Telegram Web
..የከተማው...መናኝ💂
ገጣሚ እና አንባቢ፦ሊዮ ማክ©
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ

-ከአዲስ አቀራረብ ጋር🙆

>>በየቀኑ አዳዲስ ግጥም ይደርሳቹ ዘንድ ቤተሰብ ይሁኑ!!
@gGetem
@gGetem
>>Comment  @sirak6
💆💃🙇
1👍1🤔1
ለአንድ ግጥም አስር ብር...
ገጣሚ፦ ሚካኤል አስጨናቂ
አንባቢ፦ ሊዮ ማክ
የሆሄያት ህብር
#የጥበብ_ማዕድ
😍በየቀኑ አዳዲስ የግጥም ስራዎችን ለማግኘት ቤተሰብ ይሁኑ!!!
@gGetem
Comment_
@sirak6
#እንደ ህያዋን_
1💯1
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
💆‍♀💆‍♂ቀን የጨለመበት💆‍♀💆‍♂
#ረቢና
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
@gGetem
@gGetem
👍1🥰1
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
😱😱😱 የኗሪ አኗኗሪ🙈🙈🙈
#ላምሪ
የሆሄያት ህብር 🦋🦋🦋🦋
@gGetem
@gGetem
@gGetem
😁1🤔1
ምሽት በረንዳ ላይ
(በእውቀቱ ስዩም)

አገር ምድሩ መሽቶ
ሌቱ ምጣድ ሆኖ ፥ በኮከብ ተሟሽቶ 
የጎዳናው መብራት ፥ጨለማው ላይ ሲገን 
ከመስኮት አምልጦ ፥የወጣ ወጋንን
ሳር ቅጠሉን ሲያሳይ
አጥብቄ ስፈልግ ፥የእለት ያይኔን ሲሳይ
የሌት አይኔን ሲሳይ

በኩርማን ገላዋ፤ እራፊ ደርባ
የራሷ ሻጭ ሆና ፤ለሸመታ ቀርባ   
በሌት ይፋ ሆና፥ በቀን ልትደበቅ
ያልቀጠረችውን ፥የምትጠባበቅ
አንዲት ሴት እያየሁ
አሰላስላለሁ ፤

“ አብረዋት ያደጉ፤ ብጤዎቿ ሁሉ
በድሜና በውበት እሷን የሚያክሉ
ተድረው እንደ ሴት፥ ተከብረው እንደ ሰው
የባሎቻቸውን ደረት ተንተርሰው
ፍቅር ሲያጣጥሙ
ወይ በንቅልፍ ሲሰጥሙ
ይች ወገን አልባ
የሌሊት አበባ
በቀትር ተኝታ ለውድቅት የነቃች
የቱን ፍሬ በልታ ለዚህ ፍዳ በቃች ?”

እያልሁ አስባለሁ፥ 



ደሞ ከደጃፌ ትንሽ ማዶ ርቆ
የመሸበት ለማኝ ፤ መንገዱ ዳር ወድቆ

በግልጥ  ይታየኛል
“ ረፍትን ላክልኝ ፥ወይ እንጎቻህን ጣል
በራብ እና በንቅልፍ ሰው እንዴት ይቀጣል"
የሚል ይመስለኛል  ፤

በረንዳ ላይ ቆሜ፥ በሌሊት  ስምሪት
ከመስኮት በወጣ፥ የብርሀን ቅሪት
አይቼ ማልዘልቀው
ያገሬ ጎዳና የት ላይ ነው የሚያልቀው
መከራና ውበት የሚያፈራርቀው::

@gGetem
@gGetem
@sirak6
👍1🥰1
(ምን መሰለሽ? )

ሌላን ሴት ጠይቀው
‘እሺ’ የተባሉ …
በርግጥ ለአንድ ቀን
ፈክተው ይስቃሉ።

ሆኖም የገረመን

አንቺን ተለማምጠው
‘እንቢ’ ብለሽ እንኳን
ድግስ ደግሰዋል..
ዳስ ጥለዋል ድንኳን።

‘እርሷን ሞክሪያለሁ’
ብሎ ማውራት ለካ
አስከብሮ ያኖራል
እንደ ሰፈር ዋርካ !

@gGetem
(ሚካኤል አ)
@leoyri
❤‍🔥1🤣1
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#በአንቀልባ_ያዘለው
────────────

"ረገጥኩት!" ይላል ፥ ሰይጣንን በእግሬ
"ጨፈለኩት!" ይላል ፥ ያንን ክፉ አውሬ
መሬት እየደቃ ፥ ዘራፍ ይላል ጃሎ
"እዩት ጣልኩት!" ይላል ፥ የሞተውን ገ'ሎ
ጄነራሉን ሰይጣን ፥ በጀርባው ላይ አዝሎ ።


​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
✍🏽© ሰሎሞን ሞገስ
╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈


ምንጭ ➸ ብዕር ያለው ያውጋ

ለመቀላቀል 👉🏽 @gGetem
አስተያየት 👉🏽 @Leoyri
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨፨ #ዛሬን_ያነበበ ፨፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨ #ነገን_ይማራል❗️፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
1
"ተስፋ ማለት በተሸነቆረው የመኖር ግንብ ውሰጥ አጮልቆ ረቂቅ የህይወት ጨረሮችን እንደማየት ነው።

ተስፋ ከጨለማው ይልቅ የኮከቦችን ድምቀት እያየን ዛሬን ሽምጥ ወደፊት በህሊናችን ዳስ አስፈንጥረን በነገ ውሰጥ መቃኘት እንዲቻለን የሚያደርግ የህይወት ቁልፍ ሚስጥር ነው። "

ህሊና በላይነሽ
@gGetem
@leoyri

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗


╚═══❖•🌺🌸
❖═══╝
4 any comment

❥❥________⚘_______❥❥
👏1
▨▨▨▨▨▨▨▨▨▨▨



#እንስተ_ፀሎት
#ገጣሚ_ሊዮ_ማክ ©
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
www.tgoop.com/leoyri
www.tgoop.com/gGetem
Mole Enter_🍁
Plc share&Join
🎤🎬 #ሳሮን_ተክለ_ወልድ©
ተፃፈ፦04-09-2015ዓ.ም
የሳምንቱ_ ለ
▦▦▦▦▦▦▦▦▦▦▥▦▦▦
በትዕግስት ለጠበቃችሁን ከልብ እናመሰግናለን ።❤️🙏
1🤗1
🇪🇹እሮብ ሚያዝያ ፳፰ ፳፻፲፪ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#ሰው_ብቻ
───────
አሁንማ ጀንበር ገባች
አይናችን ስር ተስፋ ሞተ
የመጀገን ቀን አበቃ
የስንፋናህ ዘመን ባተ
አልልህም ምን ብደክም
ርቃን እውነት አስገርፎኝ
በበደልህ ብታሸንፍ
ሀቄ በቁም ህይወት ገፎኝ
መኖርና መሞት መሀል
ያለን ጣዕም አስክረሳ
ባሳልፍም ብዙ ዘመን
እርጥብ ቁስል እልፍ አበሳ

ሙት አለሜ ደስ ብሎኛል!
ዋንዛ ልብህ እንደሙጃ
ሲልፈሰፈስ ተሸንፎ
ጥቅጥቅ ነፍስ ሲገላለጥ
ወና ሲሆን እንደቀፎ
ኧረ አሜን ነው
አሜን አሜን
ደግሞ አሜን አሜን ብዙ
"ይቅርታ" ሲል ይገለጣል
ትሁት ሲሆን የሰው ወዙ
ኧረ አሜን ነው የምን እንቢ
ቀን ጣለልኝ ብሎ ጉራ
ሰው መሆኑ ከስጋ ያልፋል
ለወደቀ ሰው ሲራራ

ልመናዬ እዬ ዬ ዬ
አልነበረም ከንፈሮቼ
ከንፈርህን እንዲስሙ
አልነበረም ወይም ጥዬህ
ድል ማድረጌን እንዲሰሙ
ባንተ አዝኜ እንዳይጠፋኝ
ነበር ያልኩት የሰው መልኩ
ተመስገን ዛሬ አሳየህ
አላነሰም አልወረደም
ከሰውነት የሰው ልኩ ።

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
✍🏽© ቤተልሔም ታችበል
╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈


ምንጭ ➸ የሚካኤል አስጨናቂ ግጥሞች

ለመቀላቀል 👉🏽 @gGetem
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨፨ #ዛሬን_ያነበበ ፨፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨ #ነገን_ይማራል❗️፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
1😁1
የባከነ ሌሊት!!!!
(በእውቀቱ ስዩም)
ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቁሜ
ቤተክስያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ::
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ሥር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ : በደምና አቧራ
"በኡራኤል ርዱኝ " ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ሥር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ :ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ
ወይ ምግባር አልሠራሁ
ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ : ወይ ፅድቅ አላፈራሁ::
አንድ በትረ-ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሲባክን ዝምብሎ
" እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ"
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋየን ሳትሰብረው::
ወግ ቢጤ ሞንጭሬ: ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ
" እናትዋን ጨረቃ" የሚል ግጥም ሳልጥፍ::
አንዲት ሴት- አዳሪ :ቺቺንያ ምንገድ ላይ
እድሉዋ ሰባራ :ሰውነቱዋ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ : ተጋግዞ ሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠበቅ :ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች : ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
" እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን
እህት የላችሁም?" ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው : በደሏ አንገብግቦኝ
ከሁዋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ: ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ: እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ::
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳለረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለምንም ጣጣ : ያለምንም ፀጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ::

By bewuketu seyoum

@gGetem
@gGetem
@leoyri
2
🇪🇹ሐሙስ ሚያዝያ ፳፱ ፳፻፲፪ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
#እሾህን_በሾህ
─────────

ወለም ካለው ልብሽ ፥ ድንገት ከዘመመ
በፍቅር ተወግቶ ፥ ፀንቶ ከታመመ
አይገኝ ወጌሻ ፥ ለልብ ስብራት
አሽቶ የሚመልስ ፥ ከቀደመው ድነት

እናምልሽ ውዴ ፥ እሱ ነው ሚሻለው
ደግመሽ አፍቅሪበት ፥ እሾህን በሾህ ነው ፡፡

​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
✍🏽© የኔታ ፍቄ
╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈


ምንጭ ➸ ግጥም እወዳለሁ
@gGetem
@leoyri
🥰1😁1
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
ጥሩ ወግ🧤🧤🧤🧤🧣🧣🧣🧣
ሰባኪው🙏😔
🧣ተራኪ፦ሊዮ ማክ @Leoyri
@gGetem
🤔1😱1
#"የምፃተኛው_ኑዛዜ"
(በእውቀቱ ስዩም)

ካ’ገር ጫፍ እስከጫፍ በጥላህ ከልለህ
ተራራው የኔ ነው ለምን ትለኛለህ?
ወንዙ ድርሻዬ ነው ለምን ትለኛለህ?
እንኳንስ መሬቱ አንተም ያ’ንተ አይደለህ።
እኔ መጻተኛ አንተ ኗሪ ነኝ ባይ
እኔ እግሬን ስከተል ርስትህን ስታይ
ስቀርብህ ገፋኸኝ ስትገፋኝ ቦታ አጣሁ
ድንኳን ብትተክል፣ ነፋስ ሆኜ መጣሁ።
ያ’ባትህ ያ’ባቴ
ጠበኛ ስማቸው
ጠበኛ ሕልማቸው
በሕይወት ተጣሉ፣ ታረቁ ባፅማቸው
ባፈር ተቃቃሩ፣ አፈር አስማማቸው
በዙሪያቸው በቅሎ ከቧቸው ሞት ደኑ
መተቃቃፍ መርጠው ማማና ወይን ሆኑ።
ይችላል ይሉሃል ፍልሚያ ማዘጋጀት
ያ’ባት አጥንት ወስዶ ስሎ ጦር ማበጀት
አንተው ጦር ወርውረህ አንተው ቀድመህ ወድቀኽ
አካሌ ደረቴ መኾንኽን መች አወቅኽ ??? !!!

@gGetem
@gGetem
@gGetem
@leoyri
1👏1
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
👫ግጣም አልባው ገጣሚ📖📚
☔️ #ገጣሚ_ሊዮ_ማክ
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@leoyri
@leoyri
@gGetem
@gGetem
@gGetem
👁💚💛❤️
#ተፃፈ_12_06_2012_ዓ_ም
💯 quality 😍🥰
Plc share
1🥰1
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
1👍1
ለአንድ ጀግና
(በእውቀቱ ስዩም)
🤥

የጠብህን ጠበል፤ ለሁሉ አታዳርሰው
ክንድህን አትዘዝ
ሠይፍህን አትምዘዝ
ሞቶ ለመጣ ሰው፤
የድመቶች ክብር
በሞታቸው ሰዓት
በነብር ወጥመድ ውስጥ
ተንደርድሮ መግባት፤
ለሐሳዊ ነብር፤ ክንድህን አትነቅንቅ
በወጉ አያከብርም፤ በወጉ የማይንቅ

(ከስብስብ ግጥሞች)

@gGetem
@leoyri
1🥰1🤔1
እየሔዱ መጠበቅ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
‹‹እየሄድክ ጠብቀኝ›› - ስትይኝ ሄጃለሁ፤
መንገዴ እንዳይጠፋሽ….
በየደረስሁበት፤
ድንቅ ምልክትን - አኖርልሻለሁ፤
አንቺ ላትደርሺብኝ..
እኔ ግን እየሄድሁ - እጠብቅሻለሁ፡፡
*
*
እናምልሽ ውዴ…
አክሱምን እንዳየሽ፤
ታምር እና ታሪክ - ፈፅሞ እንዳይመስልሽ፤
ጠራቢው እኔ ነኝ!
ያለፍኩት በዚያ ነው - ምልክት ይሁንሽ፡፡
አጋጥሞሽ እንደሆን…
ካንድ ውቅር ድንጋይ፤
ሰማይ ጠቀስ ሐውልት - የተፈለፈለ፡
ታምር የሚመስል - ታሪክም ያይደለ፤
አክሱም ሐውልት ላይ…
አንቺን የሚጠብቅ - የኔ ጥበብ አለ!!
ቃልሽን አክብሪ - ቃሌን አከብራለሁ፤
መንገዴ እንዳይጠፋሽ..
በየደረስሁበት፤
ድንቅ ምልክትን - አኖርልሻለሁ፤
አንቺ ላትደርሺብኝ..
እኔ ግን እየሄድሁ - እጠብቅሻለሁ፡፡
*
*
እናምልሽ ውዴ - ላሊበላን አይተሸ፤
ታምር እና ታሪክ - ፈፅሞ እንዳይመስልሽ፤
ፈልፋዩ እኔ ነኝ፤…
ያለፍሁት በዚያ ነው - ምልክት ይሁንሽ፡፡
አጋጥሞሽ እንደሆን…
ካንድ ውቅር ድንጋይ፤
ህንፃ ቤተ-መቅደስ ፤ የተፈለፈለ፡፡
ታምር የሚመስል - ታሪክም ያይደለ፤
በላሊበላ ውስጥ…
አንቺን የሚጠብቅ - የኔ ፅናት አለ፡፡
ቃልሽን አክብሪ - ቃሌን አከብራለሁ፤
መንገዴ እንዳይጠፋሽ..
በየደረስሁበት፤
ድንቅ ምልክትን - አኖርልሻለሁ፤
አንቺ ላትደርሺብኝ..
እኔ ግን እየሄድሁ - እጠብቅሻለሁ፡፡
*
*
እናምልሽ ውዴ - ትክል ድንጋይ አይተሸ፤
ታምር እና ታሪክ - ፈፅሞ እንዳይመስልሽ፤
የኔው መቃብር ነው!
ውድቀቴም እዛው ነው! ምልክት ይሁንሽ፡፡
አጋጥሞሽ እንደሆን…
ባባራ ዘመኑ፤
የራሱን መቃብር - ለመትከል የቻለ፤
መኖር የሚመስል - መሞትም ያይደለ፤
በጢያ ድንጋይ ላይ…
አንቺን የሚጠብቅ - የኔ ውድቀት አለ፡፡
ከውድቀቴ ኃላ - ባይንሽ የምታዪው፤
ታምር የሚመስል - ታሪክ የምትይው፤
ምልክት የሚሆን - መንገድ ስላልተውኩኝ፤
ከመሞቴ በፊት..
ውድቀቴን፤
ሽንፈቴን፤
ከመቃብሬ ላይ - እንዲህ ብዬ ፃፍሁኝ፡፡
ሩጫዬን ጨረስኩ፤
ሰው ነኝ - ተሸነፍኩ!!!
እናምልሽ ውዴ….
‹‹እየሔድህ ጠብቀኝ›› - ያልሽው ቃል ስህተት
ነው፤
ቃሉም ገብቶሽ እንደው…
መራመድ መሄድ ነው፤
መሮጥም መሄድ ነው፤
መብረርም መሄድ ነው፤
አንቺ እንድትደርሺብኝ …
እኔ እየሞትሁ - እጠብቅሻለው!!!
**********
@leoyri
@gGetem
💯1🏆1
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
የለዛ ሞት🧖‍♂🧖‍♀🤦‍♀🤦‍♀
ገጣሚ፦ሊዮ ማክ @Leoyri
የሆሄያት ህብር🌫🌫
@gGetem
@gGetem
@gGetem
🕊1👀1
ብልጭታ
እንደኖረ ሞተ ቢሆን የሰው ሚዛን
ከ'ዚ እርከን ለማለፋ ስንት አንደበት ደቃን።
የስኬትን ቅኔ በእድሜ ልክ ውዥንብር
ፍቺ ባይኖረውም ያለ ልክ መታተር
እርምጃዬ ሁሉ በእሾህ ቢገታ
የመንገዴ ብርሃን አይሆንም ብልጭታ።
.
.
.
.
ብቻ
.
.
.
ሚመሸው ቀን ከቀን ነውና ለመንጋት
የችግሬን ቋጥኝ አልቆጥርም እንደቅጣት።
ሊዮ ማክ
🚫ሰው ባስፈለገኝ ጊዜ ከጎኔ በተለያየ ሁኔታ እና አጋጣሚ ከጎኔ ለነበራቹ እና አሁንምም ላላቹ በሙሉ ከልቤአመሰግናለሁ!።
👏👏👏👏👏👏👏
🙏🙏🙏🙏🙏
www.tgoop.com/gGetem
www.tgoop.com/leoyri
1🥰1
2025/07/13 02:36:59
Back to Top
HTML Embed Code: