Telegram Web
አጭሬን በአጭሬ ፪ በሲራክ
ሲራክ
#አጭሬን_በአጭሬ_
የአጫጭር ግጥሞች ስብስብ በድምዕ
የገጣሚ ታገል ሰይፉ
የገጣሚ ጌትነት እንየው
የገጣሚ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
የገጣሚ በረከት በላይነህ
የገጣሚ አያልነህ ሙላት
ስራዎች ተካተውበታል አንባቢ ሲራክ @siraaq

@Getamiyan
@getamiyan
የአፍቃሪ ስንብት
(መዘክር ግርማ)

እሄዳለሁ ብለሽ፣ ሻንጣሽን ካነሳሽ
ትናንትናችንን፣ በዛሬ ከረሳሽ
አላስገድድሽም፣ መሄድ ካ'ሻሽ ሂጂ
ባይሆን ተከትየሽ፣ እመጣለሁ እንጂ።

@getamiyan
@getamiyan
@getamiyan
👍1
#መቼም_አንላቀቅ
:
:
እንኩ እኔን ስደቡኝ
እሱ እንዲ ነው በሉኝ
ባ‘ይናቹ አፈር አብሉኝ።
:
:
በምላስ በወሬ
ዝለፉኝ አስሬ።
:
:
ቡናም ስትጠጡ
እኔን ለማማቱ ምክንያት አትጡ።
:
:
አሽሙር ሆነ ቅኔ
አሜን ለማለቱ ዝግጁ ነኝ እኔ።
:
:
ያሻችሁን አርጉብኝ እኔ እንደው ትቻለው
ፍቅር አስገድዶኝ እራሴን ክጃለው።
:
:
ግን እንዲ ስላቹ
ምንም ቢኖራቹ
ለኔ ብቻ አድርጉት
የማፈቅራትን ልጅ ጫፏን እንዳትነኩት።
:
:
የህይወቴን ህይወት የመኖሬን ሚስጥር
የኔን ሀሴት ደስታ፣
ያንድ አካሌን ግማድ የነብሴን ቡራኬ
የልቤን እርካታ፣
የዕድሜ ልኬን ንግስት የፀሎቴን ምላሽ
ያምላኬን ስጦታ፣
እንደው ሌላው ቀርቶ ካያቹዋት በክፉ
እውነት ነው ምላቹ መቼም አንላቀቅ
ወይ እስከምደፋ ወይ እስክትደፉ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ

@Getamiyan
@Getamiyan
👍1
🌹ካገባች በኋላ

ሌላ ወንድ አቀፋት የሚል መርዶ ሽሽት
ሌላ ሴት እያቀፍኩ በያንዳንዷ ምሽት
እሷ ናት እላለሁ
(የኔ እብደት ሲገርመኝ ይባስ የሴቶቹ)
ፍቅር የሰለቻቸው ፍቅርን የሰለቹ
እሷ ናችሁ ስላልኩ "እሷ ነን" እያሉ
እኔ እንዳነሳቸው ራሳቸውን ጣሉ


(አሌክስ አብርሀም)


@getamiyan
@getamiyan
@getamiyan
👍1
የኔ አለም
መብረር እንሻደተ አክናፍ
ገብቶኝ የማልጓዝ የጉዞዬ አፅናፍ
እከንፍልሻለሁ።
የቱ ጋር ቆመሻል ልምጣልሽ እላለሁ።
ክንፍ.......ክንፍንፍ
እፍ........እፍፍፍፍ
ንፋስን መሰንጠቅ በመሄድ መደምደም
ቀሪ መንገድ ህልሜን ካንቺ ለመካደም
አላውቀውምና
አይገበኝምና ያንቺ መዳረሻሽ
አጠገብሽ ቆሜ አጠገብሽ ልሆን እነሳለሁ ጭራሽ።
ማለትም
ማለት የምችለው
ስምሽ።ን ነውና አቤት በይ ስጠራሽ።
ማለትም ስምሽ ነው
ስምሽም ስምሽ ነው
ነው ማለት ስምሽ ነው
አራት ነጥብ ስምሽ
ቃል ሁሉ ስምሽ ነው
ምልክት በመሉ
ስምሽ መጠሪያሽ ነው ላንቺ የተገራ ላንቺ የተሰራ
በልቡ ለሚኖር
ቀና በይ ዝም ብለሽ ልቡን ለሚጣራ።
የክንፋም ልብ ወዳጅ ንፋስን ማርገብገብ
በንፋስ መንገብገብ
ንፋስን መጠርጠር
ንፋስን መመገብ
ከንፋስ መጓተት ከንፋስ መሳሳብ
ከንፋስ መሳሳም።
እነፍስልሻለሁ።
የባየር በብርሀን በጨለማ ወንበር
አንቺ ጋር እንደቆሞኩ ክንፌን አጥፍ ጀመር።
ደረስኩኝ ማለት ነው።
የክንፋም ቀልብ ጦስ መሞቻ ሞኝነት
መሄጃ ሰበብ ጋር በቶሎ መገኘት።
አለሜ
መጓዝ መድረስ ኖሮት ካስነቀለ ላባ
መድረስ ከመገኘት ከእቅፍሽ ቢያሞቀኝ
መፈለግ ደስታዬ ሳገኝሽ ራቀኝ።
መሄዴን ብውደው
ቢቆይልኝ ብዬ የክንፌን አክራሞት
እፀልይ ጀመረ
ስቀርብሽ ሂጂልኝ ሳገኝሽ እንዳልሞት።
©ገጣሚ ኤልያስ ሽታሁን

@getamiyan
@getamiyan
@getamiyan
👍1
ዒድ ሙባረክ!
عيد مبارك

እንኳን ለ1,441ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን!

መልካም በዓል

@Getamiyan
@getamiyan
አጭሬን በአጭሬ
ሲራክ
#አጭሬን_በአጭሬ_
የአጫጭር ግጥሞች ስብስብ በድምፅ
ገጣሚት ሜሮን ጌትነት
የገጣሚ ያሬድ ጌታቸው
የገጣሚ ዳዊት ተ/ማሪያም
የገጣሚ አዘርግ
የገጣሚ አዲሱ ኃይሉ ....አንባቢ ሲራክ @siraaq

@Getamiyan
@getamiyan
Audio
ሜሮን ጌትነት፣(ዙረት)


ቅጣት በበረከት
፠፠
"ለኃጥአን የመጣ . . . "
ነውና ተረቱ
ለኔ ከታዘዘው
ደርሶሃል ጥቂቱ
በል አንተም አትርሳኝ
ብድርህን መልስ
በረከት ሲያድሉህ
የድርሻዬን ቀንስ።
፠፠


@getamiyan
@getamiyan
@getamiyan
@getamiyan
👍1
🧐ዝምተኛ ልቦች🧐

(ጌትነት እንየው)

አምነው የወደዱ
ወደው የተካዱ
ተክደው የራዱ
ፍርሃት አንሸራቶ ቁልቁል የጣላቸው
የብቸኛ ልቦች የትነው መውደቂያቸው?
የትነው መድረካቸው?
ማነው አጃቢያቸው?
እንዴት ነው ምታቸው
የተካዱ ልቦች አጋር የራቃቸው
የሚያቀነቅኑት ምንድን ነው ዜማቸው?
የተመረኮዙት እምነት ታጥፎባቸው
ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው
ሚስጥር የሚያጋሩት ሰው የበደላቸው
ብቸኝነት ሰርጎ ብቻ ያስቀራቸው
ዝምተኛ ልቦች ምን ይሆን ቋንቋቸው?
ከየት ነው ጥሪያቸው?
በየት ነው ጉዟቸው?
የት ነው መድረሻቸው?
እንደ ሰብአሰገል ጠቅሶ የሚመራቸው
የቃተቱ ልቦች የታል ኮከባቸው?
መቼም ከአምላክ ትንፋሽ ከውሃ ከአፈሩ
ከእምንት እና እውነት ከፍቅር ሲሰሩ
ዝምተኛ ልቦች ጥንቱን ሲፈጥሩ
ተገፍትረው ወድቀው
ደቀው እንዳይቀሩ
በተስፋ ጸንተው ነው ዘላለም ሊኖሩ::

@getamiyan
@getamiyan
@getamiyan
'ከሽፍታ' የተሰረቀች ግጥም
(በረከት በላይነህ)

-----------
ገና!
ከእናቴ ሆድ ሳለሁ፤
ጠላት ሲዝትብኝ ሰምቻለሁ።

በዳዴ ዘመኔም፣
በ'ወፌ ቆመችም!'፤
አውዴ ክፉ ነበር ለወሬ አይመችም።

እንደ ሚዳቋ ነፍስ እንደ ነብር ጥፍር፤
ስጋትም- ጭካኔም-ነበር የዕውቀቴ ስር፣
"ተጨቆንኩ!"
"ተበደልኩ!"
"ተረገጥኩ!"
"ተገፋሁ!"
"ተቀማሁ!"።
መሬቱ ጠላቴ፤
ሰማዩ ብሶቴ።

ተስፋ ትዝታዬን ሊያጠፋ ለቃቅሞ፤
ባፈሙዝ ያየኛል ገዳይ ደጅ ቆሞ።

ወዘተ...
በእነዚህ 'ምግቦች' አድጎ ሰውነቴ፤
እኮ እንደምን አይሆን 'ጥርጣሬ' ሀብቴ?
መገርሰስ፣ መደምሰስ፣ ማሳደድ-ውበቴ?
ስለዚህ አይድነቅህ!
ቀርበህ ወደድከኝም፣ ርቀህ ጠላኸኝም፤
ገድዬህ ካላለፍኩ የኖርኩ አይመስለኝም።

@getamiyan
@getamiyan
@getamiyan
#ቀሽም_ብይን

ምሩቅ ጥበብ ሰሪ
የሸራ ቀበኛ ፥ የቀለም ቀማሪ
ጠቢባን ጠበብቶች
የቀለም አባቶች
የብሩሽ አርበኛ ፥ የኪነት ገማቾች
በዘመን የቆሙት
ከትውልዱ ወጥተው ፥ የሚተዛዘቡት
አልያ ....ዘመን አልፈው
በነጠረ ስራ....
ከኛ ጀምበር ጥላ ፥ በሞገስ የቆሙት
መናኛም.....ሆኑ ...ዝነኛ
ትሁትም ....ሆኑ ....ጉረኛ
እርቃን አፍቃሪዎች!
ምስል ደጋሚዎች!
ምጡቅ አሳቢዎች!
ብቻ.....ሰአሊ የሆኑ
ሸራ የወጠሩ ፥ ብሩሽ የዘገኑ
ሁለት ግዜ ነው.... የሚስሉ
ሁለት ግዜ ነው ....የሚያጤኑ
#አንድ...
በረጅም ግዜ ተመስጦ ...በጥቂት ግዜ መቃኘት
የሚፈለገውን ውበት ፥ ተኩሮ በማየት
በህሊና ችንካር ሸራ
ያኔ ነው ፥ የጥበብ ሽል ፥ ፅንሱ የሚዘራ
#ሁለት...
እንግዲህ በሀሳብ ፥ ምስሉ እንደታያቸው
በውን አለም ሸራ ...ይጫራል ንድፋቸው
አይን እና እጆቻቸው ፥ እኩል እስከቻሉ
የግል አይናቸውን ፥ ለሰው ይቸራሉ
ያዩትን ...ለማውረድ
ፅንፉን ለማዋደደ
ጣጥረው..
ጫጭረው...
ሞንጭረው...
የለቀለቁትን.... አቅመ ጥበብ ቅይጥ
ጋለሪ እያገባ ...ወዳጅ እንዲያቋምጥ
ሁለቴ ተረግዞ...ሁለቴ ይማጣል
አፍቃሪው በርትቶ....
ወላድ ለመጠየቅ ...አውደርይ ይወጣል
በዚህ ኩናቴ ውስጥ...
አንዳቹም ሰአሊ
ልጁን የሰቀለ ፥ በቤት በጋለሪ
እስኪያረጅ ...እስኪሸጥ
ማንጠልጠል ይወዳል ፥ ጭንቁን እንደ ትሪ
የብሩሹ አጣጣል ፥ ቀለም ስብጥሩ
የመልእክቱ ምጥቀት ፥ ብራና ሚስጥሩ
ገለፃው......ውብቱ
ጨረሩ ....ሙቀቱ
ሺህ ግዜ ፥ እልፍ አመት
እኛን ቢገርመንም...
ቢያጅበንም ...ደርሶ
የሁለቴ ምጥ ነው
ዘመን የሚሻገር ፥ በቀለማት ርሶ
አየሽልኝ ውዴ....
እንዲህ ያለውን ሰው
ወሮታው ሲዘከር ስላንጠለጠለ
በምናቤ ጓዳ...
የማይከስም ምስልን...ራሴ ላስጠለለ
አፍቃሪነት ዳሩ...
ከጠቢብም በላይ ...ጥበብ እንዳዘለ
ምስክሬ ነፍሴ
ባገኘው ወረቀ....አንቺን እንደሳለ
ምን ይሆን መስፈርቱ
ማነው የሚረዳ...
አይኔ በከደነ ፥ ገፅታሽ ሲቀዳ
ምስልሽ ሲንቀራወዝ ...በህልሜ ሰሌዳ
በውኔም በወረቀት ፥ ሲብስ በግድግዳ
የብዙ ብዙን ምጥ....አዕላፈ ውልጃ
ከሁለት ግልግል...ካንድ ተኩል ውርጃ
ለማመዛዘኛ....ቢጠፋ ብልሀቱ
ተደብቄ ኖርኩኝ ፥ የመልክሽ ሎሬቱ ።

አብርሀም_ተክሉ ( መርዕድ)

@Abrham_teklu
@Abrham_teklu
@Getamiyan
@getamiyan
👍1
አጭሬ በሲራክ
ሲራክ
ሻሎም ብያለሁ እነሆ
አጭሬን በአጭሬ ፬
➧ የገጣሚ_ሙልጌታ ተስፋዬ( #አያ_ሙሌ)
➧ የገጣሚ_ሔለን ፋንታሁን
➧ የገጣሚ_በረከት በላይነህ
➧ የገጣሚ_ጀማል ሰይድ
➧ የገጣሚ_መስፍን ወንደሰን
➧ የገጣሚ_ሙልቀን ሰ.
ግጥሞች ተካተዋል አንባቢ #_ሲራክ @siraaq
.......................//////.......................
1👍1
ወጋየው ንጋቱ

@Getamiyan
@getamiyan
እኔ ብቻ ቀረሁ
( #ካፒቴን ናትናኤል ጌቱ )

ስንት ሐመሩ "ሐ" ዎች
በሐመር መኪና ፥ ተንደላቀው ሲያልፉ
ስንት ፎሌው "ሀ" ዎች
በወርቃማ ዋንጫ ፥ ውስኪ ሲጨልፉ
ስንት ንጉስ "ኃ" ዎች
ከመሬት ተነስተው ፥ ዙፋኑን ሲወርሱ
እኔ ብቻ ቀረሁ ! ፥ እኔ ብቻ ተከዝኩ
በድሮ ልብና
በድሮ ሽክና ፥ ተከብቤ እንደቆምኩ
ጠላ ትዝታሽን
በፎሌ ተግቼ ፥ እየተንገዳገድኩ
እኔ ብቻ ቀረሁ ! እኔ ብቻ ተከዝኩ!!
ያውና! … ያውና !
አለምነሽ ካሳነሽ
እንደተሳፈሩት ፥ የድሮ መኪና
ጭሱ ቦለል ይላል ፥ የቤቴ ኩሽና
አንቺኮ የለሽም ፥ ቤቴ ምን ነክቶታል ?
ብቸኛው ርስቴን ፥ በቃ አቃጥለውታል !!
እኔ ብቻ ቀረሁ እኔ ብቻ ተከዝኩ
ሰባራ ፍቅርሽን ፥ እንደተመረኮዝኩ
ስንት ንጉስ "ሰ" ዎች
ንጉሱ "ኃ" ዎችን ፥ ሊጥሉ ሲነሱ
ስንት እሳቱ "ሰ"ዎች
አመፅ ለማስነሳት ፥ እሳት ሲለኩሱ
ስንት አለሙ "ዓ" ዎች
በደስታ ሲሰክሩ ፥ ቡጊ ሲደንሱ
አንገቴን ደፍቼ ፥ ከልቤ እያነባሁ
እኔ ብቻ ከፋኝ ፥ እኔ ብቻ ባባሁ!
ካንዲት ተራ ወንበር ፥ ቂጤ ተዘፍዝፎ
ጨቡዴና አማረ ፥ ካስተረፉት ገንፎ
እጄን እየሰደድኩ
በጎዳናው መሀል
ሺዎች ሲቀየሩ እየተመለከትኩ
እንጃ ማን እንደሆን ሽቶ የረጫቸው
ስንት ሐመሯ "ሐ" ዎች ሸክላ ከንፈራቸው
ሊፒስቲክ ተቀብቶ
ጫላ ጩቤ ጥሎ ፥ ዲሞፍተር አንስቶ
አድጎ ተመንድጎ ፥ ማሙሽ ምግብ በልቶ
እኔ ብቻ ከፋኝ
ትውስታሽ ተጠጋኝ ፥ ትዝታሽ ደረሰ
እሽሩሩ ፍቅር
እንባዬ እንደ ካሮት ፥ ቁልቁል ገሰገሰ
እኔ ብቻ ቀረሁ
የቡሄ በአልን ፥ ድፎ ሳላስደፋ
ራሴው ተደፍቼ
ሙስሊም ወንድሞቼ
ተምሩ በቅቷቸው ፥ ታምር ሲመገቡ
መካን ሊያዩ ወተው ፥ ዱባይ ሲያንጃብቡ
የረመዳን ጦሜን ፥ በውሀ እያፈጠርኩ
እኔ ብቻ ቀረሁ ፥ እኔ ብቻ ተከዝኩ
ያውና ያውና
ፊደል በሚመስል ፥ የህይወት ጎዳና
እነ ጸሎቱ "ጸ" ፥ ለስግደት ተደፍተው
ስለታቸው ሰምሮ ፥ ጭፈራ ቤት ከፍተው
ስንት አይናማው "ዐ" ዎች ፥ ባንድ አይናቸው ጠቅሰው
ከቆንጆ ተጣብሰው ፥ ቆንጆ ልጅ ወለዱ
እኔ ብቻ ጎደልኩ ፥ ከደስታ መንገዱ
እኔ ብቻ ዋተትኩ
እኔ ብቻ አዘንኩ
እኔ ብቻ ቀረሁ
ፊደል ከሚመስለው ፥ የህይወት ገበታ
ነይ ታገኚኛለሽ
የዛሬ ሺ አመታት ፥ ካስቀመጥሺኝ ቦታ
እኔ ብቻ ቀረሁ…


@getamiyan
@getamiyan
@getamiyan
👍3
እንቅልፍ እና ሴት

🌹በላይ በቀለ ወያ🌹

በአንድ አልጋ ላይና
በአንዲት ሴት ላይ
ሶስት ዓይነት አንድነት
ህልም-ፍቅር- ህይወት፡፡
ከእነዚህ መሀከል -ህልም የምንለው
ፈቺ የሚፈልግ-አሳሪ የሌለው
የኔናያንቺ ፍቅር የአልጋ ላይ ህይወት ነው
ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው
ፍቅር እንደዚህ ነው
ከራስ አስበልጦ-ሌላ ሰውን መውደድ
ባንድ አለም ተከብሮ-ባንዲት ሴት መዋረድ
ክብር ነው ትርጉሙ
በሴት ልጅ ተማርኮ-ከዙፋን ላይ መውረድ፡፡
ፍቅሬ ገብቶሽ አንደው
ህይወት እንደዚህ ነው
ተኝቶ መነሳት
የታወሰን መርሳት
ያሰሩትን መፍታት
ኖሮ ኖሮ መሞት፡፡
ፍቅሬ ገብቶሽ እንደው
ሴት አና አንቅልፍ ያው ነው፡፡
የትኛውም ፍጥረት ባልጋው ያንቀላፋል
ማንም<<ወንድ ነኝ>>ቢል-በሴት ይሸነፋል፡፡

@Getamiyan
@getamiyan
አይኔ

አይኔ አፈጠጠ ረጅም አብርቶ
በክህደትሽ ቁና ስትሰፍሪኝ አይቶ
ልብሽ ከባእድ እጅ ሰተት ብሎ ገብቶ
በብረቱ ብረት አይኔ ተመልክቶ
ዉዴ ይሄንንማ አታደርግም ከቶ
ብሎ የሚመሰክር
አይቶ በብረቱ ክዶ 'ሚከራከር
ያየውን የሚክድ ያልፈራ ኩነኔ
ይሄ ከንቱ አይኔ ያንቺ ወይስ የኔ?


በ ያሬድ መላኩ


@getamiyan
@getamiyan
👍1
Audio
ከኳረንቲኑ በስተጀርባ

@getamiyan
@getamiyan
@Abrham_teklu
Forwarded from  via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/07/13 11:49:25
Back to Top
HTML Embed Code: