Telegram Web
Audio
አንደኛ ጴጥሮስ ትርጓሜ 3
በዲ/ን አሸናፊ መኮንን
👉 ቻናሉን ተቀላቀሉ @DnglMaryamey 💛💚💙
👉 ቻናሉን ተቀላቀሉ @DnglMaryamey 💛💚💙
👉 ቻናሉን ተቀላቀሉ @DnglMaryamey 💛💚💙
ዲኒ እና በዉቄ
Daniel_bewketu
❍✰ድንገቴ✰❍

➲በጣም ደስ የሚትል ወግ ናት አድምጧት!
➲ፀሐፊው ፦ዳንኤል ክብርት
➲አቅራቢ ፦አንዱዓለም ተስፋዬ

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
👉 ቻናሉን ተቀላቀሉ @ZkreMetsahft
👉 ቻናሉን ተቀላቀሉ @ZkreMetsahft
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟
ንፅረተ-ፍቅር

💚💛❤️

አብዛኞቻችን "ፍቅር" ሲባል ከሰማን እዝነልቦናችን ላይ የሚመጣብን በወንድና በሴት መካከል ያለው የመቀራረብ ስሜት ነው ። በእርግጥም እንዲህ ያለው ፍቅር ተጨባጭና ለተመልካች ግንዛቤ የማያዳግት ነው ። ተጨባጭነቱንና ግልፅነቱን ያገኘው በቴአትሮች ፣ በሆሊውድ ፊልሞች ወይም በፍቅር ልቦለዶች ብርታት ነው ማለት አይቻልም ። በነባሩ ባህል ውስጥ ስንመለከት የኖርነው እንዲህ ያለው የወንድና የሴት ፍቅር ወደ አንድ አካልና አንድ አምሳልነት ሲያመራ ነው ።



ፍቅር አይነቱ ብዙ ነው ። በፆታዊ ፍቅር ብቻ አይገደብም ። የመጽሐፍ ቅዱሱ ንጉስ ዳዊት ቤርሳቤህን በማፍቀር ብቻ እሷን አግኝቶ አልተገታም ። በህይወቱ ውስጥ ሌላም አይነት ፍቅር እንዳለ አሳይቷል ። ለምሳሌ ለዮናታን ከፍተኛ ፍቅር ነበረው ከዚህም ባሻገር ልጁ አቢሴሎም ሲሞትም "አቢሴሎም ልጄ ልጄ" ሲል በተሰበረ ልብ ፍቅሩን ገልጿል ። ስለዚህ የጓደኝነትና የስጋ ዝምድና ፍቅር እንዳለ በዚህ እንረዳለን ። በፕሌቶና በሶቅራጥስ እንዲሁም በኢየሱስና በደቀመዛሙርቱ መካከል የነበረው ደግሞ እውቀትን ወይም ሃይማኖትን ተንተርሶ የሚመጣውን ፍቅር ይገልፅልናል ። በዚህ አይገታም የሰው ልጅ አገሩን፣ ወገኑን ፣ አቋሙን ፣ ቤተሰቡን ፣ አምላኩን በማፍቀር የተለያየ ፍቅር መኖሩን አሳይቷል ።

❇️ @ZkreMetsahft ❇️
❇️ @ZkreMetsahft ❇️

የተለያዩ ግንኙነቶችን እራሳቸውን አስችለን የምንወክልበት መጠርያ ስለምናጣላቸው በጋራ ስያሜ የምንደፈጥጥበት ግዜ ብዙ ነው ። ፍቅርም አይነቱ ብዙ ቢሆንም አንዱን ካንዱ የሚለይ ስም ግን ሲውጣለት አይታይም ። ይሄንን ክፍተት ተመልክተው ለፍቅር አይነቶች ሶስት መጠርያ ያዘጋጁ ግሪኮች ናቸው ። "ፊልያ" (Philia) ፣ "ኢሮስ" (Eros) ፣ እና "አጋፔ" (Agape) ይሏቸዋል ። ምናልባት በጥሬው ብንተረጉማቸው "የወዳጅነት" ፣ "የምኞት" እና "የልግስና" የፍቅር አይነቶች ልንላቸው እንችላለን ። ፊልያ በንጉስ ዳዊትና በዮናታን መካከል የነበረውን የጓደኝነት ፍቅር ይወክላል ። ኢሮስ ደግሞ አፍቃሪው ተፈቃሪውን በማግኘት እርካታን የሚቃብዝበት አይነቱ ነው ። በወንድና በሴት መካከል የሚከሰተውን ማለታችን ነው ። አጋፔ ደግሞ መንፈሳዊ ፍቅር ሆኖ በሰውና በፈጣሪው ወይም በሰዎች መካከል ይከሰታል ። በቅዱሳት መጻህፍት አማካኝነት አምላክ ለሰው ልጆች ያሳየው ፍቅር በአጋፔ ውስጥ የሚጠቃለል ነው ። በአፀፋው ሰዎች ስለፈጣሪያቸው የሚቀበሉት መከራና ሞት የዚሁ የፍቅር አይነት ውጤት ነው ።

ምኞት ያለበት ኢሮስን ጨምሮ ሶስቱም አይነት ፍቅሮች የተሸጋጋሪነት ጠባይ አላቸው ። ስለዚህ ፍቅር ሁልግዜም ከአንዱ ወደ ሌላው የሚያነጣጥር ጥልቅ ስሜት ነው ለማለት ተገደናል ። ነገር ግን እራስ አፍቃሪነትስ? የት ይመደባል? "ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ" የሚለው የአምላክ ትእዛዝ ለእራስ አፍቃሪነት እውቅና አይሰጥም? የስነ-ምግባር ሰዎች እና የስነ-ልቦና ምሁራን እራስን ማዕከል ያደረገ ፍቅርን ጤናማ ያልሆነ ስሜትና ያለመብሰል ምልክት አድርገው በመፈረጅ ያጥላሉታል ። የሃይማኖት ጉባኤዎችም ለራሳችን እራሳችን የምናሳየውን ፍቅር ያወግዙታል

❇️ @ZkreMetsahft ❇️
❇️ @ZkreMetsahft ❇️


ምንጭ ፦ " የፍልስፍና አፅናፍ "
ደራሲ ፦ ዶክተር ሞርቲመር ጄሮም
ትርጉም ፦ ዓለማየሁ ገላጋይ

፨ በነገራችን ላይ ባሁን ሰአት ግሪኮች ከላይ ከጠቀስናቸው ሶስቱ የፍቅር አይነቶች በተጨማሪ አራተኛ ስተሪጅ(Sturige) ወይም "ቤተሰባዊ ፍቅር" የሚሉት አይነት ፍቅር እንዳለም ያምናሉ አንዳንድ መጽሀፍትም በዛ መነሻነት ፍቅርን በአራት ከፍለው ይገልጹታል ።

ስለ ፍቅር የቀረበውን ሃሳብ ወደዳችሁት
ከወደዳችሁት ()

ለተጨማሪ ተቀላቀሉን

❇️ @ZkreMetsahft ❇️
❇️ @ZkreMetsahft ❇️
Forwarded from የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች
*አስገራሚው የደብረ ሊባኖስ ቤተክርስቲያን ታሪክ፦

*1362 ዓ.ም. የአቡነ ተክለሃይማኖት ዐጽም ከደብረ አስቦ ፈልሶ ዔላም በእመቤታችን ስም በተሠራው የመጀመሪያው ቤተከርስቲያን ገባ።በዚያም ለ40 ዓመታት ኖረ።

*በ1402 ዓ.ም.ሁለተኛዋ ቤተክርስቲያን በደብረ አሰቦ አጠገብ በእመቤታችን ስም በእጨጌ ቴዎድሮስ ዘመን ታነፀች።ታቦተ ማርያምና የአባታችን ዐጽም ወደዚች ቤተከርስቲያን ገባ።

*1406-1420 ዓ.ም. በዐፄ ይስሐቅ ዘመን በእጨጌ ዮሐንስ ከማ አማካኝነት ሦሰተኛዋ ቤተክርስቲያን በእመቤታችን ሰም ተሠርታ ሰኔ 21 ቀን ቅዳሴ ቤቷ ተከበረ።የአቡነ ተክለሃይማኖት ዐጽም ግን እጨጌ ቴዎድሮስ በሠሩት ቤተ ክርስቲያን ቆየ።

*በ1474 ዓ.ም. እጨጌ መርሐ ክርሰቶስ (1455-1489 ዓ.ም.) አራተኛዋን የእመቤታችንን ቤተ ክርሰቲያን አሠራ።

*1488.1500 ዓ.ም. በዐፄ ናዖድ ዘመነ መንግሥት የአቡነ ተክለሃይማኖት ዐጽም ለሦስተኛ ጊዜ ፈልሶ እጨጌ መርሐ ክርሰቶስ ወዳሠሩት የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ገባ።

*1500-1533 ዓ.ም.በዐፄ ልብነድንግል ዘመነ መንግሥት አምስተኛው ቤተ ክርስቲያን በእጨጌ ጴጥሮስ አማካኝነት ተሠራ።ግራኝ ሐምሌ 24 ቀን 1523 ዓ.ም.ያቃጠላት ይህችን ቤተ ክርስቲያን ነው።

*1533-1551 ዓ.ም. በዐፄ ገላውዴዎስ ዘመነ መንግሥት በእጨጌ ዮሐንስ አማካኝነት ስድስተኛው ቤተ ክርሰቲያን ተሠራ።

*1603 ዓ.ም የደብረ ሊባኖስ ማኅበረ መነኮሳት ወደ ጎንደር በዐፄ ሱስኒዮስ ዘመን ተሻገሩ።ገዳሙም እየተዘነጋ ሄደ።

*18ኛው መክዘ  መነኮሳት ወደ ጥንቱ ደብረ ሊባኖስ መመለስ ጀመሩ።

*1804 ዓ.ም. የሸዋው ንጉሥ ወሰን ሰገድ ሰባተኛውን ቤተ ክርስቲያን አትጋፊኝ በተባለው ቦታ ላይ ሠሩ።ነገርግን ከወራት በኋላ ተቃጠለ።

*1873 ዓ.ም. ዐፄ ዮሐንስ የጥንቱን ቤተ ክርሰቲያን ቦታ አስፈልገውና አስመንጥረው 8ኛውን ቤተ ክርስቲያን ሥራ በአኩስም ጽዮን መልክ ባለ 16 ጉልላት አድርገው ጀመሩ

*1885 ዓ.ም. ዐፄ ዮሐንስ ያሠሩት ቤተ ክርስቲያን ከ12 ዓመታት በኋላ የውጭና የውስጥ ሥራው አልቆ ታቦቱ ገባ።

*1895 ዓ.ም. ዐፄ ምኒልክ 9ኛውን ቤተ ክርስቲያን ማሠራት ጀመሩ።

*1900 ዓ.ም.ዘጠነኛው ቤተክርስቲያን ተጠናቀቀ።

*በ1929 ዓ.ም.ግንቦት 12 ቀን በግራዝያኒ ትእዛዝ የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት ተጨፈጨፉ።ቤተ ክርስቲያኑ ተቃጠለ፤ቅርሱ ተዘርፎ ሮም ተወሰደ።

*በ1952 ዓ.ም. ዐፄ ኃይለ ሥላሴ አሁን ያለውውን 10ኛውን ቤተ ክርስቲያን ማሠራት ጀመሩ።

*በ1955 ዓ.ም. አሁን ያለው ዐሥረኛው ቤተ ክርስቲያን ተጠናቀቀ።

የመረጃ ምንጭ፦/ዲ.ዳንኤል ክብረት,ኢትዮጵያዊው ሱራፊ፣945-946/
https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAEtPKw4R0R3kxdPyPQ
https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAEtPKw4R0R3kxdPyPQ
ሶቅራጥስ
(ክፍል ፩)

📖📖📜📖📖

ሶቅራጥስ የተወለደው አቴንስ ግሪክ በ469 ዓ.ዓ እንደሆነ ይታመናል እናቱ ፌናሬት ትባል የነበረች አዋላጅ ስትሆን፣ አባቱ ሶፎሮኒስከስ ደግሞ አናፂ ነበር ። የዛኔዋ ግሪክ፣ በተለይም ደግሞ አቴንስ የተለያዩ ሀሳቦች መንሸረሸርያ፣ የታላላቅ ፈላስፎች መገኛ እንዲሁም የዲሞክራሲ መፍለቅያ በመሆኗ ትታወቃለች ። ሶቅራጥስ ደግሞ አገሩን የሚያፈቅር አቴናዊ የነበረ ሲሆን፣ ከከተማይቱ መውጣትንም የማይወድ ሰው ነበር ።ያም ሆኖ ለአገሩ ለመዋጋት ሶስት ግዜ ተሰልፏል ። በጦር ሜዳም የሚያስመሰግን ጀብዱ እንደሰራ ይነገራል ።

📖📖📖

ሶቅራጥስ ዛንቲፕ የተባለች ሚስት የነበረችው ሲሆን ሦስት ልጆችንም አፍርተዋል ። ዛንቲፕ በጣም ነዝናዛ እንደነበረች ይነገራል ። የሶቅራጥስ ወዳጆች ለምን እንደማይፈታት ሲገረሙ፣ ሶቅራጥስ ግን ስለትዳር እየቀለደ እንዲህ ይላል ፦ "ምንም ቢሆን ማግባት ጥሩ ነው ። ጥሩ ሚስት ካገባህ ደስተኛ ትሆናለህ፤ ካልቀናህ ደግሞ ፈላስፋ ትሆናለህ ።" ስለ ሶቅራጥስ ህይወትም ሆነ ትምህርቶች ለመረዳት ያሉት ዋነኛ ምንጮች የአራት ፈላስፎች ጽሁፎች ሲሆኑ፣ እነዚህ አራት ፈላስፎችም አሪስቶፋነስ፣ ዜኖፎን፣ ፕሌቶ እና አርስቶትል ናቸው ።

📖📖📖

በሶቅራጥስ ዘመን ሰፊ ተቀባይነት የነበራቸው የፍልስፍና መምህራን ሶፊስቶች ነበሩ ። ሶፊዝም፣ ሰው ልክ ነው ብሎ ከሚያምንበት ውጪ እውነት የለም ብሎ ያስተምራል ። ሶቅራጥስ በመልካም ምግባር እና በግብረገብነት የፖለቲካዊ ስልጣን የመያዝ ተስፋ ያላቸውን ወጣቶች የመቃኘት ምኞት ነበረው ። ለዚህ ደግሞ የሶፊስቶች ትምህርት እንቅፋት ሆኖ እንደታየው አይጠረጠርም ። እናም እውነትን መፈለግ፣ እውነትን በመፈለግ ውስጥ ደግሞ ዕውቀትን መሻት እንደሚያስፈልግ ማስተማር ጀመረ ። ለሚያስተምረው ትምህርት ፈጽሞ ክፍያ የማይቀበል ሲሆን፣ ለኑሮው ገቢ ከየት ያገኝ እንደነበር ብዙም ግልፅ አይደለም ።

📜📜📜

አንድ ግዜ ኬሬፎን የሚባል የሶቅራጥስ ወዳጅ፣ የግሪኮች አምላክ የሆነው የአፖሎ ቤተመቅደስ ወደሚገኝበት ደልፊ ተጉዞ ከሶቅራጥስ የበለጠ ጠቢብ ይገኝ እንደሁ የአፖሎን ካህን ይጠይቃል ። የካህኒቱ መልስ " ከሶቅራጥስ የሚልቅ ጠቢብ አይገኝም " የሚል ነበር ። ይህ ለሶቅራጥስ እራሱን የሚቃረን ነገር ሆነበት፤ ምክንያቱም እርሱ ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ያምናልና ። ሶቅራጥስ ምን ያህል እውቀት ቢኖረው እንዲህ እስከመባል እንደደረሰ ሲጠየቅ የሚሰጠው መልስ " ያለኝ እውቀት ምንም አለማወቄን ማወቄ ነው " የሚል ነበር ።

📜📜📜

ሶቅራጥስ በጥልቀት በማሰብም ያምን ነበር ። ሰዎች የእውቀት ብርሃን እንዲበራላቸው ከፈለጉም በጥልቀት ማሰብን ልማድ ሊያደርጉ እንደሚገባ አስተምሯል ። ለእርሱ ማሰብ እጅግ ውብ እና አስደሳች፣ የዛኑም ያሃ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው ። አንድ ማለዳ ሶቅራጥስ ሊፈታው የቸገረውን ጉዳይ እያብሰለሰለ ረዥም ሰአት እንደቆመ ይነገራል ። ሐሳቡ አልቋጭ ቢለውም ሊተወው አልፈለገም ። ጎህ ሲቀድ የጀመረውን ሐሳቡን እኩለ ቀን ላይም ከቆመበት ሳይንቀሳቀስ ማብሰልሰል ቀጠለ ። እኩለ ቀን ሲሆን.....ሰዎች ጉዱን ለማየት ተሰበሰቡ ። ሶቅራጥስ ግን ፀሐይ ስታሽቆለቁልም ያላንዳች መረበሽ ሀሳቡን ገፋበት ። አንዳንድ ሰዎች ሌሊቱን ቆሞ ይቆይ እንደሁ ለማየት ከየቤታቸው ምንጣፍ ይዘድ ተመልሰው እዛው አንጥፈው ሲከታተሉት አነጉ ። ንጋት ላይ ሶቅራጥስ ለፀሐይቱ ምስጋናውን አድርሶ ሄደ። በቃ ጉዳዩ ይኸው ነበር - ማሰብ ።

📖📖📖

ፕሌቶ፣ ሶቅራጥስን "የማኅበረሰቡ ተንኳሽ" ሲል ይገልጸዋል ። "ኃይል ፍትህን ይገዛል" የሚለውን እምነት ሶቅራጥስ በጽኑ ይኮንን ነበር ። አቴንስ ደካማ የሚባሉ ግዛቶችን በጉልበቷ ተማምና ስትወር፣ ሶቅራጥስ አቴንስን ተቃውሟል ። ሰዎች በግላቸው እራሳቸውን ለማሻሻል መጣር እንዳለባቸው፣ ቁሳዊ ሀብት ሲሹ ከመኖር ይልቅ ራስን ለመለወጥ መሞከር ለሰዎች እንደሚበጅ አስተምሯል ።ብዙ ጊዜም ለወዳጅነት ዋጋ እንዲሰጡ ተከታዮቹን ይመክር ነበር ። ድንቅ የሚባል ሕይወትም መልካምነትን በመፈለግ ያለፈ ሕይወት እንደሆነ ተናግሯል ። ሶቅራጥስ ለአስተምህሮዎቹ ሕይወቱን እስከመክፈል ድረስ ቆራጥነቱን ማሳየቱ ደግሞ ተጽዕኖው ስር የሰደደ እንዲሆን አድርጎታል ።
ይቀጥላል....

፨፨፨

ክፍል ፪ ይቀጥላል
በንባብ አብሮነታችሁ ከኛ ጋር መሆኑን በ 👍ግለጹልን
ያነበቡትን ለወዳጅዎም ያጋሩ

ለመቀላቀል

👇👇👇👇
@ZkreMetsahft
@ZkreMetsahft
Forwarded from Quality ButtonSCAM
ለሁላችሁ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን የሚመለከት ነው!
መንፈሳውያን መጻሕፍት እና ሌሎች ለህይወት መርህ የሚያግዝ ብዙና አዳዲስ መጻሕፍት የምታገኙበት ቻናል እንሆ ብለናል !
ለአንድ ጥበበኛ "እገሌ እኮ መብረር ይችላል"አሉት፡፡
"ምኑ ይገርማል ታድያ ከእርሱ ያነሱት እነ ዝንብ እና ትንኝ ሁሉ ይበሩ የለም እንዴ!" በማለት አጣጠለባቸው፡፡
"እንትና እኮ ውሃ ላይ መሄድ ይችላል፡፡"አሉት፡፡
"ምኑ ይገርማል ታድያ ቁራጭ ጣውላም ባህር ውሃ ቢጥሉት አይሰምጥም ውሃ ላይ ይሄዳል እኮ" አላቸው፡፡
.
"እንግዲያውስ ባንቱ እይታ ገራሚው ነገር ምንድነው?" አሏቸው፡፡
እጅግ አስደናቂው ነገር ሰዎች የቱን ያህል ቢያጠፉም አለማጥፋት ፤ የያዙት አላማና መርህ ሳይለቁና ሳይስቱ በከባድ ፈተናዎች መሃል ከሰዎች ጋር መኖር
አለመዋሸት
አለመስረቅ
አለማታለል
እምነት ለጣሉብህ መታመን ፤
የተማመኑብህን አለማሳፈር ፤
ሰዎችን በየትኛውም መልኩ ቀልባቸውን አለመስበር፡፡

እጅግ አስደናቂ ነገር ይህ ነው፡፡
ሰው በጠፋበት ዘመን እውነተኛ ሰው መሆን መቻል ነው፡፡
💚💛💜 @ZkreMetsahft 💚💛💜
💚💛💜 @ZkreMetsahft 💚💛💜
ሶቅራጥስ...
ክፍል ፪
( የመጨረሻው ክፍል )

🗒🗒🗒

ሶቅራጥስ በተራው ሕዝብ ዘንድ እጅግ ተውዳጅ ሆኖ ነበር ። ያላንዳች ክፍያ የሚያስተምራቸው ተማሪዎቹ ደግሞ አለመጠን ያፈቅሩት ነበር ። ይህ ግን ጠላቶች አልነበሩትም ማለት አይደለም ። ቀድሞ ነገር፣ ያለው ሰፊ ተቀባይነት በራሱ ስማቸው ገናና የነበረ የሶፊስት ፈላስፎች በክፉ ዐይን እንዲያዩት አድርጎታል ። ሶቅራጥስ በዘመኑ እንደነበሩት የፍልስፍና መምህራን ራሱን የማይኮፍስ፣ እንደውም ምንም እንደማያውቅ የሚናገር አዲስ አተያይን ይዞ የመጣ ሰው ነው ።
"የግሪክ ሰዎች እኔን እጅግ ጠቢብ ቢያደርጉም እኔ ደግሞ የማውቀው አለማወቄን ነው፤ አለማወቄን ማወቅ ብቻ ሳይሆን አውቃለሁ ብዬም አስቤ አላውቅም " በማለት ስለራሱ ይናገር ነበር ።

📜📜📜

ተከራካሪዎችን ተከታታይ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ብቻ ራሳቸውን እንዲቀረኑ በማድረግ(ፓራዶክስ) ዘዴው ብዙ የአቴንስ የተከበሩ የሚባሉ ሰዎችን በራሳቸው ንግግር እየጠለፈ ጅል ያስመስላቸው ነበር ። እንደውም ከተከራካሪዎቹ ሙግት ይልቅ የአድማጩ ሳቅ እንደሚያስቸግረው ይናገር ነበር ። "እውነትን ብቻ መፈለግ እና ለእውነት መቆም" የሚለው እምነቱ በርካታ ፖለቲከኞች ጥርስ ውስጥ ከመግባት አላስቀረውም ። ይህ እንዳለ ሆኖ፣ ወጣቱ ትውልድ ለሶቅራጥስ ያለው ስሜት እና ለእርሱ ያለው ታማኝነት ልዩ ነበር ።
" ሰው ከእንስሳ የሚለየው በማሰቡ ነው " የሚለው ሕግ ለሶቅራጥስ ቦታ የለውም ። ምነው ቢሉ " ማሰብ የለየው ሰውን ከእንስሳ ሳይሆን ሰውን ከሰው ነው " ይለናል ። "ለግሪክ አማልክት ሕዝቡ የሚሰግደው ስለሚያምንባቸው ሳይሆን ማሰብ ስለማይችል ነው " በማለት ይሳለቅባቸው ነበር ። ሶቅራጥስ በአቋሙ ኢ-አማኒ አልነበረም የብዙ አማልክትን መኖር ግን የሚነቅፍ በአንድ አምላክም መኖር የሚያምን ነበር ።

📖📖📖

#ሶቅራጥስ እና ክስ

የሶቅራጥስ "ትንኮሳ" እረፍት የነሳቸው እና ከዚህ በላይ ሊቋቋሙት እንደማይችሉ የተሰማቸው የአቴንስ ኃያላን የራሳቸውን ምስክሮች በማዘጋጀት "በአማልክቱ ባለማመን" እና "ወጣቶችን በማበላሸት" ክስ አቀረቡበት ። ለክሱ ያቀረበው መከላከያ "የሶቅራጥስ አፖሎጂ" በሚል ርዕስ በፕሌቶ የተመዘገበ ሲሆን፣ እንደዘወትር ንግግሩ በዋዛ የተቀመመው አቀራረቡ ከፍልስፍና ዘመን አይሽሬ ንግግሮች አንዱ ሆኖ ይጠቀሳል ።

📜📜📜

ሶቅራጥስ የክስ መከላከያ ንግግሩን ያገባደደው እንዲህ በማለት ነበር ...
"...ጠላቶች አሉኝ ። የምጠፉ ከሆነ መጥፊያዬ የሚሆኑትም እነርሱ ናቸው....ይህ የዓለም ክፋት እና አሳሳችነት ለብዙ መልካም ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኗል፤ ለሌሎች ብዙዎችም መሞቻ ምክንያት ይሆን ይሆናል ። የመጨረሻ እሆናለሁ ብዬ አላስብም "
" 'ሶቅራጥስ፣ ለዛሬ ትተንሃል፤ ብቻ በዚህ መንገድ መመርመርህን እና መጠየቅህን አቁም። እንዲህ ስታደርግ ብትያዝ ግን በሞት ትቀጣለህ' ብትሉኝ...መልሴ የሚሆነው እንዲህ ነው ፦ የአቴንስ ሰዎች ሆይ፣ አከብራችኋለሁ፤ እወዳችኋለሁ። ነገር ግን ከእናንተ ይልቅ አማላክን ልታዘዝ ይገባኛል ። ሕይወቴ እስካለች እና ብርታት እስካለኝ ድረስ ፍልስፍናዬን ከማስተማር አልቦዝንም ።...."

📖📖📖

በክሱ ጥፋተኛ መሆኑ ከተወሰነበት በኋላ ምን ዓይነት ቅጣት እንደሚሻለው እንዲመርጥ ሲጠየቅ ሶቅራጥስ የአቴንስ በጎ አሳቢና አጋዥ በመሆኑ ደመወዝ እንዲቆረጥለትና ሕይወቱን ሁሉ በነፃ እራት እንዲቀርብለት ጠየቀ ። ለፈገግተ ትዕግስት ያልነበረው ችሎት ግን ሶቅራጥስ ሄምሎክ የተባለውን መርዝ ጠጥቶ እንዲሞት ፈረደበት ። ሶቅራጥስ ከብያኔው በኋላ በችሎቱ ላይ የተናገረው የመጨረሻ ንግግር እንዲህ የሚል ነበር ። "የመለያያች ሰአት ደርሷል፣ እናም በየመንገዳችን እንሄዳለን ...እኔ ወደ ሞት እናንተ ደግሞ ወደ ህይወት ። የቱ እንደሚሻል አምላክ ያውቃል።"

📜📜📜

ወዳጆቹ ሶቅራጥስ ከእሥር ቤት እንዲያመልጥ መንገድ አመቻችተውለት ነበር ። ሶቅራጥስ ግን ለማምለጥ ፍቃደኛ አልሆነም ። እንዲህ ያለ እርምጃ የሞት ፍርሃትን ያመለክታል፤ እንደ ሶቅራጥስ አባባል ደግሞ እውነተኛ ፈላስፋ ሞትን ከቶ አይፈራም ።

🗒🗒🗒

የሞት ፍርዱ በሚፈጸምበት እለት፣ ሶቅራጥስ በወዳጆቹ እና ተማሪዎቹ ተከቦ እንዳለ የወህኒው ዘበኛ መርዙን በስኒ ይዞለት መጣ። .......ሶቅራጥስ ስኒውን በፍጹም እርጋታ አንዳችም ለውጥም ሆነ ፍርሃት ሳይታይበት ሰውዬውን በሙሉ አይኑ እያየ ተቀበለው ። ጥቂት ቆይቶ ደስታ ፊቱ ላይ እየተነበበ ባንድ ትንፋሽ ጨለጠው ። የሶቅራጥስ ሞት፣ የኖረለት እና የሞተለት ትምህርቱ ይበልጥ እንዲሰፋ እንጂ ተዳፍኖ እንዲቀር ሊያደርግ አልቻለም ።

🗒🗒🗒

ሁለት ሺህ ዓመታት ገደማ ቆይቶም የሶቅራጥስ ሞት የእውሮፓ ሕዳሴ ታሪክ ውስጥ ዋነኛ መነሳሻ፣ የነፃነት እና የሞራል መታደስ አርማ ሆኖ አገልግሏል ። በዘመናዊ ፍልስፍና ውስጥ ሶቅራጥስ ያለው ስፍራ እጅግ ከፍ ያለ ነው ። እንደውም "የዘመናዊ ፍልስፍና እና የሞራል ፍልስፍና አባት" ተብሎ ይጠራል ። የሶቅራጥስ የመጠይቅ ዘዴ በሕግ እና ፍልስፍና ትምህርት ቤቶች ለሙግት ጥቅም ላይ ይውላል ።



፨፨፨

📝 ለጽሑፉ ግብአትነት የተጠቀምናቸው መጽሐፍት
📖 "ተምሳሌቶቹ" በደራሲ ፦ አዲስ አሰፋ እንዲሁም
📖 "ጥበብ" ከጲላጦስ በደራሲ ፦ ኃይለጊዮርጊስ ማሞ

ይቀላቀሉን
@ZkreMetsahft
@ZkreMetsahft
@ZkreMetsahft
መንደርተኝነትና ሕዝብነት

📗📒📕

መንደረኛነት ማለት ከመንደር በማይወጣ አስተያየት ከመንደር በማይወጣ አስተሳሰብና ከመንደር በማይወጣ ስሜት መመራት ነው ፤ በዚህ አይነት ሁኔታ ለሚኖሩ ሰዎች ዓላማቸው መንደራቸው ነች ከዚያች መንደር ውጪ ሌላ ዓለም የለም ፤ ቢኖርም የሚንቁትና የሚጠሉት ነው ፤ መንደረኛነት በግድ ብዙ የአስተሳሰብ ግድፈቶችን ያስከትላል ፤ የራስን መንደር የዓለም እምብርት የሆነችና ዓለምንም ኢምነት አስመስሎ በመገመት ፣ መንደርዋን ወሰን-የለሽ በማድረግ እይታን ያጠናግራል ፤ በአስተሳሰብም ደረጃ መንደረኛነት ቁሞ-ቀር ያደርጋል ፤ የአካል ፣ የአእምሮንና የመንፈስን እድገትና እርምጃ ያፍናል ፣ መንደረኛነት የታሪክን መሠረትና የታሪክን ትክክለኛ አካሄድ ለመረዳትና የታሪኩ ባለቤት ለመሆን የሰው ልጅ ያለውን ችሎታ በመቀነስ ትልቅ እንቅፋት ይሆናል ።

🗒🗒🗒

የመንደረኛነት መነሻውም መድረሻውም መንደሩ ነው ፤ ከመንደሩ የሰፋ ፣ የላቀና የረቀቀ ነገር አይታየውም፤ መንደረኛነት የሚጀምረው እዛው በቅርቡ የሚታየውንና የሚሰማውን መሰረት በማድረግ ነው፤ ይህ የመንደረኛነት መሠረት ምንድን ነው? ዘር ነው፤ ቋንቋ ነው፤ ሃይማኖት ነው፤ ባህል ነው፤ መንደረኛነት ባህል ምንድን ነው? ብሎ አይጠይቅም፤ መነሻውም መድረሻውም የመንደሩ ቋንቋ የመንደሩ ሃይማኖት የመንደሩ ባህል ከሌላው ሁሉ የተሻለና የበለጠ ነው የሚል ጠባብ አስተያየት ነው መነሻውም ሆነ መድረሻው ልዩነትን ማጉላት ነው ።

🗒🗒🗒

ለመንደረኛነት አንድነት ማለት ተመሳሳይነት ነው፤ ተመሳሳይነትንም እንደአንድነት ብንቀበለው የተፈጥሮ ተመሳሳይነት ነው? ወይስ በልማድ ወይስ በኑሮ የተገኘ ተመሳሳይነት? ቋንቋ ፣ ሃይማኖትና ባህል የተፈጥሮ አይደሉም ፤ ሶስቱም ከአካባቢው የኑሮ ሁኔታ የሚገኙ ናቸው፤ በፈቃድም ሆነ ወይም በኑሮ ግዴታ የሰዎች ቋንቋ፣ ሃይማኖትና ባህል ሊለወጡ ይችላሉ፤ ይህ ቃል /ዘር/ በአማርኛም ሆነ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ከሥነፍጥረት ትርጉሙ ወጣ ያለ ፍቺን ሊይዝ ይችላል፤ ሆኖም ዘር ከቋንቋ፣ ከሃይማኖትና ከባህል ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ያለጥርጥር እንቀበለው ።

🗒🗒🗒

በዓለም ውስጥ የመንደረኛነት አርአያ የምትሆነን ደቡብ አፍሪካ ነች፤ አሁን ነበረች ማለት ይኖርብናል፤ የደቡብ አፍሪካ ነጮች ይዘውት የነበረው አፓርታይድ የሚባለው የፖለቲካ መመሪያ ንጹሕ መንደረኛነት ሲሆን የተመሰረተው በዘር ላይ ነው፣ በነጭ ዘር የበላይነት ላይ ነው፤ የደቡብ አፍሪካ ነጮች የሚያምኑት ጥቁሮችና ነጮች የተለያዩ ስለሆኑ አብረው በአንድ ስርአት ስር በእኩልነት ለመተዳደር አይችሉምና ለየብቻቸው መንግስት ማቋቋም አለባቸው በማለት ነው፤ የአፓርታይድ ትርጉሙ ይኸው ነው፤ በሌላ አነጋገር የደቡብ አፍሪካ ነጮች የሚፈልጉት አገሩ በጎሳ እንዲገነጣጠልና በተለያዩ ጎሳዎች የሚመሩ አሻንጉሊት መንግስቶች እንዲቋቋሙ ነበር፤ ጥቂቶችም እንደዚህ አይነት የአሻንጉሊት መንግስቶች ተቋቁመው ነበር፤ እንግዲህ ጠቡ ነጮቹ መገነጣጠልን፣ አፍሪካውያኑ ደግሞ አንድነትንና እኩልነትን በመምረጣቸው ነው ማለት ነው ።

🗒🗒🗒

ነጭነት በደቡብ አፍሪካ የዘር መለያ ሊሆን ይችላል፤ በሌላ ግዜና ቦታ ደግሞ ነጭነት የዘር መለያ ለመሆን አይበቃም ይሆናል፤ ለሂትለር ለምሳሌ ነጭነት ብቻውን ዋጋ አልነበረውም፤ ወርቅማ ጸጉርና ሰማያዊ ዓይን ዋናዎቹ የዘር መለያዎች ነበሩ፤ ይህ ሁሉ የሚያሳየን የመንደረኛነት ሚዛን በፈለጉበት በኩል የሚያዘነብልና ትክክለኛ መሰረት የሌለው መሆኑን ነው ።

📖📖📖

ምንጭ 👉 "መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ" ገጽ 170-172 የተቀነጨበ
ደራሲ 👉 ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
ሕይወት አዙሪት ናት

📖📖📖

ሕይወት አዙሪት ናት፡፡ ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህም የምትጨርሠው ከጀመርክበት ነው፡፡
፨ ራቁትክን ትወለዳለህ፤ እርቃንህን ወደመቃብር ትወርዳለህ ፡፡
፨ በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ፤ ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ ።
፨ የሕይወትን ትግል እየዳህ ትጀምራለህ፤ አጎንብሠህ ትጨርሳለህ፡፡

📜📜📜

ዘመንም ተምኔታዊ ነው፡፡
መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ይመጣብሃል፡፡ ሠኞ ማክሠኞ ብለህ ተጉዘህ፤ እንደገና ሠኞ ትላለህ ፡፡ ሕይወት አዙሪት ናት! መጀመሪያህ መጨረሻህ ነው፡፡ የጀመርክበትን አትርሳ፤ መጨረሻህ ነውና፡፡ የጀመርክበትን አትናቀው፤ ትጨርስበታለህና፡፡ ተራ ሠው ሆነህ ትጀምራለህ፤ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምርም፤ ነግደህ ሃብት ብታገኝ፤ ተሹመህ በሕዝብ ላይ ብትሠለጥን፤ ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ፤ የምትጨርሠው እንደተራ ሠው አፈር ለብሠህ ነው፡፡
ልብ በል! ባለማወቅ ትጀምራለህ፤ በመዘንጋት ትጨርሳህ፡፡ ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀትም ይዘህ አትሄድም፡፡ በለቅሶ ትጀምራለህ፤ በጭንቅ ትጨርሳለህ፡፡ በሠው እቅፍ ትጀምራለህ፤ በሠው ሸክም ትጨርሳለህ፡፡
ልደትህ ከሞትህ በምን ይለያል? ሞትህስ ከልደትህ በምን ይከፋል? ሕይወት መጀመሪያዋና መጨረሻዋ አንድ ነው፡፡ በዚህ የተነሣ ጠቢቡ እንዳለው ሁሉም የከንቱ ከንቱ ነው፡፡ ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም፡፡ ልብ በል! የዓለም ከንቱነት ግን ውበትዋ ነው፡፡ ዓለም አዲስ ነገር ቢኖራት እኛን እንዴት በፀፀተን፤ ሞት የእውነት መጨረሻ ቢሆን እንዴት በቆጨን!!
‹‹ርቀህ የሄድክ ቢመስልህም፤ ትልቅ ክብ ሠርተህ ተመልሠህ እዚህ ትመጣለህ፡፡ ዋናውን ተግባርክን ግን እስካሁን አልጀመርከውም፡፡››

ምንጭ ፦ ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ
(መርበብት - ከገጽ 314 - 315)
ያንብቡት ይወዱታል

በተጨማሪም መነበብና መጋበዝ አለባቸው የምትሏቸውን ከመጽሐፍት ገጽ የተገኙ ፅሁፎች በዚህች አድራሻ አድርሱን


ያነበቡትን ለወዳጅዎም ያካፍሉ(ይጋብዙ)
https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAETna_q_yoo2wsRYgg
Forwarded from “ስለ ድንግል ማርያም አማላጅነት እንመሰክራለን ”
የመ/ር ምሕረትአብ አሰፋና የለሎች ኦርቶዶክሳውያን ትምህርት!
ብጹእ አባታችን አቡነ ጰጥሮስ ሰማእትነት ሲቀበሉ የተናገሩት የመጨርሻ ቃል !
https://www.tgoop.com/YgbayLechristos
Forwarded from የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት Orthodox Tewahdo
ማራ ናታ አዲስ ኦርቶዶክሳዊ ቻነል ነው ሁላችሁም ጆይን በሉት
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAFW4SsEToZwtEgYS8g
https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAFW4SsEToZwtEgYS8g
https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAFW4SsEToZwtEgYS8g
የሆነም ያልሆነም!
/ ክፍል 1 /
(ስብሀት ገብረእግዚአብሔር)

📗📒📕

እንፈላሰፍ እንግዲህ እንዳመጣብን!
መፈላሰፍ ማለት ከሃሳባችን ጋር መጫወት ማለት ነው ። <እንዳመጣብን> ያልኩት ላለማሰብ ስለማንችል ነው ። ላለመተንፈስ የማንችለውን ያህል ። ከሃሳባችንማ መውጣት ብንችል ኧይ እንዴት ያለ እረፍት ነበር! እፎይ! አንድ ብቻ ሳይሆን ሃሳብ ረገፈ ። ግና ከቆዳችን መውጣት እንችላለን?

📖📖📖

ማሰብ ካልቀረልን እንግዲያው፣ የማይቀርልህን እንግዳ አጥብቀህ ሳመው ። ይሁንና እንደ ልማዱ፣ እኛ ተዝናንተን እናስብ ። እንመቻች ። ሃሳባችንን እንሳፈረውና እሱ ይዞን ሲሄድ ተጓዦች ዙርያውን እንመለካከት....

ለመሆኑ ማነው የሚያስበው?....
እኔ ነኛ!
እኔ ማለት ይህንን የጻፈውም፣ ይህንን የሚያነበውም ። ይሁን...እኔ ማን ነኝ? እንዴ፣ ምንስ ቢሆን ሃሳብኮ አሳቢውን ይጨምራል ። ማለት አሰቢው ከሌለ ሃሳቡ ከየት ይመጣል? ማን ያስበዋል? እኔ ። እኔ እገሌ!

📖📖📖

እገሌ ማን ነው? ያ ማሕጸን ውስጥ የነበረው ነው? ያ ኩኩሉ ሲጫወት የነበረው ነው? ጎረምሳ ፍቅር የሚባል እብደት አይሉት ተአምር የደረሰበት ነው? ወይስ ያ ወልዶ በልጆቹ ተደንቆ የማያባራው ሰውዬ ነው?
እነዚህ እኔዎች ሁሉ አንድ እኔ ናቸው ለማለት እችላለሁ? ወይስ ስሜ ክር ይመስል እንደ ዶቃዎች እነዚህን ሁሉ እኔዎች አያይዞ ነው?

📖📖📖

(ለወጣት ደራስያን እቺ የክርና የዶቃዎች አባባል ከነሃሳቧ የሩቅ ምስራቅ የቡድሂዝም ናት) ስሜ ነኝ እንጂ እኔ የለሁም፣ እኔዎች ነን ያለነው ። ያለሁትማ እኔ ያሁኑ እኔ ነኝ ። የቀድሞዎቹ እኔዎች የሉም ። አልፈዋል ። እኔም ይኸው እያለፍኩ ነው ።

📖📖📖

ያ ግዜ እሚሉት አይናገሬ መጣንግዲህ ። ያለፈው ፣ ያሁኑ ፣ የሚመጣው ። ትናንት የለችም ፤ አልፋለች ። የትናንትናው እኔም የለም አልፏል ኧረ የቀድሞው እኔም የለም ። ከአንድ ሰከንድ በፊት የነበረው እኔም የለም ። በዚች የአሁኗ ቅጽበት እኔ ብቻ ነው ያለው ። እሱም ያውና አለፈ ።

📖📖📖

በዚህ አካሄዳችን ጊዜም የለም-እኔም የለሁም ። ሂደት ብቻ ነው ያለው እልፈት ። ግን እዚህ ውስጥ ያልተመለከትነው ነገር አለ ። ይኸውም....

📜📜📜

ይቀጥላል...
(ምንጭ 👉 "ደቦ ቅጽ አንድ" 60 ነባርና ዳዲስ ጸሐፍት)
/ ክፍል 2 /ይቀጥል ዘንድ በንባብ አብራችሁን መሆናችሁን አሳዩን 10 (📖)ሲሆን እንቀጥላለን
👇👇👇
@ZkreMetsahft
@ZkreMetsahft
@ZkreMetsahft 👆👆👆👆
Forwarded from የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች
ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ሀፂር ያውቁ ኖሯል???
ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር የሚባል አንድ ቅዱስ ሰው ነበር:: ይህ ቅዱስ አባት በህይወት በሚኖርበት ጊዜ ካደረጋቸው ነገሮች አንዱን ላካፍላቹ ወደድኩ
ቅዱስ ዮሐንስ ሀፂር ልብስ መልበስ ሲፈልግ ልብስ ይሰራ እና በመንገድ ላይ ይጥለዋል ይህን ካደረገ በኋላ በሩቅ ቆሞ ይመለከታል ሰው አንስቶ ከለበሰው ወይኔ የሰው ልብስ ልለብስ ነበር ብሎ ያዝናል ልክ እንዲሁ በመንገድ ላይ የጣለውን ልብስ ሁሉም ሰው እየረገጠው እና ንቆት ካለፈ ግን ይኽ ለኔ ይገባኛል ብሎ ይለብሰው ነበር::
የአባታችን በረከት ይደርብን
ወስብሀት ለእግዚአብሔር
💟💟💟💟💟💟💟💟💟💟
💟💟 @YgbayLechristos. 💟
💟💟 @YgbayLechristos 💟
💟💟💟💟💟💟💟💟💟💟
Channel photo updated
Channel name was changed to «📚የአቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ ትምህርቶች📚»
“ተወዳጆች ሆይ! ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት ብቻ የምትሰሙ አትሁኑ፡፡ እነርሱን ለመምሰልም ተጣጣሩ እንጂ፡፡ ለጊዜው ብቻ የምታደንቋቸው አትሁኑ፡፡ ወደ ቤታችሁ ብቻ ሳይሆን ወደ ልቡናችሁ ውሳጤም ዘልቀው እንዲገቡ አድርጉ፡፡ ዘወትር አስቧቸው፡፡ በልቡናችሁ ጓዳ እንዲገቡ አድርጓቸው፡፡ እናንተን ትተው ይሔዱ ዘንድ አትፍቀዱላቸው፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ዘወትር እያያችኋቸው ትበረታላችሁ፡፡ በእምነት ትጸናላችሁ፡፡ የለበሱትን የጽድቅ ጥሩር፣ የያዙትን ምግባረ ወንጌል፣ የእምነት ጋሻ፣ የመዳን ራስ ቁር፣ የመንፈስ ቅዱስንም ሰይፍ እየተመለከታችሁ ትበረታላችሁ፡፡”
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ )
💟 @EzneLbona 💟
💟 @EzneLbona 💟
💟 @EzneLbona 💟
Audio
የምድር ጌጥ ሃይማኖት ነው የሚያደንቅ ትምህርት ነው ተከታተሉት
መጋቢ ብሉይ ወሐዲስ አባ ግ/ኪዳን
💚 @SleDnglMariam 💚
💛 @SleDnglMariam 💛
❤️ @SleDnglMariam ❤️
2025/03/29 01:12:46
Back to Top
HTML Embed Code: