tgoop.com/husseyn_y_abdery_wedaj/4003
Last Update:
#ረመዷን_22
ከሂጅራ በኃላ በ40ኛው አ.ሂ፣ በረመዷን 22 ላይ ነበር ሐሰን ኢብኑ ዐልይ አባታቸው ከተገደሉ በኃላ ኺላፋነትን የተረከቡት። (ዐለይሂመ ሰላም)
#ረመዷን_23
በሂጅራ አቆጣጠር በ9ኛው አ.ሂ፣ በረመዷን 23ተኛው ቀን ላይ ነበር ... ሱሓቢዩ "ሙጊራ ኢብኑ ሹዕባ" ሙሽሪኮች የሚገዙትን "አል-ላት" የተባለን ጣኦት ያፈረሰው።
ረመዷን_24
በዑመር ኢብን አል-ኸጧብ ትዕዛዝ ዐምር ኢብን አል-ዐስ በሂጅራ አቆጣጠር በ20ኛው አ.ሂ ግብፅን ከፍተዋል። በ21ኛው አ.ሂ፣ በረመዷን 24 ደግሞ በግብፅ ሚገኘው "ዐምር ኢብን አል-ዐስ" በመባል በስማቸው የተሰየመው መስጅድ ግንባታው ተጠናቋል።
#ረመዷን_25
ከሂጅራ በኃላ በ8ኛው አ.ሂ፣ በረመዷን 25 ነበር መልእክተኛው ﷺ ኻሊድ ኢብኑ ወሊድን ጣኦታትን እንዲያፈርስ የላኩት፤ እንዲያፈርስ ከተላከበት ጣኦታት መካከል "ዑዛ" የተባለ ጣኦት ይገኝበታል። እንደዚሁም ዐምር ኢብን አል- ዐስ "ሱዋዕ" የተባለን ጣኦት እንዲያፈርስ የተላከው እንዲሁም ኢብኑ ዘይድ አል-አሽሃሊይ "መናት" የተባለን ጣኦት እንዲያፈርስ የተላከው በዚህ ተመሳሳይ ቀን ነበር ።
#ረመዷን_26
በሂጅራ አቆጣጠር በ9ነኛው አ.ሂ ፣ በረመዷን 26 ነበር መልእክተኛው ﷺ ከሱሓቦቻቸው ጋር ከተቡክ ዘመቻ የተመለሱት።
#ረመዷን_27
በሂጅራ አቆጣጠር በ2ኛው አ.ሂ፣ በረመዷን 27 ነበር "ዘካተል ፊጥር" ግዴታ የሆነው።
:¨·.·¨: ❀
`·. ሑሰይን የዐብደሪይ ወዳጅ
T.me/husseyn_y_abdery_wedaj
BY ሑሰይን የዐብደሪይ ወዳጅ - official
Share with your friend now:
tgoop.com/husseyn_y_abdery_wedaj/4003