Telegram Web
#የኢትዮጵያ_በረከቶች
በሒሶፕ ኢንተርቴይመንት ተከሽኖ የኛን መምጣት እና ማክሰኞ መጋቢት 12ን የሚጠብቀው ድንቅ የስነጽሁፍ ዝግጅት... የተለያዩ ገጣምያን፣ ድምፃውያንን እና በድንቅ ወጉ የምናውቀውን አዱኛው አዲስን ጨምሮ የኢትዮጵያ የባህል ቡድን ጊዜያችንን ለማሳመር ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል። በመድረክ አጋፋሪው አዲሱ ገረመው ውብ ለዛ የሚመራውን ድንቅ ፕሮግራም ልጋብዛችሁ...ሄደን ዘና ፈታ ብለን ተረፍረፍ አድርገን እንመለስ!!
0939015249 ላይ እየደወልን አለን ቦታ ያዙልን እንበላቸው😁😁

@infokenamu
እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን አደረሳችሁ
በሁለተኛው ሚሊኒየም መባቻ ላይ በሰባት የአርባ ምንጭ ተማሪዎች ምስረታውን ያደረገው የሁላችን ቤት የባች ልዩነትን በቁጥር እንጂ ለክለቡ ባለን ፍቅር ያላሳየን ዛሬ አስራ አምስት ዓመት በኋላም እንደያኔው በፍቅር ግን በብዛት በዝተን የምስረታ በዓሉን ልናከብር ዕለተ እሁድን ግንቦት 27 2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የሚገኘው ቤታችን እንገናኝ ተብላችኃል ያው እዛ ካሉት ቤተሰቦቻችን ውጭ ኢንፎክንን በቅርቡ የማየት ዕድል በማግኘት ይህንን መልዕክት እንዳስተላልፍ ተነግሮኝ ነው ስለዚህ ከሩቅም ከቅርብም ያላችሁ የኢንፎክን ቤተሰቦች በዕለቱ እንድንገናኝ ይሁን።
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኢንፎክን (INFOKEN) የመጻሕፍትና መረጃ ማዕከል ከበጎ አድራጎት ማዕከል (Charity Center) ጋር በመተባበር የማጣቀሻ መጻሕፍትና አልባሳት ድጋፍ አበረከተ!

ለተጨማሪ ንባብ:- https://www.amu.edu.et/2741-infoken-charity-
ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ ኢንፎክናዊያን። የኢንፎክን ጀግና የሆነው ወንድማችን ካሌብ የፊታችን ማክሰኞ ድንቅ የጥበብ ድግስ አዘጋጅቷል።ሁላችንም በቦታው በመገኘት የድግሱ ተካፋይ እንድንሆን በአክብሮት ተጋብዘናል።
ሒሶፕ ኢንተርቴይመንት የባለ ዜመኛዋን ድንቅ ገጣሚ መንበረ ማርያም ሀይሉ ሁለተኛ መፅሐፍ የጊዜ ሠሌዳ በአስደማሚ ዝግጅት ለማስመረቅ ከአንጋፋ ዕውቅ የኪነ-ጥበብ ሰዎች ጋር ወጣት ፀሀፊያን የውዝዋዜ ቡድን፣ የሙዚቃ ኳየር ከአዲስ የሙዚቃ ስራ ጋር፣ ሰዓሊ ፣ መሳሪያ ተጫዋቾችን ልዩ ልዩ ባለተሰጥኦ ወጣቶችን በማካተት በልዩ የኪነ-ጥበብ ስራ ሐምሌ አንድ ምሽት 11:00 ሰዓት በብሔራዊ ቴአትር ለማስመረቅ ዝግጅት አድርጓል። በዚህ ዝግጅት ትታደሙ ዘንድ ከወዲሁ ይጋብዛል።

መግቢያ በሰዓቱ መገኘት

#ሒሶፕ_ኢንተርቴይመንት በስራው የሚመርጡት!‌‌


Hyssop Entertainment, to launch the poet Menbere Maryam Hailu's second book in an exciting book graduation event, together with veteran artists, including a young writer, a dance group, music choir, painter, instrument players and various talented young people in a special art work on July 01/2016 E.C at 5:00 pm(11:00 LT) it made preparations to graduate at the National Theatre. You are already invited to attend this event.

Entrance fee is - Arrival on time

#Hyssop_Entertainment who chooses the job!‌‌

Contact us phone 0961510000
.
Forwarded from KalebWondimu
መፅሐፍ ልንመርቅ ነው ኢቨንቱን እየሰራሁ ነው ጓደኛም መጋበዝ ይቻላል
Forwarded from KalebWondimu
ወጪ በኔ ነው ተጋብዛቹሀል ሰኞ 11 ሰዓት ብሔራዊ አዘጋጅቼ ጠብቃቹሀለው
ዩንቨርስቲ እያለን የምንወደው አርባምንጭ ማለታችን ነው፣ INFOKEN - ኢንፎክን የሚባል የመጻሕፍት ማዕከል ነበረን። ነበረን ያልኳችሁ፣ ስለ ቀደመ ጊዜ ለማውራት ያህል ነው እንጂ ማዕከሉ አሁንም በንባብ የነቃ ትውልድ ለማፍራት በትጋት ላይ የሚገኝ ነው። ማዕከሉ ከሚሰራቸው ስራዎች መሃል ዋነኛው ሁለገብ መጻሐፍትን ለዩንቨርስቲው ማህበረሰብ በቅናሽ ዋጋ ማከራየት ነው። ከኪራይ በሚገኘው ገንዘብም ሌሎች መጻሕፍትን በመግዛት ራሱን ያደራጃል። የማዕከሉ አባላትም ዋነኛ ሚናቸው እነዚህን መጻሕፍት ማከራየትና በሰዓቱ ተመላሽ እንዲሆኑ ማድረግ ነው።

ታዲያ በስራችን ወቅት ዋነኛው ፈተና፣ ተማሪዎች ለንባብ የተዋሱትን መጽሐፍ ሳይመልሱ ይጠፋሉ። በተለይ ይሄ ነገር ተመራቂ ተማሪዎች ላይ ይበረታል። በዓመቱ ከተከራዩት መጻሕፍት መካከል ቢያንስ 30% የሚሆኑት አይመለሱም። ይሄ ድርጊት የማዕከሉን የመጻሕፍት ክምችት ቢያመነምነውም እኛ ኢንፎክናውያን ግን ብዙም አንደነግጥም። ምክንያቱም በአንድም በሌላም መንገድ ማዕከሉ የተቋቋመበትን ዓላማ እንደማይስት ስለምናምን ነው። ማለትም መጻሕፍት የትም ሄዱ የትም ለንባብ ጥቅም ብቻ እንደሚውሉ እናምናለን። አንድ ተመራቂ ተማሪ የተዋሰውን መጽሐፍ ሳይመልስ ይዞት ከጊቢ ቢወጣም፣ መጽሐፉ ግን በሄደበት ሁሉ ስራውን መስራቱን አያቆምም። ስለዚህ ኢንፎክን አይከስርም ማለት ነው።

ይሄንን ለመጻፍ ያነሳሳኝ ባለፈው ሳምንት ያጋጠመኝን ገጠመኝ ልነግራችሁ በመሻቴ ነው። አንዲት ሴት ስልክ ደወላ ስሜን ካረጋገጠች በኋላ፣ በቴሌግራም የመጻሕፍት ውይይት ላይ ለተጠየቀ ጥያቄ ምላሽ መመለሴን እንዳረጋግጥላት ጠየቀችኝ። "አይ በፍጹም እኔ ቴሌግራም ውይይት ተካፍዬ አላውቅም" አልኩ። የውይይቱን አይነትና ርዕስ ነግራኝ በድጋሜ እንዳስታውስ አሳሰበችኝ። 100% አስረግጬ አለመሳተፌን ተናገርኩ። የስም ስህተት ሊሆን ስለሚችል ድጋሜ አመሳክራ እንደምትደውል ነግራኝ ስልኩ ተዘጋ።

በሁለተኛው ቀን ያችው ሴት ደወለች። "መጽሐፉ ከጀርመን  ሃገር በቅርቡ እንደገባና አድርሺ ለተባልኩት ሰዎች ሁሉ እያቀበልኩኝ ነው፣ እናም ለአንተ የት ላቀብልህ" የሚል ጥያቄ ጠየቀችኝ።  አሁንስ ይቺ ሴትዮ ለምን በመጽሐፍ ትፈታተነኛለች ብዬ "በቃ እኔ  በመጽሐፍ አልጨክንም፣ ሜክሲኮ ከሆንሽ ሀሁ መጻሕፍት ጋር አስቀምጪልኝ አልኳት።

ከአፍታ በኋላ ደውላ "ስምህን ጽፌ አስቀምጬልሃለሁ!" አለቺኝ። እኔም "እሺ አመሰግናለሁ!" ብዬ ስልኩን ዘጋሁ። በመሃል ረስቼው ነበርና ዛሬ ትዝ ሲለኝ ሜክሲኮ አካባቢ ስለነበርኩ "ሀሁ" ጋር ጎራ አልኩኝ። ጉዳዩን ስነግረው ከትንሽ ፍለጋ በኋላ "ቀዩ ባሐር፣ ኀዘንተኛው ባሕር" የሚል መጽሐፍ አቀበለኝ። እውነትም ስሜ ተጽፎበታል።

እናም ለማለት የፈለኩት የስም ስህተትም ከሆነ "ለኔ ነው የተላከው" የሚል ወገን ካለ አንብቤ የማቀብለው እንደሆነ ለማሳወቅ ነው። የኔ እንዳልሆነ እያወቅሁም የተቀበልኩት ከላይ በጠቀስኩላችሁ የኢንፎክን መርህ መሰረት ነው። መጽሐፍት የትም ይሁኑ የትም እስከተነበቡ ድረስ አይጠፉም፣ አይከስሩም። አይሰረቁም! በቀጣይ ደግሞ ከመጽሐፉ ላይ ሃሳብ አጋራችኋለሁ። ወደ ንባብ!

©ገረመው ፀጋው @gere_perspective
እንደዋዛ የነበረን ሁሉም ነገር መትነን ጀምሯል። የማንመለሰውን መንገድ ብዙ ርቀት ተጉዘናል። "ለይስሙላ ነው" እያልን የምንኮንነው ማህበራዊ ወገንተኝነትና እዝነታችን ሳይቀር አሁን ቢጠሩት አይሰማም። ለካ ባለ ነገር ላይ ነው ኩነኔ፣ ትችትና ወቀሳ። የሰብአዊነት ወዛችንን ደጋግመን አጠብነው። ማጠባችን ሳያንስ ርዝራዥ እንዳይቀር ጨምቀንና ጠምዝዘን አሰጣነው። "ሃገሬን በሃዘን" የተሰኘው የሱራፌል ወንድሙ ግጥም ላይ በባዕድ ሃገር የሚኖር ሰው ሃዘን በገጠመው ጊዜ "ኡኡ" ብሎ ማልቀስ አለመቻሉ ምን ያህል ሰቀቀን እንደሆነበት የሚያሳዩ ስንኞች አሉ። አሁን ያገር ሰው በሃገሩ የለም፣ ከእዝነት ልቡ ሸሽቷል።

ሰሞነኛውን የጎፋ ህዝብ ህመም በተመለከተ በየቢሮው በየቡናው ላይ የሚሰሙ ድምጾችን ላስተዋለ፣ የወትሮው ያገር ሰው በቦታው እንደሌለ ያመላክታል።

"ኧረ በስማም አንተ የሞቱት እኮ ቁጥራቸው 150 አለፉ ተባለ"

"እንዴ የመቼህን? ገና ማታ ላይ 170 እንደደረሱ አንብቤያለሁ"

"ገበያ ነበር እንዴ፣ ይሄ ሁላ ሰው እንዴት አንድ ቦታ ላይ ተገኘ"

"በየሱስ ስም፣ 260 አለፉ የሚል ነገር ተጽፎ አየሁ"

መሰል፣ መሰል ዘገባዎች ከዚያና ከዚህ ይወራወራሉ። በአንዱም ውስጥ ሃዘኔታ የለም። በአንዱም ውስጥ "እኔን 💔" የሚል ድምጽ የለም። አስመሳይ ሃዘኔታችን ለዛ ነበረው። ለወትሮው ስንሰበር ደረት የሚደልቅልን አይቸግርም ነበር። ዛሬ እሱ ብርቅና ሩቅ ነው። እንደማህበረሰብ ሰው ሟች መሆኑን አለቅጥ አምነናል። አለቅጥ ተፅናንተናል። Trauma ሸሽቶናል። ሃዘን የሚጎዳቸውንና የሚበረታባቸውን ሰዎች ሳይ ብርቅ እየሆኑብን ነው። ሁሉም Move on ላይ ጡንቻ አውጥቷል። ይሄ ይሄ ያስፈራል ሲበዛ።

አንዱ ጓደኛዬ ምን አለኝ፣ "ከንፈር የሚመጡ እናቶች የት ገቡ"

አዎ እንዴት ነው ግን ፣ ከንፈር መምጠጥ እንኳን ብርቅ የሆነብን። አዎ ከተለማመዱት ሁሉም ነገር ይለመዳል። በሞት አለመደንገጥን ያለልክ ተለማመድን። የሞት ዜና ሰዓት የማብሰሪያ ድምጽ ያህል ትኩረት እስኪያጣ ተጋትነው።

በርግጥ ይሄ ይሄ እንደሚመጣብን ደራሲው አዳም ረታም "ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ" መጽሐፉ ላይ የሚከተለውን ከትቦልን ነበር።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
" . . . እውነቴን ነው፤ እናቶች ተትረፍርፈዋል፡፡

ነጠላ ደርበው 'ልጄ' የሚሉ፣

መንገድ ላይ የውሸት የሚቆጡ
(መቆጣት የሚችሉ ይመስላቸዋል ግን)

ለጠማው መንገደኛ ፈልሰስ እያሉ (ስለ ወፈሩ ወይም ስለ ደከሙ) ጠላ በጣሳ የሚያቀርቡ
(ይህችን ይህችን እወዳለሁ)

ጠዋት ጎሕ ሳይቀድ ለቤተክርስቲያን የሚታጠቁ፣ ፀሎታቸው ሩቅ የሚሰማ……

ዓይኖቻቸውን ከድነው በፍቅር የሚስሙ
(ጨርቅ የለበሰ ጠበል ያቀፈ ገንቦ)……

'እሰይ የእኔ ልጅ' ሲሉ ትንፋሽ የሚያጥራቸው……

ትልልቅ ጡቶች ያላቸው
(ከአምስት በላይ ያጠቡ)

ቡና እያፈሉ ነጠላ የሚቋጩ
(ሰነፍ ይጠላሉና)

ከሽሮ ወጥ ፋሲካ የሚሠሩ
(ከፍትፍቷ ፊቷ)

በቆሎና በንፍሮ ሽር ጉድ የሚሉ፤ ጋብዘው የማይጠግቡ

የውሸት የሚቆነጥጡ

ሲደነግጡ ነጠላ ጥለው ደረት የሚመቱ

ያለ መሐረብ የሚናፈጡ (በማሽቀናጠር ስላደጉ---- ከወንዝ ወንዝ የሚወረወሩ)

በነጠላቸው ጥለት ዓይኖቻቸውን የሚያብሱ

እነኚህን ዓይነት እናቶች ይጠፉ ይሆናል
('ኋላ ቀር' ብለናቸው)

ብዙ መልካሞችና መልካምነቶች እንደጠፉ ሁሉ……
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
በቅጽበት ላጣናቸው የአንድ ቀበሌ ህዝቦች ለነፍሳቸው ምህረት ይስጥልን። የሚወዷቸውን ላጡ ሁሉ መጽናናትን በቅጡ ይስጥልን። ያጡት ይበቃልና ዳግመኛ ማጣት እንዳይጎበኛቸው በምንችለው እናቋቁማቸው።

©ገረመው ፀጋው @gere_perspective
2024/11/15 05:56:32
Back to Top
HTML Embed Code: