Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
7772 - Telegram Web
Telegram Web
ዓሣ አንበሪው ዮናስን በሦስተኛ ቀኑ ከነነዌ የባህር ዳርቻ ሲደርስ  ተፋው። ዮናስ እግዚአብሔርን አመሠገነ። ወደ ነነዌ ከተማ ገባ ሕዝቡንም ሰበከ። ከህጻን እስከ አዋቂ፣ ከእንስሳ እስከ ሰው፣ ከሎሌ እስከ ንጉሥ ድረስ  አዳመጡት። በክፋታቸው ተጸጸቱ። ጾሙ፣ ራሳቸውን ስለ እግዚአብሔር አዋረዱ። እግዚአብሔርም ማራቸው።

ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይኾን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡ ስለኾነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመኾኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ኾነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡

ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኀጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቶ፣ ልመናችንን ተቀብሎና ጾማችንን አስቦ ምሕረትን ያድርግልን፤የነነዌ ህዝብን በምህረቱ የጎበኘ ቸሩ አምላካችን ሀገራችንን ህዝባችንንም በምህረት አይኑ ይጎብኝልን ቸርነቱን ያብዛልን ፆሙንም ለጥያቄያችን መልስ የምናገኝበት የበረከት ፆም ይሆንልን ዘንድ የአምላካችን ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን  አሜን!!!  🙏
መገናኛ ብዙኅን ንዑስ ክፍል
🍁️️️️🌿🍁️️️️🌿🍁️️️️🌿🍁️️️️🌿
የሰንበት ትምህርት ቤቱ 45ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ተከናወነ ።

የካቲት 2/2017 ዓ.ም የተከናወነው ይህ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በ2016/17 በጀት ዓመት የስድስት ወራት በሰንበት ትምህርት ቤቱ የተሰሩ ሥራዎች  ፤ የስድስት ወር ሥራ የአፈጻጸም ዘገባ/ሪፖርት የቀረበበት ነበር ።

በዚሁ መሠረት የየክፍላቱ የክዋኔ ሪፖርት ፣  የሂሳብ ሪፖርት እንዲሁም የኦዲት እና ኢንስፔክሽ ሪፖርቶች በቅደም ተከተል ቀርበዋል ።

በክዋኔ  ሪፖርቱ በእቅዱ መሰረት የተከናወኑ ፣ ታቅደው ያልተከናወኑ እንዲሁም ከእቅድ ውጪ የተሰሩ ሥራዎች ካጋጠሙ ችግሮችና ከተወሰዱት መፍትሔዎች ጋር የነበራቸውን የበጀት አጠቃቀም ጨምሮ የተጣመረበት ሪፖርት ቀርቧል  ።

በኦዲት እና ኢንስፔክሽን ክፍል ሪፖርት የየክፍላቱ  የኢንስፔክሽን ሥራ ግኝትና  የሰንበት ትምህርት ቤቱ የሂሳብ ኦዲት ሪፖርት ቀርቧል ። በዚህ የኦዲት እና ኢንስፔክሽን ሪፖርትም ጥሩና ሊቀጥሉ የሚገቡና ክፍተቶች ሊሻሻሉ ይገባቸዋል የተባሉት የኦዲት ምክረ ሐሳቦች ቀርበዋል ።

እነዚህን ሪፖርቶችን ያደመጠው ጠቅላላ ጉባኤ የጉባኤውን መዘጋጀት በማድነቅ  የተለያዪ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን አቅርቧል። ከጉባኤው ለተነሱት አስተያየት እና ጥያቄዎች በሰንበት ትምህርት ቤቱና በጉባኤው ሰብሳቢ በኩል ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠባቸው ሲሆን የታዩት ክፍተቶች እና የተሰጡት አበረታች አስተያየቶች እንዲሁም በትኩረት ሊሰሩባቸው  የሚገቡ  የተጠቀሱት በቀጣይ መንፈቅ የሥራ እና በጀት ዓመት አካቶ ለመሥራት እና ለመከወን ድምዳሜ ተደርሶባቸው የቀረቡት ሪፖርቶች የሰንበት ትምህርት ቤቱ የ45ኛ ዓመት የመጀመሪያው የስድስት ወር ሪፖርት ሆኖ በሙሉ ድምጽ ጉባኤው አጽድቋል።

በመጨረሻም በአገልግሎቱና በጉባኤው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የተሳተፉና የደገፉትን  ሁሉ በሰንበት ት/ቤቱ ስም በሰብሳቢው ምስጋና ቀርቦ ጉባኤው በጸሎት ተጠናቋል።

መገናኛ ብዙኅን ንዑስ ክፍል
እንኳን አደረሳቹ
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ መዝ 121-1
            #ፍኖተ_ሕይወት
መንፈሳዊ የሕይወት ጉዞ ወደ ፈታሔ ማኅጸን ካራ ደጋ ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን
#ባሉበት_ሆነው_ጉዞውን በኦንላይን_ይመዝገቡ_ጉዞውን_ይጓዙ
@finotebirhanbot

የአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
▭▭▭▭  ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝  ▭▭▭▭
🔎ዩቲዩብ ገፅ፡https://www.youtube.com/@finotebirhan328
🔎 ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@finotebrhan

🔎ቴሌግራም ገፅ፦
ትምህርትና መረጃዎች፡

https://www.tgoop.com/finottebiirhan
@finotebrhan
የካቲት 4  በቅዳሴ ቅድመ ወንጌል የሚባል  ምስባክ

የአብነት እና አርድእት ንዑስ ክፍል
የአቃቂ መንበረ ህይወት መድኅኔዓለም ቤተክርስቲያን የመጀመሪያው አስተዳዳሪ ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ ሊቀ ጳጳስ

(ከ1923 እስከ 1998 ዓ . ም )

ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ ከአቶ ደሴ አሉላና ከወ/ሮ ወርቂቱ ታፈረ በሰቆጣ አውራጃ ልዩ ስሙ አርም አርባዕቱ እንስሳ በሚባል ደብር ጥር 15 ቀን 1923 ዓ.ም ተወለዱ፡፡

ብፁዕነታቸው ከፊደል እስከ ግብረ ዲቁና በትውልድ ቦታቸው ተምረዋል፡ በመቀጠል ከመምህር ኤልሳዕ ምዕራፍ ጾመ ድጓ ከተማሩ በኋላ ወደ ወይብላ ማርያም በመሔድ አቋቋምና ዝማሬ፣ መዋሥዕት ከአለቃ መርዓዊ ዘንድ ጠንቅቀዋል፡፡ ወደ ትግራይ በመሔድ በተምቤን አውራጃ በእንደባ ሰላማ ገዳም ከነበሩት ከመምህር ኃይለ ሥላሴ ክብረ በዓልና መዝሙር በክለሳ መልክ አጠናቅቀዋል፡፡

የቅኔ ትምህርት እንዲረታ አይቤቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተብሎ በሚጠራው ታላቅ ደብር ከመምህር ጌራ ወርቅ ከጉባኤ ቃና እስከ ቅኔ ዘረፋ ያለውን ሙያ በሦስት ዓመታት አጠናቅቀው ተምረዋል፡፡ በዋልድባ ገዳምም ከመምህር ገበየሁ በላቸውና ከመምህር ተመስገን ከልካይ የቅኔውን ሙያ ከነአገባቡ አጠናቀው በመምህርነት ተመርቀዋል፡፡ በ1944 ዓ.ም መዐርገ ምንኲስናንና ቅስናን ከብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ተቀብለዋል፡፡

ብፁዕነታቸው ወደ ትውልድ ቦታቸው ተመልሰው አርካአቦ በተባለው ቦታ በ21 ዓመታት ጉባኤ አስፋፍተው ቅኔ አስተምረዋል፤ ብዙ ደቀ መዛሙርትም አፍርተዋል፡፡ ወደ አዲስ አበባ መጥተው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅኔ እያስተማሩ ሐዲሳትን ከመምህር መርሐ ጽድቅ ቀጽለዋል፡፡
ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመዛወርም ከመምህር ጸጋየ (ከብፁዕ አቡነ ታዴዎስ) ትርጓሜ ኢሳይያስን አጥንተዋል፡፡ በዚሁ ቦታ በዘመናዊ ትምህርት እስከ 8ኛ ክፍል ተምረዋል፡፡ ብፁዕነታቸው በሰሜን ኦሞ በሰባኬ ወንጌልነትና፣ በአዲስ አበባ የቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪነት ለአምስት ዓመታት አገልግለዋል፡፡

ከ1972 -1982 ዓ.ም ድረስ በደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከ1982-1984 ዓ.ም ድረስ በጎላ ጽርሐ ጽዮን ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በአስተዳዳሪነት አገልግለዋል፡፡ በመቀጠልም ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ በእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገዳምና በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሰብከተ ወንጌል አገልግሎት አበርክተዋል፡፡

ብፁዕነታቸው ሐምሌ 5 ቀን 1991 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት አንብሮተ እድ የነገሌ ቦረና ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ ሆነው ተሹመዋል፡፡ ከጥቅምት 20 ቀን 1996 ዓ.ም ጀምሮ የምሥራቅ ሐረርጌና የጅጅጋ አህጉረ ስብከት ጳጳስ ሆነውም ሠርተዋል፡፡ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ

የኦጋዴን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን በማገልገል ላይ እንዳሉ ወደ ሀገረ ስብከታቸው ሲጓዙ በደረሰባቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ በ75 ዓመታቸው ሕይወታቸው አልፏል፡፡

የብፁዕነታቸው አስከሬን ወደ ናዝሬት ቅድስት ማርያም ካቴድራል ተወስዶ ካረፈ በኋላ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ታጅቦ የካቲት 4 ቀን 1998 ዓ,ም ወደ አዲስ አበባ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ገብቷል፡፡

የብፁዕነታቸው የቀብር ሥነ ሥርዓትም የካቲት 4 ቀን 1998 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተዘጋጀ መካነ መቃብር ተፈጽሟል፡፡
የብፁዕነታቸው በረከት አይለየን አሜን፡፡

መልአከ ሰላም አባ ኪሮስ ወልደአብ
የካቲት 4 ቀን 2017ዓ.ም

© EOTC
የአቃቂ መንበረ ህይወት መድኅኔዓለም ቤተክርስቲያን የመጀመሪያው አስተዳዳሪ ብጹዕ አቡነ ዲሜጥሮስ በረከታቸው ይደርብን !!
የካቲት 5 በቅዳሴ ቅድመ ወንጌል የሚባል  ምስባክ

የአብነት እና አርድእት ንዑስ ክፍል
ወደ ባሕር ማዶ ለሚጓዙት የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት  በሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት አሸኛኘት ተደረገላቸው።

መምህር ታሪኩ ግዛቸው ፣ ዘማሪት ኢየሩሳሌም ግዛቸውና ዘማሪ ኢዩኤል ግዛቸው ከህጻናት ክፍል ጀምሮ በሰንበት ት/ቤቱ በአገልግሎት ያደጉና ያሉ ሲሆን በኑሮ ምክንያት ወደ ሰሜን አሜሪካ ስለሚሔዱ የመሸኛ ጉባኤው ተዘጋጅቷል።

በጉባኤውም የመሸኛ አባታዊ ጸሎት  እንዲሁም ውይይት ተደርጓል። በውይይቱም ልዩ የሆነ የማይረሱት የሰንበት ት/ቤቱ ፍቅር እንዳላቸው አረጋግጠው ለነበራቸው የሰንበት ት/ቤት የአገልግሎት ቆይታ አመስግነዋል በሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት በበኩልም ላበረከቱት የእስከዛሬ ቆይታ በማመስገን አገልግሎት በጊዜና በቦታ ስለማይገደብ በሚሔዱበት ቦታም በቤተክርስቲያን አገልግሎት እንዲበረቱና ከሰንበት ት/ቤቱም ጋር ያላቸው  ግንኙነት እንዳይቋረጥ አሳስበዋል።

በዚሁ አጋጣሚ እግዚአብሔር መንገዳቸውን እንዲያቀናላቸው መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

የሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት
የካቲት 4/2017 ዓ.ም
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ መዝ 121-1
            #ፍኖተ_ሕይወት
መንፈሳዊ የሕይወት ጉዞ ወደ ፈታሔ ማኅጸን ካራ ደጋ ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን
#ባሉበት_ሆነው_ጉዞውን በኦንላይን_ይመዝገቡ_ጉዞውን_ይጓዙ
@finotebirhanbot

የአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
▭▭▭▭  ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝  ▭▭▭▭
🔎ዩቲዩብ ገፅ፡https://www.youtube.com/@finotebirhan328
🔎 ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@finotebrhan

🔎ቴሌግራም ገፅ፦
ትምህርትና መረጃዎች፡

https://www.tgoop.com/finottebiirhan
@finotebrhan
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ መዝ 121-1
            #ፍኖተ_ሕይወት
መንፈሳዊ የሕይወት ጉዞ ወደ ፈታሔ ማኅጸን ካራ ደጋ ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን
#ባሉበት_ሆነው_ጉዞውን በኦንላይን_ይመዝገቡ_ጉዞውን_ይጓዙ
@finotebirhanbot

የአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
▭▭▭▭  ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝  ▭▭▭▭
🔎ዩቲዩብ ገፅ፡https://www.youtube.com/@finotebirhan328
🔎 ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@finotebrhan

🔎ቴሌግራም ገፅ፦
ትምህርትና መረጃዎች፡

https://www.tgoop.com/finottebiirhan
@finotebrhan
2025/03/04 13:07:11
Back to Top
HTML Embed Code: