስህ ደስታ ይልቅ ለልጆችህ ቅድምያ እንድትሰጥ ያዝሃል።ይህ ደግሞ ተፈጥሮ ነው አብ...😢

....Jol...F
ድቅድቅ አለም......

የኔማ ይህ ነበር ሀሳቤ ይህ ነው ፍላጎቴ
ስውር እውነታዬን ገሃድ ምስልነቴ
በውስጤ የታፈነው ንዳዱ ክስለቴ የጋመው ስሜቴ

በእኔነት ሚዛኔ እልፍ አመት ያሰርኩት
በምናልባት አለም ቅዥቴን የኖርኩት
እኔ ነኝ ፍርደኛህ
የት አባቱስና ተፈጥሮ ጠፍንጎኝ ቃላቴን ሸሽጎ
በክንዶችህ እቅፍ ከልብህ መሽጎ
እጦት ገላዬን ገርፎት ፍጹም ካለኔ እያደረ
ወዳንተ ጠፍቶ እየመጣ ወዳንተ እየሰደረ

ምናኔዬ እንደ ሸማ በውብ ጥለት ተጠላላልፎ
የገልነት የፍርሃቴ የተሰዋው ቀኔ አልፎ
ዝማም ነው ዛሬማ መኖርን ውሉን ቸረኝ
ይህ ነው የኔ አለም ላንተው የሚያኖረኝ

............Jo
" ልጽፍልሽ ነበር...."

ያቀናሁት እጄን የገዛ እንባዬ ዘንቦ እየገረፈው
እንደምን በርትቼ ከወረቀቱ ላይ ስምሽን ልጻፈው

የለኮስኩት ኩራዝ ጨልሞ እስኪፈዝ አቅም እነስኪነሳው
በምን ልቋጨው ነው አንቺን በመናፈቅ ብእር የማነሳው

ልጽፍልሽ ነበር.....

አልተሳካም እንጂ ቢሳካልኝና ፊደል ቢታዘዘኝ
እንዴት ያለ ናፍቆት እንዴት ያለ ፍቅር ካንቺ እንደያዘኝ

ልነግርሽ አስቤ ሰርዤ ደልዤ ይህንን ስላልኩኝ
የጻፍኩትን ሳይሆን አንብቢው ብዬ ነው ልጽፍ እንዳሰብኩኝ::
(" #ያልተኖረው_ጸጋ" )

እውነት መኖር ግን ምንድነው?
በዝግታ ጉዞዬን ወደ ኮረብታው አደረኩት የልብን ብቻ ሳይሆን የጉልበትንም ጥንካሬና መዛል ማየትን መርጫለው እሱስ እንደ ልቤ አንድ ክፉ ቀን ሲመጣ ትቶኝ እንደማይቀር ምን አውቃለው።እርግጥ አዎ..... የመኖርን ፍልስፍና ይበልጥ የጀመርኩት አዕምሮዬ በማጣት ስሜት ውስጥ በዋዠቀበት ጊዜ ነበር።የኮረብታውን ላይ ጸጥታ ተላምጄዋለው ሰላም ይሰጠኛል። ያቺ ቀን ናት ድንገት ትውስታዬ ሁና የቀረችውና አቅሜን ያጣሁባት።

የማይፈታልኝን የህይወት ቋጠሮ እንደ እንዝርት አሹራ የተበተበችብኝ። ለምን ግን ዳግም የማንኖራቸውና ያለቁ ታሪኮች ዘወትር በልባችን ይጻፋሉ ለምንስ ሰርክ ከአምሮአችን ያለፉ ማህደሮች ከተቀመጡበት ስፍራ ይነካካሉ። ደግመው ላይመጡ ተስፋቸው መንኖ ሂዷል ከእውነትም ርቀው እውነት ሁነዋል ለልብ ህይወት ብቻ ሳይሆን የመኖር ሞትንም ሰብከዋል ። ስለማግኘት ብዙ ለፍፈው ስለ ማጣት ጥቂት ጽፈውም ሸውደውናል ብዙ ጊዜ እንዳምን ከሆንኩኝ በኋላ ተክጃለው ድንገት በእውን እየኖርኩኝ ከከረምኩበት አለምም ቅዠት ነው ተብዬ ስባረር ተስፈንጥሬ ገስግሻለው።

መባረር ብርቄ መስሏታል ገና የስድስተኛ ክፍል ተማሪ እያለው ነበር በአደራ ከተሰጠውበት ቤት የተገፋውት ከዛም ጎዳናን የተዋወቅኩትና በቀሪ ብዛት ከት/ት ቤት ተባርሬ ትምህርቴን አቁሜ ህይወትን በመንገድ ዳር ላይ የጀመርኳት 'አዲሴ መስሏታል።' ማጣትን በምወዳቸው ሰዎች በክፋት ነው መነጠቅ የጀመርኩት ተሼን(ዶክተርንም) ያጣሁት እንዲሁ ድንገት ነበር።

የዛን እለት የቀን ውሎአችንን ለማሳመር በጠዋት ማልጄ ነው የተነሳውት እነ Dr እነ ሳምሶን እነ ጸዲ ሁሉም ተኝተዋል።ወደዚ ወደዛ ብልም ግን ከአንድ ሰው ቁርስ ውጪ መዝለል የማትችል ገንዘብ በቀር ላገኝ አልቻልኩም።መከራ ለኛ አዲስ ስላልሆነ ምንም ቢገጥመን ስቀን ነው የምናሳልፈው
ወደ ቤት ስመለስ ተሼ ተኝቷል በእጄ ቀሰቀስኩት።ዛሬ ተሸንፈሃል እንደዚህ ተኝተህ አታውቅምኮ ጀምበሯ ራሱ ተቀይማሃለች ተነስ እንጂ
"ዝም...."
አረ ምንሼ ዶክ ቀና በል እንጂ ቁርስ
"ዝም..."
ከላዩ ላይ ያለውን ላስቲክ ሳነሳው በአፉ ደም ደፍቋል ሰውነቱ ይቀዘቅዛል።ጸዲ!!!. ጸዲ!!!....ወይኔ ብጮው ባብድ ባለቅስ ምን ሊፈይድ እሱ ለዘላለም አሸልቧል 😢
በዚያች እለት ተሼን አጣውት
የመኖሬ አቅጣጫም ወደ ገሃነም የተወረወረው ያኔ ነበር።መኖር ቃል ብቻ ሆነ ለወራት አስጠሊታ ጊዜን አሳለፍኩኝህመሙ ግን አለቅ አለኝ
"ተሼ ማለት በእውነተኛ እናትና አባት አምሳል የተሰበጠረ መልካም ሰው ነው።ያለንን ያን አስቀያሚ የህወት ጉዞ ለመለወጥ ት/ቴን ያስቀጠለኝ ፣ጥንካሬን አብሮት የተለደው እስኪመስል ድረስ በነገው ላይ ተስፋው የገነነ በእኛም ላይ ያሰረጸ ፊደልን ከ ሀ 'ለ' ሐ'መ ና 'ሠ ውጪ የማይቆጥር ነገር ግን እሳቤውና ሰብአዊነቱ ከልሂቃን የተስተካከለ ነበር እሱ የመጪው ብርሃናችን ነው። መነጠቅን የተለማመድኩት ከነፍሴ ከተቆራኙት ሰዎች ጀምሬ ነው

ታዲያ ትናንትናዬን አምኖ መቀበል የከበዳት፣ ያሳለፍኩት ህይወት ውስጥ በሰበብ መኖር የቀለላት እኔነቴን ስታውቀውና ሳልደብቅ ስነግራት በግልጽነቴ ልታከብረኝ ሲገባት በእውነቴ የተጸየፈችኝ እንስት እንለያይ ስትለኝ
ሳቅ አልኩላትና
" እሺ አልኳት" አዲሴ መስሏታል።

.....Jo
እኔና አንቺ pinned «⌚️♥️⌚️🕙🕙🕙🕓 ኒውዮርክ ከካሊፎርኒያ በ3 ሰዓት ትቀድማለች ነገር ግን ይህ ካሊፎርኒያን ቀርፋፋ አያደርጋትም።ም/ክ የራሷ የሆነ ጊዜና ሰአት አላትና አንዳንድ ሰው በ22አመቱ ይመረቅና ስራ ለመያዝ አምስት አመት ይፈጅበታል ሌላው በ25 አመቱ የድርጅት ሀላፊ ሆኖ በ50 አመቱ ሲሞት ሌላው በ50 አመቱ ሃላፊ ሁኖ እስከ 90 አመት ይኖራል። ኦባማ በ55 አመቱ ፕሬዝዳንትነቱን ጨረሰ ነገር ግን ትራምፕ በ70አመቱ…»
#እኔና_አንቺ

አባት የመጀመርያም የመጨረሻም የሆነ ብቸኛ ልጁን ሊድር ድል ያለ ሰርግ ደግሶ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆቹን ጠርቶ የምሳ ግብዣውን እየተዟዟረ ይመለከታል።

‹‹ማን ቀረ ማን መጣ›› የሚለውን በትኩረት እየተመለከተ ሳለ የቅርብ የግድግዳ ጎረቤቱን ከእይታው ያጣዋል። ግራ በመጋባት እየተዟዟረ ቢመለከትም ጎረቤቱንም ሆነ የጎረቤቱን ልጆች ሊያይ አልቻለም።

‹‹የልብ ወዳጄ በዛሬ ቀን እንዴት ከጎኔ ይጠፋል›› እያለ በንዴት ስሜት በመብሰልሰል ላይ ሳለ ድንገት የጎረቤቱ ልጅ ብቅ አለ ና በፍጥነት ትንሽ ምግብ ቀማምሶ ትቶ ወጣ።

ይህን ትዕይንት የተመለከተው ደጋሽ በንዴት ተብከነከነ። የአባቱ በደስታው ግዜ አለመገኘት ሳያንሰው ልጁ መጥቶ በምግቡ አላግጦ መውጣቱ አበሳጨው።

በዚህ መሀል የሙሽራው አጃቢዎች ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት ጉዞ ሊጀምሩ መኪናቸውን ማንቀሳቀስ ሲጀምሩ ምግቡን ቀማምሶ በፍጥነት የወጣው የጎረቤቱ ልጅ ሙሽራውን ለማጀብ ከግቢ መኪናውን ይዞ ይወጣል።

አባት ተበሳጨ፣ ንዴቱን መቆጣጠር ቢያቅተው በቁጣ መንፈስ ተሞልቶ ወደ ጎረቤቱ ልጅ በመሄድ፦‹‹አባትህ ጎረቤቴ ሁኖ ደስታዬ ላይ አልተገኘም፣ ታላላቅ ወንድሞችህም እንደዝያው፤:ታድያ አንተ ምን አስበህ ነው በምግብ አላግጠህ ትተህ የወጣኸው? አሁን ተመለስ ያንተን አጃቢነት አንፈልግም›› ብሎ መለሰው። ልጁም እቤቱ ገባ፤ ሰርገኛዎችም ሙሽራውን ይዘው ወደ ሙሽሪት ቤት አቀኑ።

በመጨረሻም አጃቢዎች ሙሽሮችን ይዘው ወደ ቤት በመግባት የደስታቸው ተካፋይ ከሆኑ በኋላ ቀኑ ሲጨልም ሁሉም ተበታትኖ ሰርግ ቤቱ በሙሽሪት እና በሙሽራው ጭር አለ።

አባት አሁንም በጎረቤቶቹ ንዴት እየተብሰለሰለ ነው። ድንገት ከመሸ ያለ ወትሮው የጎረቤቱ ጊቢ ተከፈተ። የሙሽራው አባት እየተመለከተ ነው።

የጎረቤቱ ልጆች በትከሻቸው አስክሬን ተሸክመው ከቤታቸው ሲወጡም ተመለከተ። ፍፁም ዝግታ እና እርጋታም በሚስተዋልበት እርምጃ ልጆቹም ይራመዱ ጀመር።

የሙሽራው አባት ጠጋ አለ። ፦‹‹ምንድነው? የማንን አስክሬን ነው የተሸከማችሁት ›› ሲልም ጠየቃቸው።

‹‹አባታችን ጠዋት ሙቶ ነው፤ ሲሞትም በሱ ለቅሶ ምክንያት ያንተ ደስታ እንዳይጓደል መሞቱን ከሰርግህ በፊት ለማንም እንዳንናገር እና ድምፅ አውጥተን እንዳናለቅስ ተናዞልን ነበር። ለዝያ ነው ድግሱ ላይ መገኘት ያልቻልነው። ›› በማለት ጀናዛ የተሸከሙ ልጆች ጉዳያቸውን አስረዱ።

ደጋሽ ተፀፀተ፦‹‹ እኔ በሱ ቦታ ብሆን ይህን የማድረግ አቅም አይኖረኝም ነበር›› ሲልም የፀፀት እንባ ያነባ ጀመር።

በህይወታችን ችላ ያሉ እየመሰሉ በቁስላቸው ደስታችንን ላለማበላሸት ሲሉ ከአከባቢያችን የሚርቁ ሰዎችን አምላክ ይዘንላቸው።

@fikrhn
@fikrhn
@fikrhn
2025/03/30 02:36:08
Back to Top
HTML Embed Code: