Telegram Web
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo Leጅ)
👂📩ነጋሪት በጆሮ📩👂
👩‍⚖🧑‍⚖
#የቃልዬ_ደብዳቤ_®
#ቀን_20_03_2010_ዓ_ም_
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
የፍቅር ደብዳቤዎች

@gGetem
@gGetem
@leoyri
​​●●◦🍃የይቅርታ መሐልይ🍃◦●●

ማነዉ የፈለገኝ?
በማይነጋ ሌሊት
በማይመሽ ቀን መሀል
ተዘርሬ ስገኝ።
ከተዉሽኝ በኀላ 'ርቃን ቀርታ ነፍሴ
እንኳን ከሰው ዐዉድ ተነጠልኩ ከራሴ፡፡

ተመልሼ ልምጣ ተመልሰሽ ነዪ
ልጣል ምሰሶዬን ማገርሽን ጣዪ
አዲስ ቤት መገንባት ዛሬ መች ይደላል
ለምደዉ ወደተዉት መመለስ ይቀላል፡፡

ካሳ ባልክልሽ ቁና ጤፍ ሰፍሬ
ባዶ እጄን አልቆምም ከደጅሽ ደፍሬ
ጵንፍ የለሽ ይቅርታን ውሰጅ ከከንፈሬ፡፡

✰ገጣሚ በእውቀቱ ስዩም

@gGetem
@leoyri
ከመሸ መጣሽ
ከመሸ ...
ቀናቴ ከሸሸ
ትዝታሽ ከራቀኝ
ህመም ከተሻለኝ
ሲዘነጋኝ መልክሽ 
ተተረሳኝ ድምፅሽ
ከመሸ መጣሽ
ከመሸ ...
ቅስሜ ከሟሸሸ
እንደ ጋሪ ፈረስ 
የኋላው ተጋርዶኝ ..
ታሪክሽ ሰይጣኑ
ጠበል ተረጭቶበት
እየጮኸ ለቆኝ ..
ሀሞቴ ሲመርር 
ኮሶ ሲሆን ሬት 
አንጀቴ ሲደድር
እንደ ድርቃም መሬት..
ከመሸ መጣሽ
ከመሸ.. .
ልቤ ከጠለሸ
ስምሽ እንደ ንጉስ
ተሽሮ በሌላ ...
ገላዬ ሲለምድ
የአዲስ ሴት ገላ 
ሁሉ ሲፈጣጠም
ሲዘጋ ክፍቱ በር 
እንዲህ ሆኜ ባይሆን 
መምጣት ጥሩ ነበር !!

(ሚካኤል.አ)

@sirak6
www.tgoop.com/gGetem
የሆሄያት ህብር💐💐💐
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#አይፀለይም !

ለሁሉም ግዜ አለው ፥ ይሉትን ዘንግቼ
ያላቅሜ ፀሎት ፥ ሱባኤ ገብቼ
በፆም ተግቼ
ስጠኝ በአንዲት ጀንበር
እያልኩኝ ሳስቸግር
እርሱም ዝም አላለኝ ፥ ልመናዬን ሰምቶ
የምፈልገውን ፥ አደለኝ አብዝቶ
እኔመች አውቄው ፥ እንደምሞት ቶሎ
ለካ አይፀለይም
አታስርበኝ እንጂ ፥ ጥጋብ ስጠኝ ተብሎ።

​​               ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
       ✍🏽©       በሜሮን ጌትነት
    ╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈ 


ምንጭ ➸ ሶልያና
ለመቀላቀል 👉🏽 @gGetem
አስተያየት 👉🏽 @sirak6
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━


ናላ በጭጋግ ሲሸፈን ፥
                      ልቦና በስጋት ሲባባ ፣
መርሳት በራስ ቤት ሲሰራ ፥
                      ፍርሃት ግንቡን ሲገነባ  ፣
ጭንቀት ጓዙን ሲያሳርፍ ፥
                      መጠርጠር ጫፉ ሲተባ ፣
ላወቀ መንቃት ያኔ ነው ፥
                       የህይወት ክረምት ሲገባ ፣
    
​​               ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
       ✍🏽©          ጌትነት እንየው
    ╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉

📔 የደራሲው ማስታወሻ
✍🏽 ተስፋዬ ገብረአብ


ለመቀላቀል 👉🏽 @gGetem
አስተያየት 👉🏽 @sirak6
👴አህያ ባረገው🐴
ገጣሚ፦ ጌትነት እንየው
አንባቢ፦ ሊዮ ማክ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
#ማጀቢያ፦ ሰለና ሀብቶም(ሰሊሀ)👧
😍በየቀኑ አዳዲስ የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!!!
@gGetem
Comment_
@sirak6
#ሸጋ ቅዳሜ
#ከድንቅ አቀራረብ ጋር....😘😢
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
👂ነጋሪት በጆሮ😋👂
#የቃልዬ_ደብዳቤ_®
#ቀን_04_02_2008_ዓ_ም_
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@gGetem
@gGetem
@leoyri
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
👨‍🌾👩‍🌾 አባቴ👨‍🌾👨‍🌾
#ማሂ 👩‍🎤👩‍🎤
የሆሄያት ህብር 🦋🦋🦋🦋
ለሀሳብ እና አስተያየት @Leoyri
@gGetem
@gGetem
@gGetem
ሸርተትበገዛ አንደበት
እመዳፌ ያለች ግልጦሽ ያልዳሰሳት
መታፈሪያ ጥዑም መለያ ቢሆናት
ፈቀቅ ከእምነት ጥግ፤
እንዲሁ በቀላል ለይስሙላ ወገግ፤
ሆኖ ቢጎበኛት....
አረፈችው አሉ....
          ብትደክም በጩኸት።

ደግሞ አሉ እኮ ነው፤
ባልተገራ ወሬ ለ'ውነት ያልቀረበ
በማይፀና ልሳን ሀሠት  የተራበ።
ከእውነታ ውሎ ከሀቅ ያላደረ
   ብዙ ልሳን አለ!!!!!
® #ሊዮሪ
@leoyri
@gGetem
18/12/2013ዓ.ም (WR)
🔎🔎ሀቅን ባናስተውላትም እንመለከታታለን!!!!!!!
የተሰደደ ልብ
ፀሀፊ፦ሊዮ ማ.

ደግሞም  የትኛውም በእውነተኛ የፍቅር መሰረት ላይ የታነፀ ፍቅር አንዱ ወደ አንዱ የማይመለስ መስሎት ቢሰደድ እንኳን መዳረሻው ግን ተስፋ አጥቶ ቆሞ በቀረበት መዳረሻ ላይ ሳለ የይቅርታ አልያም የመናፈቅ ንፋስ መልሶ ሸሽቶ ከተሸሸገበት ልብ አጠገብ መልሶ መላልሶ ማስቀመጡ አይቀሬ ነው።ምክንያቱም የቱንም ያክል በአብሮነት ከገነባነው የጥምረት ጎጆ መሸሽ፣መራቅ፣ማምለጥ ብናልምም የፀሐፊው ፍቃድ ከሆነ በምንም መልክ መለያየት ፈፅሞ የማይሆን ነገር ነው።
  "በእኛም የፍቅር ታሪክ የተፈጠረው ይሄው እውነት ነው!!!
....
#መሳጭ_ታሪክ
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
👂ነጋሪት በጆሮ😋👂
#የጆሲ_ደብዳቤ_®
#ቀን_11_03_2008_ዓ_ም_
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@gGetem
@gGetem
@leoyri
ዐየኋት!
አማልክት እሳት ጭረው፥ ፈንድሻ እንደቆሉበት
ጥርሷ ከንፈር እየጣሰ፥ ይፈነዳል እንደዘበት
እ.ን.ደ.ዘ.በ.ት.
ያወራታል...ትስቃለች
ተርገፍግፋ
ተንፈራፍራ
በወጉ እቶን ትነፍራለች
ሁለት ዐይኗ እስኪከደን፥ ያለችበት እስኪጠፋት
ፊቷ ሳምባ እስኪመስል፥እንባ ቁልቁል እስኪረግፋት
ባሳሳቋ እንግዴነት፥ ማን መኾኗ እስኪጠፋኝ
"ከኔ ስትስቅ አልነበረም?" እስክል ድረስ እስኪከፋኝ።
ትነፍራለች እ..ን..ደ..ዘ..በ..ት..
ቧጥጦ መውጫው ከቸገረኝ
ከሳቋ አምባ ያለ እጅ'ግር፥ በቀልድ አክናፍ ሲወጣበት
የናፈቅሁት ፈገግታ ላይ፥ ጭንጋፍ ወጋም ሰው ሲያዝበት
እ...ን...ደ...ዘ...በ...ት...
ኾድና ብብቱን
እንደኮረኮሩት፥ ጨቅላ ሳቅ ሲያጠምቃት
እንደዐለት ካይኖቿ
በጨዋታው በትር፥ እንባ ሲያስፈልቃት
ለመታዘብ ማቃት፤
ቢቻል ባንዳች መላ
እውን ላይ ተኝቶ፡ ወደ ቅዠት መንቃት።
የአፍቃሪ የወዳጅ ጸሎት ምርቃቱ
ብትገመስ እንኳ
የልቡ ሴት... ሐሴት
ክብሩ ሞገሱ እንጂ፥ መች ነበር ጥቃቱ?
ማለት ማመዛዘን ... ራስ መግራት ከንቱ!
ተውኝ ላልቅስበት
ጥርሷ ላይ ታውቆኛል፡
ተስፋ እያርከፈከፍኩ
ወራት ያቆየሁት፡ ፍቅራችን መሞቱ።
ወትሮም...
ቢታረድ ቢቀጠፍ ቢጣፍጥ መብሉ
በጥርስ ነውና፥ የሚፈታው ውሉ
በገደል በጋራው፥ ፍቅራችን ቢያልፍ ሁሉን
ሳቅ ነበር መለኪያው፥ መክበዱን መቅለሉን።
እንዳ'ደይ መፍካቷ፥
ልቤንም ቢከፋው፡ ልቤን ደስም ቢለው
ከቶ እንደምን ብዬ፥
በጥርሷ ሚዛን ላይ፥ መቅለሌን ልቻለው?

@gGetem
@gGetem
@sirak6
“ለምን ትመጫለሽ?
ወና መሆን ለምዷል
ባይተዋር ነው ሆዴ
ትራስ አቅፎ ማደር
ለምዶበታል ክንዴ።
ገላዬ ቀዝቅዟል
ልቤ ተሰቅዟል
እንስት እንዴት ልመን?
ዜሮ ነኝ ስተመን
ብትመጭም ከንቱ ነው
መመለስሽ ምንም
ስታወሪ አልስቅም
በእንባሽ አልቆዝምም
በድን ነኝ አልድንም ።
የለሁም በድሮ
ሌላ ነኝ ዘንድሮ
ግዴ አይደለም ነገ
ወጋገን ማለዳው
ለዛሬ ሶስት ዓመት
ዛሬን ነው ‘ምቀዳው።
አትገርመኝም ጀንበር
ብራና ክረምቱ
ቢዛወር ዓመቱ
ጨፍሬ አልደክርም
አልመታም አታሞ
ዓመት አንድ ቀን ነው
ለከሸፈ ታሞ ።
ለምን ትመጫለሽ ?
መምጣትሽ እንደ ቧልት
መመለስሽ ምንም ...”
ይህንን እያልኩኝ
ብናገር ብገጥምም
ስትመጪ ስዳበስ
በጣት በመዳፍሽ
ያልኩትን ዘንግቼ
አዲስ ሰው ሆንኩልሽ።

አትሄጂም አይደለ ?🙄

(ሚካኤል አ)
For Comment
@sirak
www.tgoop.com/gGetem
የመብረር ነፃ_ነት👼
ገጣሚ፦ ሚካኤል አስጨናቂ
አንባቢ፦ ሊዮ ማክ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
#ስክነት፦አቢ ላላ  🧏
😍በየቀኑ አዳዲስ የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!!!
@gGetem
Comment_
@sirak6
🧎‍♂👨‍🦯🚶‍♂🏃‍♂
ሚስጥር
<unknown>
🤷‍♂ሚስጥር ቅኔ ትርጉም🤝
ገጣሚ፦ ስንታየው ስንሻው 🙍‍♂
አንባቢ፦ አዚታ 🙍‍♀
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
#ውህደት፦ቃልኪዳን አለማየሁ💇‍♀  
🕸በየቀኑ አዳዲስ የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!!!
@gGetem
Comment_🧑‍💻
@sirak6
💚💛
📻 #ሆሄ_በሬድዮ 📻
#የወይን_መስኮቶች 🍇🏠
ውህደት፦ሲፈን ሞሲሳ
ምንጭ፦ FM ADISS 97.1
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@sirak6
www.tgoop.com/gGetem
እኔ ምልህ?
አገኘሀት?
:
ያቺን ምጥን
የሰው ምታ'ት!
.
ምናለችህ - ስታወጉ ?
ምን ብላለች ~ ስትጫወት ?
ያምና ውድህ ~ ያይንህ ውበት !
.
ትዝ ይላታል ስላለፈው ?
በዛ ቀሚስ ~ ስስ ነፍስህን ስትንጠው?


ትዝ ይላታል ~ ያንተ ሳቅህ ?
ታወሳት ወይ ~ ያ ደረትህ ?
የክንድህ ላይ ~ ንቅሳትህ
ስሟን ያተምክበት
..............ጥቁር ምልክትህ
ትዝ አላት ወይ?
ጥርስ ገላጭ ~ ለዛ ቀልድህ?

ምን ትላለች
ስለ ትናንት —-
ከንፈርህ ዳሳ - ተኩሳህ እንደ እሳት
ልብህን አድብናት…
ቀልብህን አጉናት ...
ስትነጥልህ ፦  ከሰው መንጋ
ለሌላው ጨልመህ ለርሷ ስትነጋ፤

ታወሳት ፦ ትዝ አላት?
.
ተበድረህ ለልደቷ
የአንገት ሀብል ስትገዛላት?
ለብርቋ ቀን ስትደርስላት
.
ውዴ ብላ
ተንጎማላ
ውዱ ብላ
ተገማሽራ
ስትሸጎጥ ስርህ
ተሞልታ ~ በኩራት
ከእናቷ ለጥቆ
በፍቅር ወልደሀት..
ሞገስ ሆነህ
ቅባት ሆነህ
እንደ ጣይቱ አንግሰሀት
ጓዶቿ ፊት ጌጥ ሆነሀት

እንደው ምናለችህ ?
ስታገኛት ፣ ስትቀርባት
ያቺ ምጥን
የሰው ምታ’ት?
.
ምን ብላለች ስትጫወት?
ያምና ውድህ ያይንህ ውበት !

.
ብዬ ብጠይቀው
እየተናነቀው...
.
"ሳቄ አይደል ጠረኔ
ምኑም የላት ከኔ
ይልቅ ስጠይቃት
የታወሳት የገረማት...
ከቀን መርጦ የመጣላት
የኔ ችጋር ~ የኔ ማጣት
ለዓይኗ እንኳ ጠገነንኳት ።"

ብሎ መለሰልኝ...

(ሚካኤል አ)
🫥🤥
@sirak6
www.tgoop.com/gGetem
ጊዜ እንዳለኝ እያሰብኩ ነበር — እንደምኖር።

በመጻሕፍት መደርደሪያዬ እኔን መጠበቅ ያደከማቸው ያልተነበቡ መጻሕፍት ተገጥግጠዋል።

አንድ ቀን እንደማነባቸው ተስፋ ሳደርግ ምጽዓት ደረሰ —ሀገሬ። በሲዖል ውስጥ መጽሐፍ ማንበብ አይቻልም። አንደኛ ሀገሩ የእሳት ነው። በእሳት ሀገር ወረቀት ቀለም ይዞ አይቆይም። ይነዳል፥ አመድ ይሆናል። ብዙ ጩኸት አለ —ሰቆቃ። እና አይመችም። ዙሪያው ገደል ነው። ልብ ዝቅ ያደርጋል።

ቀን በቀን መጻሕፍቴን እየተሰናበትኩ ነበር። ምን ትርጉም አለው? ሳልፈልግ አእምሮዬ እንደተረበሸ ከተማ ሐሳብ ይጎሎጉላል።  በሥነ ሥርዓት ላጠነጥን እሞክራለሁ —መሥመር ላስይዝ። ግን አልችልም ይሳከርብኛል። አንጎሌ፥ ሰውነቴ ይሰንፋል። 

የምናደርገው ነገር ትርጉም መስጠት ያቆመበት በሚመስልበት ጊዜ ላይ ነን። እዚህ ሀገር ልጅ እንወልዳለን። የምናወርሰው ሀገር ግን ሲዖል ነው። ምሽቶች ባሎቻቸው ድንገት በወጡበት ይቀራሉ። ይታፈናሉ፥ ይታገታሉ። ልጆች ያልጠገቡትን፥ በውል ያለዩትን አባቶቻቸውን ባልጠበቁት ቅጽበት ይሰናበታሉ። ለሀገራቸው ውለታ የዋሉ ዋርካ ሰዎች በልጅ እግሮች ይገደላሉ። ደም ይፈሳል —በየመንገዱ፥ በየጫካው።  አድባራት አንድ ባንድ ይፈርሳሉ። ማንም ምንም ማምጣት የሚችል አይመስልም። ድንገት ኢምንትነት እንዲሰማህ ትሆናለህ።

ሞት እየጠራህ ትማራለህ? ሞት እያነፈነፈህ ታከማቻለህ? በደጅህ ሞት እያደባ ታገባለህ? ሀገር እየተቃጠለ ትሰርጋለህ? ቆንጆ ቆንጆ ልጆች የጥይት እራት እንዲሆኑ ትወልዳለህ? መሣሪያ የታጠቀ ወንበዴ ቤትህን እየሠረሠረ ታንቀላፋለህ? ዳሩ ብትነቃስ ምን ታደርጋለህ? የዓለም ምጽዓት አንተ ጋር እስከሚደርስ ብትተኛ አይከፋም፥ ብትማር፥ ብትቆጥብ፥ ብታገባ፥ ብትወልድ።

ሀገሩ የባለጌ ነው። ማን ጌታ እንደሆነ አይታወቅም። በመንገድ ስታልፍ ረግጦህ የገላመጥከው ሰው ዘመደ ብዙ ነው። የጦር መሣሪያ አለው። ባታውቀውም የጎበዝ አለቃ ነው። ትንሽ መንግሥት ነው። ሕይወትህን ከአፈር ይደባልቀዋል። ያየህ እስከማይገኝ ድረስ ድራሽህ ይጠፋል። ወዝህ ያስቀናው ሰው ዳር ሊያስይዝህ ይችላል።

ሀገርህ ከየት እስከየት እንደሆነ አታውቅም። እግርህ ከቤት ወጣ እንዳለ የጠላት ሀገር ነህ። በካርታ ባይከለልም የተበጀ ድምበር አለ። ድንገት  ትጨመደዳለህ፥ እጅ ትሰጣለህ። ብትማረክም ትገደላለህ። ከቀን ውሎህ ተርፈህ፥ በሰላም ወጥተህ ከገባህ እድለኛ ነህ።  ከሄድክበት ስትመለስ ቤትህን በገነባህበት ስፍራ ላታገኘው ትችላለህ። ማንንም መርዳት አትችልም። ግፍና መከራ ተንከባሎ በሁሉም ቤት ይደርሳል። እስከዚያው ግን ተራው ያንተ ከሆነ ያንተ ነው። ትከሻህን ማስፋት፥ መቻል፥ መቀበል ይጠበቅብሃል። እውነት አይመስልም አይደል? ትላንት በእቅፍህ የነበረ ሰው እንደወጣ ሲቀር? ደብዛው ሲጠፋ?? ግን ይህ የብቻህ እውነት ነው። ይህ የብቻህ ሕመም ነው —ጽና።

እ. . .

ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን በሌላ አውድ የጻፈው አንድ ግጥም አለ። ያለ ዐውዱ እዚህ ጋር እንድጠቀመው ይፈቀድልኝ፦

“...ተገልለህ ርቀህ
እውነት ይተዉኛል ብለህ
እንዴት ተስፋ ታደርጋለህ?! . . . .
ተስፋ አድርገህስ ምን ልትሆን ፡ ወይስ ተስፋው ምን ሊሆንህ ?
እንቅልፍ እንጂ እሚያስወስድህ።”
Esubalew Nigussie
😢😢😢😢😢😢😢😢
@sirak6
www.tgoop.com/gGetem
ብቸኝነት  (በድሉ ዋቅጅራ)

እልፍኝህ እንዳʽብርሀም ቤት፣
አደባባይህ እንደጥምቀት፤
የሰው አሸን ቢወረው፣ ጠጠር መጣያ ቢገድም፤
ለመሀላህ ካስማ ʽሚሆን፣ ሲያነቅፍህ የምʽጠራው ስም፤
ከልቦናህ ሲነጥፍ፣ አንደበትህን ሲያንቀው፤
ብቻህን ነህ፣ ያኔ እወቀው፡፡

-----------
@leoyri
www.tgoop.com/gGetem
2024/06/26 02:44:17
Back to Top
HTML Embed Code: