Forwarded from ✝🕊አ͍ባ͍ ጊ͍ዮ͍ር͍ጊ͍ስ͍ ዘ͍ጋ͍ስ͍ጫ͍(ሰግላዊ)🕊✝ (ᵉᶻᵉᵏⁱᵉˡ @҉ 1҉ 6҉ ሕ҈ ዝ҈ ቅ҈ ኤ҈ ል҈ )
እስኪ ዛሬ ደግሞ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለእኔ የፃፈልኝን ልንገራችሁ።።
ሰው ነህ ፤ ግን ⁉️⁉️⁉️
ሰው ነህ፤ ግን ደግሞ እንደ እባብ🐍🐍 መርዝ ትተፋለህ፡፡ ሰው ያውም ክርስቲያን ነኝ ትላለህ፤ ነገር ግን ከበረሀ አውሬ ይልቅ ስትደነፋ እመለከታለሁ፡፡ አንደበት የተሰጠህ ሰዎችን ከቁስለ ሥጋ ከቁስለ ነፍስ ታድንበት ዘንድ ነበር፤ ነገር ግን ወንድምህን ስታቆስልበት አያለሁ፡፡ ታድያ አንተን ማን ብዬ ልጥራህ?⁉️⁉️
ሰው 🙎♂🙎🙎♂🙎⁉️⁉️
ወይስ አውሬ🐅🐊🐆🐍⁉️⁉️ ምን ብየ ልመልስለት አውሬ ወይስ ሰው ልበለው 😞😞
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
https://www.tgoop.com/betelhem29

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
የሰኔ ጾም ወይም ጾመ ሐዋርያት
ሰኔ 6 ይገባል እስኪ ትንሽ ልንገራችሁ ስለ ጾመ ሐዋርያት ቅድመ ጰራቅሊጦስ እና ድኅረ ጰራቅሊጦስ
#ጾመ_ሐዋርያት: ቅድመ ጰራቅሊጦስ
ቀደምት የቤተክርስቲያን መጻሕፍት እንደሚያስረዱት ቅዱሳን ሐዋርያት ከጌታችን ዕርገት እስከ ኀምሳኛው ቀን (ለ10 ቀናት) ድረስ በጾምና በጸሎት ቆይተዋል፡፡ እነዚህንም 10ቀናት የጾሙት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምድር ላይ እያለ ‹‹ እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው…ወላጆች እንደ ሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም›› (ዮሐ 14፡16-18) ብሎ የሰጣቸውን ተስፋ እየተጠባበቁ ነበር፡፡ ይህንን ጾም በመጾም ሐዋርያት ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ራሳቸውን አዘጋጅተውበታል፡፡ ዛሬም ካህናት ክህነት ከመቀበላቸው በፊት፣ አዳዲስ ተጠማቂዎችም ከጥምቀት በፊት እንዲሁም ክርስቲያኖች ሁሉ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ከመቀበላቸው በፊት የሚጾሙት ይህንን አብነት አድርገው ነው፡፡ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ለመቀበል ራስን በጾምና በጸሎት ማዘጋጀት ያስፈልጋልና፡፡
#ጾመ_ሐዋርያት_ድኅረ_ጰራቅሊጦስ
ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላም ጾምን የአገልግሎታቸው መጀመሪያ አድርገውታል፡፡ ሐዋርያት የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከተቀበሉ በኋላ የጾሙት ስለሁለት ዓላማ ነው፡፡ አንደኛው ስለተሰጣቸው ጸጋ መንፈስ ቅዱስ አምላካቸውን ለማመስገን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በዓለሙ ሁሉ ዞረው ለሚሰብኩት ወንጌል ራሳቸውን ለማዘጋጀት ነው፡፡ ስለዚህም ነው መንፈሳዊ አገልግሎትና ስብከት የዚህ ጾም አንኳር ነጥቦች የሆኑት፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ መጾማቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አብነት አድርገው ነው፡፡ እርሱ በማየ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ሲጠመቅ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ጌትነቱን ለመመስከር ከወረደ በኋላ ሳይውል ሳያድር ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ ሄዶ በዚያ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ጾሟልና እነርሱ ደግሞ ኃይል ይሆናቸው ዘንድ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን በበዓለ ጰራቅሊጦስ ዕለት ከተቀበሉ በኋላ ጾምን የሥራቸው ሁሉ መጀመሪያ አድርገዋል፡፡ አንዳንድ መዛግብት በመጀመሪያዎቹ ዘመናት የሐዋርያት ጾም የሚጀምረው ከጰራቅሊጦስ አንድ ሳምንት በኋላ ነበር ይላሉ፡፡ ከዚያም በ258ዓ.ም ከበዓለ ጰራቅሊጦስ እስከ ሐዋርያት በዓል (The Feast of the Holy Apostles) (ሐምሌ 5) ድረስ እንዲሆን አባቶች ደነገጉ በማለት ያስረዳሉ፡፡ ይህም የተረደገው የቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ጴጥሮስ በኔሮን ቄሳር በሮም አደባባይ ሰማዕትነት የተቀበሉበትን ዕለት አብሮ ለማሰብ እንዲረዳ ነው በማለት ያጠናክሩታል፡፡ መጽሐፈ ድዲስቅሊያ ደግሞ ሐዋርያት 40 ቀን እንደጾሙ ከዚያም በኋላ ቅዱስ ጴጥሮስ እግራቸውን አጥቧቸው ለስብከተ ወንጌል እንደተሰማሩ ያስረዳል፡፡
‹‹እናንተ ስትጦሙ›› እና ‹‹አንተ ግን ስትጦም››
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ጾም የፈቃድ ብቻ ሳይሆን ትዕዛዝ መሆኑንም ለሐዋርያቱና ለሚከተለው ሕዝብ ሲያስተምር ‹‹ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። ማቴ 6፡16-18›› ብሏል፡፡ በዚህም ትምህርቱ እርሱ የሚወደው ጾም ምን አይነት እንደሆነና እንዲሁም የማኅበርና የግል ጾም መኖሩን ‹‹እናንተ ስትጦሙ›› እና ‹‹አንተ ግን ስትጦም›› ብሎ ለይቶ አስተምሯል፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድም የተወደደ ጾም እንዴት አይነቱ እንደሆነ ነቢያት አስቀድመው ‹‹የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን? እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?›› ብለው ጽፈዋል፡፡ ኢሳ 58፡6-8

Telegram
✝🕊አ͍ባ͍ ጊ͍ዮ͍ር͍ጊ͍ስ͍ ዘ͍ጋ͍ስ͍ጫ͍(ሰግላዊ)🕊✝
👨🦳👨🦳👴👴የዱሮውን ዘመን ዐስብ፥የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል አባትህን ጠይቅ፥ያስታውቅህማል ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ይነግሩህማል። ዘዳግሞ 32÷7👨🦳👨🦳👴👴
ቄርሎስ ወአፈወርቅ ዘኢትዮጵያ
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
🕊🌈ር͓̽ግ͓̽ቤ͓̽ አ͓̽ን͓̽ዲ͓̽ት͓̽ ና͓̽ት͓̽🌈🌿🕊
https://www.instagram.com/p/CcgAfLBIFww/?igshid=YmMyMTA2M2Y=
ቄርሎስ ወአፈወርቅ ዘኢትዮጵያ
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
🕊🌈ር͓̽ግ͓̽ቤ͓̽ አ͓̽ን͓̽ዲ͓̽ት͓̽ ና͓̽ት͓̽🌈🌿🕊
https://www.instagram.com/p/CcgAfLBIFww/?igshid=YmMyMTA2M2Y=
Forwarded from ✝🕊አ͍ባ͍ ጊ͍ዮ͍ር͍ጊ͍ስ͍ ዘ͍ጋ͍ስ͍ጫ͍(ሰግላዊ)🕊✝ (ᵉᶻᵉᵏⁱᵉˡ @҉ 1҉ 6҉ ሕ҈ ዝ҈ ቅ҈ ኤ҈ ል҈ )
ሰኔ 5'' በዓለ ጰራቅሊጦስ''የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በሁሉም ላይ አረፉባቸው፡፡
ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፣ ሰባ ሁለቱ አርድእት እና ሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት በኢየሩሳሌም ከተማ በአንድነት ሆነው በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ‹‹እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፤›› ሲል ለሐዋርያቱ በሰጣቸው የተስፋ ቃል መሠረት በዐረገ በዐሥረኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል (ሉቃ. ፳፬፥፵፱)፡፡ ሁሉም በአንድ ቦታ ተሰባስበው ሳሉ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ ወርዶ የነበሩበትን ቤት ሞላው፡፡ ከዚያም የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በሁሉም ላይ አረፉባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሁላቸውም መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየሀገሩ ቋንቋዎች ሁሉ ተናገሩ፡፡ (ሐዋ.፪፥፩-፬)
ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ዐሥራቱን፣ በኵራቱን፣ ቀዳምያቱን ካህናተ ኦሪት ስለሚቀበሉበት በብሉይ ኪዳን በዓለ ሠዊት ተብሎ ይከበር ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ስለ ተቀበሉበት በበዓለ ሠዊት ምትክ በዓለ ጰራቅሊጦስ ተብሎ ይከበራል።።
የሐዋርያት ስራ ምዕ 2 ÷1_9
በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ሁሉም ባንድ ልብ ሆነው ዐብረው ሳሉ፥ድንገት እንደሚነጥቅ ዐውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።
እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታይዋቸው በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።
በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።

የ ኢንስታግራም ገፃችንን ይጎብኙ። አብሮነታችሁ አይለየን https://www.instagram.com/p/CcgAfLBIFww/?igshid=YmMyMTA2M2Y=
ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰባስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጐልምሰዋል፤ ጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ሆነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል፡፡ ቀድሞ ይናገሩት ከነበሩት ቋንቋ በተጨማሪ ፸፩ [71] ቋንቋዎች ተገልጠውላቸው ምሥጢራትን በልዩ ልዩ ቋንቋ መተርጐም ጀምረዋል፡፡
ሐዋርያት በየሀገሩ ቋንቋ ሲናገሩ የሰሙ በዚያ የነበሩ ሰዎችም በሐዋርያት ተገረሙ፡፡ አንዳንድ የአይሁድ ወገኖች ግን በሐዋርያት ላይ ያዩት ክሥተት አዲስ ነገር ስለሆነባቸው ‹‹ጉሽ ጠጅ ጠጥተው ሰክረው የሆነ ያልሆነውን ይቀባጥራሉ›› እያሉ ሐዋርያትን ያሟቸው ነበር፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስም ይህንን ሐሳባቸውን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ‹‹ሰክረዋል የምትሉ እናንተ እንደምትጠራጠሩት አይደለም፡፡ ጊዜው ማለዳ፣ ሰዓቱም ገና ሦስት ሰዓት ነውና፡፡ ግን በነቢዩ ኢዩኤል ‹ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ› ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ
°°°°°°°°° ይህንን ድንቅ ተአምር ያደረገው እናንተ የሰቀላችሁት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤››በማለት ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ሰጥቷቸዋል፡፡ (ኢዩ.2፥28)•••••°°°°°°°°

🍓🍓🍓#ቤተማርያም🍓🍓🍓
ሐምሌ 7
#ሥሉስ_ቅዱስ
#በአንድነቱ_ምንታዌ_ሁለትነት #በሶስትነቱ_ርባዌ_አራትነት_የሌለበት የዘላለም #አምላክ የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ #እግዚአብሔር_አብ #እግዚአብሔር_ወልድ_እግዚአብሔር #መንፈስ ቅዱስ ሐምሌ 7 አመታዊ ክብረ በዓላቸው ነው።።
መፃህፍታት እንዲህ ይላሉ 👉ከፍጥረት ወገን #ከእመቤታችን ቀጥሎ #የአብርሃምን_ያክል_በእግዚአብሔር ዘንድ የሚወደድ ፍጡር የለም።።አባታችን አብርሃም #የደግነት ሁሉ አባት ነውና #በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ስር #ስላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል።።
አባታችን አብርሃም በ 99 አመቱ እናታችን ሳራ በ 89 አመታቸው የሁሉ ፈጣሪ የሆኑትን #ሥላሴን አስተናገዱ።።
አብርሃም እግራቸውን አጠበ
ምሳቸውን አቀረበላቸው
በዚች ዕለትም መካን የነበረችው ሳራን በሚቀጥለው አመት ስንመጣ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ ተብላ ተበሰሩ ሳራ ግን ሳቀች #ሥላሴ_ምንት_አስሐቃ_ለሣራ_ለባሕቲታ ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት #ይሳቅ ተባለ።።
ወዳጆቸ ስላሴን ያስተናገደች ድንኳን ( ሐይመት) #እመቤታችን_ማርያም ምሳሌ ናት።። በድንግል ላይ አብ ለአፀንኦ መንፈስ ቅዱስ ለአንፅኦ ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በርሷ ላይ አርፈዋል።
❤️❤️መልካም ቀን ተመኝን❤️❤️
https://www.tgoop.com/kidstarsema6

#ሥላሴ_ምንት_አስሐቃ_ለሣራ_ለባሕቲታእግዚአብሔር አብርሃምን ጠርቶ ‹‹ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት?›› አለው፡፡ አብርሃምም ከድንኳኑ ውስጥ እንዳለች ነገረው፡፡ እግዚአብሔርም ‹‹የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ፤ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች›› ብሎ ለአብርሃም አበሠረው፡፡ ሣራ ይህንን ቃል በሰማች ጊዜ ባለቤቷም አርጅቶ፤ እርሷም የሴቶች ግዳጅ ትቷት ነበርና ‹‹‹ሲያረጁ አምባር ይዋጁ› እንዲሉ ‹‹እስከ ዛሬ ድረስ ቆንጆ ነኝን? ጌታዬ አብርሃምስ ገና ጐረምሳ ነውን?›› ብላ በማሰቧና መውለዷን በመጠራጠሯ ሳቀች፡፡ እግዚአብሔርም ምሥጢሩን በአጽንዖት ለማስረዳትና አስረግጦ ለመንገር አብርሃምን ‹‹ሣራ ለምን ትስቃለች? በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን?›› አለው፡፡ ሣራም ስለፈራች ‹‹አልሳቅሁም›› አለች፡፡ እግዚአብሔርም መሳቋን እንዳወቀባት ከነገራት በኋላ በድጋሜ በዓመቱ ወደ አብርሃም ቤት እንደሚመጣና ሣራ ወንድ ልጅ (ይስሐቅን) እንደምትወልድ አብሥሯቸዋል፡፡
Forwarded from ✝🕊አ͍ባ͍ ጊ͍ዮ͍ር͍ጊ͍ስ͍ ዘ͍ጋ͍ስ͍ጫ͍(ሰግላዊ)🕊✝ (ᵉᶻᵉᵏⁱᵉˡ @҉ 1҉ 6҉ ሕ҈ ዝ҈ ቅ҈ ኤ҈ ል҈ )
Watch "Ezekiel Tube__ሕዝቅኤል ቲዩብ በጣም የምወደው በሰማው የማይሰለቸኝን መዝሙር ተጋበዙልኝ።" on YouTube
https://youtu.be/55DQ1c-H3q8
https://youtu.be/55DQ1c-H3q8
Forwarded from ✝🕊አ͍ባ͍ ጊ͍ዮ͍ር͍ጊ͍ስ͍ ዘ͍ጋ͍ስ͍ጫ͍(ሰግላዊ)🕊✝ (ᵉᶻᵉᵏⁱᵉˡ @҉ 1҉ 6҉ ሕ҈ ዝ҈ ቅ҈ ኤ҈ ል҈ )
በጣም የምወደውን ዝማሬ ልጋብዛችሁ subscribe and like በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
🌿🌷🕊ቤ࿆ ተ࿆ _ ማ࿆ ር࿆ ያ࿆ ም࿆ 🌿🌷🕊
https://youtu.be/yhXqPxwK1oM
የድፍረት ኃጢያት እንዳይገዛኝ ነው የሚል። መዝሙሩ የሁላችንም ሕይወት የሚመለከት ነው። subscribe share and like በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
Forwarded from ✝🕊አ͍ባ͍ ጊ͍ዮ͍ር͍ጊ͍ስ͍ ዘ͍ጋ͍ስ͍ጫ͍(ሰግላዊ)🕊✝ (ᵉᶻᵉᵏⁱᵉˡ @҉ 1҉ 6҉ ሕ҈ ዝ҈ ቅ҈ ኤ҈ ል҈ )
እግዚአብሔር የለም
..አንድ አባት ፀጉራቸውን ሊስተካከሉ በቅርባቸው ወዳለው አንድ ፀጉር ቤት ያዘግማሉ ከፀጉር ቤቱም ከደረሱ በኋላ ከመስተካከያው ወንበር ላይ ቁጭ ብለው ፀጉር አስተካካዮ ፀጉራቸውን መከርከም ይጀምራል
ድንገት ይህ ፀጉር አስተካካይ "እግዚአብሔርማ የለም" በማለት ወሬውን ይጀምራል ሸማግሌው በጣም ደነገጡ ድንጋጤቸው እዳይታወቅባቸው ያልደነገጡ መስለው በመረጋጋት የልጁን ንግግር ማብሰልሰል ጀመሩ ...ንግግሩ ግራ ስለገባቸው ምነው ልጄ እዴት እደዚህ ልትል ቻልክ አሉት?
አስተካካዮም ቀበል አለና አይ አባቴ እሄ ንግግር አሁን ምን ማብራሪያ ያስፈልገዋል አያዩም እዴ? ሰው እርስ በእርሱ ተጨካክኖ ሲባላ ሲገዳደል ደሀ ሲበደል ፍርድ ሲጓደል ጦርነቱ ረሀቡ ግፉ በሰው ልጅ ላይ የሚደርሰው ሰብዓዊ የመብት ጥሰት የተፈጥሮ አደጋው እረ ምኑን ነግሬዎት ምኑን ልተው እሄንን ሁሉ እያዪ እግዚአብሔር አለ ማለት እዴት ይቻላል ?እረ የለም አለ እራሱ ለራሱ መልሶ።
በልጁ ንግግር የተበሳጩት አዛውንት ንግግሩ እጅግ ቢያበግናቸውም ቀስ ብለው በመረጋጋት ልጁን ካጠኑት በኋላ በዝምታ ትንሽ ዘግየት አሉና እሳቸውም ተራቸውን
" ፀጉር አስተካካይማ የለም አሉ".
አስተካካዩ ተራውን ደነገጠ እዴ ምንም ማለቶት ነው ?
እዴት የለም ይላሉ ከተማውን ሁሉ የሞላውስ ፀጉር ቤት አይደል እርሶንስ እያስተካከልኩ ያለውት እኔ ፀጉር አስተካካይ አይደለሁ እዴ? አላቸው
እሳቸውም ኮራ ብለው ፀጉር አስተካካይ ቢኖርማ ወንዱ ሁሉ ፀጉሩ ተንጨባሮ ግማሹ ጉንጉን ሰርቶት ግማሹ ጠቅልሎት የቅጫም መነሀሪያ አርጉት አይሄድም ነበር ተመልከት በመንገድ ላይ ወጪ ወራጁን ሁሉ ፀጉሩ ያልተስተካከለ ነው እና ለምን ይመስልሀል? አሉትና ፀጉር ቆራጭ ስለሌለ ነው ብለው የራሳቸውን ጥያቄ ራሳቸው መለሱለት
አስተካካዩም በንዴት እያረረ እዴ እነሱ እኮ ወደ ፀጉር ቤት ስላልመጡና ከፀጉር አስተካካዩቹ ጋር ስላልተገናኙ ነው የእነርሱ ፀጉር መንጨባረር የፀጉር አስተካካዪችን አለመኖር አይገልጥም የሚገልጠው የእነርሱ ወደ ፀጉር አስተካካዩቹ ጋር አለመሄዳቸውን ነው ብሎ መለሰላቸው
እርሳቸውም ትክክል መልሰሀል አየህ አንተም እግዚአብሔር የለም ከማለትህ በፊት እነዛ ቅድም የነገርከኝ ፋርድ የተጓደለባቸው ደሀ የተበደለባቸው ግፍ የደረሰባቸው በምድር ላይ የሚደርሰው አሰቃቂ ነገር በሙ እየደረሰ ያለው እግዚአብሔር ስለሌለ ሳይሆን ሰዎቹ ወደ እግዚአብሔር ስላልሄዱ ነው ቅድም አተ እዳልከው የፀጉር መንጨባረር የፀጉር አስተካካዪችን አለመኖር አይገልጥም
የሚገልጠው የእነርሱ ወደ ፀጉር አስተካካዩቹ ጋር አለመሄዳቸውን ነው ብለህ ነበር አየህ
እዚህ ምድር ላይ የሚደርሰው ግፋና መከራ የእግዚአብሔርን አለመኖር አይገልጥም ።
ይልቅ ሰው ወደ እግዚአብሔር አለሜሄዱን ነው የሚገልጠው ሰው ከእግዚአብሔር በራቀ ቁጥር ለሀጥያት ለዲያብሎስ እና ለስጋ ምኞቱ ተገዢ ይሆናል የስጋ ምኞት ወደሞት እደሚመራን አሳምረህ ታውቃለህ አይደል አሉት? አስተካካዪም አዎ አለ
ከሚመጣው መከራ ለማምለጥ ወደ እግዚአብሔር መሮጥ እሱን መለመን ይጠበቅብና
በማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 7÷7
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።
የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።
ተብሎ የተመዘገበውንስ ታስታውሰዋለህ አይደል አሉት አስተካካዮም አዎ አለ
እሳቸውም ቀጠል አደረጉና አየህ ልጄ ለማግኘት መለመን አለብህ ለመግባትም ማንኳኳት ይጠበቅብሐል ።
በዝናብ አብቅሎ በፀሀይ አብስሎ የሚመግብህን አምላክ የለም በማለት የሰራህው ስህተት ከባድ ስህተት ነው ሐጥያትም ጭምር ነውና ሄደህ ለመምህረ ንሐህ ንገር አሉት አስተካካዪም ከስህተቱ ተሞሮ ወደ ንሰሀ አባቱ ለመሄድ ቃል ገባ..........
https://youtu.be/-3Hz2gharD8