Telegram Web
ጠጥቻለሁ ... መራር ኃጥያት
በልቻለሁ ... እርጉም ክፋት
ወጥቻለሁ ... ከሰው ተራ
ተስያለሁ ... እንደ ካራ

ማረድ ... የጽድቅ አንገት
መቁረጥ ... የጾም አንጀት
መበጠስ ... የጸሎት ክር
መጉረድ ... የምጽዋት ስር

ግብሬ ሆኖ የተጣባኝ
የቁም ሞትን መኖር ቀባኝ

ድንግል ማርያም የለሁም በእውነት
ካንች ተለይቶ መች አለ ህይወት

አጥቢኝ የጾም ወተት ኃጥያትን ማርከሻ
ልጉረስ ከ'ጅሽ ፍቅር ክፋት መደምሰሻ
እናቴ እያልኩኝ ልጥራሽ እንደ ሰው
ውለጅኝ በምልጃሽ ሞቴን ልደምስሰው

#ኤልዳን
@eldan29

@getem
@getem
@getem
ዛሬ
እየዳነ ኼደ
የመፅሃፍ ምርቃት በዋልያ መፀሃፍ

@getem
ምሽት በረንዳ ላይ
(በእውቀቱ ስዩም)

አገር ምድሩ መሽቶ
ሌቱ ምጣድ ሆኖ ፥ በኮከብ ተሟሽቶ
የጎዳናው መብራት ፥ጨለማው ላይ ሲገን
ከመስኮት አምልጦ ፥የወጣ ወጋንን
ሳር ቅጠሉን ሲያሳይ
አጥብቄ ስፈልግ ፥የእለት ያይኔን ሲሳይ
የሌት አይኔን ሲሳይ

በኩርማን ገላዋ፤ እራፊ ደርባ
የራሷ ሻጭ ሆና ፤ለሸመታ ቀርባ
በሌት ይፋ ሆና፥ በቀን ልትደበቅ
ያልቀጠረችውን ፥የምትጠባበቅ
አንዲት ሴት እያየሁ
አሰላስላለሁ ፤

“ አብረዋት ያደጉ፤ ብጤዎቿ ሁሉ
በድሜና በውበት እሷን የሚያክሉ
ተድረው እንደ ሴት፥ ተከብረው እንደ ሰው
የባሎቻቸውን ደረት ተንተርሰው
ፍቅር ሲያጣጥሙ
ወይ በንቅልፍ ሲሰጥሙ
ይች ወገን አልባ
የሌሊት አበባ
በቀትር ተኝታ ለውድቅት የነቃች
የቱን ፍሬ በልታ ለዚህ ፍዳ በቃች ?”

እያልሁ አስባለሁ፥



ደሞ ከደጃፌ ትንሽ ማዶ ርቆ
የመሸበት ለማኝ ፤ መንገዱ ዳር ወድቆ

በግልጥ ይታየኛል
“ ረፍትን ላክልኝ ፥ወይ እንጎቻህን ጣል
በራብ እና በንቅልፍ ሰው እንዴት ይቀጣል"
የሚል ይመስለኛል ፤

በረንዳ ላይ ቆሜ፥ በሌሊት ስምሪት
ከመስኮት በወጣ፥ የብርሀን ቅሪት
አይቼ ማልዘልቀው
ያገሬ ጎዳና የት ላይ ነው የሚያልቀው
መከራና ውበት የሚያፈራርቀው::

@getem
@getem
@getem
በሁለት ዋልታ ተከብቤ
ምረጥ አሉኝ
ከአንዱ እንዲያርፍ ልቤ
በሰሜን ትላንት
በደቡብ ነገ
አንዱላይ እንድገኝ
ለምን ተፈለገ?
ትላንት ትላንቴ ነው
ነገ ደሞ ምኞት
እኔን የናፈቀኝ
የዛሬ ህይወት!

              

   
Follow my IG & Tiktok @be_Olyon

       ✍️ Olyon
                       
           
              አስተያየት (@be_Olyon)


     @getem
                   @getem
                                  @getem
( አያሌው ሞኙ )
=============

ተቆጥሮ የማያልቅ
ለፍቅር ገዳሟ
እልፍ ነው መናኙ
ምን አገኝ ብለህ ነው
ዛሬም ተኮራምተህ
የምትጠብቃት .... ወይ አያሌው ሞኙ

"አለሷ እረፍት ምኔ"
ብለህ የደከምክላት
"አለሷ ዓለም ምኔ"
ብለህ የመነንክላት
በል እርምህን አውጣ

ያላንተ ዓለም አላት !

(እውነት እየሸሹ
አይመጣማ ንጋት...)

@kiyorna

@getem
@getem
@paappii
[የጅራፍ ጠበቃ]
_
እነ ተረት አዋቂ  ...
(እነ ጸጉር ሰንጣቂ....)
«ጅራፍ እራሱ ገርፎ ፥ እራሱ ይጮኻል»
(ይሉሃል....፤)
እንዲህ ሲነግሩህ — ምን ይሰማኻል?

አይተህ አይደል ወይ....!?
(ምስኪኑን ጅራፍ....)
ቁልቁል ከመሬት  እያላተመው
— እረኛው ጠልፎ ፤
እንዴት ይባላል...!?
«እራሱ ጮኸ — እራሱ ገርፎ » ?
²
(ጅራፉ ጥፋት የለበት....)
ሀሰት ነው —·· ውንጀላ ክሱ  ፤
(ገራፊ ካልሰነዘረው....)
መች ያውቃል —·· ገርፎ በራሱ!?
³
ሳትፈቅድ ተገፈህ
(ሳትወድ ተጠልፈህ...)
"ጅራፍ ሁነኝ" መባል....
(ለዱላ መታጨት....፤)
መግረፍ ነው? – መጋጨት?

(ግርፊያ በሚል ሰበብ..)
ጎርባጣ ጀርባ ላይ— ሄዶ በማረፉ ፤
ከበሬው ገላ እኩል — ያመዋል ጅራፉ ።

(ቢጮኽ አልፈርድበት......)
___
By @Bekalushumye

@getem
@getem
@paappii
የእግዜር ፍርድ


አንድት ቆንጆ
በእግዜር እጆች የተሳለች   ድንቅ ስራ
ቆዝማለች
ተክዛለች  ለብቻዋ  ከሰው መሆን ብትፈራ

እኔን የገረመኝ
የእሷ አይደለም  ይልቅስ የግዜሩ
የነፍስ ምግብ
አርጎ ፈጥሯት  ለማስከፋት መሞከሩ

እግዜር ጨካኝ  ፍርድ አያውቅም
ውበት የሰጠ   ደስታ አይነጥቅም
ከሀዘን ቢሰውራት እንጂ   ቢከልላት
ዋስ ቢሆናት እንጂ    ቢሰያስጠልላት
ውበትን ጎድቶ  ከሰው አያርቅም
እግዜርስ አንዳንዴ  ፍርድ አያውቅም

By kerim

@getem
@getem
@paappii
መገረም
"""""""""
እንገረም እንጂ
የመገረም ዘመን
ሁሌ እያስደነቀን፤

ጀንበር ለሊት ወጥታ
ስታደምቀን ብትውል
ጨረቃ እኩለ ቀን...

ፈገግታዬ ጠልቆ
እየኮረኮረ
ሀዘኔም ቢያስቀኝ፤

የተስፋን መሰንቆ
እየገዘገዝኩኝ
ትዝታዬን ብቀኝ...

የሾምኩት ሲገፋኝ
የሻርኩትን ብመኝ
እያነቀኝ ሲቃ፤

ምን እፈይዳለሁ
በእቴ እሜቴ ሀገር
መገረም ነው በቃ...!

By Abrham F. Yekedas

@getem
@getem
@getem
Audio
መቼ ትመጫለሽ??
በዔደን ታደሰ እና ኤልሻዳይ(ኤል ቶ)
ተፅፎ እንደቀረበ
@topazionnn
@getem
@getem
እስኪ ምን ላርግልሽ

ካንቺ የተፀናወተኝ ማፍቀሬ እንዲገባሽ
ከአይኖችሽ የያዘኝ መውደዴ እንዲታይሽ
ንገሪኝ የኔ ዓለም እስኪ ምን ላርግልሽ
ከምድር እስከ ሰማይ ወጥቼ ወርጄ ስልጣን ተበድሬ
በዓለም ሚኖሩትን ሕዝቡን ሚገዙትን ነገስታትን ሽሬ
ለዘውድሽ እንድትሆን ከሰማየ ሰማይ ፀሐይን አውርጄ
ግርማሽ እንዲያስፈራ መጎናፀፍያሽን በእሳት ጋርጄ
ከሰው ሁሉ እንድትልቂ ተከብረሽ ተነግሰሽ
ዉበትሽ እንዲታይ እንዲጎላ መልክሽ
ጨረቃን አውርጄ ልሰራት ካንገትሽ
ኮከብ አዋቅሬ ልብስሽን ልስራልሽ
ከእሳት እና ከዉሃ  ዙፋን ልገንባልሽ
ስምሽ እንዳይረሳ ዓለም እንዲያስታውስ ትውልድ ሁሉ እንዲያውቀው
ቃላት እየመረጥኩ ግጥም እየፃፍኩኝ መልክሽ ልሳለው
ማፍቀሬ እንዲገባሽ መውደዴ እንዲታይሽ
ንገሪኝ ፍቅሬ ሆይ እስኪ ምን ላርግልሽ ?


                    ዘረ-ሠናይ
         
@Prince_Zeresenay

@getem
@getem
@getem
በደረቅ ሌሊቱ
ሰው በሌለበቱ
ሲጋራ ለኩሼ
ህመም ተንተርሼ
ፍቅርን ሳስተነትን
በጭሱ መካከል አገኝሽ ይመስል
ስባትል ስኳትን
ያለፉ ሌሊቶች ፍቅርሽ የገዛቸው
እግዜር ይቁጠራቸው።


by kerim

@getem
@getem
@getem
[ለሻማ ሕይወቶች....]

🕯️
፩.

ሻማዬ ...ሞቆሻል አይደል?!
ላብሽ — ይንጠፈጠፋል ፤
እንዳላበርድሽ (ጨነቀኝ)
የቤቴ ብርሃን — ይጠፋል ።

["ይነጋል" ግን — አልልሽም...
አጉል ተስፋን— አልሰጥሽም ።]

አውቃለሁ በደጄ በራፍ·· —
የጠዋት ጮራ ይሰለፋል ፤
ያኔ ግን ከጨለማው ጋር —
ሕይወትሽም አብሮ ያልፋል ።

🕯️
፪.
(አንተም አንተም የኔ ወዳጅ....)
የሠው ልጅም በጨለማ....
ቢለኮስ – ቢቀልጥ – ቢቃጠል ፤
(እንባ ላቡ ቢንጠለጠል...)
"ይነጋል " አትበለው — እረፍ !
(ጀንበር 'በራሁ' — እስክትል...)
ማለቁ አይቀርም ሲሸረፍ ።

[ሰም ለበስ ነውና — ሠውም እንደ ሻማ እስከ ንጋት ድረስ — ያልቃል በጨለማ ።]

ከቻልክ "እፍ" በለው....
`ሳቱን አብርድለት ፤
ላንተ ብርሃን ተብሎ...
— ማለቅ አይወድለት ።
🕯️|
___
By @Bekalushumye

@getem
@getem
@getem
ጠብም


አምላክ ሊታረቀ
ባንቺ ሊባርከኝ

ሊያመጣሽ ነው መሰል


ሰማዩ ዳመነ
ጨለማው ገነነ
ልክ አንደረተቱ
አይቀርም መንጋቱ
ቀኑ ሲጨላለልም
ብርሀን ሲጠልም
ሰማይ ሲደማምን
አላህን ልለምን
በስግደት በዱዓ
በፆም በጁምዓ
መሬት ተንበረከኩ
እናም አንቺን ለመንኩ

ለመንኩት ለመንኩት
ባንቺ አከበርኩት
አንቺን እንድሰጠኝ
አንድ አንቺን እንዲመፀወተኝ


ተረቱስ ተለለ
ጠብም ያለ የለ

ደመናው ለዝናብ
ጨለማው ለብርሀን
ቦታውን ለቀቀ
ተረቱም አለቀ

መስገዴ በከንቱ
ጠብም ያለ የለ
ካላህ በማውራቱ

አላህም እንዳንቺ
አላህም አንደሰው
ጨካኝነት ባሰው

ጨለማን  ሲያነግስ ጭካኔ
በግርማሽ  ሲፈራረስ  ወኔ
እኔም ጠፋሁ ከኔ ።


by kerim

@getem
@getem
@getem
እስኪ ምን ላርግልሽ

ካንቺ የተፀናወተኝ ማፍቀሬ እንዲገባሽ
ከአይኖችሽ የያዘኝ መውደዴ እንዲታይሽ
ንገሪኝ የኔ ዓለም እስኪ ምን ላርግልሽ
ከምድር እስከ ሰማይ ወጥቼ ወርጄ ስልጣን ተበድሬ
በዓለም ሚኖሩትን ሕዝቡን ሚገዙትን ነገስታትን ሽሬ
ለዘውድሽ እንድትሆን ከሰማየ ሰማይ ፀሐይን አውርጄ
ግርማሽ እንዲያስፈራ መጎናፀፍያሽን በእሳት ጋርጄ
ከሰው ሁሉ እንድትልቂ ተከብረሽ ተነግሰሽ
ዉበትሽ እንዲታይ እንዲጎላ መልክሽ
ጨረቃን አውርጄ ልሰራት ካንገትሽ
ኮከብ አዋቅሬ ልብስሽን ልስራልሽ
ከእሳት እና ከዉሃ  ዙፋን ልገንባልሽ
ስምሽ እንዳይረሳ ዓለም እንዲያስታውስ ትውልድ ሁሉ እንዲያውቀው
ቃላት እየመረጥኩ ግጥም እየፃፍኩኝ መልክሽ ልሳለው
ማፍቀሬ እንዲገባሽ መውደዴ እንዲታይሽ
ንገሪኝ ፍቅሬ ሆይ እስኪ ምን ላርግልሽ ?


                    ዘረ-ሠናይ
         
@Prince_Zeresenay

@getem
@getem
@getem
አህያ

ጀርባው ይዞ ትልቅ ጭነት

አንገት ደፍቶ ሁሉ ሰው ፊት

አገልግሎት እንዳልሰጠ

በውጭ ገንዘብ ተለወጠ።

አንገቱ ላይ አርፎ ቢላ

ለእርድ ቀርቧል ነው እንዲበላ።
📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

       ✍️ @BEGITIMENAWGA

@getem
@getem
@getem
🤔
.
.
ግራ መጋባቴ እንደዉ ግራ ገብቶኝ፤
ስቋጥር ስፈታ እጅጉን አሳስቦኝ፤

ባስብ ባሰላስል ከልቤ አጣሀት፤
ግራ የገባኝን ግራ ገብቶኝ ተዉኩት።
..........................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
አንዳንዴ ይታክታል
እልክ አስጨርሶ
ያዝኩ ያልከው ይርቃል
ካጠገብህ ደርሶ፤
ነገን ያስጠላኻል
የፊትህን እዳትኖር
እንዳከፍት አድርጎ
የተዘጋብህን በር፤
በምናብህ ይጭራል
የጨለማን ፅልመት
ያደላች እስኪመስልህ
የተወችክ እይወት፤
ጭንቅህን ሲያበዛው
አሳብህ ተዛብቶ
ክርናፍ ክርናፍ ይልሀል
የገዛኸው ሽቶ፤
ታዲያ ጊዜ ሲጠምብህ
እድል ካንተህ ስትርቅ
ከማንም አይደለም
ከራስህ ተታረቅ፤
         ያልፋል!!!#M.G
@getem
@getem
ለማታዉቀኝ 1 ✍️በዔደን
<unknown>
ለማታዉቀኝ...
ገጣሚ እና አንባቢ ዔደን ታደሰ
ክፍል 2 ይቀጥላል...........
@topazionnn
@getem
@getem
/በኔ ብሶ/,,
የተንከራተትኩት ፍዳዬን የበላው
መስሎኝ እንጂ ፍቅርን ካንቺ የማገኘው፤
ላንቺም የኔ ልፋት ምንም ያልመሰለሽ
ላትረጂኝ ነገር ለምን ልለምንሽ፤
ጥሬ የቻልኩትን መልስ ካንቺ ባጣ
ተውኩት መከጀሉን ወዳንቺ ልመጣ፤
እርሺው የኔን ስቃይ ይሁን አትዘኚልኝ
ድካሜም አይሰማሽ ከቶ አታስቢልኝ፤
ምናልባት አንድ ቀን ያንቺ ተራ ደርሶ
እንዳልገኝ ፍሪ ኃላ በኔ ብሶ
◈መሳይ ግርማ
@getem
@getem
2024/10/01 11:42:40
Back to Top
HTML Embed Code: