Telegram Web
Live stream finished (1 minute)
ውድ የቃሉን ጻፈው ተወዳዳሪዎቻችንየ ሁለተኛ ዙር LIVE ኘሮግራም ተጀምሯል!
በሁለተኛ ዙር የሚጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍት በቴሌግራም ሙሉ ማብራርያ ይለቃል።!
ውድ የቃሉን ጻፈው ተሳታፊዎች
ተረጋግታቹ መጻፋችሁን እንድትጀምሩ እያልን በዚህ ሁለተኛ ዙር ውድድር አጠቃላይ የተሰጠውን የመጽሐፍት ክፍሎች ጽፎ ለማጠናቀቅ የተመደበው ጊዜ
150 ቀን ነው።

እነዚህን ማብራሪያዎችን እና ምክሮችን በመከተል መጻፍ መጀመር ይቻላል፦

- ከሁሉም አስቀድማቹ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በምታሳልፉት ግዜ እንድትደሰቱ እና ከእግዚብአሔር ቃል ለመማር እንድትጸልዩ፣

- የምትጽፉት ጹሁፍ የሚነበብ እና በእርጋታ በጥራት እንዲሁም ባለመዘግየት በፍጥነት የተዘጋጀ እና መጽሐፍ ቅዱስ የሚያሰተላልፈውን መልዕክት የሚያስተላልፍ ሆኖ መቅረብ በሚችልበት ሁኔታ እንዲጻፍ፣

- ወላጆች እና ታላላቆች ህጻናትን እንድታበረታቱ እና እያረፉም እየፈጠኑም እንዲጽፉ በመደገፍ እንድትከታተሏቸው፣

- ታዳጊዎች እና ወጣቶች የአለምን ታላቁን መጽሐፍ ለመመርመር ለማገላበጥ፣ የአምላክን ታሪክ እና ለሰው ልጅ ያለውን እቅድ ለማወቅ ይህንን አጋጣሚ እንድትጠቀሙበት፣

- ጎልማሶች እና አባቶች እናቶች ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በመቆየት ልምላሜ እንዲሆንላቹ፣

ጥሪው ለሁላችንም ነው!
ልዪ ልዮ መግለጫዎች፡

- የሚጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እና በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር የታተሙ የ66ቱ መጽሐፍት እትም እንዲሁም በቢብሊካ ኢትዮጵያ የታተሙ የመጽሐፍ ቅጂዎችን ነው። የቋንቋ ገደብ የለም።

- በመሃል የሚገኙ ማጣቀሻወች አይጻፉም፣

- በግርጌ የሚገኝ መግለጫ አይጻፍም፣

- ቁጥሮች በአዲስ መስመር አይጀምሩም፤

- ምዕራፍም ሆነ መፅሀፍ በአዲስ መስመር መጀመር አለበት።

- ከሁለት ነጥብ ውጪ ያሉ ስርዓተ ነጥቦች ሁሉ መጻፍ አለባቸው፣

- ተመሳሳይ ድምፅ ያላቸውን ሆሄአት ማቀያየር አይቻልም፤በመጽሐፍ ቅዱሱ ላይ በሠፈሩበት መልክ መጻፍ አለባቸው፣

- ደብተር ወይም የሚጽፉበት ጥራዝ ሲያልቅ መጨመር ይቻላል፣

- እያንዳዱ መጽሐፍ ማለትም ዘፍጥረት ፣ ዘጸአት ፣ ዘኁልቁ እያላቹ ስትቀጥሉ አስቀድማችሁ

'ቃሉን ጻፈው ሁለተኛ (2ኛ) ዙር '
'መጽሐፍ ቅዱሴን እጽፈዋለሁ!'
'መጽሐፍ ቅዱሴን እጠብቃለሁ!'
ብሎ መጻፍን አትርሱ፣

- በየመሀሉ ያሉ ርዕሶች መጻፍ ይኖርባቸዋል (ለአዲሱ መደበኛ ትርጉም ተጠቃሚዎች)፣
- እንዳመቺነቱ ምዕራፍ አንድ ምዕራፍ ሁለት እያላቹ መቀጠል የምትችሉ ሲሆን ምዕራፍ አንድ ወይም ሁለት የሚለውን በመጻፍ ፈንታ ቁጥሩን እራሱ ጎላ አርጎ በመጻፍ ማለትም ምዕራፍ አንድ ሲሆን ተለቅ ተደርጎ የተጻፈ 1, 2 ሲሆን እንደዛው ጎላ አድርጋቹ በመጻፍ መቀጠል ትችላላቹ።
በሁለተኛ ዙር የሚጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍት፡
ኦሪት ዘፍጥረት
ኦሪት ዘጸአት
ኦሪት ዘሌዋውያን
ኦሪት ዘኁልቁ
ኦሪት ዘዳግም
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደነዌ
መጽሐፈ መሳፍንት
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ
መጽሐፈ ኢዮብ
መዝሙረ ዳዊት
መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን
ትንቢተ ኢሳያስ
ትንቢተ ኤርምያስ
ትንቢተ አሞጽ
ትንቢተ ናሆም
ትንቢተ ሐጌ እና
ትንቢተ ሚልክያስ

18 መጽሐፍት ናቸው።
ዘፍጥረት 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
² ምድርም ባዶ ነበረች፥ አንዳችም አልነበረባትም፤ ጨለማም በጥልቁ ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር።
³ እግዚአብሔርም፦ ብርሃን ይሁን አለ፤ ብርሃንም ሆነ።
⁴ እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፥ እግዚአብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ።
⁵ እግዚአብሔርም ብርሃኑን ቀን ብሎ ጠራው፥ ጨለማውንም ሌሊት አለው። ማታም ሆነ ጥዋትም ሆነ፥ አንድ ቀን።
ማሳሰብያ፡
'ቁጥሮች በአዲስ መስመር አይጀመሩም' ተብሎ ከላይ በመግለጫው የተቀመጠው የሚያስረዳው ተያያዥ ሀሳቦችን ለያይተን መጻፍ አንችልም። ሆኖም ግን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በአዲስ መስመር ላይ የተቀመጡ ቁጥሮችን እንደአቀማመጣቸው ልንጽፋቸው ይገባል።
ከቀናት ሁሉ የባከነ ቀን ቢኖር መጽሐፍ ቅዱስን ሳናነብ የዋልንበት ቀን ነው።
ዘጸአት 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² ከሂሶጵ ቅጠልም ጭብጥ ውሰዱ፥ በዕቃ ውስጥ ባለውም ደም ንከሩት፥ በዕቃውም ውስጥ ካለው ደም ሁለቱን መቃኖችና ጉበኑን እርጩ ከእናንተም አንድ ሰው ከቤቱ ደጅ እስኪነጋ ድረስ አይውጣ።


²⁴ ለእናንተ ለልጆቻችሁም ለዘላለም ሥርዓት አድርጋችሁ ይህችን ነገር ጠብቁ።


⁴² ይህች ሌሊት ከግብፅ ምድር ስላወጣቸው ለእግዚአብሔር የተጠበቀች ናት፤ ይህች ሌሊት በእስራኤል ልጆች ሁሉ ዘንድ እስከ ልጅ ልጃቸው ድረስ ለእግዚአብሔር የተጠበቀች ናት።
⁴³ እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን አለ፦ ይህ የፋሲካ ሕግ ነው፤ ከእርሱ እንግዳ ሰው አይብላ።
በተለያየ ምክኒያት ያልተመዘገባቹ በዚህ ሳምንት መመዝገብ ትችላላቹ!
ቃሉን ጻፈው Kalun Tsafew pinned «በሁለተኛ ዙር የሚጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍት፡ ኦሪት ዘፍጥረት ኦሪት ዘጸአት ኦሪት ዘሌዋውያን ኦሪት ዘኁልቁ ኦሪት ዘዳግም መጽሐፈ ኢያሱ ወልደነዌ መጽሐፈ መሳፍንት መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ መጽሐፈ ኢዮብ መዝሙረ ዳዊት መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ትንቢተ ኢሳያስ ትንቢተ ኤርምያስ ትንቢተ አሞጽ ትንቢተ ናሆም ትንቢተ ሐጌ እና ትንቢተ ሚልክያስ 18 መጽሐፍት ናቸው።»
ቃሉን ጻፈው Kalun Tsafew pinned «ልዪ ልዮ መግለጫዎች፡ - የሚጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እና በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር የታተሙ የ66ቱ መጽሐፍት እትም እንዲሁም በቢብሊካ ኢትዮጵያ የታተሙ የመጽሐፍ ቅጂዎችን ነው። የቋንቋ ገደብ የለም። - በመሃል የሚገኙ ማጣቀሻወች አይጻፉም፣ - በግርጌ የሚገኝ መግለጫ አይጻፍም፣ - ቁጥሮች በአዲስ መስመር አይጀምሩም፤ - ምዕራፍም ሆነ መፅሀፍ በአዲስ መስመር መጀመር…»
ቃሉን ጻፈው Kalun Tsafew pinned «በሁለተኛ ዙር የሚጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍት፡ ኦሪት ዘፍጥረት ኦሪት ዘጸአት ኦሪት ዘሌዋውያን ኦሪት ዘኁልቁ ኦሪት ዘዳግም መጽሐፈ ኢያሱ ወልደነዌ መጽሐፈ መሳፍንት መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ መጽሐፈ ኢዮብ መዝሙረ ዳዊት መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ትንቢተ ኢሳያስ ትንቢተ ኤርምያስ ትንቢተ አሞጽ ትንቢተ ናሆም ትንቢተ ሐጌ እና ትንቢተ ሚልክያስ 18 መጽሐፍት ናቸው።»
ውድ የቃሉን ጻፈው ተወዳዳሪዎች:
የመወዳደሪያ ህጎችን እና በሁለተኛው ዙር የሚጻፉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከላይ 'pinned message' የሚለው ላይ በቀላሉ ማግኘት ትችላላችሁ።
2024/11/19 21:02:14
Back to Top
HTML Embed Code: