tgoop.com/fkrnatafetro/593
Last Update:
#ትዳር
====================
ሚስትህን ካስረገዝካት በኋላ እንዴት እንደ ኮረዳዎች አማላይነት እንዲኖራት ትጠብቃለህ? አስረገዝካት እኮ ከወለዳችሁ በኋላም አንተና ልጆችህ ለመመገብ ደፋ ቀና ትላለች ብትታመም ራሱ የቤቱ ስራ አይቀርላትም ኩሽና ብቻ ዓለም እንዲሆናት ፈርደህባታል ሚስትህን የዚህ ህዝብ ኋላቀር ባህል ሰለባ አድርገሃታል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ብዙ ሸክም ችለዋል በተለይ ያልሰለጠነ ሰው ያገቡ ሴቶች ደህና መልበስ መሰልጠን እየመሰላቸው፣ ደህና መኪና ማሽከርከር መሰልጠን እየመሰላቸው ብዙ ሴቶች ተጎድተዋል ባል ሲመርጡ ህልማቸው ተበልተዋል።
ብር ያለው ወንድ ማግባት ጥሩ ነው ብር ስላለው ግን አይደለም ያ ብር ማንነቱን ደብቆበት እንደ ልቡ ይሆናል
ብር የሌለው ሰው (ወንድም ሴትም) ብዙ ጊዜ ራሱን ለመሆን ይቸገራል
የፊታቸውን መከፋት በሜክአብ የሸፈኑ በትንሽ ነገር ብዙ የሚበሳጩ ሴቶች ታክሲ ውስጥ ታገኛለህ እነሱ ህልማቸው የተበሉ ሚስቶች ናቸው ደግሞ አሉ መጠጥ ቤቶች ውስጥ በአማላይ ኮረዶች የተሞሉ እዚያ የሚያንዣብቡ ወንዶችም አሉ እነሱ እነዚያ ያልሰለጠኑ ባሎች ናቸው የሚስቶቻቸው አናት ላይ ወጥተው የረዘሙ
ሁለቱም ተጋቢዎች (ወንዷና ሴቱ) ያሳዝናሉ የእውቀት እጥረትና የኋላቀር ባህል ሰለባ ናቸው ትዳር ጥሩ ነው የእውቀት እጥረትና የኋላቀር ባህል ሰለባ ከመሆን ራስን መጠበቅ ግን ያስፈልጋል
ካነበብኩት
BY ፍቅርን በመፃፍት
Share with your friend now:
tgoop.com/fkrnatafetro/593