Telegram Web
አዲስ ልብስ የገዛችሁ ፤ የተገዛላችሁ ይህን ዱዓ አስታውሱ፥

عن معاذ بن أنس، عن النبي ﷺ قال: (مَن لبس ثوبًا فقال : الحمد لله الذي كَساني هذا الثوب ورَزَقَنِيه مِن غير حَوْلٍ مِني ولا قُوة غُفِرَ له ما تَقدَّم مِن ذَنبِه). رواه أبو داود.


https://www.tgoop.com/halale_merdaja_dilla
የቢላል መስጂድ አዛን በሰአት መመሳሰል በስተት የተባለ ነው አትረበሹ ሁሉም ወደ ቤት በሰላም ይግባ አጣርተናል ሁሉም ነገር ሰላም ነው አልሃምዱሊላህ

https://www.tgoop.com/halale_merdaja_dilla
* አስታዋሽ 69 *

🔴 ሙስሊም ስለሆንክ ብቻ ምን ይቀርልሀል?

ጉዳዩን ከመሀል እንጀምረውና ... ከነብያችን ሞት ቡኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በቀሽምና ችኩል ሙስሊሞች ስልጣን ልቀቅ የተባሉት መሪ ማን እንደሆን ታውቃለህ? ሀብታምና የጀነት ሰው ፣ ሁሉንም የመሪነት ብቃት የሚያሟሉት ኸሊፋው ዑስማን ቢን ዓፋን ነበሩ። ከነብያችን ሞት ቡኃላ በሀሰተኛ ወሬ ተወንጅለው፣ በደቦ ፍርድ በደደብና ባለጌ ሙስሊሞች የተገ**ደሉት ደግ ሰውስ ማን እንደሆኑ ታውቃለህ? ከአዛውንቱ ዑስማን ቢን ዓፋን ውጭ ማን አለ ብለህ ነው?

ከነብያችን ሞት ቡኃላ በሁለት የነብያችን የቅርብ ወዳጆች መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ የወራት ምክክርና ድርድር ጉዳዩን ሳይፈታው ቀርቶ፣ ሰ*ይፍ ይማዘዛሉ ብለህስ? ይሄን ሳስታውስህ ልቤ በሀዘን ተሞልቶ ነው። ግን እናዚያ ደጋግ ሶሀቦችና አላህን በመፍራት አቻ የሌላቸው ድንቅ ትውልዶች፣ ቅድሚያ የቱን እናስቀድም በሚል አጀንዳ (የፖለቲካ አጀንዳ ልዩነት ልትለው ትችላለህ) ጎራ ለይተው ሰውኛ የሆነ ታሪክ ተመዝገበ።

በነብያችን የህይወት መንገድ ቀስ እያልን ስናዘግም፣ የነብያችንን ባልደረቦች ስናስታውስ የምናነበው የታሪክ ምእራፍ ... በዚህ ምድር ላይ ስትኖር ሙስሊም በመሆንህ ብቻ የምታገኘው የተለዬ ነገር አለመኖሩን ነው። መልካምም ሆነ አስቀያሚ ነገር እንደማንኛውም ሰው ይደርስብሀል።

አኽላቅህ ፀዴ ሆንክ ወይም ከወንጀል ተቆጠብክ የህይወት ስንክሳሮች ተሰልፈው ነው የሚመጡልህ። በተለይ በማህበረሰባችንና በግለሰብ ደረጃ መጥፎና ክፉ ነገር ሲከሰት ቸኩለን ከሀጢያት/ወንጀል ጋር እናያይዛለን። ይሄ ግን ፈፅሞ የተሳሳተ አመለካካት ነው። አንዳንዱ የዋህ ፊልስጢኖች የሚሰቃዩት በሱ ወንጅል ወይም በነሱ ወንጅል ይመስለዋል። ከንቱ😡!

ስማኝማ ሙስሊም ስለሆንክ ብቻ ምን የሚቀርልህ ይመስልሀል? ምንም! ምንም አይቀርልህም ሀቢቢ። ይህንን እውነት እንድንክድና በተገኘው ቀዳዳ ሁሉ ሙስሊም አይደለህ እንዴ? እንዴት እንደዚህ ታስባለህ? ሙስሊም አይደለሽ እንዴ እንዴት እንደዚህ ታደርጊያለሽ? ሙስሊም ነው አይደል? ለምን አይተውላቸውምና አንድ አይሆኑም፣ እረ ሙስሊም ወንድማማች ነው አንድ ነን አትለያዩ፣ በዛ ወጥቶ በዚህ ገብቶ ጅኒ ጀቡቲ...እየተባለ ፍፁምነትን መጠበቅ ከፍ ሲልም ሀቅን መጋፋትና የሰዎችን የሀሳብ ነፃነት መጨፍለቅ፣ የሰዎችን የይገባኛል መብትና ንያ መመርመር እየተዘወረተ ይገኛል። እና ሙስሊም ቢሆንስ? እሺ ሙስሊማ ብትሆንስ ምን ይፈጠር?

በነገራችን ላይ ሙስሊም ስለሆን ብቻ ለራሳችን የምንሰጠው ግምትም ከእውነታው ፈፅሞ የተለዬ ነው። ሙስሊም ስለሆንክ ብቻ በትምህርት ጎበዝ አትሆንም፣ ነግደህ አታተርፍም፣ ትዳርህ አይሰምርም፣ ከአደጋ አታመልጥም፣ የመድረክ ዝግጅትህ አይደምቅም፣ ሙስሊም ሰራተኛ ስለሰበሰብክ ብቻ ድርጅትህ አያድግም፣ አታተርፍም፣ ትወድቃለህ ትነሳለህ፣ ታሸንፋለህ ትሸነፋለህ፣ ድሀ ትሆናለህ ሀብት ታገኛለህ፣ ትጣላለህ ትታረቃለህ...

🚶‍♀️➡️🚶‍♀️➡️🚶ወደ አጀንዳችን ስንመለስ...

ጉዳዩ ምን መሰለህ? በሙስሊም ማህበረሰብ መሪዎች/ኡስታዞች መካከል አንድነት የሚመስል ነገር አለ። ይዘውትርልን። ነገ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ግን አናውቅም። ሙስሊም ሰለሆን ብቻ ሽኩቻ አይደርስብንም ማለት የዋህነት ነው። በኛ የፍላጎትና የጊዜ አለመጣጣም፣ የፖለቲካው በተለይ የብሄር ፖለቲካው በከፍተኛ ሁኔታ መለዋወጥ፣ የአጀንዳ ቅደም ተከተል ላይ አለመግባባት ወዘተ የማናመልጠው ቀውስ ውስጥ ይከተናል።

የማህበረሰባችን መሪዎች/ኡስታዞች/ዑለማ ምን አልባት በአንድ ወይም በሁለት ሀገራዊ ወይም ሀይማኖታዊ አጀንዳዎች ላይ ሊለያዩና ላይስመሙ ይችላሉ። መለያየታቸው ሰውኛ ባህሪ ነው። እስከዛሬም ድረስ ያለመለያየታቸው ሚስጥር አንድም ጉዳዩን በዘዴ ይዘውት አደባባይ አልወጡትም ወይም ወደ አደባባይ የሚያስወጣ ከባድ አጀንዳ አልተፈጠረም። (የዘንድሮውን ታላቁ የአደባባይ ኢፍጣር ላይ የታየውን ሹኩቻ አስታውስ)። እርግጥ ነው ለጊዜው ከኢስላም መርህ ባልተናነሰ የፖለቲካ ስርአት ምቹነት በመሀላቸው ያለውን አንድነት የበለጠ አጠናክሮታል😊

የዚህ ፁሁፍ አላማ ለማይቀርልን ነገር ራሳችንን ማዘጋጀት ግድ ስለሚለን፣ ከተፈጠረስ ምን ብናደርግ ይሻላል በሚል የነብይህን ሱና መሰረት አድርጎ ለማስታወስ የተፃፋ ነው።

ከእለታት በአንዱ ቀን የራሳቸው ደጋፊ ባላቸው መሪዎች/ኡስታዞች መካከል አደገኛ የሀሳብ ልዩነት ቢነሳ ምን ሊከሰት የሚችል ይመስለሀል?

እያሟረትኩብህ ሳይሆን መፈጠሩ የማይቀረውን ነገር እየነገርኩህ ነው። ምን አልባት ሁለት ከባድ ሚዛን ኡስታዞች (ሰም ብጠቅስ እንዳይከፋህ ብዬ ነው😊) በተለያዬ አጀንዳ ተለያይተው ደጋፊዎቻቸውን አሰማርተው ጎራ ለይተው ሲወጋገዙ ሊያጋጥምህ ይችላል። ደነገጥክ እንዴ? ሙስሊም ስለሆኑ ይሄን አያደርጉም ብለህ ታስብ ይሆናል ፣ ሙስሊም ስለሆኑ አንዱ የአንዱን ትእዛዝ ይቀበላል ብለህ ተመኝተህ ይሆናል፣ ሙስሊም ስለሆኑ ፍላጎቶቻቸውን ትተው ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ጥቅም ቅድሚያ ይሰጣሉ ብለህ አስበህ ይሆናል። ይሁን መመኘት መልካም ነው። ታሪክ ግን እንዲህ እንዲሆን የሚፈቅድልን አይመስለኝም። ሲጀመር የመለያየታቸው ጉዳይ እኔ የያዝኩት አጀንዳ የበለጠ ጠቃሚ ስለሆነ አንተ ዝም በል ነው።

ብዙ የታሪክ መረጃ ቢኖረኝም እነዚያ የነብይህ ወዳጆች አሁን ካሉት ኡስታዞች በተሻለ የነብይህ የቅርብ ሰዎችና አላህን የሚፈሩ ነበሩ። ግን ግን የሙስሊሙ አጀንዳ ላይ የተለያዬ ሀሳብ አፈለቁ ። ለሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚበጀው ፣ ትኩረት መስጠት ያለብን ጉዳይ የቱ ነው? በሚል ጎራ በሀሳብ ተለያይተዋል። የኛም ከዚህ ተለየ አይደለም።

የማወራልህ ልዩነት በመሪነት ደረጃ ያሉትን ነው፣ ሌላውማ ካድሬ በለው። ወዳጄ በ leadership and strategy ላይ ትኩረት አድርጌ የምፅፈው ሁሉም ነገር የሚሽከረከው እዛ ላይ ስለሆነ ነው። ቢሆንም ቢሆንም... ምን አልባት የፈራነው ደርሶ መሪዎች በግራና በግራ ተሰልፈው ሲወጋገዙ ብታይ ፣ ሙስሊም አይደሉ? እንዴት እንደዚህ ይደረጋል? ብለህ ከመጠየቅህ በፊት ምን ማድረግ ይገባናል በሚለው ላይ ገራገር መፍተሄ ልጠቁምህ።

🎯 የፍላጎት ስትራቴጂ

🎈1ኛ የአብደላህ ቢን ዑመርና የብዙዎቹ ሶሀባ መንገድ

ለሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚጠቅመውና ቅድሚያ መስጠት አለብን ብላችሁ ባሰባችሁት አጀንዳ ላይ እዛው ተጨቃጭቃችሁ፣ ተወጋግዛችሁ ጨርሱ። እኔ እንደዚህ አይነት ሽኩቻ ውስጥ አልገባም ብለህ ራስህን ከየትኛውም ቡድትነኝነት ታቅባለህ፣ ማንንም በአደባባይ አትደግፍም አትቃወምም፣ ሶላትና ፆምህን እያደረክ ዒባዳህ ላይ መበርታት ነው። አንዱ አሸንፎ ኢስላምንና ሙስሊሞችን የሚጠቅም ስራ ከሰራ ታግዛለህ።

🎈2ኛ የአማር ቢን ያሲርና የዓምር ቢን ዓስ መንገድ

ሽማግሌው ዓማር ከመጀመሪያ የነብይህ ተከታዮች ውስጥና ከማንም በፊት ጀነት ቃል የተገባላቸው ሲሆን፣ አዛውንቱና ሙእሚኑ ዓምር መካ ከመከፈቱ ቀድሞ ብሎ የሰለሙ ናቸው። ሁለቱም በተለያዬ ሜዳ ሀቅ ነው ብለው ያመኑበትን አጀንዳ ደግፈዋል። ቅድሚያ ልንሰጠው ይገባል ብለህ ያመንክበትን ሀሳብ የሚያራምደውን መሪ/ኡስታዝ መከተል። አርጅተህም ቢሆን ላመንክበት ነገር መታገል።

🎈3ኛ የአቡ ሁረይራና የዓብደላ ቢን ዓባስ መንገድ
ኮሽታ ከሰማህ፣ ፍትጊያና የቃላት መወራወር ከተመለከትክ ወገብህን ጠበቅ አድርገህ ነገሩን ለማረጋጋት መሞከር፣ ለማስማማት መጣር፣ ሽምግልና ላይ መበርታት ። ቁርኣኑም ያግዘሀል።

በመጨረሻም የዱዐን ሀያልነትና በአላህ ላይ የሚደረግን ተስፋ፣ አላህ ለሙስሊሞች የሰጣቸውን የልብ መረጋጋትንና ሞራል፣ በአኼራ ደግሞ ያዘጋጀላቸውን የሰላም ሀገር ጀነትን ዘንግቼ እንዳልሆን ልብ በል።

በነገራችን ላይ በዚህ ሽኩቻ የሚያሳዝነው ነገር ሀይል ይባክናል፣ ጥላት ይስቅብናል፣ ጥላት አንዱን ደግፎ ሌላውን ለመጣል በርትቶ ይሰራል በመጨረሻም ሁለቱም ይወድቃሉ። ሙስሊም አይደሉ ለምን እንደዚህ ያደርጋሉ? ብለህ ከጠየክ መልሱ... ሙስሊም ቢሆኑስ? ውጤቱ ጠፍቷቸው መሰለህ? በድጋሜ እያሟረትኩብህ አይደለም።

ሰላም!
እናመሰግናለን 🙏🙏

ለ14 ሰዎች የስራ እድል በዚ ወር የተፈጠረላቸወረ ሲሆን ሁሉም ወደ ስራ ገብተዋል በአላህ ፍቃድ አዋሽ ከወለድ ነፃ ኢኽላስ ቅርንጫፍ ለ50 ሰዎች ለእያንዳንዳቸው 1000ሺ ብር በአካውንታቸው ስላስገባልን ከልብ እናመሰግናለን 🙏

ሀላል በጎ አድራጎት ማህበር ዲላ🥰🥰

https://www.tgoop.com/halale_merdaja_dilla
እውነት ወይም ሀሰት ፣ ዒማን ወይም ኩفር ፣ ጀነት ወይም ጀሃነም እንዲህ እያለ ነው ህይወት የሚመራው ። ጉዞውም ወደዚያው ነው ። እነዚህ ምርጫዎች መሃል የሚባል የላቸውም ። በዒማን ትኖራለህ አልያም በኩفር ። ከእውነት ጋር ትቆማለህ ወይ ደግሞ ከሀሰት ፣ በመጨረሻም ጀነት አልያም ጀሐነም ትገባለህ ። ወደ ኢስላም መግቢያው የምስክርነት ቃልም የሚያመለክተን ይህንኑ ነው ። በሀሰት የሚመለኩ ጣዖታትን እርግፍ አድርጎ የአላህን ብቸኛ እውነተኛ አምላክነት መመስከር ነው ። ከውሸት ወደ እውነት ። ወደ እውነት የሚጠራህ በዒማንህ ስትደክም የሚመልስህ ወዳጅ ከሌለህ የተከበብከው በውሸታሞች ነው ። እውነተኞች ግባቸው ጀነት ነው ። ጉዞዋቸውም በዒማን ነው ።
https://www.tgoop.com/halale_merdaja_dilla
Forwarded from Men Har
አረፋን ከመሳኪኖች ጋር #በሀላል በጎ አድራጎት ማህበር

እኛ እያለንማ የኢድ ቀናቸዉን ተከፍተዉ አያሳልፉም። ወላሂ እኛ እያለን ጉድለታቸዉ እንዲሰማቸዉ ማድረግ የለብንም። በምንችለዉ እንረባረብ እና መጪዉን የኢድ ቀን ደስታ እንሙላላቸው ኢንሻ አላህ

ከታላቅ የምስራች ጋር የበሬ ዋጋ አስወደዳቹ ለምትሉን ይቅር በሉን🙏 ትክክለኛ ደስታ በእርዳታ

👉ሀላል በጎ አድራጎት ማህበርን በምትችሉት ሁሉ ማገዝ ለምትሹ አካላት፦

አድራሻችን፦ ዲላ ቢላል መስጂድ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ ያገኙናል።

ስልክ፦
09-12-33-00-91
09-30-66-66-13
09-10-88-30-37

#ኑ_በጋራ_ሆነን_የተሻለ_ማህበረሰብ_ለመፍጠር_እንትጋ!

https://www.tgoop.com/halale_merdaja_dilla
አረፋን በደስታ😍😍😍
ከ200 በላይ ከብቶች ለዲላና አካባቢዋ አሰናድተን እነሆ ለእርድ አቅርበናል አንድም ሚስኪን ሳይደሰትና ሳይበላ አያልፈውም በአላህ ፍቃድ
#ሀላል_በጎ_አድራጎት_ማህበር
#ከኢማን_ኢስላማዊ_ማህበር

👉ሀላል በጎ አድራጎት ማህበርን በምትችሉት ሁሉ ማገዝ ለምትሹ አካላት፦

አድራሻችን፦ ዲላ ቢላል መስጂድ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ ያገኙናል።

ስልክ፦
09-12-33-00-91
09-30-66-66-13
09-10-88-30-37

CBE:- 1000568405677

#ኑ_በጋራ_ሆነን_የተሻለ_ማህበረሰብ_ለመፍጠር_እንትጋ!

https://www.tgoop.com/halale_merdaja_dilla
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
200 በሬዎችን ከታች ለተዘረዘሩት በተሳካ መልኩ አዳርሰናል ይህንን ስራ በኢማሞችና በሀገር ሸማግሌ አስመርቀን ጀምረነው በተሳካ መልኩ በአንድ ቀን ተጠናቋል በስራው ላይ ለተሳተፋቹ በሙሉ አላህ ያክብራቹ ለቀልጣፈ አገልግሎት ቄራን እናመሰግናለን ለዝርዝር መረጃው እመለሳለው

በዲላ
በጪጩ
በቱምቲቻ
በኢሬዴ
በኦኮሉ
በቡሌ
በአዳዶ
በኦጢቻ
በአንዲዳ
በአይጠሌ
በጓንጓ
በዳራ
በለገዳራ ኦዶላ
በጨፌ
በገደብ
በጨልቤሳ
በጎቲት
በወርቃ
በላሌሳ
በዲላ ማረሚያ
በካሊድ መስጂድ
በሙሀጅሪን መስጂድ
በአጃይብ  መስጅድ
በወናጎ

#ሀላል_በጎ_አድራጎት_ማህበር 
#ከኢማን_ኢስላማዊ_ማህበር

👉ሀላል በጎ አድራጎት ማህበርን በምትችሉት ሁሉ ማገዝ ለምትሹ አካላት፦

አድራሻችን፦ ዲላ ቢላል መስጂድ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ ያገኙናል።

ስልክ፦
09-12-33-00-91
09-30-66-66-13
09-10-88-30-37

CBE:- 1000568405677

#ኑ_በጋራ_ሆነን_የተሻለ_ማህበረሰብ_ለመፍጠር_እንትጋ!

https://www.tgoop.com/halale_merdaja_dilla
2024/09/30 14:07:51
Back to Top
HTML Embed Code: