ምን አልባት Internet ሊዘጋ ይችላል እየተባለ ነው እና ይቺን ነገር ብናውቃት ጥሩ ነው 🙏
ደውል በተለያየ ሰዓት በቤተክርስቲያን ውስጥ ለአገልግሎት ይደወላል። ነገር ግን ለሁሉም አገልግሎት አንድ ዓይነት ደውል አይደውልም!
"በአደጋ ጊዜ ሲደወል ከሌሎቹ የሚለየው ደውሉን ቶሎ ቶሎ በፍጥነት ሲደወል ቤተ ክርስቲያን ላይ ችግር አለ ድረሱልን ማለት ነው።"
ቤተክርስቲያን ችግር ከገጠማት "ያለማቋረጥና በደውሎቹ መካከል ያለምንም እረፍት በተከታታይ ትደውላለች።" ይህ ጥሪ ቤተክርስቲያን የተለያየ ድንገተኛ አደጋ ሲገጥማት ነው።
ቤተ ክርስቲያን የተለያዩ የደውል አደዋወል አላት ነገር ግን በአደጋ ጊዜ ሲደወል ከሌሎቹ የሚለየው ደውሉን ቶሎ ቶሎ በፍጥነት ሲደወል ቤተ ክርስቲያን ላይ ችግር አለ ድረሱልን ማለት ነው
ሼር አድርጉ ለጎደኞቻችሁ በቁምነገር መሃል አውሩት።🙏

🕊 ♡ 🕊 ㅤ ❍ㅤ YAHWEH NSi ♡ ㅤ 🕊 ❍ㅤ 🕊
📡 "ያህዌህ ንሲ" የሚለው ቃል የዕብራይስጥ ቃል ሆኖ ትርጉሙ "እግዚአብሔር አላማዬ ነው" ማለት ነው !! እግዚአብሔር ዓላማህን በማድርግ የእግዚአብሄርን ቃል ፣መንፈሳዊ ትምህርት ፣ የቤተክርስትያን ታሪክ ትውፊት እና ሥርዓት ለምእመናን ማድረስ መባረክ ነው።
↪ እንዲሁም እግዚአብሄር ዓላማችሁ አድርጋችሁ መንፈሳዊ ትምህርት ለምታስትላልፉ ሁላችሁ መምህራን፣ምእመናን በየቻናሎቻችሁ የተለያዩ አገልግሎቶችን የምታቀርቡ ሰዎች በሙሉ በመጀመርያ ምስጋና ይገባችኋል።
↪ ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን እንዲዳረሱ ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ። 500 members ካለው 5ሺ members ያሉ በጣም ብዙ ናቸው ። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ #ከ5ሺ እስከ 50ሺ members የያዙ እና ከዛ በላይ አባሎች የያዙ ቻናሎችን እያሳደግን እንገኛለን እና ያለን ቦታ የተወሰነ ሰለሆነ ሁላችሁም የቻናል ባሌቤቶች (Owners ) በተሎ እንድትመዘገቡ በትሕትና እናሳውቃለን ።
↪ በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ያስመዝግቡ
= @YEmeAmlak_DnglMaryam_Ljoch_Bot
= ♡@Azaheill♡
☎ Tel :- +251943686155 📞 ያገኙናል !!
⏸⏯ የፕሮሞሽኑ ሰዓት የተመለከተ ⏸⏯
❇ የሳምንት ፕሮግራም
➱ ማክሰኞ
➱ ሀሙስ
➱ ቅዳሜ
➱ እሁድ
🔘 ሰአት ፦ ከምሽቱ 12:00 - ጧት 2:00
🔘 Resend ፦ ከምሽቱ 2:00 ላይ ይደርጋል !!
➕የፕሮሞሽን ማስታወቅያዎች በሰዓቱ እንለቃለን እንዲሁም
በሰዓቱ እንሰርዛለን !!

✨ የማታ,,ኮከቦች
>> ይሄንን ያቃሉ ማታ ማታ የምናያቸው ኮከቦች የሚለቁት ብርሃን ምድር ላይ የሚደርሰው በሚሊየኖች ወይም ከሺዎች አመታት በዋላ ነው ።
ይሄም ማለተ አውን የምናየው የኮከቦች ብርሃን ምድር ላይ ደረሶ የምናየው ከቢልየን ወይም ከሚልየን አመታት በፊት የተላከ ነው በተቃራኒው ወደነዚህ ኮከቦች እኛ የብርሃን ጨረር ወይም እንደምሳሌ የእጅ ባትሪ ቢያበሩ ብርሃኑ የሚደርሰው ከሺህ ወይም ከሚልየን አመታቶች በዋላ ነው።
አስተውሉ ይሄ ሁሉ የሚሆነው ብርሀን በ Second 350,000kM እየተጓዘ ነው ይሄ ሁሉ አመተ የሚፈጅበተ።

ክፍል ፩፦
ባሕረ ሐሳብ ማለት ምን ማለት ነው?
✍🏾.ባሕረ ሐሳብ ማለት ቁጥር ያለው ዘመን ማለት ነው።
✍🏾.ባሕርን ዘመን ብሎ የተረጎመው ዕዝራ ሱቱኤል ነው።"እስመ በመዳልው ተደልወ ዓለም ወበመስፈርት ሰፈሮ ለባሕር ወኢያረምምሂ ወኢይነቅህ እስከ ይትፌፀም መስፈርት ዘተውህበ ሎቱ" (ይህ ዓለም በሚዛን ተመዝኗልና ባሕርንም በላዳን ሰፍሮታል የተሰጠው ዘመኑ እስኪፈፀም ድረስ ዝም ይላል አያልፍም ብሏል። ሱቱኤል ዕዝራ (፪፥፴፯)
✍🏾.የኢትዮጵያ መተርጉማንም "ወበመስፈርት ሰፈሮ ለባሕር" የሚለውን ንባብ ዘመኑንም ከ8ሺ ወስኖታልና ብለው ይተረጉሙታል።
✍🏾.ሐሳብንም ቁጥር ብሎ የተረጎመው ነብዩ ዳዊት ነው።"ብፁዓን እለ ተኀድገ ሎሙ ኃጢያቶሙ ወእለ ኢሐሰብ ሎሙ ኩሎ ጌጋዮሙ"(ኃጢአታቸው በንስሐ የተሰረየላቸው በደላቸውም በንስሐ ያልተቆጠረባቸው ሰዎች ንዑዳን ክቡራን ናቸው።መዝ ፴፩፥፩
✍🏾.የኢትዮጵያ ሊቃውንት ባሕረ ሐሳብን #መርሐ ዕውር #ሐሳበ አቡሻኽር እና #ሐሰበ ፈለክ ብለው በ፫ ይከፍሉታል። አንዳንዶች ደግሞ ሐሳበ ፈለክን በአቡሻኽር አስገብተው በ፪ ይከፍሉታል።
፩.መርሐ ዕውር፦ማለት አላዋቂዎችን ከድንቁርና ጨለማ ሰፊ ወደ ሆነው የዕውቀት ብርሃን መርቶ የሚያደርስ ማለት ነው።በውስጡም የበዓላትን እና አፅዋማትን አወጣጥ እንዲሁም ኢየዓርግና እና ኢይወርድን ማለትም ገደባቸው ከዚህ አይወጡም አይወርዱም በዚህ ይመላለሳሉ የሚለውን ያስረዳል።
፪.ሐሳበ አቡሻኽር፦አቡሻኽር የሚለውን መጠሪያ የተወሰደው ከእራሱ ከፀሐፊው ሲሆን ሙሉ ስሙ አቡሻኽር ኢብን ቡትሩስ ራሒብ ሲሆን የኖረው በአሁኗ ግብፅ በድሮው ምስር በምትባል ሀገር በ፲፫ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደነበር ይነገራል።በውስጡም ረቂቅ የሆነውን የፀሐይን፣የጨረቃን እና የከዋክብትን እንዲሁም የስነ-ፈለክ ነገርን በጠቅላላ ይናገራል።ሁልሽም #Astrophysics,#Astrology እያልክ ከምትሮጥ ሰከን ብለህ ሀገር በቀል የሆነችውን እውቀት ከአባቶችህ ስር ቁጭ ብለህ ብትማር፣ብትቀስም፣ብትጦምር ዛሬ የት በደረስክ ነበር ለነገሩ አንተ ምን ታረግ #English ስትናገር እና ማንም የነጭ ውርጋጥ የፈለሰፈውን ትምህርት ተንትነህ ስትናገር ሲጨበጨብልህ እና ጎበዝ ጀግና ስትባል አድገህ በተቃራኒው #ዓውደ ነገሥትን ስትቆጥር ተንቋይ #ዕፀ ደብዳቤን ተጠቅመህ ሰው ስትፈውስ ስር ማሽ እየተባለ በማህበረሰቡ ያለ ግብር ስም ሲሰጡህ ይቆዩና #Astrology,#numerology,#Biomedical ብለው ቁንፅል የሆነ እውቀትን ገልብጠው ሲሰጡህ ክብረት ይስጥልኝ ብለህ ትቀበላለህ። በሌላኛው ጎን ግዕዝን አቀላጥፈው ሲናገሩ ኧረወዲያ እየተባሉ እና ቦታ ሳይሰጣቸው የቀሩትን ሊቃውንት ስትመለከት በአንድ በኩል ደግሞ ነጮች ግዕዝን በphd ደረጃ ሲማሩትት ስትመለከት ጀግኖች እያሉ ሲያሞግሱ ስታይ አንተ ምን ታረግ #ሀይማኖትህን፣#ባህልህን፣#ቱፊትህን፣#ወግህን፣#የአኗኗር ስርዓትህን እንዲሁም #ፈሪሀ እግዚአብሔርን የሚያስረሳውን ትምህርት ትከተል ጀመር።እስኪ ሌላው ይቅርና ገና በለጋ እድሜያቸው የ፬ኛ እና ፭ኛ ክፍል ተማሪን ስለ ግብረ ስጋ ግንኙነት ያስተምሩታል ከዛ ምን ያደርጋሉ መተፋፈር የሚባለው ነገር እንዲቀር በቡድን ተወያዩ ይላሉ በኋላ ይሄ ሀገር ይረከባል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት ትውልድ ምን አይነት ስነ-ምግባር እንደሚኖረው መገመት አያዳግትም።ኧረ ተው ጎበዝ የምንሄድበትን ጎዳና እናስተውል እስከ ዛሬ በዚህ ጎዳና ሂደን ምንም ለውጥ አላመጣንም ስለዚህ ይሄ መንገድ አዋጭ አለመሆኑን በሚገባ አውቀናል እኔ ግን አንዳንዴ በዚህ ትውልድ ላይ #ተደግሞበት ወይም #መፍዝዝ ተደርጎበት ይሆን እንዴ ብዬ አስባለው ምንም ያህል ያሰብኩት የጅል ሀሳብ ቢሆንም።እና ምን እላችኋለው ወገኖቼ ወዳጆቼ በእነሱ መንገድ እስካሁን ከበቂ በላይ ተጉዘናል አሁን የእነሱን ጎዳና ትተን በራሳችን ጎዳና የምንጓዝበት ጊዜ የደረሰ ይመስለኛል።ከርዕስ ስለወጣው ይቅር በሉኝ ነገሩን በራሴ መያዝ ስለመረረኝ ነው ሀገር ገደል ስትገባ ማየት ስለመረረኝ እና ስለአንገሸገሸኝ ነው ያው የሀገር ስሜት እንደ በፊት አባቶች ስሜት አለኝ ለማለት ባልደፍርም የስንዴ ቅንጣት ታህል አለኝ ብዬ አስባለው።ነገሩ "በእጅ የያዙት ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል ይላሉ አበው" የእኛም ሀገር በቀል እውቀት እንደ መዳብ ነው የሆነብን ቆይ ቆይ አኔ የምለው በአንድ ዕለት ተዋነይ 700 መወድስ ዘረፈ ብለህ ስትነግረው ምንም ደንታ የማይሰጠው ሶቅራጠስ እንዲህ አለ ብለህ የእሱን አንድ አባባል ስትነግረው ቆሞ የሚያጨበጭብን ትውልድ እንዴት አድርገህ ትለውጠዋለህ እንዴትስ ብለህ በነጮች የቀኝ አዙር ቀጭ ግዛት የተገዛውን አመለካከቱን በምንስ መልኩ ትቀይረዋለህ እኔ እኮ አላወቅነውም እንጂ በነጮች ቀኝ ግዛት እየተገዛን ነው ምናልባት እያወቅንም ይሆናል ብቻ አንዳንዴ እስቃለው መልሼ ደግሞ አዝናለው ብቻ ተውት ሁሉም በጊዜው ይሆናል።ቅኔ ሲባል እንደ ተራ የሚቆጠርበት philosophy(ፍልስፍና) ሲባል እንደ ትልቅ ነገር የሚቆጠርበት ነገር አይገባኝም እኔ ልንገራችሁ ብታምኑም ባታምኑም የእኛው የእነ #ተዋነይ፣#ክፍለ ዮሐንስ፣#ዮሐንስ ገብላዊ ቅኔ ወይም በዘመኑ አማርኛ ፍልስፍና ከእነ #ዲዮጋን፣#ሶቅራጠስ፣#አርስቶትል በመቶ ሺህ እጅ ይረቃል፣ይደንቃል፣ይልቃልም።
✍🏾."የእራስን ጥሎ የሌሎችን አንጠልጥሎ "የሚለው የአበው ብሂል በእኛ ላይ መሆን የለበትም ባይ ነኝ ለነገሩ ብሂሉ እርግጥ ሆኗል ለማንኛውም ወደ ዕለቱ መርሐ ግብር ልመለስ።
፫.ሐሳበ ፈለክ፦የብርሃናቱን ፀሐይ፣ጨረቃ፣ከዋክብት መመላለሻን ማለትም ሚጠተ ብርሃናትን እንዲሁም የነፋሳትን ነገር በዝርዝር ይናገራል።
✍🏾.በአጠቃላይ እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን የያዘ መጽሐፍ አንድ አድርገው ባሕረ ሐሳብ ብለው ሊቃውንት ሰይመውታል።አንዳንድ ሊቃውንት ከትምህርቱ ስፋት እና ጥልቀት የተነሳ "ባሕረ ሐሳብን ተምሬ እጨርሳለው ማለት ውቅያኖስን በእንቁላል ቅርፊት እየጨለፍኩ እጨርሰዋለው እንደማለት ነው"ብለው ይመስሉታል።
💪🏾.ክብር ይሄን እውቀት ጠብቀው ለአሁኑ ዘመን ላስተላለፉ አባቶች።

ክፍል፪፦
ድሜጥሮስ
✍🏾.ባሕረ ሐሳብ የሚለውን ስያሜ ትርጉም ከመጀመሪያው የፃፍኩት ሲሆን ይሄን ባሕረ ሐሳብ የሚባለውን ት/ት ያልተማረ ካህን ውሃ በሌለው ወንዝ እና ሰው በሌለው ሀገር ይመሰላል(ካህን ዘኢተምህረ ባሕረ ሐሳብ ይመስል ከመፈለግ ዘአልቦ ማይ ወከመ ሀገር ዘአልቦ ሰብእ እንዳለ መርሐ ዕውር)።
✍🏾 .መርሐ ዕውር ማለት ባሕረ ሐሳብ ያልተማሩትን ወደ ት/ቱ የሚመራ ማለት ነው።
✍🏾.ነጋዴዎች አልፈው ሲሄዱ አሽዋው ተዘርግቶ ቅጠሉ ለምልሞ ከርቀት ይታያቸዋል እነርሱም ወደ ወንዙ ሄደን ጠል(ጠል ማለት ቀዝቀዝ ያለ ቦታ ማለት ነው) ነስተን ጥሬ ቆርጥመን እንምጣ ብለው በሄዱ ጊዜ ደረቅ ነውና አፍረው አዝነው ተመለሱ።ባሕረ ሐሳብን ያልተማረ ካህን ደግሞ አምሞ ጠምጥሞ ልብሱን አጥርቶ በሩቅ ይታያቸዋል።ምዕመኑም ከአባትችን ሂደን አፅዋማትን እና በአላትን ጠይቀን እንረዳ ብለው ሂደው በጠየቁ ጊዜ ያልተማረ ነውና ምላሽ ያጣል እነርሱም አፍረው አዝነው ይመለሳሉ።ለመግቢያ ይሄን ካልን ወደ ድሜጥሮስ እንመለስ።
✍🏾.ድሜጥሮስ 11ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ሲሆን ባሕረ ሐሳብን የደረሰው ጳጳስ በሆነ በ47 አመት ነው።
📖.ድሜጥርስ ማለት መስታውት ማለት ነው?
📚.አንድም መስታውት የራስ ጉድፍ የጥርስ እድፍ እንደሚያሳይ ሁሉ ድሜጥሮስም የተሰወሩ አፅዋማትን የተበተኑ በአላት አውጥቶ ያሳያልና።
📚.አንድም መነጸር ይለዋል ይህ መነፀር የራቀውን አቅርቦ የረቀቀውን አጉልቶ እንደሚያሳይ ሁሉ ድሜጥሮስም የራቁትን የተበተኑትን አፅዋማትና በዓላት አውጥቶ ያሳያልና መነፀር አለው።
✍🏾.ባሕረ ሐሳብን ለምን ደረሰው?
📚.ባሕረ ሐሳብን ስለምን ደረሰው ቢሉ ዘመኑ ዘመነ አላዊ ስለነበር ወደ አርመን ሐገር ተሰዶ መሄድ ይመጣልና ያን ጊዜ አፅዋማትን አውጥቶ ለመፆም በዓላትን ለማክበር ሲል ጌታው ተምሮ ለሌላው እንዲያስተምር።
✍🏾.የድሜጥሮስ እና የልዕልተ ወይን ጋብቻ፦
✍🏾.አርማስቆስ እና ደማሲቆስ የሚባሉ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ።አርማስቆስ የድሜጥሮስ አባት ሲሆን ደማሲቆስ ደግሞ የልዕልተ ወይን አባት ናቸው።
📚.ደማሲቆስ ከሞተ በኋላ አርማስቆስ ሁለቱንም አጋባቸው ስለምን ቢሉ፦
📖. አንድም ህንፃ ነፍስ ከሚፈርስ ህንፃ ስጋ ይፍረስ፤ህንፃ ሀይማኖት ከሚፈርስ ህንፃ ህግ ይፍረስ፤ህንፃ ተዋሕዶ ከሚፈርስ ህንፃ ተዛምዶ ይፍረስ።(ይህን ያለበት ምክንያት ዕርስ በዕርስ ካላጋቧቸው ከአሕዛብ ጋር ይጋባሉ በዚህ ምክንያት ከላይ የተዘረዘሩት በሙሉ ይፈርሳሉ ማለት ነው)
📖.አንድም ወንድሙ ሲሞት ማለትም ዲማሲቆስ ልጅህን ከልጄ እንዳትለያት ብሎት ስለነበር ነው።
📚.ሁለቱም ከተጋቡ በኋላ በንፅህና ማለትም ከግብረ ስጋ ግንኙነት ውጭ ሆነው በአንድ አልጋ፣በአንድ ምንጣፍ 48(፵፰) ዘመን አብረው ኖሩ።ይህም ይታወቅ ዘንድ ቅዱስ ሚካኤል ግራ ክንፋን ለእሱ ቀኝ ክንፋን ለእሷ አልብሷቸው ሲነጋ በርግብ አምሳል ጠዋት በመስኮቱ ወጦ ይሄዳል።
✍🏾.ድሜጥሮስ ተክል አፅድቆ ይኖር ነበርና ከዕለታት አንድ ቀን ከአትክልቱ ገብቶ የወደቀውን ለማንሳት፣የጎበጠውን ለማቃናት ሲመለከት ሳለ አብቦ ያፈራ ባለ 3(፫) የወይን ዘለላ አገኘ ይህንስ አልቀምሰውም ብሎ ለልዕልተ ወይን ሰጣት እርሷም ይሄንስ ወስደህ አስባርከው አለችው።

ክፍል ፫ ፦
የድሜጥሮስ ጳጳስነት
✍🏾.አስረኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ የሆነው ዮልዮስ ሕዝቡን ሰብስቦ እኔ አርጅቻለው ከእኔ ቀጥሎ የሚሾመውን ምረጡ አለ።እነርሱም አንተ ምረጥልን እኛ ምን እናውቃለን አሉት እርሱም እንግዲያውስ ሁላችንም ሱባዔ እንግባ አለ።ጳጳሱ ሱባዔ እንደገባ መልአኩ ተገልጾለት 3(፫) የወይን ዘለላ ይዞ የሚመጣ አለ እሱን ሹመው ብሎ በራዕይ ነገረው።
✍🏾.ድሜጥሮስም የወይን ዘለላውን ለማስባረክ ይዞ በሚመጣ ሰዓት ጳጳሱ ከባረከለት በኋላ ለህዝቡ ይሄን ነው የምትሾሙት ብሎ ሳይውል ሳያድር አረፈ።"ወንበር ያለ ሹም ሀገር ያለ ዳኛ ከብት ያለ እረኛ አይውልም አያድርምና"ህዝቡም ዮልዮስን ቀብረው ከተመለሱ በኋላ ህዝቡ በግድ ሊቀ ጳጳስ አድርገው ሾሙት።
✍🏾.ድሜጥሮስ ከተሾመ በኋላ ህዝቡን አንተ ሐጢያተኛ ነህ አንተ ሐጢአተኛ አይደለህም ፣አንተ መቁረብ ትችላለህ አንተ አትችልም እያለ ሲገፅሳቸው እርሱን ማማት ጀመሩ።መልአኩም ወርዶ እያሙህ ከሚጎዱ ክብርህን ግለፅላቸው አለው።ለህዝቡም አዋጅ አስነግሮ ሁሉም ሰው አንድ አንድ እንጨት ይዘው እንዲመጡ አዘዘ ካመጡ በኋላ ደመራ ደምሩ አላቸው ከዛም ለኮሱት ከተለኮሰ በኋላ ድሜጥሮስ እስከ ልብሰ ተክህኖው 3 ጊዜ ገብቶ ወጣ ይሄም የ3(፫) ቱ አቅማራት ምሳሌ ነው።እነርሱም፦
~.ንዑስ ቀመር
~.ማዕከላዊ ቀመር
~.አብይ ቀመር ናቸው።
📚.መልአኩም ለድሜጥሮስ ከቀኑ 7(፯)
ሱባዔ በ7(፯),ከሌሊቱ ደግሞ 23(፳፫) ሱባዔ በ7(፯) ግባ ተባለ።
~.7*7=49 ይሆናል በአንድ ሰላሳ ስንገድፈው 19(፲፱) ይሆናል ይሄም የጥንተ መጥቅዕ ምሳሌ አመጣጥ ነው።
~.23*7=121 ይሆናል ይሄም በ5(፭) 30(፴) መግደፍ ነው ከዚህም 11(፲፩) ይቀራል ይሄም የጥንተ አበቅቴ ምሳሌ ይሆናል።
📚.ድሜጥሮስ ሱባዔ የጀመረው ቅዳሜ ነበርና ቅዳሜ 8(፰)የወይን ዘለላ መልአኩ አምጦቶ ሰጠው ይህም የቅዳሜ ተውሳክ(ጭማሪይ) ይሁንህ ሲለው ነው እንደዚህ እያሉ እስከ አርብ 2 ድረስ እየቀነሱ መሄድ ነው።
💪🏾.ክብር ይሄን እውቀት ጠብቀው ላቆዩልን አባቶቻችን ይሁን።

ክፍል ፬ ፦
የዕለታት ተውሳክ
• ቅዳሜ=8
• እሁድ=7
• ሰኞ=6
• ማግሰኞ=5
• ረቡዕ=4
• ሐሙስ=3
• ዓርብ=2
የአፅዋማት እና በዓላት ተውሳክ
~ጾመ ነነዌ ተውሳክ የለውም በመባጅ ሐመር ይወጣል።
~ዓብይ ጾም ተውሳኩ 14 ነው።
~ደብረ ዘይት፡ ተውሳኩ 11 ነው፡፡
~ሆሣዕና ተውሳኩ 2 ነው፡፡
~ስቅለት ተውሳኩ 7 ነው።
~ትንሣኤ ተውሳኩ 9 ነው።
~ርክበ ካህናት ተውሳኩ 3 ነው።
~ዕርገት ተውሳኩ 18 ነው።
~ጰራቅሊጦስ ተውሳኩ 28 ነው።
~ፆመ ሐዋርያት ተውሳኩ 29 ነው።
~ፆመ ድኅነት ተውሳኩ 1 ነው።
የዕለታት ተውሳክ
• ቅዳሜ=8
• እሁድ=7
• ሰኞ=6
• ማግሰኞ=5
• ረቡዕ=4
• ሐሙስ=3
• ዓርብ=2
የአፅዋማት እና በዓላት ተውሳክ
~ጾመ ነነዌ ተውሳክ የለውም በመባጅ ሐመር ይወጣል።
~ዓብይ ጾም ተውሳኩ 14 ነው።
~ደብረ ዘይት፡ ተውሳኩ 11 ነው፡፡
~ሆሣዕና ተውሳኩ 2 ነው፡፡
~ስቅለት ተውሳኩ 7 ነው።
~ትንሣኤ ተውሳኩ 9 ነው።
~ርክበ ካህናት ተውሳኩ 3 ነው።
~ዕርገት ተውሳኩ 18 ነው።
~ጰራቅሊጦስ ተውሳኩ 28 ነው።
~ፆመ ሐዋርያት ተውሳኩ 29 ነው።
~ፆመ ድኅነት ተውሳኩ 1 ነው።
ክፍል ፭፦
📜ባሕረ ሐሳብ📜
✍የባሕረ ሐሳብን ፍቺ ከላይ የተመለከትን ሲሆን ዛሬ የመባጅ ሐመር፣የወንበር፣የጥንተ ዮን እንዲሁም አበቅቴና መጥቅዕ አወጣጥ የምንመለከት ይሆናል።
✍.ዓመተ ፍዳ ማለት ከክርቶስ ልደት በፊት ያለው ሲሆን ይኸውም 5500 ዘመን ነው።
✍ .ዓመተ ምህረት ማለት ከክርስቶስ ወዲህ ያለው ዘመን ነው ይኸውም 2014 ዘመን ነው።
📚.ዓመተ ዓለም = ዓመተ ምህረት + ዓመተ ኩነኔ = 2014+ 5500 =7514
📖.ወንጌላዊው ማን እንደሆነ ለማወቅ፦
~7514 ÷ 4 = 1878 ደርሶ ቀሪ 2 ይሆናል።
~1878 ፦ መጠነ ራብዒት ተብላ ትጠራለች፡፡
~ቀሪው 1 ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ
~ቀሪው 2 ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ
~ቀሪው 3 ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ
~ቀሪው 0 ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ይሆናል።
✍.ስለዚህ ቀሪው 2 ስለሆነ የዘንድሮው ወንጌላዊ ማርቆስ ሲሆን ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ ይባላል።
ጥንተ ዮን(ኦን)
~ጥንተ ዮን ማለት መስከረም አንድ የሚውልበት ቀን ማለት ነው፡፡
ጥንተ ኦን= ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት÷7(ሰባቱ ዕለታት)
= 7514 + 1878 =9392
= 9392 ÷ 7 = 1341 ቀሪ 5
✍.ከዚህ ቀጥሎ ከቀሪው 5 ላይ 1 እንቀንሳለን ለአለፈው መሸኛ ለሚመጣው መቀበያ ተብሎ 1 ይታተታል(ይቀነሳል) ስለዚህ ከ5-1=4 ይሆናል።
✍.ጥንተ ኦን ከረቡዕ ይጀምራል፦
ቀሪው 1 ከሆነ ረቡዕ
ቀሪው 2 ከሆነ ሐሙስ
ቀሪው 3 ከሆነ ዓርብ
ቀሪው 4 ከሆነ ቅዳሜ
ቀሪው 5 ከሆነ እሁድ
ቀሪው 6 ከሆነ ሰኞ
ቀሪው 7 ከሆነ ማግሰኞ ይሆናል ማለት ነው። በመሆኑም የዘንድሮ 4 ስለሆነ ጥንተ ዮን(የመስከረም መባቻ)ቅዳሜ ይሆናል።
ወንበር
📚.ወንበርን ለማግኘት የአብይ ቀመር የጊዜው መደቡን በእድያው አባዝተን ከዓመተ ዓለሙ ላይ መቀነስ ከዛ በ19 መግደፍ ማለትም፦
~14*532=7448
~7514-7448=66
~65፥19=3 ቀሪ 9
ከቀሪው ላይ ላለፈው መሸኛ ለሚመጣው መቀበያ አንድ እናትታለን ከዛ ወንበርን እናገኛለን።
ወንበር =9 - 1= 8 ይሆናል።
አበቅቴ
📚.አበቅቴ ፦ጥንተ አበቅቴን በወንበር አባዝተን በ30 ገድፈን እናገኛለን።
አበቅቴ = ጥንተ አበቅቴ*ወንበር
11*8=88
88፥30= 2 ደርሶ ቀሪው 28 ሲሆን የዘንድሮ አበቅቴ 28 ይሆናል።
አበቅቴን ለማግኘት ሌላው አማራጭ አበቅቴ እና መጥቅዕ ድምራቸው ከ30 አይበልጡም አያንሱም ስለዚህ አንዱን ካገኘን ከ30 ላይ ቀንሰን ማግኘት ይቻላል። ይህም ማለት የ2013 ዓ.ም አበቅቴ 17 ነበር፤ ስለዚህ 30-17=13 ይሆናል ስለዚህ የ2013 መጥቅዕ 13 ነበር ማለት ነው።
መጥቅዕ
📚.መጥቅዕ፦ ጥንተ መጥቅዕን በወንበር አባዝተን ለ30 በመግደፍ(በማካፈል) እናገኛለን።
መጥቅዕ =ጥንተ መጥቅዕ*ወንበር
19×8 = 152
152 ÷ 30= 5 ቀሪው 2 ስለሆነ መጥቅዕ ዘንድሮ 2 ይሆናል።
መጥቅዕን ለማግኘት ሌላው አማራጭ መጥቅዕን ወይ አበቅቴ ካገኘን ከ30 መቀነስ ነው።
“አበቅቴ ወመጥቅ ክሌሆሙ ኢይበዝሁ እም30 ወኢይኅዱ እም 30 ወትረ ይከዉኑ 30 "አበቅቴ ቢበዛ መጥቅ ቢያንስ መጥቅ ቢበዛ አበቅቴ ቢያንስ ከ30 አይበዙም አያንሱም” ይህም ማለት በሌላ አገላለጽ መጥቅዕና አብቅቴ ተደምረዉ ዉጤቱ ከ30 መብለጥና ማነስ የለበትም፤ ሁሌ 30 ይሆናል፡፡ የዘንድሮዉ ~የ2014 ዓ.ም = 28+2= 30
✍.መጥቅዕ ከ14 በላይ ከሆነ በታህታይ ቀመር በመስከረም ይውላል።
✍.መጥቅዕ ከ14 በታች ከሆነ በላዕላይ ቀመር በጥቅምት ይዉላል።
~መጥቅዕ በመስከረም ቢዉል ጾመ ነነዌ በጥር፣ መጥቅዕ በጥቅምት ቢዉል ጾመ ነነዌ በየካቲት ይብታል።
ስለዚህ በዚህ ዓመት መጥቅዕ 2 ሲሆን ከ14 ያንሳል፤ ስለዚህም መጥቅዕ በጥቅምት ይዉላል።
ስለዚህ የ2014 መጥቅዕ ጥቅምት 2 ነው ሲሆን ዕለተ መጥቅዕ ማግሰኞ ይሆናል፡፡
መባጅ ሐመር
📚.የዕለት ተውሳክን ከላይ ስለተመለከትን ቀጥታ ወደ አወጣጡ እንሄዳለን።
📚.መባጃ ሐመርን ለማግኘት መጥቅዕንና በዓለ መጥቅዕ የዋለበትን ዕለት ተውሳክ መደመር ነው።በዓለ መጥቅዕ የዋለው ጥቅምት ላይ ሆኖ ማግሰኞ ስለሆነ የማግሰኞ ተውሳክ 5 ነው።መባጃ ሐመር= 2+5=7
መባጃ ሐመር ከ30 ስለሚያንስ ራሱ 7 ይያዝና መጥቅዕ በጥቅምት ስለዋለ ጾመ ነነዌ በየካቲት 7 በዕለተ ሰኞ ይውላል ማለት ነው።
✝ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።✝

በእናት ኢትዮጵያ በመሬት ውስጥ
የተቀበሩ የፒራሚድና ሌሎች
ከተሞች ማን እንደ ሠራቸው፣
📚.እንዴት ተሰሩ በማን እጅ
🌍.በመሬት ውስጥ ስለ ተቀበሩ ከተሞችና ፒራሚዶች ማን እንደ ሠራቸው ከመግለጼ በፊት በጥንት ስሙ ምሥር ዛሬ ደግሞ ግብጽ ተብሎ በሚጠራው ሀገር ስለሚገኙ ሐውልቶችና ፒራሚዶች እንዲሁም ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚገኙ ሐውልቶችና በጣም አስደናቂ የሆኑ የቤተ መቅደስ ሕንጻዎችን በኣጭሩ መጥቀስና መግለጽ አስፈላጊ ነው ።
📚.ይኸውም ብዙ የዓለም የታሪክ ጸሐፊዎችና የከርሠ ምድር ተመራማሪዎች የጥንት ቅርሳቅርስ አዋቂዎች ማለትም አርክዮሎጂስቶች ስለ ጥንት የኢትዮጵያ ቤተ መቅደሶችና ሐውልቶች እንዲሁም ደግሞ ስለ ጥንት የግብጽ ሐውልቶችና ፒራሚዶች ብዙ መጻሕፍት ጽፈዋል ብዙም መላምት የሆኑ ማስረጃዎችን ኣቅርበዋል ።
📔.ቢሆንም ከእየሀገሩ ተወላጆች የሆኑ ሁሉ የተሳሳተ የቃል መረጃ
በመቀበል ራሳቸው ተመራምረው እንደ አገኙት በማስመሰል ያቀረቡት ጽሑፍ ሁሉ ፍጹም የሆነ ሐሰት ሲሆን በተለይ ደግሞ በእስላይድና በቪዲዮ የሰጡት ገለጻ በሙሉ ከእውነት የራቀ መሆኑን በአዋቂዎች ዘንድ የታወቀ ከመሆኑም በላይ ከግብጽ በፊት እነርሱ የማያውቋቸው ፱ የፒራሚድ ከተሞች ከመኖራቶውም በላይ እንዲሁም ደግሞ የአክሱም የላሊበላ ዓይነት ፲፯ከተሞች ይገኛሉ ። እነዚህም ሲከፈሉ የአክሱም ዓይነት ፯ ብቻ ሲሆኑ የላሊበላ ደሞ ፲ ናቸው ። ስለዚህ ማን እንደ ሥራቸውና በማን ኃይል እንደ ታነጹ አብዛኛው ምስጢር እንደተጠበቀ ሆኖ ለመግቢያ ያህል የተወሰነ እንበል:-
፩..በራሱ በራፋኤል እጅ የተሠሩ
📘📖.በ፱ሺ፮፻፴ ቅ.ል.ክ (B.C)
በመሬት ውስጥ የተቀበሩ ፒራሚዶችንና በጣም አስደናቂ የሆኑ ከተሞች የተሠሩት በራፋኤል ትእዛዝ መሆኑ ቢታወቅም በተለይ ደግሞ በጥንት ዘመን የኢትዮጵያ ወደብ ወደ ነበረው በአዶሊስ በቀይ ባሕር አካባቢ የተሠሩ የፒራሚድ ከተሞች የኃይሉ ማረፊያ እንዲሆኑት በራሱ በራፋኤል እጅ ነው።
📚.የፒራሚዶቹ ሥራ ባለ ፫ት መአዝን ወይም ትሪአንግል ሲሆን ቁጥራቸውም ፫ት ናቸው የተሠሩትም መበላለጥ ሣይኖርባቸው እኩል ሆነው እንደ ፫ቱ ሥላሴዎች ሥዕል ሲሆኑ በ፩፻ሺ ሜትር ርቀት በአስደናቂ ሁኔታ ቁመው ይታያሉ ሥራቸውም ዓይነቱ የማይታወቅ ድንጋይ የሚመስል ሆኖ ቅጥልጥል የሌለበት አንድ ወጥ ነው ። ፫ቱም ፒራሚዶች በጣም የሚያምር የራሳቸው የሆነ ፫ት ዓይነት ቀለም አላቸው ። ይኸውም ከአዶሊስ ፊቱን ወደ ምሥራቅ አዙሮ በተለየ ዓይን በርቀት ሲመለከቷቸው ከመሓል ወደ ቀኝ ያለው ፒራሚድ ቀለሙ ፍጹም አረንጓደ ነው ። መሐለኛው ብጫ ቀለም ሲሆን በግራ በኩል ያለው ፒራሚድ ደግሞ ቀለሙ ፍጹም ቀይ ነው ። ማለትም እንደዛሬዋ የእናት ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለም ነው ቢሆንም የፒራሚዶቹ ውስጣዊ አካል ግን ይህንን ይመስላል ብሎ በፍጡር አንደበት ሊነገር አይችልም ይላል መጽሐፈ ምሥጢር ዘአዶናይ ራፋኤል።በሚቀጥለው ደግሞ በሱራፌል እና ኪሩቤል እንዲሁም በሳጥናኤል የተሰሩትን ፒራሚዶች የምንመለከት ይሆናል።
✝.ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።✝

የቀደምት ኢትዮጵያውያን ታሪክ እና ጥበብ:
ጥንት ጀምሮ የነበሩ የሰው ልጆች ዋና ጥያቄዎች ሆነው የቆዩ ቢሆንም አሁን ባለንበት ዘመንም በዘመናዊ የሳይንሳዊ ምርምር መስኮች ውስጥ ትልቅ ትኩረት ከሚሰጣቸው ዘርፎች ውስጥ የስነ-ህዋ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዋነኞቹ ናቸው:: ስለ እልፍ አዕላፍ ስነ-ከዋክብት: አፈጣጠራቸው: ከሰው ልጅ ውጭ ሌላ አለማት/ስልጣኔዎች ስለመኖራቸውና ስላለመኖራቸው ወዘተ… የተለያዩ ሳይንሳዊ መላ ምቶችን መሰረት አድርገው የመስኩ ሊቃውንት በትኩረት እያጠኑ ይገኛሉ:: ይህ አዲስ ቢመስለንምና አዲስ ነገር ፍለጋ ወደ እነዚህ ዘመናዊ የሳይንሳዊ ምርምር ውጤቶች ብናዘነብልም ግን የሃገራችን ጥንታዊ አባቶች ስለ ሰማያትና የተለያዩ አለማት በተሰጣቸው መገለጥ መሰረት ብዙ ጽፈውልን ያለፉ ነገሮች አሉ::
ከዘመናዊ ሳይንሱ ጎን ለጎን እኒህን ሃገር በቀል ምንጮችንም መልከት ማድረጉ አይከፋምና ስለ ሰባቱ ሰማያትና በውስጣቸው ስለሚገኙ አለማት ተጽፈው ከተገኙት ውስጥ የግዕዝና ቅኔ ሊቅ በሆኑት በመሪራስ አማን በላይ አማካኝነት ከግዕዝ ተተርጉሞ ከታተመ ‘መጽሐፍ ብሩክ..ዣንሸዋ ቀዳማዊ’ ከተሰኘው መጽሃፋቸው ውስጥ ከድረ-ገጽ ካገኘሁት ስለ ‘ሰባቱ ሰማያትና በውስጣቸው ስለሚገኙ መቶ አለማት’ ጥቂቱን እንካፈል::
የሰባቱ ሰማያት ስም ዓለሞቻቸው
1 ኢዮር (አየር) አሥራ ሁለት 12
2 ራማ ራማየ ሠላሳ ሦስት 33
3 ኢየሩይ (ሰማያዊት ኢየሩሳሌም/ጌልጌል) አንድ 1
4 ውዱድ ዲድያኤል ሃያ አንድ 21
5 አርያ – አርያም (መንበረ ጸባኦት ያለበት) 0 0
6 ኤረር ኢሮርያ ሠላሣ ሦስት 33
7 ሻዳይ ኤልሻዳይ (የሕይወት ምንጭ የአለበት፡ ስሙም ጔልጔል ይባላል) 0 0
1. ኢዮር ሰማይ
በ አዮር ሰማይ ክልል ውስጥ የአሉት አሥራ ሁለት ዓለሞች
ሐመልማል
ይህ የምድር ሠራዊት እንሆን ዘንድ እኛ የተፈጠርንበት ዓለም ነው። ጠባቂውና እንዲሰለጥንበት እግዚአብሔር የፈቀደለት አድማኤል ኪሩብ ይባላል። የአዳም ነገድ ሁሉ ከእርሱ አብራክ ወጥቶአል።
ረሐም
የዚህ ዓለም ጠባቂ መልአክ ሳውራኤል ኪሩብ ነው። በዓለም ረሐም ውስጥ የሚኖሩ ፍጥረቶች የበግና የፍየል መልክ የመሰለ ገፅ ሲኖራቸው የተሰጣቸው አእምሮ ከሰው ልጆች የላቀ የራቀውን የሚያውቁ የረቀቀውን የእግዚአብሔር ፍጥረትን ማየት የሚችሉ ናቸው። ከነርሱም ሌላ በረሐም ዓለም ውስጥ የተለያዩ ገጽ ያላቸው ቁጥራቸው ትእልፈተ-ትእልፊታት ፍጥረታቶች አሉ።
ገውዛ
የዚህ ዓለም ጠባቂው ኪሩብ መልአክ ሱርያኤል ነው። ገውዛውያን መልካቸው እንደ ሰው ልጆች መልክ ሁኖ ቀንድና ጅራት አላቸው። የጅንጆሮና የጉሬዛ መልክ የመሰለ የአላቸውም አሉ። ሁሉም ሁለት እጆችና ሁለለት እግር አሏቸው እንዲሁ ግዙፋንና እረቂቃን የሆኑ በራሪዎች ይኖሩባቸዋል። እርስ በእርሳቸው አይነካኩም የሳውራ አፈር ቅመው ይኖራሉ።
ሻርታ
የዚህ ዓለም ጠባቂው…

✍🏽.ውድ የዚኽ ቻናል ተከታዮች ከሁኔታዎች አለመመቻቸት ጋር ተያይዞ ለብዙ ጊዜያት ተራርቀን ቆይተናል ለዚኽም እጅግ በጣም ይቅርታ እያልኹ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በአዲስ መልክ ትምህርታችንን የምንጀምር ይሆናል እስከዚያ ቸር ሰንብቱልኝ።🙏🏾