Telegram Web
አንዳንዴ የምንፈልገውን ለማግኘት ስንሮጥ ያለንን እናጣለን፤ ግን ሁሌም ህይወት በማግኘትና በማጣት ውስጥ ትኖራለች።

ሰዎች የሚፈልጉትን ለማግኘት ሲሉ የሚያስፈልገንን ሊያሳጡን ይችላሉ። ፈጣሪ ግን እንደሚያስፈልገን ስለሚያውቅ ይክሰናል። እናም እኛ እንደነሱ ክፉ መሆን የለብንም ይልቁኑ በነገር ሁሉ ፈጣሪን አመስጋኝ እንጂ።

ሁሌም ቢሆን ፍቅር ከሁሉም ነገር ይበልጣል።
ሰዎች ሲበድሉን በፍቅር እንካሳቸው። በደልን በበደል ከመለስን ግን የኛ በደል ከነሱ ይብሳል።
የፍቅር መስፈርቱ ደግሞ ፍቅር ብቻ ነውና።
           


          ጓደኝነት

ሁለት ተማሪ ጓደኛሞች የጠበቀ ወዳጅነት አላቸው፡፡ ወደ ትምህርት ቤትም ዘውትር አብረው ነው የሚሄዱት፡፡ አንደኛው ታዲያ የጓደኛውን ቦርሳ ተደብቆ በመፈተሽ ቼኮሌቱን የመስረቅ መጥፎ አመል ነበረበት፡፡

አንድ ቀን በዚህ አመሉ ክፉኛ የጥፋተኛነት ስሜት ተሰማው እና ያደረገውን ሁሉ ለጓደኛው ሊናዘዝ ፈለገ፡፡ ነገር ግን በቀጥታ በጓደኛው ፊት ለመናገር ድፍረት አጣ፡፡ ስለዚህም ደብዳቤ ጻፈለት፡፡

‹‹እስከ ዛሬ ድረስ ከቦርሳህ ውስጥ ቼኮሌቶቹን ስሰርቅህ የነበርኩት እኔ ነኝ፡፡ ለዚህም በድርጊቴ በጣም ነው የማዝነው፡፡››

ጓደኛውም ደብዳቤውን ሲያነብ ሳቀ፡፡ መልሶ ሌላ ደብዳቤ ላከለት፡፡

‹‹ብዙም አትጨነቅ፡፡ ቼኮሌቶቹን ከቦርሳዬ ውስጥ አንተ እንደምትወስድ አውቅ ነበር፡፡ ለዚያም ነው ቼኮሌቶቹን በተመሳሳይ ስፍራ ሁሌም የማስቀምጣቸው፡፡›› ይላል፡፡
____
ስንቶቻችን እንሆን ጓደኛችን እያስቀየመንም ቢሆን ለጓደኝነት ጥንካሬ ስንል አይተን እንዳላየን ሰምተን እንዳልሰማን የምናልፈው???
ስንቶቻችንስ ለመጣላት እንሮጥ ይሆን እስኪ እራሳችን እንይበት፡፡

🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

@fker12
┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ሲያነቃቁን ለምን አንነቃም? ሙተን ይሆን እንዴ?
(አሌክስ አብርሃም)

ለመጀመሪያ ጊዜ self-help book የሚሏቸውን ሳነብ በጣም ነቅቸ ነበር!  አስታውሳለሁ የ Rhonda Byrne ን The secret  ሳነብ በጣም ከመንቃቴ የተነሳ ለስራ እጀን ከመጠቀም ይልቅ አዕምሮየን ለመጠቀም ወስኘ ነበር። ለምሳሌ መብራት አጥፍቸ ከመተኛት ተኝቸ መብራቱ ልክ እንቅልፍ ሲወስደኝ ይጠፋል ብየ ለራሴ እነግረዋለሁ፤ጧት ስነሳ እንደበራ ባገኘው አልደነቅም፣ ከእንቅልፌ ከመንቃቴ አንድ ደይቃ በፊት በራሱ ጊዜ እንደበራ አምናለሁ። የወሩ የመብራት ሂሳብ ግን የነገረኝ ሌላ ሆነ፤ ተው ወንድሜ በጣም አትንቃ አለኝ። እናም እያጠፋሁ መተኛት ጀመርኩ። ከ1890 ዓ/ም ጀምሮ መብራት ሀይል መብራት ያላጠፋበት ብቸኛ ወር ነበር። ስንነቃ አይወዱ😀

ኦሾን ያነበቡ የኔ ዘመን ወጣቶች ደግሞ "ሐይማኖት ባህል ገለመሌ ከጫነብን ፍዘት ወጣን" አሉና በየመንገዱ ፀጉራቸውን በመፍተል መቆዘም ጀመሩ፤ ይህንንም "ውስጣዊ ንቃት" አሉት። ከአመታት በኋላ ሁሉም ጠበል ገብተው  እየጮሁ ከንቃታቸው በጣም ነቁ። በቀን አምስቴ ኡዱ የሚያደርጉ፣ ለጁመዓ የሽቷቸው  መዓዛ ከሞያሌ  የሚጣራ ፣ እንዴት ያሉ ንፁህ ሙስሊም ወዳጆቸ ሳይቀሩ ጀዝበው ገላቸውን መታጠብ አቁመው  ነበርኮ!  ስንት ተቀርቶባቸው ተመለሱ። የዛን ሰሞን ወጣቱ ሁሉ ውስጣችን በራልን እያለ ስንት ጨለማ ተከናነበ። ራሳቸውን ያጠፉም ነበሩ። ኦሾና አለቃ ገብርሃና ተረታቸው እንጅ ኑሯቸው አያምርም።

ይሄው በዚህኛው ዘመን ደግሞ አነቃቂወች እንደአሸን ፈሉና "ያሰብከውን ትሆናለህ፣ ነኝ በል፣ አለኝ በል፣ ደርሻለሁ በል፣ እችላለሁ በል፣ በሀሳብህ መኪና አስነሳ፣ አሉ፤ ወጣቱ የሀሳብ መኪና አስነሳ፤ በሀሳብ ሲጋልብ ራሱጋር ተጋጨ፣ ቤተሰቡ ጋር ተጋጨ፣ አገሩ ጋር ተጋጨ፣ፈጣሪው ጋር ተጋጨ ።  ከሆነስ ሆነና  ለምንድነው  በዚህ ዘመን ይሄ ሀሁሉ አነቃቂ ንግግር ያላነቃን? የእውነት የሆነ ጊዜ ያነቃን ነበርኮ፣ እየቆየ ግን እንኳን ሊያነቃን ያስተኛን ጀመረ፤ እኮ ለምን?

የህክምና ባለሙያወች ከተሳሳትኩ አፉ ብለው ያርሙኝና  በእነሱ ሙያ  Drug tolerance የሚሉት ነገር አለ አሉ፤ በትክክል ከተረዳሁት ለሆነ ህመም የተሰጣችሁ መድሀኒት ከሆነ ጊዜ በኋላ በሽታችሁ ጋር ይግባቡና ፍሬንድ ይሆናሉ። በሽታው መድሃኒቱን ይላመደዋል።ጉቦ እንደበላ ደንብ አስከባሪ በሽታችሁ መንገድ ዳር ሲያሰጣችሁ መድሀኒቱ እንዳላየ ያልፈዋል። ለምሳሌ የእንቅልፍ ችግር ገጠማችሁና በሐኪማችሁ የእንቅልፍ ኪኒን ታዘዘላችሁ እንበል ፤ የመጀመሪያ ሰሞን ድብን ያለ እንቅልፍ ያስወስዳችኋል፤ እየቆየ ሰውነታችሁ ሲላመደው መድሀኒቱን ውጣችሁም ቁልጭ ቁልጭ ስትሉ ታነጋላችሁ። ወይ አይነቱን ወይ መጠኑን ባለሙያ ካልቀየረው በቃ ለውጥ የለም። አይ መጠኑን ራሴ እቀይረዋለሁ ብላችሁ ጨመር አድርጋችሁ ከወሰዳችሁ ደግሞ ትተኙ ይሆናል ግን እንደገና ላትነሱ ትችላላችሁ።

   ወደህይወት ስናመጣው እኛ ኢትዮጵያዊያን በአሁኑ ሰዓት ማንኛውንም ማነቃቂያ ከመላመድ አልፈን እንደዘፈን ሸምድደነው አብረን እየደገምነው ነው። ገና ፊቱን ስታዮት አብራችሁ  "ብሮሮሮሮሮ" አትሉም?!  ለዛ ነው ከነዋሪ መካሪና ዘማሪ የበዛው። የፈለገ ብንመከር ብንዘከር ብንሰበክ ብንወገዝ ወይ ፍንክች። አሁን ሞራል፣ ሐይማኖት፣ የአገርም ይሁን የሰው ፍቅር፣ ይሉኝታ ፣መማር ፣ የራስ ክብር ወዘተ አእምሯችን ተላምዷቸው ተራ ነገር ሁነውብናል።

የሞራል ተቋሞቻችን  በሞራል ድሽቀት ከተራው ህዝብ ቀድመው ባፍጢማቸው ተተክለዋል፤ የትዳር ሰባኪወቹ  ማግባትና መፍታት መድረክ ላይ እንደመውጣትና መውረድ ቀሏቸዋል፤እንደውም የጓዳቸውን ውድቀት እንደባንዲራ በአደባባይ እየሰቀሉ እዮልን ባይ ሆኑ።  አሁን እንደህዝብ ሁለት ነገሮች ብቻ ናቸው የሚያነቁን ወይ (((ብር ማጣት))) አልያም (((ብር ማግኘት))) ይሄ የመጨረሻው ዶዝ(መጠን) ነው!  ሰው ክብሬ፣ ገመናየ ፣ማንነቴ የሚለውን ነገር ሁሉ ይዞ ገበያ ከወረደ ምን ይመልሰዋል?! ከዚህ በኋላስ? ምን ያነቃን ይሆን?  ምክንያቱም በብር የሚመጣ ንቃት በአንዴ አይረካም፤ እንደአደንዛዢ ዕፅ  በየቀኑ መጠኑን እየጨመሩ ካልወሰዱት መጨረሻ የለውም። መመለስም መቀጠልም የማንችልበት አውላላ ሜዳ ላይ የሚያስቀር መርገምት ነው!! ምን ላድርግ ቸገረኝ፣ የማደርገው አጣሁ ልሙት እንዴ ታዲያ  በሚል ሰበብ ከሰውነት ድንበር ከምንርቅ በየግላችን "ይሄንኛው ነገሬ ለገበያ ከሚቀርብ ሞቴን እመርጣለሁ" የምንልለት የሆነ መስመር ልናሰምር ግድ ነው። ሰው ራሱ ወስኖ ያሰመረውን መስመር ከሞት በስተቀር ምን ያሻግረዋል?!

🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

@fker12
┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
አንዴ ብቻ ይድላኝ
አንዴ ብቻ ልረፍ
አንዴ ብቻ ልኑር
አንዴ ብቻ ልትረፍ
ፋታ ብቻ ላግኝ እንደምፈልገው
እንዴት እንደማለቅስ እኔ ነኝ የማውቀው ።

✍️ሀብታሙ ሀደራ

🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

@fker12
┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
Frits Thaulow
"Moonlight in Beaulieu"
1904 #Thaulow
#ስለ_ፍቅር (sele fkr)❤️
Photo
ዛንዛኒንን ነው የምጠራልህ ፡ ሲባል የማይፈራ ህጻን የለም ።
......
የዚህ ልጅ እናት ፡ ይህንን ህጻን የገኘችው ፡ ከአመታት የልጅ ናፍቆት በኋላ ነው ። ከሱ በፊት አምስት ልጅ ወልዳ በሞት አጥታቸዋለች ። እና በመጨረሻ ግን አንድ ልጅ ወለደች ።
ዛንዛኒ ስልት ስም አወጣችለት ። ሆኖም የወለደችው ልጅ ፡ ከሌላው ሰውነቱ አንጻር ሲታይ የጭንቅላቱ መጠን አነስተኛ ነበር ።
ይህም ገፅታው የተለየ አይነት መልክ ይሰጠው ጀመር ።
......
ይህም ገፅታው በመንደሩ ሰወች እንዲያገሉት ምክንያት ሆነበት ። በመንደሩ ውስጥ ህጻናት ሲጫወቱ አይቶ አብሮ ለመጫወት ሲጠጋ ፡ የያዙትን መጫወቻ ጥለው ይሮጣሉ ። ወላጆች ልጆቻቸው ሲያጠፉ ፡ ዛንዛኒን ነው የምጠራልህ በማለት ልጆቻቸውን ያስፈራሩበት ጀመር ።
ይህ የማግለል ነገር በዚህ አላበቃም ። የመንደሩ ሰወች ሲያዩት ጦጣው እያሉ ይሰድቡት ፡ ጀመር ።
ብቸኛ ፍቅር የምትሰጠው ፡ እናቱ ነበረች ። ዛንዛሚ ኤሊ ፡ በእድሜ እያደገ መጥቶ ፡ ትምህርት ቤት የሚገባበት ጊዜ ደረሰ ።
እናቱ ይዛው በአካባቢው ወደሚገኘው ት/ቤት ይዛው ሄደች ።
ሆኖም የመገለሉ ደረጃ ከፍተኛ ሆኖ ነበርና ፡ ወደትምህርት ቤት ለመሄድ ሲሞክር ፡ ተማሪዎች ከጦጣ ጋርማ አንማርም እያሉ ሰላም ነሱት ።
....
ይህ የማግለልና የጥላቻ ሁኔታ ፡ እየባሰ ሲነጣም ፡ ሁሉን ነገር ተወላቸውና ፡ ጫካ ገባና ፡ ውሎው እዛ ሆነ ። ዛፍ ለዛፍ እየተንጠላጠለ ዱር ውሎ ይገባል ።
.......
እናትና ልጅ ፡ በዚህ ሁኔታ ፡ የመንደሩ ሰው አግልሏቸው ፡ ለአመታት ኖሩ ። ሆኖም ግን ታሪክ ሊለወጥ ግድ ሆነና ፡ ይህንን የዛንዛኒን ሁኔታ የሰማ አንድ የአፍሪማክስ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ወደ መንደራቸው መጥቶ ፡ የደረሰባቸውን መገለልና ፡ የድህነት ህይወታቸውን በተመለከተ ፡ አንድ ሰፊ ዶክመንተሪ ተሰርቶ በቴሌቪዥን ተላለፈ ።

ይህ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሚሊዮኖች ተመለከቱት ። ከቀናት በኋላም ዛንዛኒ ኤሊንና እናቱን ለመርዳት የጎ ፈንድ ሚ አካውንት ተከፈተ ።
.......
በአውሮፓ አሜሪካና አፍሪካ የሚገኙ ፡ ፕሮግራሙን የተከታተሉ ሁሉ ፡ ለዚህ ቤተሰብ ደግነታቸውን አሳይተው ብዙ ገንዘብ ተሰበሰበ ።
........
ህይወታቸው ተቀየረ ። ዘመናዊ ቤት ተገነባላቸው ። ለእናትየው የስራ እድል ተከፈተላት ።
ያ ፡ ጦጣው እየተባለ ጫካ የሚውለው ዛንዛኒ ኤሊ ፡ ለአመታት አብራው ያረጀችውን አሮጌ ልብስ ጣለ ። በደርዘን የሚቆጠሩ ዘመናዊ ልብሶችና ጫማዎች እየቀያየረ የሚለብስ ፡ ዘናጭ ሰው ሆነ ።
ትምህርት ቤት ገባ ። አስጠኚ ተቀጠረለት ። ትምህርት ቤት የሚሄደው በሹፌር ነው ። አሁን ያ የድሮው ማግለል የለም ።
የመንደሩ ልጆች ፡ ብስክሌት እንዲያስነዳቸው የሚከቡት ። ከሱ ጋር ለመጫወት በልጆች የሚከበብ ሰው ሆኗል .
ይህን በተመለከተ እናትየው ስትናገር ፡ ፈጣሪ አንድ ቀን ታሪካችንን እንደሚለውጠው አምን ነበር ብላለች ።
.......
ደጋግና ፡ መልካም አሳቢ ሰወች እስካሉ ድረስ ተባብረው የማይቀይሩት ነገር የለም ።

©በዋሲሁን ተስፋዬ
በአንድ ወቅት ስሙ የገነነው ታላቁ ፈላስፋ ዲዮጋን አለምን ከሞሏት ሚሊዮኖች ሰዎች ውስጥ ሰው ፈልጎ ቢያጣባት በየገበያውና በየሰርጣ ሰርጡ በቀን በጠራራ ጸሀይ ወጣ።

የቀን ጋኔን፣ የአለምን ማጋነንና ሃሜት ሳይፈራ ፋኖሱን አብርቶ ሰው ፍለጋ ጀመረ። ግን ዲዮጋን የፋኖሱን መብራት በላዩ አብርቶ ራሱን ተመልክቷል? ራሱን ሰው አድርጎ ነው ሰው ፍለጋ የወጣው? በአለም ፈልጌ አንድ ሰወ አጣሁ ያለውስ ራሱም ሰው ሆኖ አልተገኘም ይሆን? በርግጥ በዛን ዘመን በአለም ከነበሩ ሚሊዮኖች አሊያም መቶ ሺዎች አሁን ላይ በራሱ ከቢሊዮኖች ውስጥ ሰውን ማግኘት ከባድ ሆኗል፤ ሰው የሆነን ሰው ከመፈለግ የማያልቀውን ህልቁ መሳፍርት መላው ዩኒቨርስን አርሶና አዳርሶ፤ አረስርሶ መጨረስ ይቀላል።

እያንዳንዳችን ሰው ለመሆን የምንሞክር የሰው ምስል ፎቶ ነን እንጂ 8 ቢሊዮን ህዝብ አለምን አልሞላትም።

በኢየሩሳሌም የነገሰው ንጉሥ "ንጉሥ ዳዊት " ለልጁ ኑዛዜ ሲያስተላልፍለት "ልጄ ሆይ ሰው ሁን!" ነው ያለው።

ወደ ሰውነት ጉዞ መጀመር አለብን ባይ ነኝ። የስታቲስቲክሱን ነገር ለጊዜው ወደጎን ብለነው "በቁጥር አለም ይህን ያህል ሰው ያዘች " ብለን ከመለፈፋችን አስቀድመን ሰው የሆነና ሰው ያልሆነውን እንደ ዲዮጋን ማሿችንን ከራሳችን ጀምረን እያበራን "የሰው ያለህ" ማለት ይገባናል።

የሀይማኖት ተቋማት በእኛ እምነት የሚያምኑ "ሚሊዮኖች " አሉ ብለን ከመደስኮራቸንና ቁመት ከመለካካታችን አስቀድመን " ሰው" የተባለውን ፍጡር ከጥልቁ ጨለማ አስሰን ማግኘትና ሰውነትን ማጎልመስ ይገባናል ከሚሉት ነኝ።
✍️ሀብታሙ ሀደራ

🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

@fker12
┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ሀሳብ አስተያየቶይ 🫴@selefker12_bot
አሁን ልሸውድህ ነው!እየነገርኩህ እንኳን እሸውድሃለው!‼️ከተሸወድክ ግን ቻናሉን #share ማድረግ ግዴታህ ነው‼️

👉አልሸወድም ካልክ ማንበብ ትችላለህ




















ሽወዳ በየቀኑ በየጊዜው የሚከወን ድርጊት ነው::በተለያዩ ሀገራቶች እንደሚፈጸም የሚታወቅ ቢሆንም በያንዳንዱ ሃገሮች ደግሞ ለየት ይላል

ለምሳሌ በኛ ሃገር በአንዲት ግዛት አንድ ሰው ለጨዋታ በሚልና በአስቂኝ ሁኔታ ሰውን ከሸወደ 1368832789960632 ገደማ ያክል ይሸለማል

አሁን መሸወድህ ላረጋግጥልህ ??

        💥ማረጋገጫ 💥

1)ከላይ ያለውን ቁጥር ሙሉ በሙሉ አላነበብከውም……ማለት ሳታነብ ዘለልከው አይደል??

2)በዚህም ምክንያት "ኦ" የተባለችዋን የእንግሊዘኛ ፊደል እንዳለች አላየህም😳







ባክህ የለችም ተመለስ 😁

አሁን መሸነፍህን ካመንክ
             #Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ሀሳብ አስተያየቶይ 🫴@selefker12_bot
በወንዝ ዳር በጫካ ውስጥ የሚኖር ዝንጀሮ ነበር። አንድ ቀን ዝንጀሮው አንድ አሳ በወንዙ ውስጥ ሲዋኝ አሳው እየታገለ እንደሆነ አሰበ። ዝንጀሮው ርኅራኄ ስለተሰማው ዓሣውን ለማዳን ወሰነ። በፍጥነት ከዛፉ ላይ ወረደና እጁን ዘርግቶ ዓሣውን ከውሃ ውስጥ በማውጣት ወደ ላይ ተመልሶ ዓሣውን በዛፍ ቅርንጫፍ ላይ አስቀመጠ፡፡ ከዚያም ዓሣው በኃይል ተንፈራፈረና ብዙም ሳይቆይ ሞተ። ዝንጀሮው ግራ ገባው እሱ መርዳት ብቻ ነበር የፈለገው።

ይህ ታሪክ የተለያዩ አመለካከቶችና አረዳዶችን ያሳያል። ማለትም ዝንጀሮው በመሬት ላይ የሚኖር ፍጡር በመሆኑ ሁኔታውን ከአካባቢው እና ከልምዱ በመነሳት ስለገመተ የዓሳውን መዋኘት እንደ መታገል ወይም እንደተሰቃየ ይተረጉመዋል። ዓሳዎቹ በውኃ ውስጥ ሲሆኑ አየርን እንደማይተነፍሱ ተመለከተና ዓሣው አደጋ ላይ እንደሆነ ገመተ። ለማገዝ ባደረገው ጥረት አሳውን ከተፈጥሮ አካባቢው አውጥቶ ወደ ራሱ አካባቢ በማስገባቱ ለዓሣው መጥፋት ምክንያት ሆኗል።

ይህ ታሪክ ለአንድ ሰው ትክክል ወይም ተፈጥሯዊ የሆነው ነገር ማድረግ የግድ ሌሎችን ይመለከታል ብሎ ከማሰብ መጠንቀቅ እንዳለብን ያሳያል። አንዳንዴ ፍላጎታቸውን፣ ተፈጥሮአቸውን ወይም አካባቢያቸውን በትክክል ሳንረዳ የራሳችንን አመለካከቶች እና አኗኗራችንን በሌሎች ላይ መጫን ለአደጋ ይዳርጋል።

ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው በአለም ውስጥ የራሱ የሆነ ልዩ ባህሪ አለውና ሁሉም ሰው እኔን ምሰል ወይም የእኔ ብቻ ተቀበል ማለት የለበትም!

#Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ሀሳብ አስተያየቶይ 🫴@selefker12_bot
እኔ እና ብዕሬ

አትዘንጋ፤
በዚህ በአለንባት ምድር ምንም ነገር የኔ የምትለው ለዘለቂታ ካንተ ጋር የሚቆይ ነገር የለም።

አንድ ወፍ በህይወት እያለች ጉንዳንን እያጣጣመች ትመገባታለች፤ጉንዳን ደግሞ በተራዋ ወፎ ስትሞት ጠብቆ አጣጥሞ ይስለቅታታል፡፡ ይገርማል፤ጊዜና ሁኔታ ተለዋዋጭ ናቸው፡፡ በህይወት ማንንም አሳንሰህ አትይ ወይም አትጉዳ። ዛሬ አንተ ለራስህ ጥንካሬህ ይታይ ይሆናል ግን አንተ ሳትሆን ጊዜ ከአንተ የላቀ ጠንካራ መሆኑ መዘንጋትህ ይመስለኛል።

በአንድ የዛፍ ግንድ ብዙ የክብሪት እንጨቶች ይመረታል ግን አንድ የክብሪት እንጨት በሚሊዩን የሚቆጠሩ ዛፎችን ታቃጥላለች፡፡

ስለዚህ አንዲት መጥፎ፣መልካም ያልሆነ ሃሳብ(negatuvity thought) ወይም ነገር ለብዙ መልካም ወይም ጥሩ ሃሳቦች (positivity thought) ማጥፊያ እንዳትሆን በህይወትህ አትፍቀድላት። ስለዚህ መልካም ሁን እንዲሁም መልካም አድርግ።
መልካም ዕለተ አርቢት ለዕለት ቅዳሚት አሸጋገረን፡፡

ቤስቶ(besto)


#Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ሀሳብ አስተያየቶይ 🫴@selefker12_bot
[አንድ ግጥም ፃፊ]

ዓይን ያልመረመረው፣
ጆሮ ያልቆጠረው፣
ምላስ ያልነካካው፣
እጅ አልፎ ያልለካው፣
ከቆዳ ዝላይ ሂያጅ፣
አንድ ግጥም ፃፊ፤
ገሎ ማዳን ልመጅ፣
ከእይታ ግዘፊ፣
ብራና አለ ልብሽ፣ እጄን ተደገፊ።

ሰጠሁሽ ዋርካውን፣ ለቀለም ውቀጭው
ጥላው አይምሽበት፣ ማልደሽ አስቆርጭው
እጄን በሴት አንገት፣ የቆየ እንዳያየው
ልቤን እንደ በካር፣ ቀይ ደም እለቢው።

ሁለት ቀለም አለሽ፣
የዋርካ ለነጩ፣ የልቤ ቀይ ደማቅ
ሁለት ጀብዱ ሰራሽ፣
ጎንደር እጅ ሰጠሽ፣ ጃንተከል እስኪደርቅ
በቃ አሁን እረፊ፣
እስኪ ግጥም ፃፊ
ብራና አለ ልብሽ፣ እጄን ተደገፊ።

አሁን አየ አሞራ፣ ሟቿን ገዳይ አለ
አሁን ዞረ ንስር፣ ግዳይ ተቀበለ
"ዋ ጀግና ዋ ገዳይ
እስኪ አዝልቋት ትታይ
ሽኝቷ እስከነፍሱ፣ ባሩዷ የቀለም"
ይሸለል ይፎከር፣ ይንገሩልሽ 'ላለም።

በቃ አሁን እረፊ፣
አንድ ግጥም ፃፊ
ብራና አለ ልብሽ፣ እጄን ተደገፊ
ቃላት ያከንፋሉ፣ ቃላት ይሰብራሉ
ሆሄያት ያናግራሉ፣ሆሄያት ይቀብራሉ
ህመምን አስታመው፣ ፍቅርን እስኪያበቃ
ታምሚያለሁ መሰል፣ ወደቅኩኝ እንደ እቃ
እጄን ትራስ ውሰጅ፣ ወንድነቴ አበቃ።

©ክፍሌ

#Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ሀሳብ አስተያየቶይ 🫴@selefker12_bot
#ከመፅሃፍ_ገፆች

ይቺን አስተማሪ ግጥም በቃሉ የሚችላት?

"ሁለቱ መላጦች"

ሁለቱ መላጦች

ሁለት በራ ሠዎች ሲያልፉ በጎዳና
ዕቃ መሬት ወድቆ ብልጭ ሲል ያዩና
ተሽቀዳድመው ሄደው ከቦታው ሲደርሱ
ተፎካከሩበት ሁለቱም ሊያነሱ።

በኋላም ተማተው በጥፊ በጡጫ
አንደኛው ነጠቀ በጉልበቱ ብልጫ
አገላበጠና ቢመለከት ፈጥኖ
ዕቃውን አገኘው ማበጠሪያ ሆኖ።

እስኪ ሁላችሁም በሉ ፍረዱት
እሱ ራሱ በራ ፀጉር የለበት
ሮጦ ተማቶ ቀምቶ ቢያመጣ
ምን ያደርግለታል ሚዶ ለመላጣ?


ሰዎች ይፋጃሉ አስበው ሳይፈርዱ
የተጣሉበትን ጥቅሙን ሣይረዱ
ከመጣላት በፊት ከመቀያየም
የነገሩን ፍሬ መረዳት መልካም።

#Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
🕑የቤተሰብ ሰዓት

🌊 አንድ ነገር ልንሞክር ነው ። አይምሯችሁ ላይ የሚፈጠረውን ተዓምር በማየት ፣ እናንተ እራሳችሁ ምን እንደጠቀማችሁ ትነግሩኛላችሁ! The power of Now - approach ነው የምንጠቀመው!

📮ብቻችሁን ብትሆኑ አሪፍ ነው ፣ በመጀመሪያ ዘና ብላችሁ ለመቀመጥ ወይ ደግሞ ጋደም ለማለት ሞክሩ!አይናችሁን ክደኑት ፣ አንደኛው እጃችሁን ልባችሁ ላይ አርጉት! ከዛን በጥልቀት መተንፈስ ጀምሩ ፣ በጆሯችሁ የሚመጡ ነገሮችን በሙሉ ስሙ! ስለምትሰሙት ነገር አታስቡ!ዝም ብላችሁ ስሙት! በጆሯችሁ ከሚመጣው ድምፅ ጋር እንዲሁ ትንፋሽ ወደ አፍንጫችሁ ሲገባ Feel አርጉት ፣ በ አፋችሁ ሲወጣም እንዲሁ የወላፈኑ ግርፋት ይሰማችሁ! በእጃችሁ የልባችሁን ትረታ አዳምጡ! ስለ ፍቅረኛችሁ አታስቡ ፣ ስለ ኑሮ አታስቡ ፣ ምንም አታስቡ ፤ ለዛ ቅፅበት ብቻ ስሜት ይኑራችሁ! በጆሯችሁ ድምፆች ሲገቡ የሰማችሁ ፤ በገላችሁ ላይ አየሩ ሲዳብሳችሁ ይሰማችሁ ፣ የልባችሁ ትርታ በእጃችሁ ይሰማችሁ ፣ ትንፋሻችሁ ሲገባ ሲወጣ ይሰማችሁ! ሌላ ምንም አታስቡ ፣ የነገርኳችሁን ስሜቶች ብቻ አዳምጡ! ይሄን ማረጋችሁ ሞኝነት አደለም ፣ የሚፈጠረውን ተዓምር ታያላችሁ ፣ የሩቅ ምስራቅ መነኩሴም ላረጋችሁ አደለም ፣በሳይንስ የተረጋገጠ Mindfulness State ነው! ለ 5 ደቂቃ ብቻ አድርጉት! ከዛን የተሰማችሁን መታችሁ ከስር Comment ላይ ትነግሩኛላችሁ! ከመጀመራችሁ በፊት ለ5 Minute የሚሆን Alarm ሙሉ ፣ ከዛ ጀምሩ! አሁኑኑ ሞክሩት

#Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
በትንሽ መጀመርና ትልቅ ማለም አንዱ ባንዱ ውስጥ የተደበቁ የስኬት ምስጢሮች ናቸው። ትልቅ ህልም ይዘው አንድም ሳይሠሩ የሚሞቱ ሰዎች የውድቀታቸው ምስጢር ብዙ ጊዜ ትልቁን ህልማቸውን በሚመስል ወይም ለዚያ በሚያዘጋጃቸው ነገር ላይ ያጠፉት ጊዜ ስለሌለ ነው። በትንሽ ነገር ላይ ተጣብቀው እንደማቀቁ የሚሞቱም ብዙ ሰዎች ትልልቅ ነገር ሊሠሩ እንደሚችሉና እንደሚገባቸው ማመን ስለሚሳናቸው ነው። ሌላው ቁልፍ ግን ሰዎች ባላቸው ነገር አሁኑኑ ከመጀመር ይልቅ ነገን ሲጠብቁና የተሻለን ቀን ሲናፍቁ ዕድልም ዕድሜም ያመልጣቸዋል። በትንሽ አሁን መጀመርና ለትልቅ ነገር እየተዘጋጁ ለነገ ማቀድ በርግጥም ጥበብ ነው።

#Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
ስፔናዊው አትሌት ኢቫን ፈርናንዴዝ እና ኬንያዊው አትሌት አቤል ሙታይ በአንድ የሀገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር ላይ ለሜዳልያ ፉክክር እያደረጉ ነበር።

ኬንያዊው አቤል ሙታይ ውድድሩን እየመራ ስፔናዊው ኢቫን ፈርናንዴዝ ደግሞ ሁለተኛ ሆኖ እየተከተለው ትንቅን ላይ ነበሩ።

በድንገት ግን ከውድድሩ ፍጻሜ መስመር ላይ ሊደርሱ በግምት 10 ሜትር ገደማ ሲቀራቸው ኬንያዊው የውድድሩ መሪ አቤል ሙታይ ውድድሩን ያጠናቀቀ መስሎት በስህተት ውድድሩን አቋርጦ ቆመ:: ይህንን ክስተት የተመለከተው ስፔናዊው ሯጭ አቤል ሙታይ ውድድሩን እንዲቀጥል እና መስመሩን እንዲያቋርጥ ከኃላው ሆኖ ይጮህበት ጀመር

የስፓኒሽ ቋንቋ ጆሮውን ቢቆርጡት የማይሰማው አቤል ሙታይ ምን እንደተፈጠረ ሊገባው አልቻለም:: በመሆኑም ስፔናዊው ሯጭ ኢቫን መስመሩን አቋርጦ ውድድሩን ከማሸነፍ ይልቅ አቤል ሙታይን በመግፋት ውድድሩን አሸንፎ የወርቅ ሜዳልያውን እንዲያሸንፍ አደረገው።

ውድድሩ መጠናቀቁ ተከትሎ አንድ ጋዜጠኛ ለኢቫን ጥያቄ አቀረበለት ...

"ለምን እንደዚያ አደረግክ?"

"የእኔ የህይወት ህልም አንዳችን ሌላችንን በመግፋት አሸናፊ እንድንሆን ማገዝ ነው:: ህልሜ እርስ በእርሱ ተደጋግፎ አሸናፊ የሚሆን ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት ነው" ሲል መለሰለት።

"ለምን ኬንያዊው እንዲያሸንፍ አደረግክ ?" ደግሞ ጠየቀው

"እኔ እንዲያሸንፍ አላደረግኩትም:: እሱ መጀመርያም ሊያሸንፍ ነበር"

"ግን እኮ አሸንፈህ የወርቅ ሜዳልያውን ማጥለቅ ትችል ነበር" ጋዜጠኛው አሁንም ጠየቀው

"ድል የማድረግ መርሁ እና ጣእሙ ምንድነው? እንዲህ ሆኖ የማሸንፈው ሜዳሊያ ክብሩ ምንድነው? እናቴ ይህንን ስታይ ምን ትለኛለች?" ሲል ጋዜጠኛውን አስደመመው

Moral of the story 👉አሸንፍ...ሌሎችም እንዲያሸንፉ #share አድርግ
ጋሽ ፕሮፌሰሩ

ፕሮፌሰሩ በባቡር ጉዞ እያደረገ ነው። በመንገዱ ተሰላችቶ ስለነበር ጊዜውን ለማሳለፍ የጨዋታ ሀሳብ ለማቅረብ ዳዳውና ከጎኑ ለነበረው ገበሬ ዞር አለና "አንድ ጥያቄ እጠይቅሃለሁ" "መመለስ ካልቻልክ 5 ዶላር ትሰጠኛለህ። ከዚያም አንድ ጥያቄ ትጠይቀኛለህ። መልስ መስጠት ካልቻልኩ 500 ዶላር እሰጥሃለሁ። ምን ትላለህ?" ይለዋል ገበሬውም በመስማማት እሺ ይለዋል።
ፕሮፌሰሩ “በምድር እና በጨረቃ መካከል ያለው ርቀት ምን ያህል ነው?” በማለት ጥያቄውን ይጀምራል። ገበሬው ዝም ብሎ 5 ዶላር አውጥቶ ለፕሮፌሰሩ ሰጠው።

አሁን ተራው የገበሬው ሆነ።
እንዲህም ሲል ጠየቀው “ተራራ ሲወጣ ሶስት እግር ያለው፣ ሲወርድ አራት እግር ያለው የትኛው እንስሳ ነው?” ሲል ጠየቀ።
ፕሮፌሰሩ ከበደው ሆኖም በቻለው መጠን ምክንያታዊ ማብራሪያዎችን ለመፈለግ ሞከረ ማስታወሻ ደብተሩን ገለጠ መልስ ግን ማግኘት አልቻለም። ተበሳጨና 500 ዶላር ለገበሬው አስረከበ። ገበሬው ገንዘቡን በፈገግታ ወስዶ ለማረፍ ወደ ኋላ ሄደ። የማወቅ ጉጉት በእጅጉ ያደረበት ፕሮፌሰሩ ገበሬውን ከእንቅልፉ ቀስቅሰውና “እሺ፣ የትኛው እንስሳ ነው?” ሲል ጠየቀው። ገበሬው ዝም ብሎ 5 ዶላር አውጥቶ ለፕሮፌሰሩ ሰጠውና ተመልሶ ተኛ።

ጌቱ ወንድወሰን

#Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
መተው ወይም መልቀቅ ወደ ፈውስ የሚወስድ እርምጃ ነው :: በሕይወታችን ያጋጠሙን መጥፎ ነገሮች አሳምመውን ያለፉ ወይም አሁንም እያሳመሙን ያሉ ይሆናሉ :: ሀዘን ቢሆን ፣ በሚወዱት በሚያምኑት መከዳት ፣ ቢሆን ወይም ኪሳራ ቢሆን ሌሎችም ህመሞች ቢሆኑ በውስጣችን ይዘን በተብሰለሰልን ቁጥር አየበሉን እያሳሱን እየቆረጡን ነው የሚሄዱት ::

መተው ወይም መልቀቅ ማለት የተፈጠረውን ነገር እንዳልተፈጠረ መርሳት አይደለም ነገር ግን ለመርሳት መንገድ መክፈት ፣ ለአዲስ ሀሳብ ለአዲስ Energy ቦታ ማስለቀቅ ፣ ለለውጥ ልብን መክፈት ማለት ነው :: ከአለፈ ነገራችን ጋር ተጋብተን የምንኖር ከሆነ ቁስላችንን መቼም አይሽርም ህክምና ያስፈልገዋል መድሀኒቱም መልቀቅ ወይም መተው ነው ::

Sometimes letting go is the way to heal.


#Share

┄┄┉┉✽‌»‌🌺✿»🌺✽┉┉┄┄

         ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
           @fker12  @fker12
         ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
እድሜህ ምን አስተማረህ ...??

ሁላችንም ባልተመረመርናቸው በሽታዎች የምንሰቃይ ምስኪኖች ነን ፤ እድሜያችን ያስተማረንን እንኳ የማናውቅ ።

ብዙ ያልተጠየቅናቸው ጥያቄዎች አሉብን በግዜ ሂደት ህመም እየሆኑ እኛነታችንን ከእግዜር የነጠሉ

ብንጠየቅም
ደሞ መልስ የማናገኝላቸው ሺህ ጥያቄዎች ...

እኔ እድሜዬ መዳብ የሆነብኝን ወርቅ ከሔደ ደግሜ እንደማላገኝ አስተማረኝ..እናንተስ
ለምንድነው ከስራ ይልቅ ቢዝነስ ያልመረጥኩት ?😕

በቻይና ውስጥ በጣም ሀብታም ሰው "ሙዝ እና ገንዘብ በዝንጀሮዎች ፊት ብታስቀምጡ ዝንጀሮዎች ሙዙን ይመርጣሉ ምክንያቱም ገንዘብ ብዙ ሙዝ ሊገዛ እንደሚችል ስለማያውቁ ነው. እንዲያውም ሥራ እና ንግድ ለሰዎች ብታቀርቡ, መስራትን ይመርጣሉ ምክንያቱም አብዛኛው ሰው ቢዝነስ ከደመወዝ የበለጠ ገንዘብ እንደሚያስገኝ ስለማያውቅ ድሆች ከሚሆኑባቸው ምክንያቶች አንዱ የንግድ ሥራ እውቅና ባለማግኘታቸው ነው። እድሎች በትምህርት ቤት ውስጥ ብዙ ጊዜ ያሳልፋሉ, እና በትምህርት ቤት ውስጥ የሚማሩት ለራሳቸው ከመስራት ይልቅ ለደሞዝ መሥራት ነው።
2025/02/21 09:47:13
Back to Top
HTML Embed Code: