Telegram Web
ቢርበኝ ቢጠማኝ
ባዝንም በዚች አለም፤
አንቺ እስካለሺኝ ግን
መሸነፍ አላውቅም።

ዝቅ ብለሽ አንገት ደፍተሽ
ያሳደግሺኝ፤
በሰዎች ፊት አንዳላፍር 
ያስከበርሺኝ።

የኔ ኒሻን መክበሪያዬ
የምወድሽ፤
እማዪዬ  የኔ ህይወት
ጀግናዬ ነሽ።❤️

(ሺ አመት ኑሪልኝ!)


@gGetem
@gGetem
ሎጥ ነሽ
🦘

ቅጥልጥል ፥ብግንግን ፥እርር እምር  ፤
ዝምም፥ ልምም ፥እድር ፤
እፍን፥ እምቅ ፥ላጀብ ፥ብድር ፤
ለወዝ ላይላፋ ፥ለዳገቱ ስብር ፤
ተንስኢ ላስነግር ፥በዋጉ ሰው አንዲር ፤
እኛ...እ'ድር..እኔ ላብር ፥ለራስ ሳድር ፣
ላለም ደረት ንፍት፥ ለራስ አንገት ስብር

'
'
ላክል ፤
ባክል ፤

ላንስ ፤
ዳንስ ፤

አይሆን ላይሆን ፥
ላገር ስሪያ ማሰሪያ ፣
መች አምሳሏ ነበረ፥
ያከበረችው ጥያ ፣
ቀጥ ብላ ማንጋጠጥ፥
ሎጥነሽ ወይ ?ኢትዬጵያ....
'
'


@gGetem
@gGetem
@gGetem
ነበርሽ ፤…
የጠዋት ፀሐይ
በቀስታ ደም የምታሞቅ ።

ነበርሽ ፤…
የዓለት ስር አበባ
ድንጋይ ተደብቆ የሳቃት ።

ነበርሽ ፤…
ልሙጥ የሻይ ብርጭቆ
ወገብሽ የሚያቃጥል  ፤

ቀስ አድርገው
አለሳልሰው
እፍፍ ብለው
ልካቸው ድረስ አብርደው
በከንፈርሽ የሚቀምሱሽ ፤

ነበርሽ ፤…
ለሕይወት ተኩል
ለሞት አምስት ጉዳይ ።


@gGetem
@gGetem
@gGetem
ዕዳዋ የለብኝ~አበዳሪ አይደለች
ደም አልተቃባችኝ~ዘመድ አልገደለች
አላስቀየመችኝ~ተናግራ ክፉ ቃል
እንከን አጣሁ ተብሎ~ሰው እንዴት ይራቃል?
ወይ አይደለች ሻማ~ጨርሼ አላነዳት
አንዳች አልሰረቀች~እንዳላሳድዳት
እንዴት ብለከፍ ነው~ስትርቅ የምወዳት?


@gGetem
@gGetem
@gGetem
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አቀርቃሪ አሉኝ፣
ቀና ብሎ ማየት መራመድ ሲሸሸኝ፣
ሊያብድላት ነው አሉኝ፣
በቁሜም በሕልሜም ቅዠት ሲረብሸኝ።

ሊረታ ነው አሉኝ፣
ስንቀጠቀጥላት ስሟ ትዝ ሲለኝ፣
ትክክል ናቸው ወይ፣
እኔ ከምወስን እናንተ ንገሩኝ?



@gGetem
@gGetem
@gGetem
.............



ትብታብ አይደለም ድግምት
ደብተራ አይደለም አስማት
ንጹሕ ፍቅር ነው ምናኔ
ለሚወዱት የመሞት ጭካኔ
እንኳን አሁን፤ከገላዬም ደም ቢነጥፍ
ደምስሬም ጅማቴም
ስምክን ነው የሚጥፍ
ዘረ ደሀ አፈቀርሽ
ዘራችንን አረከሽ
ብለው ቢያጠምቁኝም
ለፍቅርህ ስለሆን
የክፉዋች ጸበል፤መድን አይሆነኝም
ይልቅ በዛብህ፤አንጀትክን ሰብስብ
ከዛሬ ይልቅ፤ነገህን አስብ
አይዞህ በዛብህ፤ይህን ቀን ቻለው
ሰብለ ወንጌልህ
ከአትሮንስ ወርጄ ተጠፍሬያለው
ግን አትሳቀቅ፤ይህም ቀን ያልፈል
የክፉ ጅራፍ፤ጽናት ይጽፉል
የሚለው ቃሏን፤ከፍቅሩ ሰምቶ
በተስፋ አባብሎ፤ልቡን አጽናንቶ
ከተማ ገብቶ ቢጠብቃትም
ወንጌሉን ካሻው አላገኛትም
የእግዜር ኑዛዜ፤የእውነት ቃሉ
የአዳም ጥፋት፤የአምላክ አምሳሉ
የሄዌን ስህተት፤ክፉይ አካሉ
አትብላ ካለው፤ከፍሬው በልቶ
ፍቅርን በደለው፤የሞት ሞት ሞቶ
ግን በበዛብህ፤ቃሉ ልዩ ነው
ከህይወት መስቀል፤አዳኙ ማነው
አዳም ከበላው፤በለስ ሲያላምጥ
ከወንጌል ይልቅ፤ልቡን ሲያስበልጥ
ፍቅርን በደለው፤የኑሮ ጣጣው
በቃሉ አኑሮ በእውነቱ ቀጣው
ድሮም ያን ጊዜ፤በኦሪት ዘመን
ክፉ ጎልያድ፤በሀይል ሲዘምን
ጉልበቱን ነስቶ፤መሬት ያኖረ
ጠጠሩ ሳይሆን፤እምነት ነበረ
በማፍቀር እምነት፤ነፍሱን አጽንቶ
ቢጠብቃትም ከተማ ገብቶ
ወንጌሉን አጣት፤ከባዕድ ሀገር
የህመም ጥልቁን፤ለማን ይናገር
ህልሙን አለሙን፤ሁሉንም ትቶ
አቅሉን እስኪስት፤ወንበዴ እጅ ገብቶ
በፍቅር መስቀለ የተሰቀለ
ኤሎሄ አይደለም፤ሰብለ ነው ያለ
የእግዜር ማቅ ለባሽ፤አንቺ መነኩሴ ሴት
እረፍትን ፍለጋ፤ከገባሽበት ቤት
ካልጋ ያገኘሽው፤እሱ ነው ወንጌልሽ
ጣር ባሰረው ድምጸት
ሰ...ሰ..ሰብለ ብሎ የሚልሽ
እንዲ ነው ፍቅር፤እንዲ ነው ስቅለት
እንዲ ነው መሞት፤እንዲህ ነው ድህነት
ፍቅር ቢበድል፤የእውነት ልኩ
ወንጌል ያጣ ሰው፤ወንጌል ነው መልኩ

Based on ፍቅር እስከ መቃብር

    

@gGetem
@gGetem
@gGetem
የነገዬ ምርኩዝ የትናንት መፅናኛ

የህይወቴ ትርጉም የጊዜ መዳኛ

መራመጃ መንገድ ህመምን አስረሽ

የፅልመቴ መብራት እኔን አስታዋሽ


          ጣዕም ሰጭ ስኳር ህይወት ማጣፈጫ

          የዛሬን ትካዜ

          የዛሬን ፍዛዜ

          በያልፋል ደስታ ስሜት መቀየጫ


የዋሻ ውስጥ ጮራ ፍንጣቂ ብርሀን

የህይወቴ ካርታ የመርከቤ ካፕቴን

ትርጉም አልባን እኔን ሀዘን የወረረኝ

ከጥልቅ ትካዜ ውስጥ ወዝውዞ ያነቃኝ

ተስፋ ነው ሻማዬ...

ተስፋ ነው ሻማዬ

የትናንትን ፅልመት ዛሬን ያበራልኝ
     
@gGetem
@gGetem
@gGetem
መልካም ልደት 'ላዳም
.
.
ብርሃኑ ተገፎ ልጅነቱን ላጣ ፤
እርቃኑን ተሰዶ ከገነት ለወጣ፤
ምድር ለተጣለ አምላክነት ሽቶ፤
ሞትን ላነገሰ በፈቃዱ ገዝቶ።
.
መልካም ልደት 'ላዳም
.
አዝኖ ተጎሳቁሎ ፅልመት ለወረሰዉ፤
እዡን ለሚያነባ መደሰት ለራቀዉ፤
ስብራቱ ገዝፎ ስቃዩ አይሎ፤
መስዋት ለሚያቀርብ ከደሙ ቀላቅሎ።
.
መልካም ልደት ለኛ.....
.
ፅድቃችን በሙሉ መርገም ለሆንብን፤
ደረት ለምንደቃ አበሳ ለገበርን፤
እንደወራጅ ዉሃ እንባችን ለሚፈስ፤
የልባችን ልቅሶ ፀባኦት ለማይደርስ።

መልካም ልደት ለእኛ......
የማይነጥፍ ተስፋን ኪዳኑን ለሰጠን፤
በግርግም ተወልዶ ዳግም ለወለደን፤
በመስቀል ተሰቅሎ እርሱ ለተቤዠን፤
መልካም ልደት ለኛ ድኅነትን ላገኘን።
...............................................
@gGetem
@gGetem
ቢሆንም


ፍቅር ይሉት ጣጣ  ሲፀነስ
ሰው ከሰውነቱ ላይ  ሲቀነስ
አይተናል
          
አይተናል  የነበር ፍቅር ሲለፈፍ
በከሸፈ ፍቅር   ጤንነት ሲቀሰፍ
አይተናል


ፍቅር  የመርገምት ቃል እስኪመስለን
ከእጦት በላይ  ንቀታቸው ያቆሰለን
አይተናል


በጫማቸው  በረገጡን
ከትቢያ ላይ  ባስቀመጡን
ላቀመሱን የፍቅርን ፅዋ  መራር ጣዕም
ልክፍት ነውና
    ይሄው እስከዛሬ  እንፅፋለን ግጥም


ቢሆንም

በዬ ዘፈኑ  ሆድ የባሰን
የናፍቆት ህመም የዳበሰን
አንድ ሰው ለመውደድ   ዘመናት ያነሰን
ስንት አፍቃሪ አለን
         የትዝታ ፈረስ  ወስዶ  ሚመልሰን


የማይመጣ እንደሚጠብቁ  ቢታወቅም ቅሉ
በአልኮል በሲጋራ  በጫትም ገረባ የተጠለሉ
ከእልፍ አእላፍ የበዙ   ስንት ልቦች አሉ ?




@gGetem
@gGetem
@gGetem
አለመሳቅ እኮ ይቻላል...
-----------------------

አለመሳቅ እኮ ይቻላል -
አለማልቀስ ነው ጭንቁ፣
የመንፈስን እንጉርጉሮ -
በመንፈስ እምባ ማመቁ፣

ውስጥ ውስጡን እየደሙ -
በቀቢፀ ተስፋ መድቀቁ፣
ለተስለመለመች እውነት -
የደም ደብዳቤ ማርቀቁ፣

በቅሬታ ሰደድ እሳት -
ህዋሳትን መጨፍለቁ፣
አለመሳቅ እኮ ይቻላል -
አለማልቀስ ነው ጭንቁ።

     - ደበበ ሰይፉ
   
@gGetem
@gGetem
ምሳሌ መስጠት ባልወድም
አንድ ምሳሌ ልንገርሽ
ስለፍቅር አንስቼ
ሃሳቤን ለሰው ሳወራው
"እንደዚህ ሆኖ" እያልኩኝ
ነገሩን ከስር ሳብራራው
በምሳሌዎቼ መካከል
ስምሽን ብቻ ነዉ 'ምጠራው

(እንደዚህ ነሽ ለኔ)

@gGetem
@gGetem
🙎‍♂🙍   አዳም ዕድለኛዉ    🙎‍♂🙍

ስልኩዋን ሳይቀበላት ፡ ሳይቀርባት ለተንኮል ፣
ልቡን ሳታጠፋዉ ፡ በአስቀያሚ ሚስኮል
💑
ካርድ ሳይሞላላት ፣
ሳይያዝ በዱቤ ፣
ከቶ ሳይልክላት ፡ የፍቅር ደብዳቤ ፤
የዘፍጥረት አቡን ፡ ቀድሞ የተገኘ ፣
አዳም ዕድለኛ ፡ ሄዋንን አገኘ ፡፡
💑
ይደንቃል ዘፍጥረት .. .. ..
ይኖራል ዝንታለም ፡ እንደተተረከ ፣
አዳም ራቁቱን ፡ ሄዋንን ማረከ ፡፡
ሲኪኒ ሳይሸምት ፡ የቻይናዉን ሱሪ ፣
ቀለበት ሳያስር ፡ ሳይገዛላት ድሪ ፤
ቫላንታይን ዕለት ፡ ሳይሰጣት አበባ ፣
በፈጣሪ ምሎ ፡ ለሷ ቃል ሳይገባ ፣
አማጋጭ ሳይኖራት ፡ ሳይፈጠር ምቀኛዉ ሄዋንን ጠበሳት ፡ አዳም ዕድለኛዉ ፡፡
💑
ገንዘብ ሳትጠይቀዉ ፡
ቪላ ቤት መኖሪያ ፣
ጌጣጌጥ ኮስሞቲክስ ፡ የፀጉር ማሰሪያ ፤
ሳትሞሸር በሰርግ ፣ ሳትለብስ ቬሎ ፣
አዳም ቤቱ አስገባት ፡ ሄዋንን ጠቅልሎ ፡፡
💑
አዳም ሚዜ ሆኖ ፣
ሽማግሌም ሆኖ ፣
ራሱን ሞሸረ ፣
ከፍጥረት ኡደት ጋር ፡ እየተሳከረ ፡፡
በዘፍጥረት ድርሳን ፣
በኦሪት ሊቅ ልሳን ፣ እንደተተረከ ፣
አዳም ራቁቱን ፡ ሄዋንን ማረከ ፡፡

💑


         @gGetem
        @gGetem
    ❤️❤️❤️_▭▬▭▬
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
👂ነጋሪት በጆሮ👦👂
#የጆሲ_ደብዳቤ_®
#ቀን_24_04_2008_ዓ_ም_
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@gGetem
@gGetem
@leoyri
@yosikeman
እስትንፋሴን የልቤን ትርታ
አንጠፍጥፌ  የፍቅሬን  ጠብታ
አንዳች እንኳን ሳላስቀር
ለአንቺ ደስታን ልፈጥር ስታትር
እኔ እኔነቴን ጥዬ
አንቺን አንቺን ብዬ
ያንቺን ህይወት ሳደላድል
ከራሴ ህይወት ስጎድል
እንደ ፀሃይ እንድትደምቂ
አንደ አደይ  እንድትፈኪ
በሃዘንሽ  እየኖርኩኝ
በህምምሽ ስንቴ ሞትኩኝ
ግና አንቺ ሁሉን ረስተሽ
እኔን ከትዝታሽ አቆራኝተሽ
ርቀሽ ሄድሽ
በመሄድሽ አላዘንኩም
ደግሞም የሄደን ሰው ለመመለስ አልሞክርም
ይልቅ ልመርቅሽ
በሄድሽበት ክፉ አይንካሽ
ያየሽ ሁሉ የሚወድሽ
ለእኔ ብሎ የሚመኝሽ
መልከ መልካም ሴትን ያድርግሽ
@gGetem
@gGetem
አንተ እንባዬ ምረጥ
ልግለጥህ?
ልዋጥህ?
ላፍንህ?
ልልቀቅህ?
ላፍስስህ
ላምቅህ?
ምን ላርግህ? ምከረኝ
ምንድነህ? ንገረኝ

እህል ትሆን ጠፊ?
ወይስ ሽል ነህ ገፊ?
በጊዜ ልወቅህ...
ላቅርብ ወይ ላርቅህ...
አጫጅ ነህ አራሚ?
ተጓዥ ነህ ከራሚ?
አላፊ ነህ ቋሚ?
ምንድነህ?
ምን ላርግህ?
ላግድህ?
ላውርድህ?
ጋርጄ ልካድምህ?
አውርጄ ልካድህ?
ቢያፍኑህ ቀሪ ነህ?
ቢለቁህ ኗሪ ነህ?

እንባዬ ምን ላድርግህ?
ላስርግህ?
ልጥረግህ?
እንዳ'ይን እንዳ'ፍንጫ
ቋሚ መገለጫ
መታወቂያ መልኬ ፡ ሆነህ ትኖራለህ?
ወይስ ላ'ንዴ ወርደህ፡ በዚያው ትቀራለህ?

አንተ እንባዬ ምረጥ
ላብስህ?
ላልብስህ?
ወይስ እንዳላየ፡
ከኔ የወጣ ሁሉ፡
የኔ አይደለም ብዬ
ልተውህ እንባዬ?

ወይስ ልገላገል?
እውነቱን ልናገር?
እንዲህ ነህ እንዲያ ነህ
እያልኩኝ ከማበል
አላውቅህም ልበል?


@gGetem
@gGetem
ባያቸውስ ኖሮ ?
(ሚካኤል አስጨናቂ)

እርግት ያለች ወተት
ስክን ያለች ቡና …
ይሄን ችኩል ዘመን
አልዋጀችምና …
ተንገበገብኩላት
ተሳተብኝ አቅሌ
ሆንኩላት ባተሌ ።

ጥልል እንደ ጠላ
ኩልል እንደ ጠበል
ከአንገቷ ስር ገነት
ገድ ጥሎኝ ብጠለል
አ..ን..ሰ…ፈ…ሰ…ፈ…ች….ኝ
አ…ር..ገ…ፈ...ገ…ፈ…ች…ኝ
ቃላት ሳ’ተነፍስ
ጥርሶቿን ሳትገልጥ
ቅቤ ሆነ ልቤ..
ገጽዋ ላይ ሲቀልጥ ፤

ያን ጊዜ ተቃናች !
ብታጣብኝ ኩራት
ስስ ጎኔ ቢገርማት
(ዓይኖቿ ፍም እሳት)
አንገቴን ሰበርኩኝ
ፈርቼው ይሄን ፍም
ቢሆንም …
ቢሆንም …
ለዓይኖቿ አፀፋ
መስጠት ሳልፈልግም
ለንቋሳው
……………………….. ተንጋለልሁ
ለዚ’ች ሞቃት ግርግም
:
ደረቷ ላይ ፍግም !

@gGetem
@gGetem
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
🇪🇹የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#ለኔ_ውበትሽ

ቁንጅናማ ያበቃል ፣
    እስከ ሞት አይገኝም ፣
               ጥቂት ነው ጊዜ መኖሪያው
ለኔ ውበትሽ ቀሚስሽ ነው ፣
     የልቤን በር የሚያንኳኳ ፣
                  የፍቅሬን ጥግ የሚያስሰው
ለኔ ውበትሽ ማፈርሽ ነው ፣
       እንደ ማለዳ ጮራ ፣
                  ውስጤን ዳብሶ የሚያነቃ
ከጉራንጉር እሩቅ ሃሳብ ፣
          አዕምሮዬን ደርሶ ነጥቆ፣ 
                  ለብሩህ ዓይን የሚያበቃ
ለኔ ውበትሽ ቃልሽ ነው ፣
           በማዕበል የማይናጥ ፣
                     ባዲስ ቅኔ ማይወሰድ
የእባብ ምላስ የማይመስል ፣
              መንታ አመል የሌለበት ፣
                      በኪዳን ታስሮ ሚገመድ
ለኔ ውበትሽ እምነትሽ ነው ፣
               እንደ አደይ እያበበ ፣
                        እለት በለት ሚለመልም
በህሊና የራስ ዳኛ ፣
              በተሞረደ ንፁህ ልብ ፣
                     የህይወት ማሳ የሚያርም
ለኔ ውበትሽ ማተብሽ ነው ፣
እንደ አልማዝ ክቡር ድንጋይ፣
ላይኔ ቀድሞ የሚበራ        
እንደ ምስራቅ ፀሃይ ብርሃን  ፣
           የደመናን መጋረጃ ፣
                   ፀዓዳ አርጎ የሚያጠራ ።

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
✍🏽© ደሱ ተገኝ
╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈


ምንጭ ➸ ዐውደ ጥበብ
ለመቀላቀል 👉🏽 @gGetem
አስተያየት 👉🏽 @leoyri
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
🍋የዋርካ ስር ጤዛ 🍋🍋
🍋🍋🍋🍋🍋🍋🍋
........... ©ሲራክ ......
በእለተ ከተራ ፥ በበዓል ዋዜማ፣
አደባባይ ሳይሽ ፥ ደምቀሽ በሃገር ሸማ ፣
ወርውር ወርውር አለኝ ፥ ሎሚውን ግዛና፣
ሎሚ ሻጭ ፈለግኩኝ......
ጎዳናውን ሙሉ ፥ ስዞር አመሸሁኝ።
በጥምቀተ ባህር ፥ ህዝብ ሁሉ በሆታ ፣
እያጨበጨበ ፥ ታቦቱን አጅቦ ሲገባ በእልልታ፣
ማጨብጨብ ተስኖኝ ...
እልልታ ጠፍቶብኝ...
ሎሚ ፈልጋለሁ ፥ ከአይኔ ሳትጠፊብኝ።
ይኸውልሽ ውዴ ....
አትታደል ሲለኝ ፥ ቢጠፋ ነው እንጂ ..
እድሌ ባይቀና ፥ ብኩን ብሆን እንጂ..
ከአስራ አምስት ቀን በፊት ፥ ለጨዋታ ብዬ ፣
ለገና ጨዋታ ፥ ለአሲና ገናዬ ፣
ዱላ እየፈለግኩኝ ፥ ከጫካ ገብቼ ፥
ሎሚ ጨፍጭፌያለሁ ፥ ዛፉን ተመኝቼ ።
እድል እንደዚህ ናት ፥ የዋርካ ስር ጤዛ ፣
ይኸው እኔ ዛሬ ፥ በዋዛ ፈዛዛ፣
እልፍ የሎሚ ዛፍ ፥ ጨፍጭፌ ሳበቃ፣
አንድ ሎሚ አጣው ፥ ለአንቺ የሚበቃ ።
አዬ እድል እያልኩኝ ፥ ከወደ አመሻሽ ፥ ከቤቴ ገብቼ ፣
ሎሚ ዛፍ ተከልኩኝ ፥ ለዓመቱ አስልቼ ።
እስከዛ ግን አንቺ .....
ሎሚ ወርዋሪዎች ፥ በሌሉበት መንገድ
ሂጂልኝ ግድ የለም፣
ዘንድሮን ያለፍኩት ፥ ሎሚ ቢጠፋ እንጂ...
ፈርቼስ አይደለም።
ወርውር ያለኝ ልቤ .....
ተግቶ ተሰናድቶ ፥ ዓመቱን ጠብቆ፥ በእለተ ከተራ ፣
እመጣለሁ ብሏል ፥ ከአስር ሎሚ ጋራ።
🍋🍋🍋🍋የዋርካ ስር ጤዛ 🍋🍋🍋🍋
--------- ሲራክ ወንድሙ @siraaq
@gGetem
@gGetem
@gGetem
2025/06/25 15:20:26
Back to Top
HTML Embed Code: