Telegram Web
እንኳን ለሰባተኛው_ሳምንትና ለኒቆዲሞስ፤ በዓል በሠላም አደረስዎ
#የዕለቱ_ምንባባትና_መዝሙራት
ሰባተኛው ሳምንት ኒቆዲሞስ ይባላል፤ በዚህ ሳምንትም ይህ ይታሰብበታል፡፡
‹‹ኒቆዲሞስ››፤ * አይሁዳዊ ሲሆን ከፈሪሳውያን ወገን የነበረ ነው
* በኢየሩሳሌም በሀብት ቢሉ በዕውቀት እንዲሁም በሥልጣን የአይሁድ አለቃ ነበር፡፡
* ማታ ማታ ጌታችን ዘንድ እየተገኘ ይማር ነበር፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ እንዲህ አስቀምጦልናል፦
፨ ‹‹ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ ‹‹መምህር ሆይ እግዚአብሔር ከእሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህ ተዓምራቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን›› አለው፡፡
⊚ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።
፨ ኒቆዲሞስም፦ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው።
⊚ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። #ከሥጋ_የተወለደ_ሥጋ_ነው#ከመንፈስም_የተወለደ_መንፈስ_ነው።›› /ዮሐ. ፫፥ ዘ፩-፲፭/
፨ለምን በሌሊት ይመጣ ነበር?
⊚ አይሁድ ‹‹ማንም ከእኛ ወገን የሆነ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ከሆነ ሀብት ንብረቱ ይወሰድ፣ በቤተመቅደስ አይግባ፣ መሥዋዕት አይሠዋ›› ብለው ነበርና አይሁድን ፈርቶ፥ ሀብት ንብረቱን ወዶ፥ እንዳይታወቅበት በሌሊት ይመጣ ነበር፡፡
⊚ በሌላ በኩል ደግሞ የቀን ልብ ባካና ነው፤ ዓይን ብዙ ያያል፥ ሐሳብ ይበታተናል፡፡ በተሰበሰበ ልብ ለመማር፤ በተጨማሪ ‹‹ሊቅ ነኝ›› እያለ ‹‹እስከ ዛሬ ትምህርት አልጨረሰም›› እንዳይሉት በሌሊት ይመጣ ነበር፤ ይህንንም የቀድሞ ሊቃውንት "ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ፤ አኮኑ አጽባሕት እምነ አጽባሕት የአቢ።" በሚል ጕባኤ ቃና ቅኔ አራቅቀውታል፤ ይህ ቅኔም ለተማሪዎች የቅኔ ሀሁ ነው።
⊚ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንኳን ለመማር የመጣውን እራሱ እየሄደ ያስተምር ነበርና ኒቆዲሞስ ምንም በሌሊት ቢመጣም ማወቅን ፈልጎ ነውና ስለዳግም መወለድ (ስለጥምቀት) በእግዚአብሔር ልጅ ስለማመንና ስለ ጽድቅ ስራ በዝርዝር አስተምሮታል፡፡
⊚ ኒቆዲሞስ ከአርማትያው ዮሴፍ ጋር በመጨረሻው ቀን በዕለተ ዐርብ ጌታችንን በስቅለቱ ጊዜ፤ ከመስቀል ላይ ሥጋውን ለማውረድና ገንዞ ለመቅበር ቀድሞ ተገኝቷል፡፡ /ዮሐ. ፲፱፥፴፰/

ከኒቆዲሞስ ሕይወት የምንማረው፡-
፩. #ትሕትና፦ ኒቆዲሞስ በትምህርት፣ በሹመት፣ በባለጸግነት የአይሁድ አለቃ ሲሆን፤ አለቅነቱ ግን ከጌታ እግር ስር ቁጭ ብሎ እርሱ ተገኝቶ ለመማር አልከለከለውም፡፡ (የቅኔውን ትርጕም ከመምህራን ይጠይቁ)
፪. #አለማመካኘት፦ ከመጀመሪያ ሰዎች ከአዳምና ከሔዋን ጀምሮ ሰዎች በምክንያተኝነት በአመፅ መንገድ ይጓዛሉ፡፡ ኒቆዲሞስም ወደ ጌታ በመቅረቡ የጸሐፍት ፈሪሳውያን አድማና ግርግር ታላቅ እንቅፋትና ምክንያት መሆን እንደሚችል ያውቃል፡፡ ነገር ግን ይህ ምክንያት በእግዚአብሔር ፊት እንደማያዋጣ አውቆ የሚያዋጣውን አደረገ፡፡
፫. #ጥበብ፦ በክርስትና ጉዞ ውስጥ ጥበብ የመጀመሪያ ቦታ ትይዛለች፡፡ ኒቆዲሞስም ጕዞውን በጥበብ አደረገ፡፡ በሌሊት ያደረገበት ምክንያት፡- ራሱ መምህር ሆኖ ሌላ ትምህርት አስፈለገው ብለው ሌሎች እንዳይሰናከሉበት፣ የመዓልት ልቦና ስለሚሰበሰብ በቂ ዕውቀት ለማግኘት፣ መንፈሳዊ ፍሬ ለማፍራት በመዓልትም በሌሊትም ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንዳለብን ለማጠየቅ፣ ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ያሉ ነፍሳት በሲዖል ይገኛሉ ሲል፣ በመዓልትም በሌሊትም ብትፈልጉ ትገኛለች ሲል ነው፡፡ በእውነት ግሩም ጥበብ!
፬. የተነገረውን አምኖ በመቀበሉ፡- ጸሐፍት ፈሪሳውያን ብዙ ምክንያቶች እየደረደሩ የጌታን አምላክነት አምኖ መቀበል ሲያቅታቸው እርሱ ግን ጌትነቱን ለመቀበል ጊዜ አልወሰደበትም፡፡
፭. ለእውነት መመስከር፡- እነርሱ ሲክዱ ጌታ ላይም ትርፍ ቃል ሲናገሩ፤ በድፍረት መክሰሳቸውን እየነገራቸው የጌታችን አምላክነቱን በግልጽ ይመሰክር ነበር፡፡
፮. ጽንዓት፡- ብዙዎች በመከራ ጊዜ ላይለዩት ቃል ቢገቡም መጨረሻ ላይ ያኔ በመከራ ሰዓት ከመስቀሉ ሥር ሊገኙ የቻሉ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ኒቆዲሞስም በዚች ሰዓት ያንን መከራ ታግሶ በጽነዓት ከዮሴፍ ጋር የጌታን ሥጋ ከመስቀል አውርደው በአዲስ መቃብር ቀብረውታል፡፡
ምንጭ፤ የዮሐንስ ወንጌል ትርጓሜ
፠፨፠ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፠፨፠
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
የ666(ኢሊሚናቲ) እና ሌሎች ያልተነገሩ ምሥጢራት
በዚህ ቻናል በዓለማችን ውስጥ ስላሉ ድብቅ ምሥጢር ስለሆኑ
ቦታዎች
ፍጥረቶች 🐾
ሀሳቦች
እና አካላት
የሚያትት ሲሆን ኢትዮጵያም በነዚህ ትላልቅ ምሥጢራት ውስጥ ያላትን ትልቅ ቦታ እንመለከታለን።
https://www.tgoop.com/yaltenegeru_mistroch
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
________
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!

ጥያቄ #ስለ_ሰሙነሕማማት_ማብራርያ

#መልስ እግዚአብሔር በፈቀደ መጠን እንደሚከተለው አቅርበናል
👇 👇 👇 👇
በዓቢይ ጾም ከሰርከ ሆሳዕና ጀምሮ እስከ ትንሳኤ ሌሊት ያሉት ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላሉ፡፡ ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ፤ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡ በእነዚህ ዕለታት ውስጥ የተለያዩ ትውፊታዊ እና ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ክንዋኔዎች ውስጥ አለመሳሳም፤ አክፍሎት፤ ቄጤማ ማሰር፤ ጥብጣብ፤ ጉልባን እና ሕጽበተ እግር ይገኙበታል፡፡

አለመሳሳም
በሰሙነ ሕማማት ምእመናን መስቀል እንደማይሳለሙት ሁሉ መጨባበጥ፤ መሳሳምና የትከሻ ሰላምታ መለዋወጥን አይፈጽሙም፡፡ ሰላምታ የማንለዋወጥበት ምክንያት አይሁድ ጌታን ለመስቀል ሰኞ እና ማክሰኞ መከሩ አልሰመረላቸውም፡፡ ምክራቸው የተፈጸመው ረቡዕ ነው፡፡
ስለዚህ አይሁድ እያንሾካሾኩ እንስቀለው . . እንግደለው ብለው ይማከሩ ነበር፡፡ ያንን ለማስታወስ ሰላምታ አንለዋወጥም፤ መስቀልም አንሳለምም፡፡ ሳምንቱ የክፋት ምክር የተመከረበት እንጂ የፍቅርና የደስታ ሰላምታ የታየበት ባለመሆኑ ይህንን በማሰብ ሰላምታ አንለዋወጥም፡፡
ይሁዳ ጌታን በጠላቶቹ ለማስያዝ እኔ የምስመው እርሱ ነው ያዙት ብሎ በሰላምታው ምልክት ሰጣቸው፤ ይህ ሰላምታ አምሐ ቅድሳት /የተቀደሰ ስጦታ/ አይደለም፤ ተንኮል የተሞላበት እንጂ፡፡ የዲያቢሎስም ሰላምታ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሄዋንን ሰላም ለኪ ብሎ ነው ያታለላት፡፡ ስለዚህ ይህንን ወቅትና ሁኔታ ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት የሰላምታ ልውውጥ አይደረግም፡፡

ሕጽበተ እግር
የጸሎተ ሐሙስ ዕለት ጌታ በፍጹም ትሕትና የደቀመዛሙርቱን እግር ያጠበበት፤ ከሐዋርያት ጋር ግብር የገባበትና የክርስትና ሕይወት ማሕተም የሆነውን ምስጢረ ቁርባን ያከናወነበት ዕለት ነው፡፡
ሕጽበተ እግር ጌታችን እናንተ ለወንድማችሁ እንዲህ አድርጉ በማለት የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት የተሰጠ ምሳሌ ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም፤ መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም፤ ይህን ብታውቁ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ /ዮሐ.13፡16-17/ በማለት ትሕትናውን አሳይቷል፡፡
ጌታ በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር ሲያጥብ እኔ መምህራችሁ ስሆን እግራችሁን ካጠብኳችሁ አርአያን ሰጥቻችኋለሁ፤ እናንተም የወንድማችሁን እግር ታጥቡ ዘንድ ይገባል፡፡ ነገር ግን ከእናንተ አንዱ ለሞት አሳልፎ ይሰጠኛል አለ፡፡ ደቀመዛሙርቱም ማን ይሆን? አሉ፡፡ ጌታም ኅብስት ቆርሼ፤ ከወጡም አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው አላቸው፡፡ ደቀመዛሙርቱም ደነገጡ፡፡ ይሁዳን ማመልከቱ ነበር፤ ለጊዜው ግን አልገባቸውም፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሐዋርያቱን እግር በማጠብ ትሕትናን ካስተማራቸው በኋላ፤ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በመስጠት የኦሪትን መስዋዕት የሻረው እና መስዋዕተ ሐዲስን የሠራው በዚሁ ዕለት ነው፡፡

ይህንን ዕለት በማስታወስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ እስከ ቀሳውስት ያሉት አባቶች በያሉበት አጥቢያ /ደብር/ በመገኘት በመዓርግ የሚያንሷቸውን የካህናት፤ የዲያቆናት እና የምእመናንን እግር ያጥባሉ፤ የሚያጥቡትም የወይራና የወይን ቅጠል በውኃ በመዘፍዘፍ ነው፡፡

አክፍሎት
በሰሙነ ሕማማት ዕለተ ዓርብ ከስግደት በኋላ ምእመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ለቁመተ ሥጋ ቀምሰው እስከ እሁድ /የትንሳኤ ሰዓት/ ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል፡፡ ከአርብ እስከ ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙዎች ያከፍላሉ፡፡ አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ ይህም እመቤታችን፤ ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታን ትንሳኤ ሳናይ እህል ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው፡፡
ይህንን ትውፊት አስመልክቶ ሄሬኔዎስ፤ አውሳብዮስ የተባሉ ጸሐፍት፤ ሐዋርያት በሰሙነ ሕማማት ከደረቅ ዳቦ እና ከትንሽ ውኃ በቀር እንደማይመገቡ፤ ከሐሙስ ጀምረው እንደሚያከፍሉም ጽፈዋል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ሐዋርያት ሌሎቹንም እንዲያከፍሉ እንዳሳሰቡና ከሐሙስ ጀምሮ ያልተቻለው ቢያንስ ከዓርብ ጀምሮ እንዲያከፍል ማዘዛቸውን ጽፈዋል፡፡ የእኛ ቤተ ክርስቲያን ትምህርትም ይኸው ነው፡፡
.................👇👇👇👇..............ይቀጥላል
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
.........👆👇👇👆........
________

ጉልባን
ጉልባን ከባቄላ ክክ፤ ከስንዴ ወይም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ የጉልባን ትውፊት እስራኤላውያን ከግብፅ ተሰደው በሚወጡበት ጊዜ በችኮላ ስለነበር አቡክተው ጋግረው መብላት ያለመቻላቸውን ሁኔታ ያመለክታል፡፡ ያን ጊዜ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መብላት፤ ንፍሮም ቀቅለው ስንቅ መያዝ ተግባራቸው ነበር፡፡ ይህን ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ቂጣና ጉልባን በማዘጋጀት በዓሉ ይታሰባል፡፡
በጸሎተ ሐሙስ ይህንን መሠረት በማድረግ የሚዘጋጀው ጉልባን እንዲሁም ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ጨው ውኃ የሚያስጠማ በመሆኑ የጌታን መጠማት ያስታውሳል፡፡ ይህ ትውፊታዊ ሥርዓት ከእስራኤላውያን የመጣ ሲሆን፤ በኢትዮጵያም አብዛኞቹን የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ሥርዓቱ ዛሬም ይታሰባል፡፡
ጥብጣብ
በሰሙነ ሕማማት ዕለት ዓርብ የስቅለቱ መታሰቢያ ነው፡፡ ምእመናኑ በሰሙነ ሕማማት የሠሩትን ይናዘዛሉ፡፡ ካህናቱም በወይራ ቅጠል ትከሻቸውን እየጠበጠቡ ቀን ከሰገዱት ስግደት በተጨማሪ ሌላ ስግደት ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሳፅ ምሳሌ ነው፡፡ ጥብጣብ የሚደረግለት ሰው በሕማማት ወቅት የፈጸመው በደል ወይም ኃጢአት ካለ ይህንኑ በመናገር የስግደቱ ቁጥር ከፍ እንዲል ይደረጋል፡፡
ሕዝበ ክርስቲያኑ በዕለተ ስቅለት ሲሰግድ፤ ሲጸልይ፤ ሲያነብ ከዋለ በኋላ ሰርሆተ ሕዝብ /የሕዝብ መሰነባበቻ/ ከመሆኑ በፊት በወይራ ቅጠል እያንዳንዱን ምእመን ጀርባ ቸብቸብ መደረጉ የጌታን ግርፋት ለማሰብ ነው፡፡ ማቴ.27፡26፤ 19፤1-3/
ቄጤማ
በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለ ዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሳኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር ጌታ በመስቀሉ ሰላም እንደሰጠን እና ትንሳኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም ገጸ በረከት ያቀርባሉ፤ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሰሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡
በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው፤ ቃጭል ሲያቃጭሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሳኤውን ለሚናፍቁ ምእመናን ትልቅ ብስራት ነው።

ይቆየን
ወስብሀት ለእግዚአብሔር!

________
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
............የቀጠለ.........
#በሕማማት_የማይፈቀዱ

በዚህ በሰሙነ ሕማማት ሳምንትም ቅደስት ቤተ ክርስቲያን ለየት ያለ የአገልግሎት ሥርዓት ሠርታለች:: ከጸሎተ ሐሙስ በቀር ቅዳሴ አይቀደስም፡ ይህ ብቻም አይደለም፡ የዘወትር የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት የሆነው ሥርዓተ ጥምቀተ፤ ክርስትና፣ ሥርዓተ ፍትሐት፣ ሥርዓተ ማኅሌት፣ ሥርዓተ ተክሊልና ሌሎችም የተለመዱ አገልግሎቶች አይካሔዱም፡፡

👉በመስቀል መባረክ፣ ኑዛዜ መስጠትና መቀበል፣ እግዚአብሔር ይፍታህ ማለት የለም፡፡
በአጠቃላይ ከዓመት እስከ ዓመት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አማካይነት ለምእመናን ይሰጡ የነበሩ መንፈሳውያት አገልግሎቶች አቁመው ወቅታዊ በሆኑ ማለትም የጌታችንን ሕማሙን፤ መከራውን፤ መከሰሱን፤ መያዙን፤ ልብሱን መገፈፉን፤ በጲላጦስ ዐደባባይ መቆሙን፣ መስቀል ላይ መዋሉን፤ ሐሞት መጠጣቱን እና ሌሎችንም ለኀጢአተኛው የሰው ልጅ ሲባል የተከፈለውን ዕዳ በሚያስታውሱ አገልግሎቶች ይተካሉ፡፡

እነዚህንም ሥርዓታዊና ምስጢራዊ የሰሙነ ሕማማት አገልግሎቶች እስከ ቀዳም ሥዑር ድረስ እንዴት እንደሚከናወኑ በአጭር በአጭሩ እንመለከታለን፡፡

ከትንሣኤ በፊት ያለው ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡ ይኸውም በነቢዩ ኢሳይያስ ነስአ ደዌነ ወፆረ ሕማምነ፣ በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንም ተሸከመ፤ በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን፡፡ /ኢሳ. 5፤34-36/ ተብሎ በመንፈስ ቅዱስ ትንቢት የተነገረው ቃል ተፈጸመ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ሳምንት ውስጥ ለድኅነተ ዓለም ሲል በአጭር ቁመት፣ በጠባብ ደረት ተወስኖ የተቀበለውን ጸዋትወ መከራ ለማስታወስ የወጣ ስያሜ ነው፡፡
በሰሙነ ሕማማት መስቀል መሳለምና እርስ በእርስ መሳሳም የለም፡፡ ይህም ይሁዳ ጌታን በመሳም አሳልፎ እንደሰጠው ለማሰብ ነው፡፡
በዚህ ሣምንት ውስጥ ያሉት ዕለታት ስያሜያቸውና በየአንዳንዳቸው ዕለታት የተፈጸሙትን ድርጊቶች እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡

ሰኞ
ጌታችን የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ በምትባል መንደር ያድራል በማግስቱም ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ /ማር. 11፣11-14/ ቅጠል ያላትን በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፣ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት፡፡ በዚህ ምክንያት ይህ ዕለት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፡፡

👉በለስ የተባለች
ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች፣ ሃይማኖትና ምግባር ናት፡፡ ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፡፡ እስራኤልን ሕዝበ እግዚአብሔር መባልን እንጂ፣ ነቢይነት፣ ካህንነት፣ መሥዋዕት አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡ በመርገሙ ምክንያት ትንቢት ክህነት መሥዋዕት ከቤተ እስራኤል ጠፉ፡፡

👉በለስ ኦሪት ናት
ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና ፍሬ ባንቺ አይሁን አላት፤ ድኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡ በአዲስ ኪዳን የድኅነት ዘመንም ተተካች፡፡

👉በለስ ኃጢአት ናት፡፡ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሠሩት ደስ ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፡፡ በለሷም ስትረገም ፈጥና መድረቋ፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡

ከዚህ ቀጥሎ ወደ ቤተ መቅደስ ሔደ፤ ቤተ መቅደስ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምሥያጥ /የንግድ ቤት/ ሆኖ ቢያገኘው፤ «ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች... እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት» ማቴ.21፣13 ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸዉ፣ ገርፎም አስወጣቸዉ፣ ይህም የሚያሳየዉ ማደሪያው ቤቱ የነበርን እኛ የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ አንጽሖተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ሰኞም ይባላል፡፡
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

👉#ማክሰኞ
የጥያቄ ቀን በመባል ይታወቃል፡፡

ምክንያቱም ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፡፡

ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታት በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? የሚል ነበር ይህንስ ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው? አላቸው፡፡ እነርሱም ከሰማይ ነው ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም? ይለናል፡፡ ከሰው ነው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፤ እንደ መምህርነቱም ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ እኔም አልነግራችሁም አላቸው፡፡ ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም፡፡ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነው እንጂ፡፡

🌿በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስም ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል፡፡ ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ፣ መክሮ መመለስ እንደሚገባ ሲያስተምር ነው፡፡

👉#ረቡዕ
ይህ ዕለት የምክር ቀን ይባላል፡፡

የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሓፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር የጀመሩበት ወይም የያዙበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት በመሆኑ ብዙውን ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱን የሚያደንቁ ስለነበር ሁከት እንዳይፈጥር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ /ማቴ. 26፤1-5፣ ማር. 14፤1-2/

የሐዲስ ኪዳን ካህናት ምእመናን በዚህ ዕለት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው ከእህልና ውኃ ተለይተው፣ መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው፣ የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ፣ ስለዚህ ታሪክ የሚያወሳውንም በማንበብ እስከ ኮከብ መውጫ በጾም፣ በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡

🌿መልካም መዓዛ ያለው ቀንም ይባላል፡፡ ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት ከእንግዲህ በኃጢአት ተጎድቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚሁ መልካም ሽቶ ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የሞላ ሽቱ ይዛ በመሄድ በጠጉሩ /በራሱ/ ላይ በማርከፍከፍ ስላቀረበች ነው፡፡

🌿የእንባ ቀንም ይባላል፡፡ ይህም ይህችው ሴት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፡፡ /ማቴ. 26፤6-13፣ ማር. 14፤3-9፣ ዮሐ. 12፤1/

❄️ ከዚህም እያንዳንዳችን ልንማር የሚገባን ነገር አለ፡፡ ይኸውም የራሱን ኃጢአት በማሰብ ማልቀስና ራስን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ነው፡፡
💐.............👇👇👇...............💐
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
👉#ሐሙስ
ከስቅለትና ከትንሣኤ በፊት ያለው ሐሙስ በቤተ ክርስቲያናችን የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡

🌿ሕጽበተ እግር ይባላል፡፡

ይህ ስያሜ የተሰጠው ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ምክንያት ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህንን ለማስታወስ ዛሬ ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝቡን ኃጢአት እጠብ ሲሉ በቤተ ክርስቲያናችን የተገኙትን ምእመናን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ሲያጥቡ ያረፍዳሉ፡፡ /ዮሐ. 13፤4-15/

🌿የጸሎት ሐሙስ ይባላል፡፡

የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ የሚደክም ሥጋን የተዋሐደ አምላክ ፍጹም ሰው መሆኑን ለመግለጽና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ በጌቴ ሴማኒ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ነው፡፡ /ማቴ. 26፤36፣ ዮሐ. 17፤1/

🌿የምስጢር ቀንም ይባላል፡፡

ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷል፡፡ ይኸውም ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፤ እንካችሁ ብሉ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው፤ ከእርሱም ጠጡ፡፡በማለት እኛ ከእርሱ ጋር አንድ የምንሆንበትን መንገድ ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡

በዚህ ዕለት ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ የሚቀደሰውም በለሆሳስ ሲሆን እንደ ቃጭል በመሆን የሚያገለግለውም ጽናጽል ነው፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ ሲመጡ ድምፃቸውን ዝግ አድርገው በለሆሳስ እየተነጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ ነው፡፡ በቅዳሴውም ኑዛዜ አይደረግም፡፡ ሥርዓተ ቁርባን ግን ይፈጸምበታል፡፡ ይህም ጌታችን የሰጠውን ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን ለማሰብ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ተዘጋጅቶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ይኖርበታል፡፡

🌿የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡፡

ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳ ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ /ሉቃ. 22፤18-20/ ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው ደሜ የሚሆን የአዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱም ጠጡ በማለቱ ይታወቃል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓማዊ ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት መሆኑን በማሰብ የቃል ኪዳኑ ፈጻሚዎች ጠባቂዎች መሆን እንደሚገባን እንማራለን፡፡

🌿የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡፡

ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ራሱም ጌታችን መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆቼ ግን ብያችኋለሁ በማለቱ /ዮሐ.15፤15/ ከባርነት ነጻ የወጣንበት ቀን መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ክርስቲያን ከኃጢአት ባርነት በመራቅ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን በቅድስና መምራት ይኖርበታል፡፡ እርሱ ጠላቶቹ ስንሆን ወዳጆቹ አድርጎናል፡፡ /ማቴ 26፤17-19/

🌿አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአትክልት ቦታ ስለ ጸለየ፡፡

👉#ዕለተ ዓርብ

🌿የስቅለት ዓርብ ይባላል

የዓለም ሁሉ መድኃኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ መዋሉን ለማስታወስ ነው፡፡ /ማቴ. 27፣35/፡፡

🌿መልካሙ ዓርብ ይባላል

ይህም የሚያስገነዝበን ከስቅለተ ክርስቶስ በፊት አንድ ሰው ሲያጠፋ ተሰቅሎ ይሞታል፡፡ በሮማውያን ሕግ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት ነበር፡፡ በዚህ ዕለት የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምሕረት ምልክት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያብሎስ ድል መንሻ ስለ አደረገው፣ በሞቱ መልካሙን ሕይወትን ስለአገኘን መልካሙ ዓርብ ተብሏል፡፡

ጌታችን ለዓለሙ ያሰበውን ቤዛነት ሊፈጽም በመስቀል ላይ መሰቀሉ የሚታሰብበት ነውና ለስቀለቱ መታሰቢያ የሚሆን አጎበር ተዘጋጅቶ ከርቤ እየታጠነ ስቅለቱ የሚመለከቱ ምንባባት ሲነበብና ሲሰገድ ይዋላል፡፡ የሰው ልጅ በሙሉ በእግረ አጋንንት ረግጦ ከፈጣሪው ተጣልቶ ለ5500 ዘመን በጨለማ መኖሩን ለማስታወስም መንበሩ ታቦቱ በዚህ ቀን በጥቁር ልብስ ይሸፈናሉ፡፡

ዲያቆኑም በቤተ ክርስቲያን በመዞር የሚያሰማው የቃጭል ድምፅ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለቅሶ
አንድም ዋይ ዋይ እያሉ የተከተሉት የኢየሩሳሌም ሴቶችን ሙሾም ምሳሌ ነው፡፡ /ሉቃ. 23፤31/

በዕለተ ዓርብ ነፍሳት ከሲኦል ወጡ፡፡ አንቀጸ ገነት ተከፈተልን፣ ርስተ መንግስተ ሰማያት ተመለሰችልን፤ አባታችን አዳምም ከፈጣሪው ጋር ታረቀልን በማለት ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃዶ እያልን የተድላ፣ የደስታ ምልክት ወይም መገለጫ የሆነ ልምላሜ ያለውን ቆጽለ ሆሣዕና ወይም ቄጤማ ግጫ ይዘን የምሥራች እንባባላለን፡፡ /ኤፌ. 2፤14-15/ ወዘእንበለ ምሳሌሰ ኢተናግሮሙ፣ ያለ ምሳሌ አልተናገረምና እንዳለ /ማቴ 13፤34-35/ በኖኅ ጊዜም ርግብ ሐጸ ማየ አይኅ፣ ነትገ ማየ አይኅ፣ የጥፋት ውኃ ጎደለ፣ አለቀ እያለች ቈጽለ ዕፀ ዘይት ይዛ ለኖኅ አብስራዋለች፡፡ /ዘፍ. 8፤8-11
ይቆየን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
ክርስቶስ ተንሥአ እምሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሠሮ ለሰይጣን አግዓዞ ለአዳም፤ ሰላም እምይእዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሰላም።
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ አደረሰን።
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
🎙የመጋቤ ሀዲስ እሸቱ ድንቅ ንግግር🎙

መጋቤ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ  ዳላስ ውስጥ በነበረ አንድ ሀይማኖታዊ የምክክር መድረክ ላይ ዘመኑን የመሰሉ ጥያቄዎች ከአንዳንድ ወገኖች ቀርቦላቸው ነበር፤

ጥያቄ :- (በዘመናችን ዝናቸው ስለ ገነነው አንድ አጥማቂ ነበር) በአንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ የተወገዙ ሆነው ሳለ በአንፃሩ ደግሞ ሌሎችሊቃነ ጳጳሳት ተቀብለዋቸዋል፡፡ ያም ሆነ ይህመጋቢ ሀዲስ በዚሁ ዙሪያ ያሎት አቋም ምንድነው? ይህ ነገርስ ከትውፊት ውጪ ከሆነለምንስ ብዙ ሰው ግራ ገብቶት እያለ እናንተ መምህራን ዝምታን መረጣችሁ? የሚል ነበር።

መጋቤ ሀዲስእሸቱ አለማየሁ፦ ማንም ሰው ጳጳስስ ላወገዘ ወይንም ስለተቀበለ አይደለም እውነታን ማወቅ የሚችለው። ሁሉም እኮ ከቤተ ክርስቲያን በታች ነው። ፓትርያርኩም ቢሆኑ። ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርኩን አፈራች እንጂ የትኛውም ፓትርያርክ ቤተክርስቲያንን አልመሰረተም። ስለዚህ ለጥያቄዎች ሁሉ ጳጳስ እንዲህ አለ፣ ሰባኪው ይሄንአለ ሳይሆን ወንጌል ምን አለ? በአፀደ ነፍስ ያሉት፣ በገድል በትሩፋት ያለፉት የቅዱሳኑ ታሪክምን አለ? ማለት ነው ያለብን እንጂ እገሌ እንዲህ አለ ማለት ከንቱነት ነው። ሰው ሊስት ይችላል፤በስጋ ያለ ሰው ጳጳስም ቢሆን ሊሳሳት ይችላል፣መሳሳት አይደለም ሀይማኖቱን ሊክድ ይችላል ፤ያኔ ግን ጳጳስ የምንከተል ሰዎች እነርሱም ሲክዱ እኛም አብረን እንክዳለን ማለት ነው።

በዘመኑ የምናየውን የማጥመቅ አገልግሎት ስህተት ነው አትከተሉ ብዬ በአውደ ምህረት ከመስበኬ በፊት መጀመሪያ የእኔን ጉድፍ ስመለከት አዝንና ስለሌላው ጉድፍ እንዴት ብዬ አውደ ምህረት ላይ  ልስበክ? ብዬ እተወዋለው። (ትህትናዊ መልስ)። አዎ በዘመናችን ያሉ የመቁጠሪያ ንግድን የያዙ፣ የፀጉር ቅባትን ቅባቅዱስ ነው ብለው የሚሸጡ፣ የአጋንንት ምስክርነትን በሲዲ በመሸጥ የሚኖሩ፣ ተአምራትን በመስራት ኑሮአቸውን የሚገፉ ሰዎች አሉ። ምዕመኑም በእነዚህ ሰዎች ጠንቅ መፅሀፍ ቅዱስን ትራሱ አድርጎ ከሰይጣን ምስክርነት እማራለው ብሎ ሲዲ ገዝቶ ቁጭ ብሎ ሲያዳምጥ ነው የሚውል። "ተአምረ ለእግዚትነ ማርያም" ሲባል ጆሮውን እያከከ በሀሳብ ቤቱ ውስጥ ስላለው ሲዲያስባል።

የእኛ ምዕመን ቤተክርስቲያን ለካህናት ክብር ብላ የዘረጋችውን ጥላ ዘቅዝቃ ስትለምን ዝም ያለ አንድ ተአምር መስራት ቻልኩ ያለ ግለሰብ ወይንም ባህታዊ ሲመጣ አስራት በኩራት ማውጣት ይጀምራል። ቤተ ክርስቲያን ጹሙ፣ ፀልዩ፣ ቁረቡብላ ስታስተምር ጆሮው የተከደነበት ሁሉ ተአምርማድረግ የሚጀምር ሰው ሲመጣ ‹‹እኔ ወንጌልን ያስተማረኝ እርሱ ነው›› ማለት እንጀምራለን፣እንከተላለን፣ ከዛም..... ። የጌታን ተአምር ሰምቶ የተከተለው አይሁድ ይሰቀል ብሎ ለመካድ ቅርብ ነበር፤  ከቅፅረ ቤተ ክርስቲያን ውጪ በየሜዳው የፀበል አገልግሎት በቤተክርስቲያናችን ይፈቀዳልእንዴ? ክርስቶስ ደዌ ዘስጋ፣ ደዌ ዘነፍስም ሲያደርግ አጋንንቶች እንዲመሰክሩ፣ የሰዎቹምሀጢያት በአጋንንቱ አማካኝት በመድረክ ላይ እንዲናዘዙ መቼ ፈቀደ? መቼስ አደረገ? እንደውም ከፈወሰ በኋላ ለማንም እንዳትናገሩ እያለሲልካቸው እንደነበረ ነው እኔ የማውቀው። (በግልካህን አግኙ ከማለት በስተቀር።) በዘመናችን ያለክህነት ማጥመቅ እየተለመደ መጥቷል፤ እንደውም አንዳንድ ዝነኛ አጥማቂዎች የክህነት ስም በአቋራጭ (በገንዘብ) ያገኛሉ ወይ?ለሚለው ጥያቄ አዎን በሚገባ ያገኛሉ።

 ይህንን እኛ ጠንቅቀን እናውቃለን። ዛሬ የቤተ ክርስቲያን አበሳዋ በዝቷል። በዚህ ተሀድሶው፣በዚያ ሙሰኛው፣ በዚያ ጠንቋዩ... እንደ በረዶ የነጣችው ይቺ ቤተ ክርስቲያን የቡና ፍንጣሪ ሲነካት ጥቁሯ ነጥብ ጎልቶ ይታይባታል። ለዚያ ነው ብዙዎች ተሰናክለው የሚጠፉት። እኔ ለነገሩ ከእነዚህ ነጋዴ አጥማቂ ነን ባዮች ይልቅ ለቤተ ክርስቲያኗ ስጋት የሆኑ ሌሎች አካላት አሉ። ለምሳሌ ተሀድሶ!! እነዚህ ሲዲ ነጋዴዎች ዛሬ ታይተው ነገ ይጠፋሉ። ብዙ ባህታውያን ነን ባዮች ከዚህ በፊት ብዙዎችን ተከታይ አድርገው አልፈዋል፤ ብዙ አጥማቂ ነን ባዮችም ከዚህ በፊት ተነስተው አልፈዋል። እነዚህም ያልፋሉ፣ ከዚህ ይበልጥ የሚያሰጋኝ በቤተክርስቲያናችን  የሚተክሉ፣ አስተምሮዋን የሚበርዙ፣ በውስጥ ለውስጥ ስር እየሰደዱ ያሉን ተሀድሶዎች ናቸው። እነርሱን አጥብቀን መቃወም ነው ያለብን
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
"ከሞት ወዲያ መብራት አለ ።
ከመቃብር በላይ ብርሃን አለ ።"
@gibi_gubae

🔱ታላቁ ሊቅ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል … ‹ሰው እግዚአብሔር ሲለየው፤ ጠባዩ እንደ አራዊት፤ አመጋገቡ እንደ እንስሳ፣ ሆኖ መልኩ ብቻ የእግዚአብሔር ሆኖ ይቀራል›።

🔱በጣም ቀለል ባለ አገላለጽ ሲም ካርዱ የወጣ ሞባይል ማለት ነው። ጥሪ የማይቀበል…....እኔ በዕውነቱ ከተማው ፈርሶ እየተሰራ ነው እየተባለ ዐይናማዎቹ ሲያወሩም ሲያስወሩም እሰማለው። ፈርሶ መሰራት ያለበት ግን የሰዉ አስተሳሰብ ነው።... የሰዉ አስተሳሰብ ፈርሶ ካልተሰራ፤ የተሰራ ከተማ ይፈርሳል። ጃፓንና ቻይና ሀገራቸውን ያለሙት መጀመሪያ አስተሳሰባቸውን አልምተው ነው።

🔱ቤታችሁ ገብታችሁ እንድታጤኑት ነው  እንደምታዩኝ እኔ ዐይነ ስውር ነኝ። ቀላል አይደለም.... እንክዋን ዘውትር ዓይን አጥቶ አንድ ቀን መብራት ሲሄድ ስንት እንደምታማርሩ ታውቅታላችሁ።

🔱እኔ ግን ዓይኔ ባለማየቱ አንድ ቀን እንኳን አልቅሼ አላውቅም። ከሞት ወዲያ መብራት አለ። ከመቃብር በላይ መብራት አለ።
 
🔱 ወደ መቃብር ሲወርድ ማንም ዓይነ ስውር ነው። ማንም ዐይኑ እያየ የተቀበረ የለም።

🔱ተስፋችን ግን ምንድን ነው?

🔱ከሞት ወዲያ ሕይወት አለ። ከሞት ወዲያ ብርሃን አለ...

🔱አንድ አንድ ጊዜ እመኛለሁ የማይረባ ነገር ስናይ (ዓይናችንን) የሚያጠፋ ቆጣሪ ቢኖር... መልካም ነገር እስክናይ ድረስ ለጊዜው የሚያጠፋ ቆጣሪ ቢኖር።

🔱አሁን እንደው ጆሮ በካርድ የሚሰራ ቢሆን ሐሜት እንሰማ ነበር? የምንፈልገውን (ብቻ) አውርተን ስዊች ኦፍ እናደርገው ነበር። ችግሩ ብዙ ነው፡፡ ስንት ዞማ ጸጉር ይዞ አስተሳሰቡ የከረደደ አለ።

🔱እባካችሁ ሰው እንሁን… የንጉሠ ነገሥቱ የክርስቶስ አልጋ ወራሾች ነን... የደስታችሁ ልኬት የደስታችሁ ሚዛን ምግብና መጠጥ አይሁን፤ መኪናና ቤት ዝናንም አታርጉ።

እኛ መለኪያችን ጽድቅ ነው።
መከኪያችን መንግሥተ ሰማያት ነው።
ያ የምንገባበት ቤት ደግም የተዋበ፣ የደመቀ፣ መብራት ውሀ የማይሄድበት፤ 24 ሰዓት ክርስቶስ የሚያበራበት፤ 24 ሰዓት የሕይወት ውሀ የሚጠጣበት፤ ሀብታም፤ ደሀ፣ ተራ ሰው የማይባልበት፣ እገሌ ግባ እገሌ ውጣ የማይባልበት ቦታ
ነው።

🙏ሁላችንንም የመንግስቱ ወራሽ ያድርገን ፣ አሜን።🙏

🎤በመጋቤ ሐዲስ እሸቱ🎤
  
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
@gibi_gubae
እግዚአብሔር እንዴት ይፈርዳል

አንድ ግብፃዊ መነኩሴ ለገዳሙ መርጃ የእጃቸው ሥራ የሆኑትን ቅርጫቶች ሊሸጡ ወደ እስክንድርያ ለመጓዝ በጠዋት ተነሡ፡፡

በመንገድ ላይ ታዲያ ትልቅ የቀብር ሥነ ሥርዓት ለማድረግ የሚጓዝ ሕዝብ ገጠማቸው፡፡ ሟቹ ዝነኛ አረማዊ ገዢ ሲሆን በዘመነ ሰማዕታት በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን የገደለ ሰው ነበር፡፡ አሁን ዕድሜ ጠግቦ ሞቶ ነው፡፡ ቀኑ ውብ ፀሐያማ ቀን ነበርና የሀገሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ገዢያቸውን እየቀበሩ ነው፡፡

ይህንን ያዩት መነኩሴ ጉዳያቸውን ፈጽመው ወደ ገዳም ሲመለሱ አሳዛኝ ዜና ሰሙ፡፡ ለስድሳ ዓመታት በበረሃ በብሕትውና ቅጠልና የበረሃ ፍሬ ብቻ እየበላ የኖረ ባሕታዊ በዚያች ዕለት በጅብ ተበልቶ ሞቶ ነበር፡፡
መነኩሴው እጅግ ጥልቅ ኀዘን ውስጥ ሆነው እንዲህ ሲሉ አሰቡ ፦

‘በሺህ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን የገደለው አረማዊ ሰው በታላቅ ክብር ታጅቦ ሲቀበር ሕይወቱን ሙሉ በጾምና በጸሎት ፈጣሪውን ያገለገለው ባሕታዊ በጅብ ተበልቶ የተዋረደ አሟሟት ሞተ፡፡ይህ እንዴት ዓይነት ፍርድ ነው? እግዚአብሔር ከመልካምነቱ ሁሉ ጋር ኢፍትሐዊ ነገሮች ሲሆኑ ዝም ብሎ ይፈቅዳል፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ሰዎች የፈጣሪን መኖር ይጠራጠራሉ፡፡ እኔም ፍርዱን እንዲገልጽልኝ መጸለይ ይኖርብኛል’ አሉ፡፡

ከዚያች ቀን ጀምሮ መላልሰው ወደ ፈጣሪ ‘’ፍርድህን ግለጽልኝ’ ብለው ደጋግመው ጸለዩ፡፡ ብዙም ሳይቆይ እግዚአብሔር ፍርዱን እንዲህ ገለጠላቸው፡፡

ከሳምንታት በኋላ እንደተለመደው ወደ እስክንድርያ የሦስት ቀን ጉዞ ሊሔዱና ቅርጫታቸውን ሊሸጡ ተነሡ፡፡መንገዱን እንደጀመሩ ድንገት አንድ ወጣት መነኩሴ ወደ እርሳቸው ሲመጣ ተመለከቱ፡፡

‘’አባቴ ይባርኩኝ’

‘እግዚአብሔር ይባርክህ ልጄ’

‘አባቴ ወዴት ይሔዳሉ?’ አለ ወጣቱ መነኩሴ

‘ወደ እስክንድርያ ቅርጫቴን ልሸጥ እየሔድኩ ነው’ አሉት

‘ጥሩ አጋጣሚ ነው አባ እኔም ወደዛ እየሔድኩ ነው’ አለ በትሕትና

‘ጎሽ አብረን እንጓዛለና’ አሉ አባ፡፡ ወጣቱ መነኩሴ ከእጃቸው ሸክማቸውን ተቀበለ፡፡ ጥቂት እንደሔዱ እንዲህ አላቸው፡፡

‘አባ ያው እንደሚያውቁት እንደ መነኮሳት ሥርዓት ጉዞ ስንጓዝ በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር አለብን አይደል?’’ አላቸው፡፡

‘ልክ ነው ልጄ’ አሉት

‘እንግዲያውስ ለሦስት ቀን አብረን ስንጓዝ እስክንድርያ እስክንደርስ ድረስ አንዲትም ቃል አንነጋገር ፤ ምናልባት በሦስቱ ቀን ጉዞአችን ለማየት የሚከብድ ነገር እንኳን ሳደርግ ቢያዩኝ ላይናገሩኝ ላይፈርዱብኝና የአርምሞ ቃልኪዳንዎን ላያፈርሱ ቃል ይግቡልኝ’ አላቸው፡፡

አባ እየተገረሙ ‘እሺ በሕያው አምላክ እምላለሁ ልጄ አንዲትም ቃል አልተነፍስም’ አሉት፡፡
ሁለቱ አባቶች በጠዋቱ የአርምሞ ጉዞአቸውን ጀመሩ፡፡ ቀትር ላይ ወደ አንዲት መንደር ደረሱ፡፡

ሁለት ወጣቶች እነዚህን መነኮሳት አዩአቸው፡፡ ከሁለቱ አንዱ ‘ቅዱሳን አባቶች’ እያለ ወደ እነርሱ ሮጠ ‘ቅዱሳን አባቶቼ ፀሐዩ እስኪበርድ ድረስ እባካችሁን እኛ ቤት አረፍ በሉ’ አላቸው፡፡ ፀሐይዋ እየከረረች ስትመጣ በበረሃማዋ ግብፅ ጉዞ በጠዋትና ማታ እንጂ በቀትር ስለማይታሰብ ጉዞአቸውን ማቋረጥ ነበረባቸው፡፡ ስለዚህ ሁለቱ ወጣቶች እነዚህን መነኮሳት በክብር ተቀብለው ከቤታቸው አስገቧቸው፡፡እግራቸውን አጠቧቸው፡፡ በቤታቸው ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ የከበረ እጅግ ውድ የብር ሰሐን ላይ ምግብ አቀረቡላቸው፡፡ መነኮሳቱ በዝምታ ተመገቡ፡፡ ከዚያም ትንሽ አረፍ የሚሉበት ክፍል ተሠጣቸው፡፡

ትንሽ እንደቆዩ ወጣቱ መነኩሴ ቀስ ብሎ ወደ ምግብ ማብሰያው ክፍል ገብቶ ይበሉበትን ውድ የብር ሳህን በልብሱ ደብቆ ይዞት መጣና አባን ጠቅሶ ጠራቸው፡፡ ተሰናብተው ከወጡ በኋላ አባ በቀሚሱ ውስጥ የደበቀውን የብር ሳህን ሲያዩ ደነገጡ፡፡ መናገር ባይችሉም በልባቸው እንዲህ አሉ ፦

‘እነዚያ ደግ ወጣቶች በክብር ተቀበሉን ፤ እግራችንን አጥበው መገቡን፡፡ እውነት ለውለታቸው ምላሹ ውዱን ንብረታቸውን መስረቅ ነው?’’ ብለው አዘኑ፡፡

ጥቂት እንደተጓዙ የመስኖ ውኃ ወደተከማቸበት አንድ ድልድይ ጋር ደረሱ፡፡ ውኃውን ሲሻገሩ ታዲያ ወጣቱ መነኩሴ በብር ሳህኑ ላይ ካማተበበት በኋላ ወደ ወንዙ ወረወረው፡፡

አባ እንዲህ ብለው አልጎመጎሙ ፦
‘’እንዴት ያለ ነገር ነው? ሳህኑን የሰረቀው ሊወረውረው ነው? እዚያው አይተውላቸውም ነበር?’’ አሉ አርምሞአቸውን ሊያፈርሱ አይችሉምና ዝም አሉ፡፡

ሲመሽ ወደ አንድ ወጣት ባልና ሚስት ቤት ደረሱ፡፡ እንደ ቀኖቹ ወጣቶች እነዚህም በክብር እግር አጥበው አስተናገዷቸውና ማረፊያ ሠጧቸው፡፡ ባልና ሚስቱ የሁለት ወር ሕፃን ልጅ ነበራቸው፡፡ በጠዋት ሲነሡ ወላጆች ሳይነሡ ወጣቱ መነኩሴ ቀስ ብሎ ሔዶ የተኛውን ሕፃን ገደለው፡፡ አባ ሊያስጥሉት ቢሉም አልቻሉም፡፡ እየጎተተ ይዞአቸው ወጣ፡፡ ‘ጌታ ሆይ ምን ዓይነት ርጉም ነው ንጹሑን ሕፃን ገደለው እኮ’ እያሉ እንባቸው ወረደ፡፡ ምንም እንኳን አንጀታቸው በኀዘን ቢኮማተርም በመሓላ የገቡበትን አርምሞ አፍርሰው ከግዝት ላለመግባት አንዲት ቃል ግን አልተናገሩም፡፡

በቀጣዩ ቀን ሁለቱ መነኮሳት ወደ አንድ መጠጥ ቤት ደጅ ደረሱ ፤ የጭፈራው ድምፅ ከሩቅ ይሰማል ፤ ሰካራሞቹ መነኮሳቱን ሲያዩ ‘ቅዱሳን’ እያሉ ተሳለቁ፡፡ በሰካራም አንደበት የሚናገረው ዲያቢሎስ ነው ብለው ዝም አሉ፡፡

ወጣቱ መነኩሴ ግን ወደ መጠጥ ቤቱ አቅጣጫ በግንባሩ ተደፋና ሦስት ጊዜ ሰግዶ ተሳለመው፡፡
ጥቂት እንደሔዱ አንድ ያረጀ ፤ መስቀሉ ከጉልላቱ የተነቀለ በርና መስኮት የሌለው ቤተ ክርስቲያን አዩ
ወጣቱ መነኩሴ ድንጋዮች ለቀመና አማተበባቸው ወደ ፈረሰው መቅደስም ወረወረው

አባ ይሄን ጊዜ ፦ መጠጥ ቤቱን ተደፍቶ ተሳለመ ፤ ወደ ቤተ መቅደሱ ድንጋይ ወረወረ ! ብለው በዝምታ ተንጨረጨሩ ::

አሁን ሦስተኛው ቀን ሞላ በጠዋቱ ወደ አንድ በሸንበቆ የተሠራ ቤት ደረሱ እናታቸው የሞተችባቸውና በአጎታቸው እርዳታ ብቻ የሚኖሩ አምስት ሕፃናት ተቀምጠው ያለቅሳሉ፡፡ አባ በርኅራኄ ለሕፃናቱ ምግብ ሠጧቸው፡፡ እሳቸው ከሕፃናቱ ጋር ሲነጋገሩ ወጣቱ መነኩሴ ደሞ የሸንበቆውን ቤት በእሳት እያያያዘ ነበር፡፡ ሕፃናቱ ከሚነደው ቤት ሮጠው አመለጡ፡፡

‘ይህን ነፍሰ ገዳይ እስከመቼ እታገሰዋለሁ’ ሲሉ የቆዩት አባ እስክንድርያ ደርሰዋልና በምሬት መናገር ጀመሩ
‘’እስቲ ንገረኝ ከዚህ በኋላ ዝም ልልህ አልችልም፡፡ መልስልኝ አንተ ሰው ነው ወይስ ሰይጣን ነህ?’

‘ምነው አባ ምን አጠፋሁ?’ አለ መነኩሴው
‘በዚህ ሦስት ቀን ውስጥ ምን ያላደረግከው ነገር አለ? በበረሃ አክብረው የተቀበሉንን ሰዎች የብር ሳህን ሰርቀህ ወንዝ ውስጥ አልጨመርህም? እነርሱም መነኩሳት በቤታችን ተቀብለን ሰርቀውን ሄዱ እያሉ ይሆናል’

መነኩሴው መለሰ :- ‘አባ ትልቅ ነገር ነው እኮ ነው ያደረግሁላቸው፡፡ ያቀረቡልን የብር ሳህን ቅድም አያታቸው ከጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን የሰረቀው ጻህል /የቅዱስ ቁርባን ማቅረቢያ/ ነበር፡፡ መላው ቤተሰብ ይህንን ሳያውቅ በዚያ ቤት ለብዙ ዘመን ሲቀባበሉት ነበር፡፡በላዩ ላይም በላቲን ቋንቋ ይህ ጻህል ለቅዱስ ኒቆላዎስ ቤተ ክርስቲያን የተሠጠ የሚል ጽሑፍ አለበት፡፡ በዚህ ምክንያት ያንን ቅዱስ ንዋይ የሚጠቀሙ ሁሉ እስካልተመለሰ ድረስ በእግዚአብሔር ላይ ድፍረት ይሆንባቸዋል፡፡ የሞቱት ወላጆቻቸውም በዚያ ቅዱስ ንዋይ የተነሣ ነፍሳቸው ትታወካለች፡፡ እነዚያም ወጣቶች በጻሕሉ እኛን በማስተናገዳቸው ነፍሳቸው እንዳትጎዳ አዘንኩላቸው፡፡ ስለዚህም ሰረቅኋቸው፡፡ የሰረቅሁት ፈልጌው አይደለምና ውኃ
ው ውስጥ ወረወርሁት፡፡

በማግሥቱ የደብሩ ዘበኛ ሊታጠብ ወደ ውኃው ይመጣል፡፡ በውኃው ውስጥም ያገኘዋል፡፡ የላቲን ቋንቋ ስለሚያውቅ የተጻፈውን ያነበዋል፡፡ ወስዶም ለካህኑ ይሠጠዋል፡፡ ፃህሉ ከብሮ ድጋሚ ሲቀደስበት የሞቱትም ያርፋሉ የቆሙትም ከጥፋት ይድናሉ፡፡ ’ አላቸው፡፡
አባ ተደነቁ ፤ ‘እሺ ሕፃኑንስ የገደልከው ለመልካም ብለህ ነው?’

‘አባ የእግዚአብሔርን ፍርድ አይመዝኑ ፤ ሕፃኑ የተፀነሰው በኃጢአት ነው ፤ ለወደፊት ደግሞ እጅግ ጨካኝ ወንጀለኛ ሆኖ ወላጆቹን የሚገድል ብዙዎችን የሚያሰቃይ ነው፡፡ ስለዚህ ልጁን በመግደሌ ሦስት መልካም ነገሮች አደረግሁ፡፡ ሕፃኑ ከንጽሕናው ጋር ወደ ሰማይ እንዲሔድ አደረግሁት ፤ ወላጆቹንም በልጃቸው እጅ ከመሞት አዳንኋቸው፡፡በዚህ ልጅ ኀዘን ምክንያት ወላጆቹም ልባቸው በመሰበሩ የቀደመ ኃጢአታቸው ይቅር ይባልላቸዋል’

‘እሺ መጠጥ ቤቱ ደጃፍ ላይ የሰገድከው ምን ሆነህ ነው?’
‘ሦስት ሰዎች በዚያ መጠጥ ቤት ውስጥ ሆነው የፈረሰውን የከተማችንን ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንሥራ እያሉ እየተጨነቁ ይነጋገሩ ነበር፡፡ ምንም እንኳን የተሰበሰቡበት ቦታ መጥፎ ቢሆንም በልባቸው ያለው ሃሳብ ቅን ስለሆነ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው ወድቄ ሰግጄ ለመንሁት’’

‘ታዲያ ወደ ፈረሰው ቤተ መቅደስ ድንጋይ ለምን ወረወርህ?’
‘በፈረሰው መቅደስ ላይ እየተሳለቁ አጋንንት ሲጨፍሩ አየሁ፡፡ በመስቀል ምልክት አማትቤ ድንጋይ ወረወርሁ ፤ በዚህም ምክንያት አጋንንቱ በንነው ሸሹ’ አለ መነኩሴው፡፡

አባ ቀጠሉ ‘የእነዛን የሙት ልጅ የሆኑ ሕፃናት ቤትስ ለምን አቃጠልከው?’
‘’እነዚያ ሕፃናት እንደሚያውቁት ወላጆቻቸው ሞተውባቸዋል ፤ የቀራቸው ንብረትም ቤቱ ብቻ ነው፡፡ ቅድመ አያታቸው የቀብሩት እጅግ ብዙ ሀብት ግን ከዚያ ቤት በታች አለ፡፡ ከቃጠሎው በኋላ በቀረው ክፍል ለማደር ልጆቹ ሲገቡ የተቀበረውን ሀብት ያዩታል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጠባቂነት ለሚያገለግል አጎታቸውም ሔደው ይነግሩታል፡፡ በረሃብ መሞታቸው ቀርቶ በጥሩ ሁኔታ ያድጋሉ’’ አለ መነኩሴው፡፡

አባ ምንም እንኳን ነገሩ ቢያስደንቃቸውም አንድ ወጣት መነኩሴ ይህንን ሁሉ እንዴት ሊያውቅ ይችላል የሚል ጥርጣሬ አደረባቸውና ‘አንተ ማን ነህ?’ አሉት፡፡
‘የእኔ ማንነት ይቆይና እርስዎ በዚህ ሰሞን መላልሰው ፈጣሪን የጠየቁት ነገር ካለ ይንገሩኝ’ አላቸው
‘እኔማ እግዚአብሔር ሆይ ፍርድህን አሳየኝ ብዬ በምድር ላይ ስለሚደረጉ ኢፍትሐዊ ነገሮች ጠይቄው ነበር’ አሉት፡፡

‘እግዚአብሔር ‘ሰማይ ከምድር እንደሚርቅ መንገዴ ከመንገዳችሁ ሃሳቤም ከሃሳባችሁ የራቀ ነው’ ብሏልና ፍርዱ አይመረመርም፡፡ ለመላእክት እንኳን ያልተገለጸውን የእግዚአብሔርን ፍርድ እንዴት እርስዎ በሰው አቅም ሊመረምሩ ይፈልጋሉ፡፡ ጸሎትዎን ሰምቶ እግዚአብሔር ያዩትን ሁሉ እንዳደርግና ፍርዱን እንዳሳይዎት ላከኝ’’ አላቸው፡፡

ቅዱስ ዑርኤል ለዕዝራ እንዲህ አለው፦
‘የምትፈርስ የምበሰብስ አንተ የማይፈርስ የማይበሰብስ የሕያው እግዚአብሔርን ፍርዱን ልትመረምር አትችልም’

የመንፈሳዊ ሕይወትዎን ማሰደግ ይፈልጋሉ?

መጸለይ እንዳለቦት ያውቃሉ። ግን እንዴት ወደ ጸሎት ሕይወት መግባት እንደሚችሉ ግራ ተጋብተዋል?

ወደ መልካሚ መንገድ ለመሄድ ግልጽ በሆነ አቀራረብ የተዘጋጀውን የመንፈሳዊ ሕይወት ማሻሻያ ጽሁፍ ለማግኘት ይህን ቻናል ይቀላቀሉ።

@zebisrat
@zebisrat
@zebisrat
@zebisrat
በሽታ በቅርቡ እንደሚጠፋ ታምናለህ?
በዲ/ን አቤል ኃይሉ(ዶ/ር)

አንድ ወቅት በጠዋቱ ወደ አንድ ክሊኒክ ለሥራ እየሄድኩ ሳለ መንገድ ላይ ሁለት ሰዎች አስቁመውኝ ስለመጽሐፍ ቅዱስ እናውራ ተባልኩ፡፡ እሺ ብዬ ቆምኩኝ፡፡ ‹‹በሽታ በቅርቡ እንደሚጠፋ ታምናለህ?›› አሉኝ፡፡ የእኔ መልስ የነበረው ‹‹ለምንድነው የሚጠፋው?›› ነበር፡፡ ትንሽ ገረማቸው፡፡ በሽታ እንዲጠፋ የማይፈልግ ይህ ደግሞ ማነው? ሳይሉ አልቀሩም!

ቀጠሉ፡፡ ‹‹ዓለም በበሽታ ተጨንቃላች፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ከምድር ላይ በሽታን ያጠፋልና ‹‹እንድትጽናና›› ፈልገን ነው አሉኝ፡፡ የሚቀጥለውን ምክር አዘል ቃል ተናገርኩኝ፡፡ ‹‹በሽታ ይጠፋል፤ ፍጹም ሰላም ይመጣል፡፡ ለጥ ብላችሁ ትተኛላችሁ …ወዘተ ›› እያላችሁ ሰዉን አታስንፉት፡፡ ‹‹ለምን ይጠፋል?›› እንዲህ ብዬ የመለስኩት በበሽታ መኖር ደስተኛ ሆኜ አይደለም፤ ሀሳባችው ግን አጥፊ ስለሆነ ነው፡፡ በመቀጠልም ጌታ በወንጌል ለይ ያስተማረውን ቃል አስቀመጥኩላቸው፡፡‹‹በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፡፡ነገር ግን አይዟችሁ፡፡ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለው፡፡›› ዮሐ 16÷30

ይሄ እውነት እስከጌታ ምጽአት ድረስ ይቀጥላል፡፡ ጌታ ቃል የገባልን እንዳሸነፍኩት ታሸንፋላችሁ ነው እንጂ በሽታ ፣ስቃይ አይኖርባችሁም አላለንም፡፡ ሰዎችንም ዘወትር ልናስተምራቸው የሚገባው እንዴት ማሸነፍ እንደሚችሉ ነው እንጂ በቅርቡ በሽታ ይጠፋል ብለን ላያገባት አገባሸለው ብሎ ያልሆነ ተስፋ እንደተሰጣት ሴትዮ እንዳያደርጉን ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡

@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
2025/02/23 00:19:52
Back to Top
HTML Embed Code: