Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
7818 - Telegram Web
Telegram Web
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ መዝ 121-1
            #ፍኖተ_ሕይወት

መንፈሳዊ የሕይወት ጉዞ ወደ ፈታሔ ማኅጸን ካራ ደጋ ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን
#ባሉበት_ሆነው_ጉዞውን በኦንላይን_ይመዝገቡ_ጉዞውን_ይጓዙ
@finotebirhanbot

የአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
▭▭▭▭  ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝  ▭▭▭▭
🔎ዩቲዩብ ገፅ፡https://www.youtube.com/@finotebirhan328
🔎 ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@finotebrhan

🔎ቴሌግራም ገፅ፦
ትምህርትና መረጃዎች፡

https://www.tgoop.com/finottebiirhan
@finotebrhan
“ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው።.... ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል።”
  ራእይ 14፥13
የደብረ ሰላም ቱሉዲምቱ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን  ውሉደ ሰማዕት ሰንበት ት/ቤት ነባር አጋልጋይ የሆነው  ወንድማችን ዲ/ን እንዳለ መርሻ /ተክለ ማቴዎስ/ ዕረፍት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘንን እየገለጽን። አባታችን መድኃኔዓለም የወንድማችንን ነፍስ የቅዱሳን አበው ነፍሳት ባረፉበት መካነ ዕረፍት እንዲያሳርፍልን : ለውሉደ ሰማዕት ሰንበት ት/ቤት አባላትና ለደብሩ አገልጋዮች እንዲሁም ቤተሰቦቹ የመጽናናት አምላክ የሆነ እግዚአብሔር ፍጹም መጽናናትን እንዲሰጥልን እንመኛለን።

የፍኖተ ብርሐን ሰንበት ት/ቤት ጽ/ቤት
የካቲት 9/2017 ዓ.ም
“ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው።.... ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል።” ራዕ 14፥13

በሰንበት ትምህርት ቤታችን በአገልግሎት ያሳለፈቸው እህታችን አይናለም ሰቦቃ እድሜ ዘመን ገትቷ ወደ አምላኳ እቅፍ ሄዳለች ። ሥርዓተ ቀብሯም በትናንትናው ዕለት የካቲት 9/2017 ዓ.ም በምትኖርበት ሲዳም አዋሽ ደብረ መንክራት ዋሻው ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል ። እግዚአብሔር አምላክ የእህታችንን ነፍስ ቅዱሳን አንስት ባረፉት ሥፍራ ያሳርፍ ለመላው ቤተሰብ መጽናናትን ይስጥል ።


ውስጥ ግንኙነት ንዑስ ክፍል
የካቲት 10/2017 ዓ.ም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ መዝ 121-1
☘️#ፍኖተ_ሕይወት☘️
✝️ መንፈሳዊ የሕይወት ጉዞ ወደ ፈታሔ ማኅጸን ካራ ደጋ ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን ✝️
☘️#ባሉበት_ሆነው_ጉዞውን በኦንላይን_ይመዝገቡ_ጉዞውን_ይጓዙ ☘️
@finotebirhanbot
https://vm.tiktok.com/ZMk729kET/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
☘️#ፍኖተ_ሕይወት☘️
✝️ መንፈሳዊ የሕይወት ጉዞ ወደ ፈታሔ ማኅጸን ካራ ደጋ ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን ✝️
☘️#ባሉበት_ሆነው_ጉዞውን በኦንላይን_ይመዝገቡ_ጉዞውን_ይጓዙ ☘️
@finotebirhanbot https://vm.tiktok.com/ZMk7W2Mnf/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite
"ጾምን የምንጾመው  ዲያብሎስንና ግብረ ኃጢአትን ለማሸነፍ  ነው::" ቅዱስነታቸው

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2017 ዓ.ም የዐቢይ ጾምን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ !

የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው መነሻ <<ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከተጠመቀ በኋላ ሳይውል ሳያድር ወዲያውኑ ወደ በረኻ በመሄድ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመ፡፡>> በማለት የጌታችንና አምላካችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጾሙን ጥንተ ነገር አውስተዋል።

ቅዱስነታቸው በአርባ ቀናት ውስጥ የጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በዲያቢሎስ መፈተንና ድል መንሳትም አብራርተው  ሲያወሱ <<በዚህ ጊዜ የጌታችን መልስ “ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ ኣይኖርም” የሚል ነበረ፤
ጌታችን በዚህ አባባሉ የዲያብሎስን ክፉ ሐሳብ የሚንድ እንጂ የእሱ ታዛዥ አለመሆኑን ኣሳየ፤ ዲያብሎስ በዚህ ሳያበቃ በትዕቢት በፍቅረ ንዋይና በባዕድ አምልኮ ሊጥለው ደጋግሞ ሙከራ አደረገ፤ ግን አልተሳካለትም፤>> ብለዋል።

ቅዱስነታቸው የመጾማችንን ምክንያት ሲያጠይቁ <<...የዲያብሎስን ፈተናዎች እንዴት በድል ማለፍ እንደምንችል ጌታችን በተግባር ኣሳይቶናል፤ ጌታችን ዲያብሎስን ያሸነበፈበት ስልት በመንፈስ ልዕልና እንጂ በዱላም፣ በካባድ መሳሪያም ኣይደለም፤ አለመሆኑንም የድርጊቱ ሂደት በግልጽ ያመለክታል፤ እንግዲያውስ እኛም ዲያብሎስን የምናሸንፈው በዚህ የመንፈስ  ልዕልና ነው ማለት ነው::... ስለሆነም ጾምን የምንጾመው በዚህ ስልት ዲያብሎስንና ግብረ ኃጢአትን ለማሸነፍ  ነው::
ከዚህ አኳያ ዲያብሎስን ለማሸነፍ መጾም ግድ ስለሆነ ጌታችን በከፈተልንና ባሳየን መንገድ እንጾማለን>> ብለዋል።

ስንጾምም <<የምንጾመው መልካም ኅሊና ኖሮን ለእግዚአብሔር ለመታዘዝና ለመገዛት፣ ከዚያም ከቃሉ በተነገረን መሠረት የተራቡትን ልንመግብ፣ የተራቈቱትን ልናለብስ፣ የተጣሉትን ልናስታርቅ፣ ፍትሕ ያጡትን ፍትሕ እንዲያገኙ ልናደርግ፣ ለንኡሳን የሕብረተ ሰብ ክፍሎች የተለየ ትኵረት ልንሰጥ፤ እኩልና ፍትሓዊ የሀብት ክፍፍል በሰው ልጆች መካከል ልናረጋግጥ፣ ሰብኣዊ ክብር እንዳይነካ ጦርነት፣ ጥላቻ፣ አደገኛ የቃላት ውርወራና መነቃቀፍ እንዲቀር ልናደርግ ነው፤>> በማለት አጽንዖት ሰጥተው አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የካቲት 16 በቅዳሴ ቅድመ ወንጌል የሚባል  ምስባክ

የአብነት እና አርድእት ንዑስ ክፍል
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ መዝ 121-1
            #ፍኖተ_ሕይወት
የፍኖተ ሕይወት ቤተሰብ ይሁኑ ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ
https://www.tgoop.com/finote_hiwot_familly
መንፈሳዊ የሕይወት ጉዞ ወደ ፈታሔ ማኅጸን ካራ ደጋ ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን
#ባሉበት_ሆነው_ጉዞውን በኦንላይን_ይመዝገቡ_ጉዞውን_ይጓዙ
@finotebirhanbot

የአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት
▭▭▭▭  ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝ 
@finotebrhan
“ጾምን አውጁ” (ኢዩ.፪፥፲፭)

እንኳን ለዐቢይ ጾም አደረሰን!

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ከሚታወጁት ሰባት አጽዋማት መካከል ታላቅ ለሆነው ለዐቢይ ጾም ስላደረሰን አምላካችን እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው!  

ዐቢይ ጾም ማለት ምን ማለት ነው?

በመጀመሪያ ‹‹ዐቢይ›› የሚለው ቃል ‹‹አበየ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ትርጓሜውም ‹‹ከፍ አለ›› ማለት ነው፡፡ ጾሙም ዐቢይ የተባለበት ሦስት ዓበይት ምክንያቶች አሉት። የመጀመሪያው ጌታቸን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ የጾመው ስለሆነ ነው፡፡ (ማቴ.፬፥፫-፫) በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት ስለ ሚበልጥና የቀኑ ብዛትም ፶፭ ቀንም ነው፡፡ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች እንዲሁም ደግሞ ሦስቱ ርእሰ ኃጢአት (ትዕቢት፣ ስስት ፍቅረ ነዋይ) በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ድል የተመቱበት በመሆኑ ዐቢይ (ታላቅ) ጾም ተብሏል፡፡ (ማቴ.፬፥፫-፲፩)፡፡

የዐቢይ ጾም ስያሜዎች

ዐቢይ ጾም ከቀኑ ርዝማኔ በተጨማሪ የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡ 
ጾመ ሁዳዴ፡- ሁዳድ ማለት ሰፊ (ትልቅ) የእርሻ ቦታ ማለት ነው፡፡  በሰፊ እርሻ የተመሰለበት ምክንያት የቀኑ ብዛት ከሌሎች አጽዋማት ስለሚበዛ ነው፡፡

የካሣ ጾም፡- አዳምና ሔዋን በዲያቢሎስ ግዞት እያሉ ክርስቶስ ደሙን በመክፈል (በመካስ) ነጻ ስላውጣቸው የካሣ እየተባለ ይጠራል፡፡

የድል ጾም፡- ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ጾም ሰይጣንን ድል ያደረገበት በመሆኑ የድል ጾም ተብሏል፡፡

ጾም አስተምህሮ፡- ዐቢይ ጾም ‹‹ጾም አስተምህሮ›› የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማስተማር የጾመው በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡

የዐቢይ ጾም ሳምንታት

ዐቢይ ጾም በያዘው በ፶፭ ቀኑ ውስጥ ሰባት ቅዳሜና ስምንት እሑዶቸን ይዟል፤ የእነዚህ የስምንቱ እሑዶች የተለያየ ስያሜ አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም የሰጣቸው የቤተ ክርስቲያናችን የዜማው ሊቅ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ ዘወረደ፣ ቅድስት፣ ምኩራብ፣ ደብረዘይት፣ ገብረ ኄር፣ ኒቆዲሞስ ፣ መፃጉዕ፣ ሆሣዕና ናቸው፡፡
 
፩ኛ. ዘወረደ፡- በመጀመርያው ሳምንት ዘወረደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማያት መውረዱን፣ ከአመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን እና እኛን ማዳኑን በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚወሳበትና የሚዘከርበት ወቅት ሲሆን ይህንንም የሚዘክሩ መዝሙሮች ይቀርባሉ፤ ትምህርቶች ይሰጣሉ፤ ይህንንም እያሰብን ጾሙን እንጾማለን፡፡
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ ለሐዋርያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን በሥርዓቱ ጹመን እንዲንጠቀም እርዳን፤ አሜን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

ፀልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን
ፍኖት:
🌿🌿🌿
"ጾም ነፍስን ያነጻል አእምሮን ያሳድጋል፣ ሥጋን ለነፍስ ያስገዛል፣ የምኞት ደመናን ይበትናል፣ የፍትወት እሳትን ያጠፋል፣ የንጽሕና እውነተኛ ብርሃን ያበራል።"
   /ቅዱስ አውግስጢን/


1. #ዘወረደ
   ይህ የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ከጾመ ሕርቃል በተጨማሪ ዘወረደ ይባላል፡፡ ይኸውም በባሕርዩ ከላይ ያለውን ለማውረድ መንጠራራት ከታች ያለውንም ለማንሳት ማጎንበስ የሌለበት፣ ሥልጣን ሁሉ የባሕርይ ገንዘቡ የሆነለት፣ የሚታየውና የማይታየውም ሁሉ በእጁ መዳፍ የተያዘለት አምላክ ወልደ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምንና ልጆቹን ሊያድን ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ፍጹም ሰው መሆኑ የሚዘከርበት ሳምንት ነው።
   ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ተጠመቀ፣ በገዳመ ቆሮንጦስ ጾመ፣ በጌቴሴማኒ ጸለየ፣ በቀራንዮ ተሰቀለ፣ ሞተ፣ተቀበረ፣ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፣ ወደ ሰማይ ዐረገ ለሚለው ሁሉ ጥንቱ ከሰማያት ወረደ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ተፀነሰ፣ ተወለደ የሚለው ነው፡፡ ለዚህም ቢሆን ጥንት አለው፤ ይኸውም ወንጌላዊው ዮሐንስ ‹‹በመጀመሪያ ቃል ነበር›› (ዮሐ 1፥1) የሚለው ነው፡፡ በዚህ ሳምንት የወልደ እግዚአብሔር ከሰማያት መውረዱና ሰው መሆኑ ይዘከራል።
   በዚህ ሳምንት ከዳዊት መዝሙር ‹‹ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፤ በረዓድም ደስ ይበላችሁ›› (መዝ 2፥11) የሚለው ሲሆን ከወንጌል ክፍል ደግሞ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአይሁድን አለቃ ኒቆዲሞስን ባስተማረበት ትምህርቱ ‹‹ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፤ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው›› (ዮሐ 3፥10-29) ብሎ ያስተማረውን ሊቃውንት ያስተምሩታል ያብራሩታልም።
          ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ወንጌል አንድምታ (ማቴ 4፥1-3) ፣ ሰባቱ አጽዋማት

━━━━━✦📖📖✦━━━━━
ዐቢይ ጾም
ፀልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን
"ጾም የነፍስን ቁስል ታድናለች!" ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ
#ፍኖተ_ሕይወት
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ጾም ፤ ዓቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ!

ጾሙን የበረከት ያድርግልን!
#ፍኖተ_ሕይወት
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ መዝ 121-1
            ☘️#ፍኖተ_ሕይወት☘️
✝️ መንፈሳዊ የሕይወት ጉዞ ወደ ፈታሔ ማኅጸን ካራ ደጋ ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን ✝️
☘️#ባሉበት_ሆነው_ጉዞውን በኦንላይን_ይመዝገቡ_ጉዞውን_ይጓዙ ☘️
@finotebirhanbot
"አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ" ተከለከለ
=========
(የካቲት ፲፱/፳፻፲፯ ዓ/ም፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ)

አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ መከልከሉን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስታወቀ።

ሀገረ ስብከቱ የዐቢይ ጾምን አስመልክቶ አገልግሎቱ እንዴት መከናወን እንዳለበት ከሁሉም ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎችና ሰባክያነ ወንጌል እንዲሁም ቄሰ ገበዞች ጋር ባደረገው ውይይትና ስምምነት መነሻነት የተለያዩ መመሪያዎች መተላለፋቸው ተገልጿል።

ከመመሪያዎች አንዱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚከናወኑ የጸሎተ ቅዳሴና ሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች የእጅ ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከተለ መሆኑን ለሁሉም ገዳማትና አድባራት በተላከው የመመሪያ ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል።

በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት መሠረት ቅዳሴ የሁሉም ጸሎታት ማጠናቀቂያ፣ ቀራንዮ ላይ ምንገኝበት፣ የበጉ ሠርግ ላይ የምንታደምበት፣ የጌታችንን የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በአንድነት ለኃጢአት ሥርየት፣ ለነፍስ ሕይወት፣ ለሃይማኖት ጽንዐትና ለመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ይሆነን ዘንድ የምንቀበልበት ታላቅ የጸሎት ሰዓት ነው።

በመሆኑም አላስፈላጊ የእጅ ስልክ አጠቃቀም ጎልጎታን ከሚያስረሱ፣ በረከትን ከሚያሳጡና ጸጋን ከሚያስወስዱ ድርጊቶች መካከል አንዱ በመሆኑ እንደተከለከለም ተገልጿል።

ይህንን መመሪያም የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ሰበካ ጉባኤያት ጥብቅ ክትትል በማድረግ እንዲያስፈጽሙ መታዘዛቸውን በተጻፈ ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል።


(አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ )
2025/03/04 05:40:20
Back to Top
HTML Embed Code: