😩😩😅
ጉዞ ከፒያሳ ወደ መካኒሳ
" ኧረ እባካችሁ ያልተዘጋ የጠጅ ጀሪካን ካለ ዝጉ! አግማማችሁን "......የ5 ቁጥር አንባሳ ባስ ቲኬት ቆራጭ!
" እኔን ነውኮ! " አለኝ አንድ በጠጅ ፊቱ እስኪመሽ የሰከረ ሞልፋጣ!
" እማማ መቼ የሚነጠር ቅቤ ነው? " ይላል ሰካራሙ የጸጉር ቅቤያቸውን በተመስጦ እያሸተተ።
" አምቡሌያም! " አሉ እማማ።
" ግፉ ግፉ ግፉ "
" ማንን ነው ? "
" በሩ አልዘጋ ብሎ ነው።"
ሾፌሩ ወርዶ መጨረሻ የመጣሁት እኔ ስለነበርኩ መቀመጫዬን ይዞ ወደ ዉስጥ ይገፋኛል። አፈርኩ፡..ሆ!
" መሃሉ ባዶ ነው ጠጋ ጠጋ በሉ ! "
" ተባበሩ! " ትላለች ትኬት ቆራጯ
" ይሄ ሰዉዬ መቀመጫዬን እንደ ፓፓዬ ታቅፎ መቅረቱ ነዉንዴ?! "....... መናደድ ጀመርኩ።
በመጨረሻም በሩ " ችስስስስ " ብሎ ተዘጋ!
ነጭ ሽንኩርት፣ ጠጅ፣ ጫማ፣ ብብት፣ ቅቤ፣ ለውዝ፣ቅመሞች...በቀጥታ ስርጭት ከ 5 ቁጥር የሚተላለፉልኝ ጠረኖች ናቸው መቼስ ! የቅድሙ ሰካራም ( የሞላው ጀሪካን ) ፍዝዝ ብሎ እያየኝ
" ሊጣላኝ ነው አቡ! አቡ...አቢ.....ቲ! "
አደራሽን ማርያም! አልኩ በሆዴ። እላዬ ላይ ከልብሶት የጋራዥ በር መስዬ እንዳልቀር በአዛኝቷ!
ከፊቴ ከኋላዬ ከጎንና ጎኔ በወፋፍራም ሰዎች ተጣብቄ ቀረሁላችሁ። እንደዛን ቀን ቀጥ ብዬ ቆሜ አላውቅም!
" ፍሬንድ "
" አቤት "
" ሶፍት አለሽ? "
" ምነው? "
" ምንም!........ ላቤ አይኔ ውስጥ ሊገባ ነው "
" እና? " ኮስተር ብሎ
" እጄን ማንቀሳቀስ አልቻልኩም፡ ጥረጊልኝ!?
ላቤ ቀጥ ብሎ ይወርዳል። እጆቼ ቢንቀሳቀሱ መጀመሪያ የሚነኩት አጠገቤ ያሉትን አዛውንት ሙሃሂት ይሆናል!
ሜክሲኮ ስንደርስ፡ ጅራፍ ምላሷ፡
" ጠጋ ጠጋ በሉ! መሃሉ ባዶ ነው ".... ኧረ በወለላይቱ!
በሩ ሲከፈት ወደበሩ ተንሸራትቼ በሩ ስር ሽጉጥ ብዬ ቀረሁ.....እንደ ስሙኒ ቂጣ!
በሩ ሲዘጋ ፊቴ በበሩ መስታወት ተጣብቆ ቁጭ!
ከላዬ ላይ ህዝቤን ከነድውለቱ ተሸክሜ ጉዞ ወደ መካኒሳ !........ባፋንኩሉ!
የተረሳ ነገር! ግራ እግሬስ? ከረገጥኩበት ወደ 15 ደቂቆች አለፉኝ! እግርም ይናፍቃል?
" አንዴ ልርገጥ? "
" ማንን? " አለኝ አንድ ጠማማ! ( ቲሸርቱ ላይ በ 97 ምርጫ የተስጠውን የቅንጅት ጣት የታተመበት ቲሽርት የለበስ ስውዬ....አሄሄ! )
" አይደለምኮ ግራ እግሬ አየር ላይ........"
አንዱ አቋረጠኝ
" ተመስገን በል! " አለኝ እንደ ህዋ ጠፈርተኛ አየር ላይ ተንሳፎ!
ፊቴ ከመስታወቱ ጋር ከመጣበቁ የተነሳ ከውጪ ለሚመለከተኝ ሁሉ የማሳዝን ፍጡር መሰልኩ። የሆነ ፌርማታ ስንደርስ ከዉጪ ክላስ ሜቴን ትራንስፖርት ሲጠብቅ ተያየን!
ሊለየኝ አልቻለም! እጆቼ ስለማይነቃነቁ በአይኖቼ ስቅበዘበዝ አየኝና አማተበ!.....ምናባቱ ሆነ?
በኋላ እንደነገረኝ ሌላ ፍጡር መስየው ነው። የምሬን ነው።
" ወርዳችሁ አስወርዱኝ! " አለ አንዱ በንዋይ ደበበ ድምጽ።...... ኤጭ!! እንደገና ልንፈርስ ነው!
" በታክሲ ተመለስ! "....
" ዋ ዛሬ! "
ወረድን። ሰውየው ሰው ላይ እየዋኘ ወረደ። አዳዲስ ሰዎች ገቡ! በምን ልግባ?.........
" ሹፌር አንዴ አቁም....አቁም......ኧረ ልግባ..........ሃሎ!...ጥሎኝ እልም
አፈር ያስበላህ አቦ! "
እናላችሁ ጥላ ጥላውን ሄጄ እቤቴ አሁን ደረስኩ እላችኋለው
#ምንጭ
(የነቋሪዉ መጣጥፎች እና ሌሎችም ወጎች)
@fikrhn

#ርዕስ _የለውም..
ከፈረሰው ድንኳን ደርሶ ከሰፈሬ፣
ንገረን ይሉኛል የጻፍከውን ዛሬ፣
የት ነው.... ቤትህ አሉኝ እኔ ቤት የለኝም፣
ነፍሴ ከሷ አድራ ከቤቴ ብመጣ መኖር አያሰኝም፤
ስለዚህ እኔ ቤት የለኝም።
ዛሬምኮ አየዋት ከቤቷ ስትወጣ፤እጅጉን አምራለች
በፍቅር መስፈርቴ ጸሃይ ጨለማ ናት እሷ ታበራለች
ፀጉሯም ጥሩ ነው ሙሉ ተውባለች
የእርግብ ላባ ይመስል ገላዋ ለስልሷል
ድንገት ጎንበስ ብዬ ራሴን ስመለከት
አብርያት ለመሆን በአለም ሚዛን አንሷል
የጎፈረው ጺሜ አለቅጥ ያደገው ጨብራራው ፀጉሬ
እድሜ ያጠገበው በሸፋፋ ጫማ የተጫማው እግሬ
ከመሬት ተመስሏል ቆሜበት ከስሬ
ቅጡ እማይታወቅ ዝብርቅርቁ ልብሴ
ከርካሳው ስጋዬ ጊዜ ያስረጃት ነፍሴ
ድምራቸው ባዶ ብዜታቸው ዜሮ
የመጣ ውጤቱ
ከውሸት የታረቁ ከእውነት የተፋቱ
ይህ ነው ጊዜ ደጉ ይህ ነው ቁስ ክፋቱ።
✍.... #ያልሄደው
@fikrhn
@fikrhn
@fikrhn
ከፈረሰው ድንኳን ደርሶ ከሰፈሬ፣
ንገረን ይሉኛል የጻፍከውን ዛሬ፣
የት ነው.... ቤትህ አሉኝ እኔ ቤት የለኝም፣
ነፍሴ ከሷ አድራ ከቤቴ ብመጣ መኖር አያሰኝም፤
ስለዚህ እኔ ቤት የለኝም።
ዛሬምኮ አየዋት ከቤቷ ስትወጣ፤እጅጉን አምራለች
በፍቅር መስፈርቴ ጸሃይ ጨለማ ናት እሷ ታበራለች
ፀጉሯም ጥሩ ነው ሙሉ ተውባለች
የእርግብ ላባ ይመስል ገላዋ ለስልሷል
ድንገት ጎንበስ ብዬ ራሴን ስመለከት
አብርያት ለመሆን በአለም ሚዛን አንሷል
የጎፈረው ጺሜ አለቅጥ ያደገው ጨብራራው ፀጉሬ
እድሜ ያጠገበው በሸፋፋ ጫማ የተጫማው እግሬ
ከመሬት ተመስሏል ቆሜበት ከስሬ
ቅጡ እማይታወቅ ዝብርቅርቁ ልብሴ
ከርካሳው ስጋዬ ጊዜ ያስረጃት ነፍሴ
ድምራቸው ባዶ ብዜታቸው ዜሮ
የመጣ ውጤቱ
ከውሸት የታረቁ ከእውነት የተፋቱ
ይህ ነው ጊዜ ደጉ ይህ ነው ቁስ ክፋቱ።
✍.... #ያልሄደው
@fikrhn
@fikrhn
@fikrhn
#መልስ_ጥያቄ_ይሆናል:: 🤔
አንቺ ያልወደድሽውን ነገር ሁሉ መተው ጀምርያለው፣ ስትሳሺልኝኮ ምን እንደማደርግልሽ እየጠፋብኝ ነው.... የምጠላቸውን ሁሉ መውደዴ አስገረመኝ..... ምናልባት ኢሄ ሌላ አለም ይሆን አንዴ....?
ምናልባት ይገባኝ ይሆን እንዴ....?

የተጀመረውን ማስቀጠል....
》ከፍቅር አጋርህ ጋር ያለህ ቅርርብ መልካም እንዲሆን እነዚህን የፍቅር መንገዶች ተጠቀም!!
1: እንድትለወጥ በምትነግራት ጊዜ ሁሉ የምትጠቀምባቸውን ቃላት ለስለስና ይቅር ባይነት የሞላባቸው መሆናቸውን አረጋግጥ::
°°° እጮኛህ ቁጣ በተሞላባቸው ቃላት ከጮህክባት አትለወጥም:: "እጮኛዬ አይወደኝም::" በማለት ራሷን ታሳምናለች:: እንዴት ልትለወጥ እንደምትችልና የተሻለች የፍቅር አጋር እንደምትሆን ልታስብ አትፈልግም:: በዛ ፈንታ ታለቅሳለች ወይም መልሳ ትጮህብሀለች::
》ቃሎችህ ለስለስና ይቅር ባይነት የሞላባቸው ከሆኑ ግን ፍቅርህ ይሰማታልና ለመለወጥ ዝግጁ ትሆናለች::
" የለዘበች መልስ ቍጣን ትመልሳለች ሸካራ ቃል ግን ቍጣን ታስነሣለች። "
(መጽሐፈ ምሳሌ 15:1)
2: ለመናገር ቁጣህ እስኪበርድ ጠብቅ::
ለምሳሌ የሆነ ነገር ተነጋግራቹ በተባባላቹበት ጊዜ አላከናወነችውም እንበል:: ወዲያው ስለሁኔታው እንደሰማክ አትናገራት:: እንዴት መለወጥ እንዳለባት ልትነግራት ይህ ጥሩ ጊዜ አይደለም:: ቁጣህ እስኪበርድ ድረስ ጠብቅ ተቆጥተህ እያለህ ብትናገር ቃሎችህ ለስላሳና ይቅርታን የተሞሉ ሊሆኑ አይችሉም::
3: በምትናገርበት ጊዜ "አንቺ" እንዲህ አደረግሽ ወዘተ... ከማለት "ይሰማኛል" በል::
》ቀጥሎ በዚህ መንገድ እንዴት እንደምትናገር የሚያሳይ ምሳሌዎች ተጠቀም::
》 "በተቀጣጠርንበት ቦታ በጊዜ አትገኚም(ትቀርያለሽ) ምክንያቱም ትዝ አልልሽም::" ከማለት ይልቅ በመጀመርያ አንተ ራስህ ቀጠሮ አክባሪ ሁን ከዛ " በተቀጣጠርንበት ቦታ በጊዜ ስትገኚ ለእኔ ያለሽ ፍቅር እና ክብር ትልቅ እንደሆነ ይሰማኛል::" ብትል መልካም ነው::
》 "እኔን ስታናግሪ ትህትና የለሽም ምክንያቱም አስተዳደግሽ ልክ ያልሆነ ጋጠወጥ እና ባለጌ ነሽ:: "አትበል ይህ ነቀፋ ነው:: ይህ ይጎዳታል እንጂ እንድትለወጥ አያደርጋትም:: በዚህ ምትክ " ረጋ ብለሽ ስታወሪኝ እና ነገሮችን ሰከን ባለ መንገድ ስታስረጂኝ እጅግ እንደምታፈቅሪኝ እና ለእኔ ያለሽን መልካም ስሜት የሚያሳይ ይመስለኛል::" ብትል እጅግ የተሻለ ነው::

#ደርሰሽልኝ_ቀረሁ 😥😥
ህመምን አውቃለው ምን ይኖራል ብዬ ከሞት የሚከፋ
ይመስለኝ ነበረ በጠባሳ እሚድን በጊዜ እሚጠፋ
አይደለም ለአምሳሉ ሰው ለሚለው ቀርቶ
እቤቱን ያፈርሳል ራበኝ ሲል እንቦሳው ከክዳኑ ፈቶ
በጠበቀ አንጀቱ መራመድ አቅቶት በደከመ ገላው
ለበጎቹ ያዝናል ለራሱ ሳይኖረው አንዳች የሚበላው
ያ ምስኪን ባላገር ያ መልካም ገበሬ
አዘንኩ አነባሁኝ.....
ያጎረሰኝ እጁ ቸግሮት ባይ ዛሬ
ለካስ ከቶ አይደለም የሀገር መዋቧ ገላዋን ማድመቋ
አሞኝ እያየችኝ ደና ነህ እያለች ለሌላ ማጥመቋ
የኛ ኩታ ገጠም ቦረናን ካስነባ
ነፍስን ከለያየ ቸነፈር ካስገባ
ድንጋይ ሁኚ አፈሬ ፍሬሽ ይምከንብሽ
ዘርሽ አልቦ ይሁን ቋጥኝ ይብቀልብሽ
ያረስኩብሽ እጄ ይቆረጥ ከእጅሽ
ሞቴ ማብቅያሽ ይሁን
የሀዘኔም እንባ እሳት ሆኖ ይፍጅሽ።
✍.......ጆlly
ህመምን አውቃለው ምን ይኖራል ብዬ ከሞት የሚከፋ
ይመስለኝ ነበረ በጠባሳ እሚድን በጊዜ እሚጠፋ
አይደለም ለአምሳሉ ሰው ለሚለው ቀርቶ
እቤቱን ያፈርሳል ራበኝ ሲል እንቦሳው ከክዳኑ ፈቶ
በጠበቀ አንጀቱ መራመድ አቅቶት በደከመ ገላው
ለበጎቹ ያዝናል ለራሱ ሳይኖረው አንዳች የሚበላው
ያ ምስኪን ባላገር ያ መልካም ገበሬ
አዘንኩ አነባሁኝ.....
ያጎረሰኝ እጁ ቸግሮት ባይ ዛሬ
ለካስ ከቶ አይደለም የሀገር መዋቧ ገላዋን ማድመቋ
አሞኝ እያየችኝ ደና ነህ እያለች ለሌላ ማጥመቋ
የኛ ኩታ ገጠም ቦረናን ካስነባ
ነፍስን ከለያየ ቸነፈር ካስገባ
ድንጋይ ሁኚ አፈሬ ፍሬሽ ይምከንብሽ
ዘርሽ አልቦ ይሁን ቋጥኝ ይብቀልብሽ
ያረስኩብሽ እጄ ይቆረጥ ከእጅሽ
ሞቴ ማብቅያሽ ይሁን
የሀዘኔም እንባ እሳት ሆኖ ይፍጅሽ።
✍.......ጆlly
Its Okay....
ላይሆን ካሰበ አንዳንድ ጊዜ እንቅፋትህ የተራራ ያህል ሆኖ ይመታሃል(አስበው በተራራ እንቅፋት መመታት) ፣እሻገራለው ያልክበት ድልድይ እንደ ክር የቀጠነ ይሆናል፣ዘወትር ሳቅህ ውስጥ ሃዘን የቀላቀለ እንባ አብሮ ይወርዳል፣መቆየት በማትፈልግበት ነገር ውስጥ ትታሰራለህ የማትወደው ነገር እንኳን በቅጽበታት ደቂት ለዘመናት አብሮህ የኖረ ያህል ይሰማሃል.....ያ የትናንት ማንነትህ ይናፍቅሃል፣ለእውነት ስለእውነት የኖርከው ጊዜ ትዝታው ብቻ እንደ እፉዬ ገላ እፍ እያለ ይሄዳል፣የማታገኘው ነገር በጉጉት ጠፍንጎ ያስርሃል ምኞትህ ሩቅቅቅ ይወስድሃል ከዛም ባዶነትህ ጎልቶ ይታይሃል። መቼ ነው የሚያበቃው...? መቼ ነው የሚቆመው...? ትላለህ:: ኢሄ ሁሉ የሆነ ጊዜ ላይ በሆነ ህይወትህ ውስጥ ይካሄዳል።ስንቅ የሌለው ጉዞ አድካሚ ነው ወይ ከመንገድህ ወይ ከመድረሻህ አያደርግህምና ተጠንቀቅ።የሚጸናና ጥሩ አስቦ የሚሰራ ነው ባለድል:ሁሌም ቢሆን ሁለት እቅድ ይኑርህ(አጭርና ረጅም)........የሆነው ቢሆን መተንፈስ እስካላቆምክ ድረስ፣ጠንካራ ሁን ሁሉም ይቀጥላል።የመኖር ገጿ ነውና ተቀበለው......እመነኝ ለትናንት ያልተሸነፈ ዛሬ የለም።ምኞት ብቻውን አቁመህ መስራት ስትጀምር....
all things gonna be Okay believe ur slf......
Take challenges in any way then
Say its okay! its okay!.

የተሰጠህ ያንተ ባይሆን እንኳን እንድትፈተንበት ነው።አይገባኝም አትበል መሻገርያህ ነውና።
" በልክ መኖር "
አያ አንበሶ ምን አለ መሰላችሁ " የፈለገ ሁኔታዬ ይዝቀጥ ይውረድ እንጂ እኔ ሳር አልበላም ይህ ለኔ ኩራት አይደለም ማንነቴ ስለማይፈቅድልኝ ነው ! እኔ አንበሳ ነኝ አንበሳ ደግሞ ቅጠል አይበላም" ።
ዛሬ በማንኛውም የህይወት ደረጃ ላይ ብትሆኑ ሰውነት ክቡር ነው ።
ማንም ሊያወርዳችሁ ቢሞክር ሰውነቴ አይፈቅድልኝም በሉት !
ህይወት የአግባብ ስጦታ እንጂ የፍቃድ ድርጊት ብቻ አይደለችም።

የእስረኞቹ እንቆቅልሽ
አንተ እና ጓደኛህ በአንድ ወንጀል ተጠርጥራችሁ ታሰራችሁ፡፡ ሆኖም መርማሪ ፖሊሶቹ ምንም አይነት ማስረጃ ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ እናም ሁለታችሁም በተለያየ ክፍል እንድትሆኑ ተደረገ። መርማሪዎቹም ለየብቻችሁ ያሉትን አማራጮች አቀረቡላችሁ።
አማራጭ አንድ - አንተ ከተባበርክ እና ወንጀላችሁን ከተናዘዝክ ነገር ግን ጓደኛህ ዝም ካለ አንተን በነጻ እንለቅሃለን እርሱ ግን
አስራ አምስት አመታት ይታሰራል፡፡
አማራጭ ሁለት - ጓደኛህ ወንጀላችሁን ከተናዘዘ ነገር ግን አንተ ዝም ካልክ፣ እርሱ በነጻ ይለቀቃል... አንተ አስራ አምስት አመታትን ትታሰራለህ።
አማራጭ ሶስት- ጓደኛህም አንተም ከተባበራችሁን ሁለታችሁም አምስት አመታትን ትታሰራላችሁ፡፡
አማራጭ አራት- አንተም ጓደኛህም ካልተናዘዛችሁ፤ ሁለታችሁም ቀላል የሆነ የአንድ አመት እስራት ትታሰራላችሁ።
በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ብትሆን ምን ታደርጋለህ?
መናዘዝህ የተሻለ ውጤትን የሚያስገኝ ይመስላል፤ ጓደኛህን ብትከዳውና ብትናዘዝ የሚገጥምህ በነጻ የመለቀቅ ዕድል ነው᎓᎓በተቃራኒው ዝም ብትልና ባትናዘዝ፣ የአንድ አመት ወይም የአስራ አምስት አመት እስራት ይጠብቅሃል።
ሆኖም አንተ ነጻ ሁነህ ጓደኛህ አስራ አምስት አመታትን በእስር ቤት ሲማቅቅ ማየት ምን አይነት ስሜት ይፈጥርብሃል?
እናም ይህ እንቆቅልሽ የሚያስነሳው መሰረታዊ ጥያቄ “እንደ ማህበረሰብ ማሰብ” ወይስ “እንደ ግለሰብ ማሰብ” የሚል ይሆናል። ለሁላችንም የተሻለ አማራጭ የሚሆነው እንደ ማህበረሰብ ማሰብ ነው፤ ሆኖም ሌላኛው ሰው ምን እንደሚያስብ አናውቅምና ለራሳችን
መልካም የሚሆነውን ለማድረግ ስንል ራስ ወዳድ እንሆናለን፡፡ እኔ እንኳ ባልስርቅ ሌላው ይሰርቃል የሚል ሃሳብ ይፈጠራል። ይህ አስተሳሰብም በድሃ አገራት ላለው የሙስና እና ስርዓት አልበኝነት አንዱ ምክንያት ነው፡፡
ለምሳሌ ያህል፣ አንድ አሳ የሚሰገርበት ሃይቅ አለ ብለን እናስብ። አሳ አስጋሪዎች በዚህ ሃይቅ ውስጥ ያሉት አሳዎች በራስ ወዳድነት ያለ ልክ የሚያጠምዱ ከሆነ፣ የአሳዎቹ ቁጥር ተመናምኖ በአንድ አመት ውስጥ ሃይቁ አሳ አልባ ይሆናል። ሆኖም ግን አግባብ ባለው ሁኔታ በልክ እና በመጠን የሚያሰግሩ ከሆነ፣ የአሳዎቹ ቁጥር አይመናመንም፤ እንዲያውም ከአመት ወደ አመት የሚያገኙት የአሳ ቁጥር እየጨመረ ይመጣል።
እዚህ ላይ ዋነኛ ጥያቄው መተማመን የሚለው ነው፡፡ አሳ አስጋሪዎቹ በመጠን ሊያሰግሩ ቢስማሙም አንዳቸው ሌላኛውን እስካላመኑ ድረስ ስምምነታቸው ዋጋ አይኖረውም፡፡ ልክ በሁለት ክፍሎች ውስጥ ለብቻቸው ተቀምጠው እንዳሉ እስረኞችም ይሆናሉ፡፡
ምንጭ- ፍልስፍና ከዘርዓ እስከ ሶቅራጠስ
ዝግጅት-ፍሉይ አለም

(አንድ ጊዜ ሁል ጊዜ ይሆናል)
ጥሩ የአመታት ጓደኛሞች ነን ። ከረጅም ጊዜ ኩርፍያ በኋላ ነበር ዳግም ወደ እቅፌ የገባችው።በተፈጥሮዋ ትንንሽ ነገሮች አይሸውዷትም(ቃል፣ዝና ፍራንክ፣ጉራና ሌሎችም) ለዛ ይመስለኛል ብዙዎቹን በቀላሉ የምትስባቸው ምክንያቱም በሚኮሩበት ነገር ላይ ግዴለሽነቷ ያበሽቃቸዋል።ባመኑበት ነገር ላይ ሲሸነፉ ደስ አይላቸውም ሲቀርቧት ደግሞ እሷ ስር ባለ ምንምና ባዶነታቸው ጎልቶ ይታያቸዋል።በያዙት ነገር ላይ ባላቸው አመለካከት በእርጋታ ስታስረዳቸው ተንኳሰው እንደ እፉዬ ገላ መንገድ አልባ ሁነው ይጠፋሉ(እኚ ውሸታሞች ትላለች)።በመሄዳቸውም በመምጣታቸውም አንዳች አትገረምም ነገረ ስራቸው ያስቃታል።እኔም የሚሆነውን ሳይ እናደዳለው ፍላጎቷ ግራ ይገባኛል።
ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ ክንዶቼ ላይ እንዴት እንዳረፈች እያሰብኩኝ ቁጭ ብለናል......
"እስኪ ስለ ፍቅር መንገድ ምን ያክል ታውቃለህ አለች ማለቴ አንተ ስለሄድክበት(ደግሞ ነገ በሚጠፋ እውነት እንዳትነግረኝ)።"
የመዋደድ መንገድኮ አባጣ ጎርባጣ ነው።አንዳንዴ በተራራ ላይ አንዳዴ በድንጋይ መሃል አንዳንዴ በውሃ ውስጥ አንዳንዴ በድልድይ ላይ ብዙ ብዙ ነው ከነዚህ ሁሉ ደሞ እኔ ድልድዩን ነኝ ሌሎችን ወደ ሌላ ወደ አዲስ ምድር ማሻገር የምፈልግ ወዳመኑበት ትልቅነት የማደርስ ትንሽ የጅረት መሻገርያ ነኝ።መንገድ ዳርም ጥሩ ቤት አለኝ አንቺስ ማለፍ(ማረፍ) ትፈልጊያለሽ ? ጥያቄዬ ድንገት ነበር።
ዝም ካለች በኋላ በትኩረት አየችኝና ከዛ በኋላስ አለች ከዛ በኋላማ የፈለግሽውን መሆን፣መምረጥ ትችያለሽ።የኔ ስራ ማሳለፍ ነው
የመረጥኩት ከድልድዩ ወድያ(በፊት) ቢሆንስ?
እኔ ላንቺ አሻጋሪ ሳልሆን እቀራለዋ።ደግሞ የመጨረሻዋ ተሻጋሪ ነበርሽ።ሳቅ ብላ አየችኝና
"አይ አይ ይቆየኝ አለች"
አሁን ባንቺ አለም ባንቺ ህይወት ቢሆን ቢሳካልሽ ደስ የሚልሽ ነገር ምንድነው?
ረጋ ያለች ናት ብዙ አሰበችና ከጉያዬ እንዳለች "አንተ የኔ ብትሆን አለች" ቀልድ አያምር......አላስጨረሰችኝም ተቆጣች የእውነቴን ነው። አንተ ጋር እረፍትና ሰላም ይሰማኛል አልጨነቅም። የሆነ ስለ ነገ ህይወት ስለመኖር የምጓጓው አንተን ሳስብ ነው። በኔ ዓለም ቢሆን ደስ የሚለኝ ኢሄ ነው አለች። ዝምታ ሰፈነ ጸጥ አልን ከሚቆራረጥ ትንፋሽና የልብ ምት ውጪ የሚሰማን አንዳች አልነበረም ደንዝዘናል። ከሚሻፍዱባት ወንዶች ጥሩ ጥሩውን ስመርጥላት ታኮርፍ የነበረው ገባኝ፣ የምትሆነውን ትናንቷንና ነገዋን ሳትደብቅ የምትነግረኝ ትዝ አለኝ።በኔ አትቀልድም ሌሎች ሴት ጓደኞቼ እንኳን እጄን ሲይዙ ታስለቅቃቸው ነበር ለምን ስላት አንተ ምርጡ ጓደኛዬ ስለሆንክ ትላለች።አንዴ ታምሜ ተኝቼ ሀኪም ቤት መጥታ ስታለቅስ እንደነበር ጓደኞቼ የነገሩኝ ትዝ አለኝ።የማስታውሳቸው አጋጣሚዎች በዙ....... አንገቷ ስር ስሜ እጆቿን ልቤ ላይ አደረኳቸው ደንግጣ ቀና ብላ ስታየኝ ዓይኖቼ በእንባ ዘለላ ተሞልተው ነበር።ምክንያቱም ከሷ በላይ እወዳት የነበርኩት እኔ ነኛ ነፍሴ ቦረቀች ከዛ መልሳ አቀፈችኝ እኔም በስስት አቀፍኳት ......
✍....#Jo_ሊ