#ቅኔ_ዘዓርብ
👉 ይህች አለም ብሎም ይህች አገር የመከራ ማዕበል እያማታት በድካም ተውጣለች። ወደየቤቱ ስንሄድ የምንሰማው ሰቆቃ ለመኖር አያስመኝም። የሰው ልጅ መተሳሰብ ፤ መረዳዳት ካቆመ ሰንበት ሰንበት ብሏል። ይህ የመዋዕለ ዓለም ተፍጻሜት ዋዜማ ነው።
👉 ጌታ ሆይ ቶሎ ና ብለን የምንለምንበት ጊዜ አሁን ቢሆን ኃጢዓታችንን ስናስብ ይሰቅቀናል። ይህችን ቅድስት ሀገር እግዚአብሔር ይጎበኛት ዘንድ ሁላችንም አምላክን መለመን ግድ ይለናል።
👉 በገዳም ወድቀው ስለሚለምኑ ባህታውያን ፣ ስለ ንፁሐን መነኮሳት ፣ በከተማ ውስጥ ስለ መሸጉ የአምላክ ባለሟሎች ብሎ እግዚአብሔር የመከራውን ዘመን አሳጥሮ በጎውን ዘመን ያሳየን።
መወድስ ዘዮሐንስ ዘደብረ ዘይት
ማዕበለ ነነዌ በሰዶም አለመ ተገፍዖ
ጠለ መከራ ዘጢሮስ ወበረደ ኅልፈት ዘኬልቄዶን
አመ ጽልመታ ለኢዮር ክፍለ ኤርሞን
እስመ አድለቅለቀ ወወረደ
ደብረ ኤፍሬም ቅርብተ ነነዌ እንተ ኤፍሬም ቀርን
ወሀዘነ ራሄል ዘትበኪ
ዘበውስተ ቤታ ለራሄል ኮነ ይከውን
መብረቅሂ አመ ወረደ ወአስተርአየ በዓይን
ቆላተ ኢያዜር ክፍለ ነዌ ነግደ ገሊላ ወኤፌሶን
ወአመ ተሰረወት ምድረ ምድረ ዘማልኮስ ዕዝን
ምክረ አኪጦፌል በነነዌ ወምክረ ኩሲ በባቢሎን

ሆሳዕና ዘወልደ ዳዊት
በጥንተ ፍጥረት ዲያብሎስ አላመሰግንም ባለበት በዚያ ጊዜ ፤ እርሱን ባደረው ጨለማ ጠቅሎ ወደ መትህተ ምድር ከሰደደ በኋላ አመስጋኝ የሆነውን የሰው ልጅ ከአራት ባህርያተ ስጋ ከአምስተኛ ባህርየ ነፍስ የፈጠረ አምላክ ፤ የምስጋና ደሀ ስሏቸው ጸሐፍት ፈሪሳውያን አናመሰግንም ብለው እንደ ዲያብሎስ ቢያምጹ አንደበት ያላወጡ ህጻናትና ግዕዛን የሌላቸው የቢታንያ ድንጋዮች ሆሳዕና ለወልደ ዳዊት ብለው አመስግነዋል።
ዛሬ ጥንተ ሆሳዕናሁ ለወልደ ዳዊት ይባላል። በዘመን ቀመር ትርጓሜ መሠረት ጥንት የሚለው ቃል "የኩነቱን ቀዳማዊ ዘመን ፣ ወርኅ ፣ መዓልት ፣ ሌሊት ፣ ዕለት ፣ ጨረቃ እና ሌሎች አቅማራትን የሚገልፅ ቃል ነው"።
ለምሳሌ የሆሳዕና በዓል መነሻው (ጥንተ በዓል) እንደሚከተለው ተከትቧል።
👉 በ5534 ዓመተ ፀሐይ
👉 በ34 ዓመተ ምህረት
👉 በ1383 መጠነ ራብዒት
👉 በዓውደ ወንጌላዊ ማርቆስ
👉 ዕለተ ዮሐንስ ሰሉስ በዋለበት
👉 14 አበቅቴ ፣ 16 መጥቅዕ ፣ 20 መባጃ ሐመር ፣ 7 ጥንተ ዖን በተገኘበት ዘመን
👉 ወርኁ መጋቢት ፣ መዓልቱ 22 ፣ ሌሊቱ 10 ፣ ጨረቃ በመላችበት በ14ተኛው ሠርቅ ፣ በዕለተ እሁድ ጌታን እስራኤላውያንና ነባብያን ያልሆኑ ድንጋዮች "ሆሳዕና በአርያም ፣ ሆሳዕና ለወልደ ዳዊት" ብለው ያከበረቡት ዕለት ነበር።
ታዲያ ጥንተ ዕለቱን በመያዝ በየአመቱ መጋቢት 22 ቀን ጥንተ ሆሳዕና በመባል ይታሰባል። ይህ በዓል በየዓመቱ በመጥቅዕ ከምናገኘው የሆሳዕና ሳምንት ጋር ሁልጊዜ አይተካከልም።
ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።
መምህር ዮሐንስ እሸቱ

"ዮሐንስ አፈ ወርቅ ፤ ዮሐንስ ዕንቆ ጳዝዮን ፤ ዮሐንስ ልሳነ ወርቅ"
ይህንን ገጽ Follow ማድረግ እንዳይዘነጉ።
👉🏽 ትምህርቱ ያማረ ፣ አንደበቱ በወንጌል ትርጓሜ የታሸ ፣ የክርስቶስን አምላክነት ለአለም ሁሉ ያስተማረ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ነው። የእመቤታችንን ዘለዓለማዊ ድንግልና ለነገስታቱ ያስረዳ ፣ የሐዲስ ኪዳንን ጠንካራ ሀሳቦች አምላክ በገለጸለት የጥበብ መንገድና ለሰው በሚረዳ መልኩ የተረጎመ የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ።
👉🏽 ኢትዮጵያን በብርሃኑ ያበራ ፣ ሐዲስ ሐዋርያ ተብሎ የተጠራ ፣ የተክለ ሐይማኖት ፍልሰተ ዓጽሙ በዚሁ ቀን ይከበራል። ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳንን በህይወተ ስጋ ሳሉ ብቻ ሳይሆን ካረፉም በኋላ መልካም ስራቸውን ትዘክራለች። ቅዱሳንም በምድር ላይ እያሉ ብቻ ሳይሆን በክርስቶስ እቅፍ ሆነውም ሰውን እንድሚረዱ አማናዊቷ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለምዕመናን ታስተምራለች። የቅድስት ክርስቶስ ሰምራንም ዜና ተጋድሎ ሁልጊዜ ትዘክራለች።
👉🏽 አፈ ወርቅ ዮሐንስ ለንጉሱ ለአርቃድዮስ "ኢያእመራ ዮሴፍ እስከአመወለደት ወልደ ዘበኩራ" ያለውን የሐዋርያውን ቃል እንዲህ አስረድቶት ነበር።
👉🏽 በዘመኑ ንጉሱ አርቃድዮስ ሊቀጳጳሱ ዮሐንስ አፈወርቅ ነበሩ። እጠይቀዋለሁ ሲል ይዘነጋዋል ከእለታት በአንዳቸው ንጉሱ ከነሰራዊቱ ሊቀጳጳሱ ከነማህበሩ በተሰበሰበት ንጉሱ ሊቀጳጳሱን ኢያእመራ ዮሴፍ እስከአመወለደት ወልደ ዘበኩራ ያለው የሐዋርያው ቃል ወንዶች ሴቶችን ከወለዱ በኋላ በግብር እንዲያውቋቸው ከወለደች በኋላ በግብር አወቃት ማለት ነውን ብሎ ጠየቀው። ዮሐንስም መልሶ ይህ እስከ ፍጻሜ የሌለው እስከ ነው ኢወለደት ሜልኮል እስከ አመ ሞተት ይላል ከሞተች በኋላ ወለደች ማለት ነውን ፤ ኢተመይጠ ቋዕ እስከአመነትገ ማየአይኅ ይላል ከጎደለ በኋላ ተመለሰ ማለት ነውን ፤ ወአነ እሄሉ ምስሌክሙ እስከኅልቀተአለም ይላል ከዚያ በኋላ ከኛ ጋር አይኖርም ማለት ነውን? ይህም እስከ እንዲህ ያለ ፍጻሜ የሌለው እስከ ነው ብሎ አስረድቶታል።
👉🏽 አንድም ፍጻሜ ያለው ነው ለነቢያት በብዙ ኅብረመልክዕ የሚታይ ጌታ በማህጸኗ ባደረ ጊዜ ቦ አመ ታቅየሀይህ ከመ ፅጌ ሮማን ወቦ አመ ትጸዓዱ ከመ ጽጌረዳ ወቦ አመ ታህመለምል ከመ ሀመልማለ ገነት ወቦ አመ ታጽደለድል ከመ ጽጌ ናርዶስ ብርሌ ጠጅ ቢቀዱበት ጠጅ ፤ ጠላ ቢቀዱበት ጠላ ፤ ውሃ ቢቀዱበት ውሃ መስሎ እንዲታይ እመቤታችንም ጸንሳ ሳለች በብዙ ኅብረመልክዕ እየተለዋወጠች ትታየው ነበር ጌታን ከወለደች በኋላ ግን በአንድ ኅብረመልክዕ አውቋታል ብሎ ተርጉሞለታል።
👉🏽 ይህን ሲተረጉምለት ከሰገነት የነበረች የእመቤታችን ስዕል ከቦታዋ ላይ አፈፍ ብላ ተነስታ ሠናየ ተናገርከ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ሠናየ ተናገርከ ዮሐንስ ዕንቆ ጳዝዮን ሠናየ ተናገርከ ዮሐንስ ልሳነ ወርቅ ብላ ስማው ዞራ ከሰገነቷ ላይ ሄዳ ተቀምጣለች። ስታመሰግንም ከፊት በር እስከ ኋላ በር ድረስ ተሰምታለች በዚህ ጊዜ ንጉሱ ከወርቁ የጠራውን ፤ ከጃን ሸላሚ ብልሁን አስመጥቶ ሁለት ልሳናተ ወርቅ አሰርቶ አንዱን ከቤተ እግዚአብሔር አንዱን ከቤተመዛግብት አኑሮታል። ንጉሱ እንዲህ ብሎ ጠየቀ ሊቀጳጳሱ እንዲህ ብሎ መለሰ ለመባል ለዝክረ ነገር።
የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል በረከትና ረድኤት እንዲሁም ጥበቃ አይለየን።
Telegram Channel : https://www.tgoop.com/gubaeQene
Facebook Page : https://www.facebook.com/memheryohanneseshetu

Telegram
ጉባኤ መፃህፍት ወቅኔያት
የብሉያት ትርጓሜ ፣ የቅኔና የግዕዝ ሰዋስው እንዲሁም የአቡሻኽር ትምህርቶች ይሰጡበታል
Afa_warq__btv1b53138752s.pdf
71.8 MB
የዮሐንስ አፈወርቅን አመታዊ የመታሰቢያ በዓል በማስመልከት ፤ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የጳውሎስን መልዕክታት የተረጎመበትን ጥንታዊ የብራና መጽሐፍ በዚሁ የቴልግራም ቻናል ላይ አቅርበንላችኋል።
የኔታ ዛሬ ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ዋዜማ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ያደረጉት ዋዜማ ቅኔ
ዋዜማ ዘመምህር ዘካርያስ አምባው መምህረ ቅኔ ወመጻሕፍት
ለዮሐንስ እምከብካቡ
ልደተ ስጋ ወዓፅም ለዘተከዘ አስሐቆ
ዘካርያስ ዘአስተዋደዶ ዮሐንስ መሰንቆ
በጣዕመ ቃሉ ሐዋዝ አምጣነ ያረስዕ ጻሕቆ
ወከርሰ ኤልሳቤጥ ጳውሎስ ዘደማስቆ
አጠየቀ ለዮሐንስ ጽድቆ
መልካም የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ክብረ በዓል ይሁንልን።

ትማልም ከመ ዮም
የዛሬ ሶስት ዓመት የተናገርነው መወድስ ግዘፍ ነስቶ እንበለ ህሳዌ ደርሶ ሲታይ "በአማን ቅኔ ቅኑይ ለመንፈስ ቅዱስ ዘይሁብ ቃለ ተነብዮ" አስብሎናል። "ኢይደቅ እመንበሩ ዐቀብዎ መላእክት" እንዳልን ዳግመኛም ቅዱስነትዎን እንደ ነገስታቱ ስርዓት በቃለ ወልድና "ሕየው አቡነ ወራሲሃ ለመንበረ ተክለ ሃይማኖት" እንላለን።
"ይነስእ ሀይለ ደማስቆ ፤ ወይትካፈል ምሕርካ ዘሶርያ" እንዲል ነቢዩ ኢሳይያስ
መወድስ ዘዮሐንስ
መኑ ይነብር እንበለ ተገፍዖ
እምነ ቀዳሚ ዳንኤል ተወካፌ ነግድ እሳት
እስከ ደኃራዊ ጳውሎስ መፍቀሬ ዘመድ መጥባህት
አምጣነ ተሰርዐ ለኩሎሙ
ኤርምያስ እንተ ይሴሰዮ ተገፍዖ ህብስት
ወከመ ተነግረ በምሳሌ
ተገፍዖ ያነብር መልዕልተ ኩሉ ፍጥረት
ማትያስሂ አመ ተገፍዐ በዘዖድዎ ተኩላት
ኢይደቅ እመንበሩ ዐቀብዎ መላዕክት
ወከመ ቀዳሚ ሰማዕነ እምቃለ አበው ቀደምት
ለፀዊረ አክሊል ርዕሰ ዳዊት ወርዕሰ ጎልያድ ለመቅበርት
ወንድማችን ዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው እንደመለሰው።
ማን ይድናል ከመገፋት?
የተፈተነዉን በእንግዳ እሳት፣
ዳንኤልን ብናይ ብነነሣ ከጥንት፣
ሰይፍን የወደደው በዝምድና ስሜት፣
ጳውሎስ ቢጠቀስ ከሐዲሱ ሥርዓት፣
ተሠርቶላቸዋል ለኹሉም በአንድነት፤
ኤርምያስ የበላው የመገፋት ኅብስት።
እንደ ተነገረ በምሳሌ ቃላት፣
ከፍ ከፍ ያደርጋል ከኹሉም ፍጥረታት፤
ከሰው ያስከብራል ዋጋ አለው መገፋት።
በዙሪያው በቆሙ አደገኛ ተኵላት፣
ማትያስ ቢከበብ የኹላችን አባት፣
መንበሩ እንዳይወድቅ እንዲጸና በእምነት፣
ጠባቂዎች አሉት ቅዱሳን መላእክት።
እንደ ተረዳነው ከአበው አንደበት፣
ለዙፋን ሲበቃ የተገፋው ዳዊት፣
ጎልያድ ግፈኛው ተዘጋጅቷል ለሞት።

"ወልጦተ ርዕስ ይቀድም እምወልጦ ሰብእ"
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እኛ ያላደረግነውን ያልፈጸምነውን ነገር ለሌሎች አድርጉ ማለታችን ረብ የለሽ መሆኑን ሲናገር "ኢትስርቁ ትብል ወለሊከ ትሰርቅ" ብሎ ያዳኝብናል።
"በሕግም የእውቀትና የእውነት መልክ ስላለህ፥ የዕውሮች መሪ፥ በጨለማም ላሉ ብርሃን፥ የሰነፎችም አስተማሪ፥ የሕፃናትም መምህር እንደ ሆንህ በራስህ ብትታመን፤ እንግዲህ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ ትሰርቃለህን?" ሮሜ : ፪ ÷ ፲፱
በዘመናችን የሚታዩት በየትኛውም ሃይማኖት ያሉ ሰባኪዎች ፣ አነቃቂዎች ፣ ፖለቲከኞች አድማጩን ወይም ሰፊውን ማኅበረሰብ ለመለወጥ የሀሳብ እና የገንዘብ በጀታቸውን በሰፊው ይመድባሉ።
እንደ ጳውሎስ ቃል ግን ከምንም ነገር አስቀድሞ ራስን መለወጥ ቅድሚያ የሚሰጠው ግብር መሆኑን ዘንግተነዋል። አንዳንዴ ሌባ ሆነህ አትስረቁ ብትል ፣ ገዳይ ሆነህ አትግደሉ ብለህ ብትጮኽ ፣ ድሃ ሆነህ ወርቅ ለማግኘት እንዲህ አድርጉ ብትል ፣ ውስጥህ በሀዘን ተቆራምዶ ሌሎች ያዘኑ ሰዎችን አስቃለሁ ብትል ከንቱ ድካም ነው። ሰው በተፈጥሮው ከአንደበት ይልቅ ግብር ላይ የሚያተኩር ፍጥረት ነውና።
ለዚህም ነው አማናዊት ህገ ወንጌል በቃል ብቻ ሳይሆን በግብር ክርስቶስን መስለን እንድናስተምር ያዘዘችን። የዛሬው መወድስ በዚህ ሀሳብ ላይ የሚያጠነጥን ነው።
መወድስ ዘዮሐንስ
ወልጦተ ርዕስ ይቀድም እምወልጦ ሰብእ
ወኢይትከሀሎ ለሰብእ ካልአኒሁ ከመ ያጽድቅ
እመልበሰ ጽድቅ ዘአብራም እንዘ ውእቱ ዕሩቅ
ሰብእሰ ኢያፍቅር ወርቀ ዓመጻ
ዘይሜህር ነዳየ ምሳሌ ይደክም ለወርቅ
ወበኀዘነ ልብ ዘየሀድር
እለ የኀዝኑ ሰብአ እፎኑመ ያስህቅ
ንሕነሰ እለ ወረድነ ውስተ ባህረ ፍዳ ዕሙቅ
ለወልጦ ሰብእ ንደክም እንዘ እም ርዕስነ ንርህቅ
በከመ ይቤ ጳውሎስ ዘቤተ ገማልያል ሊቅ
ኢትስርቁ እንዘ ንብል አምጣነ ለሊነ ንሰርቅ
ሰናይ ዕለተ ዓርብ
የቴሌግራም ገጽ ፡ https://www.tgoop.com/gubaeQene

የሞት ነገር ክቡድ ነው። ዜናውም ያስፈራል። ሰባኬ ወንጌል ፣ ተላዌ ጥበባት ፣ ባዕለ ትሕትና መልአከ ፀሐይ መኮንን ደስታ መታመማቸውን ሳንሰማ ኅልፈታቸውን ሰማን። ከልብ ወንድምነትን የሚያውቁ ፣ መተናነስን ገንዘብ ያደረጉ አባት ወንድም ነበሩ።
ለጥቂት ጊዜ በማኑስክሪፕት ተዛማጅ ቅጂዎች ላይ በነበረን ፕሮጀክት ላይ ትልቅ እገዛ ያደረጉልኝ የልብ ወዳጅ ናቸው። ለተጠየቁት ነገር ስስት የማይታይባቸው ትሁት ፣ አዋቂ ፣ መንፈሳዊ አባት መሆናቸውን ተመልክቻለሁ።
መቼስ ከሞት የሚቀር የለም። የጊዜ ሁኔታ ነው እንጂ ሁላችንም ወደዚያው ነን። የወዳጅነትን ፍቅር ከሞት በኋላ ማየት አለመቻላችን ጉድለት ቢሆንብንም ፣ የመጨረሻውን ስንብት በመወድስ አድርገነዋል። የደጉን የገብረ ሥላሴን ነፍስ አምላክ በእቅፉ ያኑርልን። አሜን!
መወድስ ዘዮሐንስ
መኑ ይፌጽም ፍኖተ ዚአሁ
ወመኑ ረከበ ዘሀለየ እምልቡና
መቃብር ወሞት ዘአፈድፈዱ ሙስና
ልበ ሰብእ ርሁቀ እንዘ ይሄሊ
ፍጡነ እስመ ይቀውሙ በዘሰብእ ፍና
ወለግብረ ሀጉል ኢየአርፍ
አርዌ ምድር ሞት እንተ የዓቅብ ሰኮና
ደንገጽነሂ ወኢነበብነ ውሉደ ቤቱ ለዮና
በነፋሰ አልዓዛር መቃብር ዘየዓርግ ደብረ ሲና
አየረ ሞቱ ለአቤል አመ ተልዕለ ልዕልና
እስመ እንዘ ይጸውር መኮንነ ተሰወረ በደመና
ሰናይ ዕለት

በዕለተ ሰንበት ዘሰሙነ ቅድስት በስርዓተ ማኅሌቱ የተደረጉ ቅኔያት :
ሚበዝሁ ዘዮሐንስ
ጠበብተ አሐቲ ከነዓን ሀሊበ እንስሳ ወቅብዕ እለ ሰብአ ያፈቅሩ
አይቴኑመ ገብኡ ወኀበ አይቴኑመ ተሰወሩ
እስመ ዘመዶሙ ከርስ ዐዊዶ ዓለመ ኢረከቦሙ እምድሩ
---------------------------------------------------------
ጉባኤ ቃና ዘዮሐንስ
ከበሮ ህሙም ዘልማድከ ተጽምሞ
እስከ ሆሳዕና ትረክብ ይኄይሰከ አርምሞ

ዋዜማ ዘዮሐንስ
ተዐቀብ እምተናግሮ
ቀርነ ማኅሌት ልሂቅ ዘተገፋዕከ ይእዜ
ዮም አምጣነ ኢኮነ ዘዚአከ ጊዜ
እስከ ደኃራዊ ዕለት ይከውነከ አግዓዜ
ባህቱ ታረምም እስከ ማእዜ
እስመ ልበ ይሰብር ትካዜ

መወድስ ዘመምህር ዘካርያስ አምባው
ሐተታ ብዙኃ ለእመ ሐተቱ
ሀሊብ ወቅብዕ እለ ሰብአ ያፈቅሩ
እምአዝማደ መብልዕ መኑመ ኢይበጽሆ እምድሩ
ለዋህድ ባህታዌ ቀኖና ዘክቡት ግብሩ
እንዘ ደመና መንኮራኩሩ
አምጣነ ጽሩይ ማይ ያንጸፈጽፍ እም ጠፈሩ
ኪሩቤልሂ ብካያቲሁ ከመ እለ ቄጥሩ
ገጸ ከመ ሰብእ በገጽ ይትናጸሩ
መዝሙረ ሀዲስ አንብዕ እንዘ ይዜምሩ
እስመ ኀበ አንጸረ ቀዳማዊ አርባዕቲሆሙ የሐውሩ

ጉባኤ ቃና ዘመምህር ዘካርያስ አምባው
ከበሮ የዋኅ እንተ ክልኤቱ አፉሁ
ከመ ፈያታዊ ተሰቅለ በዘኢኮነ እዳሁ
ሰናይ ሰሙን

ነገራተ ክልዔ ....
፩. የኅልፈተ ዓለም ነገር የእውቀት ማሳያና ሰውን ማስደንገጫ ሳይሆን ወደ ንስሐና ተወክፎተ ስጋ ወደም የሚያደርስ ጽኑ አስተምህሮ ነው። በመሰረቱ ሊያሳስበን የሚገባው ኅልፈተ ዓለም ሳይሆን ኅልፈተ ዚአነ ነው። ዓለምማ ማለፏ አይቀርም። ከዚያ በኋላ ላለው ፍርድ ግን ምን ያህል ዝግጁ ነን? ከሚያለቅሱት ሳይሆን ከሚደሰቱት ወገን ያደርገን ዘንድ በመንፈሳዊ ህይወት መጽናት አለብን።
፪. በጥልቀት ስላልተረዳነው ነገር ባንናገር ባንጽፍ የብዙ የዋሃንን አእምሮ ከማቆሸሽና ከደኃሪ ተዋርዶ እንድናለን። ክርስትና ከፍጥነት ይልቅ ቁጥብነት ፣ ከነቢብ ይልቅ አርምሞ ፣ ከድፍረት ይልቅ ትህትናን የተመላ አስተምህሮ ነውና። መዋዕለ ዓለምን (ነገረ ምጽአትን) በዚህ ገጽ መተንተን ድካም ቢሆንብንም ብዙ ምዕመናን ብሎም ሰባክያን "ቤተክርስቲያን" በዘመን ቀመር ትምህርቷ የማታስተምረውን ሀሳብ ሲያንጸባርቁ ማየት አማናዊቷን ቤተ ክርስቲያን ሀሳዊት ከማስባል ይቆጠራልና በጥልቀት ያወቅነውን ፣ የመረመርነውን እናስተምር ዘንድ እንትጋ። በጉባኤ ቃና ብዙውን ሐሳብ ጠቅልለን አቅርበናልና በቁጥራዊ ስሌቶች እንመርምረው።
ጉባኤ ቃና ዘዮሐንስ
ማእዜ ይመጽእ አማኑኤል እምነ ጽርሑ ዘወጽአ
ሠረገላ ዐቢይ ቀመር እስመ ፍጹመ ኢመልአ
ሰናይ መንፈቀ ጾም

እመቤታችን በህይወታችን ያደረገችልንን ነገር አንደበት ተናግሮ ሊፈጽመው አይችልም። ሊቁ "ናርምም እስመ ኢንክል ፈጽሞ ጥንቁቀ ነጊረ በእንተ እበዩ ለውእቱ ገባሬ ሰናያት በብዙኅ መንክር ራዕይ" ያለውን አባቶቻችን ሲተረጉሙት "ናርምም" ን "እናድንቅ" ብለው ነውና እኛም ፈጽሞ መናገር ባይቻለን በቅኔያችን እናደንቃለን! የእመቤታችንን ተራድኦ!
መወድስ ዘዮሐንስ (ስእለት ዘቅኔ)
ዕጸ ደብረ ሲና ድንግል ምጽላለ ርኅራሄ
ፍኖተ ህላዌ መብዕስ ለእመ ይርህቅ ብየ
ወዓለመ ስጋ ፀሐይ እመ ታውዒ ኪያየ
ታህቴኪ እምከመ አዕረፍኩ የዓርፍ ልብየ
ወአብርሃም ህሊናየ
ዕለተ ዚአኪ ይርአይ ፍጹመ ተመነየ
ለሰብእሰ ህልወ ምድር ዘመደ አሐቲ ስጋየ
ሀዘነ ዚአየ ያስህቆ ወያበክዮ ተድላ ዚአየ
ወመዓዛሃ ለዕጽ እመ ኢሀሎ ምስሌየ
በዐዘቅተ ድካም እምተቀብረ ኤርምያስ ህሊናየ
የእመቤታችን ተራድኦ በህይወት ዘመናችን ሁሉ አይለየን።

ማኅደረ ስብሐት
ህሊና ሲደክም ሊያርፍበት ፣ ልቡና ሲያዝን ሊጽናናበት ፣ ውሳጣዊ አዕምሮ ሲደሰት የደስታውን ነበልባል በምስጋና ሊሞቅበት የሚሻው ቦታ አለ።
ማኅደረ ስብሐት ለድካመ ህሊናችን ማረፊያ ፣ ለልባቸን ሀዘን መጽናኛ ፣ ለደስታችን ነበልባል መሞቂያ ናት። ይህች የውሳጣዊ እኛነታችን ማረፊያ ፣ በቃለ ሳዊሮስ ሊቀ ጳጳሳት ዘደቡበ ኢትዮጵያ ቅዳሴ ቤቷ ከተከበረ ድፍን 95 ዓመታትን አሳልፋ ዛሬ ላይ ደርሳለች።
የእናታችን ረድኤት ፣ የደብረ ምጥማቅ በረከት አይለየን። አሜን!
መወድስ ዘዮሐንስ
ኢይትዔረያ መኑመ ወኢይመስላ
ለወለተ የዋህ ሳዊሮስ ቅርብተ ራሔል ወልያ
አመ ልዕልናሃ ተነግረ ወአስተርአየ ዕበያ
ሊቃውንተ ኢዮር መላእክቲሃ
እስመ ይብሉ ማኅደረ ስብሐት እኅትነ ነያ
ሳዊሮስሂ አመ ነፀራ
እምነ ኩሎን አንስት አድባራተ ፅዮን ተመነያ
እስራኤልሂ ሊቃውንቲሃ ድህረ አንከሩ ላህያ
በቃለ ሣዊሮስ አቡሆሙ ሰመይዋ ሰማርያ
ወአመ ክብራ ተነግረ እምደብረ ኤፍሬም ሶርያ
አዕላፈ ገለዓድ ያነክሩ ወአንስተ ኬብሮን ይገንያ
#MSKLideta #ልደታ_ለማርያም #ደብረ_መድኃኒት_መድኃኔዓለም

ደመና የሸፈናት ቀዳሚት ጨረቃ
ደግም ሆነ መጥፎውን ነገር እየሰማን ፣ በሚያስደስተው ነገር ልባችን ሀሴት እያደረገ ፣ በሚያስከፋው ነገር ደግሞ ልባችን እየጠየመ ዘመን ያስረጀን ይዟል።
የ7517 ዓመተ ፀሐይ ቀዳማዊት ወርኅ የምትሄድበት የዑደት መንገድ የሰውን ልጅ ፍና ህይወት ያመላክታል። ወያንበሰብሱ ደመናት እምዐረብ ወሠርቅ እንዲል ደራሲ ደመናት ወዲያና ወዲህ እያሉ ሲመላለሱ ብርሃናማዋን ጨረቃ በጨለማ ይሸፍኗታል።
ለጊዜው የደመናቱ ጽልመት የጨረቃዋን ብርሃን ያሸነፈው ይመስላል። ደመናት ግን በባህርያቸው ነፋስ የሚመራቸውና ወዲያና ወዲህ የሚያመላልሳቸው ስለሆኑ በአንድ ቦታ ረግተው አይቆሙም። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ደመናቱ ወዲያ ተገፈው ፣ ጨረቃዋ ፍንትው ብላ የምትታይበት እና በራሷ ኃይል ደምቃ የምታትይበት ሁነት ቅርብ ነው።
የሰው ልጅም እንደ ጨረቃዋ ነው። በህይወት መንገድ ላይ ሲጓዝ ብዙ መሰናክሎች ሊገጥሙት ይችላሉ። እነዚያ ሁሉ ግን ኃላፊዎች ናቸው። በአምላኩ ረዳትነት የጨለማውን ጊዜ አሳልፎ ፣ ፍንትው ብሎ የሚታይበት ጊዜም ሩቅ አይደለም።
ደመና የሸፈናት ፣ ደመናውንም አሸንፋ ብርሃኗን ያሳየችው የመስከረም ጨረቃ በማቴዎስ ምግብና ፣ በሶስተኛው የሌሊት ሰርቅ ፣ በቀዳማዊው ሰርቀ መዓልት ፣ በሰባተኛው የጨረቃ ቁጥር ፣ በተፈጠረችበት ዕለተ ረቡዕ ታይታ የሰውን ልጅ ዑደተ ህይወት አሳየችን።
መልካም ዘመን

ልቡናን በተመስጦ ለመሰወር ፣ በደስታ ስሜትም ወዲያ ወዲህ ለማለት ሁለት ነገሮች ያስፈልጋሉ ብለን እናስባለን። የሚወዱትን ድምጽ መስማት አልያም ደግሞ በምስጢር ያማረ መወድስ ማድመጥ። ከእነዚህ ከሁለቱ ግን ልቡናችን ወደ መወድሱ ታደላለች።
ከየኔታ ጋር በስልክ ስንነጋገር ፣ አንድ መወድስ ስነግራቸው "ቆይ እኔም ልጨምርልህ" ብለው ይህንን ልብ የሚመስጥ በምስጢር የተዋበ ፍልስፍናዊ ሀሳብ ያለውን ቅኔ ነገሩኝ። እኔ ብቻ ሰምቼው ለምን ይቅር! እስኪ ላጋራችሁ።
ቅኔው የሕይወት እና የሞትን ነገር በአንጻራዊ ምስጢር ያቀርባል። እነዚህ ሁለት የፍጡራን መነሻና መድረሻዎች አንድ ሆነው አያውቁም። የትኛው ገፊ ፣ የትኛው ተገፊ እንደሆነ ሳይታወቅ አንዱ በአንዱ ላይ እየተነሳ በፍጡራን ነፍስ ላይ ይመላለሳሉ። ይህንን ሀሳብ አልዓዛርና ኤልያስ በሞትና በሕይወት አንጻር ሆነው ያስረዱናል። መቼስ ይህ ንጽጽራዊ የቅኔ መንገድ ልብን የሚመስጥ እንደሆነ ብንረዳውም ደጋግመን ስንሰማው ነፍሳችን ሐሴት ታደርጋለች።
ቅኔ ዘመምህር ዘካርያስ አምባው
እምነ ሕይወት ወሞት እለ ይትበአሱ
ተገፋዒሁ መኑመ ወመኑመ ገፋኢሁ
አኮኑ ባዕሶሙ ለለመዋዕሉ ወወርኁ
ቀሊል አኮ ይትመየጥ ድኅሬሁ
እንዘ ሞት ለሕይወት
ወእንዘ ሕይወት ለሞት ያፈደፍድ ዐመጻሁ
አልአዛርሂ ወኤልያስ አረጋውያን ዘተግሁ
ኢረከቡ ሰላሞሙ እመ ዘልፈ ይሰርሑ
ለሞት አልዓዛር እንዘ ያደሉ በፍትሑ
አምጣነ ኤልያስ አረጋዊ ለሕይወት ሰዋቂሁ
#ቅኔ_ዘዓርብ
#ጉባኤ_መጻሕፍት

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሁለተኛው የማኅሌተ ጽጌ ሳምንት እመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ በገባችበት ቀን የዋለ ሲሆን ቀለማቱ በሙሉ በዓተ ቤተ መቅደስን (በዓታ ለማርያም ውስተ ቤተ መቅደስ) ያመለክታሉ።
የሰው ልጅ በወርቅና በዕንቁ ተሸላልሞ አምሮና ተውቦ ይታያል። እመቤታችን ግን በስጋና በነፍስ ቅድስና ተውባና ተሻላልማ ፤ አባቷ ዳዊት "ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ ፤ እስመ ፈተወ ንጉስ ስነኪ" እያላት በዓውደ ንጽህና ለሁሉ ትታያለች።
ወዲህ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ጳጦስ (ጳጦስ የሚለው እንጆሪውን ፣ ደደሆውን ፣ ጀበራውን ነው) በተባለችው ዕጽ አንጻር በደብረ ሲና የተመለከታትን ባለ ብዙ ምሳሌ የሆነችውን እመቤታችንን ወላጆቿ ኢያቄምና ሀና በሶስት ዓመቷ ወስደው ለሊቀ ካሕናቱ መስጠታቸውን አስመልክቶ የማኅሌተ ጽጌው ደራሲ ባማረው ድርሰቱ ያመሰገነውን ምስጋና ቅዱስ ያሬድ ወዳሳየን ፍና ማኅሌት ፤ ወንድማችን ሊቀ መዘምራን ዘርይሁን ወርቅነህ ባማረው ላኅዩ ይወስደናል።
በቅድስና ማርያም ሥርጉት ሥርጉተ ስጋ ወነፍስ ፤
ኢያቄም ወሐና እምዘጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ ፤
#ማኅሌተ_ጽጌ

አንዳንድ ጊዜ ህሊናችን (ሀሳባችን) የራሳችን ጠላት ሆኖ ይከሰትብናል። ለምሳሌ...
➛ የገዛ ህሊናችን በወንድማችን ላይ በቅንዓትና በመዓት እንድንነሳ ወዳጅ መስሎ ምክሩን ይለግሰናል። (ከመ ቃየል ዘቀተለ እኅዋሁ)
➛ የምንጓዝበት መንገድ ልክ እንዳልሆነ እያወቀ በል ፣ ሂድ ፣ ጥሩ አድርገሃል እያለ የምንጠፋበትን ምክር ይመክረናል።
ህሊና ሲበላሽ ከትህትና ይልቅ መታበይን ፣ ላንተ ከማለት ይልቅ ለኔ ማለትን ፣ ከትዕግስት ይልቅ ቁጣን እንድንመርጥ ረቂቅ በሆነው ምክሩ ይመራናል።
አንዳንዴማ እውነታውን ልባችን እያወቀው ፤ ሀሰት ነው ብሎ ያሳምነናል። ራሳችንን እንድናታልል መንገዱን ይከፍትልናል። ህሊና በቅጡ ካልተያዘና ልጓም ካልተበጀለት ፣ እኛ ሳንሆን እርሱ ከተቆጣጠረን መዘዙ የከፋ ሊሆን ይችላል።
ለዚህም ነው የመዝሙረ ክርስቶሱ ደራሲ
ክርስቶስ ሀበኒ ዘየሐይወኒ ምክረ ፣
ምክረ ህሊናየሰ እንዘ ይትሜሰል ፍቁረ ፣
ናሁ ኮነኒ ዘይቀትል ጸረ ፣
ብሎ ጸሎቱን ያቀረበው። ህሊናችን የሚገዛን ያይደለን የምንገዛው ያድርገን።
ያማረች ቀዳሚት ሰንበት!