አርብ 2:30 ማለት ከደቂቃዎች በሗላ ነው...!
ቤትዎ ይግቡ‼
በጣቢያው የዩቱዩብ መገናኛም በተመሳሳይ ሰዓት አለን!
https://www.tgoop.com/Gazetaw
ቤትዎ ይግቡ‼
በጣቢያው የዩቱዩብ መገናኛም በተመሳሳይ ሰዓት አለን!
https://www.tgoop.com/Gazetaw
የማምሻ ወግ...!
✅ፊታውራሪው ያወጓችሗል
፩(₁).«ኢትዮጵያ ማርቆስ አባቴ እስክንድሪያ እናቴ ብላ አምና የሃይማኖት ክርክር በተነሳ ቁጥር ስትሠለፍ የኖረችው ከእስክንድሪያው ፓትሪያርክ ጎን መሆኑን ታሪክ ይመሰክራል።
፪(₂).«ሀገራችንን ግራኝ በወረረ ጊዜ ካቶሊካዊ የሆኑት የፖርቹጋል ሰዎች ለእርዳታ መጥተው ታላቅ መሥዋዕት በመክፈል ሲረዱን የግብጽ እስላማዊ መንግስት ከቱርክ ጋር ሆኖ ግራኝን ሲረዳ እንደነበረ ታሪኩ ይመሰክራል።»
፫(₃).«አፄ ምኒልክ ሀገራቸውን በስልጣኔ ለመምራት አስበው አዲስ አበባ የዳግማዊ ምኒልክን ትምህርት ቤት ሲከፍቱ ግብፆች በሃይማኖት አስታከው እኛ እናስተምራለን ብለው የትምህርት ቤቱን አስተዳደር ሥራ ሥልጣን ከጨበጡ በኋላ በፈረንሳዊ ና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚሰጠው ትምሕርት በመጠኑ ከማንበብና ከመፃፍ ደረጃ እንዳያልፍ ወስነው ተማሪ ቤቱ ሲሠራ በአንድ ዓይነት ፕላንና መሠረት አብሮ ተሠርቶ ጣራው ተከድኖ፣የጣራው ፕላፎንና የመሬቱ ወለል በሳንቃ ማልበስና ማንጠፍ መዝጊያ እና መስኮት መግጠም ሲቀረው ሥራው ቆሞ የእርግቦች መኖሪያ ሆነው የኖሩትን ሁለት ክፍሎች ማስጨረስና በሥራ ላይ ማዋል ይመስል በቸልተኝነት ማኖራቸው የትምሕርቱንም አሰጣጥ በዘመናዊ እቅድ ባለመምራታቸው በአባይ ጅረት ምክንያት ኢትዮጵያ ሠልጥና ኃይል እንዳታገኝ የሚመኘውን የሀገራቸው እስላማዊ መንግሥት ሲአደርገው የኖረውን የቁጥጥር ፖሊሲ ሲጠብቁ እንደነበረ ያሳያል።»
በአባይ ጅረት ምክንያት ኢትዮጵያ ሠልጥና ኃይል እንዳታገኝ የሚመኘው የግብጽ መንግሥት፣ፊታውራሪ አርአያ ሥላሴ ዘለቀ፣ከገጽ 14—15 የተቆነጠረ!
ወጉን ያጋራችሁ ሰውየ @gazetaw1 ውስጥ አለ!

«ቆጣ ቆጣ አልሽሳ»...!?
አጨራረሱ «ኦሮማይ»ነው።
ደግሞ ጠቅላዩ በዓሉ ግርማ'ን «የመደመር መንገድ»መጽሐፋቸው ላይ ጠርተው የማይጠግቡት ነገር ይገርመኛል!
https://www.tgoop.com/Gazetaw
አጨራረሱ «ኦሮማይ»ነው።
ደግሞ ጠቅላዩ በዓሉ ግርማ'ን «የመደመር መንገድ»መጽሐፋቸው ላይ ጠርተው የማይጠግቡት ነገር ይገርመኛል!
https://www.tgoop.com/Gazetaw
«አስደንጋጭ» የቅዳሜ ቡና ቁርስ...!
⎧በታመነ መንግስቴ ውቤ⎫
ምን...!?
✍️የከፍተኛ አካባቢው ክርስትያን መንግስት(Christian Highland Kingdom) ጦረኛ መሪ ዐፄ ዓምደ ጽዮን የአባቱን ሚስት አግብቶ ነበር!
ለምን...!?
✍️የዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም አጭር ታሪክ የተሰኘ መጽሔት በገጽ-6 እንደሚያትተው «በዚያን ዘመን ንጉሡ...ብዙ ውጊያዎችን ከአረማዊያን ጋር በማድረጉ ከእነርሱ የተማራቸው ብዙ ባህሎች ነበሩት።በዚህ ምክንያት የእንጀራ እናቱን እስከማግባት ደረሰ።»
እሺ ከዚያስ ወዲያ...!?
✍️ጠላትህን አብዝተህ ስታሳድድ የእሱ ጠባይ ሳታስበው ተዋርሶህ እንዳያሳድድህ ተጠንቀቅ!
ፃፉልኝ @gazetaw1
ግቡ https://www.tgoop.com/Gazetaw

የሰንበት ወግ
ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ወልደ ሕይወት ያወጋችሗል፦
«አንተ ግን የአስተማሩህን ሁሉን ራስህ ሳትመረምረውና እውነትም ከሐሰት ስአትለይ በቀር ሰዎች የአስተማሩህን ምንም አትመን።
ሰዎች ሊዋሹ ይችልኣሉና፤እውነት ወይም ሐሰት ቢአስተምሩህም አታውቅም።
እንዲሁም ሰአትመረምራቸውና እውነት ሆነው ሰአትኣገኛቸው፣በመጽሐፍት የተፃፈውን አትመን።
መፃሕፍትንም ሊዋሹ የእሚችሉ ሰዎች ናቸው የፃፉአቸው።
አንተ ግን መፃሕፍትን ከመረመርሃቸው እግዚአብሔር እውነት እንድንፈልግበት ከሰጠነ ከልቦናችን ጋር የእምአይስማማ ክፉ ጥበብ ተኣገኝባቸውአለህ።»
ጥበብ-ቅፅ ፪ ፣ጲላጦስ(ኃይለጊዮርጊስ ማሞ)፣ገጽ 234

«ዋናው ሞራል ነው!»
«...ልጆቼ ለማንኛውም ለአገራችን ችግሮች ሁሉ ትልቁ መፍትሔ ከፈጣሪ በታች የገዛ ሞራል ነው።ፈሪኃ ፈጣሪ ኖሮት በሞራል የተገነባ ሕዝብ በራስ መተማመን ይኖረዋል።
ከሌብነት' ና ከሙስና የፀዳ ነው።አገርን ለማሳደግ 'ና ሕዝብን ከድህነት ለማውጣት ወሳኙ ሞራል ነው።
ሞራል ያለው ትውልድ በማንም አይበገርም።
ሞራል ሲላሸቅ ኪሳራው ከባድ ነው።ሞራል ሲገነባ ግን እንኳን ለራሳችን ለሌላውም እንተርፋለን።»
በ ሪፖርተር ጋዜጣ|ረቡዕ ሚያዚያ 11 ቀን 2015 ዓ.ም የ «ታክሲ»አምድ ላይ የተጠቀሱ አንዲት ከጉርድ ሾላ ወደ መገናኛ በታክሲ ይጓዙ ነበር የተባሉ ኢትዮጵያዊት አዛውንት የተናገሩት!

የምርመራ ዘገባው ከምን ደረሰ...!?
ዛሬ የማወጋችሁ በቀኃሥ ዘመን በኢትዮጵያ የሚኖር የግሪክ ማኅበረሰብ እንዲማርበት ተቋቁሞ ከዓመታት በሗላ ራሱን በድብቅ ወደ ንግድ ተቋምነት ቀይሮ ላለፉት 25 ዓመታት አምስት ሳንቲም ግብር ሳይከፍል ከአንድ ልጅ በመቶ ሺሆች ብር እያስከፈለ በመቀጠል ላይ ስላለ «የግሪክ ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት»ስለሚባል ተቋም ነው።
ግሪክ እና ኢትዮጵያ ከእነ ሔሮድተስ እስከ ባለቅኔው ሆሜር ዘመን፣ከታላቁ እስክንድር እስከ ታላቂቱ ሕንደኬ ጊዜ፣ከዘጠኙ ቅዱሳት እስከ 19ነኛው ክፍለ ዘመን የሲራራ ነጋዴዎች ወቅት የተሻገረ ለዓለም የሥልጣኔ ጮራ ሆኖ የማብራት የጋራ ድል ጌቶች ናቸው።
ግሪካዊው ባለቅኔ ሆሜር በዘመኑ በአፍሪቃ ምድር ያበበችውን ውብ አገር ኢትዮጵያ አወድሶ አይጠግብም።
ኮስመስ የተባለው ግሪካዊ ተጓዥ ስለ አክሱም ወርቃማ ዓመታት ለመክተብ ባሕር አቋርጦ በእነ ዞስካለስ መንደር፣በአዶሊስ ቀየ ሰነባብቷል።
የታላቁ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሐፊ ጳውሎስ ኞኞ አባት ያንን ባለ ብሩህ አዕምሮ ልጃቸው ለመውለድ ከኢትዮጵያዊት ሴት ወይዘሮ ትበልጫለሽ አንዳርጌ ቀየ መገኘት ነበረባቸው።
ይህ ሁሉ የሁለቱ ቀደምት ሕዝቦች ውብ የታሪክ ሰበዝ ሲመዘዝ የሚገኘ ሃቅ ነው።
በቅርብ ዓመታት ውስጥ ግን ግሪክም ሆነች ኢትዮጵያ የዓለም ጭራ ሆነዋል።የሶቆራጥስ አገር በአውሮጳ አበዳሪዎቿ የተናቀች ድሃ ምድር ከሆነች ዓመታት «እንደ መስክ ውሃ ፈሰሱ»።
የቅዱስ ያሬድ ምድር ኢትዮጵያ ደግሞ ዛሬ ድረስ ልጆቿን በሰላም ማኖር ተስኗታል።
ከሁሉም የከፋው ግን ለወራት የአፍሪካ ሕዳሴ ቴሌቪዥን አገልግሎት(Arts tv) በግሪካዊያን ባለቤትነት በሚተዳደረው፣ከብዙ ስሞቹ በአንዱ"የግሪክ ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት"ብለን በምንጠራው የትምህርት ተቋም ውስጥ አተኩሮ የያዘው የምርመራ ዘገባ ላይ የሚታየው ነገር ነው።
ከዚህ ጽሁፍ ቀደም ብሎ በጉዳዩ ዙሪያ ከስድስት በላይ ዝግጅቶችን አስተላልፈናል፣ብዙ ጋዜጦች እና ብዙኃን መገናኛዎች የግሪክ ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ለዓመታት ግብር ሳይከፍል በመሐል አዲስ አበባ መነገዱን ዘግበዋል፣ትምህርት ሚኒስቴር ከ2014 የትምህርት ዘመን በሗላ ማስተማር እንደሚከለክለው በአደባባይ ተናግሯል፣ብዙ ብዙ ነገሮች አልፈዋል።
ይህ ጽሁፍ በማኅበራዊ መገናኛዎቸ በሚነበብበት አፍታ፦
1.ከብዙ መጠሪያ ስሞቹ በአንዱ«የግሪክ ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት»የሚባለው ተቋም በትምህርት ሚኒስቴር፣ፍትሕ ሚኒስቴር፣የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን እና በትምህርት ቤቱ ወላጅ ማኅበር በሕገ-ወጥ አሠራሮች ተጠርጥሯል።
2.ይህን ላለፉት ከ20 በላይ ዓመታት አገሪቱን ከ አራት ቢሊዮን ብር የሚበልጥ ግብር እንደሠረቀ የሚገመት ትምህርት ቤት ለትርፍ ወዳልተቋቋመ ድርጅትነት ለመመለስ በቁጥር አንድ የተጠቀሱትን አካላት እና ራሱን ትምህርት ቤቱን የሚወክሉ አባላት ያሉት ኮሚቴ ተቋቁሟል።
3.ይህ በእንዲህ እንዳለ ትምህርት ቤቱ እንደሽፋን ተጠቅሞ ከኢትዮጵያ ድሃ ሕዝብ ላይ ግብር ያጭበረብርበታል የተባለው በእየ ሁለት ዓመቱ የሚታደስ ጊዚያዊ የማኅበረሰብ ትምህርት ቤቶች ፈቃድ ከፈረንጆቹ መጋቢት 30 ቀን 2023 ወዲህ አብቅቷል።አልታደሰም።
4.ተቋሙ በአርትስ ቴሌቪዥን፣በእኔ እና መረጃ በመሥጠት በተባበሩ አገር ወዳድ ቁርጠኛ የተማሪ ወላጆች፣መምህራን ላይ የ«እንከሳችሗለን፣እናባርራችሗለን»ዛቻ በጽሁፍም ሆነ በድምጽ ከወረወረ በሗላ አልሳካለት ብሎ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ ፍርድ ቤት ውስጥ የጊዚያዊ ኮሚቴው ሒደት እንዲቆምለት ትምህርት ሚኒስቴር'ን ና የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣንን ከሶ በአንድ ቀን እግድ ተፈቅዶለት ሒደቱን እያጓተተ ይገኛል።
5.በጉዳዩ ላይ የከፊል ምርመራ ዘገባው ቡድን መሪ በመሆን ላለፉት በርከት ያሉ ወራት ብዙ የተቋማትን ደጅ ረግጫለሁ።አብዛኞቹ በአካሄድ ስልቴ የተነሳ መጠነኛ መረጃዎች ሰጥተውኛል።የጉዳዩ ቀጥተኛ ባለቤት የሆነው ትምህርት ሚኒስቴር ግን እስከዚች አፍታ ድረስ መረጃ ለመስጠት አልቻለም።
ከሰሞኑ ለሁለተኛ ጊዜ ሁለት ደብዳቤዎች ወደ ተቋሙ እንዳስገባ ከጠየቁኝ ባለሥልጣን ላይ ጥሩ ተስፋ ይታየኛል።ፈጣን ምላሽ እጠብቃለሁ።
አድናቆት...!
ሃላፊነቱ የሆነን ሰው አላመሰግንም።መደናነቅ ግን የአንድ ዘመን ሰዎች ልማድ መሆን አለበት።
ስለሆነም፦
ሀ.የግሪክ ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት'ን እንከኖች ተመልክተው በከፍተኛ ቁርጠኝነት መረጃ በመሥጠት እየተባበሩኝ ያሉትን አካላት(ወላጆች፣መምህራን፣የሕግባለሞያዎች፣የቀድሞ ሠራተኞች)
ሁ.አገሩ ሁሉ «ግደለው፣ስቀለው»ወይም «አሸሸ ገዳሜ»በሆነበት ጊዜ እንዲህ ያለ ትውልድ የሚያድን ሥራ እንዲሠራበት ጣቢያውን ለፈቀዱት የአርትስ ቴሌቪዥን ከፍተኛ አመራሮች፣
ሂ.በተቃራኒ አንፃር ሆነው የትምህርት ቤቱን መልካምነት ና ሕጋዊ አካሄድ ለማስረዳት በራቸውን እና አንደበታቸውን የከፈቱ አካላት አድናቆት ይገባቸዋል።
ከሞላ ጎደል ጫፍ ላይ የደረሰውን የግሪክ ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ጉዳይ እየተከታተልኩ ሃቅ ለሚገዳቸው ሁሉ አደርሳለሁ።
ታመነ መንግስቴ ውቤ—ጋዜጠኛ
የአፍሪካ ሕዳሴ ቴሌቪዥን አገልግሎት(Arts tv) በግሪክ ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ላይ እየከወነው ባለው የምርመራ ዘገባ ሒደት ለሕዝብ ዕይታ የቀረቡ ዝግጅቶች በቅደም ተከተል፦
1.https://youtu.be/NMTu7865Cdk
2.https://youtu.be/v-kSmKPEOFE
3.https://youtu.be/4bAUAZ8fm3w
4.https://youtu.be/3R5UcMFYcGk
5.https://youtu.be/3R5UcMFYcGk
6.https://youtu.be/jgnUn_3wZMc
ናቸው!

YouTube
''ከ25 ዓመታት በላይ ግብር ያልከፈለ ተቋም!''|የግሪክ ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት|Ethiopia@ArtsTvWorld
Subscribe: https://www.youtube.com/channel/UCSnwxtpNr-2QupM0qi11Y6Q?sub_confirmation=1
Facebook : https://www.facebook.com/ArtsTvWorld
Website : http://artstv.tv
Instagram : https://www.instagram.com/ArtsTvWorld
Twitter : https://twitter.com/ArtsTvWorld…

፩
#የንጉሥ_ተክለ_ሃይማኖት አያት የሆኑት የጎጃም ነጋሽ የደጃዝማች ጎሹ ዘውዴ ወታደር የነበረው ፈረንሳዊው አርኖ ሚሼል ዳባዲ፤ የደጃዝማች ጎሹን ጀግንነትና አስተዋይነት፤ ሃይማኖት ጠበቃነታቸውን...፤ አማረኛ ቋንቋን ተምሮ በራሳቸው ቋንቋ እንስከሚያጠናቸውና እስከሚያወራቸው ድረስ ፍቅር፤ ወዳጅነትና ወንድምነት አሳይተውታል፡፡ #ከሰለጠነችዋ_ፈረንሳይ መጥቶ ከጎጃም ብዙ የተማረ መሆኑን ይነግረናል፡፡
፪
“የደጃች ጎሹ ቤት ቆይታዩ ለኔ ጠቅሞኛል፡፡ ብዙ የማላውቀው ነገር አውቂያለሁ፡፡ ብዙ ነገር ግልፅ ሆኖልኛል፡፡ በግቢያቸው የነገሠው ይህ ጥልቅ ክርስቲያናዊ ስሜት፣ ከየትኛው ጥንታዊ ሐረግ እንደሚመዘዙ በቅጡ ያልተረዳሁት #ሞት_አይፈሬነታቸውና ያ ግድየለሽነት የተላበሰ #ጀግንነታቸው ይገርመኝ ነበር፡፡ በሠፈር በአደባባያቸው የተነዛው የወንድነት ወኔና ጀግንነታቸው የበለጠ እንዳውቃቸው ጥረት እንዳደርግ ግድ አለኝ፡፡ በነዚህ ሁሉ ምክንያቶች የአገራቸውን ባህልና ወጋቸውን የበለጠ የማወቅ ጉጉቴ ጠነከረና የበለጠ እንድረዳቸው #የአማረኛ_ቋንቋ_መማር_ጀመርሁ፡፡
፫
#ከዚህ_ጀግና_የጎጃሜ_ጦር_ጎን_ተሰልፌ_የተካፈልሁበት ዘመቻ የእውቀት አድማሴን በማስፋት አዲስ የምርምርና የጥናት አቅጣጫ እንድይዝ አድርጎኛል፡፡..." ሲል ይጽፋል።
፬
ዳባዲ ከብዙ ጊዜ ቆይታ በኋላ የአማረኛ ቋንቋን ትምህርቱን አጠናቆ፤ በአማረኛ መግባባት ጀምሯል፡፡
...ለእኒህ መስፍን ያለኝ ፍቅር ከቀን ወደቀን እየጨመረ ነው የመጣው፡፡ #አሁንማ_አማረኛ_በደንብ_ስለምናገር የምጠራቸውም እንደ አገሩ ልማድ #ጌቶች› እያልሁ ነው፡፡...እኒህ ሉል አስተሳሰባቸው የደረጀና የውጭውንም ዓለም የማወቅና የመረዳት ፍላጎታቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ስለሆነም እድሌን ከእድላቸው አስተሳስሬ አብሬአቸው ለመሆን ወሰንኩ፡፡...”
ሲል ዳባዲ ዕድሉን ከደጃዝማች ጎሹ ጋር ኑሮውን ከጎጃም አስተሳስሮ መኖሩን ቀጠለ።
የማወጋችሁም እንዲሁ ይቀጥልና
፭
አበረ አ. አዳሙ

⎡በደስአለኝ ከፍአለ— ከመካነ ሰላም⎤
«ሲያነብ የሚተኛ ትውልድ እንዳናፈራ!»
የመማሪያ ክፍል ውስጥ ነኝ። ዘግይተን የጀመርነውን ኮርስ ለማካካስ ጧት፣ ከሰዓት እና ቅዳሜን ጨምሮ በመማር ላይ ነን።
መካነ አዕምሮአችን የገጠመው የመምህራን እጥረት ለኮርሱ መዘግየት ምክንያት ነበር።
ዶ/ር ሰውአገኝ ይባላሉ። የመቅደላ አምባ መካነ አዕምሮ የአማርኛ ቋንቋ እና ሥነ ፅሑፍ መምህር ናቸው።የዘገየውን ኮርስ የሚያስተምሩን መምህራችንም ናቸው።
ይሀንን ኮርስ በማስተማር ላይ እያሉ ነበር ከላይ ለወጓ አርዕስት ያደረኳትን ምክር አዘል ንግግር ጣል ያደረጓት።
ከኮርሱ አንደኛው ርዕስ መንደርደሪያ ሆናቸውና እንዲህ አሉ «አሁን አሁን የተረት መፅሐፍትን በማንበብ ህፃናት ልጆችን ማስተኛት ልምድ ከሆነ ቆይቷል» ሲሉ ሌላ ነገር ሊያወሩ እንደሆነ ገባኝና በደንብ ልከታተላቸው ተዘጋጀሁ።
ማብራሪያቸውን ቀጠሉ«ህፃናት ልጆችን ለማስተኛት የተረት መፀሐፍ ይዘን ከአልጋ ላይ ተቀምጠን ማንበብ የብዙዎቻችን ልምድ እየሆነ መጥቷል»።
«ታዲያ ይህ ተግባር ሌላ ትልቅ ችግር እንደሚያስከትል የተገነዘብነው አይመስለኝም »።
«ልጆችን መፅሐፍ እያነበብን እንዲተኙ የምናደርጋቸው ከሆነ ነገ ከነገ ወዲያ ወደ ት/ት ተቋም ተቀላቅለው በትምህርታቸው ለመብረታት ሲያነቡ እንዲተኙ ይገደዳሉ ማለት አይደል? »ሲሉ ይጠይቃሉ።
«በርግጥ ተረት ህፃን ልጆችን ለማስተማር፣ በጥሩ ሥነ ምግባር ለማሳደግ፣ የወጡበትን ማህበረሰብ ወግ፣ባህል፣ ልማድ እና ሌሎችንም ማህበራዊ መስተጋብሮች እንዲያውቁ ለማድረግ የማይተካ ሚና አለው »ይላሉ።
ዳሩ ግን መቼ፣ እንዴትና በምን አይነት ሁኔታ እንጠቀማው የሚለውን እንዲህ ይናገራሉ:-
« ተረትን መፅሐፉን ይዘን እያነበብን እንዲተኙ ከምናደርጋቸው ይልቅ፣ እኛ በሚገባ ካነበብነው በኋላ በቃል እየተረክን፣የአካል እንቅስቃሴ(ከዋኔ) በማድረግ ትኩረታቸውን ወደ እኛ በመሣብ በደንብ አዳምጠውን እንዲማሩበት ማድረግ አለብን »ይላሉ።
«ካልሆነ ግን መዋል ላለበት ዓላማ ቀርቶ፣ መዋል ለሌበት ዓላማ በማዋል ትልቅ ነገር በሚሰሩና ትልቅ ነገር በሚጠብቃቸው የዛሬዎቹ ህፃናት ፣የነገዎቹ ወጣቶች እና ጎልማሶች ላይ ችግር መፍጠር ይሆንብናል»የሚል ፅኑ አቋም አላቸው።
«ከሥነ ቃል አይነቶች አንዱ የሆነውን ተረት ለአንድ አገር ወይም ማህበረሰብ ትውልድን በመቅረጽ ረገድ የሚያበረክተውን የማይተካ አስተዋጽኦ ማደብዘዝ እና ማጥፋት እንዳይሆን »ሲሉ ስጋታቸውን ይገልፃሉ።
«ይህም ሲያነብ የሚተኛ ትውልድ አፍርተን ለአገር ዕድገት የጀርባ አጥንት የሆነውን የትምህርት ስርዓት ልጆች በንቃት እንዳይሳተፋበትና ውጤታማ እንዳይሆኑበት ያደርጋቸዋል » በማለት ትዝብታቸውን ተናገሩ።
ነገሩን ያጤንኩት በእኛ መካነ አዕምሮ ውስጥ እንደቀልድ የምናደርገው መሆኑ ትዝ ሲለኝ ነበር።
አንድ የዶርም ተማሪ «እንቅልፍ እምቢ አለኝ? » ካለ ጋደም በልና መፅሐፍ ገለጥበት ወዲያው ይወስድሃል። እንበባላለን።
መምህሬ እውነታቸውን ነው። ይኸው እንዳሉት ማንበብን ለዕውቀት ሳይሆን ለእንቅልፍ እየተጠቀምንበት ነው። ታዲያ ከዚህ በላይ ስጋት ቢያደርባቸው በእሳቸው አልፈርድም።ትውልድ እየተዘናጋ ነውና።
ምክንያቱም ለአገራችን ኢትዮጵያ ቀርቶ ለአፍሪካ እና ለመላው ዓለም አንባቢ ትውልድ ያስፈልገዋል።
በተለይ ለአሁኗ ኢትዮጵያ ያነበበ፣ ወደፊትም የሚያነብ፣ታሪክን ያወቀ፣ወደፊትም የሚያውቅ እና የሚረዳ ችግር ፍቺ ትውልድ ያስፈልጋታል።
በመጨረሻም « እናተም በኋላ ልጆቻችሁን የተረት መፅሐፍት በማንበብ እንዲተኙ እንዳታደርጉ፣ ሲያነብ የሚተኛ ትውልድ እንዳናፈራ!» በማለት አደራ ጥለውብን ተለያየን።
እናተስ ምን ትላላችሁ?
ትዝብታችሁን አጋሩን🙏
መልካም ዕለተ ሰንበት ተመኘሁ🙏

ዛሬ ሰኞ ምሽት 2:30 በጋራ ጉዳያችን ላይ ከ ካሳሁን ፎሎ—የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን(ኢሠማኮ) ፕሬዚደንት ጋር እናመሻለን።
በጊዜ ግቡ❤
https://youtu.be/rDspYgDTAiI
በጊዜ ግቡ❤
https://youtu.be/rDspYgDTAiI