Warning: mkdir(): Permission denied in /var/www/tgoop/function.php on line 85

Warning: file_put_contents(aCache/detail/i/w/n/e/iwnetlehullu1.txt): Failed to open stream: Permission denied in /var/www/tgoop/function.php on line 87

Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
አሥሠላሙ ዓለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ያ ጀማዓህ!
ይህ የወንድማችን አቡኪ ቻናል ነው ተቀላቀሉ👇
https://www.tgoop.com/buki145
☝️ ጎበዝ ልጅ ነው። ትጠቀማላችሁ እንጂ አትጎዱም💫
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💫🌴የኡስታዝ አቡ ሀይደር ሐፊዙላህ መልእክት² ይደመጥ💫🌴
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💫🌴የኡስታዝ አቡ ሀይደር ሐፊዙላህ መልእክት³ ይደመጥ💫🌴

-➠ሶላት ላይ ቀስር እና ጀምዕ ምንድናቸው 2 ደቂቃ

https://www.tgoop.com/abuhyder
☝️የኡስታዝ ቻናል
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
▣የነቢዩ ﷺ ስብዕና▣
ብዙ ግዜ ካፊሮች አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ዶዒፍ ሀዲሶችን ከጉግል እየለቃቀሙ እና አንዳንድ ሶሒሕ ሀዲሶችን በትክክል ባለመረዳት የነቢዩ ስምን ሲያጎድፉ ይታያሉ።

"የውሻ ጩኸት ደመናን አይጎዳም!" ነውና

በነብያችን ﷺ ላይ የሚሳለቅ ራሱን እንጂ እሳቸውን ምንም ሊያደርጋቸው አይችልም።
የላካቸው አምላክ "መወሳትህን/ዝናህን ከፍ አደረግንልህ" ብሏቸዋል። ይሄው የዝናቸው ከፍ ማለትም ነው ዛሬ በርካታ ውሾችን እያስጮኻቸው ያለው።

በአላህ ፈቃድ ስለ ውዱ ነቢያችን ስብዕና የተወሰኑ ሀዲሶችን እናያለን

ውዱ ነቢያችን ከሁሉም የትልቅ ስነምግባር እና ጠባይ ባለቤት ነበሩ

-አላህ እንዲህ ይላል👇
وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٍ
(ሱረቱ አል-ቀለም - 4)
አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ፡

وعن أنس رضي الله عنه قال‏: ‏ كان رسول الله صلى الله عليه وسلم أحسن الناس خلقاً ‏(‌‏(‏متفق عليه‏)‌‏)‌‏.‏
አነስ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንዲህ ብሏል
“ነብዩ ﷺ ከሁሉም የላቀ ስነ-ምግባር የነበራቸው ነበሩ።”
📘Bukhari 3549 muslim 2310a

ውዷ ሚስታቸው ዓኢሻህም ስለ ነብዩ ﷺ ሥነ-ምግባር ስትነግረን፡-
كان خلقه القرآن (رواه مسلم)
“የነብዩ ﷺ ስነ-ምግባራቸው ቁርኣን ነበር” ትለናለች
📘Sahih Muslim 746a

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ إِنَّمَا بُعِثْتُ لِأُتَمِّمَ صَالِحَ الأَخْلاق
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“እኔ የተላኩት መልካም ሥነ-ምግባርን ላሟላ ነው”*።
📘 Adab al-mufrad 273

قال أَنَس رضي الله عنهَ :
« لَقَدْ خَدَمْتُ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ عَشْرَ سِنِينَ ، فَوَاللَّهِ مَا قَالَ لِي : أُفٍّ قَطُّ ، وَلَمْ يَقُلْ لِشَيْءٍ فَعَلْتُهُ : لِمَ فَعَلْتَ كَذَا ، وَلا لِشَيْءٍ لَمْ أَفْعَلْهُ أَلا فَعَلْتَ كَذَا »
አነስ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንዲህ ብሏል
"የአሏህ መልእክተኛን ﷺ አስር አመት አገልግያለሁ። ወላሂ! ፈፅሞ 'ኤጭ!' ብለውኝ አያውቁም። አንድንም ጉዳይ 'ለምን ይህን ሰራህ?'፣ 'እንዲህ ብትሰራ ኖሮ' ብለውኝ አያውቁም»
📘sahih muslim 2309

ውዱ ነቢያችን በጣም ለጋስ ነበሩ።

جَابِرَ بْنَ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ مَا سُئِلَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم شَيْئًا قَطُّ فَقَالَ لاَ ‏.‏
ጃቢር(ረዲየሏሁ ዓንሁ) እንዲህ ብሏል
" የአላህ መልእክተኛ ﷺ አንድን ነገር እንዲሰጧቸው ተጠይቀው እምቢ አልሰጥም ብለው አያቁም።
📘Sahih Muslim 2311a

➠ ውዱ ነቢያችን ጠላቶቻቸው በነበሩ የመካ አጋሪዎች ሳይቀር ታማኙ ሙሐመድ ተብለው ይጠሩ ነበር።
በመካከላቸው ልዩነት በተፈጠረ ግዜ ታማኙ ሙሐመድ ያፋርደናል ብለው እንዳፋረዷቸው
📘musnad ahmad 15504 ተጠቅሷል

إِنَّا كَفَيْنَاكَ الْمُسْتَهْزِئِينَ
[ ሱረቱ አል-ሒጅር - 95 ]
ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል፡፡

🌴አላሁመ ሶሊ ዐላ ነቢይና ሙሐመድ 🌴
https://www.tgoop.com/iwnetlehullu1
ሙስሊም=ስንት አምላክ ነው ምታመልኩት?
ክርስቲያን= ስንት ሚስት ነው ምታገቡት😁
▣ቁርአን የአላህ ቃል ነው▣

   بسم الله الرحمن الرحيم
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው


➠ባሳለፍነው ርዕሳችን ላይ የቁርአን ምንነት አይተን ነበረ።
ዛሬ ደግሞ ቁርአን የአላህ ቃል እንደሆነ ከቁርአን ከሐዲስና ከሰለፎች ኢጅማዕ(ስምምነት) እናያለን ኢንሻአላህ።

ቁርአናዊ ማስረጃ👇

وَإِنْ أَحَدٌ مِّنَ الْمُشْرِكِينَ اسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ أَبْلِغْهُ مَأْمَنَهُ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْلَمُونَ
(📗ሱረቱ አል-ተውባህ - 6)
ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ አስጠጋው፡፡ ከዚያም ወደ መጠበቂያው ስፍራ አድርሰው፡፡ ይህ እነሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው፡፡

ሐዲሳዊ ማስረጃ
رَجُلٌ يَحْمِلُنِى إِلَى قَوْمِهِ فَإِنَّ قُرَيْشًا قَدْ مَنَعُونِى أَنْ أُبَلِّغَ كَلاَمَ رَبِّى
“አዋጅ! የጌታዬን ንግግር ወደ ህዝቦቹ እንዳደርስ የሚወስደኝ ሰው ይኖራልን? ቁረይሾች የጌታዬን ንግግር እንዳላደርስ በርግጥም ከልክለውኛል።
[📘አቡ ዳውድ፡ 4734]
[📘ቲርሚዚ፡ 2925]
[📘ኢብኑ ማጀህ፡ 201

ቀደምት ሰለፎቻችንም ቁርአን የአላህ ቃል እና ባህሪይ በመሆኑ ላይ በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል።

قال أحمدُ بنُ محمَّدِ بنِ حَنبَلٍ رحمه اللهُ: لقيتُ الرِّجالَ، والعُلَماءَ، والفُقَهاءَ، بمكَّةَ والمدينةِ والكوفةِ والبَصرةِ والشَّامِ والثُّغورِ وخُراسان، فرأيتُهم على السُّنَّةِ والجماعةِ، وسألتُ عنها الفُقَهاءَ؟ فكُلٌّ يقولُ: القُرآنُ كلامُ اللهِ، غيرُ مخلوقٍ، منه بدأ، وإليه يعودُ
ኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሐንበል{164-241ሂ) እንዲህ ብሏል" በመካ፣በመዲናህ፣በኩፋህ፣በበስራህ፣በሻም፣በሰغوር እና በኸራሳን ብዙ ኡለሞች(ሊቃውንት) በአህለ-ሱናህ ላይ ሆነው አይቻቸዋለሁ።ሁሉም ቁርአን የአላህ ቃል ነው፣ፍጡር አይደለም ከአላህ ዘንድ መውረድ ጀመረ ወደሱም ይመለሳል ብለው ያምኑ ነበር።
📘ኢኽቲሷስ አል-ቁርአን ገፅ 21

عن عمر ابن دينار قال أدركت مشايخنا منذ سبعين سنة) يقولون: (القرآن كلام الله منه بدأ وإليه يعود).
➠ በተመሳሳይ ዐምር ኢብኑ ዲናር {46-126ሂ}
ለ70 አመታት ያህል ኡለሞችን አግኝቻለሁ።ሁሉም ቁርአን የአላህ ቃል ከአላህ ዘንድ መውረድ ጀመረ ወደሱም ይመለሳል ብለው ያምኑ ነበር።
ብሏል
📘ኢኽቲሷስ አል-ቁርአን ገፅ 27

📘 አል-ዑሉዉ ሊል ዓሊይ አል-غፋር ገፅ  156

➠ ኢማም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል
" ቁርአን የአላህ ባህሪይ በመሆኑ ላይ የሱናህ ባለቤቶች ተስማምተዋል።"
📘መጅሙዕ አል-ፈታዋ ቅጽ 17 ገፅ 78

ኢማም አቡ ሐቲም አል-ራዚ{195-277ሂ} እና አቡ ዙርዓህ አል-ራዚ{207-264ሂ) በሁሉም የዐለማችን ክፍሎች የነበሩ ኡለሞች የነበሩበትን እምነት ሲጠቅሱ " ሁሉም ቁርአን የአላህ ቃል ነው፤ ፍጡር አይደለም ብለው ያምኑ ነበር" ብለዋል።
📘ሸርሕ ኡሱል ኢዕቲቃዱ አህሊ-ሱና ወል-ጀማዓህ ገፅ 279


ስለዚህ ቁርአን የአላሁ ሱብሐነሀ ወተዓላ ንግግር እንጂ የፍጡራን ንግግር አይደለም ሊሆንም አይችልም።
አላህ እንዲህ ይላል

أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا
ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር፡፡
[📗አል-ኒሳእ 4:82]


ረመዷን ግማሽ ደርሰናል። ወሩ ሊያልቅ ነው😥
የተቀሩት ጥቂት ቀናቶችን ይህን የአላህ ቃል በመቅራት፣መልካም ስራዎችን በማብዛት እንጠቀምባቸው።
እስካሁን ተዳክመን ከነበርን ካሁኑ እንጀምር ይህ ትልቅ እድል እንዳያልፈን።

አላህ በዚህ በተከበረው ወር ቁርአንን ቀርተው ከሚጠቀሙ ባሮቹ ያድርገን
አሚን🤲🤲🤲🤲🤲
https://www.tgoop.com/iwnetlehullu1
عن أَبِي هُرَيْرَةَ ، قَالَ : قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : [" لَا تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يُقْبَضَ الْعِلْمُ، وَتَكْثُرَ الزَّلَازِلُ، وَيَتَقَارَبَ الزَّمَانُ، وَتَظْهَرَ الْفِتَنُ، وَيَكْثُرَ الْهَرْجُ، وَهُوَ الْقَتْلُ الْقَتْلُ، حَتَّى يَكْثُرَ فِيكُمُ الْمَالُ فَيَفِيضَ]
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ
«
ዕውቀት እስከ ሚነሳ
፣ (የመሬት) መንቀጥቀጥ እስከ ሚበዛ ወቅት (ጊዜ) እስከ ሚቀራረብ ፊትናዎች ግልፅ እስከ ሚኾኑ፣ ግድያ እስከ ሚበዛ እና ገንዘብ እስከ ሚትረፈረፍ ድረስ ቂያማ አትቆምም»
[📘Sahih al-Bukhari 1036]

صدق رسول الله
ነቢያችንﷺ እውነት ተናገሩ
ግዜ እንዴት እየሄደ እንደሆነ ሁላችን እያየን ነው። ስለዚህ የተቀሩት ጥቂት የረመዷን ቀናቶችን እንጠቀምባቸው።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኡስታዝ ሁሱ
ሰዎችን እያሰለመ ሳይሆን ድራማ እየሰራ ነው ወዘተ ለሚሉት ክርስቲያኖች ላኩላቸው።

ወለተ ሀና የነበረው ኢብራሂም ሆነ?
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ነቢያችሁ የዘር ፈሳሽ ያፈስ ስለነበረ ትክክለኛ ነቢይ አይደለም ለሚሉ አላዋቂዎች ላኩላቸው
🎤ኡስታዝ ሁሱ
አንድ ነገር ላስታውሳችሁ
➠ስሑር በልታችሁ ፈጅር(ሱብሒ) ሰላትን ሳትሰግዱ እንዳትተኙ
ያለ ሰላት ፆም ዋጋ የለውም
▣ ቁርአን ፍጡር አይደለም ▣

  بسم الله الرحمن الرحيم
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

➠ ባሳለፍነው ርዕሳችን ላይ ቁርአን የአላህ ቃል መሆኑን ከቁርአን ከሐድስና ከሰለፎች ንግግር በማስረጃ አይተናል። ዛሬ ደግሞ በአላህ ፈቃድ ቁርአን ፍጡር እንዳልሆነ እናያለን ኢንሻአላህ።

ቁርአን ፍጡር እንዳልሆነ ማስረጃዎቻችን👇
➥ ባለፈው ርዕስ ላይ ቁርአን የአላህ ቃል እንደሆነ አይተን ነበር።ቁርአን የአላህ ቃል ከሆነ ቁርአን ፍጡር ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም የአላህ ቃል የአላህ ባህሪይና መገለጫ እንጂ ፍጡር አይደለም። የአላህ ንግግር ከአላህ ተነጥሎ የሚቆም ነገር ስላልሆነ የአላህ ባህሪይና መገለጫ እንጂ ፍጡር አይደለም።

➥ ቁርአን ፍጡር እንዳልሆነ ካወቅንባቸው ማስረጃዎች ሁለተኛው
አላሁ ሱብሀነሁ ወተዐላ በቁርአኑ ወስጥ ትዕዛዙን ከፍጥረት ለይቶ ስላመጣው ፍጥረት እና ትዕዛዝ ለየ ቅል የሆኑ የተለያዩ ነገሮች ናቸው።

ألا لهُ الْخَلْقُ وَالْأَمْرُ ۗ تَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ
ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ (ክብሩ) ላቀ፡፡
[📗አዕራፍ 54]

☝️አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ እዚህ አንቀጽ ላይ ፍጥረት እና ትዕዛዝ ለይቶ ጠቅሷል።
ሁለቱም የተለያዩ ነገሮች ስለሆኑ የአላህ ትዕዛዝ ፍጡር አይደለም።

ቁርአን ደግሞ የአላህ ትዕዛዝ ስለሆነ ፍጡር ሊሆን አይችልም።

አላህ እንዲህ ይላል👇
وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَٰكِن جَعَلْنَاهُ نُورًا نَّهْدِي بِهِ مَن نَّشَاءُ مِنْ عِبَادِنَا ۚ وَإِنَّكَ لَتَهْدِي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ

እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም፡፡ ግን (መንፈሱን) ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ፡፡
[📗 ሹራ 42:52]

➥ ቁርአን ፍጡር እንዳልሆነ ካወቅንባቸው ማስረጃዎች ሌላኛው አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ በቁርአኑ ላይ እንዲህ ይላል👇
إِنَّا كُلَّ شَيْءٍ خَلَقْنَاهُ بِقَدَرٍ
እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው፡፡
[📗 አል'ቀመር 54:49]

አላህ የፈጠራቸው ነገሮች ገደብ እና ውስኑነት ማለቂያ አላቸው። ፍጡር የሆነ ነገር ሁሉ ያልቃል።
የአላህ ቃል ደግሞ ፍጡር ስላልሆነ ማለቂያ የለውም።

አላህ እንዲህ ይላል👇
قُل لَّوْ كَانَ الْبَحْرُ مِدَادًا لِّكَلِمَاتِ رَبِّي لَنَفِدَ الْبَحْرُ قَبْلَ أَن تَنفَدَ كَلِمَاتُ رَبِّي وَلَوْ جِئْنَا بِمِثْلِهِ مَدَدًا
«ባሕሩ ለጌታዬ ቃላት (መጻፊያ) ቀለሞችን በሆነ ኖሮ ብጤውን ጭማሪ ብናመጣም እንኳን የጌታዬ ቃላት ከማለቋ በፊት ባሕሩ ባለቀ ነበር» በላቸው፡፡
(📗ሱረቱል ከህፍ 18:109)

-ፍጡር ማለቂያ ካለውና የሚያልቅ ከሆነ
-የአላህ ቃል ደግሞ ማለቂያ ከሌለው
የአላህ ቃል ፍጡር ሊሆን አይችልም።

➥ በተጨማሪም ሀዲስ ላይ ነቢዩ ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በአላህ ንግግሮች ሲጠበቁ እና እንድንጠበቅ እየመከሩን እናያለን።

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إِذا نَزَلَ أَحَدُكُمْ مَنْزِلًا، فَلْيَقُلْ: أَعُوذُ بكَلِماتِ اللهِ التّامّاتِ مِن شَرِّ ما خَلَقَ، فإنَّه لا يَضُرُّهُ شيءٌ حتّى يَرْتَحِلَ منه.﴾
“አንዳችሁ የሆነ ቦታ ካረፈ ‘ሙሉ በሆኑት የአላህ ንግግሮች እሱ ከፈጠራቸው ተንኮሎች እጠበቃለሁ’ ካለ ከቦታው እስኪሄድ ድረስ ምንም ነገር አይጎዳውም።”
(📘ሙስሊም ዘግበውታል: 2708 )

➠እንደሚታወቀው ፍጡር በሆኑት ነገሮች መጠበቅ አይፈቀድም ክልክል ነው። ነቢዩ ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በአላህ ንግግሮች መጠበቃቸው የአላህ ንግግሮች ፍጡር አለመሆናቸው ያመላክታል። የአላህ ንግግሮች ፍጡር ቢሆኑ ኖሮማ ነቢዩ ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በአላህ ንግግሮች ባልተጠበቁ ነበር። ቁርአን ደግሞ የአላህ ንግግር ስለሆነ ፍጡር አይደለም።

ቀደምት ሰለፎቻችንም ቁርአን የአላህ ቃል እና ባህሪይ እንደሆነ ፍጡር  እንዳልሆነ በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል።

قال أحمدُ بنُ محمَّدِ بنِ حَنبَلٍ رحمه اللهُ: لقيتُ الرِّجالَ، والعُلَماءَ، والفُقَهاءَ، بمكَّةَ والمدينةِ والكوفةِ والبَصرةِ والشَّامِ والثُّغورِ وخُراسان، فرأيتُهم على السُّنَّةِ والجماعةِ، وسألتُ عنها الفُقَهاءَ؟ فكُلٌّ يقولُ: القُرآنُ كلامُ اللهِ، غيرُ مخلوقٍ، منه بدأ، وإليه يعودُ
ኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሐንበል{164-241ሂ) እንዲህ ብሏል" በመካ፣በመዲናህ፣በኩፋህ፣በበስራህ፣በሻም፣በሰغوር እና በኸራሳን ብዙ ኡለሞች(ሊቃውንት) በአህለ-ሱናህ ላይ ሆነው አይቻቸዋለሁ።ሁሉም ቁርአን የአላህ ቃል ነው፣ፍጡር አይደለም ከአላህ ዘንድ መውረድ ጀመረ ወደሱም ይመለሳል ብለው ያምኑ ነበር።
📘ኢኽቲሷስ አል-ቁርአን ገፅ 21

➠ ኢማም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል
" ቁርአን የአላህ ባህሪይ በመሆኑ ላይ የሱናህ ባለቤቶች ተስማምተዋል።"
📘መጅሙዕ አል-ፈታዋ ቅጽ 17 ገፅ 78

ኢማም አቡ ሐቲም አል-ራዚ{195-277ሂ} እና አቡ ዙርዓህ አል-ራዚ{207-264ሂ) በሁሉም የዐለማችን ክፍሎች የነበሩ ኡለሞች የነበሩበትን እምነት ሲጠቅሱ " ሁሉም ቁርአን የአላህ ቃል ነው፤ ፍጡር አይደለም ብለው ያምኑ ነበር" ብለዋል።
📘ሸርሕ ኡሱል ኢዕቲቃዱ አህሊ-ሱና ወል-ጀማዓህ ገፅ 279


ስለዚህ ቁርአን የአላሁ ሱብሐነሀ ወተዓላ ንግግር እና ባህሪይ እንጂ ፍጡር አይደለም።
https://www.tgoop.com/iwnetlehullu1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ክርስቲያኖች እስልምናን ለማንቋሸሽ ከተለያዩ ሐዲሳት አገኘናቸው ብለው የሚያመጡዋቸው ጥያቄዎች፣ በአብዛኛው የሚያተኩሩት ከፆታዊ ግንኙነት/ከትዳር/ የተያያዘ ነው።ይህን ፈልገው መርጠው ያመጡና ተመልሰው እስልምና ስለ /Sex/ ብቻ ነው የሚያወራው ይላሉ።

ወገኔ ያንተ እምነትማ ክስ ሰለምታቀርብባቸው ጉዳይ ምን ያስተምራል? ብትባል መልስ የለህም!

እኛ እናንተ የምታነሱዋቸውን ጉዳዮች ትዝም ብሎን አያቅም። ስጋዊ  ባህሪ/ስሜት/ የፈጠርልን አምላክ እንዴት በአግባቡ መጠቀምም እንዳለብን አስተምሮናል። በምድርም መንኩሰን በሰማይም እንደመላእክት ከሆንማ የሰው ልጅ ስጋዊ ስሜት እንዲኖረው ተደርጎ መፈጠሩ ምን ጥቅም አለው?  ያው መላእክት ሆነ እኮ!!

https://www.tgoop.com/Abuyusra3
▣ጥቂት ነጥቦች ስለ ኢዕቲካፍ! ▣
~
* ትርጓሜውለአላህ ዒባዳ(አምልኮ) ለመፈፀም በማሰብ መስጂድ ውስጥ መቆየት ማለት ነው።
* ብይኑ፦ በቁርኣን በሱና የተረጋገጠ ሙስተሐብ (የተወደደ) ዒባዳ ነው። ስለት ለተሳለበት ሰው ግዴታ ይሆናል። አዕቲካፍ ለሴቶችም የተፈቀደ ነው
* አላማው፦ ልብንም አካልንም ስብስብ አድርጎ በዒባዳ መጠመድ ነው። ኢዕቲካፍ የገባ ሰው ከትርፍ ወሬ፣ ከትርፍ ቅልቅል፣ ከትርፍ እንቅልፍ መቀነስ ይገባል።
* ጊዜው፦ አብዛኞቹ ዑለማእ ዘንድ በረመዷንም ይሁን ከረመዷን ውጭ መፈፀም ይቻላል። በላጩ ጊዜ ግን ረመዷን ነው። ከረመዷንም የመጨረሻዎቹ አስሮቹ የበለጡ ናቸው።
* ቦታው፦ ለወንድም ይሁን ለሴት መስጂድ ውስጥ ብቻ ነው።
* የጀመረ ሰው መጨረስ ግዴታ ነው? የሚያስገድድ ማስረጃ የለም።
* ዝቅተኛው ጊዜ ምን ያህል ነው? ገደብ የለውም። ያሰኘውን መጠን ያክል ነይቶ መቀመጥ ይችላል።
* ኢዕቲካፍ የገባ ሰው ለመፀዳዳት መውጣት ይችላል። የታመመን ለመጠየቅ፣ ጀናዛ ለመሸኘትና መሰል ጉዳዮች ግን አይወጣም። ግንኙነት፣ ግብይት፣ ስራ መስራት አይቻልም። ኢዕቲካፍ ላይ እያለ የታመመ ሰው መታገስና መቆየት የሚችል ከሆነ መውጣት የለበትም።
* የረመዷን የመጨረሻዎቹን አስር መግባት የፈለገ መቼ ይጀምር? የረመዷን 20ኛው ቀን ከመጥለቋ በፊት ቢሆን መልካም ነው።
* የሚወጣበት ደግሞ ረመዷን ተጠናቆ የዒድ ሌሊት ሲገባ ነው። ወላሁ አዕለም።
=
✍️ኡስታዝ Ibnu munewor

ቴሌግራም ቻናል፡- https://www.tgoop.com/IbnuMunewor
አሥሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱሏሂ ወበረካቱሁ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ

ሰለምቴዎችን አደራ
➘ ሰለምቴዎችን ስናገኝ ፍቅር እንስጣቸው እንንከባከባቸው እነሱ ለአላህ ብለው የተመቻቸ ኑሮን ትተው ብዙ ችግሮች ሲደርስባቸው እኛ ለነሱ ጀርባ ልንሰጣቸው ይቅርና በጣም ልንኸድማቸው ልንንከባከባቸው ይገባል።
በቻልነው ልክ እነሱን መርዳት አለብን።
ውዱ ነቢያችን ለሰለሙ ሰዎች እስከ 100 ግመል ይሰጡ ነበር። አስቡት ለአንድ ሰው 100 ግመል።
100 ግመል ስጡ አልላችሁም ቢያንስ የምትችሉትን ያክል አግዟቸው እርዷቸው ብቸኛ አታድርጓቸው።

➥ አንዳንድ ወንድም እህቶቻችን ለሚጠይቋቸው አንዳንድ ጥያቄዎች አላስፈላጊ መልስ አንስጣቸው። የተጠየቀውን ከመመለስ ይልቅ
አንተ ሙስሊም አይደለህምንዴ? ይሄ እንዴት ይጠፋሀል? ሙስሊም አትመስለኝም. ወዘተ እያሉ ሰዎችን ጥያቄ በመጠየቃቸው ብቻ የሚያከፍሩ አላዋቂዎች አሉ። አድቡ ስርዓት ያዙ መመለስ ባትችሉንኳ ዝም በሉ።
"በአላህና በመጨረሻ ቀን የሚያምን መልካም ይናገር ወይም ዝም ይበል ብለዋል ውዱ ነቢያችን
📘Muslim book 1 hadith 80

*ጠያቂዎቹ ገና አዲስ ሰለምቴ ሊሆኑ ይችላሉ ወይም ከእስልምና ራቅ ብለው የነበሩና የቶበቱ ሊሆኑ ይችላሉ ስለዚህ አደብ ሊኖረን ይገባል።
ካፊሮችንም እንደዛው አላህ በቁርአኑ
ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው (ዘዴ) ተከራከራቸው፡፡ 📗16:125
ብሎ እንዳዘዘን የአላህ ትዕዛዝ መፈፀም አለብን።
ነቢያችን ሊገድሏቸው ሊሰድቧቸው የመጡ ስንትና ስንት ሰዎችን ነው በመልካም ስነምግባራቸው አስልመው ያስቀሩት።
ሰለምቴዎችን ከራሳችሁ ጋር አስፈጥረ
➥ የሰለሙ ሰዎች የሰለሙበትን ቪድዮ አትለቀቁ፣ የሰለሙበትን ሀገር ስም አትጥቀሱ ይሀ ለነሱ ፊትና ነው የሚሆነው
➥ ዘካ የምታወጡ ሰዎች ደግሞ ዘካህ ከሚሰጣቸው ሰዎች መካከል ሰለምቴዎች ናቸውና ዘካህ ለሰለምቴዎች አውጡ
➥ሰለምቴዎችን አደራ አደራ➥
2025/03/21 21:26:24
Back to Top
HTML Embed Code: