Telegram Web
የሐውልት ላይ ፁሁፍ

"ፀሀፊው በምን አረፈ?"
ተብላችሁ ብትጠየቁ
ኑሮውን ስትዘክሩ፣
እንዲህ ብላችሁ መስክሩ
ፀሀፊው ነብይ ነበረ
ብዕሩ ቀለም ተሞልታ
ልቦናው በሀሳብ ታጭቆ
እንዲፅፍ የተፈጠረ
አንጋሹ ቀቢው በርክቶ
ከፍ ከፍ አድራጊው በዝቶ
በእብሪት እንደታበተ
ጥቂት መስመር እንደጫረ
በሆነ መድረክ እግርጌ
ጭብጨባ ጨፍልቆት ሞተ።

ገጣሚ:- ቴድሮስ ፀጋየ

@hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈
.......... መሪና ተመሪ

በጉደኞች ....ቀዬ
በጉደኞች...ሀገር

ምራኝ ...ምራኝ ብሎ
በወጉ ...በልኩ ፥ እጁን ያልሰጠ ሰው
ገደል የገባ እንደው...
አውቆ ጣለኝ ብሎ ...መሪን ነው ሚወቅሰው

እንዲሁ ባለ ዘንግ ...መንገድ አመላካች
እርምጃ ባይለካ
ከፍታ ባይመጥን ... ላመነው ተመልካች
እያደናበረ
ገጣቢ አስገጣቢ ፥ ይሆናል አስፈንካች ።

አብርሀም_ተክሉ

@hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈
አንቺን ለመርሳት
"""""""""""""""""""
ጥለሽኝ ከጠፋሽ
ከጠላሽኝ ኃላ ምን ያልሆንኩት አለ፤
ብዙ የለመደ
መከረኛ ልቤ ሰርክ አንቺን እያለ፤
ከንፍስያዬ ጥግ
ስቃይና ህመም እየጎነቆለ፤
ከእሸት እምነቴ
ረመጥ እሳትን እየፈለፈለ፤
እንቺ ከሄድሽ ኃላ ምን ያልሆነው አለ?

አንቺ ከሄድሽ ኃላ
ጥለሽኝ ከጠፋሽ ጊዜው ከነጎደ፤
መከረኛ ልቤ
እረሳሽ እያለ ብዙ ተላመደ፤
ሴቶችን ለመደ፥
ሲጋራን ወደደ፥
መጠጥን እያለ
ባሰኘሽው ሰዓት
ለትኩስ ስሜቱ ከጊዜ አረፈደ!

ግና አንቺ የለሽም
ሴቶቹን ብቀርብም እንዳንቺም አላገኝ፤
አልባብ እንሸት ብለው
ከደረት የነፉት ሽቶ ሰነፈጠኝ!
ኩላቸው አይደምቅም
ሊፒስቲክ ቢቀቡ ካንቺ በልጦ የነሱ፤
ጭራሽ ያስጠላሉ
አውሬ ያስንቃሉ መስለው ደም የላሱ፤
ያላንቺ ማን ሊገኝ ምድርን ቢያስሱ..

(ይገርምሻል ውዴ)
አሁን በቀደም ለት
ያስረሳኝ ይመስል እያጨስኩ ሲጋራ፤
አፌ በለሆሳስ
ስላንቺ ውዳሴ ከራሱ እያወራ!
ቁልቁል እየሄድኩኝ
ጭሱን ስተነፍስ የማጉ'ት ትምባሆ፤
ከሰተሽ ከፊቴ በጭስ አንቺን ስሎ!
ስትፍለቀለቂ፥
ስትፈነድቂ፥
ከኔ ስትቦርቂ!
ጣልኳት ሲጋራዬን በእግሬም እረገጥኳት፤
መች በሱስ አጥምዳኝ ያጨስኩት ለመርሳት!

(ይገርምሻል ውዴ)
አሁን በቀደም ለት
ዘው ብዬ ገባሁ ከገዳም ነሽ ጠላ፤
አንቅሬ ልተፋሽ
መለኪያ ጨብጬ ልጋት ካቲካላ!
መቼም እሳት አይደል
አረቄ አወጣጧ ሙያ የገዳምነሽ፤
ከራሴ እርቄ
በሁለት መለኪያ ከወኔዬ ስሸሽ!
ልቤን እየሞቃት
ነፍሴን እየሳትኩኝ አይኔ እየሰከረ
የአንድ ያንቺ ሲገርመኝ
ሁለት አንቺን አርጎ ያሳየኝ ጀመረ!
ወጣሁ ስደናበር
ብዙ ብትሆኚብኝ ከግድግዳው ሳፈጥ፤
የፍቅር አኩኩሉ
ካንቺ ተደብቆ ወዴትስ ሊመለጥ?

መች ሊያስጥለኝ ውዴ
ድካም እንጂ ትርፉ ለሌላ መ.ጋ.በ.ዝ፤
ፍቅር ከገነነ
መች ይስጥላል ሌላ? መች ያስጥላል ግዑዝ?

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)


@hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈
እግዚኦ ጊዜው ያማል፤ጭንቅ ሆኗል ዘንድሮ
አዲስ ዘመን መቶም፤ዳግም ዛሬም እሮሮ
ሰማይ ጥቁር ሆነ፤ምድር ደም ለበሰች
እንደ ሲኦል በሮች፤የሰው ነፍስ ረከሰች
ሟች አፈር ራቀው፤ልቡ ተገነዘ
ገዳይ ነፍስ ነስቶ፤ያለ ፍርድ ተጓዘ።
አረ ይሄ ምንድነው?
የአኬልዳማ ምድር...
የአይምሮ አልባ ዘመን፤የዲያቢሎስ ህብር።

ልጅ ሞሌ


@hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈
ይድረስ👉 ለማይደርስልን መንግስት 😒

እንደምነህ መንግስት እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልን የለውጥ ጎዳና
ሺዎችን ገብረን ፣ ለአንድ ብልፅግና
እየተሰበርን ሰበር በሚል ዜና
ተራ እየጠበቅን ፣ ለሞት ተሰልፈን
እግረ መንገዳችን ፣ድንገት ከሞት ተርፈን
ከደብዳቢ ጋራ
ደብዳቤ እስክንልክ፣በደማችን ፅፈን
እኛ አለን በተድላ
እንደምን ነህልን?
እንደምን ነህልን ካልንህስ በኋላ ?!
እኛ አለን በድሎት
እኛ አለን በፀሎት
ከገዳያችን ጋር ቀብር ስናስፈጥም
ስንኖር ኢትዮጵያዊ
ስንሞት ምን እንደሆንን፣ባናረጋግጥም
እኛ አለን በተአምር፣እኛ አለን በደህና
እየተገደልን
"መግደል መሸነፍ ነው"፣በሚል ፍልስፍና !
አንተ ግን እንዴት ነህ?
እልፎች ሚቃወሙህ፣የብዙዎች ምርጫ
ፍትህ ለሚጠይቅ ፣ምትሰጥ መግለጫ
የእልፎች አሻጋሪ ፣የእልፎች እንቅፋት
ትኩረት የምትሰጥ
ከሰዎች ነፍስ ይልቅ ፣ለአበቦች መጥፋት
እንደምን ነህ አንተ?!

@hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈
'እነሱን'
ሳያቸው 'እነሱን'
ስሰማ ገድላቸውን
ሳይ ውበታቸውን
ተመኘሁ መሆንን
እናማ....
የሠሊጥ ንጣቴን በከሠል ለቅልቄ
ከኑግ እደመር ዘንድ እኔነቴን ንቄ
"ድሮ ግን ማን ነበርኩ?"
እስኪያሰኘኝ ድረስ
እስክጠይቅ ራሴን
አጣሁ እኔነቴን
ሄድሁ ተደባለቅሁ
'እነሱን'ም መሠልሁ
አብሬ ልወቀጥ
እራሴን አቀናሁ
እናማ....
ዘነዘናው መጣ
ሙቀጫውም መጣ
ከየቱ ገብቼ ከየትኛው ልውጣ
ከኑግ እንዳልሆነው
'እነሱን'አይደለሁ
ከሠሊጥ እንዳልሆን
መልኬ'ኮ ልዩ ነው
አዬ.....
ሊያቅተኝ ነው መሰል
ማፅዳት የኔን ከሰል
እናማ....
'እነሱን'ልሆን ስል ያጣኋትን ውበት
አሁን ከየት ላምጣት
ለካስ....ለካስ
ልሆን ስል 'እነሱን'
አጥቼ ነው ራሴን
መስከረም 24 2013
የቲ

@hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈
በቃሌ ልይዝሽ እያነበነብኩኝ፤
በመንገድ ሳልፍ ነው አብዷል የተባልኩኝ፤
ማበዴ ካልቀረ
ትውስታ ምስልሽን ለመቅረፅ ስታገል፤
አንድ ነገር ልበል!...
.
ጎዳናው በሙሉ ሞልቷል ያንቺ ምስል፤
ተራማጅ ባያይም
መንገድ ዘግቻለሁ እንዳይረግጡብኝ ስል🙄
ከስንቱ ተጣላሁ ካላፊ ካግዳሚው፤
ባልጠፋ ማረፊያ
መንገድ ላይ መለጠፍ አደራ እንዳትደግሚው፤
(ልዑል ኃይሌ)
ጥቅምት 19,13


@hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈
#የጎዳናው ስዕል!
።።።
ምን ናፈቀህ አትበይ ...ያልናፈቀኝ የታል ?
ቀን በገፋ ቁጥር ፍቅር ከሰው ሸሽቷል
አሁን እንደ ድሮው እኔን መንገድ አይቶ
ናፈከኝ አይለኝም ከጉያው ውስጥ ከቶ።
ትናንት የነበረው የገጠሬው ልማድ
በከተሜው ልምሻ በፅኑው ታሞብን
ለእንግድነት ብንሄድ ፍቅር ጎደለብን
ጎደለ !
ጎደለ !
እንዲያ እንደ ቀድሞ እግር የሚያጥብ የለ ...
እሸቱን ፈልፍሎ የሚያጎርሰን የለ ...
ክፋት ተዚህ አልፎ ምስኪኖች ደጅ ዋለ ።
እቴ ምን አለፋሽ !
ሁሉ ወዝ አልባ ነው ያልሞላ ጎዶሎ
መንፈሱ ሲታመም ደጁ ተጠልሎ
ሰው ለፈጣሪው እንዳይወድቅ
ከእግሩ አሸብርኮ.. .
ግቢው በግፈኞች ተገዝቷል በምርኮ።
እዚህም እዛም ያለው የሚሰማው ጩኸት
እዚም እዛም ያለው የሚታየው ስዕል የጎዳናው እውነት
በማር ተለውሶ እንደሚቀርብ ሬት
በገንፎ ውስጥ ያለ የእሾህ ተምሳሌት
እዚም እዛም ያለው የተንኮል መራቀቅ
ለጆሮ እንኳ ከብዶ አቤት እንደሰሚሰቅ..
እቴ ምን አለፋሽ?!
የቤተ መቅደስን ደጃፍ የሚከቡ
ለአይን ተሽሞንሙነው እጅግ የተዋቡ
ከነዛ አፀዶች በላይ ዳስ ከልለው
ተመስገን የሚሉት መዝሙራት አፍልቀው
ወፎች ወዴት ጠፉ ?
አባቶች ፀጋ አተው ...
ለምን በኛ ከፉ ?
ምን ያለው ዘመን ነው ?
የዘመን ቅራሪ ፈጣሪን ማበያ
አሁን ያለንበት ...
የፈጣሪ ቤት ነው ወይስ ነው ገበያ?
እዚም እዛም ያለው የሚሰማው ጩኸት
ንዋይ ማግበስበስ ነው እግዜር የሌለበት
እሺ ወዴት እንጩህ?
ወዴት እንሸሸግ?
ሁሉ አልባ ነው ክብር ሁሉ አልባ ነው ማረግ።
ታመምን ታመምን
ለፍቅር ጎደልን ...
ለህብረት ሰነፍን...
ከአዳምነት ወርደን ለዘር ተፋለምን
ለክህደት ተድረን ትዳርን ወሸምን
ሁሉ ወዝ አልባ ነው ያልሞላ ጎዶሎ
ፍቅር ሀገር ለቋል ጓዙን አንጠልጥሎ
አሁን እዚህ ያለው የሚሰማው ጩኸት
ከአንገት በላይ ያለው ያስመሳዮች ስብከት
ለጉድ ተዥጎድጉዶ በቃላት ቢወርድም
ለጆሮ ነው እንጂ ከልብ ውስጥ አይያድርም
እቴ ምን አለፋሽ ?
ጓደኝነት ሞቷል.. . ትዳር ተቀዛቅዟል
ስጋ ያቀዳጀው ... ዝምድናም ተሽሯል
ዓለሙ ብልጥ ነው የነዋይ ናፋቂ
ጎዳናው ሸንጋይ ነው ሳይደሰት ሳቂ
ሁሉም አስመሳይ ነው
የጥርስ ፈገግተኛ ከአንጀት አታላይ
የቃላት አርበኛ ... ያነጋገር ሸንጋይ
ምን ናፈቀህ አትበይ ያልናፈቀኝ የታል ?
በሰው ተከብቤ ዓይኔ ሰው ተርቧል።
...
(ሚካኤል አስጨናቂ)


@hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈 @hutoffun 👈
Forwarded from Qualitybuttonbot
📚ልዩ የግዕዝ ትምህርት📚
📕ስለ ግእዝ ቋንቋ በቀላሉ መማር ፤ ማወቅ ፤ ማጥናት መናገር ፤ ብዙ የብራና መጻሕፍትን አንብበው መረዳት ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ ምን ይጠብቃሉ ተቀላቅለው መማር ይችላሉ🙏
👇ተቀላቀሉን👇
https://www.tgoop.com/joinchat-AAAAAFLvqSNaKPXNxFAPBA
እንኩዋን ለሊቀ መላእክት "ቅዱስ ሚካኤል" እና "ለቅዱሳኑ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት

=>ቅዱስ ሚካኤል በጥንተ ተፈጥሮ በኢዮር: ኃይላት በተባሉት ነገደ መላእክት ተሹሞ ነበር:: ሳጥናኤል በካደ ጊዜ እግዚአብሔር ባወቀ: አንድም በትሕትናውና ደግነቱ በ99ኙ ነገደ መላእክት ላይ ሁሉ ተሹሟል::

+ከፍጥረት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የቅዱስ ሚካኤልን ያሕል ክብርና ርሕሩሕ የለም:: በምልጃውም: በረዳትነቱም የታወቀ መልአክ ነው:: መጽሐፍ "መልአከ ምክሩ ለእግዚአብሔር" ይለዋል:: "ወስሙ መስተሣሕልም" ይለዋል:: ቂም የሌለው: ለምሕረት የሚፋጠን: ደግ መልአክ ነውና::

+በብሉይ ኪዳን በመከራ ለነበሩ ቅዱሳን ሁሉ ሞገስ: ረዳትና አዳኝ ቢሆናቸው "መጋቤ ብሉይ" ተሰኝቷል:: እሥራኤልን 40 ዘመን በበርሃ መርቷል:: መግቧልም:: ቅዱስ መጽሐፍ ስለ እርሱ ብዙ ይላል:: (ዘፍ. 48:16, ኢያ. 5:13, መሳ. 13:17, ዳን. 10:21, 12:1, መዝ. 33:7, ራዕይ. 12:7)

+ደስ የሚለው ደግሞ ርሕሩሑ መልአክ ከእመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር አለው:: ከእናቷ ማሕጸን ጀምሮ እስከ ዛሬ እነሆ አብሯት አለ:: ደስ ብሎት ይታዘዛታል:: ማማለድ ሲፈልግም "እመቤቴ ሆይ! ቅደሚ" ይላታል:: ወደ እሳት መጋረጃ አብረው ገብተው ለዓለም ምሕረትን: በረከትን ያወርዳሉ::

+"+ ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ +"+

=>ዳግመኛ በዚህች ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ኢያሱን እንደ ረዳው ታስተምራለች:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+በመጽሐፈ ኢያሱ ምዕራፍ 5 ላይ እንደ ተጻፈው ቅዱሱ መልአክ ለኢያሱ ተገልጦለታል:: እሥራኤልን በምድረ በዳ የመራ ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ሲያርፍ ታላቅ ሐዘንና ድንጋጤ ተፈጥሮ ነበር::

+እግዚአብሔር ግን ኢያሱን አስነስቶ አረጋግቷቸዋል:: ቅዱስ ሚካኤል 40ውን ዘመን እሥራኤልን ደመና ጋርዶ: መና አውርዶ: ክንፉን ዘርግቶ: ጠላትን መክቶ ከሙሴ ጋ እንደ መራቸው ከኢያሱ ጋርም ይሆን ዘንድ ከሰማይ ወረደ::

+በኢያሪኮ አካባቢም የተመዘዘ ሰይፉን ይዞ በግርማ ለኢያሱ ታየው:: ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ "አንተ ከእኛ ወገን ነህን? ወይስ ከጠላቶቻችን?" ሲል ጠየቀው:: ቅዱስ ሚካኤልም መልሶ "እረዳህ ዘንድ እነሆ የሠራዊት አለቃ ሆኜ ተሹሜ መጥተቻለሁ" አለው::

+ያን ጊዜ ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኢያሱ በግንባሩ ተደፍቶ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሰገደለት:: ቅዱሱ መልአክም አክሎ "ፍታሕ ቶታነ አሳዕኒከ እም እገሪከ: እስመ ምድር እንተ ትከይዳ ቅድስት ይዕቲ - የረገጥካት ምድር የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ" አለው::

+ኢያሱም የተባለውን አደረገ:: ለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያናችን "ለመላእክት የጸጋ (የአክብሮ) ስግደት ይገባል: በቅዱሳኑ ፊትም ጫማ ተለብሶ አይቆምም" የምትለው:: ያ መሬት ሊቀ መላእክት ቢቆምበት ተቀድሷል:: ዛሬም ቤቱ በታነጸበት: ታቦቱ በተቀረጸበት ቦታ ሁሉ ቅዱሱ መልአክ አለና ጫማን አውልቆ: ባጭሩ ታጥቆ መግባት ይገባል::

+ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከኢያሱ ጋር ሆኖ አማሌቅን ጨምሮ የእሥራኤልን ጠላት አጥፍቷል:: ጥቅመ ኢያሪኮን (ቅጥሩን) አፍርሷል:: ምድረ ርስትን አውርሷል:: በገባኦን ፀሐይን: በቆላተ ኤሎምም ጨረቃን ሲያቆም ከእርሱ ጋር ሆኖ ረድቶታል::

+"+ ዱራታኦስና ቴዎብስታ +"+

=>ቅዱሳኑ ዱራታኦስ (ዶርታኦስ) እና ቴዎብስታ (ቴዎብስትያ) የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች ናቸውና በዚህች ዕለት ይታሰባሉ:: በድርሳነ ሚካኤልና በመጽሐፈ ስንክሳር ተጽፎ እንደምናገኘው 2ቱ ቅዱሳን በተቀደሰ ትዳር ተወስነው: ሕጉን ትዕዛዙን ፈጽመው: ለነዳያን ራርተው: ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለው የሚኖሩ ነበሩ::

+ይልቁኑ ግን የጌታችን: የእመቤታችንን እና የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ ያለማስታጐል ያደርጉ ነበር:: ከጊዜ በሁዋላ ግን ሐብት ንብረታቸው አልቆ ተቸገሩ:: ግን የጨነቃቸው መቸገራቸው ሳይሆን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ ሊያቆሙ መሆናቸው ነው::

+አማራጭ ሲያጡ ተቀምጠው ተመካከሩ:: የቅዱሱ መልአክ ዝክር ከሚቀር ልብሳቸውን (ያውም የክብር ልብሳቸውን) ሊሸጡ ተስማሙ:: በዚህ መሰረት ቅዱስ ዱራታኦስ ወደ ገበያ ሲሔድ ወዳጁ ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወረደለት::

+መንገድ ላይም የጦር መኮንን ሃገረ ገዢ መስሎ ተገናኝቶ አጫወተው:: ችግሩን ጠይቆም መፍትሔውን ነገረው:: "እኔ እዋስሃለሁና ለበዓል የሚያስፈልጉህን ነገሮች ሁሉ ገዝተህ አሰናዳ" አለው::

+"እኔ ወደ ቤትህ መጥቼ ስለምስተናገድ አንድ አሣ አምጥተህ አቆየኝ:: እኔ ሳልመጣ ግን አትረደው" አለው:: ቅዱስ ዱራታኦስ የተባለውን ሁሉ ፈጽሞ ወደ ቤቱ ሲሔድ ድንቅ ነገርን ተመለከተ:: ሚስቱ ቅድስት ቴዎብስታ በቤቱ መካከል ሁና ቤቱ በበረከት ሞልቷል::

+ማሩ: ቅቤው: እሕሉ ሁሉ በየሥፍራው ሞልቷል:: ባልና ሚስቱ ደስ ብሏቸው:: ነዳያንን ሲያበሉ: እንግዳ ሲቀበሉ ዋሉ:: በሁዋላ ያ መኮንን (ቅዱስ ሚካኤል) በቤታቸው መጥቶ ተስተናገደ::

+በእርሱ ትዕዛዝ የአሣው ራስ (ሆድ) ሲከፈት በውስጡ 300 ዲናር ወርቅ (እንቁ) ተገኘ:: ቅዱሳኑ ይህን ተመልክተው ሲደነግጡ ቅዱስ ሚካኤል ክንፉን ዘርግቶ ራሱን ገለጸላቸው:: ደንግጠው በግንባራቸው ተደፉ::

+እርሱ ግን "በተገኘው ሃብት እዳችሁን ክፈሉ:: ከዚህ በሁዋላ ግን በምድር አትቸገሩም:: በሰማይም ክፍላችሁ ከእኔ ጋር ነው" ብሎ ባርኩዋቸው ወደ ሰማይ ዐረገ:: እነርሱም በሐሴትና በበጐ ምግባር ኖረው ዐርፈዋል:: ለርስቱም በቅተዋል::

+"+ ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ +"+

=>የደጋግ ክርስቲያኖች ግን የድሆች ልጅ::
*በሕጻንነቱ በግፍ ወደ ባሕር የተጣለ::
*በእግዚአብሔር ጥበብ አድጎ የግፈኛውን ንብረት የወረሰ::
*በመልካም ትዳር በቅስና ያገለገለ::
*ምጽዋትን ያዘወተረ::
*አብያተ ክርስቲያናትን ያሳነጸ ደግ ክርስቲያን ነው::
¤አርፎ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጁ በዕረፍተ ገነት አኑሮታል::

+"+ አፄ በእደ ማርያም +"+

=>"በዕደ ማርያም" ማለት "በማርያም እጅ" እንደ ማለት ነው:: እኒህ ሰው የኢትዮዽያ ንጉሥ ሲሆኑ የነገሡትም በ1460 ዓ/ም ነው:: ደጉ አባታቸው አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ሲያርፉ በመንግስቱ ተተክተው ሃገራችንን አስተዳድረዋል:: ድርሰት ደርሰዋል:: አብያተ መቃድስ አንጸዋል::

+በተለይ ለቅኔ ትምሕርት ማበብ ልዩ የሆነ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ይነገራል:: ልክ በነገሡ በ10 ዓመታቸው ግን መንግስተ ምድር በቃኝ ብለው በምናኔ በርሃ ገብተዋል:: በዙፋናቸውም አፄ እስክንድር ተተክተዋል:: ጻድቁ ንጉሥ ግን ቅዱስ ሚካኤልን ይወዱት ነበርና በዚህች ቀን ዐርፈዋል::

=>አምላከ ቅዱሳን በክንፈ ሚካኤል ከክፉው ሁሉ ይሰውረን:: ከበረከታቸውም አይለየን::

=>ኅዳር 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ
3.ቅዱሳን ዱራታኦስና ቴዎብስታ
4.አፄ በዕደ ማርያም ጻድቅ
5.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
6.ቅዱስ ባሕራን ቀሲስ
7.አባ ፊላታዎስ ሊቀ ዻዻሳት

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
2.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
3.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
4.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
5.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
6.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
7.ቅዱስ ድሜጥሮስ ሊቅ

=>+"+ በሰማይም ሰልፍ ሆነ:: ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ:: ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ:: አልቻላቸውምም:: ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም:: ዓለ
(አሌክስ አብርሀም)
🌹ካገባች በኋላ

ሌላ ወንድ አቀፋት የሚል መርዶ ሽሽት
ሌላ ሴት እያቀፍኩ በያንዳንዷ ምሽት
እሷ ናት እላለሁ
(የኔ እብደት ሲገርመኝ ይባስ የሴቶቹ)
ፍቅር የሰለቻቸው ፍቅርን የሰለቹ
እሷ ናችሁ ስላልኩ "እሷ ነን" እያሉ
እኔ እንዳነሳቸው ራሳቸውን ጣሉ





@hutoffun
@hutoffun
@hutoffun
ምንም አልል...
ሎሬት ፀጋዬ ግብረመድህን


እኽ..ሺ እንግዲህ በዝምታ
የልቤን ደም ሥር ትርታ
የደቂቅ እድሜን ትዝታ
ትር ስትል አፍታ ለአፍታ
እያዳመጥኩ እያስታመምኩ ፥ ጊዜዬን እያሠላሠልኩ
ሳልናገር ሳልጋገር ፥ እየደገምኩ እያሠለሥኩ
ሳልሰለች እየመላለስኩ......

እኽ ሺ እንግዲህ በፀጥታ
የልቤን ደም ሥር ትርታ
የእስትንፋሴን ቃል ጉምጉምታ
ትር ስትል አፍታ ለአፍታ
ሳልሰለች እየደጋገምኩ
በእግረ ህሲና እያደቀቅኩ
እየቋጠርኩ እየቆጠርኩ......

እሺ እንግዲህ አልናገርም
በአንደበቴ አልተነፍስም
በልሳኔ አመሰክርም
አልልም። ምንም አልልም
እንዲያው ዝም እንጂ ዝም ዝም
የልቤ ደም ሥር ሲያቃጭል
ልሳኔን ሲያስነሳ ሲያሰጥል
ቃላቴን ሲቃኝ ሲያጋግል
ትንፋሼን ሲያንር ሲያዳውል
ክል ሲል ትር ድም ሲል
ማዳመጥ ማስታመም እንጂ ፥ ሌላ ምንም ምንም አልል።

ጥቅምት ፦ ፲፱፻፷፫ ፒያሳ
ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድሕን
" እሣት ወይ አበባ "
@hutoffun
@hutoffun
አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ 😭የ 3 ሰዎችን ህይወት እንታደግ

እናታችን ረሂማ ስትመርቀን አግኝቶ ከማጣት ይጠብቃጩ ብላለች እግኝቶ ማጣት ቤቷ ሰተት ብሎ ስለገባ ቁስሉን ታቀዋለች ። ረሂማ እና ባሏ በሚያመጡት ደና የሚባል ህይወት ትኖር ነበር።ነገር ግን ፈጣሪ ዘሯን የሚያስቀጥል ልጅ አልሰጣትም። ከወለደች ከትንሽ አመት ቡሀላ ይሞታሉ። አይታቸው ሳጠግብ በሚያሳሳ እድሜ ላይ እያል ከአይኗ ይሰወራሉ ። 4 ልጆች ከ ሞቱባት በኋላ ፈጣሪ አንድ ልጅ ሰጣት ልጁ ግን መናገር መንቀሳቀስ አይችልም ኦቲዝም / የአእምሮ ዝግመት/ እለበት። እሱን ከወለድች ቡሀላ ብዙም ወታ መስራት አልቻለችም። ዘወትር የሷን ከጎን መሆን ይሻልና። አስከትሎም ፈጣሪ ሌላ ልጅ ተካላት ይህ ልጅ ሲተካ ግን ባል ሌላ ሴት ልቡ ከጀለ። ጥሏትም ሄደ የሰው ሀገር ሄዳ ያሰራችውን ቤት ካልተካፈልኩ አለ። በዚ ኑሮ ክራይ ተጨምሮ ብላ ብር ፈልጌ ልስጥህ አለችው ትንሽጊዜ አግኝታ በሰዎች ብር ተሰበሰበላት ብሩ ሳይሞላላት ባሏ ይሁን አሁን በማለቱ ቤቱ ተሽጦ ተካፈሉ ። ከሰው ጋር አጋጭታ ደከም ያለ ቤት ገዛች እንኳን ለመኖር ለማየት የማይመች ቤት ገብታ መኖር ጀመረች ኑሮን ለማሸነፍ ትልቁ ልጇ (ሀምዛ) ላይ ቆልፋ እየወጣች ያገኘችውን ሰርታ ትመለስ ነበር።ዛሬ ላይ እሷም ህመም ጣለባት የሀሞት ጠጠር ሰውነቷ ውስጥ በመነኘቱ operation መደረግ አለብሽ ተባለች ልጆቼ ያለኔ ምን ሊሆኑ ብላ ሰጋች በተለይ ትልቁ ያለሷ ማንም አይመግበውም። operation ከምደረግ ብላ የባህል መድሀኒት ወሰደች። የሞት ሽረት ትግል ከዛ ጉበቷ ተነካ ። መመገብ አትችልም ትንሽ ስትመገብ ሆዷ ያብጣል።ህመሟ ስለበረታ ወታ መስራት አልቻለችም። በዚ ሰአት በየእለቱ ፖንፐርስ የሚያስፈልገው ለሀምዛ ፓንፐርስ መግዣ አታለች። እነዚህ ሶስት ሰዋች ላይ ረሀብ በትሩን አሳረፈባቸው። ሲቸግራት የቤት እቃ እየሸጠች ለምግብ አውላለች።
ሰሞኑ ደወለች ኑሰይባ ቀበሌዋች ህገወጥ ቤት ነው ይነሳ ብለው ለጠፉብኝ አለችኝ። ምንም ማለት አልቻልኩም። ኑር ኢኒስቲትዩት በስራችን ያለች ሴት ብቶንም እኛም በዚ ሰአት እጅ አጥሮናል እና የናንተን እገዛ ስለምንሻ ረሂማን ለእናንተ አደራ ብለናቹሀል። አደራቹን እንደምትወጡ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ።
ረሂማን መዘየር እንፈልጋለን ለምትሉ።
አድራሻ :-ካራ ቆሬ ግራር ሀናን ዳቦ ጀርባ
ለበለጠ መረጃ:-0993815805 በመደወል በማንኛውም ሰአት ቦታዋን እናሳዮታለን
" በአንድነት የእናታችን የረሂማን እንባ እናብስ "
የሚገቡ እቃዋች
1.ፓንፐርስ 4ቁጥር
2.እሽግ ምግቦች(አስቤዛ)
3.ገንዘብ ለማስገባት:-
አቢሲኒያ ባንክ:--Rehima Abdela Ahmed
የሂሳብ ቁጥር:- 45727068
ከላይ ያሉትን ማረግ ካልቻላቹ ቀላል በሆነው share በማድረግ አደራችንን ተቀበሉን።

ከኑር ኢኒስቲትዩት

ወዳጆቼ ልብ ይሰብራል..ፅሁፉን አንብባችሁ ከስር የለቀኩላችሁን ፎቶዎች አይታችሁ የበኩላችሁን እንድታደርጉ እጠይቃችኋለሁ..ሰዉን ለመርዳት ሰዉ መሆን በቂ ነዉ።...ቻናል ያላችሁ አድሚኖች ብትለጥፉት ዩትዩብ ላይም ብዙ ተከታይ ያላችሁ ቤተሰቦች ከላይ በተጠቀሰዉ ስልክ በመደወል እናት ረሂማን አግኝታችሁ ብትሰሩላቸዉ መልካም ነዉ።

Share አይዘንጋ
ሴት አስጠኚ ለምትፈልጉ


በየካቲት መጨረሻ ላይ ፈተና እንዳለ የሚታወቅ ነው በመሆኑም ለsocial ተፈታኞች በሙሉ በአንድ ሳምንት economics የ11 እና የ12 ክፍል ሙሉውን ሪቫይዝ አድርጎ የሚጨርስ አስጠኚ ለምትፈልጉ


በሰዓት 80ብር፡
በቡድን ለሚመጡ ቅናሽ እናደርጋለን፡
በቀን ለ3ሰዓት እናስጠናለን፡



ለበለጠ መረጃ
0923428496
0966273456
Forwarded from ጎሐጽባህ
የሴት አስጠኚ ይፈልጋሉ።



ከ7 እስከ 10 ክፍል በሁሉም የትምህርት አይነቶች ብቃትና ልምድ ባላቸው ሴት አስጠኚዎች በፈለጉት ትምህርት የሚያስጠኑ ሲሆኑ ከ11 ጀምሮ ደግሞ የ social ተማሪዎችን ሙሉ ትምህርት ማስጠናት እንዲሁም ለማትሪክ ማዘጋጀት ላይ በብቃት ይሰራሉ ክፍያው እንደ ቦታው በስምምነት የሚከፈል ይሆናል።


ለበለጠ መረጃ
0923428496
0966273456
2024/09/28 08:23:54
Back to Top
HTML Embed Code: