Telegram Web
"ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤" |ዕብራውያን 10 : 24|
@kaletsidkzm
Forwarded from ከቤዘማርያም
"ብፅዕት ከርሥ እንተ ጾረተከ
  ወብፁዓት አጥባት እለ ሐፀናከ
ብፁዕ ነህ ያሬድ ሆይ የተመሰገንህ
ሰማያዊ ዜማን ለምድር ያሰማህ"

የመካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ቀበና አቦ) ቤተ-ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ዛሬ እናንተን ይጠብቃል።

ዛሬ ግንቦት 10 እግሮች ኹሉ ወደ መካነሕይወት ያቀናሉ ሌሎች ወንድም እህቶችን ቤተሰብ ጎረቤታችንን በመጋበዝ በአሳደገችን ቤተክርስቲያን አውደምሕረት እንገናኝ

ዛሬ 11:00 ሰዓት በጸሎት ይጀመራል

ታላቁን
የዜማ መሠረት
የቅኔ ሊቅ
ባሕታዊ ግሑስ አባት
የመጻሕፍት ደራሲ
የቤተክርስቲያን ውበት
በምስጋና ጌጥ የተዋበ
ንጹሕ ብፁዕ ብእሴ እግዚአብሔር
ቅዱስ ያሬድን እንዘክር

መቅረት አይፈቀድም ማርፈድ ያስቆጫል

መካነሕይወት ሰንበት ት/ቤት
መምህሩም (አጎቱ) ዐንገቱን አቅፎ ስሞ ትምህርቱን እንዲቀጥል  ፈቀደለት ድጓ ከዚህ በኋላ በጾም በጸሎትና በልቅሶ በሐዘን ወደ እግዚአብሔር ቢለምን መንፈስ ቅዱስ ገለጸለትና በዐጭር ጊዜ ብሉይንና ሐዲስን ተምሮ ዲቁና ተሾመ፡፡ በዚያ ወራት በከፍተኛ ቃል የመዝሙር ማሕሌት የለም፡፡ ጌታ ግን መታሰቢያ ሊያቆምለት በወደደ ጊዜ ፫ ወፎችን ከገነት ላከለት፡፡ በሰው ቋንቋ ተነጋገሩትና ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት አወጡት፡፡ በዚያም የ፳፬ቱን ካህናተ ሰማይ ማሕሌት ተማረ፡፡ ተመልሶም በአክሱም ቤተ ክርስቲያን በ፫ ሰዓት ገበቶ ኅዳር ፮ ቀን በአክሱም ዐውደ ምሕረት በታላቅ ቃል ‹‹ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ›› እንዲል ብሎ አመሰገነ፡፡ይቺንም ምስጋና አርያም ብሎ ጠራት። ስለዚህ ከኅዳር ፮-፲፪ አስተምሕሮ ተባለ፡፡
ከዚያም በኋላ ከዓመት እስከ ዓመት በየክፈለ ዘመኑ በክረምትና በበጋ በመጸውና በጸደይ በአጽዋማትና በበዓላት በሰንበታትም እንዲሁም በመላእክት በዓል በነቢያትና በሐዋርያት በጻድቃንና በሰማዕታት በደናግልም በዓል የሚሆን አድርጎ በሦስቱ ዜማው ሠራ ይኸውም ግዕዝ ዕዝል አራራይ ነው።
ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን አገር ሒዶ በጾም በጸሎት ተወስኖ ሥጋውን እጅግ እያደከመ ኖሮ ገድሉን በዚያ ፈጸመ።
እግዚአብሔር ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጥቶታል።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታችን በቅዱስ ያሬድ ጸሎት ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን።
              ወስበሐት ለእግዚአብሔር
በትላንትናው ዕለት በመካነ ሕይወት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን  የዝክረ ቅዱስ ያሬድን በዓል በታላቅ ድምቀት ተከበረ
ግንቦት 10 2017ዓ.ም
በመካነ ሕይወት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን መካነ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዜማ አባት የሆነው የቅዱስ ያሬድ መታሰቢያ በዓል በታላቅ ድምቀት አከበረ። በዓሉ በቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ውስጥ የተካሄደ ሲሆን  ምዕመናን፣ የሃይማኖት አባቶችና የማኅበረሰብ አንጋፋዎች ተገኝተዋል።
በዓሉ መንፈሳዊ ዕውቀትን፣ ባህላዊ ትውፊትን ያሳየ ነበር። ተሳታፊዎች ስለ ቅዱስ ያሬድ ሕይወት፣ ለኢትዮጵያ የዜማ ባህል ያበረከተውን አስተዋጽኦ ተምረዋል።
በዓሉም ላይ በቅዱስ ያሬድ የዜማ ድርሰቶች ላይ በተመሰረተ ጸሎት ተከፍቷል በመቀጠልም በህጻናት ክፍል የመክፈቻ መዝሙር ቀረበ ከዛም ነፍስን የሚመግብ ስለ ቅዱስ ያሬድ የሚያትት በመምህር ደረሰ ቃለ ወንጌል ተሰቷል።እንዲህ እንዲህ እያለ  በሰንበት ትምሀርት ቤቱ የቅዱስ ያሬድን የህይወት ታሪክ የሚያሳይ ስራ በኪነ ጥበበ ክፍል ቀርቧል። በመቀጠልም የቅዱሱን አባት የዜማ ድርሰት በወረብ እና በመዝሙር  አግዚአብሔርን አመስግነናል።አምላከ ቅዱስ ያሬድ ያዓመት ሰው ይበለን።
2025/05/20 02:43:12
Back to Top
HTML Embed Code: