Telegram Web
ከጊዜ ጋ ጊዜ
ከቦታ ጋ ቦታ
ከሁኔታ ሁኔታ

ሆኖ የተበጀ
ሆኖ የተሰፋ
የሰው እጣ ፈንታ

በሆኑት ይፀናል።
በሳቱት ይፈርሳል።

ስ'ተት ልክነት ግን
በሰው ስፍር ሳይሆን በራስ ይመዘናል።
አሁን የቆሙበት
በመጡት መንገድ ልክ ሐዘን ወይም ደስታ ሆኖ ይከሰታል።

By Jhonny Habte

@getem
@getem
@paappii
..
ለገላዋ እራፊ ፡  ብጣሽ አልገዛሁም፤
እረዥም ታሪኳን ፡  ቁጭ ብዬ አልሰማሁም
ምኞት ፍላጎቷን ፡  ለይቼ አላወኩም
የእግሯን ወለምታ ፡ አሽቼ አላዳንኩም፤
አሞሌ ጭንቀቷን ፡ በሳቅ አላሟሟው፤
ያመቃትን ስቃይ  ፡ ጠጋ ብዬ አልሰማው

ከድርብርብ ውጥረት
አስሮ ከደበቃት፤
ሽሮ ለመላቀቅ  ፡ ቀልዴ ለሚበቃት
ማድያት ሽፍታ  ፡
ሲያጨላልም መልኳን፤
ተራራ ሆኖብኝ  ፥
"ምነው?" ማለት እንኳን
ፈገግታ እድሜዋን ፡ ጊዜ ሲከረክም፤
የትም እንደማትሄድ ፡ የኔን ብቻ ሳክም
ለእንስፍስፍ አንጀቷ ፡ ላይሆን መቀነቻ
ወኔዬም ፣ ጀብዱዬም ፡
"ወዳታለው" ብቻ።


ይቅርታ.. እማ።

@mikiyas_feyisa
@getem
@getem
...ልመንህ ወይ
ላፈቅርህ ነዉ አተወኝም
ልመንህ ወይ አትከዳኝም
ገብሬልን ማርያምን በልና ማልልኝ
በልብህ ዙፋን ላይ ቃልኪዳን ግባልኝ
አልተውሽም ብለህ በላ በላኮ ማልልኝ
አምኜህ ልቀመጥ ቀልቤ ይረፍልኝ
ደግመህ እንደማተወኝ ልቤ ይወቅልኝ
በላ በላ በላኮ ማልልኝ


By

@Hanipia

@getem
@getem
@Hanipiagetem
ጥቁር ልብ
.
.
ዉስብስብ ቀለሞች የበዙበት ስዕል፤
በዝብርቅርቅ ገፁ የጎደፈ ምስል፤

በሰአሊዉ መንፈስ ልክ እንደ ስእሉ፤
እልፍ ሽንቁራቶች በህይወቱ አሉ፤

ፀሊም ትዉስታዎች ክፉ ትዝታዎች፤
ድነዉ የማይድኑ የትናንት ህመሞች፤

በሰዓሊዉ መንፈስ ልክ እንደ ስዕሉ፤
እልፍ ሽንቁራቶች በህይወቱ አሉ፤

ከነፍሱ ተጋምደዉ ዘመን አስቆጠሩ፤
አብረዉ ተባብረዉ ልቡን አጠቆሩ።
.............................................
✍️ዔደን ታደሰ
@ediwub
@getem
@getem
የተቀነጨበ

ጨዋታ ከሳቅሽ
ከለዛ አንደበትሽ ተደማምሮ ሳለ
ከተፈጥሮሽ እንጂ ከልብሽ ምን አለ?
.
.
.
እንጃልን እኛማ
ላወጋልን ሁሉ
ለሳቀልን ሁሉ ሞትን ካልንማ።

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
ሲኖር የሚገርመኝ
አይደለም እንደ ሟች
ይሄ ሁሉ ተጓዥ ፣ ይሄ ሁሉ ዘማች ፤
ሁሉም ጥሬ አሳሽ ፣ ስብስብ ነው የዶሮ
አነር ያድነዋል ፣ እንደ ዱር መንጥሮ።
ከስብስቡ መኃል ፣ ባለቀን ሲነጠቅ
ሌላው ዶሮ ይጮኃል ፣ ፈርቶ በመሳቀቅ።
ሲሞላ ግን አፍታ
እየው አበክረህ
ወንድሙን የሸኘ
ያን አልቃሻ ዶሮ
ጥሬ ይናጠቃል
ዛሬም እንደ ዱሮ።
አይገርምም ?
አይደንቅም?
የሞት ማግስት ወጉ
አነርን ይረሳል የዶሮ ዝንጉ።
🐓

(ሚካኤል አ)

@getem
@getem
@getem
በሰዉ ዘንድ መገፋት፤
ደግ ፊት መነሳት፤
እስከ ጥግ አዉቃለሁ.....
ክፉ ደግ ያሳለፍን፤
ጎረቤቶቼ እንኳን፤
ያለፍኩ እንደሆነ ድንገት በበራቸዉ፤
እንደዚህ ይሉኛል ቃል እያጠራቸዉ፤
ምኑን ቢያቀምሷት፤
በምን ቢመርዟት፤
አልባሷን ቀዳዳ ጎዳና የወጣች፤
ከሰዉ ተነጥላ ብቻዋን ያወራች፤
እርሷ እኮ እንዲህ ነች እያሉ፤
ምኑንም ሳያዉቁ ፍርድ ይበይናሉ፤
ፍፁም ሰላምና ጤንነትን ሽቼ፤
ራሴን አገኘሁ ከገዳም ሰንብቼ፤
እናም አካላቴ እዉነት ናፍቀኸኛል፤
በክንድህ መሸሸግ እቅፍህ ያሻኛል፤
ትዝ ይልሃል አይደል......
የኔ ልብ ካንተ ያንተም ልብ ከኔ፤
በፍፁም ተጋምዶ በፍቅራችን ቅኔ፤
ለሰርጋችን ድምቀት እቅድ ስናወጣ፤
ነጠላ አጣፍተን ተሳልመን ስንመጣ፤
ትዝ ይልሃል አይደል......
ለዚህ ያደረሰኝ ቤተሰብ ጓዳዬ፤
ስንት የደከምኩበት ፍቅርና አላማዬ፤
ትናንት በጉያዬ በእጄ የነበረ፤
ተስፋ ያደረኩት መና ሆኖ ቀረ።
ማነዉ ተጠያቂ ልቤ ለመድማቱ
እዉነተኛ ደስታ ከእኔ ለመጥፋቱ
ማነዉ ተጠያቂ?????
......................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
እንደ ተበዳይ አታልቅሺ
ለበደል ነበር አመጣጥሽ
ፀባይ አመልሽን ማጣፈጥሽ
እስስት ውስጥሽን መለወጥሽ

እንደ ንፁህ ሰው "እሪ" አትበይ
ባገር በሰፈር አታሳጂኝ
የሳልሽው ብረት በላሽ እንጂ
እቅድሽ ነበር ልትጎጂኝ

የዋህ አልነበርሽም እንዳሰብኩሽ
ጅል አልነበርኩም እንዳሰብሺኝ
አባዝተሽ ከኔ ለመውሰድ ነው
ሽሙንሙን ፍቅር የሰጠሺኝ

ፍቅርሽን ይዤ ዝም ብልሽ
ከእብድ አየሺኝ ከወንበዴ
ክፉ ሰው ሆንኩኝ ልትሄጂ ስል
ቀድሜሽ እኔ በመሄዴ

እሰይ ደግ አረኩ
የኔ አስመሳይ
ብትቀበሪም ፡  አላምንሽም
እምባሽ ላይ ሳቅሽ ይታየኛል
ውሸት አትፈሪም እየማልሽም
ድራማሽ ይብቃ ተነቃቃን
ከበቀል ጠጪ ከእልሁም
መለየት መርሳት እችላለው
እንደ ወንዶችሽ አይደለሁም!

እንዲያ ነው ብለሽ አውጂልኝ
ይሄ ጥቅስ አለ ከኔ ዘንዳ
"ደግ ነው በዳይ የሚያስለቅስ
  ብፁዕ ነው ክፉ  የሚጎዳ!"

እሰይ ..
እንኳን ጎዳሁሽ
© @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii
ሲሸሹኝ ስጎትት ሲርቁኝ ስጣራ፤
ሲሄዱ ስከተል ሲዘጉኝ ሳወራ።

አሁንስ ዝም አልኩኝ ልቤን ደካከመው፤
ሁለት እየሆነ አንድ ነው ያልኩት ሰው።

ብቻ በመንገዴ፥

ከነሳቸው ሠላም ከነሳቸው ጤና እኔ መከተሌ፤
ለበደለኝ ሁሉ ለበደልኩት ሁሉ ይቅርታ ነው ቃሌ።

ሄጃለሁ ከእንግዲህ በቃ ለልከተል🚶‍♀➡️🚶‍♀➡️🚶‍♀➡️🚶‍♀➡️🚶‍♀➡️

ጦቢያ

@getem
@getem
@getem
የቱ ጋር መሰለህ…
(ሚካኤል አ)

መባቻ ጅምርህ
የነፍስህ ድባቴ
ውድቀት እንግልትህ
ያኔ …
ባሽትሪ መያዣ ፣ በሲጋራ ብናኝ
በርጋፊ ቅጠል ፣ ድባቧ የሚቃኝ
በዛች ጠባብ ክፍል
ምጥን መሰብሰቢያ
ዙሪያህን ሰው ሞልቶህ
ቀንህን ማጣፊያ
ለአፕላይ ግብዣ የተዘረጋች ጣት
በሚግተለተል ጢስ ፣ ሰንቃልህ እሳት
እሷን ለመቀበል ስትፈግግ ባ’ክብሮት
የሰበብ አስባብ ጢስ
ቀረ ቤትህን ወርሶት።
የቱ ጋር መሰለህ?
በቀይ መብራት ፍካት
በቅልቅል ሽቶ አዲስ አይነት ክርፋት
በጭላጭ ብርጭቆ ተላኮበት ድራፍት
ከስፒከር ማህፀን ሙዚቃ ተለቆ
ጭፈራ እና ዳንሱ አንድ ላይ ተዛንቆ
የቀይ ሴት ታፋ ዓይንህ በስስ ሰርቆ
በምራቅህ ድርቀት ጉሮሮህ ተጨንቆ
ጠቅሰህ ስትጠራት
ያቺን የሞት ብልቃጥ
ከባቷ ፈልቅቀህ ዕፅዋን ስትቀምሳት
በገላህ ፍሰሀ መቅደስህን ናድካት ።
የቱ ጋር መሰለህ?
የልጅነት ልምድህ
ከሰንበት ቤት ገዳም
ምልልስ ብርታትህ
በሀይኪንግ ሲቀየር
የያሬዱ ወረብ
በእስክስታ ሲዛወር
ሳትቆም ለፀሎት
ሳይንስ ከእምነት ልቆት
ኒቼ ቦታ ሲወርስ የየኔታን መንበር
የነፍስህ ቁዘማ መንደርደሪያ ነበር።
ትዝ አለህ?
ዘር መራጭ ስትሆን
የደም ሴል መንጣሪ
ጆሮህ ዳባ ሲለብስ
ለፍጥረት እንግልት
ለህፃናት ጥሪ…
መንገድህ ሲሳለጥ
በ V 8 መኪና
ዝርግ አስፓልት ሲመስልህ
ጉርብጥብጥ ጎዳና ፤
ስቆልኛል ስትል ጥርሱን የነከሰ
እንባው አንሸራሽሮህ ጌታ ዘንድ ደረሰ።
ምላሹስ የከፋው መቼ ላይ ሆነና?
ጥሬ እየቆረጥክ ሆድህ ሲመረመር
እስቲም ሳውና ገብተህ ፊትህ ሲጭበረበር
በድሎትህ መኃል
ገላን የሚያኮስስ የእሾህ ስንጥር ነበር።
ትዝ አለህ?
መኝታህ በምቾት ተሞልቶ በአጀብ
እንቅልፍህ ሲናጠብ?
ትዝ አለህ?
በውድ ቀለም ቤቶች ልጆችህ ሲማሩ
ከግብረገብ ታዛ ተናንሰው ሲቀሩ?
ትዝ አለህ?
የጉያህ መልካም ሴት
የአጥንትህ ፍላጭ
አሁን ከምን ጊዜው
ሆነችብኝ ምላጭ?
ብለህ ስትቆዝም …
እንዲያ ነው አይዋ
ግፍ ፅዋው ሲሞላ
በትሩን አይመርጥም።
ትዝ አለህ?
ታወሰህ?
የቱ ጋር መሰለህ?
የተፈታው ውሉ
የጎደልክ ከሙሉ
ኧረ ስከን ሲሉ
ከዕድሜ የተማሩ
የጋሽ ውቤን ምክር
የእመት ጉሌን ዝክር
ረግጠህ ስትበር…
ስትሻገር ፣ ስጥስ
የምስኪናን ድንበር
የዛሬ ውድቀትህ ፣ በግጥም ሊነገር
ክንፍህ የተመታው ይሄን ጊዜ ነበር።
ትዝ አለህ?

አዎን እሱ ጋር ነው!

@getem
@getem
@getem
በቅንድቧ ባይኗ በኩል
አልተቀባም አንዳችም ኩል
አልደረበች ማዳመቂያ አልፈጠራት በጎደሎ
ያኖረልን በግሩምታ ንፁህ ልቧን አስመስሎ
የሰው ሰራሽ ቅርፀ ብዙ
         አሎዞራትም በአካሏ
በክፋት የማትኖር
          ትሁት መልሰ ቃሏ

ያቹት......እርሷ!


ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

@getem
@getem
@getem
ቤትህ…
በመኃልይ ልባስ
መልኩን የደበቀ
መልከኛ እዬዬ ገባ ተሸሽጎ
ለደጅህ የላኩት
እንዳማረ በቃ ላደባባይ ሸንጎ።

በተመስገን መዳፍ
በቡራኬ ከንፈር
ወደሰማይ ያልኩት ተቀላቅሎ ካ’ፈር
ለጓዳዬ አይበቃም እንኳንስ ለጠፈር።
አንተው በጣቶችህ
ጣራ ስር ከቀረ ዋይታዬ ስር አንሳኝ
ወይም ጸሎት ንሳኝ።

ዘመን ቢተራመስ እድሜ ቢቀናጣ
እንባዬ ቢጋለጥ ደስታዬ ቢሰጣ
አደባባይ መውጫ ግጥም ብቻ አልጣ።

@getem
@getem
@paappii

By Yadel Tizazu
አካሄድ

የስንፍናን ጡዘት
ካንሸዋረሩበት
ከአካሄዱ ጀርባ
ሀፍረትን ቢመርጡም
ወደው ለሄዱበት
ነፃነት አይቀሙም
...
ግና................
ተዘክረው ቢመጡም
እንደአካሄዳቸው
ምህረትን ፍለጋ
ዳር ዳር ቅኝታቸው...
ልዝቡን ሹክሹክታ
ሽቅብ ቢያደምጡም
ባልኖሩት ንሰሃ
ፍቅርን አያቀልሙም።

           By ኢያሱ ከበደ
           መስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም
            @josheyasuu

@getem
@getem
@getem
የኔ ዓለም!
(ሚካኤል አስጨናቂ)

እንዳንቺ 'ሚጣፍጥ - አንጀት የሚያረካ
ጣፋጭ የለም ለካ!
ጥዑም ናቸው ያሉኝ ማርና ቸኮሌት
ካንቺ ሲነፃፀር ፣ መረሩኝ እንደ ሬት።
.
ማርያምን !
.
ከድምፀትሽ ልቆ - 'ሚሰማ ሙዚቃ
ከአንባሰል ከባቲ ከብሉዝ ትዝታ
ወድያም ከብሉዙ ፡ ደግሞም ከአፍሪቃ
አንድም የለም በቃ!
.
ማርያምን!
.
እንደውም ፣ እንደውም
ካንቺ ጋራ ስሆን ሀዘን ጭንቄን ሽሮ
የደስታ ወሰኔን ፣ አለቅጥ አንሮ
የሚገርመኝ የለም ከዓለሟ ተፈጥሮ።
.
እውነት አይገርመኝም !!
ይኸው ለምሳሌ...
ያቺ የሰማይ ሳህን
ምንድናት ጨረቃ?
እንዲያ ስትሞገስ
ተስላ ፣ ተፅፋ
በሁሉ ተደንቃ...
አንቺን ያየሁ ጊዜ
ዓይኔ ውስጥ ከሰመች
ተዋርዳ ፣ ተንቃ።
.
ማርያምን...
የቱ ኮሜዲ ነው የትኛው ቀልደኛ
እኔን የሚያደርገኝ የወሬው ምርኮኛ?
ደግሞ ካንቺ በላይ
እኔን ለማሳሳቅ ማነው የሚደፍረው ?
ባንቺ ጨዋታ ነው
የተደበቀውን.. . ጥርሴን የምገልጠው።
.
ማርያምን !
እንደውም ባጭሩ.. .
አሁን ይሄ ግጥም
የቃላት ጥርቅም
እጅግ መሳጭ ሆኖ አንባቢው ቢያደንቅም
ካንቺ ግን አይበልጥም።
.
ማርያምን።

@getem
@getem
@getem
የመዳፌን መሃል
ነክቶኝ መሃል ጣቷ
አሰፈረችብኝ~'ማይነቀል ቆሌ
ከአያት ቅድም አያቷ
(ክ...ፋ...ቷ!)
አልል ጥፍሯ ወጋኝ
ተቆርጧል ባጭሩ
ምን ብትቋጥርበት
ጣቷ መናዘሩ
ሀጥያት ማስዘርዘሩ...
ነፍስ ማስገበሩ...
የእንጨት አፍሮ አይገቤ
የመቅደስ ስር እጣን
ጩህ ጩህ እንደሚለው
ትዕቢተኛ ሰይጣን
እሪ ልል ስነሳ
ለአፍታ በነካችኝ
ጉሮሮ እንዲከዳኝ
ከንፈር ደገመችኝ

(ጉድ እሷ!)

መቼስ በሀገር ታሪክ
እኛ በምናውቀው
እንጂ ነጭ ሲወር
ምድሩን ሲያስጨንቀው
መዳፉን ተስሞ
እስኪጠፋው አለም
ለጠላቱም ቢሆን
እጅ ያልሰጠ የለም

(እንኪ እጅ ጀብኣ በይ!)

ዘማርቆስ
@wogegnit

@getem
@getem
@paappii
የወራት ዘመኑ ቀኑ ተቆረጠ
የማህፀኗን እቅፍ በጊዜ አሳቦ
ሆዷን ረገጠ

በ 18 ምሽት
ለ 19 አጥቢያ ቀኑ ከረፈደ
ማርያም
ማርያም..... ሲባል ዮኒ ተወለደ
🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂
🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳
🥳@getem
🥳@getem
🥳@getem
🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳🥳

12:35 PM

🎂@yonatoz🎂
ዮኒ
ኣታን
ገጣሚው
ማንም ያላየውን
ማንም ያልፃፈውን
በፊት ያልነበረ …
ስንኝ ለማዋቀር
መወጠን ጀመረ ።
ሆኖም ግን አንድ አጣ
ያልተፃፈ በሰው
ሁሉን ቢያሰላስል
ቢያወጣ ፣ ቢያወርደው
አንድም አልነበረ
ሌላው ያልጀመረው ።
አሰበ ገጣሚው
አወረደ ፣ አወጣ
አዲስ ነገር ልፃፍ
ብሎ የጀመረ
ገጣሚ ግን አጣ።
እናም ይሄን ጊዜ
የሱን ክታብ ሲቃኝ
ቀለሙን ሲያዋድድ
ከዝርጉ ወረቀት
'አዲስ ነገር ልፃፍ'
የሚል ነበረበት ።
ስንኙ አበቃ
ብዕር ተሰለበች
ታጠፈች ወረቀት
ግጥም ቀን ወጣላት ፤
አዲስ ነገር ፃፈ
አዲስ ነገር ልፃፍ
ብሎ በመነሳት ።

(ሚካኤል አ )

@getem
@getem
@getem
2024/10/01 05:40:12
Back to Top
HTML Embed Code: