#አልፎ_አልፎ_መሞት
ሰው
አንድም - በእግዜር፡
አንድም - በመውዜር፡
እያዋሀደ የዕድሜውን አመል፡
ማታ በውስኪ ጠዋት በጠበል።
ሰው ቢያጣ መንገድ ሰው ቢያጣ ምርጫ፡
ተከፋፍለው ተስፋን ለቅርጫ።
ተመዳደቡብኝ የመኖሬን ኮታ፡
አንድ ላይ ለበሱት ነፍሴን እንደኩታ።
እኔ ግን፡
ይጥቀማቸው ብዬ አልተወው መኖሬን፡
ብረግፍም አለሁኝ እድሜ ይስጠው ስሬን።
ሰው
ይመስለዋል እንጂ መተንፈስ አክራሞት፡
ስንቱን ያሻግራል አልፎ አልፎ መሞት።
@gGetem
@gGetem
ሰው
አንድም - በእግዜር፡
አንድም - በመውዜር፡
እያዋሀደ የዕድሜውን አመል፡
ማታ በውስኪ ጠዋት በጠበል።
ሰው ቢያጣ መንገድ ሰው ቢያጣ ምርጫ፡
ተከፋፍለው ተስፋን ለቅርጫ።
ተመዳደቡብኝ የመኖሬን ኮታ፡
አንድ ላይ ለበሱት ነፍሴን እንደኩታ።
እኔ ግን፡
ይጥቀማቸው ብዬ አልተወው መኖሬን፡
ብረግፍም አለሁኝ እድሜ ይስጠው ስሬን።
ሰው
ይመስለዋል እንጂ መተንፈስ አክራሞት፡
ስንቱን ያሻግራል አልፎ አልፎ መሞት።
@gGetem
@gGetem
የሆሄያት ህብር📝📝
ተለቀቀ... 👇👇👇 #ቲቸር_ለታይ_እና_ትውስታዎቿ ( #ፀሐፊ_ሊዮ_ማክ ) ክፍል አንድ (፩) ማለዳ ለስራ ከመውጣቴ አስቀድሜ እንደለመድኩት ሰፈር ውስጥ ከምትገኝ የሙስጢ ኪዮስክ ሻይ ቅጠል ለመግዛት አመራው።ሙስጢ ማለትም በትክክለኛው ስሙ ሙስጠፋ ጉራጌ በመሆኑ የተነሳ አማርኛ ሲናገር ልብን በሳቅ ፍርስ ያደረጋል።በተለይ ሁሌም ጠዋት ላይ ካንዲት ሴት ጋር የሚያደርገው እልህ…
#ቲቸር_ለታይ_እና_ትውስታዎቿ
( #ፀሐፊ_ሊዮ_ማክ )
ክፍል ሁለት (፪)
..... አይ ሙስጢ እሳት የላሰች ጉራጌ ናት እኮ "ጉድ ሞርኒንግ" ማለቱ ሰላምታውን አልነበረም የቀን ከቀን ሸመታዬ የሆነችውን ሻይ ቅጠል ለመፎገር እንጂ እውነት እንግሊዘኛ መናገር ለእሱ እንደ ጌታ ታምራት በውሀ ላይ የመራመድ ያክል ነው።ደግሞ ውሀ ብል አሉልኛ፡ልክ እንደ ስማቸው ውፍረታቸው የመርከብ ያክል የሚሰፋው ውሀ አስቀጅዬ እትዬ መርከብ።እንደውም ብዙ ጊዜ ቁጣቸውን በመፍራት ጠይቃቸዋለው እያልኩኝ ተወዋለው። እናት እና አባታቸው ምን ያክል የወደፊቱ ቢታያቸው ይሆን ገና በለጋ እድሜዋ መርከብ ሲሉ ያወጡላቸው።.....እንጃ
ብቻ እትዬ መርከብ ልጃቸው አረብ ሀገር በስደት ከሔደች በኃላ ሁለ ነገራቸው ተለዋዉጧል።በንግግራቸው መሀል ከንግግሩ ጋር ይስማማም አይስማማም እንግሊዘኛ ጣል ያደርጋሉ፣ቤታቸው እንኳን ካለ ቢቢሲ እና ሲኤንኤን አይከፈትም አሉ።እንደውም አንድ ጊዜ ጉረቤት ለቅሶ ላይ ወንዶች ተቀምጠው ወቅታዊ መነጋገሪያ ስለነበረው የራሺያ እና ዩክሬን የጦርነት ጉዳይ አንስተው ሲያወሩ እትዬ መርከብ ወሬው ቀልባቸውን ስለገዛው ከተቀመጡበት ፍራሽ ላይ ተስፈንጥረው ተነስተው ትንታኔ ሲሰጡ ነበር የተባለው ነገር በርግጥም በትኩረት መከታተላቸውን ያሳያል።በዚህ የተነሳ ይመስላል ውሀ ልቀዳ በሔድኩ ቁጥር በእጄ ላይ ያለውን ጄሪካን እያዩ እንኳን "ዋተር ነው?"ይሉኛል እንደው ማን ይሙት እና ሌላ እርሳቸው ናፍቀውኝ አልያም ለመንደርተኛው እንደሚያሳዩት ልጃቸው በነጭ ቢጃማ ግድንግድ አልጋ ላይ ሆና ተነስታ የምትልክላቸውን ፎቶ ለማየት አይሆን መቼም፤ ብቻ ይገርሙኛል እንዲህ ናቸው።በዚያ ላይ ባይደን ስለሰጠው የጣልቃ ገብነት ሀተታ ፣አፍጋን ላይ ስለተፈፀመው የሽብር ጥቃት፣ስለ ሀማስ ማስጠንቀቂያ አረ ስንቱ አሁን እሳቸው ከሀማስ ማስጠንቀቂያ ይልቅ ያለባቸውን አስም መላ ቢሉ በተሻላቸው ነበር።
(የ 6ኛ F ክፍል የነበራቹ.....😭አላቹ?😩)
ይቀጥላል
ሀሳብ እና አስተያየታችሁ አይለየኝ!!!!
www.tgoop.com/leoyri
www.tgoop.com/gGetem
( #ፀሐፊ_ሊዮ_ማክ )
ክፍል ሁለት (፪)
..... አይ ሙስጢ እሳት የላሰች ጉራጌ ናት እኮ "ጉድ ሞርኒንግ" ማለቱ ሰላምታውን አልነበረም የቀን ከቀን ሸመታዬ የሆነችውን ሻይ ቅጠል ለመፎገር እንጂ እውነት እንግሊዘኛ መናገር ለእሱ እንደ ጌታ ታምራት በውሀ ላይ የመራመድ ያክል ነው።ደግሞ ውሀ ብል አሉልኛ፡ልክ እንደ ስማቸው ውፍረታቸው የመርከብ ያክል የሚሰፋው ውሀ አስቀጅዬ እትዬ መርከብ።እንደውም ብዙ ጊዜ ቁጣቸውን በመፍራት ጠይቃቸዋለው እያልኩኝ ተወዋለው። እናት እና አባታቸው ምን ያክል የወደፊቱ ቢታያቸው ይሆን ገና በለጋ እድሜዋ መርከብ ሲሉ ያወጡላቸው።.....እንጃ
ብቻ እትዬ መርከብ ልጃቸው አረብ ሀገር በስደት ከሔደች በኃላ ሁለ ነገራቸው ተለዋዉጧል።በንግግራቸው መሀል ከንግግሩ ጋር ይስማማም አይስማማም እንግሊዘኛ ጣል ያደርጋሉ፣ቤታቸው እንኳን ካለ ቢቢሲ እና ሲኤንኤን አይከፈትም አሉ።እንደውም አንድ ጊዜ ጉረቤት ለቅሶ ላይ ወንዶች ተቀምጠው ወቅታዊ መነጋገሪያ ስለነበረው የራሺያ እና ዩክሬን የጦርነት ጉዳይ አንስተው ሲያወሩ እትዬ መርከብ ወሬው ቀልባቸውን ስለገዛው ከተቀመጡበት ፍራሽ ላይ ተስፈንጥረው ተነስተው ትንታኔ ሲሰጡ ነበር የተባለው ነገር በርግጥም በትኩረት መከታተላቸውን ያሳያል።በዚህ የተነሳ ይመስላል ውሀ ልቀዳ በሔድኩ ቁጥር በእጄ ላይ ያለውን ጄሪካን እያዩ እንኳን "ዋተር ነው?"ይሉኛል እንደው ማን ይሙት እና ሌላ እርሳቸው ናፍቀውኝ አልያም ለመንደርተኛው እንደሚያሳዩት ልጃቸው በነጭ ቢጃማ ግድንግድ አልጋ ላይ ሆና ተነስታ የምትልክላቸውን ፎቶ ለማየት አይሆን መቼም፤ ብቻ ይገርሙኛል እንዲህ ናቸው።በዚያ ላይ ባይደን ስለሰጠው የጣልቃ ገብነት ሀተታ ፣አፍጋን ላይ ስለተፈፀመው የሽብር ጥቃት፣ስለ ሀማስ ማስጠንቀቂያ አረ ስንቱ አሁን እሳቸው ከሀማስ ማስጠንቀቂያ ይልቅ ያለባቸውን አስም መላ ቢሉ በተሻላቸው ነበር።
(የ 6ኛ F ክፍል የነበራቹ.....😭አላቹ?😩)
ይቀጥላል
ሀሳብ እና አስተያየታችሁ አይለየኝ!!!!
www.tgoop.com/leoyri
www.tgoop.com/gGetem
Telegram
Sirake Péterøs👦☞Ye Yerijo Leጅ
ሰኔ 16😘 kidanua🥰
👍1
እንደ ሰርከስ
መኖር በሀገርህ
የሰርከስ ትርኢት እንደማሳየት ነው
ስልጠናው ሳይኖርህ ::
በሚያድጥ ዳገት ላይ ፥በብጤህ መጋለብ
በሁለት መዳፎች፥ ሳይፎርሹ መቅለብ
-ደርዘን ሙሉ አሎሎ፥
አሎሎ ቢጠፋ ፥እሾህ ተደብልብሎ
በሳት ቀለበት ውስጥ ፥ማለፍ ሹልክ ብሎ፤
እንደ ህልም እሪታ፥ በሰለለ ገመድ
ባንድ እግር መራመድ፤
ይሄን ሁሉ አድርገህ፤ ትርኢቱም አልቆ
ካጥንቶችህ መሀል፥ አንዱ ተሰንጥቆ
አንደኛው ደንድኖ
እጅህ ወንፊት ሆኖ፤
ምንም ባትታደል፥ አንቱ የሚባል ስም
አሞጋሽ ለክብርህ፥ ነጋሪት ባይጎስም
ምናልባት ካተረፍክ-
ያልተራገፈ ጥርስ ፥ያልተሰበረ ቅስም
የድል ሳቅህን ሳቅ፥ በተረፈው ጥርስህ
በወንፊት መዳፍህ፥ አጨብጭብ ለራስህ::
@gGetem
@gGetem
@yosikeman
መኖር በሀገርህ
የሰርከስ ትርኢት እንደማሳየት ነው
ስልጠናው ሳይኖርህ ::
በሚያድጥ ዳገት ላይ ፥በብጤህ መጋለብ
በሁለት መዳፎች፥ ሳይፎርሹ መቅለብ
-ደርዘን ሙሉ አሎሎ፥
አሎሎ ቢጠፋ ፥እሾህ ተደብልብሎ
በሳት ቀለበት ውስጥ ፥ማለፍ ሹልክ ብሎ፤
እንደ ህልም እሪታ፥ በሰለለ ገመድ
ባንድ እግር መራመድ፤
ይሄን ሁሉ አድርገህ፤ ትርኢቱም አልቆ
ካጥንቶችህ መሀል፥ አንዱ ተሰንጥቆ
አንደኛው ደንድኖ
እጅህ ወንፊት ሆኖ፤
ምንም ባትታደል፥ አንቱ የሚባል ስም
አሞጋሽ ለክብርህ፥ ነጋሪት ባይጎስም
ምናልባት ካተረፍክ-
ያልተራገፈ ጥርስ ፥ያልተሰበረ ቅስም
የድል ሳቅህን ሳቅ፥ በተረፈው ጥርስህ
በወንፊት መዳፍህ፥ አጨብጭብ ለራስህ::
@gGetem
@gGetem
@yosikeman
👍2❤1
የቢሆን ዓለም ክፍል 10
@gGetem
⎈❉ የቢሆን ዓለም ❉⎈
✅ #ክፍል_10
✰ ደራሲ - ደጉ ቁምቢ
✰ ተራኪ - ተስፋሁን ገ/ዩሐንስ
✅✅ ሁላችሁንም ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ የፍቅርና ሳይንሳዊ ነክ ልቦለድ።
※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════ @yosikeman
✅ #ክፍል_10
✰ ደራሲ - ደጉ ቁምቢ
✰ ተራኪ - ተስፋሁን ገ/ዩሐንስ
✅✅ ሁላችሁንም ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ የፍቅርና ሳይንሳዊ ነክ ልቦለድ።
※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════ @yosikeman
የቱ ጋር መሰለህ…
(ሚካኤል አ)
መባቻ ጅምርህ
የነፍስህ ድባቴ
ውድቀት እንግልትህ
ያኔ …
ባሽትሪ መያዣ ፣ በሲጋራ ብናኝ
በርጋፊ ቅጠል ፣ ድባቧ የሚቃኝ
በዛች ጠባብ ክፍል
ምጥን መሰብሰቢያ
ዙሪያህን ሰው ሞልቶህ
ቀንህን ማጣፊያ
ለአፕላይ ግብዣ የተዘረጋች ጣት
በሚግተለተል ጢስ ፣ ሰንቃልህ እሳት
እሷን ለመቀበል ስትፈግግ ባ’ክብሮት
የሰበብ አስባብ ጢስ
ቀረ ቤትህን ወርሶት።
፡
የቱ ጋር መሰለህ?
፡
በቀይ መብራት ፍካት
በቅልቅል ሽቶ አዲስ አይነት ክርፋት
በጭላጭ ብርጭቆ ተላኮበት ድራፍት
ከስፒከር ማህፀን ሙዚቃ ተለቆ
ጭፈራ እና ዳንሱ አንድ ላይ ተዛንቆ
የቀይ ሴትን ታፋ ዓይንህ በስስ ሰርቆ
በምራቅህ ድርቀት ጉሮሮህ ተጨንቆ
ጠቅሰህ ስትጠራት
ያቺን የሞት ብልቃጥ
ከባቷ ፈልቅቀህ ዕፅዋን ስትቀምሳት
በገላህ ፍሰሀ መቅደስህን ናድካት ።
፡
የቱ ጋር መሰለህ?
፡
የልጅነት ልምድህ
ከሰንበት ቤት ገዳም
ምልልስ ብርታትህ
በዋዛ ሲቀየር
የያሬዱ ወረብ
በእስክስታ ሲዛወር
ስትዘነጋ ፀሎት
ሳይንስ ከእምነት ልቆት
ኒቼ ቦታ ሲወርስ የየኔታን መንበር
የነፍስህ ቁዘማ መንደርደሪያ ነበር።
፡
ትዝ አለህ?
፡
ዘር መራጭ ስትሆን
የደም ሴል መንጣሪ
ጆሮህ ዳባ ሲለብስ
ለፍጥረት እንግልት
ለህፃናት ጥሪ…
መንገድህ ሲሳለጥ
በ V 8 መኪና
ዝርግ አስፓልት ሲመስልህ
ጉርብጥብጥ ጎዳና ፤
ስቆልኛል ስትል ጥርሱን የነከሰ
እንባው አንሸራሽሮህ ጌታ ዘንድ ደረሰ።
፡
ያን ጊዜ ተከፋህ!
፡
ጥሬ እየቆረጥክ ሆድህ ሲመረመር
እስቲም ሳውና ገብተህ ፊትህ ሲጭበረበር
በድሎትህ መኃል
ገላን የሚያኮስስ የእሾህ ስንጥር ነበር።
፡
ትዝ አለህ?
፡
መኝታህ በምቾት ተሞልቶ በአጀብ
እንቅልፍህ ሲናጠብ?
፡
ትዝ አለህ?
፡
በውድ ቀለም ቤቶች ልጆችህ ሲማሩ
ከግብረገብ ታዛ ተናንሰው ሲቀሩ?
፡
ትዝ አለህ?
፡
የጉያህ መልካም ሴት
የአጥንትህ ፍላጭ
‘አሁን ከምን ጊዜው
ሆነችብኝ ምላጭ? ‘
ብለህ ስትቆዝም … ?
፡
እንዲያ ነው አይዋ…
ግፍ ፅዋው ሲሞላ
በትሩን አይመርጥም።
፡
ትዝ አለህ?
ታወሰህ?
የቱ ጋር መሰለህ?
የተፈታው ውሉ
የጎደልክ ከሙሉ
‘ኧረ ስከን’ ሲሉ
ከዕድሜ የተማሩ
የጋሽ ውቤን ምክር
የእመት ጉሌን ዝክር
ረግጠህ ስትበር…
ስትሻገር ፣ ስጥስ
የምስኪናን ድንበር
የዛሬ ውድቀትህ ፣ በግጥም ሊነገር
ክንፍህ የተመታው ይሄን ጊዜ ነበር።
ትዝ አለህ?
፡
አዎን እሱ ጋር ነው!
@gGetem
@gGetem
@gGetem
(ሚካኤል አ)
መባቻ ጅምርህ
የነፍስህ ድባቴ
ውድቀት እንግልትህ
ያኔ …
ባሽትሪ መያዣ ፣ በሲጋራ ብናኝ
በርጋፊ ቅጠል ፣ ድባቧ የሚቃኝ
በዛች ጠባብ ክፍል
ምጥን መሰብሰቢያ
ዙሪያህን ሰው ሞልቶህ
ቀንህን ማጣፊያ
ለአፕላይ ግብዣ የተዘረጋች ጣት
በሚግተለተል ጢስ ፣ ሰንቃልህ እሳት
እሷን ለመቀበል ስትፈግግ ባ’ክብሮት
የሰበብ አስባብ ጢስ
ቀረ ቤትህን ወርሶት።
፡
የቱ ጋር መሰለህ?
፡
በቀይ መብራት ፍካት
በቅልቅል ሽቶ አዲስ አይነት ክርፋት
በጭላጭ ብርጭቆ ተላኮበት ድራፍት
ከስፒከር ማህፀን ሙዚቃ ተለቆ
ጭፈራ እና ዳንሱ አንድ ላይ ተዛንቆ
የቀይ ሴትን ታፋ ዓይንህ በስስ ሰርቆ
በምራቅህ ድርቀት ጉሮሮህ ተጨንቆ
ጠቅሰህ ስትጠራት
ያቺን የሞት ብልቃጥ
ከባቷ ፈልቅቀህ ዕፅዋን ስትቀምሳት
በገላህ ፍሰሀ መቅደስህን ናድካት ።
፡
የቱ ጋር መሰለህ?
፡
የልጅነት ልምድህ
ከሰንበት ቤት ገዳም
ምልልስ ብርታትህ
በዋዛ ሲቀየር
የያሬዱ ወረብ
በእስክስታ ሲዛወር
ስትዘነጋ ፀሎት
ሳይንስ ከእምነት ልቆት
ኒቼ ቦታ ሲወርስ የየኔታን መንበር
የነፍስህ ቁዘማ መንደርደሪያ ነበር።
፡
ትዝ አለህ?
፡
ዘር መራጭ ስትሆን
የደም ሴል መንጣሪ
ጆሮህ ዳባ ሲለብስ
ለፍጥረት እንግልት
ለህፃናት ጥሪ…
መንገድህ ሲሳለጥ
በ V 8 መኪና
ዝርግ አስፓልት ሲመስልህ
ጉርብጥብጥ ጎዳና ፤
ስቆልኛል ስትል ጥርሱን የነከሰ
እንባው አንሸራሽሮህ ጌታ ዘንድ ደረሰ።
፡
ያን ጊዜ ተከፋህ!
፡
ጥሬ እየቆረጥክ ሆድህ ሲመረመር
እስቲም ሳውና ገብተህ ፊትህ ሲጭበረበር
በድሎትህ መኃል
ገላን የሚያኮስስ የእሾህ ስንጥር ነበር።
፡
ትዝ አለህ?
፡
መኝታህ በምቾት ተሞልቶ በአጀብ
እንቅልፍህ ሲናጠብ?
፡
ትዝ አለህ?
፡
በውድ ቀለም ቤቶች ልጆችህ ሲማሩ
ከግብረገብ ታዛ ተናንሰው ሲቀሩ?
፡
ትዝ አለህ?
፡
የጉያህ መልካም ሴት
የአጥንትህ ፍላጭ
‘አሁን ከምን ጊዜው
ሆነችብኝ ምላጭ? ‘
ብለህ ስትቆዝም … ?
፡
እንዲያ ነው አይዋ…
ግፍ ፅዋው ሲሞላ
በትሩን አይመርጥም።
፡
ትዝ አለህ?
ታወሰህ?
የቱ ጋር መሰለህ?
የተፈታው ውሉ
የጎደልክ ከሙሉ
‘ኧረ ስከን’ ሲሉ
ከዕድሜ የተማሩ
የጋሽ ውቤን ምክር
የእመት ጉሌን ዝክር
ረግጠህ ስትበር…
ስትሻገር ፣ ስጥስ
የምስኪናን ድንበር
የዛሬ ውድቀትህ ፣ በግጥም ሊነገር
ክንፍህ የተመታው ይሄን ጊዜ ነበር።
ትዝ አለህ?
፡
አዎን እሱ ጋር ነው!
@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍1
Audio
።።ለ እግዜር የተላከ ደብዳቤ።።
እንደምነህ እግዜር ሰማይቤት እንዴት ነው
እመጣለው ብለህ ቆየህሳ ምነው
እኛማ... ለእልፍ አላፍ አለቃ ማመልከቻ ፅፈን
ለወፈ ሰማይ ህዝብ መድረክ ላይ ለፍፈን
ጸሎት ቤታችንን እኛው ለይ ቆልፈን
የምድር ሃተካራ ህግጋቱን አልፈን
ደብዳቤ ላክንልህ ✉️
አይንህን ካየነው ሁለት ሺ ዘመን እንደ ቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ተስፋ እየኮሰመነ መቅረትህ ገዘፈ
አረረረረረረረ.......
እንደውም እንደውም
በመጣለው ተስፋ ሁለት ሺ ዘመን ገትሮን ከጠፋ
በቀጠሮ ሰዓት መምጣት ከተሳነው እግዜር ሃበሻ ነው
እያሉ ያሙሃል
እኔ ምን አውቃለው...ህ እኔ ምን አውቃለው...
አመስግነው ሲሉኝ እልልታ የማቀልጥ
ቃሉን ስማ ሲሉኝ ሰባኪው እግር ስር በደስታ ምቀመጥ
እግዚሆ በል ሲሉኝ እንባዬን የማፈስ
ሃሌሉያ ሲሉኝ በሳቅ ልቤ ሚፈርስ
ምናምኒት እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ
እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ
እኔ.... እኔ ምን አውቃለው
ግን አንተ ደህና ነህ
ከምር እንደሚያሙት ምፅሃት ቀረ እንዴ
የሰናፍጭ ቅንጣት ጥርጣሬ እትከፋም አንዳንዴ
ከሆነስ ሆነና ሰማይቤት እንዴት ነው
አብረሃም ሰላም ነው
እዛስ ቤት ገነባ ዛሬም በድንኳን ነው
እኛማ የውልህ በቤት ኪራይ ችንካር እየተሰቀልን
ኤሎሄ እንላለን ጎጆ እንድጥልልን
ወደላይ ገነባን ወደጎን አሰፋን
ወደላይም ከላይ ወደጎንም ከጎን እንደጉድ ተጋፋን
ቤት ለእንግዳ ማለት ጭራሹኑ ጠፋን
ውይ... አባታችን ሙሴ እንዴት ነው ለክብሩ
እውቂያኖስ መክፈያው ደህና ናት በትሩ
እኛማ የውልህ እንጀራ ፍለጋ በሃር ስናቋርጥ
የተስፋዋን ምድር አሸዋ ሳንረግጥ
የትም ውሃ በላን የትም አሳ ላሰን
ንገርልን እና ብትሩን ያውሰን..
※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
ண @gGetem
════ ♢.✰.♢ ═══ @yosikeman
እንደምነህ እግዜር ሰማይቤት እንዴት ነው
እመጣለው ብለህ ቆየህሳ ምነው
እኛማ... ለእልፍ አላፍ አለቃ ማመልከቻ ፅፈን
ለወፈ ሰማይ ህዝብ መድረክ ላይ ለፍፈን
ጸሎት ቤታችንን እኛው ለይ ቆልፈን
የምድር ሃተካራ ህግጋቱን አልፈን
ደብዳቤ ላክንልህ ✉️
አይንህን ካየነው ሁለት ሺ ዘመን እንደ ቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ተስፋ እየኮሰመነ መቅረትህ ገዘፈ
አረረረረረረረ.......
እንደውም እንደውም
በመጣለው ተስፋ ሁለት ሺ ዘመን ገትሮን ከጠፋ
በቀጠሮ ሰዓት መምጣት ከተሳነው እግዜር ሃበሻ ነው
እያሉ ያሙሃል
እኔ ምን አውቃለው...ህ እኔ ምን አውቃለው...
አመስግነው ሲሉኝ እልልታ የማቀልጥ
ቃሉን ስማ ሲሉኝ ሰባኪው እግር ስር በደስታ ምቀመጥ
እግዚሆ በል ሲሉኝ እንባዬን የማፈስ
ሃሌሉያ ሲሉኝ በሳቅ ልቤ ሚፈርስ
ምናምኒት እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ
እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ
እኔ.... እኔ ምን አውቃለው
ግን አንተ ደህና ነህ
ከምር እንደሚያሙት ምፅሃት ቀረ እንዴ
የሰናፍጭ ቅንጣት ጥርጣሬ እትከፋም አንዳንዴ
ከሆነስ ሆነና ሰማይቤት እንዴት ነው
አብረሃም ሰላም ነው
እዛስ ቤት ገነባ ዛሬም በድንኳን ነው
እኛማ የውልህ በቤት ኪራይ ችንካር እየተሰቀልን
ኤሎሄ እንላለን ጎጆ እንድጥልልን
ወደላይ ገነባን ወደጎን አሰፋን
ወደላይም ከላይ ወደጎንም ከጎን እንደጉድ ተጋፋን
ቤት ለእንግዳ ማለት ጭራሹኑ ጠፋን
ውይ... አባታችን ሙሴ እንዴት ነው ለክብሩ
እውቂያኖስ መክፈያው ደህና ናት በትሩ
እኛማ የውልህ እንጀራ ፍለጋ በሃር ስናቋርጥ
የተስፋዋን ምድር አሸዋ ሳንረግጥ
የትም ውሃ በላን የትም አሳ ላሰን
ንገርልን እና ብትሩን ያውሰን..
※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
ண @gGetem
════ ♢.✰.♢ ═══ @yosikeman
❤2
(ስረቂኝ ልስረቅሽ)
ነይ እንሰራረቅ
ህግን ገንድሰነው እንጣል ከስሩ
ሌባና ባለቤት ተሳማምተው ይደሩ
ነይና ስረቂኝ
አንቺ ክቡር ሌባ ተሰናድቷል ቤቱ
እጠብቅሻለሁ በናፍቆት ጓጊቼ እኔ ባለቤቱ
ነይና ስረቂኝ
በዘረፋ ስርቆት ባዶ ቤቴን ፍጂው
ከአዳራሹ ዘልቀሽ ነይ ልቤን ውሰጂው።
ነይ ልስረቅሽ ደሞ
አበጃጂ ቤቱን እንቶፈንቶው ይውጣ
ስቀሽ ተቀበይኝ ልሰርቅሽ ስመጣ
እናፋልስ ህጉን
ልብሽን ስሰርቀው ስቀሽ ተሰረቂኝ
ሃገር ልይዘኝ ስል
ንፁ ሌባ ብለሽ አፅድቂና ላኪኝ።
ነይ እንሰራረቅ
@gGetem
@gGetem
ነይ እንሰራረቅ
ህግን ገንድሰነው እንጣል ከስሩ
ሌባና ባለቤት ተሳማምተው ይደሩ
ነይና ስረቂኝ
አንቺ ክቡር ሌባ ተሰናድቷል ቤቱ
እጠብቅሻለሁ በናፍቆት ጓጊቼ እኔ ባለቤቱ
ነይና ስረቂኝ
በዘረፋ ስርቆት ባዶ ቤቴን ፍጂው
ከአዳራሹ ዘልቀሽ ነይ ልቤን ውሰጂው።
ነይ ልስረቅሽ ደሞ
አበጃጂ ቤቱን እንቶፈንቶው ይውጣ
ስቀሽ ተቀበይኝ ልሰርቅሽ ስመጣ
እናፋልስ ህጉን
ልብሽን ስሰርቀው ስቀሽ ተሰረቂኝ
ሃገር ልይዘኝ ስል
ንፁ ሌባ ብለሽ አፅድቂና ላኪኝ።
ነይ እንሰራረቅ
@gGetem
@gGetem
🥰1
የኔ ጌታ የልቤ ሰው
በልቤ ላይ የነገስከው
ጆሮ ስጠኝ እስኪ ላፍታ
እንድነግርህ የልቤን እውነታ
ከግሪክ ከግእዝ ከኩሽ አማርጬ
ከሳባውያኑ ፊደላት ቀይጬ
ቃላት አዋድጄ ቤቱን አማትቼ
ስንኝን ከአንጓ ለውሼ ፈትፍቼ
ከአለማት ቋንቋ ፊደላት ተውሼ
ቅንጣት እስከማይቀር ብእራት ጨርሼ
የሞነጫጨርኩት ወሰን አልባ ግጥም
ፈፅሞ አንተን አይገልፅህም
የኔ አባት የኔ ጀግና
መልከመልካም ልበ ቀና
ቁመናህም ደም ግባትህ
ልብ ይሰርቃል አካሄድህ
......ታውቃለህ ግን...
ካንተ ስውል ሙሉ አለሜን አረሳለሁ
በደስታ ሰክሬ እፈለቀለቃለሁ
ፈገግ ስትልማ
ይመስለኛል የምሰማው ማህሌታይ ዜማ
ነፍሴን ስተቃኛት
በፍቅርህ ቃላት
ውዴ የኔ ስትላት
ምን ብዬ ልንገር
ፀሎቷ የሰመረ የልቧን ያገኘች
ተመስገን ተመስገን ቅኔን የተቀኘች
ያቺን ሴት ሆኛለሁ
አምላኬን ስላንተ አመሰግናለሁ
የኔ ውድ አፈቅርሃለሁ
ገጣሚ: ጆሲ(JOY see)
※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════ @yosikeman
በልቤ ላይ የነገስከው
ጆሮ ስጠኝ እስኪ ላፍታ
እንድነግርህ የልቤን እውነታ
ከግሪክ ከግእዝ ከኩሽ አማርጬ
ከሳባውያኑ ፊደላት ቀይጬ
ቃላት አዋድጄ ቤቱን አማትቼ
ስንኝን ከአንጓ ለውሼ ፈትፍቼ
ከአለማት ቋንቋ ፊደላት ተውሼ
ቅንጣት እስከማይቀር ብእራት ጨርሼ
የሞነጫጨርኩት ወሰን አልባ ግጥም
ፈፅሞ አንተን አይገልፅህም
የኔ አባት የኔ ጀግና
መልከመልካም ልበ ቀና
ቁመናህም ደም ግባትህ
ልብ ይሰርቃል አካሄድህ
......ታውቃለህ ግን...
ካንተ ስውል ሙሉ አለሜን አረሳለሁ
በደስታ ሰክሬ እፈለቀለቃለሁ
ፈገግ ስትልማ
ይመስለኛል የምሰማው ማህሌታይ ዜማ
ነፍሴን ስተቃኛት
በፍቅርህ ቃላት
ውዴ የኔ ስትላት
ምን ብዬ ልንገር
ፀሎቷ የሰመረ የልቧን ያገኘች
ተመስገን ተመስገን ቅኔን የተቀኘች
ያቺን ሴት ሆኛለሁ
አምላኬን ስላንተ አመሰግናለሁ
የኔ ውድ አፈቅርሃለሁ
ገጣሚ: ጆሲ(JOY see)
※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════ @yosikeman
👏4👍1
አንቺን ነበር የፈለኩት
ላንቺ ነበር የተሳልኩት
ወይ አለችኝ ህልም ብላ
ጋኔል አለች ጨለም ብላ
መቼ ሰማች ወይብላ
የጠራናት ከአመት ቁስል
ሞተን ቆየን መጣሁ ስትል
ደከምኩኝ እስካለሽ
ተብከነከንኩ በየአፍ
ይቅናህ በይኝ እንዳገኝሽ
አልደረስኩም ስንቱን ባልፍ
ደሜን ማነው ያባከነው
ሞቴን ብቻ ሚመነዝር
አንቺን ከእኔ እያራቁ
ቃሉን ደግመው የሚያሰምር
ማነው አንቺን የሚያፈቅር ?
ማነው አንቺን አምኖ ሚያድር
ማነው ላንቺ የሚሰክር ?
ከእኔ ብቻ ዕንባ ዕንባ
ከእኔ ሌላ ህመም አለ?
ወይ'ብላም አጠራኝም
ኮሶ ብቻ መድን ካለ
ኑሮሽን እንድሸከም
ወንድሞቼን ፈለኳቸው
ተከዜ ላይ ጎርፉን ሆነው
ወድቀው ነው ያየኋቸው
ሶስት አይን ጥቁር ያላት
ሀዘን ጫንቃ የበዛባት
ይቺ ሀገር ሀገር ሳትሆን
የሲኦል በር ማለፊያ ናት
@gGetem
@gGetem
@gGetem
ላንቺ ነበር የተሳልኩት
ወይ አለችኝ ህልም ብላ
ጋኔል አለች ጨለም ብላ
መቼ ሰማች ወይብላ
የጠራናት ከአመት ቁስል
ሞተን ቆየን መጣሁ ስትል
ደከምኩኝ እስካለሽ
ተብከነከንኩ በየአፍ
ይቅናህ በይኝ እንዳገኝሽ
አልደረስኩም ስንቱን ባልፍ
ደሜን ማነው ያባከነው
ሞቴን ብቻ ሚመነዝር
አንቺን ከእኔ እያራቁ
ቃሉን ደግመው የሚያሰምር
ማነው አንቺን የሚያፈቅር ?
ማነው አንቺን አምኖ ሚያድር
ማነው ላንቺ የሚሰክር ?
ከእኔ ብቻ ዕንባ ዕንባ
ከእኔ ሌላ ህመም አለ?
ወይ'ብላም አጠራኝም
ኮሶ ብቻ መድን ካለ
ኑሮሽን እንድሸከም
ወንድሞቼን ፈለኳቸው
ተከዜ ላይ ጎርፉን ሆነው
ወድቀው ነው ያየኋቸው
ሶስት አይን ጥቁር ያላት
ሀዘን ጫንቃ የበዛባት
ይቺ ሀገር ሀገር ሳትሆን
የሲኦል በር ማለፊያ ናት
@gGetem
@gGetem
@gGetem
👍3
, ፍልቅልቅ
ለጋው ሽንጥሽ ጯርቃ እጆችሽ
ጣፋጭ ማዛ ውብ ጠረንሽ ጨዋታዎችሽ
የልጅነት ፍልቅልቅ ጥርስና አይኖችሽ
አሁንማ ተቀይረው ጎልማሳ ሆነው
በቨሰለ ድርብ ስጋ ተሸፍነው ተከድነው
እንደድሮው ባይታዪም ከሩቅ ገነው
ብቻ ግን ባዬኋቼው ዳግመኛ የኔ ሆነው
መቼም እኔ ጭቀቴ ሀሳቤ ብዙ
ያባክነኛል ያንቺ ፍቅር መዘዙ
ማዕበል ፍቅርሽ ከልቤ ላይ ቋያ ፈጥሮ
ህዋሳቴን ያናውጣል እስትፋሴን ተቆጣጥሮ
ውብ ቀለምሽ ጣፋጭ ማዛሽ ጎልቶ ነጥሮ
ዳንኩኝ ስል ይገለኛል ይጥለኛል አሽቀጥሮ
@gGetem
@gGetem
@gGetem
ለጋው ሽንጥሽ ጯርቃ እጆችሽ
ጣፋጭ ማዛ ውብ ጠረንሽ ጨዋታዎችሽ
የልጅነት ፍልቅልቅ ጥርስና አይኖችሽ
አሁንማ ተቀይረው ጎልማሳ ሆነው
በቨሰለ ድርብ ስጋ ተሸፍነው ተከድነው
እንደድሮው ባይታዪም ከሩቅ ገነው
ብቻ ግን ባዬኋቼው ዳግመኛ የኔ ሆነው
መቼም እኔ ጭቀቴ ሀሳቤ ብዙ
ያባክነኛል ያንቺ ፍቅር መዘዙ
ማዕበል ፍቅርሽ ከልቤ ላይ ቋያ ፈጥሮ
ህዋሳቴን ያናውጣል እስትፋሴን ተቆጣጥሮ
ውብ ቀለምሽ ጣፋጭ ማዛሽ ጎልቶ ነጥሮ
ዳንኩኝ ስል ይገለኛል ይጥለኛል አሽቀጥሮ
@gGetem
@gGetem
@gGetem
ይኧው ከመቅፅበት
ሁለት ሚስኪን ጥንዶች
ጊዜ ያጣመራቸው
ጨዋታ ቀልዳቀልድ
ቃል ያገናኛቸው
ለመታመን ብለው
ለነገ ፍቅራቸው
መፅሀፍ ቅዱስ ይዘው
ሲምሉ ባያቸው
ካንተ ውጭ ካንች ውጭ
ብለው ቃል ሲገቡ
ሲማማሉ አይቼ
ሁኔታቸው ገርሞኝ
መብላት አምሮኝ
ነበር ፍርፍር ወጥ ሰርቼ
ፈጣሪ ከዙፋን
ሰማይና ምድርን
በቃሉ ቢያፀናም
በቃላት እስትንፋስ
ጎባጣ ቢያቀናም
በፍጡር ህግ ግን
ቃል ፍቅር አይሰራም
ሌላ ሄዋን ሲመኝ ሲሆን አመንዝራ
ፍቅሩን ችላ ብሎ መሀላ ከፈራ
ሌላ ገላ ሲሻ ቃሉ ከመለሰው
ቃል አክባሪ ሳይሆን
ፈሪ ነው ይኧ ሰው
እናም የአዳም ዘር ሆይ
ከፍጥረት ተመራጭ
ሄዋን ውዷ እህቴ
የአዳም አጥንት ፍላጭ
የፍቅ'ር ልኬቱን ከጌታ ተማሩ
ሰሙን ብቻ ሳይሆን
ቅኔም አመስጥሩ
ልክ እንደ ክርስቶስ
ፍቅርን በፍቅር እንጅ
በቃል አትጀምሩ
@gGetem
@gGetem
ሁለት ሚስኪን ጥንዶች
ጊዜ ያጣመራቸው
ጨዋታ ቀልዳቀልድ
ቃል ያገናኛቸው
ለመታመን ብለው
ለነገ ፍቅራቸው
መፅሀፍ ቅዱስ ይዘው
ሲምሉ ባያቸው
ካንተ ውጭ ካንች ውጭ
ብለው ቃል ሲገቡ
ሲማማሉ አይቼ
ሁኔታቸው ገርሞኝ
መብላት አምሮኝ
ነበር ፍርፍር ወጥ ሰርቼ
ፈጣሪ ከዙፋን
ሰማይና ምድርን
በቃሉ ቢያፀናም
በቃላት እስትንፋስ
ጎባጣ ቢያቀናም
በፍጡር ህግ ግን
ቃል ፍቅር አይሰራም
ሌላ ሄዋን ሲመኝ ሲሆን አመንዝራ
ፍቅሩን ችላ ብሎ መሀላ ከፈራ
ሌላ ገላ ሲሻ ቃሉ ከመለሰው
ቃል አክባሪ ሳይሆን
ፈሪ ነው ይኧ ሰው
እናም የአዳም ዘር ሆይ
ከፍጥረት ተመራጭ
ሄዋን ውዷ እህቴ
የአዳም አጥንት ፍላጭ
የፍቅ'ር ልኬቱን ከጌታ ተማሩ
ሰሙን ብቻ ሳይሆን
ቅኔም አመስጥሩ
ልክ እንደ ክርስቶስ
ፍቅርን በፍቅር እንጅ
በቃል አትጀምሩ
@gGetem
@gGetem
👍1
። ። ካለሽ አለሁ።።
አንቺ ጎኔ ካለሽ ፀሀዪ ይደምቃል፣
ፍቅርሽ ገደብ የለዉ ከፍቅርም ይልቃል።
አንቺ ጎኔ ካለሽ ጨረቃ ታንሳለች፣
ዉበቷ ያንስና ታቀረቅራለች።
አንቺ ጎኔ ካለሽ ሳቄ ይመነጫል፣
ምንም ሆነ ምንም ጥርስን ያስከፍታል።
ገነትን ሳላየዉ ገነቴ ነሽ ብልም፣
ገነት እንደሚያምር አልጠራጠርም።
የሚያስጠላዉ ነገር
አንቺ ጎኔ ካልኖርሽ ፀሀይ ትጠፋለች፣
ማማሯ ያልቅና ወዲያው ትረግፋለች።
አንቺ ጎኔ ካልኖርሽ የለችም ጨረቃ፣
አንቺን ለመፈለግ ገብታለች መሰለኝ ባሕር ዉስጥ ጠልቃ፣
ሄዳለች ርቃ።
ገነት እንደሚያምር ባልጠራጠርም፣
አንቺ ሲኦል ካለሽ መምጣቴ አይቀርም።
ስለዚህ ፍቅርዬ
የትም ብትገቢ እንጦሮጦስ ገደል፣
ተዘጋጅቻለሁ መከራን ልቀበል።
ምንም ብትሆኚ ሁሌ አፈቅርሻለዉ፣
ገሀነብም ግቢ እኔ ካለሽ አለሁ።
ማትስ ትምህርት እየተማርኩ xን ስፈልግ የተፃፈ ግጥም
@gGetem
@gGetem
@gGetem
አንቺ ጎኔ ካለሽ ፀሀዪ ይደምቃል፣
ፍቅርሽ ገደብ የለዉ ከፍቅርም ይልቃል።
አንቺ ጎኔ ካለሽ ጨረቃ ታንሳለች፣
ዉበቷ ያንስና ታቀረቅራለች።
አንቺ ጎኔ ካለሽ ሳቄ ይመነጫል፣
ምንም ሆነ ምንም ጥርስን ያስከፍታል።
ገነትን ሳላየዉ ገነቴ ነሽ ብልም፣
ገነት እንደሚያምር አልጠራጠርም።
የሚያስጠላዉ ነገር
አንቺ ጎኔ ካልኖርሽ ፀሀይ ትጠፋለች፣
ማማሯ ያልቅና ወዲያው ትረግፋለች።
አንቺ ጎኔ ካልኖርሽ የለችም ጨረቃ፣
አንቺን ለመፈለግ ገብታለች መሰለኝ ባሕር ዉስጥ ጠልቃ፣
ሄዳለች ርቃ።
ገነት እንደሚያምር ባልጠራጠርም፣
አንቺ ሲኦል ካለሽ መምጣቴ አይቀርም።
ስለዚህ ፍቅርዬ
የትም ብትገቢ እንጦሮጦስ ገደል፣
ተዘጋጅቻለሁ መከራን ልቀበል።
ምንም ብትሆኚ ሁሌ አፈቅርሻለዉ፣
ገሀነብም ግቢ እኔ ካለሽ አለሁ።
ማትስ ትምህርት እየተማርኩ xን ስፈልግ የተፃፈ ግጥም
@gGetem
@gGetem
@gGetem
የቢሆን ዓለም ክፍል 11
@gGetem
⎈ የቢሆን ዓለም ❉⎈
✅ #ክፍል_11
✰ ደራሲ - ደጉ ቁምቢ
✰ ተራኪ - ተስፋሁን ገ/ዩሐንስ
✅✅ ሁላችሁንም ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ የፍቅርና ሳይንሳዊ ነክ ልቦለድ።
※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════ @yosikeman
✅ #ክፍል_11
✰ ደራሲ - ደጉ ቁምቢ
✰ ተራኪ - ተስፋሁን ገ/ዩሐንስ
✅✅ ሁላችሁንም ልታዳምጡት የሚገባ ምርጥ የፍቅርና ሳይንሳዊ ነክ ልቦለድ።
※※※※※ ሼር ያድርጉ!! ※※※※※
አዘጋጅ፦ண @gGetem
ண @gGetem
═══════ ♢.✰.♢ ══════ @yosikeman