Telegram Web
አይ አንቺ ጨረቃ
.
.
.
ስንቱን ሰዉ ታዘብሽዉ?
ስንቱን አደመጥሽዉ?

የከፋዉ እንደሆን ላንቺ
     የሚያወጋዉ፤

በልቡ ያለዉን ሚስጥራቱን
   ሁሉ  የሚዘረግፈዉ፤
  
እስቲ ልጠይቅሽ?
ምን ቢያይብሽ ነዉ?


@gGetem
@gGetem
ጀምበር ገባች ፥ መሸ
ያጸዳሁት ቤቴም ፥ መልሶ ቆሸሸ
አልጠፋም መብራቱ
አልተበላም 'ራቱ
አሁንም ክፍት ነው በርና መስኮቱ ።
ለቁር ተጋለጠ ፥ ጓዳዬ እንደ ውጪው
መቼ ነው የምትመጪው ?

መጽሐፍ ገለጥኩና መልሼ ዘጋሁት
ልጽፍ አሰብኩና ብዕሬን ወረወርኩት
መቆም መንጎራደድ
መቆም መንጎራደድ
መቆዘም መተከዝ ፥ በሐሳብ መሰደድ
ደርሶ ብንን ብንን
ደሞ ቁጭ ብድግ
ካንቺ ውጭ አላውቅም ምን እንደምፈልግ ።

ምኞት ነው ያለኝ  ፥ ዝም ብሎ ምኞት
ወይ የማያኖር ፥ ወይ የማያስሞት

ትመጫለሽ እያልኩ በጉጉት ከምኖር
ምናለ በሞትኩኝ ለአንድ ለስድስት ወር ።

@gGetem
@gGetem
☑️ በመላው ዓለም ከፍተኛ ዝናን ያተረፈችው የአጋታ ክሪስቲ ዝነኛ መጽሐፍ ክህደት |Destination Unkown|
በቅርብ ቀን ወደናንተ ይደርሳል
※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※
👍1
............


ይሁን ካልሽ .....
ይሁን በቃ ትቼዋለው
ልብ ካልወደደ
ይቅር ማለት ምን ዋጋ አለው
ባትነግሪኝም ........
የገፋሽን ጥፋት
አብሮ መሆን ደርሶ ነፍስሽን ካስከፋት
ቃል እየመረኩኝ አልሻም ላባብል
ፊደል እያቀናው ስህተቴን ላስታብል
ይሁን ካልሽ
ይቅር ካልሽ
ይቅር በቃ ትቼዋለው
ልብ ካልወደደ
አብሮ መሆን ምን ዋጋ አለው
መነጣጠል ቢያረክስም
ፍቅርሽን አልከስም
ባትነግሪኝ አውቀዋለው
ኩርፊያሽ ሀቅ እንዳለው
ይቅር ብለሽ
በቃ ብለሽ
መለየት ከመረጥሽ መኖር ተነጥለሽ
ምን እላለው
ልብ ካልወደደ
አብሮ መሆን ምን ዋጋ አለው


@gGetem
@gGetem
@gGetem
ክህደት ክፍል 01 - Destination unknown
የሆሄያት ህብር| @gGetem
⎈❉ ርዕስ -  ክህደት ❉⎈
#ክፍል_01

⇝ ደራሲ >አጋታ ክሪስቲ
⇝ ተርጓሚ ጌታቸዉ መኮንን ሐሰን
⇝ ተራኪ ተስፋሁን ገ/ጊዮርጊስ (ትሳሱ)

☑️ በመላው ዓለም ከፍተኛ ዝናን ያተረፈችው የአጋታ ክሪስቲ ዝነኛ መጽሐፍ ክህደት |Destination Unkown|

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════
............

ትከተይኛለሽ ብዬ ስለማስብ
በሄድኩበት ሁሉ እጅ እንድሰበስብ
መዞር እፈራለሁ
ዞሬ ያጣሁሽ እንደው
ብቻዬን መሆኔስ ምን ነጻነት አለው
ትከተይኛለሽ
በአለሁበት አለሽ
ብዬ ስለማስብ
ትዝታ እንደ ገላ ይዳብሰኝና
አለሄደችም ብዬ
ልቤን አጽና..ና...ና
ጀርባዬን አምናለሁ
አንቺ ከነጠቀኝ
እውነት ምን ዋጋ አለው
ያልኖሩበት ነገ ተስፋው ምን ሊጠቅም
አለሽ ብዬ አምናለሁ
ዞሬ ግን አላቀም
በሄድኩበት ሁሉ
በሳር በገደሉ
እረኛ ያጣ በሬ በኮቴው ሲያደቀው
አንቺን ነሽ በዬ ነው በተስፈ የምስቀው
ጠረንሽ ቢጠፋኝ
ሽቶ ያኮፈሳት ላባም ሴት ፈልጌ
በሴሰኛ ስሜት ጭኗን ተፋትጌ
ሲረካ መንፈሴ
አንቺ ነሽ ብሎ ነው
የሚስቀው ጥርሴ
መቼም ለመኮነን
መዞርም አያሻም ሀጥያት በዝቷል ከፊት
የከፋኝ ጊዜ ነው የማቀው ያንቺን ፊት
ትከተይኛለሽ
ባለሁበት አለሽ
ብዬ ስለማምን
እንትን ተመኝቼ ጌታዬን ስለምን
የሷንም እላለው
ይሰማሽ እንደሆን
እንጃ ምን አውቃለሁ
መሄድ እንደቀላል
መንገዱን ሲያረዝመው
መድረስ አይናፍቅም
አለሽ ብዬ አምናለሁ
ዞሬ ግን አላቅም



@gGetem
@gGetem
🔥2
ክህደት ክፍል 02 - Destination unknown
የሆሄያት ህብር| @g Getem
⎈❉ ርዕስ -  ክህደት ❉⎈
#ክፍል_02

⇝ ደራሲ >አጋታ ክሪስቲ
⇝ ተርጓሚ ጌታቸዉ መኮንን ሐሰን
⇝ ተራኪ ተስፋሁን ገ/ጊዮርጊስ (ትሳሱ)

☑️ በመላው ዓለም ከፍተኛ ዝናን ያተረፈችው የአጋታ ክሪስቲ ዝነኛ መጽሐፍ ክህደት |Destination Unkown|

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════
1👍1
ክህደት ክፍል 03 - Destination unknown
የሆሄያት ህብር | @gGetem
⎈❉ ርዕስ -  ክህደት ❉⎈
#ክፍል_03

⇝ ደራሲ >አጋታ ክሪስቲ
⇝ ተርጓሚ ጌታቸዉ መኮንን ሐሰን
⇝ ተራኪ ተስፋሁን ገ/ጊዮርጊስ (ትሳሱ)

☑️ በመላው ዓለም ከፍተኛ ዝናን ያተረፈችው የአጋታ ክሪስቲ ዝነኛ መጽሐፍ ክህደት |Destination Unkown|

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━


አንድ ቀን አንድ ሰው ፥ ሲሄድ በመንገድ
የወንዝ ውሃ ሞልቶ ፥ ደፍርሶ ሲወርድ
ያው ከወንዙ ዳር ፥ እያለ ጐርደድ
አንድ አዝማሪ አገኘ ፥ ሲዘፍን አምርሮ
በሚያሳዝን ዜማ ፥ ድምፁን አሳምሮ
“ምነው አቶ አዝማሪ ፥ ምን ትሠራለህ?”
ብሎ ቢጠይቀው ፥ ምን ሁን ትላለህ?፤
አላሻግር ቢለኝ ፥ የውሃ ሙላት
እያሞጋገስኩት ፥ በግጥም ብዛት፤
ሆዱን አራርቶልኝ ፥ ቢያሻግረኝ ብዬ”
“አሁን ገና ሞኝ ሆንክ ፥ ምነዋ ሰውዬ፤
ነገሩ ባልከፋ ፥ ውሃውን ማወደስ
ግን እንደዚህ ፈጥኖ ፥ በችኮላ ሲፈስ፤
ምን ይሰማኝ ብለህ ፥ ትደክማለህ ከቶ
ድምፁን እያሽካካ ፥ መገስገሱን ትቶ?፤
እስኪ ተመልከተው ፥ ይሄ አወራረድ
ያልሰማው ሲመጣ ፥ የሰማው ሲሄድ፤
ተግሳጽም ለፀባይ ፥ ካልሆነው አራሚ
መናገር ከንቱ ነው ፥ ካልተገኘ ሰሚ!”።

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
✍🏽© ከበደ ሚካኤል
╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈


ምንጭ ➸ የማርያም መቀነት
ለመቀላቀል 👉🏽 @gGetem
👍2
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
🙎‍♀🤷‍♂ ህይወት በየፈርጅ🙎‍♂🤷‍♀
#ገጣሚ_ሊዮ_ማክ @Leoyri ☔️
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@Leoyri
@gGetem
@gGetem
@gGetem
Audio
🥰🥰የዘመናት ህልሜ🤔🤔
☔️ #ገጣሚ_ሊዮ_ማክ_®☔️
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@Leoyri
@gGetem
@gGetem
@gGetem
👁💚💛❤️
#ተፃፈ_19_04_2012_ዓ_ም
Audio
🐴🐴🏹 ADWA🏹🏹
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@yosikeman
@gGetem
@gGetem
@gGetem
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሀና ሀይሉ ግጥም
- #ደረስንልሽ_ሀገሬ
አንቺን ማቃጠሉ ስለሚቀል እንጂ
ጭስ በጭስ የሆነው
እሳቱን ለማጥፋት ስላንቺ ሚማገድ
ከአመዱ መሀል ብዙ ሰው ነው ያለው
@gGetem
@gGetem
@hanahailu
ለአስተያየት @Leoyri
ክህደት ክፍል 04 - Destination unknown
የሆሄያት ህብር | @gGetem
⎈❉ ርዕስ -  ክህደት ❉⎈
#ክፍል_04

⇝ ደራሲ >አጋታ ክሪስቲ
⇝ ተርጓሚ ጌታቸዉ መኮንን ሐሰን
⇝ ተራኪ ተስፋሁን ገ/ጊዮርጊስ (ትሳሱ)

☑️ በመላው ዓለም ከፍተኛ ዝናን ያተረፈችው የአጋታ ክሪስቲ ዝነኛ መጽሐፍ ክህደት |Destination Unkown|

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════
..........


ቀለም
ጸሀይ አይደለችም የቸረች ተፈጥሮን
ውበቷ ነው እንጂ ጨለማን ሰውሮን
በነጭና ጥቁር
በበዛበት ህይወት
ተፈጥሮን በረሳ ቀለም በናፈቀው
ጸሀይ አይደለችም
ገላሽን አቅፎ ነው ጓዳዬ የሞቀው
ቤቴ የደመቀው
ያልተጋሩት እቶን
የሚማገዱበት ልክ እንደ ዕሳት ዕራት
ሞቶ የመኖር ብስራት
በብርሀኗ ውስጥ በሚንቦገቦገው
ፍቅርን ልፈልገው
ስዳራሽ እያዩ
ሞቶ ነው እያሉ ህያዋን ሲለዩ
ለዚህ ነው የምልሽ
ቀለም
ጸሀይ አይደለችም የሰጠች ተፈጥሮን
ውበቷ ነው እንጂ ጨለማን ሰውሮን
በሳት ላልተዳሩ
ላልተፋቀሩ!
ቅሉ አይገባቸውም የቀለም አደሱ
የፍቅራቸው ምሱ ?
ዕሳት ዕራት መሆን ጸጋ መች ታደለ
ከሚነድ ወላፈን ጠብታን ያከለ
ለዕሳት ነፍስ የዘራ ስጋውን ሰውቶ
ጸሀይ አይደለችም
ውበቷ ብቻ ነው የሚታየው ጎልቶ

@gGetem
@gGetem
@gGetem
ክህደት ክፍል 05 - Destination unknown
የሆሄያት ህብር| @gGetem
⎈❉ ርዕስ -  ክህደት ❉⎈
#ክፍል_05

⇝ ደራሲ >አጋታ ክሪስቲ
⇝ ተርጓሚ ጌታቸዉ መኮንን ሐሰን
⇝ ተራኪ ተስፋሁን ገ/ጊዮርጊስ (ትሳሱ)

☑️ በመላው ዓለም ከፍተኛ ዝናን ያተረፈችው የአጋታ ክሪስቲ ዝነኛ መጽሐፍ ክህደት |Destination Unkown|

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════
👍1
"ድንቄም ቆራጭ"😁😁😁
"""""""""""""""""""""
ከልብ ተሠርንቆ ልውጣ አልውጣ እያለ፤
ያስገባንው ነገር ከአቅም ካየ"ለ።
ይውጣ ምናባቱ ልብን ከበሽተ ካላረገን ደህና፤
አንቅሮ መትፋት ነው ከሚያሳጣን ጤና።

ሰውም እንደዚህ ነው፥
የልባችን እሳት የልባችን ንዳድ ለሱ ከበረደው፤
የፍቅራችን ሙቀት ቀዝቅዞ ከታየው።
ምን ሊያረግ ይቀመጥ ሊሆነን ፈተና፤
ከተመቸው ይሂድ መንገዱ ያውና።

የልባችን መሻት መሻቱ ካልሆነ፤
የመውደድ ፍላቱ ከሱው ከተነነ።
ልቡ የሸፈተን አስረን ላናስቀረው፤
መንገዱ ያውና ይሂድ ከተመቸው።

ብዬ እፎክርና ዝቼ በሃሳቤ፤
አስሮ ያስቀመጠው ይሸነፋል ልቤ።

አድሮ ልመና...ተው ፍታኝ
የቃልህ እስረኛ ነኝ🥹

ምን ላርግ ከእኔ ዘንድ አልሰራም


@gGetem
@getem
@gGetem
ክህደት ክፍል 06 - Destination unknown
የሆሄያት ህብር| @gGetem
⎈❉ ርዕስ -  ክህደት ❉⎈
#ክፍል_06

⇝ ደራሲ >አጋታ ክሪስቲ
⇝ ተርጓሚ ጌታቸዉ መኮንን ሐሰን
⇝ ተራኪ ተስፋሁን ገ/ጊዮርጊስ (ትሳሱ)

☑️ በመላው ዓለም ከፍተኛ ዝናን ያተረፈችው የአጋታ ክሪስቲ ዝነኛ መጽሐፍ ክህደት |Destination Unkown|

※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
            ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════
2025/07/13 23:03:06
Back to Top
HTML Embed Code: