Telegram Web
ዜና እረፍት
*
የቀድሞ የሐረሪ ጉባኤ ዋና አፈ ጉባኤ የነበሩት አቶ ሬድዋን አዱስ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ጥር 27/5/2017 ዓ/ም ከዚህ አለም ድካም አርፈዋል።

አቶ ሬድዋን ከእናታቸው አይ አሲያ ከቢር ና ከአባታቸው አዱስ ኢብራሂም በ1959 የተወለዱ ሲሆን 1ኛ ና 2ተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንደጨረሱ በህግ ትምህርት ተምረው ተመርቀዋል።

አቶ ሬድዋን አዱስ በክልሉ የሐረሪ ጉባኤ ዋና አፈ ጉባኤ እንዲሁም የሐረሪ ማረሚያ ኮሚሽን ኮሚነርና በተለያዩ የመንግስት ስራ ሐላፊነቶች ላይ ሆነው ህዝብንና መንግስትን በቅንነት አገልግለዋል።

አቶ ሬድዋን ባለትዳር ና የ3 ልጆች አባት ነበሩ።

ስራአተ ቀብራቸውም የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የሐረሪ ጉባኤ አፈ ጉባኤ አቶ ሙሔዲን አህመድና የሐረሪ ክልል የብልፅግና ፖርቲ ፅ/ቤት ሐላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዛሬው እለት የተፈፅመ ሲሆን።

በአቶ ሬድዋን ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልፀው ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለመላው የክልሉ ህዝብ መፅናናትን ተመኝተዋል።

27/5/2017
ለስድስት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር በዛሬው ዕለት በወላይታ ሶዶ ተጀመረ።
****
ውድድሩ የታዳጊ ስፖርተኞች ልማት ለአሸናፊ አገር” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን 12 ክልሎችና 2 ከተማ መስተዳደሮች አትሌቲክስ እና እግር ኳስን ጨምሮ በ11 የስፖርት ዓይነቶች ይሳተፋሉ።

በውድድሩ መክፈቻ መርሃግብር ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር
ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ ውድድሩ የታዳጊዎችን ስልጠና ውጤታማነት በተግባር በመመዘን፣ ተተኪ ስፖርተኞችን መፍጠር እና ታዳጊ ወጣቶች ወደ ክለቦችና የስፖርት አካዳሚዎች የሚገቡበትን እድል ማመቻቸትን ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

መንግስት ለስፖርት ልማት በሰጠው ልዩ ትኩረት ከኮሪደር ልማት ጎን ጎን የስፖርት መሰረተ ልማተን  በመገንባት የስፖርት ዘርፉን ለማነቃቃት በትጋት በመሰራት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለያየ ምክንያቶች ተቋርጦ የነበሩ የፖሊስ ስፖርት ውድድር፣የትምህርት ቤትና ዩንቨርሲቲዎች ውድድር የባህልና ስፖርት ፌስቲቫል ውድድርና የታዳጊ ወጣቶች ምዘና ውድድር እንደገና መጀመራቸው መንግስት ለስፖርት ልማት የሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላውን ከበደ በበኩላቸው ለ6 ዓመታት ተቋርጠው የነበረው የታዳጊ ወጣቶች ምዘና ውድድር ሐገሪቱን የሚወክሉ ተተኪ ስፖርተኞች የሚፈሩበት መድረክ መሆኑን ተናግረዋል።

ከቅርብ ግዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን በዓለም ስፖርት መድረኮች ከፍ ያደረጉ አትሌቶች ተተኪ በማጣታቸው አንገት የሚስደፉ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳደሩ የኢፌዴሪ መንግስት ተተኪ ስፖርተኞች የሚፈሩበት የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ውድድር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረጉ የሚደነቅ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ስፖርት ለሀገረ መንግስት ግንባታ፣ለአብሮነትና ልማት ያለው ሚና የላቀ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአብሮነት ተምሳሌት የሆነውን ስፖርት ለማልማት ቀን ለሊት እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያን በአፍሪካ የልማትና ብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ መንግስት እያደረገ ከሚገኝ ጥረት ውስጥ የስፖርት ዘርፉ አንዱና ዋነኛው መሆኑን  የገለፁት አቶ ጥላውን የአሸናፊነት ተምሳሌት የሆነችውን ኢትዮጵያን በሁሉም የስፖርት አይነት በዓለም መድረክ ስሟን ከፍ ለማድረግ የታዳጊ ስፖርተኞች ሚና የላቀ ነው ስሉ ተናግረዋል።

ርዕሰ መአስተዳደሩ የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን ድህነትና ኋላቀርነትን ለማስቀረት ስፖርት ላይ ትኩረት ማድረግ አለብንም ብለዋል።

በዕለቱ የውድድር መክፈቻ ፕሮግራም ላይ የ12 ክልሎችና ሁለት ከተማ መስተዳደር የስፖርት ልዑካን ቡድን የተለያዩ ስፖርታዊና ባህላዊ ትርዒቶችን ለታዳሚዎች አቅርበዋል።

ሐረሪ ክልል 82 ስፖርተኞች በቦክስ፣ፓራሎምፒክ፣መስማት የተሳናቸው ስፖርት፣እጅ ኳስ፣ቅርጫት ኳስና እግር ኳስ በአጠቃላይ በ6 የስፖርት አይነቶች ይወዳደራሉ።

8ኛው የታዳጊ ወጣቶች የምዘና ውድድር ከጥር 27 እስከ የካቲት 05 ቀን 2017 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ቀጥሎ ይካሄዳል።

በፋህሚ ዚያድ

27.5.2017
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ምርታማነትን እያገዘ ያለው የኤረር መስኖ ግድብ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ SWAT ቡድን በትላንትናው ዕለት ያደረገው የChallenge ውድድር
ታንዛኒያ ባለፈው የምርት ዘመን በበቆሎ አምራች ከሆኑ አፍሪካ ሀገራት ተርታ ሁለተኛ ደረጃ ያዘች ።
*****
ከዚህ በፊት ናይጄሪያ በሁለተኝነት ትቀመጥ የነበረች ሀገር ብትሆንም አሁን ግን ስፍራዋ በታዛኒያ ተነጥቃለች።

ዘ ሲትዝን እንደ ዘገበው ከሆነ ከደበቡ አፍሪካ በመቀጠል በሁለተኝነት የተቀመጠችው ታንዛኒያ እ.ኤ.አ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ማለትም  2023 /24 የምርት ዘመን 11.7 ሚሊዮን ቶን የበቆሎ ምርት ማምረት መቻሏን የሀገሪቱ ግብርና ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል ።

ካለፈው የምርት ዓመት በፊት ቀድሞ ከነበረው ምርት ጋር ሲነፃፃር 6.4 ቶን ብልጫ አለው ተብሏል ።

ሀገሪቱ ለበቆሎ ምርት  መሻሻል ባደረገችው የማደበሪያ ድጎማ ፣ የማሽነሪ እንዲሁም ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችሉ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ማሻሻል በመቻሏ የመጣ ለውጥ ነው ተብሏል።

የበቆሎን ምርትማት ከሚቀንሱት መካከል አንዱ በቆሎን የሚመገቡ ፀረ ሰብል የሆኑ የተለያዩ ነብሳቶች ናቸው የሚለው የዓለም አቀፍ ግብርና ትስስር ድርጅት ፤ ታንዛኒያ ከጅምሩ ይህንን ለመከላከል በሰራቸው ስራ ጥሩ ውጤት አስመዝግባለች ብሏል።

በሩሲያና በዩኩሬን ጦርነት ምክንያት የማዳበሪያ ዋጋ መናር ለአፍሪካ ገበሬዎች የምርት ዓመቱን ያከበደ ቢሆንም እንደ ታንዛኒያ ያሉ ሀገራት  ድጎማ በማድረግ ብቻ ችግሩን መቋቋም ችለዋል ብሏል ድርጅቱ።

በአፍሪካ ቀዳሚ የበቆሎ አምራች ሀገር  በመሆን በዓመት ከ17 ሚሊዮን ቶን በላይ በማምረት ደበብ አፍሪካ ስትመራ ታንዛኒያ እና ናይጄሪያ ተለዋዋጭ ምርትን በየዓመቱ በማስመዝገብ የሁለተኛኝት ደረጃው ላይ ተፈራርቀው  ይቀመጣሉ ።

የተለያዩ ማመለከቻዎች እንደሚጠቀሙት  ደግሞ ኢትዮጵያ እና ግብፅ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይይዛሉ ።

በዓለማችን ከፍተኛ የበቆሎ አምራች ሀገር አሜሪካ ናት ። የዓለምን 32 እጅ ምርት ወደ  ጎተራዎ ተስገባለች ። ቻይና እና ብራዚል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን  ይይዛሉ ። በምስጋናው  ሀይሉ

28 05 17
2025/02/05 10:44:01
Back to Top
HTML Embed Code: