FKRNATAFETRO Telegram 583
አፋልጉኝ!

የዛሬ አራት አመት አካባቢ በባስ ወደ መቀሌ እየሄድን ረዳቱ ፌስታል አውጥቶ ስለ ሚካኤል ብሎ ገንዘብ መጠየቅ ጀመረ ።አማኙ ተሳፋሪ በሚዞረው ፌስታል ውስጥ የአቅሙን ከተተ ። ብሩ ተሰብስቦ እንዳለቀ ረዳቱ ቆጥሮ በፌስታሉ ቋጠረው ።

የተወሰነ መንገድ እንደሄድን መስኮት ከፍቶ ገንዘቡን አርቆ ወረወረው። ግራ ገብቶኝ ለመያዝ እየቃጣኝ ከመቀመጫዬ ብድግ አልኩ ።እንግዳ መሆኔንና መገረሜን አውቀው መንገደኛ ሰው ሲያልፍ አንዱ ላንዱ እያቀበለ ምፅዋት ለተሰጠበት ቤተክርስቲያን እንደሚያደርሱት በእርግጠኝነት ነገሩኝ ።

ከመካከል አንዱ የሳተ ቢወስደውስ?፤ ጥያቄዬ ነበር ።
"እምነቱን የሚያፈርስ የለም ፤ እግዜር ያየዋል ።ስለዚህ ማንም የሱ ያልሆነን አይወስድም ።የእግዜር እንደሆነ ያውቃል ።ይታመናል" አሉኝ። ተገርሜ በአዕምሮዬ ገንዘቡ መሬት ላይ ወድቆ ሊያገኙት የሚችሉ ሰዎችን ማንነትና ገንዘቡን ከማግኘታቸው ከደቂቃ በፊት ሊሆኑ የሚችሉበትን ሁኔታና ኑሮ በየተራ ፈጥሬ እየሳልኩ ታሪክ እየሰራሁ ተጓዝኩ።
ከአመት በኋላ በዶክመንተሪ ፊልም ስራ በዛው መስመር ተገኝተን ከሌላ ባስ የተወረወረ ገንዘብን ያገኘ ሰዉ እየተቀባበለ ሲያደርሰው ተመለክትን፣ ተደነቅን ።

በልጅነቴ ከእናቴ ጋር ዜና ማርቆስ የሚባል ገዳም እንሄድ ነበር ።እናቴና ወንድሜ አመት ጠብቀው ዛሬም ይሄዳሉ ። ወደ ገዳሙ ለመድረስ አንድን ሰርጥ ማለፍ ያስፈልጋል ።ሰርጡ ግራና ቀኝ ጥልቅ ገደል ነው ።ቁልቁለቱ ያንሸራትታል ።አንድ ሰው ነው የሚያሳልፈው ።የእንፉቅቅ ነው የሚወረደው ።ሰርጡ ጫፍ ስንደርስ የማናውቃቸው ልጆች የተጓዡን ቦርሳና ሻንጣ ለማገዝ ይቀበላሉ ። ከእናቴም ላይ ሻንጣዋንና ቦርሳዋን አንድ ልጅ ተቀበላት ።
ከሰርጡ ወደ ገዳሙ ለመድረስ ለበረታ ሶስት ለደከመ አራት ሰአታት ይፈጃል ።በመንገዳችን ሁሉ ያ ሻንጣችንን የተቀበለንን ልጅ ስላላየሁት በአዕምሮዬ ሻንጣችንን ምን እንዳደረገው እያሰላሰልኩ የገዳሙ መግቢያ ጋር ደረስን ።

ገዳሙ መግቢያ ላይ ስንደርስ ሻንጣችንን የያዘው ልጅ የሌሎች ተጓዦችን ሻንጣ ከያዙ ልጆች ጋር በረድፍ ተቀምጦ ሻንጣችንን ይዞ እየጠበቀን ነው ።
እግራችንን በአባቶች ታጥበን ንብረታችንን ተረክበን ወደ ገዳሙ ገባን።ልጆቹ ሳንቲም አልተቀበሉንም ። ሽልማታቸው ምርቃት ነበር ።
ያ እዛ ገዳም ስንሄድ ዕቃ የሚይዝልን ልጅ ዳዊት ይባላል ።ወደ አዲስ አበባ መጥቶ እኛ ቤት አድጎ ትምህርት ተምሮ የራሱን ኑሮ እስኪያበጅ ድረስ ወንድም ሆኖኝ አብረን ኖረናል።
ዛሬ ላይ ሆኜ የከተማዬን መተራመስ፣ የእምነታችንን መጉደል ሳስተውል፤ የአገር ልጅ የአገር ልጅ ላይ እጁን ሲያነሳ፣ ወንድም ወንድሙን ሲገድል ስመለከት አዝንና ደሞ በሌላ መልክ እንኳን አገሬውን በመንጋ ሊያጠቃ፣ እንኳን ለሌላው ስጋትና ፍርሀት ሊሆን መንገድ የወደቀን በእምነት የሚያስረክብ በአደራ የሚጠብቅ ህዝብ እንደነበር እንደሆነም አስብና በረታለሁ ።
ይችኛዋን ኢትዮጵያ ፈልጋታለሁ ። እናፍቃታለሁም ።
አፋልጉኝ!

✍️ጥሩ ዘር

@fkrnatafetro

tgoop.com/fkrnatafetro/583
Create:
Last Update:

BY ፍቅርን በመፃፍት

Share with your friend now:
tgoop.com/fkrnatafetro/583

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

best-secure-messaging-apps-shutterstock-1892950018.jpg Write your hashtags in the language of your target audience. To view your bio, click the Menu icon and select “View channel info.” A vandalised bank during the 2019 protest. File photo: May James/HKFP. How to Create a Private or Public Channel on Telegram?
from us

Telegram ፍቅርን በመፃፍት
FROM American