Telegram Web
💞ፍቅር በተላላቆች እይታ💕

1"ፍቅር ያለ እምነት ነፋስ ላይ
እንደተቀመጠ ሻማ💈 ነው! ( ቶማስ
ሚድልተን)

2 "በፍቅር ለሚወድቁ ሰዎች የመሬት
ስበት በፍፁም ተጠያቂ
አይደለም!" (አልበርት እንስታየን


3 "ፍቅር በተፈጥሮ የሚታደሉት ሲሆን ፣
የተሳካ የሚሆነው በቅንነት ጠበቅ
አርገው ሲገፉበት ነው (አሪስቶትል)

4" ፍቅር በእልህ ፣ በችኮላ ፣ በንትርክና
በግዴታ የሚያሸንፉት ቀላል ስሜት
አይደለም !!!" (አጋታ ክርስቲ)

5"በፍቅር ውስጥ ያለው ድል ማሸነፍ
ነው!!" (ናፖዎሊዩን ቦናፓርት)

6"ፍቅር የቡድን ስራ አይደለም!!!"(አሰፉ
ጉያ)

7 "ፍቅርን ፍቅር የሚያሰኛት አብረው
ያሳለፉት ረዥም ጊዜ አይደለም ፣
ፍቅር የምንላት የአንድ ደቂቃ ጉዳይ
ቢሆንም ጣዕሟ ለዘላለም የማይረሳ
ከሆነ ፣ እስዋን ነው ፍቅር የምንላት !!!!!"
(ደራሲ በዓሉ ግርማ)

8 "ፍቅር ገንዘብ ማስቀመጫ ኪስ የሌለው ራቁቱን የሆነ ልጅ ነው!!
"(አቪድ)

9 "ፍቅር ጥልቅ ቦታ እንጂ በከንፈር
ውስጥ ብቻ ሊኖር አይችልም!!!" (ቴኔሰን)

10 "ፍቅር ውሻ እንኳን በግጥም
እንዲጮኽ የሚያረግ ኃይል
አለው!!" (ፍራንሲስ ቦም)

🍁💙🧢 በፍቅር ያኑረን !!!!!!!!🌿

👇 JOIN US 👇

@fkrnatafetro
>አፍቃሪንስለማፍቀሩ ብትነቅፈው
ማፍቀሩን ይጨምራል >>


💔ፍቅር ቤቱን የሠራበት ልብ የታደለ ነው።
💔ፍቅር ከአለም ጭንቀት ሁሉ ማረፌያው ነውና ።

💔ፍቅር የያዘው ሰው ስለራሱ መጨነቅ ያቆማል ።

የተራራ ክምር ለአሱ እንደገለባ ብናኙ ነው። ታዲያ አፍቃሪን ስለ ማፍቀሩ ብትነቅፈው ማፍቀሩ አይጨምርበትም ትላለህ!



@fkrnatafetro
የሉሲፈር : በትር !
----------//--------
ክፍል :-(37)



ቅድስት እንደምንም ብላ ከወንበሩ ቀና በማለት የመኪናውን ኪሶች በረበረች እምታቃቸውን ጥቂት እክብሎች እና ማነቃቂያ መርፌዎች አገኘች ፈጥናም

በ መኪናው ወንበር ቀበቶ ክንዱዋን አሰረች እናእራሱዋን ወጋች አፍታም ሳትቆይ ከነበረችበት ነብስ ዘርታ መኪናውን ለኔ ስጠኝ ብላ ከ ዋሲሁን ተቀበለችው መኪናዋን ወደ አና ፖሊን ሜሪ ላንድ አቀኑ ለ ሁለት ቀናት

ከቆዩ በውኃላ እራሳቸውን ቀይረው ሀሰተኛ ፓስፖርት በማዘጋጀት ወደ ጆርጂያ ውስጥ ወደ እምተገኝው አትላንታ አቀኑ ሁለት ቀናትንም እዛው አሳለፉ።

ዋሲሁን ከቅድስት ጋር ባሳለፋቸው ሁለት ቀናት ፍጹም ሌላ ሴት ሆናበት ነበር የቆየችው አዲስ ሴት ፍጹም ልበ ሙሉ ደስተኛ ሴት ፈጽሞ ይሄን ስሜቱዋን አይቶት አያቅም ባሳለፉት ሁለት ቀናት ዋሲሁን በ" ቶ" ቅርጽ የተሰራው የ እንጨት መስቀል
ሲያብሰለስለው ነበር የከረመው እንዴት ቅድስት ሊመጣ ቻለ?

ሌላው በዚ ሰዓት እንደ ሀኪም ባለሙያነቱ ስንት የ ህክምና ተጋድሎ እያደረጉ ያሉ የህክምና ጉዋዶቹ በዚ ሰዓት መርዳት ሲኖርበት ያንን ማድረግ ሳይችል መቅረቱ ያበግነዋል እንደራሱ ለዓለም ስንተ አስተዋፆ ማድረግ ሲኖርበት ያንን ሳይታደል መቅረቱ ያሳዝናል እራሶዳድነት ግለኝነት በነገሰናት ዓለም ላይ ነብስ እማያቁ ጨቅላ ህፃናት ሲረግፉ

ንፁሀን በ ሀጢያተኞች እጅ ወድቀው ለቁጥር በሚያታክት መልኩ የሰው ልጅ እንደ ቅጠል ሲረግፍ ማየት እና በዚ ሰዓት ሊያቆመው እንደሚችል እያወቀ በክፉዋን ሰውች እጅ ላይ ወድቆ እንዲህ ዋጋ መክፈሉ ያንገበግበዋል።

በዚ ሰዓት እንደ ወታደር ትጥቁን አሙዋልቶ ለግዳጅ መቆም ነበረብኝ በዚ ሰዓት ይኔ መኖር ሆስፒታል እና ህሙማን ድንኩዋኖች ውስጥ ነበር እራሱን ማግኘት

እሚፈልገው አሁን ላይ ግን የ አይጥ እና ድመት ጨዋታ ውስጥ ነው ዋሲሁን እራሱን ያገኘው ምክኒያቱም በዚ ዘመን ሞትም ህይወትም ለነሱ ንግድ ነው
.......... ........... ........... .....
……… ………… ………… ………… ……………………

@fkrnatafetro
የሉሲፈር : በትር !
----------//--------
ክፍል :-(38)


"ዋሽንግተን"
ዋሺንግተን ዲሲ የ ዩናይትድ እስቴ አሜሪካ ዋና ከተማ ነው። የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 570,898 ሆኖ ይገመታል።

የ እንግሊዝ ሰዎች መጀመርያ በአካባቢው በደረሱ ወቅት 1600 - 1660 ዓ.ም በአሁኑ ዲሲ ሥፍራ ናኮችታንክ የተባለ የኗሪዎች ታላቅ መንደርና ንግድ ማዕከል ተገኘ። የአሁኑ ዋሺንግተን ከተማ የአሜሪካ አዲስ ልዩ ዋና ከተማ እንዲሆን በ1783 ዓ.ም. ተመሠረተ።

በ 1792 ዓ.ም. የአሜሪካ መንግሥት መቀመጫ በይፋ ከፊላዴልፊያ ወደ
ዋሺንግተን ተዛወረ።

የከተማው ስም «ዋሽንግተን» የአገሩን መጀመርያውን ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዋሺንግተን ስም ነው እምትጠራው ካሉዋት የ አየር ማረፊያዎች ውስጥ አንዱ የሆነው 'Reagan National Airport'

በ አዲሱ ወረርሽኝ ምክኒያት ጽልመት ለብሱዋል በቀን ብዙ ሺህ መንገደኞችን እሚያስተናግደው አየር መንገድ ዛሬ በመንገደኝ እርሀብ ወድቁዋል ጥቂት እሚባሉ መንገደኞች ውስጥ ሁለት አዛውንት ባል እና ሚስቶች ለመብረር ተገተዋል ነገሮች ሁላ ተቀይረዋል ላፌውች የስጦታ እቃ መሸጫ ሱቆች ሁሉም ተዘግተዋል ሁለቱ አዛውንት ባለትዳሮች እንደሌሎቹ አፋቸውን በጭንቭል ግጥም አርገው አስረው ወደ ኢትዮጲያ ከሰዓታት በውሃላ እሚበረውን የ ኢትዮጲያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን አይሮፕላን በመጠባበቅ ላይ ናቸው ።

የሙቀት ምልክታቸውን ተለክተው ወደ መተላለፊያ ተርሚናሉ ሻንጣቸውን ይዘው ሊገቡ ሲል ወዲያው ነበር ሁሉም ነገር ባለበት እንዲቆም ማንም እንዳይንቀሳቀስ ኮሪደሩ ላይ ባለው እስፒከር ተነገረ ፖሊሶች እና ሲቪል የለበሱ ሰውች ወዲያው አየር መንገዱን ወረሩት እነሱን ተከትሎ የሰማይ ስባሪ እሚያክለው ሞርጋን ገባ:

እያንዳንዱ ሰው እንዲፈተሽ አዘዘ ሁሉም ሰው ላይ ቅኝት ይደረግ ጀመር ከሁሉም ሁለቱ አዛውንት ቀልቡን ሳቡት በእርጋታ ወደ አጠገባቸው ተጠግቶ ፓስፖርታቸውን ጠየቃቸው ሽማግሌው እጃቸው እየተንቀጠቀጠ ሱፍ ጃኬታቸው ውስጥ ያለውን ፓስፖርታቸውን አውተው

ሰጡት አሮጊቱዋ ግን ዝም አሉ ሞርጋን ደግሞ ጠየቃቸው እሳቸው ግን አሁንም ዝም አሉ ሞርጋን ንዴቱ እየናረ ሲሄድ ሽማግሌው ተመልክተው ያለ አጋዥ መሳሪያ መስማት እንደማትችል ነገረው ሞርጋን ወደ ሽማግሌው ዞር በማለት ታዲያ ለማቀርብላቸው ጥያቄ እንዲሰሙ እሚያረጋቸው መሳሪያው የታል አለ ሽማግሌው ሞርጋን ለሰስ ባለ የጥርጣሬ አስተያየት ጠየቃቸው ::

ሽማግሌውም ቀስ ብለው ከ ባለቤታቸው ከ አዛውንቱ ቦርሳ ገቡ እና ውስጥ እጃቸው ሁለት ቦታ ነካ ቀጭን ዘመናዊ አውቶማቲክ መሳሪያ እና ለህመምተኞች እሚታዘዝ የጆሮ ማዳመጫ መሳሪያ የሽማግሌው እጅ ግን መሳሪያውን ነበር የጨበጠው

በዚ ሁኔታ ላይ እያሉ ነበር አንድ የፖሊስ አባል ሞርጋን ሲል የተጣራው በፍጥነት ወደ ካሜራ መቆጣጠሪያው እሩም እንዲመጣ የተጠራው ሞርጋን ጥቂት ካመነታ በውኃላ እየተጫኮለ ወደ ተጠራበት አመራ የተጠራጠሩት አንድ ምስል እንዳለ እና እንዲመለከት ነበር የጠሩት ዋሲሁን እቅስቃሴው እንዲቀጥል እና የበረራ ሰዓቶች እንዳይስተጉዋጎል አደረገ ቪዲዮውን ሞርጋን አንድ ባንድ ተንቀሳቃሽ ምስሉን መመልከት ጀመረ ግን ሀሳቡ ሁላ እነዛ ሁለት አዛውንቶች ላይ ነበር

ድንገት አንድ ምስል ተመልክቶ ቪዲኦ ኦፕሬተሩን እንዲያስቆመው አዘዘ ምስሉን በማጉላት( zoom) በማረግ ተመለከተው ሁለቱ አዛውንቶች ናቸው በ ተርሚናሉ መተላለፊያ ላይ ባስፖርታቸውን እያሳዩ ይታያል ፓስፖርት የያዙት የ አሮጊቱዋ እጅ ላይ አንድ ጠባሳ ይታያል በዛም ላይ ቀጫጭን አብለጭላጭ ጌጦች ታስረውበታል ሞርጋን ምስሉ ወደ አንድ ትውስታው መሀደር ወሰደው ቅድስት ባገኛት አጋጣሚ ሁላ ስውነቱዋን ይመለከታል በተለይ ያገኛት ቀን መላ አካሉን ሲነዝረው ተሰምቶታል የተደበቀ ምትሀታዊ ውበት ሲል አሞካሽቱዋታል

ጽጉሩዋን፥ከንፈሩዋን፥አይኑዋን፥ዳሌዋን፥ጡቱዋን ሁሉንም አንድ በአንድ አስታወሰ ግን አሁ እጁዋላይ ካለው ምልክት ላይ ቀርቱዋል ሞርጋር ወዲያው ነበር ያቺ ሴት ቅድስት ናት ብሎ ሲሮጥ ወጣ በስልክ መነጋገሪያው በፍጥነት ተርሚናሉን ዝጉት ሲል ጮኸ ነገር ግን እረፍዶ ነበር በቃ መንገደኛ ስላልነበር አይሮፕላኑ ያሉትን ከጣት ቆጠራ እማያልፉትን ሰውች ይዞ ማኮብኮብ ጀምሩዋል ሞርጋን በንዴት አጠገቡ ያለውን የፖሊስ አባል በቦክስ ነረተው ፍለፊቱ ያሉትን ሰዎች ሁላ መደብደብ እቃ:

መሰባበር ጀመረ በፍጥነት የ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎቹ አይሮፕላኑ ወደ ተነሳበት እንዲመለስ አዘዘ ነገርግን ይሄን ማድረግ እንደማይችል መለሱለት ሞርጋን ወደ መቆጣጠሪያው ክፍል በማናለብኝነት በጉልበት በመግባት አይሮፕላኑ ተመልሶ እንዲያርፍ ሲል አስገደዳቸው አንደኛው የ አየር ተቆጣጣሪ ሁለቱን ባል እና ሚስት አዛውንቶች ይዞ እሚበረውን አይሮፕላን

በፍጥነት መስመሩን በመመለስ እንዲያርፍ ለደንህነት ስጋት የሆኑ ሰዎች አይሮፕላኑስጥ ስለገቡ ከ FBI ቢሮ ስለሚፈለጉ በፍጥነት መልሶ እንዲያሳርፍ አዘዙት ከ 45 ደቂቃ የ አየር ላይ ቆይታ በውኃላ አይሮፕላኑ መልሶ አረፈ ሞርጋን መቆሙን እንዳረጋገጠ አይሮፕላኑን አስከብቦ ጊዜ ሳያባክን ወደ ውስጥ ገባ ነገር ግን ሁሉንም ቢያስስ ሁለቱ አዛውንት ባል እና ሚስቶች አይሮፕላን ውስጥ አልነበሩም ሞርጋን ደጋግሞ ደጋግሞ ፈለገ ፈጽሞ ሊያገኛቸው አልቻለም የውኃ ሽታ ሆኑ ..........

.....ይቀጥላል.....

@fkrnatafetro
#የኔ አዳም

ካወኳቸው ሁላ ልቤ አንተኑ መርጧል
ማንነትህ ማርኮት ማፍቀሩን አጋልጧል
ምን ቆንጆ ቢሞላ ቢትረፈረፍ በዝቶ
አይኔም ሌላን ላያይ ምሏል ተገዝቶ
እግሮቼም ካንተ ውጭ ከቶውን ላይሄዱ
ወስነው ቆርጠዋል ተዘግቷል መንገዱ
ከንግዲህ ለኔ ጎን ያለኸው አንተ ነህ
ብዬ ምፅፍልህ የኔ አዳም ወዴት ነህ

#ከወደዱት_ለወዳጆ_ያጋሩ
@fkrnatafetro
ሰላም ፣ ጤና ፣ ፍቅር ለናንተ ይሁን ውድ ቤተሰቦቻችን እንደምን ቆያችሁን


​​ማንኛውም የሰው ልጅ ፈልጎ ወይም
አስቦበት አያፈቅርም! ነገር ግን በአሁኑ ስአት ማፍቀር በሁለት ይከፈላል፡፡

1 ምክኒያታዊ ማፍቅር እና
2 ምክኒያት አልባ ማፍቅር ናቸው

1 ምክኒያታዊ ማፍቅር ማለት በጥቅም ,በውጫዊ ውበት ,ብቸኝነትን ለመርሳት ,የሚወዱትን ሰው ለማስቀናት ,የሚፈልገውን እስከሚያገኘ ድረስ ...ይቀጥላል በእነዚህ ምክኒያት ያፈቀረን ሰው ሲፈልገን መጥቶ ስንፈልገው ጠፍቶ ሂወታችንን
የሚያናውጥ እና በማፍቀራችን እንድንፀፀት አልያም ፍቅርን እንድንጠላ የሚያደርገን አፍቃሪ ነው።

2 ምክኒያት አልባ ማፍቅር ማለት ሳያስብበት (ሳይዘጋጅበት ) በአጋጣሚ እራስን በማያውቁት ቦታ ውስጥ ሰምጦ ማግኘት ነው። የት ? እንዴት ? መቼ ?ለምን ? =መልስ የለም ! ብቻ የልብ ትርታን ነው፡፡ የሚያዳምጠው በደስታም ይሁን በሀዘን ሁሌም ከሚያፈቅረው ሰው ጎን አይጠፋም ከእሱ ደስታ ይልቅ ያፈቀረውን ሰው ደስታ ይመርጣል ,ፍቅር መስጠት እንጂ መቀበል አይሻም
እየተጠላ ይወዳል ,እየተራቀ ይቀርባል ይህ ነው ምክኒያት አልባ ፍቅር ።

እናም አፍቃሪም ይሁን ተፈቃሪ ከምክኒያታዊ ( ግዜአዊ ) ፍቅር ይልቅ ምክኒያት አልባ (ዘላቂ)ፍቅርን መረዳት ቢችል መልካም ነው ።


✩。:*•.───── ❁ 🌹❁ ─────.•*:。✩
@fkrnatafetro
✩。:*•.───── ❁🌹❁ ─────.•*:。✩
መወድስ
(በእውቀቱ ስዩም)
ፊትሽ እንደ ምሥራቅ፡ ብርሃን ያመርታል
ፈገግታሽ ዋስ ሆኖ፣ እስረኛ ያስፈታል
ውይ መዓዛሽ ሲያምር!
የሎሚ የንጆሪ፣ የኮክ ሽታ ድምር።

ከየዛፉ ቅጠል
ንፋስ በክንዶቹ፣ ከሚሰበስበው
ከሳሩ ከሰርዶው፣ መሬት ከሚሳበው
በደብር እፀድ ላይ፣ ከሰፈነው ለምለም
ከየኔክታሩ ጣም፣ ከያበባው ቀለም
አውጣጥቶ ማን ሰጠሽ?
እንዲህ ምን አስጌጠሽ?
እንዲህ ምን አሰላሽ?
መች ተጣድሽ? መች ፈላሽ?
ለዛሽ በፊትሽ ላይ መች ተጠነሰሰ
ውበትሽ መንገድ ላይ፣ ገንፍሎ ፈሰሰ

ገላየ ጭንቅ አይችል፣ ዐይንሽ ስውር መቀስ
ኧረ ቀስ! ኧረ ቀስ!
ከደም ከሥጋ እንጂ፣ አልተሰራም ካለት በውበትሽ አምላክ፣ ለልቤ እዘኝለት

#share
@fkrnatafetro
የሉሲፈር : በትር !
----------//--------
ክፍል:-(39)
…………… …………… ……… …… ……

ዋሽንግተን ዲሲ ( እንግዳ ማረፊያ ውስጥ)

ዋሲሁን ቅድስት ባረገችው ነገር ተናዶ ጠየቃት "ለምንድ ነው እንድንመለስ የፈለክሽው ድጋሚ ልትሸጪኝ ? ድጋሚ አሳልፈሽ ልሰጪኝ? "

"ተረጋጋ ልንሳፈርበት የነበረውን አይሮፕላን በሞርጋን ትእዛዝ መልሶ እንዲያርፍ ተደርጉዋል
እኔና አንተም እዛ ብንገኝ ምን ሊያደርገን እንደሚችል አስብ ምልክት የተውኩላቸው አውቄነው አሁን እሚያቁት ወደ ኢትዮጲያ እሚሄደውን ሳይሆን ወደ ካናዳ እሚበረውን ትኬት ጭምር ነው ተመሳሳይ ሰዓት መሆኑን ሳቅ

የቆረጥኩት አሁን እኛ ወደ ካናዳ መሄዳችን እንጂ እዚህ መቅረታችንን ምንም አያውቁም በሚገባ ተወተነዋል ሜካፑን ስናወላልቅ ሽንት ቤት ውስጥ ምንም አይነት ምልክት እንዳልተውክ እርግጠኛ ነህ? አለበለዚያ የለፋንበት ሁላ ገደል ነው እሚገባው አሁን ጥቂት ብቻ ነው እራሳችንን እምንቀይረው ሌላ የዱባይ ፓስፖርት ተዘጋጅቶልናል ትኬትም ከ ሁለት ቀን በፊት ተቆርጡዋል በረራ ከነገ ጀምሮ ማንኛውም አይነት በረራ ስለሚቁዋረጥ ለሊት 7ሰዓት ላይ ወደ ዱባይ እንበራለን ከዛ ወደ ኢትዮጲኣ እንገባለንስለዚ አሁን ተረጋግተን በማስተዋል መፍጠን ነው እሚኖርብን ።

ባንተ ምክኒያት ብዙ ነገሬን ትቻለሁ ሁሉ ነገሬን ነው ያጣሁት አንተ ግን አሁንም እኔን ትወቅሳለህ እኔ አንተን ነጻ ለማውጣት መከራዬን አያለሁ አንተ ዙሪያዬ ገደል መሆኑን እያየህ ልትሸጭኝ ነው ትላለህ አረመኔ አረመኔ ነህ "

ቅድስት እያነባች ዋሲሁን ላይ ትጮህ ጀመር ዋሲሁንስሜታዊ ሆኖ በተናገረው ነገር አዘነ እና ጉተት አርጎ ከንፈሩዋን መጠጣት አልከለከለችውም ያለማቁዋረጥ ተሳሳሙ ዋሲሁን በርሀብ እንደከረመ ህፃን ተስገበገበ ቅድስትም እማታቀው እሳት ሰውነቱዋን ሲገርፈው ተሰማት ወላፍኑ ልቡዋን አሞቀው እሳት እንዳየ ሰም ቀለጡ ለደቂቃውች መቆም አልቻሉም ትንፋሽ

እሚስቡበትም ጊዜ አልነበራቸውም ዋሲሁን የሸሚዙዋን ቁልፎች እሚፈታበት ጊዜ አልነበረውም ከሰውነቱዋ ላይ እየቀደደ ጣለው ቲሸርቶቹን ወደላይ ገልባ አውለቀችው ሱሪዋን በፍጥነት መፍታት ጀመረ እሱዋም ቀበቶዉን መፍታት ጀመረች ዋሲሁን ወደላይ ከፍ አርጎ አንጠለጠላት ወገቡላይ በ እግሮቹዋ ተጠመጠምችበት አልጋው ላይ ወረወራት አካላቸው አልጋውን ያነድ ጀመር ጸሀይ በልባቸው በብርሀኑዋ ተመላለሰች ደማቸው ገላቸውን አልፎ የብርሀን ጅረት ሰራ መቃተት ብቻ ሆነ ፍፁም ፍቅር የሞላው ጥልቅ ጩኸት እማይረግብ እሚመስል ከባድ የፍቅር መአበል ወጀቡ ገላቸውን በ ላብ አራሰው ፍጹም እረፍት ሆነ ትንፋሻቸው ቁርጥ ቁርጥ አለ እንደተቃቀፉ ከባድ እንቅልፍ ጣላቸው።

የያዙት የ እንግዳ ማረፊያ በ ሞርጋን ልዩ ቅጥረኞች ተከበበ ምንም አይነት ስህተት ላለመስራት ብዛት ያላቸው ሀይሎች ቦታውን ከበው እሚሆነውን መጠባበቅ ጀመሩ ሞርጋን መኪናውስጥ ሆኖ በጥንቃቄ መመሪያ ይሰጣል በስተ መጨረሻ ሚስጥራዊው የ ጭለማው መሀበር ላይ እሚያገኘውን የክብር ካባ ሲያስበው ፈገግ አለ ያረፉበትን ክፍል በር ገንጥለው ወደ ውስጥ ገቡ…………

……… ይቀጥላል ………

@fkrnatafetro
የሉሲፈር : በትር !
----------//--------
ክፍል :-(40 )


ሞርጋርን ከውጪ መኪና ውስጥ ሆኖ እሚሆነውን ይጠባበቃል እግሩ ስር ቅድስት ክፍል የገኘውን በ ቶ ቅርጽ የተሰራውን የ እንጨት መስቀል በእጁ ያገላብጠዋል ድንገት የ እጅ ስልኩ ጠራ እና ክፍሉ ውስጥ እንደሌሉ ነገር ግን ክፍሉ ውስጥ እንደነበሩ ምልክቶችን እንዳገኙ ነገሩት ሞርጋን በብስጭት ነደደ ስልኩን አሽቀንጥሮ ወረወረ እና ከሚኪናው ወርዶ ወደ አስከበበው እነ ዋሲሁን ወደነበሩበት ክፍል አቀና።

ቅድስት እና ዶ/ር ዋሲሁን እራቅ ብለው መኪና ውስጥ ሆነው እሚሆነውን ይከታተላሉ በ ደቂቃውች ልዩነት ነበር ክፍሉን ለቀው በ አደጋ ጊዜ መውጫው በኩል ያመለጡት ።
ዶ/ር ዋሲሁን ሞርጋን ወደ ነበሩበት ሆቴል ሲገባ በቶ ቅርጽ የተሰራውን የ እንጨት መስቀል በእጁ እንደያዘ ተመለከተ ቅድስትንም እንድትመለከት አደረገ ለቅድስትም" ይሄንን መስቀል ከሞርጋን መውሰድ ይኖርብናል " ሲል ነገራት ቅድስትም ደንግጣ" በፍጹም አላደርገውም እንዲያውም እንኩዋን ገላገለኝ ትንሽ እሱን ያንደው ያኔ ልኩን ያገኛል" አለቺው

ዶ/ር ዋሲሁን ያልችው ነገር ትንሽ ግራ አጋባው እና ንግግሩን ቀጠለ ቆይ" ያንደው ስትይ " ሲል በትኩረት እያያት ጠየቃት ቅድስትም " የጭለማው መሀበር ስትገባ እራስህን እስካለህም ከሞትክም በውኃላ ፍጹም ሁሉን ነገር ክደህ ነው እምትገባው እምታምንበትን እረግጠህ ደምህን ቀድተህ ፍጹም እራሴን ሰጥቻለው ብለህ ነው

እምትገባው ከዛም ምልክቱን በክንድህ ላይ በድግምት እና በ አስማት ይደረግልሀል ሁሌም ጨረቃ በ ቦታዋ ሙሉ ስትሆን አንተም እራስህን በ አስማቱ አማካኝነት የሰውም ይሁን እንስሣ እያጠመድክ የደም መሳዋት ታቀርባለህ ግን ይሄ ጨረቃ ስትገጥም ሙሉ ስትሆን ነው ይሄ ፊልም ወይም ተረት ሊመስልህ ይችላል ግን እምኖረው የየ እለት ኑሮዬን ነው አንተም ፊልም ሆኖ በተደጋጋሚ መቼም

አይተኸዋል ይሄ ደሞ ሆን ተብሎ የሰውችን ለ ነገሩ ያለውን መጥፎ አመለካከት ለመስለብ ነው አየህ ልብህ በጎነቱን እያየ እንዲያድግ ፊክሽን በሚመስል ታሪክ በሬ ወለድ አስመስለው ይሰብኩሀል ይሄን እያየህ አንተም ልጅህም ይሄን እያየህ ታድጋለህ ከዛም ማንም እጅህን ሳይጠመዝዝ ወደህ ነብስህን ትሰጣለህ ለምን ምንም እምታቀው እምነትም ሆነ እምትፈራው ፈጣሪ አይኖርህም

ይሄው ነው እኔም ሀገሬ መፈጠሬን እስክጠላ ለዚ ገቢር መስዋት አርጋ የሰጠጪኝ ለነገሩ እዛ ከደረሰብኝ አይበልጥም እነዚ ሰተው ነው በብዙ እሚቀበሉህ ኢትዮፒያ ግን ያለኝንም እኔንም ነው የቀማቺኝ እዚካለው እዛ የደረሰብኝ ሚስተካከል እንጂ አያንስም ለኔ ሀጢያት ምንም ትንሽትልቅ የለውም ሁሉም የቅጣት ሰይፍ

ይገባዋል " ዋሲሁን አስጠግቶ አቀፋት እና ከቃሉዋ እየቀደመ እሚረግፍ እንባዋን አበሰላት እና" ከዚ በውኃላ እኔ ላንቺ እሞታለሁ በያንዳንዱ ደቂቃ ካይኔ ላጣሽ አልፈልግም

በመጀመሪያ ይሄን እንወጣዋለን አብረን ለሰራ ነው ንስሀን እንቀበላለን ከዛም ሀገራችንን ወደ ንስሀ እናመጣለን እንዳታድግ እሚያቀጭጩዋትን አንድ በ አንድ እንነቅላለን ላጥፊዎች ጅራፍን ለ በረቱት ምርኩዝን እናቀብላለን ግን አሁን ይሄ መስቀል የግድ ያስፈልገናል የግድ ልትረጂኝ ግድ ነአ ያላቺ ምንም ነኝ ቅድስቴ ጨረቃ ሙሉ እምቶንበትን ሰዓት እና ወቅት ንገሪኝ ከዛ ምን እንደምናረግ እነግርሻለሁ" አላት ዋሲሁን ወደ ሆቴሉ በትኩረት እየተመለከተ"

ቅድስትም "ለምን አስፈለገህ ይሄን ንገርኝ መጀመሪያ" አለችው በትኩረት ከ አይኑ አንዳች መልስ እየፈለገች ።
ዶ/ር ዋሲሁንም ምክኒያቱን ካልተናገረ ፍቃደኛ እንደማቶን ስለተረዳ አይኑን ወደ እሱዋ እየመለሰ እቅዱን ነገራት ቅድስትም ባታምንበትም ያሰበውን ነገር የግድ መሞከር እንዳለባት አመነች እና የጨረቃዋ ሙሉነት መች እና ምንሰዓት እንደሆነ ነገረችው።

ከዛም ቦታውን ለቀው ሸሹ አሪዞና ለ 2 ቀናት የሚጠብቁት የጨረቃ ቀጠሮ እስኪደርስ እራሳቸውን በጥንቃቄ ደብቀው ቆዩ ግን ትኩስ ፍቅራቸውን ያለገደብ እሚወጡበት ሰፊ ጊዜ አገኙ አጋጣቢያቸውን አንድ በ አንድ ተጠቀሙት ዶ/ር ዋሲሁን "ምነው የጨረቃ ሙላት ለዘላለም ቢከስም ምክኒያቱም ሙላቱዋንም ውበቱዋንም ያለገደብ አንቺ ላይ አየዋት ለኔ ከዚ በላይ ሙሉ ጨረቃ የለችም" ይላታል ጣቶቹን በጸጉሮቹዋ መሀል በእርጋታ እያሳመረ " አትቀልድ ብላ ሆዱን ጎሸም ታረገው እና መልሳታቅፈዋለች ዶ/ር ዋሲሁንም መልሶ ከንፈሮቹዋን

በከንፈሩ ወደ ውስጡ ይስበዋል መልሶ ደግሞ በፍቅር ይከንፋሉ ደጋግመው ይጠፋሉ አካሄዳቸው እሚመለሱም አይመስለም እሱ እሱዋ ውስጥ እሱዋም እሱ ውስጥ ትደበቃለች በየ ወላፍናቸው ይገራርፈሉ ቅድስት " አንተ ማነህ ሉኦሌ ማልበልህ ስለምን መጣህ እኔ እኮ አንዲት

ህጻን ልጅ እንደያዘቻት ሚስኪን አሸንጉሊት ነኝ ሲያሻቸው እሚጥሉኝ ባሳቸው ሰዓት መርፌ እዚ እና እዛ እሚጎትቶኝ እነሱን ከማጫወት በቀር እርባን የሌለኝ ተጥቅመውብኝ ሲያበኩ እሚተፉኝ ሰው ነኝ እና አንተ እኔ ጋር ምን ትሰራለህ እንዴት ብለህ በልቤ ነገስክ ንገረኝ ማነህ ዶ/ር ልመንህ ሀኪሜ መምህሬ ልበልህ ንገረኝ ማልበልህ" አለቺው ቁርጥ ርጥ ከሚለው ትንፋሹ ጋር እየታገለች።
ከተደበቁበት አዲስ ዓለም ፈጥረው ሰነበቱ.

@fkrnatafetro
አፋልጉኝ!

የዛሬ አራት አመት አካባቢ በባስ ወደ መቀሌ እየሄድን ረዳቱ ፌስታል አውጥቶ ስለ ሚካኤል ብሎ ገንዘብ መጠየቅ ጀመረ ።አማኙ ተሳፋሪ በሚዞረው ፌስታል ውስጥ የአቅሙን ከተተ ። ብሩ ተሰብስቦ እንዳለቀ ረዳቱ ቆጥሮ በፌስታሉ ቋጠረው ።

የተወሰነ መንገድ እንደሄድን መስኮት ከፍቶ ገንዘቡን አርቆ ወረወረው። ግራ ገብቶኝ ለመያዝ እየቃጣኝ ከመቀመጫዬ ብድግ አልኩ ።እንግዳ መሆኔንና መገረሜን አውቀው መንገደኛ ሰው ሲያልፍ አንዱ ላንዱ እያቀበለ ምፅዋት ለተሰጠበት ቤተክርስቲያን እንደሚያደርሱት በእርግጠኝነት ነገሩኝ ።

ከመካከል አንዱ የሳተ ቢወስደውስ?፤ ጥያቄዬ ነበር ።
"እምነቱን የሚያፈርስ የለም ፤ እግዜር ያየዋል ።ስለዚህ ማንም የሱ ያልሆነን አይወስድም ።የእግዜር እንደሆነ ያውቃል ።ይታመናል" አሉኝ። ተገርሜ በአዕምሮዬ ገንዘቡ መሬት ላይ ወድቆ ሊያገኙት የሚችሉ ሰዎችን ማንነትና ገንዘቡን ከማግኘታቸው ከደቂቃ በፊት ሊሆኑ የሚችሉበትን ሁኔታና ኑሮ በየተራ ፈጥሬ እየሳልኩ ታሪክ እየሰራሁ ተጓዝኩ።
ከአመት በኋላ በዶክመንተሪ ፊልም ስራ በዛው መስመር ተገኝተን ከሌላ ባስ የተወረወረ ገንዘብን ያገኘ ሰዉ እየተቀባበለ ሲያደርሰው ተመለክትን፣ ተደነቅን ።

በልጅነቴ ከእናቴ ጋር ዜና ማርቆስ የሚባል ገዳም እንሄድ ነበር ።እናቴና ወንድሜ አመት ጠብቀው ዛሬም ይሄዳሉ ። ወደ ገዳሙ ለመድረስ አንድን ሰርጥ ማለፍ ያስፈልጋል ።ሰርጡ ግራና ቀኝ ጥልቅ ገደል ነው ።ቁልቁለቱ ያንሸራትታል ።አንድ ሰው ነው የሚያሳልፈው ።የእንፉቅቅ ነው የሚወረደው ።ሰርጡ ጫፍ ስንደርስ የማናውቃቸው ልጆች የተጓዡን ቦርሳና ሻንጣ ለማገዝ ይቀበላሉ ። ከእናቴም ላይ ሻንጣዋንና ቦርሳዋን አንድ ልጅ ተቀበላት ።
ከሰርጡ ወደ ገዳሙ ለመድረስ ለበረታ ሶስት ለደከመ አራት ሰአታት ይፈጃል ።በመንገዳችን ሁሉ ያ ሻንጣችንን የተቀበለንን ልጅ ስላላየሁት በአዕምሮዬ ሻንጣችንን ምን እንዳደረገው እያሰላሰልኩ የገዳሙ መግቢያ ጋር ደረስን ።

ገዳሙ መግቢያ ላይ ስንደርስ ሻንጣችንን የያዘው ልጅ የሌሎች ተጓዦችን ሻንጣ ከያዙ ልጆች ጋር በረድፍ ተቀምጦ ሻንጣችንን ይዞ እየጠበቀን ነው ።
እግራችንን በአባቶች ታጥበን ንብረታችንን ተረክበን ወደ ገዳሙ ገባን።ልጆቹ ሳንቲም አልተቀበሉንም ። ሽልማታቸው ምርቃት ነበር ።
ያ እዛ ገዳም ስንሄድ ዕቃ የሚይዝልን ልጅ ዳዊት ይባላል ።ወደ አዲስ አበባ መጥቶ እኛ ቤት አድጎ ትምህርት ተምሮ የራሱን ኑሮ እስኪያበጅ ድረስ ወንድም ሆኖኝ አብረን ኖረናል።
ዛሬ ላይ ሆኜ የከተማዬን መተራመስ፣ የእምነታችንን መጉደል ሳስተውል፤ የአገር ልጅ የአገር ልጅ ላይ እጁን ሲያነሳ፣ ወንድም ወንድሙን ሲገድል ስመለከት አዝንና ደሞ በሌላ መልክ እንኳን አገሬውን በመንጋ ሊያጠቃ፣ እንኳን ለሌላው ስጋትና ፍርሀት ሊሆን መንገድ የወደቀን በእምነት የሚያስረክብ በአደራ የሚጠብቅ ህዝብ እንደነበር እንደሆነም አስብና በረታለሁ ።
ይችኛዋን ኢትዮጵያ ፈልጋታለሁ ። እናፍቃታለሁም ።
አፋልጉኝ!

✍️ጥሩ ዘር


@fkrnatafetro
ሊያገባ ነው
...ሲፈልገኝ ያገኘኛል ።
ሳይፈልገኝም አለሁ።
የምወዳቸውን ነገሮች ስለሚወድ ፤ ለኔ ብሎ የወደዳቸው ያህል ውለታው የበዛብኝ የዋኅ ፦ደረሰኝ የተቀበልኩበት ይመስል: 'የኔ' :ስለው ያለአንዳች ማፈር ነው።

ኮመዲኖየ ላይ: በፍሬም ያስቀመጥኩት የሱ ፎቶ : የሚያየኝ ይመስል፡ እንኳን ቤቴ ሰው ሊመጣ፡ እኔም አልወጣ።

ካየሁት ሳምንታት ተቆጠሩ። ስልኩ አንዴ ቢዚ አንዴ ዝግ ...

በደህናው ይሆን?! እላለሁ።

'ሊያገባ ነው አሉ!' ይሉኛል ።

'ውሸት ነው ፡የሰው ወሬ!'አልኳቸው

'ኧረ እንደውም ሽማግሌ ሊልክ ነው ይባላል ...'

----ለብቻየ ከራሴ ጋር አወራለሁ ------ እስኪ ሰው፦ ከተጣላው ሰው ለመታረቅ ፈልጎ ሽማግሌ ይልካል እንጂ እንዴት አብሯት ለመኖር የሚፈልጋት ሴት ጋ ሰው ሽማግሌ ይልካል?!

"ስላፈቀርኩዋት ይቅርታ አርጉልኝ !" ፦ሊል ነው?!

አላመንኩም! በቃ አያፈቅራትም!
እኔ ጋ ሽማግሌ የማይልከው ሽምግልና ስለማያስፈልገን ፍቅራችን ብቻውን እኛን ለማሸማገል ብቃት ስላላለው ነው" ።እላለሁ።

እንደወደዳት የነገሩኝ ቀን ደግሞ፦

" አፈቅርኳት!" ቢልም ስለማያውቅ ነው።
ትዳር እንጂ ፍቅር እንደማትፈልግ ፤አገባች መባልን ፈልጋ፦ 'ባል' ብላ እንደቀረበችው ስለማያውቅ ነው።

ልዩነቱ አልገባውም።

እሱ ለእሷ የኑሮዋ አጋር ሲሆን እሱ ለኔ ግን ኑሮየን እራሱን ነው።"
አልኩ።

ለእኔ ኑሮየ ነው! እኔ ኑሮየ ቢጎድል ቢሞላ ላሻሽለው ከመጣር ውጪ ፤ ከሱ ጋር ከመኖር በቀር ምርጫ የለኝም ።

ለእሷ ግን የኑሮዋ አጋር ስለሆነ አጋርነቱ ቢጎድል ትቀይረዋለች ። አጋርነቱ ቢጠቅም አብራው ትኖራለች ፦ስለዚህ እሱ ለእሷ የስምምነት ተግባር ፈፃሚ እንጂ የእራሷ ማንነት አይደለም ።"
አልኩ።

ይሄንን አለማወቁ አንገበገበኝ ። ግን ያውቅ ይሆን ?

አያውቅማ!

ለኔ ግን ባሌ አይደለም ። ነገሩ የሱዋም አይደለም።

እሱ ለኔ የሳቄ ምንጭ፤ የሃሳቤ አድማጭ ፤ የኔ የምለው በዓለም ላይ ያለኝ ብቸኛ የእኔነቴ ግማሽ ነው።

ሲያመው መታመሙን ሳይነግረኝ ታምሜ የእሱን ህመም ባለማወቅ በፍቅር ውስጥ የምጋራ።

ታሪኩን የኖርኩ፣ ድካሙን በድካሜ ውስጥ የማይ፤ አንጀቴን የሚበላ ማንነት ያለው።

ሁለመናየን ተቆጣጥሮ: ሪሞቴ እሱ እጅ ላይ ያለ ይመስል ----
ሲረሳኝ ራሴን ረሳለሁ፤ ሲጠፋብኝ ቀኔ ይጠፋብኛል።

አንዳንዴ ደግሞ: እሱ ጋ ያለውን ሪሞቴን : ምን ላይ ተጭኖት ይተወው ሳላውቅ ቻናል ድብልቅልቅ ላይ ሆኘ : ከሩስያ ናይጄሪያ በሃሳብ ስራወጥ እውላለሁ ።

እሱ ባሌ አይደለም። ጓደኛየም አይደለም እሱ ለእኔ ፀሃየ ነው እኔ ደግሞ የሱፍ አበባ

ወጥቶ እስኪገባ ዞሬው፤
ሲደበቅ የምዝል: በመጥለቁ አፍታ: አንገቴ የሚሰበር እኔ!

እሱ እኮ !
ስሙ ራሱ አፌ ላይ አላምጨው : እንደ ድንገተኛ የሚፈውሰኝ መድህኔ ነው።

እና ሊያገባ ነው?

መቼም በገጠር ካልሆነ በቀር በከተማ ውስጥ በሰርግ ዋዜማ የጠፋ ሙሽራ እንጂ ሙሽሪት ጠፍታ አታውቅም።

የሚከራይ ሙሽራ እንጂ: የምትከራይ ሙሽሪት የለችም።

ይሄ ሁሉ ድንቃድንቅ ተከስቶ: ሙሽሪት ብን ብላ ጠፍታ ለመጀመሪያ ጊዜ እኔ የምትከራይ ሙሽራ ብሆነውስ?

አትጠፋማ !ምን ያስጠፋታል?

ልትጠፋ ትችላለች ።ለምሳሌ የድሮ ፍቅረኛዋ ሚሊየነር ሆኖ አግኝታው ።

ወይም ቀልቧን ቅፍፍ ብሎት
ልትጠፋ ትችላለች ።

ወይም ሰርጉን ልትሰርዝ ትችላለች ።

ባዝ ውስጥ እያለች በሙቅ ውሃ ተቃጥላ

የሜካፕ ባግዋን ውጣው .... እያልኩ አስቂኝ እና አሳዛኝ መላምቶችን ሳነሳ ስጥል እውላለሁ ።

ሄሄ ይሄው ካሰብኩት መዓቶች ሁሉ : ምንም ሳይደርስባት ውበት ጨምራ ስታልፍ አያታለሁ

እያንዳንዱ ቀን ሰርጉን አፈጠነው።

ትናንት ደማቅ ከበሮ ሲመታ ነበር ።እንደነገሩ ለብሼ ቦርሳየን ይዤ የምሄድበት ሳይኖረኝ ወጣሁ።
መንገዱ አለ።

'ድድም ፣ድም፣ ድድም ..' የሚለው ድምፅ የከበሮው ይሁን የልቤ አላወቅኩም ።

ድንኳኑ እንደኢያሪኮ በእልልታቸው ቢፈርስ: እላያቸው ላይ ቢናድ: እየተመኘሁ- ዳሱን ላለመቅረብ ተጠንቅቄ በሩቅ አለፍኩ።

አይኔን አይለበልበኝም: ሰውነቴ ግን ይርዳል ።

እነ ሙራዱ ሱቅ ቆሜ : የምገዛው ነገር አማረጥኩ ፥በምን ላጠቃቸው እችላለሁ?!

በረኪና ገዝቼ መሃላቸው ልድፋባቸው ?!
የቲማቲም ጣሳ እያለምኩ ልወርውርባቸው?
በሶፍት ጠፍንጌ ልሰራቸው?
በሰንደል ልግረፋቸው?
በኮካ እና በምሪንዳ ሰርገኛውን ላምሰው?
ኤጭ ለካ የሙራዱ ሱቅ ለሽብር መፍጠሪያ የሚሆን ምንም ነገር የለውም ።

ጦርነት ስል ጦር ትዝ አለኝ ።
ጦር ትዝ ሲለኝ ጦርማስቲካ ትዝ አለኝ።

ጦር ማስቲካ ተቀበልኩት፤ ቢያንስ በመንጋጋየ መሃል ለረጅም ሰአት የማደባየው ቁጭት መወጫ ጎማ ይዣለሁ ።
ከፍየ መንገዴን ቀጠልኩ።
ብዙ እርምጃ ከተራመድኩ ወዲያ

በድንገት ልብሴ ተጎተተ
ትከሻየ ተነካ
..... ተሰማኝ

ሠርጉን ትቶ እየሮጠ ተከትሎኛል?!

ዘወር ስል ፦የሙራዱ ታናሽ ወንድም
በሮዝ ቀለም ቆዳ ልባድ የተሸፈነ ሞባይል የያዘ እጁን ዘረጋልኝ ።፦ሞባይሉ የራሴ ነው።

ማስቲካ ገዝቼ ስወጣ የረሳሁት ሞባይሌ

ተቀብየው ዞር ስል

አሁንም ትከሻየን ነካኝ
ኡፋ!ምንድነው?

'ሚዛናችንን ?!'አለኝ ኮስተር ብሎ

እ?!
ግራ እጄን አየሁት ሚዛናቸው መዳፌ ውስጥ አለ።
እንደ እጅ ቦምብ አጥብቄ መያዜን አየሁ።

የግፍተራ ያህል ሰጥቼው ዘወር እያልኩ ድርጊቴ ዘገነነኝ።

ባስማም የስንት ሰው ህይወት በእጄ ጠፍቶ ነበር።

------
ውውውውው ጩኸት ነገር ተሰማኝ
ከዲኤስ ቲቪ

ማንቼ አገባ።።።።
📶ይነበብ በማንበብ እንማርበታለን እንጂ አንማረርበትም!
ቃል ግቢልኝ
ቃል ግባልኝ
ቃልን አናቅለው አይደለም ገለባ
ሠማይና ምድር የፀናው በቃል ነው
ቃል እንድህ ከባድ ነው!!
🚻እውነተኛ ታሪክ
ሁለት ፍቅረኛሞች ነበሩ ሁለቱም እንደፍቅራቸው በአንድ ወደ እስራኤል ሀገር ኑሮን ለማሳለፍ ስደት ሄዱ። ከዛ በቅድስቷ ሀገር ቃል ተገባብተው ሞት ነው ከአንቺ የሚለየኝ እሷም ሞት ነው ከአንተ የሚለየኝ ብለው ቃልኪዳን አሰሩ። ከዛም ኑሮን ለማሻሻል በዛው ወደ አሜሪካ አቀኑ። የወንዱ (የባሏ) ዘመዶች በብዛት አሜሪካ ይኖራሉ። እና እነዚህ ጥንዶች ከተጋቡ ብዙ ቆዩ ልጅ አልወልድ ይላሉ። ከዛ ባሏ የእኔ ፍቅር እግዚአብሔር ያውቃል ልትወልጅልኝ ብየ ውል ወስጀ እኮ አላገባሁሽም የአምላክ ስጦታ ነው አትጨነቂ ይላታል ሁሌም እሷም እሸ ውዴ ብላ በባሏ ቃል ተፅናንታ ኑሯቸውን ቀጠሉ።
ከዚያም ከእለታት አንድ ቀን የባሏ ዘመዶች በቤታቸው ሆነው የሚያወሩትን ማለትም ልጅ ከአልወለደች ይፍታት ልጅ ሳይወልድ ልጃችን ወንድማችን እንዴት ይቀራል በማለት ሁሌም ይቆጫሉ። ከዚያም አንድ ቀን የልጅቱ ባል በሌለበት ወደ ምራታቸው ቤት አቀኑ ሲሄዱም ልጅቷን ብቻ አገኟት ከዚም እኛ እንወድሻለን እንፈልግሻለን ግን አንች ልጅ መውለድ ስለማትችይ ወንድማችንን ፍችውና እሱ ሌላ ሚስት አግብቶ ይውለድ ይሏታል ተሰባስበው ሄደው። እሷም እምትሆነውን አጣች አለቀሰች እያለቀሰች እነሱም ቁጭ እንዳሉ የልጅቷ ባል ከስራ ተመልሶ መጣ ሲገባ ቤት ዘመዶቹ ከበዋል ሚስቱም ታለቅሳለች። እሱም ደነገጠ ከሀገር ቤት ዘመድ ሞተ እንዴ የእኔ ፍቅር ንገሪኝ ብሎ እቅፍ አድርጎ አብሮ ማልቀስ ጀመረ። እሷም እንባዋን ተቋቁማ የሆነውን ነገረችው እሱም ምንጊዜም የወንድ ወገን ፣ ጓደኛ በፍቅር መግባታችሁን አታቆሙም። እሰይ አትውለድ ምን አገባችሁ የአገባኋት እኔ እንጅ እናንተ አይደላችሁም። ከእሷ ጋ እሚለየኝ ሞት ነው ብሎ ተናገራቸው። እነሱም ተደናግጠው ወጡ። ከዚያም ሚስቱን የእኔ ፍቅር ሳገባሽ እኮ ልጅ ትወልጃለሽ ብየ ተማክሬ አላገባሁሽም ተረጋጊ እኔን ከአንች እሚለየኝ ሞት ነው አላት። እና ቃል ኪዳን ከአሰርኩልሽ ሀገር ኢየሩሳሌም እንሂድ ደግሜ ቃል ልግባልሽ አላት። እሷም እያለቀሰች በፍቅር አይን ቀና ብላ አይታ እሽ ውዴ አለችው። ከዚያም ወዲያው ኢየሩሳሌም ሄደው ገዳማትን ተሳልመው እሷም እሱም ተረጋግተው ተመለሱ። ከዚያም ይህ ሁሉ በሆነ በወሩ ሆስፒታል ሂዳ ስትመረመር ነፍሰጡር ሆነች። አሁን የ3 ልጆች እናት አባት ሆነው በአሜሪካ ይኖራሉ።
ለእግዚአብሔር እሚሳነው ነገር የለም
፨፨፨፨እውነተኛ ታሪክ ነው ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እባካችሁ አንዳንዶች በሰው ህይወት አትግቡ። አንዳንዶች ደግሞ የሰው አሉባልታ እየሰማችሁ የሰውን ህይወት አበላሽታችሁ ለራሳችሁም አትበላሹ። የትዳር አጋራችሁን አታሳዝኑ ለዝች አጭር እድሜ ለከፋው ዘመን ሰውና ሰው በሚባላበት መራራ አለም።
ከወደዱት ሸር ሸር ሸር ለወዳጅወ


✍️decha tube


@fkrnatafetro
ደሃ ስለሆንኩ ተወችኝ ይላል ።

ደሃ ስለሆነ አይደለም የተውኩት ስንፍናውን ድል እንዲነሳው እንዳግዘው ምቹ ስላልሆነ እነጂ ፤ እሱ ችግሩን የሚፈታው በጥቅስ ነው ።

ያለውም ይሞታል የሌለውም ይሞታል አይነት የደከመው ሰው ጥቅስ ውስጥ ስለሚወሸቅ ነው

ወዳጆቹ ፣ ቤተሰቦቹ ፣ ጓደኞቹ እና ዘመዶቹ ስላላገዙት ፣ ስላላበደሩት እሮሮ እንደሚያሰማ ሰው ደካማ የለም ፤ ከዚህ ሰው ጋ እንዴት ጎጆ እቀልሳለሁ ?

እሱ ጋ ስሆን እረፍት አይሰማኝም ፣ ነገ አያጓጓኝም ፤ ችግር ሲገጥመው የሚታገልበት መንገድ ጥቅስ ነው ፤ የተሸናፊዎች ጥቅስ አሸናፊ መፍጠር እንደማይችል አያውቅም ።

ህልም እንደሌለው ሰው ደሃ የለም ፤ ህልም አልባ መሆኑን ያከፋው የእኔን ህልም ቅዠት አድርጎ መቁጠሩ ነው ።

ማሬ አንድ ቀን በዚህ ሁለት አመት ራስህን ለመለወጥ ምን አደረግክ አልኩት
" በእናትሽ ይሄ አነቃቂ ንግግር ነው ኑሮሽን የሚያወሳሰበው ፤ እነሱ እንደሚሉት በመደመር ፣ በትግል አይደለም ኑሮ የሚቀየረው በአጋጣሚ እንጂ ፤ እጣ ፈንታችን ነው ነገሮችን የሚያደላድለው" አለኝ ።

እኔ በውርስ ሀብታም ከሆነ ይልቅ ታታሪ ህልም ያለው ደሃ እንደምመርጥ ውስጤ ያለውን እውነት ባወቀልኝ ፤ ስንፍናው ነገዬን የማጨለም አቅሙ ሲታየኝ ፣ ህልሜን ሲጋርደው ነው ከህይወቱ የሄድኩት ። እንኳን ሄድኩ !
© Adhanom Mitiku


@fkrnatafetro
ለፈገግታ 😊

ዋጣት!
°°°°°°
" Know ሲነበብ k ትዋጣለች "
አሄሄ መቼስ መሄጃ የለን
...እንደለሊት ፈስ ተዝናኑብን እኚ አዛውንት
" Fikre! "...አምባረቁ
" Yes teacher "
" Read know with silent K! "
ሳይለንት ለምን አሉ?
ያው አንብበህ ዝም በል ማለታቸው ይሆናል
አትበጥብጥ ሊሉኝ ፈልገው ብዬ፡
" ክኖው " አልኩና ጭጭ!
" Read it with silent K ጥፍሮ! "
እየቦነነ!...አለ አያ በዙ
ያቺ ፍንጃል ሆዴን ይቆርጠኝ ያዘ!
አንብበህ ዝም በል አላሉምንዴ?
" I am silent teacher " የምንተፍረቴን
አማተቡ...
" Kን ዋጣት! "
" ኧ? "
" K ን ዋጣት....የ'ንግዴ ልዥ! "
" እኔ ነኝ የምውጣት ቲቸር? "
የምሬን ነው ያኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ስሰማ ነበር
" የለ አዞ እናመጣለን ከ ጫሞ! "
አሁን ይሄ ትምህርት ነው?..
ምናምኑን እያዋጡ....በሽተኛ ሆነን ልንቀር ነዊ!
ለማልቀስ ፊቴን ሳጎሳቁል፡
" Don't even try! "....ምዝዝ ብለው
" እስኪ ታለቅስና..ዋጥ! ዋጥ! "
አሃ?!...ኧረ የሚዋጠው በዛ ህብረተሰቤ!
ካሱን አስነሱ...ካሱ ደግሞ ብብቱን ማከክ ይወዳል
ብብቱን እስኪያልበው ይገዘግዛል
ኳር..ኳር..ኳር..ኳር
" አንዴ ልጅ ካሱ! "
ኳር ኳርር......እየፎከተ
" Attention please! "....ኧረሱ'ቴ
ቅንቅን እንደበላው ዶሮ፡ ክንዱን ከፈት አድርጎ በማከክ የሚያገኛትን እርካታ በሞኝ ፊት ያጣጥማል
" በደምበጫው ሚካኤል!..ረሳኝንዴ? " አሉ ቲቸር!
ተንደርድረው ሁለቱን እጆቹን ወደላይ መዘዙለት
ወይ ካሱ!
ሁለቱ እጆቹ ተይዘው ራሱ የማከክ አምሮቱ!
ማከኪያ ሲያጣ በቁሙ ወገቡን መስበቅ ያዘ.....
.....አመል ክፉ
" አንት ዐበቃም!..አርፈህ ቁም! "
ካሱ ቆመላቸው
" Read Psychology with silent P! "
ከኔ የባሰ ነሆለል ነውና
" ፒሳይቾሎግይ " አለና አረፈው
" ሁሉንም ዋጥካቸው?! "
የክፍላችን ሊቅ ፍሬዘር፡ በንቀት ያየናል..
እየገላመጠን እጁን አወጣ
" ልጅ ፍሬዘር Doubt ን እስኪ አንብባት "
" ኦዩብት "
ቲቸር ደነገጡ
" ምን? የምን ኦዩብት? "
" አይ Dን ልዋጣት ብዬ ነው "
" ሳላበላሽህ ትፋት አንት ፋንድያ! "


✍️ Hanzibal mengeshaye



@fkrnatafetro
ተቀጣጠርን። ደመና ነገር ስለሆነ ከዘነበ እንዳይበርደኝ ብዬ ጃኬት ደረብኩ። ከሩቅ ምን ምታክል ቲሸርት ለብሳ ወደዚህ የምትመጣ ልጅ ትታየኛለች። አረማመዷ ልክ እሷን ይመስላል። ግን መቼስ ዶፍ ሊጥል እየተንጋለለ ያለውን ደመና አይታማ እንደዚህ ለብሳ አትመጣም... ብዬ እያሰብኩ ትንሽ ስትቀርበኝ ለካ እሷ ነች። አልገባኝም። ብቻ ግን ያም ሆነ ይህ ቲሸርቱ ግን በጣም ቆንጆ አርጓታል። በቃ ይሁን ብዬ ትንሽ walk እንዳረግን። ትንሽ ቆይቼ ሳያት እየተንቀጠቀጠች ነው። በረደኝ እቀፈኝ ማለቷ ይሁን? ብዬም አሰብኩ። No አላቅፋትም። እልህ ተያያዝኩ። አሁንም ዞር ብዬ ሳያት ጭራሽ ጥርሷ እየተንገጫገጨ ነው። አይይ አልኩና ጃኬቴን እንደ ህንድ አክተር ወለቅ አድርጌ አለበስኳት። ምንም አልቅማማችም...ላፍ አርጋ ልብስ። እየተጓዝን ነው። ብርዱም እንደቀጠለ ነው። የሸገር ብርድ ታውቁት የሌ። ራሴን ሳየው ብርዱ ድርቅ አርጎኛል። በረደህ እንዴ? አለችኝ። አዎ እንዳልል ወይ ወንድነቴ ወይ ደግሞ አይናፋርነቴ ይዞኛል። ብቻ ጅማቴን ወጣጥሬ..አይይ ምን ይበርደኛል እንደውም ሙቀቱን አልቻልኩም አልኳት። ከዚያ ለብዙ ሰዓታት ከተጨዋወትን በኋላ ሸኘኋት። ጃኬቴን ስጭኝ እንዳልል ውይ ለዚህች ቀለሙ እንኳን ምን አይነት እንደሆን ለማይታወቅ ጃኬት ብለህ ትስገበገባለህ? እንዳትለኝ ፈርቼ ዝም አልኩ። ጃኬቱኮ በቅርቡ 900 ብር የገዛውት ነው። ሄዴች።

ይህ የሆነው የዛሬ 3 ሳምንት ነው። ከዚህ ጋር ሶስት ጃኬት ለግሻለሁ።

ይህን የፃፍኩላችሁ ዛሬ ተቀጣጥረን በሼም ጃኬቴን ከምበላ ብዬ በቲሸርት ወጥቼ ዝናብ እስኪሰለቸው ቀጥቅጦኝ ገና ዶርም ከመግባቴ ነው።

የሆነ ቀን ጓደኛዬ በነሱ በር ሳልፍ የሚሸጡ ብዙ ሰልባጅ የሚመስሉ ጃኬቶችና ሼምዞች አይቻለሁ ማለቱን ሳስብ ነው ነገሩ በደንብ የገባኝ።😐

NK



@fkrnatafetro
ፈጣሪ ፍቅርን ያድለን ❤️
.
.
.
የሆኑ ባልና ሚስት ወደ አንድ እንስሳት ማቆያ ፓርክ በአጋጣሚ ይሄዳሉ ። እንዳጋጣሚ አንድ ዝንጀሮ አብራው ካለች ጓደኛው ጋር እየተጫወተ የነበረ ዝንጀሮ አገኙ ። የሰውየው ሚስት እንዲህ አለች “ምን አይነት ፍቅር ነው ! እንዲህም አይነት አለ እንዴ ? አለች በመገረም! "

ከዚያም ወዲያው ዘወርወር ማለት እንደጀመሩ ሌላ አንድ ወንድና ሴትአንበሳ ጎን ለጎን ተለያይተው ተቀምጠው አዩና ሚስትየዋ “ፍቅር የሌለበት ምን አሳዛኝ ትዕይንት ነው አለች በማዘን " ይህን የሰማው ባልተቤቷ እንዲህ አላት
“ያን ድንጋይ ወደ አንበሳይው ወርውሪና ተመልከቺ አላት ”
እሷም ድንጋዩን አንበሳው ላይ ስትወረውር አንበሳው አንበሳይቱን ለመከላከል ሲጮኽ አየች
ባልየውም ከዝንጀሮዋ ጋርም ድገሚው አላት እሷም ለአንበሳው እንዳደረገችው ዲንጋዩን ወደ ዝንጀሮው ስትጥል ወንዱ ዝንጀሮ ዘሎ ዛፍ ላይ ወጣና ራሱን ለማዳን ሴቷን ጥሎ ሄደ ።

ባሏም እንዲህ አላት “በምታይው ነገር አትታለይ ያየሺው ሁሉ ፍቅር አይምሰልሺ ፡፡ ብዙ ጊዜ ባዶ ልብን ለመደበቅ ሲባል የሚያታልል ገጽታ ወይም አስመሳይነት ይኖራል ፡፡ ሌሎች ደግሞ አሉ ዝምተኞች ፣ ልባቸው ግን ቅን የሆነ ።

በአሁኑ ጊዜ ፣ እንደዝንጀሮው የሆኑ ብዙዎች አሉ ፣ ጥቂቶች ደግሞ እንደ አንበሳው የሆኑ አሉ ።
ለማንኛውም ፈጣሪ ንጹህ ፍቅር ይስጠን!
#########################
በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ
ምንጭ :- ከወሬ ፏፏቴ

@fkrnatafetro
አንቺ የቀይ ዳማ ፦

በረከቴን ስለምታስታውሺኝ ፤ ድከመቴን ስለማታጎይው ፤ መውደድሽ ስለማያወላውል ፤ ከማንም ጋ ስተማታወዳድሪኝ ፤ ህፀፄን ሰለምትነግሪኝ ።

መውደዴን ስለሚገባሽ ፤ ስታጠፊ ስለምታጎነብሺ ፤ የጊዜ ሃያላነት ስለገባሽ ባምላክሽ ስለምትታከኪ ።

ስንጣላ መዓዘናችን ስለማትምረኳዢው ፤ አሳልፈሽ ስለማትሰጪኝ ። ስለምትተማመኚብኝ ሳገኝሽ ሰላም እና ጥንካሬ ይሰማኛል ።

አንቺን አለ መውደድ ምርጫ አለኝ ወይ?

እወድሻለሁ ።
© Adhanom Mitiku

@fkrnatafetro
#መልካምነት👉አጭር አስተማሪ ታሪክ

አንድ ሰው ሶሰት ጓደኞች ነበሩት በጣም ነው የሚወዳቸው ብዙ ነገር ያደርግላቸዋል ያደርጉለታልም አንድ ቀን አባቱ"ልጄ ጓደኞች አሉህ" አሉት "አዎ ሶስት ጓደኞች አሉኝ በጣም የሚወዱኝ የምወዳቸው" አላቸው፡፡ እርሳቸውም "ከእነዚህ ውሰጥ የልብ ጓደኛህ ማነው?" አሉት "ሁሉም" አለ "እርግጠኛ ነህ ልጄ" ሲሉት "አዎ" አለ፡፡ "እንደዚያ ከሆነ የሆነ ነገር እንፍጠርና እውነተኛ መሆናቸውን እናረጋግጥ" ይሉታና ጓደኞቹን እንዲፈትን ያደርጉታ፡፡ ልጁም አባቱ ባለው መሰረት ለአንዱ ጓደኛው ይደውልና "ያለጥፋቴ ሰው ገድለሃል ተብዪ ፍርድ ቤት ነኝ ድርሰልኝ" ይለዋል ጓደኛውም "አዝናለሁ አልችልም" ይለዋል፡፡ አሁንም ለሁለተኛው ይደውላል ሁለተኛ ጓደኛውም "ችግር የለውም እመጣለው እርዳታየም ካሰፈለገህ የምችለውን ሁሉ አደርግልሀለው ፍርድ ቤት ግን አብሬህ አልገባም አዝናለው" ይለዋል አሁንም ለሶሰተኛው ይደውላል ሶሰተኛውም "እንዴ ኧረ ችግር የለውም ደሞ ለአንተ አይደለም ፍርድ ቤት ሌላም ቦታ እመጣልሃለሁ" አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ይህ ልጅ በአባቱ ምክር እውነተኛ የህይወት ጓደኛው ማን እንደሆነ አረጋገጠ ።

#ፍርድ_ቤት_የተባለው_የሰው_ልጅ_ይችን_ዓለም_ተሰናብቶ_የሚኖርባት_የዘላለም_ቤቱ_ሲሆን

❶- #የመጀመሪያው_አልችልም_ያለው_ገንዘብ ነው መቸም የሰው ልጅ በዚች ምድር ሲኖር ምን ያህል ሀብት ቢኖረው ከሞት አያሰጥለውም በሞት ጊዜ ተከትሎን አይመጣም ።

❷- #ሁለተኛው_ፍርድ_ቤቱ_አመጣለው እረዳሃለሁ እንጅ አልገባም ያለው ዘመድ ወይም ጓደኛ ነው፡፡ በአጠቃላይ ሰው ምን ያህል ቢወድህ ያለቅሳል ያዝናል ወደ ቀብር ቦታህ አብሮህ ይመጣል እንጅ መቸም አንተ ሞተሀልና ልሙት አይልም።

❸- #ሶሰተኛው_እሰከ_መጨረሻው_አንተ_ጋር_ነኝ ያለው በዚች አለም ሰትኖር የሰራናቸው ጥሩና መልካም ሰራዎች ናቸው፡፡ በዚህ ምድር ላይ የምንሰራቸው ጥሩ ሰራወች የዘላለም ሰንቃችን ናቸው እስከ መጨረሻው ከአኛ ጋር ይከተሉናል፡፡

ሁሌም ጥሩ ነገር እናድርግ ምክንያቱም ከክፋት ደግነት ትልቅ ዋጋ አለውና ደግነት አንድ ቀን መልሶ ይከፍላል መልካምነት ለራስ ነውና።



ከ fb መንደር



@fkrnatafetro
አንድ ሰው በጣም የሚያፈቅራትን ፍቅረኛውን ይቀጥራታል ትንሽ ከተጨዋወቱ በኋላ አንድ የተጠቀለለ ስጦታ ይሰጣታል ፍቅረኛውም ከፍታ ስታየው አሻንጉሊት ነው ወዲያውኑ አመናጭቃ ስጦታውን ትወረውረዋለች፡፡

እሱም በመናደድ ግን ረጋ ብሎ “ምነው ውዴ ለምን ወረወርሺው?”
ይላታል “ይህን የልጅ ስጦታህን አልወደድኩልህም!” ትለዋለች፡፡
ይናደድና አሻንጉሊቱን ከወደቀበት አንስቶ ጥሏት ይወጣል፡፡ በሚያስጠላና በሚገርም አጋጣሚ ጥሏት በወጣ ቅጽፈት አስፓልት ሲሻገር መኪና ገጭቶት ህይወቱ አለፈች የቀብሩም ቀን ልጅት አሻንጉሊቱን ይዛ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች፡፡

በለቅሶዋ ማሃልም ውድ ፍቅረኛዋን በአሻንጉሊቱ ምክንያት በማጣትዋ
በቁጭት አሻንጉሊቱን ጭምቅ ታደርገዋለች ወዲያውም ከሻንጉሊቱ “Will you marry me?” #ታገቢኛለሽ? የሚል ድምጽ አወጣ፡፡
ልጅቷ አልቻለችም መሬት ላይ ተዘረረች፡፡

ስትወድቅም ከአሻንጉሊቱ ኪስ ሁለት ቀለበቶች እና አንድ አጭር
ጽሑፍ ወደቀ ጽሑፉ እንዲህ ይላል. . . የኔ ፍቅር ለዘላለም ላልከዳሽ ልታመንልሽ በፍቅር ስም ቃል እገባልሻለሁ!!

የወጣት ወግ

@fkrnatafetro
#ትዳር
====================
ሚስትህን ካስረገዝካት በኋላ እንዴት እንደ ኮረዳዎች አማላይነት እንዲኖራት ትጠብቃለህ? አስረገዝካት እኮ ከወለዳችሁ በኋላም አንተና ልጆችህ ለመመገብ ደፋ ቀና ትላለች ብትታመም ራሱ የቤቱ ስራ አይቀርላትም ኩሽና ብቻ ዓለም እንዲሆናት ፈርደህባታል ሚስትህን የዚህ ህዝብ ኋላቀር ባህል ሰለባ አድርገሃታል።

የኢትዮጵያ ሴቶች ብዙ ሸክም ችለዋል በተለይ ያልሰለጠነ ሰው ያገቡ ሴቶች ደህና መልበስ መሰልጠን እየመሰላቸው፣ ደህና መኪና ማሽከርከር መሰልጠን እየመሰላቸው ብዙ ሴቶች ተጎድተዋል ባል ሲመርጡ ህልማቸው ተበልተዋል።

ብር ያለው ወንድ ማግባት ጥሩ ነው ብር ስላለው ግን አይደለም ያ ብር ማንነቱን ደብቆበት እንደ ልቡ ይሆናል
ብር የሌለው ሰው (ወንድም ሴትም) ብዙ ጊዜ ራሱን ለመሆን ይቸገራል

የፊታቸውን መከፋት በሜክአብ የሸፈኑ በትንሽ ነገር ብዙ የሚበሳጩ ሴቶች ታክሲ ውስጥ ታገኛለህ እነሱ ህልማቸው የተበሉ ሚስቶች ናቸው ደግሞ አሉ መጠጥ ቤቶች ውስጥ በአማላይ ኮረዶች የተሞሉ እዚያ የሚያንዣብቡ ወንዶችም አሉ እነሱ እነዚያ ያልሰለጠኑ ባሎች ናቸው የሚስቶቻቸው አናት ላይ ወጥተው የረዘሙ

ሁለቱም ተጋቢዎች (ወንዷና ሴቱ) ያሳዝናሉ የእውቀት እጥረትና የኋላቀር ባህል ሰለባ ናቸው ትዳር ጥሩ ነው የእውቀት እጥረትና የኋላቀር ባህል ሰለባ ከመሆን ራስን መጠበቅ ግን ያስፈልጋል

ካነበብኩት
2025/02/27 01:23:08
Back to Top
HTML Embed Code: