Telegram Web
Audio
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድን

@Abrham_teklu
@Abrham_teklu
#የመዳፍ_ላይ_እድፍ
~~~~ ©#ሲራክ ~~~~~
.
በሀሰት ድባብ ፀዳል
ከአይናችን አንደበት የእምባ ፀበል ደርቋል
ደግሞም ወዲህ ማዶ....
የግንባር ስር ደዌ ኮርቶ ተንፀባርቋል
በውብ መቃ ብዕር በህብረ ቀለም ወዙ
አሉን የሀቅ አለም ከማጣት ልቦና ከመገኘት ጓዙ
በመሸከፍ ወኔ በጮራነት ልሳን ሰፍረው ያልፈዘዙ
ከእጓላዊት ሸራፋ እቅፍ
ከአባትነት የሰማይ ግፍ
ከማስመሰል ተውኔት ጥንስስ
ከልማዳት ድግግም ዳስ
እነሆ ክቡድ ቃል
በራስህ መካከል ላይነሳ ወድቋል
በስንፍና መርፌ ለተጣፈው ሱሪህ ሳትሰጠው መባ
እዮሃ አበባ እዮሃ እዮሃ እዮሃ አበባ
ዘመንህ ተወልዷል አሜኑን ተውና ወየው ብለህ ግባ
እዮሃ ለአንተ ነው....
እነሆ ይሰበር የቀን ሰባራ ጣት
እነሆ ተስፋችን በቀኙ ይንጋላት
ምድር ገጿ ነትቦ በደም ስትጣጠብ
ከሰማይ አክናፋት ስርየት ሲታቀብ
አሜን ይሁን ላንተ ለእኔ ግን ወየው ነው
ፈጣሪ ሚበዛው ምልኪ ሲረክስ ነው
እምነት ሲጎል ነው...
ለአንተ ነኝ ባዩ ሰው አልጋህ ላይ ተጋድሞ ከመሬት ምትተኛው
ወየው ልበል እንጂ እኔማ ምን ቀረኝ
እኛማ ምን ቀረን
ካለ መድረስ ቀረን የትም ወድቀን ወድቀን
የሸከፍነው ሀሳብ እያወላገደን
/°°°°°°° #ሲራክ @siraaq °°°°\
/______~~~~~~________\

@Getamiyan
@geyamiyan
1👍1
°°°°° ፊርማ °°°°°°

©ሲራክ
ያልፈካው አበባ ሲቀጠፍ ለዝና፣
ለለማኝ ይሰጣል ያልታደለው መና።
....

@Getamiyan
@getamiyan
እርቀሽ ሔደሻል

የአዕዋፍ አለቃ የሠላም ምልክት
እርግብ ሆይ ብረሪ እስቲ ዝሪ ህይወት
ዳሩ ምን አግኝተሽ በምን ላይ ልትበሪ
የቱን ሰላም አይተሽ ምንስ ልታበስሪ
አልታይም ብለሽ ዕርቀሽ ሄደሻል
ባንቺ ክንፎች ፋንታ ፅልመት ተክተሻል

ቤተልሄም ሰለሞን

@Getamiyan
👍4
#ፍቅር_ያሸንፋል

በሰጠኸን መሬት ፍቅር መዝራት አምሮን
እድሜ ልክ ቆፈርን
ቆፈርን
ቆፈርን
ቆፈርን
ቆፍረን ስንጨርስ
ቁፋሮ አድክሟቸው
አቅም ያሳጣቸው
ወድቀው ረገፉ
ዝለው ተቀጠፉ።

የሰው ልጅ እጣ ነው
በቆፈረው ጉድጓድ
ሰርክ ይረፈረፋል
ጅምር ጉድጓድ ምሶ
ሳይጨርስ ይረግፋል።

ደግሞም...
በሰጠኸን መሬት
የበቀለው እሾህ
ይለማል ይሰፋል።

የተካዮች ኑሮ
ሰክኖ እየገዘፈ
ሲተከል ያላዩ
ሲተከል ያልሰሙ
ኑሯቸው ይከሽፋል።

ይኸው...
በህይወት መንገድ ላይ
መትከል አያባራም
መብቀልም እንደዚያው።

የሚበቅለው ሁሉ
አሜኬላ ሆኖ
ግራ ቢያጋባንም
አሁንም ግን እኛ
ፍቅር ያሸንፋል
ማለት አይደክመንም።...

© መሁብ ይመር

@Getamiyan
@getamiyan
አስደግማብኝ ነው...
‼️‼️‼️‼️‼️‼️

ለሰባት ጠንቋይ ልጅ ለደብተራ ምርኩዝ
ጠጠር ገበጣ አርጋ ላኬር እጣው እርኩዝ
"ይቺን ያየ" አስብላ
መሬት ልታስገባ ድቼ ልታስበላ
የስር ማሽ እንጉዳይ የኮከብ ቆጣሪ
የነ መገን ቦቃ የነ ጥና ጠሪ
ያንደርቢ ቁጣ የአመድ ላይ ዘዋሪ
የመዳፍ አንባቢ የሞራ መርማሪ
ለመቃብር አፈር መንገድ ላይ ቀጣሪ
መተተኛ ፍቅር ልብ ላይ ቀባሪ
የቀን ስደተኛ አርጋኝ የሌት ዟሪ
አቅሌን እያሳተች ምታስብለኝ እሪ
አስደግማብኝ ነው...
"በርሶ መጀን" ብላ
"ላሜ ላቴ ዱርዱራ
ገደፈሬ ኡብዝራ
ጮርቃ ጩቃ ገጠ ለፌ
ሊስ መላሌ ወአክናፌ"
"በርሶ መጀን" ብላ
የልቤ ሳይበቃት ልቦናየን በልታ
ጨፌ እየነከሰች በጉልበት ተደፍታ
ኩራቴን ልትነጥቀኝ ኮርታ ልትማታ
ተማ'ታም ልትረታ
ጥላየን ጀማው ፊት መሬቱ ላይ ዘርታ
"ያዙልኝ" እያለች በጠንቋይ ቱፍታ
መለመላ ነፍሴን ወናየን ዘርግታ
"ታሞ ይኑር" ብላ እኔን አስወግታ
እርጋታየን ነጥቃ እኔን ከኔ አጣልታ
በደብተራው ምርኩዝ ባስነካችው ኩታ
እንዳነክስላት ጅስሜን አስመትታ
ህልሜን እንዳልሰማ ልቤን አስደምታ
አስደግማብኝ ነው "ናልኝ" ብላ ጠርታ
የሆንኩ አንገት ደፊ የሆንኩት ከርታታ
መለየት ያቃተኝ ቀኑንና ማታ
አስደግማብኝ ነው...
አስደግማብኝ ነው...
ለነ ጥላ ወጊ ለመጫኛ ነካሽ
ለነ አፍዝ አደንግዝ ለዱር ቅጠል በጣሽ
ላውልያ ለጠንቋዩ ለኑግ ቂጣ ቆራሽ
ለመንገድ ገርጋሪ ለውቃቢ ዘራሽ
ለገሃድ ስውሩ ለነ ጽናት አፍራሽ
ለምድር ላየሩ ለየሎስ አጎንባሽ
ለባህር ለየብሱ ለጠቋሪት ደጋሽ
አስደግማብኝ ነው
ወለም ያላለኝን ዘላለም የምታሽ
አስደግማብኝ ነው...


ገጣሚ ሰለሞን ሳህሌ

@Getamiyan
@geyamiyan
👍41👏1😁1
ማህሌተ ገንቦ
(በእውቀቱ ስዩም)

"ባጭር ቀረን" ስንል ፣ እድሜ ላበደሩን
ቀርፀው ላሳመሩን
ለኩሰው ላበሩን
ቺርስ!!
።።።
ፊታችንን ዐይተው እንደተቸገርን ፣
ካይናችን ላወቁ
"ስለማርያም" ብለን
እስክንለምናቸው ፣ ቆመው ላልጠበቁ
ቺርስ!!!
።።።
ወድቀው ለማይጥሉ ፣
ነግሰው ለሚያነግሱ
ነውራችንን ዐይተው ልክ እንደ ድመት ኩስ ፣ ለሚያለባብሱ
ብድር አበድረው ፣ ፈጥነው ለሚረሱ
ቺርስ!!!!
።።፣
ላባ ላረጉልን ፣ የመከራ ሸክሙን
ቀልደው ላሳቁን ፣ተጫውተው ላከሙን
በቸከ ዘመን ላይ ስጋ ለበስ ትንግርት ፣ ሆነው ላስደመሙን
ቺርስ!!!!!

@getamiyan
@getamiyan
👍2
የፀሎት ፉክክር ፩(ልዑል ኃይሌ)
.
ለረጅም ዘመናት
እግዚአብሔር ይስጥልኝ እየተባለበት፤
በእያንዳንዱ ሠው አፍ እግዜር ዕዳ አለበት፤
እያሉ ሠምቼ
ይኸው መጥቻለሁ
እሱ ይስጥህ እያሉ ሲልኩኝ ወዳንተ፤
በል እግዜር መፅውተኝ
ምሰፍርበት አጣሁ
ምድሩን ዘር ዘርተውት
እንኳን ለኔ ቀርቶ ቦታ የለም ላንተ፤
.
ብዛ ተባዛባት
ምድሪቱንም ሙላት ብለህ ስትልከኝ፤
ምን አስበህ ይሆን?
እንደሚታነቅ ሰው ባዶ ኪስ የላክከኝ?፤
.
ፍቃድ ትዕዛዝህን
ላከብር ልበዛ ኑሮ ልጀምር ስል፤
እንዳልከው አልሆነም
አብስትራክት ሆኗል የዚህች ምድር ምስል፤
.
ፈጣሪ ሆይ ፍረድ!
በደላቸው በዛ ትዕግስትህን አይተው፤
የገዛ መሬትህን
እየሸጡልኝ ነው በስንዝር ለክተው፤
.
ወይ ምድርህን ስጠኝ
ወይ ስንዝሩን ቀማ፤
መሬቴን ብቻ ሆኗል
የዚህች ምድር ዜማ፤
እኔ አላማረኝም
መሬትህን ውሰድ በሠው ሳትቀማ፤
19-01-2012 ዓ.ም.

@getamiyan
@getamiyan
@getamiyan
👍5
ሞት አያምም!!!
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
እኖር ብዬ ብታረድም
ለመኖር ስል ብሰደድም
እኖር ብዬ ብዋረድም
ዘጠኜ ሞቴን ብሞተው…
አንዴ እንደመኖር አይከብድም!
መኖር ከመምት አይልቅም
ሞት እንደሕይወት አይጨንቅም፡፡
………………………………
የሞተ ‹‹እሞታለሁ›› ሲል…
በጭራሽ አያውቅም ፈርቶ፡፡
ያልኖረ አያውቅም ሞቶ።
።።።።
መኖር እንጂ የሚያስፈራኝ
መኖር እንጂ የሚያስገፋኝ
መኖር እንጂ የገደለኝ
መኖር እንጂ የበደለኝ
ሞት አያምም ካቆሰለኝ
ምት አያምም ከገደለኝ!

@getamiyan
@getamiyan
👍31
#እያስጠቡ_ጥማት


በኮርማ....
በርችት
ከምንቀበለው ፥ የዘመን መባቻ
ባርቲ ቡርቲ ወሬ ፥ በወገን ጥላቻ
እንደ ሀገር ኖሮ ፥ መሞት ለየብቻ
ምን አውቅልሽ በዝቶ.....
ውሎ ማደር ፈርተን ፥ በማጀት ጉልቻ
ቀናችንን ሳናምን
ጠጥተን ሳንረካ ፥ ጎርሰን ሳንጠግብ
ዛሬ ሳያከትም ፥ ለነገ ስናስብ
የሰቀቀን ጉርሻ ፥ ደጋግሞ እያነቀን
የኑሮ ውድነት ፥ በጠኔ እየናጠን
ዝም ባለ ሰፈር ፥ በፍርሀት ተጣብቀን
በጠራራ ፀሀይ
ጨለማ አውሮን ፥ ምርኩዝ ተስፋ እያጣን
በልተን እንዳልበላ ፥ ስጋት እያከሳን
ካዲስ አመት በላይ
ካዲስ ዘመን በላይ ፥ #ሰላም_ነው_የጠማን !!!

እንጂ!!......ባይከበር ...
ወጉ ሁሉስ..... ቢቀር
አሻፈረን ብንል ፥ ዘመን መች ይቆማል ?
ሲሻው የሳት እራት ፥ አልያ ዜና ገድል
የምንከትብበት
ባለ ሶስት መቶ ገፅ ፥ ብራና ያበጃል
እድሜ እየደረበ ፥ እድሜውን ይፈጃል።


" ባለ 365 ገፅ የሰላም ዘመን ይኩንልን "
#መልካም_በዓል

#አብርሀም_ተክሉ

@Getamiyan
Ethiopia: እዮሃ አበባዬ፣ የአዲስ አመት ልዩ ግጥም በባለቅኔው ሙሉጌታ ተስፋዬ ተጽፎ በአለማየሁ…
እዮሃ አበባዬ፣

የአዲስ አመት ልዩ ግጥም በባለቅኔው

◉ ሙሉጌታ ተስፋዬ ተጽፎ
◉ በአለማየሁ ታደሰ የተነበበ

@getamiyan
@getamiyan
👍1
#የራስ_ሽታ

ዝናቡ ጣለ-ጣለ፣ ራሴን መታ
የራሴ ሽታ
ለራሴ እንዲደርስ፣ የራሴ ፋንታ
ቀመስኩታ!
የ'ኔን።
አጣጣምኩታ!
ጠረኔን።
ኦ! ምን ምን ነው የምሸት?!
እሸት እሸት?………ማደለሁ።
ናርዶስ ናርዶስ?……ማደለሁ።
አደስ አደስ?…………ማደለሁ።
ብቻ እጥማለሁ!
ኦ! ጣፋጭ የደስ ደስ
መቼም ነፍሶ አያውቅም
ወደፊትም አይነፍስ
እንዲህ ያለ ጣዕም
በልዩ ሚቀመስ
ኦ!… ለዛች ጣፋጭ ይድረስ!
ይድረስ ላንተም ጣፋጭ
ያውድህ ሽታዬ
ቀምሰህ የምትወደው
ካንተ የተለየ
ሃ!
እኔ እንደጣፈጠኝ ያንተን ተቀብዬ።
ብቻ እንደልማድህ፣ አሽትተህ ስትወደው
"ከርቤ ነህ!… ሎሚ ነህ!" የምትለውን ተው!
ራስ ራሴን ነው፣ ዝናቡ የመታኝ
ራስ ራሴን ነው እኔ የምሸተው።

@getamiyan
@getamiyan

#መዘክር ግርማ
👍3
እንኳን አደረሳችሁ ፤ እንኳን አደረሰን !

በዓሉ የመተሳሰብ ፣ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የይቅርታ ይሆን ዘንድ እንመኛለን !

መልካም በዓል !
@getamiyan
ቀረሽ እንደዋዛ
•┈┈•✦•┈┈•
እንደ ድመቶቹ
የትም እንደሚያድሩት
እንደ ስልክ እንጨቶች
እንደ ዛፍ ሃረጎች
እንደ ቤት ክዳኖች
ብርድ አቆራመደኝ
ስጠብቅ ስጠብቅ
"ትመጫለሽ ብዬ ሳይ ማዶ ሳይ ማዶ
የልጅነት ዓይኔ ሙዋሙዋ እንደ በርዶ"
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስ ቆጥር
ትመጫለሽ ብዬ ሰዓቱን ስቆጥር
ትመጫለሽ ብዬ ባዝን ባንጎራጉር
ትወጫለሽ ብዬ በበራፍሽ ብዞር
ብርድ አቆራመደኝ
የመንገድ መብራቶች አይተው አፌዙብኝ
ውርጩ ቀለደብኝ
ጨለማው ሳቀብኝ።
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ያውቃሉ
መስኮቶች ጨልመው
ቤቶች ተቆልፈው
ከተማው ሲተኛ
አይተዋል ያያሉ
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ያውቃሉ።
-------------------------------
🖌 ገብረክርስቶስ ደስታ

@Getamiyan
@getamiyan
👍5
የ # ኢሬቻ ግብዣ
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ኢልማ ገልማ
አባ ገዳ ርቱእ ጀማ
ብፁእ ጀማ
ለካ አንተ ነህ
አባ ገዳ ኢልማ ገልማ
ያደ ኦሮሞ ሻማ
ዋቃ ገዲ ነማ ኦሊን ሱማ
አከ ሱማ
የተሰኘዉ እንደ አክሱም
የተባልከዉ ፍፁም ጀማ
ለካ አንተ ነህ
አገ ኦጋ
ጂገ ሎጋ
አባ ሰርዳ
አባ ገዳ
አባ ፈርደ ነበልባሉ
እም ቅድመ ኦሪት ባህሉ
ያኢ ቢያ አባ ቃሉ
የማይቀለበስ ቃሉ
ለካ አንተ ነህ
ሴራ አርካ ኦገ ገዳ
የአድባር ዋርካ
ያዴ እናቴ
ያዴ እስቴ
ያዴ አተቴ
ያዴ እቴቴ
ያቴ ሆራ የኩሽ ነዶ
አባ ቦኩ አከም ኢዶ
በአናትህ ፀሃይ ከለቻ
የምትጠልቅ አንተ ብቻ
የካም ኢደ ኢዶ ምድር
ተነባቢ የአስር ሚስጥር
አባ ወሮ አባ ወራ
አባ ባሮ አባ በራ
የጅቡቲም ጀበ ዲሾ
የመቅዲሾም መቀ ዲሾ
የነሙንቴሳ ካም በልአ
እንደ ብራቡ ከምፐላ
መነ ደላ አከ መንደላ
መቀ ደላ አከ መቅደላ
የፊላኒ ካኖደላ
የምትሰኝ የምታሰኝ
የጎና ቤት አባ ወራ
የላሊ ቤት ላሊበላ
በጎፈሬህ ስሪት ላባ
አዶ አዶየ ዉብ ቀዘባ
አዳ የከለቻ ተሸላሚ
ያዱ ግንባር ተቀዳሚ
የአዲስ ዘመን መፀዉ አደይ
አዳ...አዱኛን እልል እሰይ
የምታሰኝ...የምትሰኝ
አዱ አዱኛ
አባ ቢሌ
የአካ ኪሌ
የአባ ቢሌ
ለካ አንተ ነህ
ገዳ ገዳም
የአለም ሰላም
ገዳ ቢሊሱማ ሳቃ
ፈካ ጉራቻ አካ ዋቃ
የመፀሃፍት አምላኩ አኒ
ያለበሰህ ድርብ ካኒ
የጥቁር ፈርኦን ልሳን
የአዴ አዳ ፀሃይ ብርሃን
የአዱሊስ አዱኛ ኪዳን
አባ ገዳ አባ በአል
የቅድመ አክሱማዊት ቃል
የአስርቱ በሮች መሰላል
የማለዳ ንጋት ፀዳል
የኦሩስ ኦሪሳ ተምሳል
ለካ አንተ ነህ
አገ ኦጋ
ጂገ ሎጋ
ያኢ ቢያ አባ ቃሉ
የማይቀለበስ ቃሉ
ርቱእ ጀማ
የተባልከዉ አባ ሱማ
እንደ አክሱማ
ያደ ኦሮሞ ሻማ
አባ ገዳ ኢልመ ገልማ
ለካ አንተ ነህ::

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

ሰናይ ቅዳሚተ ሰንበት!



@getamiyan
@getamiyan
👍2
°°°ምኞት ደመና ነው!
© ሲራክ
የትነት ወዝ ገላ - የሰማዩ ግርግም ፥
ምኞት ደመና ነው - የጤዛ ጥርቅም።

@Getamiyan
°°°° ስውር ቁጣ
© ሲራክ ወንድሙ
.
ዋ!....ሲባል በድራር - ዋ!... ሲባል በዜማ ፥
ዋ!... ሲባል ዋ!... ስትይ - ዋይታሽን ሳልሰማ፥
ፍቅርሽ ሞቷል ብለው - በእምባሽ መንኜ ፥
ሰማዩ ላይ ታየው - ደመናውን ሆኜ ።
@siraaq
...............

@getamiyan
👍1
#ከትናንት_የተጫረ_‘ሳ ት...

እንደሰበዓሰገል ፡ ኮከብ ፡ ምሪት
እንደመከተል – የሰጠሽኝ ፡ ምልክት
የዐይንሽ – የቃልሽ ፡ ምሥጢር
ለዛኔው ፡ እኔ ፡ ቢጠጥር፤
ሳይገባኝ
ስቀቴ ፡ እንደመራኝ
ወርቅሽን ፡ በሰም ፡ ፈክሬ
ሲገባኝ
እሳቱ ፡ ተረፈኝ ፡ ዛሬ።
ለካ…
ወደድኩሽ ፡ ብዬ ፡ ስመናቀር
ሞትኩልህ ፡ ብለሽኝ : ነበር።

---- // ----
ገጣሚ፦ መ ዘ ክ ር ፡ ግ ር ማ

@getamiyan
@getamiyan
👍21
Audio
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

@Abrham_teklu
@Abrham_teklu
👍1👏1
2025/07/12 14:37:00
Back to Top
HTML Embed Code: