Telegram Web
#እባካችሁ ትኩረት ለገጠሯ ቤተክርስቲያን 🙏🥺
ከ500 ዓመት በላይ ያስቆጠረው የመጨካት መድኃኔዓለም ድረሱልኝ እያላችሁ ነው🥺😭🙏
#ኦርቶዶክሳውያን እባካችሁ ቸል ሳትሉ ይህንን መልዕክት አዛምቱት ክርስቲያናዊ ግዴታ ነውና #ላይክ #ሼር#ኮሜንት በማድረግ በመላው አለም ይሰራጭ😭🙏🙏

ለሚድያችን በተደረገ ተደጋጋሚ ጥሪ መሰረት ከጥምቀት በዓል ቀደም ብለን ከአዲስ አበባ 340 ኪ.ሜ ተጉዘን መንዝ ቀያ ወረዳ ስር በሚገኘው በእግራችን ለሁለት ሰአት ተጉዘን መጨካት መድኃኔዓለም ደረስን ስንደርስ የተደረገልን አቀባበል እጅግ ደስ ይላል እዛ እንግዳ በጣም ይከበራል ቀጥታ ወደቤተክርስቲያን አመራን ይህ ታላቅ ቦታ በ14ኛው ክ/ዘመን የተመሰረተ ብዙዎች የሥላሴን ልጅነት ያገኙበት ቀድሞ ነገስታቱ ጳጳሳቱ የሚጎበኙት የሚሳለሙት የሚባረኩበት ነበረ አሁን ግን😭
ከአከባቢው ወይም ከአጥቢያው ህዝብ ውጪ የሚጎኘው የሌለ አሳዛኝ የገጠር ቤተክርስቲያን ነው።
ቤተመቅደሱ ዙሪያው ውስጡ እንኳን ኮርኒስ ይቅርና ምንጣፍ የለውም ሳር በማጨድ ይጎዘጎዛል ውስጥ አገልግሎት ሲኖር ከቁንጫና ከምሰጥ ጋር ግብግብ መፍጠር የግድ ነው። እንደዚ ብዙ ችግር እያለባቸው ካህናቱ ምንም አይነት ደምዝ ሳይከፈላቸው ከግብርና ስራቸው ከሚያገኙት ብቻ ቤተክርስቲያንን ያገለግሏታል። በጣም የገረመኝ በአከባቢው የሚኖሩት ህዝቦች 25ብቻ ናቸው። አረጋውያን ናቸው በአመት ከሚያገኙት የእህል ምረት 50ኪሎ እያዋጡ ቤተክርስቲያን እንዳትዘጋ እና ቀድሞ የነበረውን በአዲስ በመስራት ላይ ይገኛሉ። ይህ ቤተክርስቲያን ከ500 አመታት በላይ አስቆጥሯል አሁን በከባቢው ያሉ ምዕመናን 25 ብቻ ናቸው እናም እነዚ አባቶቻችን እባካችሁ ሳንሞት ያላቅም ብንጀምረውም መድኃኔዓለምን አምነን ነውና የተጀመረው አልቆ እንድናይ አግዙን እያሉ በእንባ እየተማጸኑ ነው😭😭
ቤተልሄሙ በሳር ክዳን ነው ያለው
መቅደሱ ውስጡ በምስጥ እየተበላ ሊወድቅ ነው😭
ምንጣፍ ሲያምረን ግን አቅም የለም
አልባሳት የለም ቀድሞ የነበረን ነው ከጊዜ ብዛት እየተቀዳደደ እኛም እየጣፍን ነው የምንቀድሰው
25 ምዕመን በአመት ከሚያዋጣው 50ኪሎውጪ ሌላ ገቢ የለንም
በምስጡ ምክንያት አዲስ ቤተክርስቲያን ጀምረን ይኸው ለረጅም አመታት በአቅም እጥረት ከቆመብን
በእንባ የምንማጸናችሁ የጀመርነውን እንድንጨርስ ምንጣፍ እንዲኖረን ከምስጡ ከቁንጫው ከአውሬው እንድንገላገል የተቻላችሁን እንድታግዙን በመጨካት መድኃኔዓለም ስም እንለምናችኋለን 🙏🙏🙏🥺🙏🙏
የቤተክርስቲያኑ አካውንት
ንግድ ባንክ👇
ስም :-የመጨካት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን
አካውንት ቁጥር:-1000257812433
ለበለጠ መረዳት:-0905269926

#ጥላ ሚድያ
07/05/2017 ዓ.ም
እዛው ቦታው ላይ ተገኝተን ዘገብንላችሁ።
2025/03/09 04:36:56
Back to Top
HTML Embed Code: