Telegram Web
የማላውቀው ምክኒያት
ክፍል ሦስት
አመሻሽ ላይ ከስራ ስወጣ በጎዳናው እንደ ጉንዳን የሚርመሰመሱትን ሰዎች እየተመለከትኩ አንድ የጓደኛዬን ግጥም ማንሰለላሰል ጀመርኩ።

ትርምስ አንግሶ በተቃኘ አለም
ማርመምን መናፈቅ የሚገርም አይደለም
የሃሳብ ብዘሃነት ሰው የመሆን አውነት
ባለማግኘት ቅዠት
አዕምሮም ቢጠፈር በገለጣት ህይወት
ለአፍታ እድሜው እንጂ አይድንም ከመሞት
በምኖር ምህዳር የህይወት መዝገቡ በተገለጠበት
ከችግር ቁልቁለት አልሞ ለማቅናት
ቢጥርም ባይጥርም
ሰው ከተፃፈለት እጣ ፈንታ አይዘልም።
             @ ገጣሚ ሊዮ ማክ(ሲራክ)

ይህንን ግጥም እያንሰላሰልኩ ለብዙ ሰዓታት ሰለ ህይወት ራሴን ስጠይቅ ስመልስ ሳወተጣ ሳወርድ ቅየው።  ፍቅረኛዬ ደውልልኝ ማለቷን ዘነጋሁት። እንዳለችውም እኔ ለእርሷ ግድ እንደሌለኝ እንደማልወዳት እንደማላስቦት መረጋገጫ ሆነላት። በማግስቱ ስደውል አታነሳም እርሷም ሳትሰናበተኝ ሄደች። ግን ቆይ እስኪ ንገሩኝ በየ ቀኑ በየ ሰዓታቱ መደዋወል የግድ ነው በፍቅርኛሞች ህግ ?
እንደኔ እንደኔ እንጃ.....!

  በጆሲ
@gGetem
@gGetem
@yosikeman
ቅንጭብጭብ6
<unknown>
ቅንጭብጭብ 6🔥
ከ ግጥም በፎቶ የተወሰደ
አዘጋጅ እና አቅራቢ፦ ሊዮ ማክ
👉መታደል
👉እየቆሙ መሔድ
👉ያላለቀ ፍቅር
👉ጅማት
👉ያማል ቅኔው
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
@Leoyri
@gGetem
@gGetem
@gGetem
የሆሄያት ህብር📝📝
የሔርሞን_ማስታወሻ          ኡፍፍፍፍ መቼ በዚህ በቃና ብለሽ እታለም ከዚህ የእግር ብረት ከሆነ የአለም ፈተና ሲወድቁ  ሲነሱ አልፈው በስንት እና ስንት እንግዳ ሀሳብ ሲናጡ ከርመው ለትዳር የበቁት ደግሞ ፊርማቸው ገና ቀለሙ በውል እንኳን ሳይደርቅ በበነጋው ለፍቺ ፊት እና ኃላ እየተማሩ ሰርክ የፍርድቤቱን ደጃፍ ከአፍ እስከ ገደፍ የሞሉት እነማን መሰሉሽ...?!......እኚው ትናትን "በሆታ"…
ህህህ!!...እታለሜ እንድታዋሺኝ መቼ ብለሻል አደለ? ዳሩ ብትይስ አይፈረድብሽም ወንዱ ወንዱነቱን ጥሎ ከሴትነት ጓዳ ለመገኘት የሚያደርገው እሽቅድምድም ቀላል መስሎሻል...
ሴቷም ብትሆን ያው ናት የሴትነት ክብሯን ኪስ በሚቀድ ልቃቂ ዲናር ስትቸበችበው ነው የምትውለው።ደግሞስ በዚ ቢያበቃስ ጥሩ አይደል የተፈጥሮ ፀጋዋን እንደ ባለ አንድ መክሊቱ ነጋዴ አርቃ ከአራሙቻ መሀል ቀብራው የእርሷ ባልሆነ በተውሶ ነገር ከተቸራት ስጦታ ለማምለጥ ስታትር የምትውለውን ማህፀን ይቁጠረው።
እንደውም...

በተውሶ ፀጉር በተውሶ አልቦ
ታስጠዪው ጀመረ ለተረዳሽ ቀርቦ።

የሚለውን የግጥም ስንኝ አስታወሰኝ እና...
እታለሜ እንደ ሀገሬው አባባል ቤት ይቁጠረው እንዳልልሽ በቤት ተጠልሎ ከሚያድረው ይልቅ በየአውራ ጎዳናው ጥጋጥግ የሚያድረው ስለሚበልጥ ነው።
ግን ይህ ማለት ሁሉም የወንዝሽ ልጆች አንድ ናቸው እያልኩ አይደለም፤እልፍ ስለ ህሊናቸው ልዕልና፣ስለቤተሰባቸው ተግሳፅ፣ስለ እናት ሀገራቸው መፃዒ እድል ሲሉ በአግባቡ የሚኖሩ እንዳሉ የማይካድ ሀቅ ነው እታለሜ ግን ቢሆንም....ቢሆንም ግን እታለሜ በየአደባባዩ ግልጥ የሚታየው እፀፅ ምግባር ይ..በ...ል....ጣ....ል!!

🛖ሔርሞን ነች የዳር ሀገሯ
🌃በስደት ላለሽው እታለሜ
#ፀሐፊ_ሊዮ_ማክ
(ይቀጥላል)
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
ለሒስ፦ @sirak6
ለቤተሰባዊነት፦ www.tgoop.com/gGetem
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (DAVE / PAPI)
ሀዘን መለኮት ነው፣ ፈገግታ ደግሞ ሰው፣
ማን ናት ይቺ መሲህ፣ ግንብ ምታፈርሰው?
እንባን የምታስቅ፣ ሳቅ የምታለቅሰው?
ተዋህዶ ፊቷ፣ የክርስቶስ ፈለግ
ፍፁም ንፁህ እንባ፣ ፍፁም ንፁህ ፈገግ


@getem
@getem
@paappii

#Rediet aseffa
Audio
በምን እንግባባ
በጆሲ( 𝓷𝓮𝓰𝓪𝓻𝓲𝓽)የተዘጋጀ
@gGetem
@gGetem
@yosikeman
Audio
በምን እንግባባ
በጆሲ( 𝓷𝓮𝓰𝓪𝓻𝓲𝓽)የተዘጋጀ
@gGetem
@gGetem
@yosikeman
ሀገርሽ ምነኛ መንደርሽ ምነኛ#
አላውቅበት አልኩኝ ያንቺን አማርኛ# ...አለ ጠጉረ ልውጥ አፈቀርኩህ ብትለው።

ገበሬው እንዴት ያለ ሸበላ መሰላችሁ። አቤት አረማመድ አቤት እግር አጣጣል አጀብ ነው የሚስብለው። ከጎማ የተሰራችውን ሸበጥ ተጫምቶ ቁምጣውን ለብሶ በትር ይዞ በበትሯ ላይ ምሳውን ሸክፎ ከብቱን እየነዳ በሰፈሩ ያለፈ እንደው ማትማረክ ልቧ የማይርድ ሴት አልነበረችም።
ታዲያ የኔ ነው ጠጉረ ልውጧ ከተሜ ሀገር ለመጎብኘት በጎዳናው እየተዘዋወረች ሳለ ከዚህ ሸጋ ጋር የተገናኘችው። ስታየውም እንደ ሰፈሩ ሴት ልቧ ራደ "በቀዬዋ ቋንቋ ልታናግረው ሞከረች ግር አለው" እንደምንም እያሳበረች ሰላምታ ሰጠችው እጅ ነስቶ ሰላም አላት። ፎቶ ላነሳህ እችላልሁ ...እንዴታ ምን ገዶኝ ቀጭቅጪኝ አላት አነሳችው ደገመችው ደጋገመችው መሳቅ መጫወት ጀመሩ። አንዳንዱ ሳይገባው እንዳንዱን ተረድቶ ሲመልስላት ቆዩ። ከብት የሚያግድበት ስፍራ ድረስ ተከተለችው ጭራሽ በመንደሩ ዳስ ጥላ ውላ አደረች። ከቆይታ ብዛት መተዋወቅ መግባባት መላመድ ጀመሩ ፍቅር በልቧ ቋጠረች። የቋጠረችውን የፍቅር ፍሬ ጀባ ስትለው ነው ይሄንን ግጥም የገጠመላት። ..አወይ ፍቅር

በጆሲ( 𝓷𝓮𝓰𝓪𝓻𝓲𝓽)የተዘጋጀ
@gGetem
@gGetem
@yosikeman
ደስታ
ሃምሳ የሚሆኑ ሰዎች ስልጠና እየወሰዱ ነው...አሰልጣኙ በመሃል ላይ ለእያንዳንዱ
ሰልጣኝ ኳስ አደላቸውና ስማቸውን እንዲጽፉበት ጠየቃቸው.....በመቀጠልም ኳሶቹ
ተሰብስበው ወደ ሌላኛው ክፍል ተቀመጡ...ከትንሽ ገለጻም በኋላ
አሰልጣኙ
"ሁላችሁም የሚቀጥለው ክፍል ውስጥ ሄዳችሁ የራሳችሁ ስም የተጻፈበትን ኳስ
በአምስት ደቂቃ ውስጥ ይዛቹ ኑ.." ሲል ጠየቃቸው
ሁሉም ክፍሉ ውስጥ መተረማመስ ጀመሩ...ነገር ግን በአምስት ደቂዎች ውስጥ ማንም
የራሱን ኳስ ማግኘት አልቻለም።
አሰልጣኙም ትርምሱን ካስቆመ በኋላ "እያንዳንዳችሁ በእጃችሁ ያገኛችሁትን የሌላ
ሰው ኳስ ለሚመለከተው ሰው መልሱለት.." ሲል ጠየቃቸው....በሚገርም ፍጥነት
ሁሉም የየራሱን ኳስ አገኘ።
አሰልጣኙም እንዲህ በማለት ምሳሌውን አጠናቀቀ
"በህይወታችንም ውስጥ እየሆነ ያለው ይሄው ነው....ሁሉም ሰው ደስታን
ይፈልጋል...የት እንዳለ ግን አያውቀውም...ነገር ግን የእኛ ደስታ የሚገኘው የሌሎች
ሰዎች ደስታ ውስጥ ነው...ደስታቸውን መልሱላቸው....የእናንተንም ደስታ ታገኛላችሁ።"
እኛም እንላለን "እውነተኛ ደስታ ማግኘት የሚቻለው የሌሎችን ደስታ በመጨመር እና
የወሰድንባቸውን ደስታ በመመለስ ነው#

መልካም ምሽት ቤተሰቦቼ🥰


                                          comment @sirak6
for more Join☞ www.tgoop.com/gGetem
አንተ እንሽላሊት
ብርቱ እኮ ነህ በርግጥ
ልፋትህ አለቅጥ …
ርምጃህ እሩጫህ
ድብብቆሽ ጥድፊያህ
ጉብዝና ተሰልቶ
ትጉ ነህ ቢሉህም………
ጅራትህ ሲቆረጥ ፣ እንጀራ የለህም።
እናስ አንተ ብኩን ….
ሸረሪት ሁን በቃ ፤
ጅራት ባጣስ ብለህ
በጉብዝናህ ንቃ ።
ተሸሸግ ፣ ተደበቅ
ግባ ወደ ጥጉ
አስላ ሆነህ ስጉ
አቅደህ ስለ ድር
መወጠን ብትጀምር …
ሸርተት ብለህ ትበላለህ
ጅራት እግርህ ቢያጥር ።

(ሚካኤል አ
@sirak6
www.tgoop.com/gGetem
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo)
ጥሩ ወግ🧤🧤🧤🧤🧣🧣🧣🧣
ሰባኪው🙏😔
🧣ተራኪ፦ሊዮ ማክ
@Leoyri
@gGetem
ውዴ
እኔማ እመጣለሁ የትም ብትቀጥረኝ፣
ድንገት ካልተመቸህ አንተም ቃል ግባልኝ፣
አለመምጣትህን መጥተህ እንድትነግረኝ!😌

bilen ዮናስ

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
       @gGetem
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
4 any comment             
       @gGetem
❥❥__⚘_❥❥
#ለጁማችን
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo Leጅ)
🌺🌺🌺🎂🌺🌺🌺
ካነበብኩት ......
#የአና_ማስታወሻ
#ገፅ(page)-100
የሆሄያት ህብር 🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@gGetem
@leoyri
እንኳን ለየሆሄያት ህብር 4ኛ አመት የምስረታ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
📚📚📚📚📚
🎂🎂🎂🎂🎂
🇪🇹የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━


ጥቁር ቀንዲል ፥ የሌት ንጋት
አምሳለ ወንድ ፥ ምግባረ እናት ።

​​               ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
       ✍🏽©           ራስ አብ
    ╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈ 
ለእምዬ ምኒልክ የተገጠመ


ምንጭ ➸ የግጥም አብዮት
ለመቀላቀል 👉🏽 @gGetem
አስተያየት 👉🏽 @leoyri
┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─
" የለም " ማለት " አለ " ፪

( አማኑኤል አለሙ ኑርጋ ) አሙ

ባዶ ማለት ዜሮ
ዜሮ ማለት ምንም
በሆነበት አለም ..
ኪስህ ባዶ ቢሆን
" ምንም አልያዝኩኝም "
ለምን ትለኛለህ ...
በኦና ኪስህ ውስጥ ምንም'ማ አለህ!

..........
................

ካወቅከው በኀላ
ምንም ምንም የሚል
'ጣሙን በምላስህ
" ውሃ 'ጣም አልባ ነው "
ለምን ትለኛለህ ...

..........
...............

ካበቃህ በኀላ
ቢራውን ጨልጠህ
ውስጡ አየር እንዳለ
በዓይንህ እያየህ
" ጠርሙሱ ባዶ ነው "
ለምን ትለኛለህ ...

..........
...............

ስላጣኸው ብቻ
አትበል " የታለ "
የለም ያልነው ነገር
ባለመኖር አለ ።
የሆሄያት ህብር
🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
@gGetem
@gGetem
@gGetem
ከነጋሪት በጆሮ የተወሰደ

የክረምቱ ወራት አልቆ ፀሓይዋ ብቅ ስትል ሁላችንም በቤታችን የተጣለ ዳንቴል ተልትለን ኳስ እንሰራ ነበር። እኔም ለኳስ ልዩ ፍቅር የነበረኝ። በርግጥ
እኔም ብቻሳልሆን ጓደኞቼም ኳስ ለመጫወት ሳዓታችንን ጠብቀን ነበር የምንሰባሰበው፡፡ ድንገት ከመካከላችን አንደኛዉ
ስራ ታዞ እንኳን ቢሆን ተጋግዘን ሰርተን ወደ ጨዋታችን እንሄድነበር።
11ሰዓት ለኛየአለም ዋንጫ የፍፃሜ ጫወታ የሚካሄድ ነበር የሚመስለው ሁሉም ከያከበባቢው እየተሯሯጡ ተማሪው
ከትምህርቱ እረኛውም ቢሆን ከስምሪቱ የምንሰባሰበው፡፡እርስበ እርስ ያለን ፍቅር የሚያስቀና ነበር።አንዴ ትዝ ይለኛል
እጅግ መሽቶ እንኳን እርስ በአርስ መተያየት እሰከማንችል ድረስ እየተጫወትን የትምህርት ቤቱ ዘበኛ የነበሩት ጋሽ አሌ
አረ መሽቷል በቃቹ ግቡ ነገ ትጫወታላቹ ብለው አልሄድ ስንል ኳሳችንን ሲነጥቁን ወደ ድበብቆሽ ጫወታ ዞርን ብቻ የዛን
ለት ለመደበቅ በሄዱበት በዛው ወደ ቤቱ የሄደም አይጠፋም እርግጠኛ አይደለሁም ግን ብቻ ፍቅራችን ለነገ የሚባል
አልነበረም።
ዛሬ ተጣልተን እንኳን ነገ ፍቅራች ያዉ ነበር። ባቱ ትምህርት ቤት ከተባለ የማያቀን አልነበረም አንድ ሰሞን መረብ ኳስ
መጫወት ፈልገን አጫጭርና ህፃናት ስለሆንን የሚጫውተን አልነበረም እንጫወትስ ብንል የት እንጫወታለን መረብ ኳስ
ያለው ወይ ትምህርት ቤት አልያም ኳስ ሜዳ ነበር ያለዉ እዛ መሄድ ይኖርብናል እዛ ብዙ ሰዉ የሚሰባሰብበት በመሆኑ
ያደግሞ ለአኛ ነፃነት የለውም ። ታዲያ መረቡን በእጃችኝ ሰርተን በአመድ መስመር አስምረን ቁምጣ አዘጋጅተን እንጫወት ነበር። ታላላቆቻችን ራሳቸው ይቀኑብን ነበር ዙሪያችንን ከበው የኛን ጨዋታ ያያሉ።ሲላቸው አስገቡን ይሉና።
ማን ይሆን የዚህ አይነት ትዝታ ያለው?
ህይወት የትናንት የዛሬ የነገ ጥምር ውጤት ማሳያ መነፅር ናት።
በትናንት ውስጥ የሁሉ ነገር መሰረት የታላቅነት ውጥን የአልበገሬነት ልጅነት ሰንሰለት ናት በልጅነት ውስጥ ንፁው
ፍቅር ቂም የሌለበት ነፃ አለም በምንም ያልተበረዘች ሲሆን በዛሬ ውስጥ ደግሞ ታሪክ መስራት ጥንካሬን ውሳኔን በራስ
የማድረግ ከህሎትን ከስህተት መማርን መውደቅ መነሳትን የትልቅ ራዕይ አላማ ውጥን ማስቀመጥን የበረከት ፍሬን መዝራትን ወደ ነገ የሚያሻግረንን ድልድይ የምንገነባበት የታላቅነትን መንገድ በቁርጠኝነት የመጀመሪያዋን እርምጃ የምንራመድበት ጎዳና ናት።ሁሉም ሰው የራሱ የህይወት መዝገብ አለው ነገውን የሚፅፍበት ነገ ዉስጥ ተስፋን
ጥንካሬን ቁርጠኝነትን ትዕግስትን እና የመሳሰሉት ጥምር ውጤት ያለዉ በነገ ዉስጥ ነዉ።

በጆሲ( 𝓷𝓮𝓰𝓪𝓻𝓲𝓽)የተዘጋጀ
@gGetem
@gGetem
@yosikeman
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Y€ŕi ወንጌላዊት)
My Song 2.ogg
9 MB
🧟‍♂ ዘመም ይላል እንጂ🧟‍♀
#ገጣሚ_በእውቀቱ_ስዩም
አንባቢ፦ሊዮ_ማክ ©☔️
የሆሄያት ህብር🦋🦋🦋🦋
#የጥበብ_ማዕድ
💚💛❤️
@Leoyri
@gGetem
@gGetem
@gGetem
🇪🇹እሮብ               ግንቦት ፭ ፳፻፲፪ ዓ.ም
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━


እናት ብትወደስ ፥ እውነት ነው ያንሳታል
ቃላቶች ቢነጥፉም ፥ መቼ ይገልጿታል
ግን ለምን ተረሳ ፥ የእናትነት ምንጩ
አባት አይደለም ወይ ፥ የጽንሶች አማጩ
ሄዋንን ቀዳሚ ፥ እሱ አዳም ነውና
ለአባትም እንደ እናት ፥ አቅርቡ ምስጋና ።
        
​​               ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈
       ✍🏽©       ሰላማዊት ተሾመ
    ╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈

       
ምንጭ ➸  የግጥም አብዮት

ለመቀላቀል 👉🏽 @gGetem
አስተያየት 👉🏽  @Leoyri
በምንም እና ለምንም ነገር አንተ የመጀመሪያው ሰው አደለክም እና አትገረም...አትዘን...አትኮፈስም❗️❗️❗️
ምክንያቱም ...
#በስኬት ጊዜ ልትቋቋመው በሚሳንህ ደስታ አትዋጥ።
#በውድቀትህም ጊዜ ለመነሳት በሚያዳግት የስሜት መሰባበር ውስጥ #እራስህን አትጣል❗️❗️
ምክንያት፦ካንተ በፊት ብዙዎች የስኬት ጥግ አይተዋል። #እንዲሁም ካንተም በፊት ካንተ በባሰ #ውድቀት እና ስቃይ ውስጥ  በማይታመን መልኩ ገብተው እራሳቸው ስላገኙት ነው!!!!
ስለዚህ #አንተ የመጀመሪያው አይለህም❗️❗️❗️❗️
#ሊዮሪ
@gGetem
@leoyri
@leoyri
አመልካች👉
Forwarded from የሆሄያት ህብር📝📝 (Sirake peterøs ☞Ye Yerijo Leጅ)
ጭምት_ሴት
ከዝምታሽ ድባብ ከቃላትሽ ህብር
በጭንቅ ተውጣ በኑሮ ውዥንብር፤
ብዙ ጩኸት አለ
ብዙ ህመም አለ
ለተመልካች ወርዶ ለሷ ያልቀለለ።
ከዝምታሽ ጀርባ፤
ብዙ ጩኸት አለ!!!
ሊዮሪ
📷ማማ 04/09/2013ዓ.ም
08:35am
@leoyri
@gGetem
@gGetem
2024/06/26 02:08:22
Back to Top
HTML Embed Code: