Telegram Web
በአለም አቀፍ ደረጃ ዝናን ያተረፉ እነዚህን መጻሕፍት ለሀገር ውስጥ ንባብ በጥራት ታትመው ለንናብ ቀርበዋል :: ሁሉንም መጻሕፍት በሁሉም መደብሮቻዥን ያገኙታል ::

ጃዕፈር መጻሕፍት !
የደጃዝማች ከበደ ተሰማ " ነበር እንዳይረሳ ከታሪክ ማስታወሻ ባሻገር "

ይህ መጽሐፍ፣ ደጃዝማች ከበደ ተሰማ እጅግ ጥሩ ተቀባይነት ያገኘውን የታሪክ ማስታወሻ የተሰኘውን መጽሐፋቸውን 1962 ዓ.ም  ካሳተሙ በኋላ በተለያየ ጎዜ በታሪክ ጉዳይ ላይ የጻፏቸውን ማስታወሻዎች አንድ ጋር አሰባስቦ ያቀርባል ::

እነዚህን ጽሑፎች ደራሲው አንድ ጋር ጠርዘው አስቀምጠዋቸው ሰለነበር ፣ ካለፉ በኋላ ልጆቻቸው ጥራዙን ሲያገኙት ዋጋ ያለው ሥራ መሆኑን በመረዳት ተገቢው አርትኦት ከተደረገበት በኋላ እንዲታተም ይወስናሉ።

    ከጽሑፎቹ መረዳት እንደሚቻለው ፣የደራሲው ዓላማ በታሪክ ማስታወሻ ውስጥ ሊካተቱ ሲገባቸው የልተካተቱ ሁነቶችን ለትውልድ ለማቅረብ ሲሆን ፣በተጨማሪም 1953 ዓ.ም ያልተሳካ  መፈንቅለ-መንግስት ( "የታኅሣሥ ግርግር " የሚባለው-)ሲካሄድ በመንግስት ወገን ንቁ ተዋናይ ሰለነበሩ ፣ ያዩትን ፣የሰሙትን እና የታዘቡትን ጽፎ ለታሪክ ለማስቀረት ነው ።
ስለዚህ ይህ አዲሱ መጽሐፋቸው ልክ እንደቀድሞው ሥራቸው ፣ቀዳማይ ምንጭ ተደርጎ የሚወሰድ በጣም ጠቃሚ  ሰነድ ነው ። እያንዳንዱ ምዕራፍ ውስጥ እስካሁን የማናውቃቸው አዳዲስ መረጃዎች የተካተቱ ሲሆን ፣እነዚህም መረጃዎች ደራሲው በቀጥታ ከተካፈሉባቸው  ሁነቶች የተወሰዱ ፣ወይም ከተካፈሉ ሰዎች የሰሟቸው መሆኑን ፣በተደጋጋሚ ይገልጻሉ ።
 
    ከሁሉም በላይ የሚገርመው ፣በዘመኑ ሰለ"ታሪክ"ሲታሰብ ፣ሲወራ ፣ሲጻፍ "ታሪክ " ተብለው የማይገመቱ እንቅስቃሴዎችን ሁሉ ማካተታቸውን ነው።

ለምሳሌ ፣የአዲስ አበባ አሰፋፈር ፣የሴትኛ አዳሪዎችን ሁኔታ ፣የጠላ ሻጮችን አሰራር (አዝማሪ ጻዲቄ ሳትቀር ) የሌባ ሻይን አሰራር  ዘርዘር አድርጎ በመተረክ ፣ ከዚህ በፊት አንበነው የማናውቀውን የአዲስ አበቤዋች ን ኑሮ አሰነብበውናል ።

ከመጽሐፉ ጀርባ የሚነበብ ።
" በትረዳቢ "

ዛሬ የኛ የመሀይሞቹ ኋላቀር የአስተራረስ ዘይቤ ካልዘመነ፤ ነገ ዲግሪ የጫኑ ልጆቻችን ሞፈር ቀንበራችንን ተረክበው ያርሳሉ ብሎ ማሰብ ዘበት ነው። በዚህም ምክንያት ገበሬ የተባለ ፍጡር ከሀገራችን ምድር ላይ ልክ እንደ ዳይኖሰር ይጠፋል። ያንግዜ እናንተ ለልጆቻችሁ እንዲህ እያላችሁ ተረት ትነግራላችሁ፤

  " በድሮሮሮሮ ጊዜ ገበሬ የሚባል ፍጡር ነበረ። ታዲያ ይሄ ብርቱ ሰው እንቅልፍ ሳይበግረው በሌሊት ከሞቀ አልጋው ላይ ወርዶ ሞፈር ቀንበሩን ተሸክሞ በሮቹን እየነዳ ወደ ማሳው አመራ። መቼም የማሳው ስፋት ለጉድ ነውና ከበሮቹጋ ሲታገል ሰዓቱ ነጎደ። የፀሀዩ ግለትም በረታ። ነገር ግን ይሄ ብርቱ ገበሬ ፀሀዩ ሳይበግረው ድካም ጉልበቱን ሳያዝለው ማሳውን አርሶና አለስልሶ በዘር ሸፈነ። ምንም እንኳን ሰፊና ለም መሬት ቢኖረውም የሚያርሰው በኋላቀር መንገድ ስለሆነ ያገኛት ምርት አነስተኛ ነች። እሷንም ደላሎች በማይረባ ገንዘብ ገዝተው ከበሩበት። ይሄ ብርቱ ፍጡር አመቱን ሙሉ ላቡን ጠብ አድርጎ ባገኛት ገንዘብ ሳይማር ልጆቹን አስተማረ። አንደኛው ዶክተር ሌላኛው ደግሞ እንጂነር ሆነ። ግን ምንያደርጋል ከበሽታዬ ይፈውሱኛል፣ የዘመመ ጎጆዬን ያቀኑልኛል ያላቸው ልጆቹ ከተማ ቀልጠው ቀሩ። እሱም አስታማሚ አጥቶ የወላድ መካን ሆኖ ደሳሳ ጎጃው ውስጥ ማቅቆ ሞተ። ገበሬውም ከነሞፈርና ቀንበሩ ተቀበረ " ይባላል ፤

ተረቴን መልሱ መሬቴን በትራክተር እረሱ
በስንዴ በገብሱ እርቃኔን አልብሱ
ሀብትና ንብረቴን እኩል ተቋደሱ
እየለመናችሁ እኔን አታስወቅሱ
ሁለት ያላችሁ አንዱን ለግሱ
የታረዘ አልብሱ የተራበ አጉርሱ
በዘር አትባሉ ደሜን አታፍስሱ
መሬቴን በሰላም በፍቅር ቀድሱ
ፋንድያ ለመልቀም ከምትልከሰከሱ
ወደናታችሁ ጉያ ወዲህ ተመለሱ
የተኛችሁበትን ፍራሻችሁን አንሱ
ኢትዮጵያ እንድታድግ በህብረት ተነሱ
የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ለክረምት ባዘጋጀው ልዩ የሥነ-ጽሑፍ ስልጠና ላይ ለሁለት ደምበኞቻችን ነጻ ስልጠና እሰጥላቹሃለሁ ብሎናል :: እኛ ደስ ብሎናል :: ዕድሉን ተጠቀሙበት :: ይህን ዕድል ለመጠቀም የሚመለከተውን አካል ቀጥሎ በምናስቀምጠው የቴሌግራም ሊንክ ➡️ @Geze4320 ተነጋገሩ ::

እንዲሁም ይህን በአንጋፋ ታላላቅ ደራሲያንና ባለሙያዎች የሚሰጠውን ይህን የሥነጽሑፍ ስልጠና ለመውሰድ ፍላጎቱ ያላችሁ ደምበኞቻችን ፎቶው ላይ ባሉት ስልኮች መረጃዎችን መውሰድ ትችላላችሁ ::
Forwarded from Tedossier
An_Interview_with_Adam_Reta.pdf
308.5 KB
An interview with Adam Reta, by Aklilu Desalegn
Forwarded from Tedossier
ስለ ግራጫ ቃጭሎች - ስለ ኻያኛ ልደቱ
(ቁርጥርጥ ሐሳቦች)

1997 በኢትዮጵያ ታሪክ ተስፋ እና ቀቢጸ ተስፋ፣ ነጻነት እና አፈና፣ ሥልጡንነት እና አረመኒነት፣ ንቃት እና ማድባት … እየተፈራረቁ፣ እየተደበላለቁም በአደባባይ የተገለጡበት፤ ጠባሳም አሻራም ጥሎ ያለፈ ዓመት ነው። ለታሪካዊ ለውጥ የታጨ ዓመት ይመስልም ነበር። በዚህ መኻል ነበር ግራጫ ቃጭሎች የራሱን አብዮት ቀይሶ ለኅትመት የበቃው፤ በብዙ ግርግር መኻል ነበር ከአንባቢው ጋር የተገናኘው።

በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ እንደ አንድ የዘመን ለውጥ ምልክት ከማያቸው ሥራዎች አንዱ በ1983/4 ተጽፎ፣ በ1997 ዓ.ም. የታተመው የአዳም ረታ ግራጫ ቃጭሎች ነው። ይህንን የዐማርኛን ሥነ ጽሑፍ ከዐሥርት ዓመታት የረጋ ጕዞው ያናወጠውን መጽሐፍ፣ ለብዙ ዐዳዲስ የአጻጻፍ ሙክረቶች መነሻ ኾኗል። ብዙ ጥናቶችን እና ትንታኔዎችንም ጋብዟል - ገና የሚገባውን ያህል ባይጠናም፤ ለሥነ ጽሑፍ ማስተማርያነትም የሚዘወተር ባይመስለኝም።

“ልጅ ያቦካው ለራት በማይበቃበት አገር” መዝገቡ በተባለ “ታላቅ ተቀማጭ” ጎረምሳ/ኋላም ጎልማሳ/ ዐይን ዓለምን፣ ሰውን እና ከባቢውን የምናይበት ይህ ከፊል ፋንታሲያዊ ድርሰት፣ ከአዳም ረታ ጋር እንደገና ለመተዋወቅ ያበቃን ሥራ ነው። አዳም በግራጫ ቃጭሎች አደፍራሽ ኾኖ ተገልጧል። ከጦብያ ጀምሮ ለ97 ዓመት የተከተልነውን ልቦለድን በቀጤ ሴራ (linear plot) የማዋቀርን ልማድ ሽሮ የተቆራረጡ የታሪክ/የትውስታ ክፍሎችን ያለ “ከዚህ እስከዚያ” ስልት፣ ሥር በሥር እያገናኘ ተርኮልናል። ለነገሩ ደራሲው ለዘመኑ መንፈስ ታማኝ ከኾነ መስመር ተከትሎ የሚኼድን ታሪክ መጻፍ ማቆም የነበረበት ከ1966 አብዮት እና ካስከተለው ውጥንቅጥ ጀምሮ ነው ባይ ነው አዳም፦ “A society in chaos/disharmony cannot give you individuals that are comfortable in linearity. I have to look ways to represent such realities and processes.” በርግጥ ዘመኑን መግለጥ የደራሲው ኹሉ ዓላማ አይኾንም፤ አንዳንዱ ለዘመኑ የሚመኘውንም መጻፍ ይመርጣልና። የከልደት እስከ ሞት አጻጻፍም ለዝብርቅርቃችን፣ ለመበሽቀጣችን፣ ለ“ርእይ መነጠቃችን”፣ ለ“ሰብእና ንጥፈታችን” ጉልበታም መተረኪያ መኾንም ችሏል።

ኅፅን፣ #ኅፅናዊነት፤ እንጀራዊነት፣ እንጆሬያዊነት የሚባሉ የአዳምን የአጻጻፍ ምርጫ የሚገልጡ ስያሜዎች (terminologies) ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበብነውም በግራጫ ቃጭሎች ነው። ስለ ልቦለድ የተስፋፊነት እምቅ ኃይል፣ አልቆ ስላለማለቁም በግራጫው መግቢያ አንብበናል። እያንዳንዱ የኅፅን መጠቆሚያ ራሱን የቻለ ወሽመጥ ታሪክ ሲወጣው ዐይተናል። ከግራጫም በኋላ እቴሜቴ ሎሚ ሽታ ውስጥ የተጠቆሙት ኅፅኖች ሙሉ ሙሉ ታሪክ ይዘው መጥተዋል። የሎሚሽታ እና የፍቅረሥላሴ ታሪክ፣ መስኮት ገረሱን ይጠራል፣ መስኮት ገረሱ ደግሞ ስብሃትን ያስታውሳል፣ ገጸ ባሕርይ ሆኖ የገባው ስብሃት የእውኑን ደራሲ ስብሃት ገብረ እግዚአብሔርን ከነድርሰቶቹ ያስታውሰናል። አዳም ይህንኑ ቲዎሪውን እያራቀቀ መጥቶም ይመስለኛል ከ“አፍ” ወዲህ #ሥግር_ልቦለድ የሚል አጻጻፍን ያስተዋወቀን - በዐምሳ ስድሳ ገጽ ትንታኔው።

ይህ ሥራ ሐሳብን ምናባዊ ተረክ ፈጥሮ እያዋዙ መንገር እንደሚቻል ዐማርኛ እንደተማረባት የአፈወርቅ “ጦቢያ”፣ አጫጭር ተረኮችን ሰብስቦ በአንድ መጽሐፍ ማሳተም እንደሚቻል እንዳየንባት የታደሰ ሊበን “መስከረም”፣ በጽሑፍ የተደረሰ ተረት ለርእዮተ ዓለም መግለጫነት የሚውል እምቅ ፈጠራ መኾኑን እንዳወቅንባት የሐዲስ “ተረት ተረት”፣ እንደነጸጋዬም፣ እንደነ ገብረ ክርስቶስም፣ እንደነ ሰሎሞን ዴሬሳም መንገድ ቀያሽ ሥራዎች ዐዲስ አደራረስን ያማርኛ ሥነ ጽሑፍ ያስተናገደበት ሥራ ነው። ከግራጫ ወዲህ ይርቡም አይርቡም መንገዱን የተከተሉ ድርሰቶች አንብበናልና፣ ባለተጽዕኖነቱን መስክረናል።

{ግራፊክ ዲዛይኑ የብሥራት መብራቱ፣ ፎቶው ደግሞ የማኅሌት ተሾመ ነው።
መልካም 20ኛ ዓመት!
ከሰኔ 28-30፣ 2017 ዓ.ም.
ፀደይ ወንድሙ (ፀዲ)፣ ብሥሬ እና እኔ እየጻፍን፣ እያጋራን “ግራጫ ቃጭሎች”ን እንዘክረው ብለን ጋብዘናችኋል።}
“DOPAMINE DETOX “አሁን በመደብራችን ያገኙታል
☎️
0911932088
0911125324
“How to Finish EVery thing you Start “
አሁን በመደብራችን በቅናሽ ዋጋ አቅረብንሎታል።
☎️
0911932088
0911125324
Forwarded from Esubalew Abera N.
አቶ አዳም ረታ መጽሐፉን ለምን «ግራጫ ቃጭሎች» አለው? ለምሳሌ፦ Simply በዋና ገጸ ባሕርይው ስም «መዝገቡ» ብሎ ሊጠራው አይችልም ነበር? ያ ግን ተለምዷዊና ቀጥተኛ ይሆን ነበር። ከድርሰቱ ጋር በግልጽ የሚገናኝ ስያሜ ከጽሕፈቱ (text) እንደ ሰበዝ መዞ መስጠት ተለምዷዊ መንገድ ነው። አቶ አዳም ረታ ያንን ልማድ ሲሽር «ግራጫ ቃጭሎች» አለው። በዚህ የሻረው የራሱንም ነባር ልማድ ወይም የ«ማህሌት»ንም (1981) አሰያየም ይመስለኛል። አንድምታ በማያሻው መንገድ «መዝገቡ» ቢለው ኖሮ ደረቅ/literal ይሆን ነበር። «ግራጫ ቃጭሎች» የሚለው ስያሜ ግን ለአንባቢያን ትርጓሜ (for interpretation) ክፍት ነው። ለምሳሌ፦ ግራጫ እንደ ቀለም ሕይወት ነጭና ጥቁር አለመሆኑን (the moral ambiguities of life) ይናገራል። «ቃጭሉ» መዝገቡ እንደ ግለሰብ ባንቀላፋና በደነዘዘ ኅብረተሰብ መሃል፣ ሕይወትን የሚታዘብ ንቁ (conscious) የንፋስ መውጫ ዜጋ መሆኑን ሊወክል ይችላል —ሌላም፣ ሌላም።

. . .ብቻ «ግራጫ ቃጭሎች» ታላቅ ክስተት ነው !
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የተጻፉት  "ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ" የተሰኘው  መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል ::

“ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ”  በሚል ርዕስ ለንባብ የቀረበው ይህ መጽሐፍ  የአገር  በቀል ዕውቀትና ብሂል ለአገራችን ፖለቲካ መፍትሄ ጠቋሚ መንገድ ሲሆን  የመጽሐፉ ሽያጭ ገቢ ባለፈዉ ዓመት በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ሻቻ ጎዚዲ ቀበሌ በተከሰተዉ  የመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች መልሶ ማቋቋሚያና  ለትምህርት ቤት ግንባታ ይውላል ::

"ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ" መጽሐፍ የኢትዮጵያ ህዝብን የዘመናት የዴሞክራሲ ፍለጋ ይዳስሳል ፡፡ መጽሐፉ ኢትዮጵያዊ ባህል ወርቃማ የእሴት ቁልፎችን ይዟል።

ጸሐፊው በመጽሐፋቸው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ለትውልዶች ሲተላለፍ የቆየ ህዝባዊ ጥያቄ መሆኑን ገልፀው፤ ሁሉም ሲያውጠነጥነው የቆየና እስካሁንም የተሟላ ምላሽ ያልተገኘለት መሆኑን አንስተዋል።

መጽሐፉ ስለዴሞክራሲ የተከተልነውን አካሄድ እንድናጤንና በትኩረት እንድንሰራ የሚያግዝ ነው ።

" በዴሞክራሲ ላይ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት ሀገር በቀል እሴቶችን ከዘመናዊ አስተሳሰብ ጋር ማጣጣም፣ ኋላቀር የፖለቲካ ባህልን መቀየርና ሚዛናዊነትን ማጎልበት እንዲሁም የዴሞክራሲ ተቋማትን ማጠናከር ይገባል " ይላሉ ::

"ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲ ፍለጋ" መፅሐፍ ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን ማስረከብ የሚያስችል ምህዳር ለመፍጠር ጥብቅ ንድፈ ሀሳቦችን ያቀርባል ።

መጽሐፉ በሁሉም በመደብሮቻችን ይገኛል ::

https://www.facebook.com/share/r/16sGj5gi6c/
Forwarded from Tedossier
ድኅረ_ዘመናዊ_የሥነ_ጽሑፍ_መገለጫዎች_በግራጫ_ቃጭሎች_ውስጥ.pdf
221.3 KB
1. ፀዲ በ2007 ብሌን መጽሔት ላይ ያሳተመችው “ድኅረ-ዘመናዊ የሥነ-ጽሑፍ መገለጫዎች በግራጫ ቃጭሎች ውስጥ” የሚለው መጣጥፍ ዋና ሥራ ነው።
ኦ አዳም.pdf
235.5 KB
2. በ2001 ዓ.ም. አዳም ለአዲስ ነገር ጋዜጣ ጠለቅ ያለ ቃለ መጠይቅ ሰጥቶ ነበር። ያ “ኦ አዳም!” በሚል ርእስ የታተመ ቃለመጠይቅ አኹንም ድረስ ስለ ሥራዎቹ በሚጻፉ ጥናቶች ወይም መጣጥፎች የሚነሣ፣ ከአዳም ርእዮተ ኪን ጋር ያስተዋወቀን ማጣቀሻ ነው።
አዳም ሠራሽ የሥነ ጽሑፍ ዘውግ.pdf
8.3 MB
3. “አብሮነት” የሚባል መጽሔት (ዲጂታል?) ላይ “አዳም ሠራሽ የሥነ ጽሑፍ ዘውግ” በሚል በሁለት ክፍል ከቀረበው ቃለ መጠይቅ አንዱን አግኝቼዋለሁ። ሁለተኛውን ክፍል።
ADAM_S WORDS.pdf
84.1 KB
4.የ መረቅ ምረቃ ሰሞን ይመስለኛል፣ አዳም በፌስቡክ ለሚቀርቡለት ጥያቄዎች የሰጣቸውን ምላሾች፣ እነ አንተነህ ተስፋዬ ይመስሉኛል፣ በአንድ ፋይል አደራጅተው አጋርተውን ነበር። Adam’s Words ያሉት ፋይል ውስጥ ስለ ኅፅናዊነት፣ ስለ ግራጫም ተጽፏል - መጻፊያ መድረኩ በፈቀደው መጠን።
Adam Retta-s Intereconnected World.pdf
1.7 MB
5. ይህንን እንኳን ምናልባት አላያችሁት እንደሁ ብዬ ነው ያስቀመጥኩት፤ Ethiopian Business Review መጽሔት ላይ የወጣ ዘገባ/መጣጥፍ ነው።
Forwarded from Tedossier
የአዳም_ረታ_መንገድ_ኅፅናዊነትን_ስንቀርበው.pdf
301.4 KB
6. ይሄ ተዘንግቶ ቆይቶ በፀዲ አስታዋሽነት የተካተተ የእኔ ጽሑፍ ነው። ፲ ዓመት ያለፈውና ያኑበባችሁት የሚመስለኝ ጽሑፍ።
2025/07/08 11:54:25
Back to Top
HTML Embed Code: