Telegram Web
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo Leጅ)
🌺🌺🌺🎂🌺🌺🌺
ካነበብኩት ......
#የአና_ማስታወሻ
#ገፅ(page)-100
የሆሄያት ህብር 🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@gGetem
@leoyri
እንኳን ለየሆሄያት ህብር 4ኛ አመት የምስረታ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
📚📚📚📚📚
🎂🎂🎂🎂🎂
🇪🇹የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━


ጥቁር ቀንዲል ፥ የሌት ንጋት
አምሳለ ወንድ ፥ ምግባረ እናት ።

​​               ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
       ✍🏽©           ራስ አብ
    ╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈ 
ለእምዬ ምኒልክ የተገጠመ


ምንጭ ➸ የግጥም አብዮት
ለመቀላቀል 👉🏽 @gGetem
አስተያየት 👉🏽 @leoyri
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─
" የለም " ማለት " አለ " ፪

( አማኑኤል አለሙ ኑርጋ ) አሙ

ባዶ ማለት ዜሮ
ዜሮ ማለት ምንም
በሆነበት አለም ..
ኪስህ ባዶ ቢሆን
" ምንም አልያዝኩኝም "
ለምን ትለኛለህ ...
በኦና ኪስህ ውስጥ ምንም'ማ አለህ!

..........
................

ካወቅከው በኀላ
ምንም ምንም የሚል
'ጣሙን በምላስህ
" ውሃ 'ጣም አልባ ነው "
ለምን ትለኛለህ ...

..........
...............

ካበቃህ በኀላ
ቢራውን ጨልጠህ
ውስጡ አየር እንዳለ
በዓይንህ እያየህ
" ጠርሙሱ ባዶ ነው "
ለምን ትለኛለህ ...

..........
...............

ስላጣኸው ብቻ
አትበል " የታለ "
የለም ያልነው ነገር
ባለመኖር አለ ።
የሆሄያት ህብር
🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@gGetem
@gGetem
@gGetem
ከነጋሪት በጆሮ የተወሰደ

የክረምቱ ወራት አልቆ ፀሓይዋ ብቅ ስትል ሁላችንም በቤታችን የተጣለ ዳንቴል ተልትለን ኳስ እንሰራ ነበር። እኔም ለኳስ ልዩ ፍቅር የነበረኝ። በርግጥ
እኔም ብቻሳልሆን ጓደኞቼም ኳስ ለመጫወት ሳዓታችንን ጠብቀን ነበር የምንሰባሰበው፡፡ ድንገት ከመካከላችን አንደኛዉ
ስራ ታዞ እንኳን ቢሆን ተጋግዘን ሰርተን ወደ ጨዋታችን እንሄድነበር።
11ሰዓት ለኛየአለም ዋንጫ የፍፃሜ ጫወታ የሚካሄድ ነበር የሚመስለው ሁሉም ከያከበባቢው እየተሯሯጡ ተማሪው
ከትምህርቱ እረኛውም ቢሆን ከስምሪቱ የምንሰባሰበው፡፡እርስበ እርስ ያለን ፍቅር የሚያስቀና ነበር።አንዴ ትዝ ይለኛል
እጅግ መሽቶ እንኳን እርስ በአርስ መተያየት እሰከማንችል ድረስ እየተጫወትን የትምህርት ቤቱ ዘበኛ የነበሩት ጋሽ አሌ
አረ መሽቷል በቃቹ ግቡ ነገ ትጫወታላቹ ብለው አልሄድ ስንል ኳሳችንን ሲነጥቁን ወደ ድበብቆሽ ጫወታ ዞርን ብቻ የዛን
ለት ለመደበቅ በሄዱበት በዛው ወደ ቤቱ የሄደም አይጠፋም እርግጠኛ አይደለሁም ግን ብቻ ፍቅራችን ለነገ የሚባል
አልነበረም።
ዛሬ ተጣልተን እንኳን ነገ ፍቅራች ያዉ ነበር። ባቱ ትምህርት ቤት ከተባለ የማያቀን አልነበረም አንድ ሰሞን መረብ ኳስ
መጫወት ፈልገን አጫጭርና ህፃናት ስለሆንን የሚጫውተን አልነበረም እንጫወትስ ብንል የት እንጫወታለን መረብ ኳስ
ያለው ወይ ትምህርት ቤት አልያም ኳስ ሜዳ ነበር ያለዉ እዛ መሄድ ይኖርብናል እዛ ብዙ ሰዉ የሚሰባሰብበት በመሆኑ
ያደግሞ ለአኛ ነፃነት የለውም ። ታዲያ መረቡን በእጃችኝ ሰርተን በአመድ መስመር አስምረን ቁምጣ አዘጋጅተን እንጫወት ነበር። ታላላቆቻችን ራሳቸው ይቀኑብን ነበር ዙሪያችንን ከበው የኛን ጨዋታ ያያሉ።ሲላቸው አስገቡን ይሉና።
ማን ይሆን የዚህ አይነት ትዝታ ያለው?
ህይወት የትናንት የዛሬ የነገ ጥምር ውጤት ማሳያ መነፅር ናት።
በትናንት ውስጥ የሁሉ ነገር መሰረት የታላቅነት ውጥን የአልበገሬነት ልጅነት ሰንሰለት ናት በልጅነት ውስጥ ንፁው
ፍቅር ቂም የሌለበት ነፃ አለም በምንም ያልተበረዘች ሲሆን በዛሬ ውስጥ ደግሞ ታሪክ መስራት ጥንካሬን ውሳኔን በራስ
የማድረግ ከህሎትን ከስህተት መማርን መውደቅ መነሳትን የትልቅ ራዕይ አላማ ውጥን ማስቀመጥን የበረከት ፍሬን መዝራትን ወደ ነገ የሚያሻግረንን ድልድይ የምንገነባበት የታላቅነትን መንገድ በቁርጠኝነት የመጀመሪያዋን እርምጃ የምንራመድበት ጎዳና ናት።ሁሉም ሰው የራሱ የህይወት መዝገብ አለው ነገውን የሚፅፍበት ነገ ዉስጥ ተስፋን
ጥንካሬን ቁርጠኝነትን ትዕግስትን እና የመሳሰሉት ጥምር ውጤት ያለዉ በነገ ዉስጥ ነዉ።

በጆሲ( 𝓷𝓮𝓰𝓪𝓻𝓲𝓽)የተዘጋጀ
@gGetem
@gGetem
@yosikeman
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Y€ŕi ወንጌላዊት)
My Song 2.ogg
9 MB
🧟‍♂ ዘመም ይላል እንጂ🧟‍♀
#ገጣሚ_በእውቀቱ_ስዩም
አንባቢ፦ሊዮ_ማክ ©☔️
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
💚💛❤️
@Leoyri
@gGetem
@gGetem
@gGetem
🇪🇹እሮብ               ግንቦት ፭ ፳፻፲፪ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━


እናት ብትወደስ ፥ እውነት ነው ያንሳታል
ቃላቶች ቢነጥፉም ፥ መቼ ይገልጿታል
ግን ለምን ተረሳ ፥ የእናትነት ምንጩ
አባት አይደለም ወይ ፥ የጽንሶች አማጩ
ሄዋንን ቀዳሚ ፥ እሱ አዳም ነውና
ለአባትም እንደ እናት ፥ አቅርቡ ምስጋና ።
        
​​               ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
       ✍🏽©       ሰላማዊት ተሾመ
    ╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈

       
ምንጭ ➸  የግጥም አብዮት

ለመቀላቀል 👉🏽 @gGetem
አስተያየት 👉🏽  @Leoyri
በምንም እና ለምንም ነገር አንተ የመጀመሪያው ሰው አደለክም እና አትገረም...አትዘን...አትኮፈስም❗️❗️❗️
ምክንያቱም ...
#በስኬት ጊዜ ልትቋቋመው በሚሳንህ ደስታ አትዋጥ።
#በውድቀትህም ጊዜ ለመነሳት በሚያዳግት የስሜት መሰባበር ውስጥ #እራስህን አትጣል❗️❗️
ምክንያት፦ካንተ በፊት ብዙዎች የስኬት ጥግ አይተዋል። #እንዲሁም ካንተም በፊት ካንተ በባሰ #ውድቀት እና ስቃይ ውስጥ  በማይታመን መልኩ ገብተው እራሳቸው ስላገኙት ነው!!!!
ስለዚህ #አንተ የመጀመሪያው አይለህም❗️❗️❗️❗️
#ሊዮሪ
@gGetem
@leoyri
@leoyri
አመልካች👉
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo Leጅ)
ጭምት_ሴት
ከዝምታሽ ድባብ ከቃላትሽ ህብር
በጭንቅ ተውጣ በኑሮ ውዥንብር፤
ብዙ ጩኸት አለ
ብዙ ህመም አለ
ለተመልካች ወርዶ ለሷ ያልቀለለ።
ከዝምታሽ ጀርባ፤
ብዙ ጩኸት አለ!!!
ሊዮሪ
📷ማማ 04/09/2013ዓ.ም
08:35am
@leoyri
@gGetem
@gGetem
#የሔርሞን_ማስታወሻ






      እናማ በማስታወሻዬን ክታብ ልቋጥርልሽ ስለወደድኩት ስለ ዘረ-አዳም ስደት ካቆምኩበት ልቀጥልልሽማ.....
     እና በባለፈው ማስታወሻዬ ለመቀጠል አስቤ ካልቋጨሁት ሀሳብ ስቀጥልልሽ....
እንደ እድል ሆኖ በጋብቻም ተሳስረው ጥጋጥግ ቆመው ያላፊ አግዳሚውን ዘር ከሚቀጥፋ እኛ ሰው መሳይ አውሬዎች በዕድሉ እና በአምላኩ ቸርነት እንደ አጋጣሚ ተላልፎ በማህፀን የሚያደርገው ቆይታ ብዙ ንትርክ፣ድብደባ እና እንባ ከውስጥ  ሆኖ ካሳለፈ በኃላ ይቺን አለም በለመደው ለቅሶ ይቀላቀላታል።
        እታለሜ!ምንአልባት ሀብታሙም ደሀውም እያለቀሰ አይደለ ወይ የሚወለደው የእርሱ በምን ይለያል? የሚል ጥያቄ አዘል ሀሳብ ይሄኔ በአዕምሮሽ ብልጭ ሳይል እንዳልቀረ አውቃለው። ግን ልክ ነሽ ሁሉም ይቺን አለም በለቅሶ ነው የሚቀላቀለው አየሽ ግን ልዩነቱ ይህ ህፃን እርሱ ወደዚች ምድር የመምጫው ቀን ከተበሰረበት ጀምሮ እናቱ እርሱን በመፀነሷ ብዙ እንባ እና ብዙ ስቃይ ስታሳልፍ በእናቱ ህዋሳት በኩል አንዷም ሳትቀር ልቅም ብላ ስለምትደርሰው ነው እንዲያ ልልሽ የቻልኩት።
           እና የዚህ ህፃን ጉዞ ከዚያች ምሽት አንስቶ በእንዲህ አይነት ሁናቴ ስለተጀመረ ተወልዶ የሁለት የሶስት ቀን ከበዛም የሳምንታት እድሜን ከቆየ በኃላ እጅግ በሰው ህሊና ቀርቶ በፍጥረት ሁሉ አዕምሮ ሊታሰብ የማይችል ግፍ እኛን መሰል የሰው ልጆች ይህን መሰል ግፍ በየስፍራው ይፈፅማሉ።


🛖ሔርሞን ነኝ የዳር ሀገሯ
  🌃በስደት ላለሽው እታለሜ
#ፀሐፊ_ሊዮ_ማክ
(ይቀጥላል)
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
ለሒስ፦   @sirak6
ለቤተሰባዊነት፦  www.tgoop.com/gGetem
የትዝታው ካሴት
ው...ዪ አርፍጃለሁ ማለት ነው? በመንገዱ ተማሪም ሆነ ሰራተኛ አይታይም:- ሰሚ በሌለበት እኔው እራሴን ጠይቃለሁ። እጄን ተጠቅሜ ከሱሪ የቀኝ ኪስ ስልኬን አወጣሁ። በመቀጠልም ሰዓት ለመመልከት ቁልፉን ስጫን ዘግቷል።እሺ አሁን ስንት ሰዓት እንደሆነ እንኳን በምን ልወቅ? ሩጫ ቀረሽ በሆነ አረማመድ መንገዱን አሳለጥኩት። አእላፍ እርምጃወች ተራምጄ ትንፋሽ ለመሰብሰብ እንዲሁም ከጀርባዬ ያለውን ሞተር ለማሳለፍ አረማመዴን ረገብ አደረኩ።
     ሞተረኛው በከፍተኛ ፍጥነት ቢያልፈኝም በሞተሯ ላይ የተገጠመው የድምፅ ማጉያ የሚያጫውተው ሙዚቃ ከጆሮ ቀረ። ድምፁን ተከትሎ አዕምሮዬ በትዝታ መንገድ ወደ አንድ ቦታ ወሰደኝ። ቦታው ያለፉትን እያንዳንዱን የህይወት ክፍሎች የሚመዘግብና የሚያከማች ሲሆን። በአንድ ረጅም መደርደሪያ ላይ በረድፍ የተሰደሩ ካሴቶችን አሉ እያንዳንዳቸው ስም አላቸው። ከካሴቶቹ መካከል አንደኛው ትኩረቴን ሳበው የተሰማ ግን የማይረሳ የሚል ፅሑፍ በደማቅ ተፅፎበታል።አእምሮዬ ካሴቱን በልቦናዬ ላይ ያጫውት ያዘ። ሲጀምር አንድ አስገምጋሚ ድምፅ "ይህ ኢትዮጵያ ሬዲዮ ነው አሁን ከረፋዱ (-) ሰዓት ሆኗል አለና የሆነ የማይረሳ የሙዚቃ መሳሪያ ድምፅ ተሰማ።አዕምሮዬ ወዲያው ወደ ዛሬ መለሰኝ ግን የሰማሁትን ድምፅ ከአመታት በፊት አውቀዋለሁ። በየ ቤቱ የማይጠፋ ዳንቴል ለብሶ የሚቀመጥ አባቶች ሲኖሩ የሚከፈት ሬዲዮ ነበረን። ከየበቱ የሚሰማው የዚህ የሬዲዮ ድምፅ ሰዓት እንኳን የምናውቅበት የሰዓት መቁጠሪያችን ነበር። ዛሬ ግን የታለ #ያሳፍራል የትናንት ጣፋጭ ትዝታወቻችንን ለምን ይሆን የምናጠፋው ? የትናንቱን አየረሳን በዛሬ አርቴፊሻል በሆኑ የደስታ ምንጮች የምንታለለውስ ለምን ይሆን? ለእኔ ሬዲዮ ከመረጃ ምንጭነት ባለፈ#ልጅነቴ የተገነባበት ስንቄም ጭምር ነው። በዚህ ዘመን ብሰማው እንኳን ከማልጠግባቸው መካከል#የልጆች አለም ፤ ኢትዮጵያን እንቃኝ ፤ከመፃሃፍት አለም ጥቂቶቹ ናቸው።

ሁሉም ሰው ይጋራኛል የምለው የጥበብ ስራወች ብዙ አድማጭን ያተረፉ መካከል #ፍቅር እስከ መቃብር (በወጋየሁ ንጋቱ)፤መንዱባን(ዣምባልዣ) የትርጉም መፃፍ፤ የመዓበል ዋናተኞች ጥቂቶቹ ናቸው


በጆሲ( 𝓷𝓮𝓰𝓪𝓻𝓲𝓽)የተዘጋጀ
@gGetem
@gGetem
@yosikeman
እሷም ወዳ አይደለም !
(ሚካኤል አ)
“ጨዋታህ ይደርቃል
ለዛ አልባ ነው ቀልድህ”
ነበረ የሚሉኝ …
ቅስሜን ሲነርቱኝ ፤
.
እሷ ሳቀችልኝ …
ከንፈሬ ሲላቀቅ
አቤት አለማወቅ !
ወይ አትውል ይሆናል 
ከቃላት አርቃቂ …
ወግ ዘዬ ከሚያውቀው
ብዬ አልታዘብ …
ከሰው ጋር ነው ውላ
ከሰው የምታድረው ።
.
አዛኝ አልባ እኮ ነኝ
ማንም ግድ ያላለኝ
ብ’ራብም ብጠማም
ለሰው ልብ አልበቃ.ም ።
እሷን አሳዘንኳት
ለዛውም ሲደላኝ …
ይሄ ነገሯ ነው እኔን የማይገባኝ ።
.
አንድም አልነበረ
ጠጉሬን የዳበሰኝ
መዳፌን የያዘኝ
ያየ ዓይኔን በስስት
ያዝኳቸው ዓይኖቿን
ዓይኖቼን ሲያጫውት ።
አዎን
አልሰማም …
ስልኬ አይነሳም
ማንም የት ነህ ብሎኝ
ለ “ሀሎ” አልበቃም ።
.
እሷ ግን ደወለች …
ሳይኖራት ምክንያት
በስልኬ ጥሪ ነው
ዛሬም የማስባት ።
.
አይዘልቀኝም ወዳጅ
ሁሉ በኔ ፈራጅ
ስሆን እንኳን መልካም
ስሆን እንኳ ቀና
አብሮኝ የዘለቀ አንድም የለምና
አስቆጠረች ዓመት
ሳትዋረስ ወረት
ለዛውም በክፉ
በእንዝላል አመሌ
ያኔ ተረቀቀ
የሰማንያ ውሌ !!
.
ይኸው ዛሬም ድረስ
ሳቄ ሲፍለቀለቅ
እንባዬ ሲታበስ
ሲበረታ ጎኔ
ሲለግም ክናዴ
አራቀችም ላንዴ ።
እና
አሁን ገባችኝ
ልኬ አልሆንም ሲሉኝ
አንደዜ ሲረዝሙ
አንደዜ ሲጎድሉኝ …
ቆይቼ  ለየኋት …
የቆረፈ ቀልድ ውስጧን የሚያነፍራት
ቀኑን ከአጠገቤ ፣ ለሊት ከጉያዬ
ስቦ የሚያቆያት
ወዛሙ ገላዬ ፣ ገርጥቶ ‘ሚመስላት
ጠጉሬን የምትዳብስ
ለስልክ የሚመራት…
እሷም ወዳ አይደለም
እግዜር ወጥኗት ነው
ለክፍት ጎኔ ሙላት ።
@sirak6
www.tgoop.com/gGetem
የጥበብ መዓድ
https://youtube.com/watch?v=8Gau6nwGfhA&feature=shared

subscriber ማድረግ አይረሳ ድጋፋችሁን በእሱም አሳዩን
Audio
ይው በAudio ለምትፈልጉ
🥸ቢጣል አላነሳም😏


(ገጣሚ እና ተርጓሚ፦ሊዮ ማክ)

ብታምኚም ባታምኚም
ቢጣል አላነሳም።
የሴትነትሽ ወግ
ያንቺነትሽ ማዕረግ
የተፈጥሮነት ህግ፤
ሲለግስ...
ሲያዋርስ..
ሲያላብስ...
አንቺ ላይ ግን ሲደርስ
ፍቺ አልባ ሆነ...
ያንቺ ቀሚስ መልበስ።
ከልኩ ተናንሰሽ ከማንነት ቁናው
የሔዋንን ፀጋ አጥብቀሽ ስትሸሺው
የሰሪሽን ፍቃድ በእርግማን ቆጠርሺው።
ደግሞ...እስኪመስለኝ ድረስ
ክፋት ለመሸከም ያበጀው ማህፀን
በረመጥ ሲቃጠል የአዳም አንድ ጎን
ከራሱ ሲያነጉደው የስራሽ ሰመመን
ባንቺ ምክንያት ሆነ ሴትነት ሚመዘን።
ታዲያ...በየመንገዱ ዳር የሚታየው መጪ
             ሁሉ መስሎ ታየኝ ክፋትን አመንጪ።
ስለ...እዚህ
             ብታምኚም ባታምኚም
             ቢጣል  አላነሳም
             ባንቺ ስለሳልኩት  የቀሚስን ቀለም።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
"አንቺን  መሳይ ለሆኑ በአዳም እንባ ጎጆአቸውን ለሚገነቡ እና በማንነታቸው የሀፍረት ወጥመድ ተጠምደው ለሚሰቃዩት ይሁን"

የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
For comment
🤷‍♂ @sirak6
🧑‍💻 www.tgoop.com/gGetem
ምሽት በረንዳ ላይ
(በእውቀቱ ስዩም)

አገር ምድሩ መሽቶ
ሌቱ ምጣድ ሆኖ ፥ በኮከብ ተሟሽቶ 
የጎዳናው መብራት ፥ጨለማው ላይ ሲገን 
ከመስኮት አምልጦ ፥የወጣ ወጋንን
ሳር ቅጠሉን ሲያሳይ
አጥብቄ ስፈልግ ፥የእለት ያይኔን ሲሳይ
የሌት አይኔን ሲሳይ

በኩርማን ገላዋ፤ እራፊ ደርባ
የራሷ ሻጭ ሆና ፤ለሸመታ ቀርባ   
በሌት ይፋ ሆና፥ በቀን ልትደበቅ
ያልቀጠረችውን ፥የምትጠባበቅ
አንዲት ሴት እያየሁ
አሰላስላለሁ ፤

“ አብረዋት ያደጉ፤ ብጤዎቿ ሁሉ
በድሜና በውበት እሷን የሚያክሉ
ተድረው እንደ ሴት፥ ተከብረው እንደ ሰው
የባሎቻቸውን ደረት ተንተርሰው
ፍቅር ሲያጣጥሙ
ወይ በንቅልፍ ሲሰጥሙ
ይች ወገን አልባ
የሌሊት አበባ
በቀትር ተኝታ ለውድቅት የነቃች
የቱን ፍሬ በልታ ለዚህ ፍዳ በቃች ?”

እያልሁ አስባለሁ፥ 



ደሞ ከደጃፌ ትንሽ ማዶ ርቆ
የመሸበት ለማኝ ፤ መንገዱ ዳር ወድቆ

በግልጥ  ይታየኛል
“ ረፍትን ላክልኝ ፥ወይ እንጎቻህን ጣል
በራብ እና በንቅልፍ ሰው እንዴት ይቀጣል"
የሚል ይመስለኛል  ፤

በረንዳ ላይ ቆሜ፥ በሌሊት  ስምሪት
ከመስኮት በወጣ፥ የብርሀን ቅሪት
አይቼ ማልዘልቀው
ያገሬ ጎዳና የት ላይ ነው የሚያልቀው
መከራና ውበት የሚያፈራርቀው::

@gGetem
@gGetem
@sirak6
ይናፍቀኝ ነበር
(ገጣሚና ሰአሊ ገብረክርስቶስ ደስታ)
...

ዞሮ ዞሮ ከቤት
ይላል የኛ ተረት ::

አቧራው ፀሃዩ ይናፍቀኝ ነበር፤
አፈሩ ጠጠሩ ይናፍቀኝ ነበር::

የመንደር ጭስ ማታ…….
ይናፍቀኝ ነበር የሳር ቤት ጥቀርሻው
መደቡ ምሰሶው፤
ማገሩ ግድግዳው፤ አጥሩና ጥሻው::

የፈራረሰ ካብ………
ቀጭን ጠባብ መንገድ በመንደር የሚሮጥ፤

ቅጠል የሸፈነው፡
ሳር ያለባበሰው፤
እነዚህ እነዚህ ይናፍቁኝ ነበር፤

የተቆላ ቡና ፤
የሚወቀጥ ቡና፤
የጎረቤት ቡና አቦል ሁለተኛ፤
የተረጨ ቆሎ የሚያርቅ መጋኛ፤
የሚጨሰው ዕጣን………

እንጀራ በመሶብ ወጥ የፈሰሰበት
ያገልግል እንጀራ፤ የሚቧጠጥ ፍትፍት፤
የክክ ወጥ የሽሮ፤
የስጋ የዶሮ፡፡

ይናፍቀኝ ነበር ቅራሪ ጉሽ ጠላ፤
ይናፍቀኝ ነበር ፊልተር ዞማ ኮላ፡፡

ያገራችን ድግስ……..
ከበሮው ጭፈራው፤
ዝላዩ እስክስታው፤ ስካሩ ሁካታው፡፡

ትርክምክሙ ነገር ግፍያው ትንቅንቁ፤
ኳኳታው እርግጫው ዘፈን ድብልቅልቁ፡፡

“አሸወይና ወይና“
“እስቲ እንደ ጎጃሞች“
“አሲዮ ቤሌማ… ኦሆሆ አሀሀ…"
የቄስ ትምህርት ቤት
የህፃናቱ ድምፅ፤

“ሀ...ሁ…ሂ…ሃ…“ ዜማ ነበር የናፈቀኝ
የጽጌ ጭፈራ ነበር የናፈቀኝ፡፡

ከበሮ ፅናፅል፤
ሆሳዕና ጥምቀት፤
ፋሲካ ገና ሁዳዴና ስግደት፤
ቡሄ ሆያ ሆዬ፤
የእስላሞች አረፋ የኦሮሞች ሸጎዬ፤
የቁልቢ ገብርዔል፤
ልደታ፤
ፍልሰታ፡፡

ዕንቁጣጣሽ ነበር መስከረም ሲጠባ፤
አውቆ የበቀለ ወፍ ዘራሽ አበባ፡፡

ለምለም አረንጓዴ…
ያልተጠበቀ መስክ ከብት የሚግጥበት፤
የደመና ግላጭ የሚጫወትበት፡፡

ሌላም ብዙ ነበር…
ሌላም ….ደግሞ ሌላ…..፡፡

ያገሬ ሰው ነበር እኔን የናፈቀኝ፤
ጠይም ቆዳ ነበር እኔን የናፈቀኝ፤
ቀይ ዳማ ነበር ጥቁር ቆዳ ነበር፤
ቁርንጫጭ ከርዳዳ፤ ዞማ ጠጉር ነበር፤

ያገራችን ቋንቋ…
ያገሬ ሙዚቃ ያገራችን ዜማ፤
ጥበብ እጀ ጠባብ ያገራችን ሸማ፤
ነበረ ናፍቆቴ ለሁሉም…
ለሁሉ፡፡

ለሸዋ፤ ለወሎ፤ ለትግሬ፤ በጌ ምድር፤
ለጎጃም ወለጋ፤ አሩሲ ኢሉባቡር፤
ኤርትራ ገሙጎፋ፤
ሲዳሞና ከፋ፡፡
ለሁሉም ለሁሉ ነበረ ናፍቆቴ፤

አለብኝ ትዝታ
ዘመዶቼ ሳሙኝ፤
ጓደኞቼም ጋብዙኝ፤
ሊስትሮ ጨብጠኝ::

ባለጋሪ ንዳ መንደሩን አሳየኝ፤
ያገሬ ልጅ ቆንጆ “ቤት ለእንግዳ በዪኝ“፡፡

አለብኝ ትዝታ…..
አዲስ አበባ ላይ ነበረ ናፍቆቴ
መናገሻ ነበር፤ እንጦጦ ነበረ፤
ኤረር ጋራ ነበር፤ ዝቋላ ነበረ፤
ጃን ሜዳ ነበረ፤ ኮተቤ ነበረ፤
ገፈርሳ ነበረ፤ ጉለሌ ነበረ፤

አዲሱ ከተማ…
“መርካቶ ዲጂኖ ችምችም ያለው መንደር“
ከተማው እንብርት ደጃች ውቤ ሰፈር
የቸርችል ጎዳና፤
የባቡሩ ጣቢያ፤
ቢሾፍቱ ነበረ፤ ናዝሬት፤ ሞጆ አዋሽ::
ድሬዳዋ ነበር፤
ዓለምማያ ነበር::

ሐረርጌ ነበረ የተወለድኩበት
እናትና አባቴን ጥዬ የሄድኩበት::
የሚካዔል ጓሮ…
ሐረርጌ ነበረ፡፡
ዞሮ ዞሮ ከቤት…
አገሬ ነበረ እኔን የናፈቀኝ::
ኢትዮጵያ ነበረች♥️
@sirak6
www.tgoop.com/gGetem
2024/07/01 02:13:34
Back to Top
HTML Embed Code: