የልማድ ምስጢር
ብዙ ሰዎች እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ፡- “በአንድ አሳብ፣ ንግግር ወይም ጽሑፍ እነሳሳና አንድ ነገር እጀምራለሁ፣ ነገር ግን ብዙ ሳይቆይ አቆመዋለሁ”፡፡ ይህ ችግር የብዙ ሰዎች ችግር ነው፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ በርካታ ማሰብና መለማመድ የሚገቡን እውነታዎች ቢኖሩም መሰረታዊውና ዋናው ግን በመነሳሳት፣ በዲሲፕሊን፣ በድግግሞሽና በልማድ መካከል ያለውን ግንኙነትና ልዩነት ማወቅ ነው፡
መነሳሳት የሚገናኘው አንድን ጤና ቢስ ነገር ለማቆም ወይም አንድን መልካም ነገር ለማድረግ ካለን የመፈለግ ስሜት ጋር ነው፡፡
ዲሲፕሊን የሚገናኘው መቆም የፈለግነውን ነገር ለማቆም ወይም ማድረግ የፈለግነውን ነገር ለማድረግ ራስን ከማስገደድ ጋር ነው፡፡
ድግግሞሽ የሚገናኘው ማቆም በፈለግነው ወይም መጀመር በፈለግነው ነገር አንጻር ራሳችንን እየተቆጣጠርንና ዲሲፕሊን እያደረግን አንድን ነገር ካለማቆም ከመደጋገም ጋር ነው፡፡
ልማድ የሚገናኘው ምንም ሳናስብበት፣ ሳንጨነቅና ሳንገደድ አንድን ነገር ለማቆም ወይም ለማድረግ ካለን ብቃት ጋር ነው፡፡ አንድ ልምምዳችን ወደ ልማድ ደረጃ መድረሱን የምናውቀው ያንን ነገር ለማድረግ ምንም አይነት የሚቀሰቅሰን (መነሳሳት) ወይም የሚጫነን (ዲሲፕሊን) ነገር ሳይኖር ማድረግ ስንጀምር ነው፡፡
ማንኛውም ሰው አንድን መልካም ልምምድ ወደ ልማድ ደረጃ እስከሚያደርሰው ድረስ ስኬታማነቱ አጠራጣሪ ነው፡፡ ስለዚህም፣ በመነሳሳት የተጀመረን ነገር ወደ ዲሲፕሊን ደረጃ ማድረስ አስፈላጊ ነው፡፡ ራሳችንን ወደመጫንና ዲሲፕሊን ያደረግንበትን ነገር ደግሞ ልማድ እስኪሆን ድረስ መደጋገም አስፈላጊ ነው፡፡
ሁል ጊዜ በመነሳሳት የሚሰራ ሰው መነሳሳቱ ሲያቆም እሱም ያቆማል፡፡ ሁል ጊዜ በዲሲፕሊን ላይ የሚደገፍ ሰው አንድ ቀን ራስን መጫንና ማስገደድ ይሰለቸውና ወይም ዲሲፕሊን የሚደርገው ሰው ወይም ሁኔታ ሲያቆም አንድ ቀን ያቆማል፡፡ ከዲሲፕሊን ደረጃ አልፎ አንድን ነገር እስኪለምደው ድረስ ድግግሞሽ ደረጃ የዘለቀ ሰው ወደ ልማድ ቀጠና ያልፋል፡፡ በልማድ የሚሰራ ሰው ራስ-ሰር (Automatic) ስልት ውስጥ ስለገባ ሁኔታው ዝም ወደሚፈስለት ደረጃ ያልፋል - ውጤቱም ልህቀትና ስኬት ይባላል፡፡
ለምሳሌ፣ ጠዋት ስትነሳ ማንም ሳያስታውስህና ማስታወሻ ደወል ሳታደርግ የምታደርጋቸውን ነገሮች አስባቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ልማድ ደረጃ የደረሱ ስለሆነ ለማስታወስ፣ ለመነሳሳትና ለማድረግ ምንም አድካሚ አይደሉም፡፡
በሕይወትህ ስኬታማ መሆን የምትፈልግበትን ነገር ለይና በዚያ ጉዳይ ላይ በመነሳሳት ጀምረህ፣ ወደ ራስን ማስገደደ (ዲሲፕሊን) በማለፍ ልማድ እስኪሆን ድረስ መደጋገም የግድ ነው፡፡ አንድን ነገር ጀምረህ የምታቆመው ነገሩ ልማድ እስኪሆን ስላልተነሳሰህና ራስህን ዲሲፕሊን ስላላደረከው ነው፡፡ በሕይወትህ ማቆም ያቀተህ አጉል ነገር ሁሉ አስበው፣ ልማድ እስኪሆን ስለደጋገምከው ነው፡፡ ጤና ቢስም ነገር እኮ ለዚያ ነገር ተነሳስተን ጀምረነውና ደጋግመነው ነው የልማድን አቅም ያገኘው፡፡
እንደገና ልድገመውና፣ ልማድን ለመጀመር መነሳሳት አስፈላጊ ነው፡፡ መነሳሳት ግን ራስን ዲሲፕሊን ማድረግ ደረጃ ካለደረሰና ወደ እንቅስቃሴ ካልተለወጠ የትም አይሄድም፡፡ ማንኛውም እንቅስቃሴ ደግሞ ወደ ድግግሞሽ ካልዘለቀ ልማድ አይሆንም፡፡
@kibirenaw

ችግራችሁ ለምን እንደማይፈታ!
በሕይወታችሁ ያለ ማንኛውም ችግር . . . የገንዘብ፣ የኑሮ፣ የስራ ማጣት፣ የእኔ ነው የምትሉት ሰው ማጣት . . . እና የመሳሰሉት ችግር በቀላሉ አልፈታ አለኝ የምትሉ ከሆነ፣ የሚከተሉት የችግር አፈታት እንቅፋቶች እስቲ ተመልከቷቸውና መንገድ ፈላልጉ፡፡
1. ለችግራችሁ ሰዎችን የመውቀስ ዝንባሌ
ለችግራችን ሰዎችን የመውቀስ ዝንባሌ ችግራችንን ለመፍታት ሃላፊነትን እንዳንወስድ የማድረግ ተጽእኖ አለው፡፡ ምንም እንኳን ሰዎች ለችግራችን በሃላፊነት ቢጠየቁም፣ ለመፍትሄው ግን ሃላፊዎቹ እኛው ነን፡፡
2. መፍትሄ ላይ ከማተኮ ይልቅ ችግሩ ላይ ማተኮር
ሁል ጊዜ ችግሩን የሚያሰላስልና የሚያወራ ሰው ተጨማሪ ችግርን ይወልዳል፡፡ ከዚያ ይልቅ ለችግሩ የመፍትሄ መንገድ ላይ የሚያተኩር ሰው ፈጣን ለውጥን ያመጣል፡፡
3. ችግሩ ሊያስከትል የሚችልውን የከፋ ሁኔታ ጥጉ ድረስ በማሰላሰል መፍራት
ፍርሃት ያስረናል፣ የማሰብ አቅማችንን ያዳክመዋል፣ ተስፋችንን ያጨልመዋል፣ የመፍትሄ ሃሳብ እንዳንፈጥር ያደነዝዘናል፡፡ ከዚህ ይልቅ የተመረጠው መንገድ ችግራችንን ለመጋፈጥ ቆፍጠን ማለት ነው፡፡
4. ከችግሩ ባሻገር የምናየው ጠንካራና ግልጽ የወደፊት ዓላማ አለመኖር
ወደፊት እስከምናይ ድረስ ከዛሬው ችግራችን ለመውጣት መራመድ አንችልም፡፡ ከችግራችን የጠነከረ ራእይና ከዛሬው ሁኔታችን የላቀ የወደፊት እስኪኖረን ድረስ ከችግራችን የመላቀቅ አቅም አይኖንም፡፡

ስላለፈው ውሳኔያችሁ በጸጸት አትኑሩ!
ከዚህ በፊት የወሰናችሁትን ውሳኔ አሁን ስትመለከቱት፣ “ምነው ባልወሰንኩት!” የሚያሰኝ ውሳኔ ከሆነ በዚህ ውሳኔ መሰረት እየተጸጸቱ መኖር ምንም አያዋጣም፡፡ በታትነን እንመልከተው፡፡
1. ምናልባት ትክክለኛውን ውሳኔ እያወቃችሁ የተሳሳተ ውሳኔ ወስናችሁ ሊሆን ይችላል፡፡
2. ምናልባት በወቅቱ የነበራችሁን እውቀት፣ መረጃም፣ የኑሮ አቅምም ሆነ የስሜት ሁኔታ አሰባስባችሁ በተቻለ መጠን ትክክለኛ ነው ብላችሁ ያመናችሁበትን ውሳኔ ወስናችሁ ሊሆን ይችላል፡፡
3. ምናልባት በሰው ተታላችሁ ወይም በሁኔታዎች ተወዛግባችሁ ምኑንም ሳታውቁት ወስናችሁ ሊሆን ይችላል፡፡
ዛሬ ለጸጸት የዳረጋችሁ ያለፈው ውሳኔ መንስኤ ከላይ ከተዘረዘሩት መካከልም ሆነ ከዚያ ውጪ፣ ዋናው ነገር ያለፈው ውሳኔ ዛሬ ያመጣባችሁን የጸጸት ስሜት አልፋችሁ ለመሄድ ያላችሁ ቁርጠኝነት ነው፡፡
መፍትሄዎች፡-
1. በትናንትናው ውሳኔ ዛሬ፣ በዛሬ ውሳኔ ደግሞ ነገ የመጸጸት ነገር እድሜ ልክ የሚከተል እውነታ መሆኑን አትዘንጉ፡፡
2. በውሳኔያችሁ ስትጸጸቱ፣ እንደገና ማስተካከል የምትችሉትን የውሳኔውን ውጤት ለማስካከል ሞክሩ፡፡
3. በውሳኔያችሁ ስትጸጸቱ፣ እንደገና ለማስተካከል የማትችሉትን የውሳኔ ውጤት ተቀበሉት፣ ትምህርታችሁን አግኙ፣ ብሰሉበት . . . እና ወደፊት ተራመዱ፡፡
4. በውሳኔው ምክንያት ስለመጣው ችግር ከማሰላሰል ላይ ሃሳባችሁን አንሱና ስለወደፊት ራእያችሁና እቅዶቻቸው ማሰብ ጀምሩ፡፡
ፈጣሪ ጤና ይስጣችሁ!

የሕይወት ጥያቄዎቻችን ጉዳይ
ብዙ ሰዎች፣ “በሕወቴ ያሉኝ መልስ የሚፈልጉ ጥያቄዎቼ ብዙ ናቸው” በማለት የሁኔታውን አሉታዊ ጎን ብቻ በማጉላት ይናገራሉ፡፡ ልክ ነው! ማንም ሰው ያልተመለሰ ጥያቄ እንዲኖረው አይፈልግም፡፡
አንድ ነገር ግን መዘንጋት የለብንም፣ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ሲኖሩን ብቻ ነው አእምሯችንን በትክክል የማሰራትና የፈጠራ ብቃታችንን የማሳደግ እድሉ ያለን፡፡
ከልጅነታችን በትምህርት ቤት ስናልፍ እኮ አስተማሪዎቻችን ካስተማሩን በኋላ ብዙ ጥያቄዎች እየጠየቁ ነው አእምሯችንን እንድናዳብር የረዱን፡፡ መልሱን ብቻ እያቀበሉ ቢሸኙን ኖሮ የማያስብና የማያድግ አእምሮ ይዘን እንቀር ነበር፡፡
ሕይወትም ብትሆን እኮ መልሱን ብቻ ብታቀብለን ኖሮ አእምሯችን የማያድግና ዝግ ይሆን ነበር፡፡ ሕይወት ግን በየእለቱ ከባባድ ጥያቄዎችን ስለምታቀብለን የነቃ፣ የሚያስብና መልስን ከዚህም ከዚያም ፈልጎ የሚያመጣ አእምሮን ወደማዳበር እናድጋለን፡፡
ሕይወታችሁ በጥያቄ መሞላቱ አያሳስባችሁ፡፡ ይልቁንስ ራሳችሁን ነቃ በማድረግ ሕይወት ለምታቀብላችሁ ጥያቄዎች ከዚህም ከዚያም መልስን ፈልጎ የሚያመጣ ማንነትን ገንቡ፡፡ መልስ የሌለው ጥያቄ የለምና!

ሰዎች የነዱት ሰው ጸጸት
“ሌሎች ሰዎች ከእኔ የሚጠብቁብኝን ሳይሆን እኔው ራሴ ያመንኩበትን ሕይወት የመኖር ድፍረት ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ!”
(“የሕይወት ጸጸቶች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)
ብሮኒ በመጀመሪያ የምትተርከው ግሬስ ስለምትባል በታላቅ ጸጸት ውስጥ ስላለች ሴት ነው፡፡ ግሬስ ከሃምሳ አመታት በላይ በጋብቻ ሕይወት አሳልፋለች፡፡ ግሬስ ከልቧ ከምትወዳቸው ልጆቿ ከምታገኘው ደስታ ባሻገር “የአስራዎቹ” አመታት ወጣት የልጅ ልጆች ማግኘቷ የማይጠገብ የደስታ ምንጭ ሆኖላታል፡፡ ሆኖም፣ ይህ ደስታዋ ሙሉ እንዳይሆን ያደረገባት አንድ ጥቁር ነጥብ ግን በሕይወቷ ነበር፡፡ ይህም ሁኔታ የባለቤቷ ጉዳይ ነበር፡፡
አምባ ገነንና ጨካኝ የሆነው ባለቤቷ ባሳለፉት አመታት ውስጥ ጋብቻን አስቸጋሪ ያደረገባት ሰው ነበር፡፡ ወደጋብቻ ከመጡበት እለት ጀምሮ የቅስም ሰባሪ ቃላትና የተለያዩ የክፉ ተግባሮች ሰለባ አድርጓታል፡፡ ይህንንም ሁኔታውን ለማስተካከል መውሰድ የነበረባት እርምጃዎች እንዳሉ ብታውቅም፣ አንዱንም ምርጫ ለመውሰድ ድፍረቱ ሳይኖራት ለአመታት ተቀጥቅጣ ኖራለች፡፡ የባለቤቷ አስቸጋሪነት እጅግ ከመክፋቱ የተነሳ ከጥቂት አመታት በፊት ከእርጅና የተነሳ በአረጋውያን መጦሪያ ማእከል በመግባቱ እርሷ ብቻ ሳትሆን ሁኔታውን የሚያወቁ ሰዎች ሁሉ ደስተኛ ነበሩ፡፡
ግሬስ በትዳር አመታቶቿ በሙሉ አንድ ቀን ከባሏ ክፉ ተጽእኖና ጨካኝ ሁኔታ ውጪ ሆና ደስተኛ ሕይወትን ለብቻዋ የምታጣጥምበትን ቀን እንደናፈቀች ኖራለች፡፡ አሁን በሰማኒያዎች አመታት ውስጥ ብትሆንም፣ ለእድሜዋ የሚመጥን መጠነኛ ጤንነትና የአካል ብቃት ነበራት፡፡ ወደማእከሉ ስትመጣ ወዲህ ወዲያ ለማለት የሚያበቃት አቅም ነበራት፡፡
እድሜዋን በሙሉ “በድብደባ” ያሳለፈው አእምሮዋ አሁን ለዚህ ሁኔታ ከዳረጋት ባለቤቷ በመለየቷ ምክንያት የእረፍትን ጭላንጭል ያየ ይመስላል፡፡ ለብዙ ዘመናት የጠበቀችውን ይህንን ለብቻ የመሆንና ካለምንም የውጪ ሰው ተጽእኖ የማሰብ “ነጻነት” ባገኘች በአጭር ጊዜ ውስጥ በድንገት በጽኑ መታመም ጀመረች፡፡ ሕመሙ ከተሰማት ከጥቂት ቀናት በኋላ ብዙም እድሜ እንደማይኖራት የሚጠቁም ምልክት ተገኘባት፡፡ ሁኔታውን እጅግ ልብን የሚሰብር ያደረገባት፣ የህመሙ መንስኤ ለብዙ አመታት ባለቤቷ በቤት ውስጥ ሲያጨስ ከነበረው የሲጃራ ጭስ እንደሆነም ማወቋ ነው፡፡ የበሽታው ደረጃ እጅግ ከመክፋቱ የተነሳ በአንድ ወር ውስጥ አቅሟን ሁሉ አጥታ የአልጋ ቁራኛ ሆነች፡፡
“ለምን ያንን ዘመን ሁሉ እኔ ያመንኩበትንና የፈለግሁትን ነገር አላደረኩም? ለምን እንደፈለገ እንዲገዛኝና እንዲያንገላታኝ ፈቀድኩለት?” የሚሉት ጥያቄዎች ካለማቋረጥ ከግሬስ አንደበት ሲወጣ ይደመጥ ነበር፡፡ ያመነችበትን ትክክለኛ ሕይወት ለመኖር ድፍረት ሳይኖራት ዘመኗ በማለፉ ምክንያት በራሷ ላይ እጅግ በጣም ትበሳጭ ነበር፡፡ ልጆቿም ቢሆኑ እንደፈለገ ባደረጋትና ባደረገባት ባሏ ምክንያት ስላሳለፈችው ከባድ ሕይወት በግልጽ ይመሰክሩ ነበር፡፡
“አንቺ ማድረግ የምትፈልጊውን ትክክለኛ ነገር ከማድረግ ማንም ሰው እንዲከለክልሽ አትፍቀጂለት” በማለት ለተንከባካቢዋ ለብሮኒ ደጋግማ ትነግራት ነበር፡፡ “እባክሽን ይህንን እኔ የሰራሁትን ስህተት እንዳትሰሪ ቃል ግቢልኝ” በማለት ታሳስባት ነበር፡፡ አንድ ቀን ግሬስ ይህንኑ ምክር ደግማ ከነገረቻት በኋላ፣ ብሮኒ በእሺታ ምክሯን ተቀብላ እንደምትተገብረው ቃል በመግባት፣ “ራስን የመቻልና ያመኑበትን ትክክለኛ ነገር የማድረግን ትምህርት ያስተማረችኝ እናት ስለነበረችኝ እድለኛ ነኝ” በማለት ለግሬስ ነገረቻት፡፡
“አሁን ያለሁበትን ሁኔታ ተመልከችው” አለች፣ ግሬስ በመቀጠል፡፡ “በመሞት ላይ ነኝ፡፡ በሞት አፋፍ! እንዴት ቢሆን ነው እነዚያን አመታት ሁሉ ነጻና ራሴን የቻልኩ ሆኜ ለመሆን ስጠብቅ ኖሬ፣ አሁን እዚያ የተመኘሁበት የሕይወት ምእራፍ ላይ የደረስኩ ሲመስለኝ ጊዜው ያለፈብኝ?” እነዚህን መራራ ቃላት የሰማችው ብሮኒ የግሬስ ሁኔታና ጸጸት እንድታስብ ያነሳሳትን እውነታ ማሰላሰል ጀመረች፡፡
የደረሰችበትም ድምዳሜ፣ “ማንኛውም ሰው የራሱን አመለካከት ማወቅ፣ ትክክለኛውን መንገድ መለየትና ያንንም ያመነበትን ትክክለኛ ጎዳና መከተል አለበት” የሚል ነበር፡፡
ግሬስ በውስጧ የምታምንበትንና የሚሰማትን ስሜት ሳይሆን የዚያን ተቃራኒ ገጽታን በውጪ እያንጸባረቀች ዘመኗን አባከነች፡፡ እድሜዋን በሙሉ እርሷ ያመነችበትንና ከነበረባት የጭካኔ ሰለባ የሚያወጣትን ሕይወት ሳይሆን ሌሎች ሰዎች ከእርሷ የሚጠብቁባትን አይነት ሕይወት ስትኖር ካሳለፈች በኋላ፣ አሁን በመጨረሻዎቹ አመቶቿ ምርጫው የእርሷ እንደነበርና፣ ፍርሃት ከትክክለኛው ምርጫ እንደገታት ተገነዘበች፡፡ ራሷን ይቅር የማለት አስፈላጊነት ቢነገራትም እንኳን አሁን ሌላ ምርጫ ያለውን ሕይወት ለመኖር ጊዜው ያለፈባት መሆኑን ስታስብ ከአቅሟ በላይ የሆነ ስሜት ይወርሳታል፡፡
ብሮኒ በሞት አፋፍ ላይ ያሉ ሰዎች በሚኖሩበት ማእከል ውስጥ ስትሰራ ካጠናቻቸው የሰዎች ጸጸቶች ይህኛው፣ “ሌሎች ሰዎች ከእኔ የሚጠብቁብኝን ሳይሆን እኔው ራሴ ያመንኩበትን ሕይወት የመኖር ድፍረት ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ!” የሚለው ጸጸት አብዛኛዎቹን ሰዎች የሚያጠቃውና ቀንደኛው ነው፡፡ ብዙ ሰዎች የሕልማቸውን ግማሽ እንኳን ሳያጣጥሙ ዘመናቸው የሚያልፈው ያመኑበትን ትክክለኛ የሕይወት አቅጣጫ ለመከተል ምርጫ እንዳላቸው ካለማወቅና ወይም ትክክለኛውን ምርጫ እያወቁ ያንን ምርጫ ለመከተል ጉልበት ከማጣት የተነሳ ነው፡፡
ጊዜው ካለፈብህ በኋላ እዳትጸጸት ሰዎች ከአንተ የሚጠብቁትን ሳይሆን አንተ ራስህው ያመንክበትን ትክክለኛ ሕይወት የመኖርን ጉዳይ ዛሬውኑ አስብበት

🌀✅ ባለትዳሮች ወደ መኝታቸው እያመሩ ነው፡፡ በድንገት ባልየው ከቤታቸው ጀርባ ያለውን አትክልት ቤት መብራት እንዳላጠፋው ትዝ አለውና ተነስቶ ወደዛ አመራ ነገር ግን አትክልት ቤቱ ውስጥ ሶስት ሌቦች ሰብረው ገብተው ተመለከተ፡፡
ወዲያው ፖሊስ ጣቢያ ደውሎ እርዳታ ጠየቀ፡፡ ኦፊሰሩም "አሁን ሁሉም ፖሊሶች ለስራ ወጥተዋል፤ ምንም ፖሊስ የለም፡፡ እንደተመለሱ
እልክልሀለው" አለ፡፡
ሰውዬው በጣም ከመፍራቱ የተነሳ ከተወሰኑ ደቂቆች በኀላ መልሶ ደወለ፡፡ "አታስብ ኦፊሰር፤ ሶስቱንም ሌቦች ገደዬ ቆራርጬ ለውሻዬ ሰጥቻቸዋለው፤ ምንም ፖሊስ መላክ አይጠበቅብሕም" አለው፡፡
ብዙም ሳይቆይ በሶስት የፖሊስ መኪና የታጨቁ ከ10 የሚበልጡ ፖሊሶች የሰውዬውን መኖሪያ ቤት ከበቡት፡፡ ኦፊሰሩም አብሮ ነበረ፡፡ ነገር ግን ሌቦቹ እንደተባለው ተገለው ተቆራርጠው ለውሻ ተሰጥተው ሳይሆን ከእነ ነፍሳቸው ሲሰርቁ ተያዙ፡፡
#ኦፊሰር ፡- "ገድዬ ቆራርጬ ለውሻዬ ሰጥቻቸዋለው ያልክ መስሎኝ"
#ሰውየው ፡- "አንተም አሁን ምንም ፖሊስ የለም፤ ሁሉም ስራ ወጥተዋል ያልክ መስሎኝ" አለው፡፡
#ጭብጥ :- ብዙ ግዜ አብዛኞቹ በህይወታችን ያሉ ሰዎች እኛ ስንፈልጋቸው አናገኛቸውም፤ ነገር ግን በእኛ የውድቀት እና የመከራ ወቅት ያዘኑ መስለው ለማፌዝና ወደ ጥልቁ ስንወርድ ከንፈር ለመምጠጥ በዙሪያችን ይሰበሰባሉ፡፡
ታሞ አንድ ብርጭቆ ውሃ ያልሰጠነውን ሰው ሲሞት አፈር ለመጫንና
ንፍሮውን እየበላን "እንዲህ ነበር እሱ" እያልን የውሸት ድርሰታችን ለማንበብ አንጣደፍ፡፡
እውነት የምንላቸውን ሰዎች ከወደድናቸው፤ ስለ እነሱ የምናስብ ከሆነ ሰው በሚያስፈልጋቸው ወቅት ከጎናቸው እንሁን።

ንስርን የሚገዳደር ብቸኛው የወፍ ዝርያ ቁራ ነው።
ቁራ በንስሩ ጀርባ ላይ ይቀመጥና አንገቱን ይነክሰዋል። ንስሩ ምላሽ አይሰጥም ፣ ከቁራ ጋር አይጣላም ፣ ከቁራ ጋር አይታገልም ፣ በቁራ ላይ ጊዜና ጉልበቱን አያጠፋም ይልቁንም ክንፉን ዘርግቶ ወደ ሰማይ ከፍ በማለት መብረር ይጀምራል።
በረራው ከፍ ባለ መጠን ቁራው ለመተንፈስ ይቸገራል። በመጨረሻም ቁራው በኦክሲጅን እጥረት ምክንያት ይወድቃል።
🎯.ዛሬ በህይወታችሁ የሚገዳደራችሁን ምንም አይነት ነገር አትታገሉት ፣ ጉልበታችሁን እና ጊዜአችሁን በእርሱ ላይ አታጥፉ ይልቁንም ከፍ ባለ አስተሳሰብ በልጣችሁ ውጡ ፣ በእውቀት ጠንክሩ ፣ መልካም ሥራችሁን ጨምሩ።
ንስሩ በጀርባው ላይ የተንጠለጠለውን ቁራ ትቶ ከፍታው ላይ እንደሚያተኩር የሌሎችን አሉባልታ ፣ ሀሜት ፣ ማስፈራሪያ ወደታች ትታችሁ ከፍታችሁ ላይ አተኩሩ።
ቁራው ከፍታውን መቋቋም እንዳቃተው እናንተም ከነገሮች በላይ ከፍ ስትሉ የእናንተም ተግዳሮት ከፍታውን መቋቋም አቅቶት ቁልቁል ይፈጠፈጣል ።
መልካም ቀን

* ከፍ ብለህ ብረር! *
ከፍ ብለህ ለመብረር ከፈለግህ ወደ ላይ ከፍ ከፍ እንዳል የሚጎትቱህን ማናቸውንም ክብደት ያላቸው ነገሮች አወግድ የሚል ጥቅስ አንብቤያለሁ። የምትሸከመው ነገር በበዛ ቁጥር ወደ ላይ ለመውጣት ከባድ ይሆናል። ስለዚህ መውጣትህ የግድ ከሆነ እና በፍጥነት ከፍ ከፍ ለማለት የምትፈልግ ከሆነ ክብደት ያላቸውን ነገሮች በሙሉ ከላይህ ላይ ማራገፍ ያስፈልግሃል።
በሌላ አገላለጽ ወደ ስኬት በምናደርገው የለውጥ ጉዞ ከዓላማችን በፍጥነት እንዳንደርስ የሚያደናቀፉ ሰዎችን እንዲሁም አጉል የሆኑ አስተሳሰቦችና ልማዶቻችንን መተው ግድ ይለናል።

የማቆም ውሳኔ
አንድ የጀመራችሁት ነገር በፍጹም እንደማያስቀጥላችሁ እያወቃችሁ ለውጥ ማምጣት ካቃታችሁ . . . እንዲሁም ከአንድ ሰው ጋር ያላችሁ ግንኙነት ፍጹም ጤና ቢስ እንደሆነና እንደማያዛልቃችሁ እያወቃችሁት ደንዝዛችሁ እንደቀራችሁ ከተሰማችሁ፣ ችግራችሁ ነገሩን የማቆም ከመሆኑ ይልቅ አዲስ ነገር የመጀመር ጉዳይ እንደሆነ አትዘንጉ፡፡
1. እንደገና የመጀመር ፍርሃት
አንድን ነገር እንደገና የመጀመር ፍርሃት ካለብን አሁን ያለውና አላስኬድ ያለውን ነገር ማቆም እንዳለብን እያወቅነው እንኳን ያንን ማድረግ ያስቸግረናል፡፡ ሆኖም፣ የተበላሸ ነገር ይዞ የመቀጠል ሁኔታ ረጅም ርቀት የሚሄድን ችግር ይዞ እንደሚጠብቀን እናስታውስ፡፡
2. ግራ መጋባት
አንድን ነገር ማቆም እንዳለብን ብቻ አውቀን ያንን ካቆምን በኋላ ምን እንደምንጀምር ካላወቅነውና ግራ ከገባን ሁኔታው አስፈሪ ያደርገዋል፡፡ እዚህ ጋር ማስታወስ ያለብን ነገር ቢኖር አንድን ነገር ስናቆም በቶሎ ሌላ ነገር መጀመር እንደሌለብን ነው፡፡ በተለይም ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት እንዳቆምን ወዲያው ሌላ መጀመር እንዳለብን ማሰብ ወደሌላ አስቸጋሪ ግንኙነት ውስጥ እንድንገባ ሊያሳስተን ይችላል፡፡
3. ጊዜ እንዳባከንን መሰማት
አንድ ነገር አላስኬድ ሲለንና ማቆም ስንፈልግ፣ አንዳንድ ጊዜ የሚቆጨን በዚያ ነገር ላይ እስካሁን ያሳለፍነው (ያባከንነው) ጊዜ ነው፡፡ “ይህንን ያህል አመት ቆይቼ” እንላለን፣ ልክ በቁጭት ከተነሳን አሁን ያለው ነገር ይለወጥ ይመስል፡፡ አንድ ነገር ፈጽሞ እንደማያስኬደን ካወቅን በኋላ ብዙ ጊዜ አቃጥያለሁ ብሎ ማሰብ በማይሰራ ነገር ላይ ሌላ ተጨማሪ ጊዜ በመቃጠል ወደፊት ለሚቆየን የከፋ ጸጸት ራስን ማዘጋጀት ማለት ነው፡፡
አስታውሱ . . .
• አዲስ የሚተክለውን ነገር በሚገባ ያወቀ ሰው አሮጌውን መንቀል አያስቸግረውም፡፡
• አዲስ የሚገነባው ነገር የገባው ሰው አሮጌውን ማፍረስ አይከብደውም፡፡
• አዲስ የሚጀምረውን ነገር የተረዳ ሰው አሮጌውን ማቋረጥ አያዳግተውም፡፡
ችግራችን አቅጣጫን ያለማወቅ እንደሆነ ተገንዝበን ስለነገው ጉዟችን ግልጽ የሆነ እይታን ስናዳብር በፊት ያስቸገረን ነገር ምን ያህል ቀላል እንደሆነ እንደርስበታለን፡፡

* እንደገና የመጀመር ዕድል! *
ውድቀት አንድን ነገር ቀደም ሲል በሄድንበት መንገድ ሳይሆን እንደገና በጥበብ የመጀመር እድል ነው። ሄንሪ ፎርድ
ብዙዎቻችን ውድቀትን እንፈራለን። ይሁንና ውድቀት ወይም አለመሳካት በየቀኑ በትምህርት ቤት፣ በስራ ቦታ፣ በቤተሰብ ውስጥ ወዘተ. የሚከሰት፤ የሚያበሳጭ፤ ነገር ግን ልናስወግደው የማንችለው ነገር ነው።
እናም ውድቀትን ብንፈራው ከዓላማችን የሚያደናፈን፤ ከደፈርን ደግሞ ትምህርት ወስደን በአዲስ መንገድና በአዲስ ስልት እንደገና ለመጀመር እድል የሚሰጠን ነው፤

#ጓደኝነት(ወዳጅነት)_በዛፍ_ይመሰላል ያለው ማን ነበር?
ይህንን የወዳጅነትን መግለጫ ማን እንዳለው ባላስታውስም እውነቱ ግን ይህው ነው።
ወዳጅነት በዛፍ ይመሰላል፦
1) #ቅጠል፤ በቅጠል የተመሰሉት ሲያጅቡ ብዙ ውበት ይሆናሉ። ቶሎ ለሁሉ ይታያሉ። ለሁሉ ሳቢ ናቸው። ግን ምን ያደርጋል በመጀመሪያው ንፋስ ይረግፋሉ። የመከራን ሰአት ወዳጅ መሆን አይችሉም። ጓደኝነታቸው እስከ ንፋሱ መንፈስ ድረስ ብቻ ነው።
2) #ቅርንጫፍ፤ እነዚህ ከቅጠሉ ይልቅ የተቀራረቡ ናቸው። ቅጠሎቹን የተሸከሙ ለመስፋፋት ምክንያት የሆኑ ናቸው። ግን ቢንጠለጠሉባቸው ወይም ልደገፋችሁ ሲባሉ ይዘው ይወድቃሉ። ማስደገፍ የሚችሉበት የወዳጅነት ጥንካሬ የላቸውም። ወዳጅነት የሚያስከፍለውን ዋጋ ስለማይገነዘቡ መነካካትን አይፈልጉም። ለእነሱ መንካት እንጂ መነካት ነውር ነው። ስለዚህ...
3) #ግንድ፤ እነዚህኛዎቹ ወዳጆች (ጓደኞች) አብሮነትን በመከራም በምቾትም ቀን ማስቀጠል የሚችሉ ናቸው። በሁሉ ሁኔታ ውስጥ አብሮ መጽናትን የተማሩ ወይም የቻሉ ናቸው። ደክመሃል ብለው በምድረበዳ ለአውሬ ጥለው የማይሄዱ ጠንካሮች ናቸው። ይጠብቁሃል እንጂ በአደባባይ አያሰጡህም። እንደ ዮናታን ከእነሱ መብት የሚያስቀድሙህ ናቸው።
4) #ስር፤ እነዚህ ደግሞ ታዋቂና በየቅያሱ አብረው የሚታዩ አይደሉም። ቅን ለአንተና ለጓደኝነትህ ሕይወትን ሲመግቡ ይኖራሉ። በጎደኝነት ጉዞ ውስጥ ሁሌም ደግሞ ደግሞ የሕይወት ሽታና ኃይል እንዲኖር የሚተጉ ናቸው።
"ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወዳል፤" ምሳ 17:17
እንደ ግንድም እንደ ስርም የሆነ ጓደኛ እንሁን። ቅጠልና ቅርንጫፍ ለሆኑትም ልብ በመስጠት ጉዳትን አናብዛ።
የእውነት ጓደኛ ነህ? የእውነት የሆኑስ ጓደኞች ዛሬ ላይ አሉህ?

ቅደም ተከተልን የማወቅ ጥበብ
“የሚያጣድፍ ነገር ሁሉ አስፈላጊ ነገር አይደለም” - Stephen Covey
አንድ ቀን አንድ የማኔጅመንት ሳይንስ ሊቅ ለተማሪዎቹ ንግግር በማድረግ ላይ ነበር፡፡ ይህ ሰው ለእነዚህ በጣም ለተነሳሱና ብሩህ አእምሮ ላላቸው ተማሪዎች በመናገር ላይ እያለ አንድን ነገር አደረገ፡፡ አንድ ባሊ አመጣና ጠረጴዛው ላይ ካስቀመጠ በኋላ ድንጋዮችን በማምጣት ባሊውን አፉ ድረስ ጢም አድርጎ በድንጋይ ሞላው፡፡ ይህንን ካደረገ በኋላ፣ “ይህ ባሊ ሙሉ ነው የሚል እጁን ያውጣ” አለ፡፡
በክፍሉ ያሉ ተማሪዎች በሙሉ እጃቸውን አወጡ፡፡ “እርግጠኛ ናችሁ?” አላቸው፡፡ “አዎን” በማለት እርግጠኝነታቸውን አረጋገጡለት፡፡ ከዚያም ከጠረጴዛው ስር አስቀምጦት ወደነበረው ሌላ ባሊ አጁን ዘርግቶ አነሳውና በውስጡ ያለውን ጠጠር ወደዚያ ድንጋይ ሞልቶበት ወደነበረው ባሊ አፈሰሰው፡፡ ጠጠሮቹ ሹልክልክ እያሉ ባገኙት ቀዳዳ ሁሉ ገቡ፡፡
“አሁንስ ባሊው ሙሉ ነው የምትሉ ስንት ናችሁ?” አለ መልሶ፡፡ አሁን አሰልጣኙ ምን ሊል እንደፈለገ በመጠኑ እየገባቸው ስለመጣ በማንገራገር የተደባለቀ ምላሽ ሰጡት፡፡ አንዳንዶቹ፣ “አሁን ሙሉ ነው” ሲሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ፣ “አሁንም አልሞላም” አሉ፡፡ አሁንም በመቀጠል እጁን ወደ ጠረጴዛው ስር ሰደድ በማድረግ ሌላ ባሊ አነሳ፡፡
ይህኛው ባሊ በአሸዋ የተሞላ ነው፡፡ ወዲያውኑ አሸዋውን ወደዚያ ድንጋይና ጠጠር ሞልቶበት ወደነበረው ባሊ አፈሰሰው፡፡ አሸዋዎቹ ሹልክልክ እያሉ ባገኙት ቀዳዳ ሁሉ ገቡ፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ፣ “አሁንስ ባሊው ሙሉ ነው የምትሉ ስንት ናችሁ?” አሁን ተማሪዎቹ በሙሉ በአንድ ቃል፣ “ባሊው አሁንም አልሞላም” ብለው መለሱለት፣ አካሄዱ ገብቷቸው፡፡ አሰልጣኙ እንደገና ሌላ ውኃ የሞላበት ባሊ ከጠረጴዛው ስር በማንሳት ድንጋይ፣ ጠጠርና አሸዋ ሞልቶበት ወደነበረው ባሊ አፈሰሰውና በባሊው ውስጥ ሌላ ምንም ነገር መጨመር እስከማይቻል ድረስ ሞላው፡፡
የመጨረሻው ትምህርታዊ ጥያቄ እንዲህ የሚል ነበር፡፡ “ከዚህ ምሳሌ የምናገኘው ዋና ቁምነገር ምንድን ነው?” አላቸው፡፡ አንዱ ሰልጣኝ አጁን አውጥቶ፣ “ምንም እንኳ ጊዜህ በብዙ ነገር ቢጨናነቅ፣ አሁንም ሌላ ነገርን አጨናንቀህ ማድረግ እንደምትች ነው” አለው፡፡
አሰልጣኙም፣ “ተሳስተሃል! የዚህ ምሳሌ ዋነኛ ትምህርት በመጀመሪያ ትልልቆቹን ድንጋዮች ባሊው ውስጥ ባትጨምር ኖሮ ትንንሾቹን ጠጠሮች፣ አሸዋውንና ውሃውን መጨመር አትችልም ነበር፡፡ ትልልቆቹ ድንጋዮች የሚወክሉት በሕይወትህ ያሉትን ዋና ዋና የሕይወት አላማዎችና ግቦች ነው፡፡
ቤተሰብህ፣ ጤንነትህ፣ የትምህርትህ አቅጣጫ፣ ዋነኛ ሕልሞችህና የመሳሰሉት … ዋና ዋና ከሚባሉት “ድንጋዮች” መካከል ይገኛሉ፡፡ በመጀመሪያ በእነዚህ ነገር ካልተደላደልክና የሕይወትህን አቅጣጫ ካልሞላኸው፣ በጥቃቅን ነገሮች ተጨናንቀህ ሕይወትህን ታባክናለህ፡፡
አንዳንድ ሰዎች ጊዜን በአግባቡ የመጠቀምን ጥበብ ማዳበር በራሱ እጅግ አድካሚ ስራ ነው ብለው ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ሁኔታው የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ ዛሬ የሕይወቴን ዋና ዓላማ በመለየትና ቅድሚያን ለእርሱ በመስጠት መልክ የያዘ ሕይወት ለመኖር ማቀድ ካልቻልኩ ነገ በዚህና በዚያ የባከነውን ጊዜዬን መለስ ብዬ ከማየትና ከመቆጨት ውጪ ምንም ነገር ለማድረግ ያስቸግረኛል፡፡
“የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ የተቀነጨበ፡፡

“እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።”
— ዕብራውያን 6፥10
— ዕብራውያን 6፥10
1 ዜና 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³³ በምድር ሊፈርድ ይመጣልና፥ የዱር ዛፎች በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይላቸዋል።
³⁴ ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ።
³⁵ የመዳናችን አምላክ ሆይ፥ አድነን፤ ቅዱስ ስምህን እናመሰግን ዘንድ፥ በምስጋናህም እንመካ ዘንድ፥ ከአሕዛብ ሰብስበህ ታደገን በሉ።
³⁶ ከዘላለም እስከ ዘላለም፥ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበሉ፤ እግዚአብሔርንም ያመስግኑ።
መልካም አዲስ አመት 2016💟💝💝💘💘💗🔆🔆🔆🔆

ከሰዎች ጫና መውጣት!
እውነት ነው የንፋሱን አቅጣጫ መቀየር አትችልም፤ መርከቡ ግን የነፋሱን አቅጣጫ ሳይሆን ያንተን መንገድ እንዲይዝ ማድረግ ትችላለህ።
አየህ በህይወት ውስጥም የሚገጥሙህን ሁኔታዎች፣ ፈተናዎች የማይጥሙ የሰው ፀባዮችን መቆጣጠር አትችልም፤ ግን ያንተን ህይወት እንዲወስኑት አለመፍቀድ ያንተ ምርጫ ነው ምክንያቱም የመርከብህ ካፒቴን አንተ ብቻ ነህ!
መልካም የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ🙏

ከአምስት አመት በኋላ!
• የዛሬ አምስት አመት በዙሪያችሁ የሚኖሯችሁን አልሚ ወይም አጥፊ ጓደኞች የሚወስነው ዛሬ ያዳበራችሁት አመለካከት ነው፡፡
• የዛሬ አምስት አመት የሚኖራችሁን የፍቅር ወይም የትዳር ግንኙነት አይነት የሚወስነው የዛሬ ወዳጅነት ምርጫችሁ ነው፡፡
• የዛሬ አምስት አመት የሚኖራችሁን እውቀት የሚወስነው ዛሬ የምታነቧቸው መጻሕፍትና የምትወስዷቸው ስልጠኛዎች ናቸው፡፡
• የዛሬ አምስት አመት የምትገቡበትን አዲስ የሕይወት ምእራፍ የሚወስነው ዛሬ ለማድረግ የቆረጣችሁት ለውጥ ነው፡፡
• የዛሬ አምስት አመት የምትኖሩትን የኑሮ ጥራት የሚወስነው ዛሬ ያዳበራችሁት ልማድ ነው፡፡
ጥራት ያለው ሕይወት በአንድ ጀንበር አይመጣም፡፡ በአንድ ጀንበር ብቅ ያለ ነገር ካለም ደግሞ በአንድ ጀንበር ጥልቅ ማለቱ ስለማይቀር ጥራትን ዛሬ ጀምረውና በምንም ነገር እንደማይቀለበስ ሆኖ እንዲበቅል ጊዜ ስጠው፡፡
1. የሕይወታችሁን ዋነኛ ራእይና ዓላማ ለይታችሁ እወቁ፡፡
2. የምትመጧቸውን ጓደኞችም ሆኑ የምትውሉበትን ቦታ ከዚያ ዓላማ አንጻር ቃኙት፡፡
3. አብዛኛው አእምሯችሁን የምትመግቡት አመለካከትም ሆነ የእውቀት ዘርፍ ከዋና ዓላማችሁ አንጻር አድርጉት፡፡
4. የየቀን ልምምዳችሁንና ልማዳችሁን ከዋናው ዓላማችሁ አንጻር ቃኙት፡፡
@Kibirenaw

* የነገው ድንቅ ሰው አንተ! *
አንተ ማለት አሁን ያለኸው ማንነትህ ብቻ አይደለህም። በውስጥህ በጣም ብዙ የማድረግ እና የማሳካት አቅም ያለህ ድንቅ ማንነት ያለህ ሰው ነህ። ይህንን ድንቅ ማንነትህን ስታወጣው ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን ማክናወን ይችላል። ይህንን ድንቅ ማንነት ስታወጣው የነገውን ድንቅ ሰው ይፈጥራል።
እናም ወዳጄ ሆይ የነገውን ድንቅ ሰው ከውስጥህ አውጣው!
መልካሙን ሁሉ እመኝላችኋለሁ❤❤❤