tgoop.com/husseyn_y_abdery_wedaj/4000
Last Update:
#ረመዷን_12
በሂጅራህ አቆጣጠር በ597 አ.ሂ ፣ በረመዷን 12 ቀን ላይ ነበር ዓሊምና ሙሐዲስ የሆኑት “ኢብኑ ጀውዚይ” በበግዳድ ሀገር ላይ ያረፉት። "ረሒመሁሏህ"
#ረመዷን_13
በሂጅራህ አቆጣጠር በ16ኛው አ.ሂ አመት በረመዷን 13 ላይ ነበር ኸሊፋው ዑመር ኢብን አል-ኸጧብ [ረዲየሏሁ ዐንሁ] የ“በይተል መቅዲስን ” ቁልፍ ለመረከብ ሻም ሀገር የከተሙ
#ረመዷን_15
ከሂጅራ በኃላ በ3ኛው አ.ሂ በረመዷን 15 ላይ ነበር የመልዕክተኛው ﷺ የልጅ ልጅ የሆኑት “ሐሰን ኢብኑ ዐልይ” የተወለዱት። (ረዲሏሁ ዐንሁማ)
#ረመዷን_16
በሂጅራህ አቆጣጠር በ58ኛው አ.ሂ ፣በረመዷን በ16 ላይ ነበር የአቡበክር ሲዲቅ ልጅ፣ የመልዕክተኛው ﷺ ተወዳጅ ባለቤት የሆነችው "እናታችን ዓኢሻህ"(ረዲየሏሁ ዐንሃ) ይችን ዓለም የተሰናበተችው ።
#ረመዷን_17
በሂጅራህ አቆጣጠር በ2ኛው አ.ሂ በረመዷን በ17 ላይ ነበር ... ታላቁ የ#በድር ጦርነት የተካሄደው። አሏህ መልዕክተኛውን ﷺ እና ከእርሳቸው ጋር የነበሩትን ሱሐባዎች ድል ያጎናፀፈበት ታላቅ ጦርነት ነበር።
#ረመዷን_18
በሂጅራ አቆጣጠር በ21ኛው አ.ሂ በረመዷን በ18 ላይ ነበር ... ታላቁ የጦር መሪ "ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ" (ረዲዬሏሁ ዐንሁ) ይችን ዓለም የተሰናበቱት።
#ረመዷን_20
ከሂጅራ በኃላ በ8ኛው አ.ሂ በረመዷን 20 ላይ ነበር.... መካ ሀገር በሙስሊሞች የተከፈተችው።
#ረመዷን_21
ከሂጅራ በኃላ በ3ኛው አ.ሂ በረመዷን 21 ላይ ነበር .... መልዕክተኛው ﷺ ለልጅ ልጃቸው "ሑሰይን" ዐቂቃ ያረዱት። (ዐቂቃ ማለት ለተወለደ ልጅ በ7 አመቱ የሚታረድ እርድ ነው )።
:¨·.·¨: ❀
`·.ሑሰይን የዐብደሪይ ወዳጅ
T.me/husseyn_y_abdery_wedaj
BY ሑሰይን የዐብደሪይ ወዳጅ - official

Share with your friend now:
tgoop.com/husseyn_y_abdery_wedaj/4000