++++++ጠባቧ_መንገድ++++++
"በተጨባጭ እውነታ ሰፊውንና ልቅ የኾነውን መንገድ ይዘን ሳለ ጠባቡንና የቀጠነውን መንገድ እየተከተልን እንደ ኾነ በማሰብ እንዳንታለል በራሳችን ላይ ቅርብ ትኲረት እናድርግ። ቀጥሎ የሰፈረው ነገር ጠባብ መንገድ ማለት ምን እንደ ኾነ ያሳይሃል፦ ሆድን ማጎስቆል (ስስትን መግደል)፣ ትጋሃ ሌሊት (ሌሊቱን ሙሉ መቆም)፣ ጥቂት ውኃ መጠጣት፣ ቍራሽ ዳብ መብላት (ከፊለ ኅብስት)፣ በተዋርዶ ድርቅ መንጻት፣ መናቅ፣ ፌዝን መቀበል፣ መሰደብ፣ የገዛ ፈቃድን ቆርጦ መጣል፣ በሚያስቆጣ ነገር መታገሥ፣ ባለ ማጉረምረም ንቀትን መታገሥ፣ ስድቦችን ቸል ማለት፣ ያልተገባ ጠባይን ጸንቶ መታገሥ፤ ሲታሙ አለመቆጣት፣ ሲዋረዱ አለመቆጣት፣ ሲነቀፉ ትሑት መኾን ነው። የገለጽናቸውን ጎዳናዎች የሚከተሉ ብፁዓን ናቸው፣ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። ማቴ 5፡3-13።" እንዲል ዮሐንስ ዘሰዋስው። (ሳሙኤል ፍቃዱ (ተርጓሚ)፣ ምዕራግና ድርሳን፣ 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 102)።
በዚህ አባት ጽሑፍ ውስጥ አንደኛ ራሳችንን መመርመር እንዳለብን ተገልጿል። ልቅ በኾነው ሰፊ መንገድ በተባለው የዓለማዊነት መንገድ ላይ መኾን አለመኾናችንን በትኩረት እንድናስተውል ምክረ ሐሳብ ቀርቧል። ኹል ጊዜም ቢኾን ትክክለኛ ወደ ኾነው መንገድ ለመግባት አስቀድሞ የቆምንበትን መንገድ እና በዚያ መንገድ እንድንጓዝ ያደረገንን ውስጣዊ ፍላጎት መረዳት ያስፈልጋል። ምን ያህልስ ጊዜ ልቅ በኾነው የኃጢአት መንገድ ተጉዘን ይኾን? ምን ያህልስ የዚያ መንገድ ጣዕም በውስጣችን ቀርቶ ይኾን? እንዴትስ ከዚያ መንገድ መውጣት እንችላለን። እያልን በእርጋታ ለራሳችን ጥያቄ እያቀረብን ራሳችንን እንመርምር።
ኹለተኛው መሠረታዊ ነገር ጠባብ መንገድ ማለት ምን ማለት እንደ ኾነ የተገለጸበት ነው። ጥቂት መመገብን ከመለማመድ ጀምሮ ማንኛውንም ክፉ የተባሉ ነገሮችን የሚያደርጉብንን መታገሥ ተገቢ መኾኑን ያስረዳል። መንገዱን ጠባብ ያሰኘውም፥ የተገለጹትን ነገሮች ለመተግበር እጅግ የሚከብዱ ስለ ኾነ ነው። ጽድቁንና መንግሥቱን እያሰብን የምንኖር ከኾነ ግን ከባድ ሊኾኑ አይችሉም። ጠባቡ መንገድ ጣዕመ መንግሥተ እግዚአብሔርን እያሰቡ ኃጢአትን መጥላትን ማዕከል ያደረገ ነውና። የሚንቁንን፣ የሚሰድቡንን፣ የሚያሙንን መታገሥ ለብዙዎቻችን አስቸጋሪ ነው። በእውነትም የሚጠሉንን ላለመጥላት እየታገልንን ኹሌ ራሳችንን ትዕግሥትን ብናለማምድ እግዚአብሔር ይረዳናል። ትዕግሥት በእኛ ጥረት ብቻ ሳይኾን ከእግዚአብሔርም ጸጋ ኾኖ የሚሰጥም ነገር ነውና። እኛ ከልባችን ክፉን በትዕግሥት ስንቀበል እግዚአብሔር ጽናቱን ይሰጠናል። የጠባቡ መንገድ መድረሻው መንግሥተ እግዚአብሔር መኾኑን በሕሊናችን ውስጥ አስቀምጠን፥ መንግሥቱን እያሰብን እንኑር። አንድ ሯጭ ትኲረቱን በሙሉ የሚያደርገው ቀድመውት ያሉ ተወዳዳሪዎች ላይ እንደ ኾነ ኹሉ እኛም ትኲረታችንን ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር አቅጣጫ ካደረግን በእኛ ላይ የሚደረጉ ክፉ ነገሮችን ኹሉ ሳናያቸው ማለፍ እንችላለን።
ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው
https:/www.tgoop.com/kinexebebe

Telegram
መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ
መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ የሚገኝበት ቻናል ነው፡፡
ግጥሞች
መነባነቦች
ከዚያም ከዚህ
እናስተዋውቃችሁ
፡ ጭውውት
ድራማ.... ወዘተ
ለሀሳብ @ty1921 ይጠቀሙ
ግጥሞች
መነባነቦች
ከዚያም ከዚህ
እናስተዋውቃችሁ
፡ ጭውውት
ድራማ.... ወዘተ
ለሀሳብ @ty1921 ይጠቀሙ
✞#ኧረ_አልሆንልኝም_አለ✞
/ድንቅ የንስሐ መነባንብ/
ኧር አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ፤
የጭንቅ አማላጅቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?
ጸሎት ምህላ አቃተኝ መንፈሴ ለንሰሐ ሸፈተ፤
መንጸፈ ደይን ወደቅኩኝ ነፍሴ በኃጢአት ሸፈተ።
እምቢ አለኝ ፆም ጸሎት እምቢኝ አለኝ ንስሐ፤
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኘ ከዓለም ውሃ።
ኧር አንድ በይኝ እመቤቴ ወለላይቱ ተማለጂኝ፤
ጨርሶ ዓለም ሳይነጥቀኝ ከወደኩበት አንሺኝ።
ነጭ ነጠላ አጣፍቼ ከቤተ መቅደስ ስወጣ፤
መጽሐፍ ቅዱስ ዘርግቼ ለስብከት መድረክ ስወጣ፤
ልብሰ ተክህኖ ለብሼ ንፍቅ ገባሬ ሰናይ ስሆን፤
ጥቅስ በቃሌ ስደረድር ለዜማ ቅኔ ስቀኝ፤
አካሌ እዚህ ሆኖ መንፈሴ እየሸፈተ፤
ነፍሴን በኃጢአት ገንዞ ስጋዬ ነፍሴን ጎተተ።
ኧር አንድ በይኝ እመብርሃን ወለላይቱ ተማለጂኝ፤
ጨርሶ ዓለም ሳይነጥቀኝ ከወደኩበት አንሺኝ።
ማለዳ ኪዳን አድርሼ ቅዳሴ ጸሎት ጨርሼ፤
ከቤተክርስቲያን ወጥቼ ወደ ስጋ ገቢያ ተመልሼ፤
በኃጢአት ባህር ስዋኝ የግፍ ዳንኪራ ስረግጥ እውላለሁ፤
የልጅነት ፀጋዬን አውጥቼ ብኩርናዬን እሸጣለሁ።
እዚህ መልአክ መስዬ ላዬ በቅድስና በርቶ፤
ውጪ ከክፋት ከፍቼ ኃጢአት በጽድቄ ተተክቶ፤
በሀሜት የሰው ስጋ ስበላ በወንድሜ ሸር ስሸርብ፤
ስዋሽ ስቀጥፍ ውዬ ስሰርቅ ሳሽሟጥጥ ስሳደብ፤
ነጠላ ስለብስ ግን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ስገባ፤
ሰዓሊለነ ቅድስት ስል ያለ ንስሐ እንባ፤
የመውደቂያዬ ጉድጓድ ጥልቀቱ ወሰን ዳርቻ የለውም፤
እዝነ ህሊናዬ ለዓለም እንጂ ለጽድቅ ቦታ የለውም፤
መሃረነ ክርስቶስ እንዳልል ተዘከረነ ፈጣሪዬ፤
ኃጢአት በደሌ አፈነኝ በሀፍረት ነደደ ህሊናዬ፤
ምን ብዬ ልጥራው ጌታዬን ተዘከረነ ብዬ።
ስለእኔ መገረፉን የመስቀሉን ፍቅር አቃልዬ፤
እንዴት ማረኝ ልበለው ስለ ስጋ ጣዕም ተቃጥዬ።
ምን ብዬ ልጥራው ጌታዬን?
ዓይኔን ወደ ፀፍፀፈ ሰማይ ወደ ሥላሴ መንበር፤
አንስቼ ማየት አቃተኝ ማረኝ ብዬ ለመናገር።
ለሰው ጻድቅ መስዬ የኃጢአት ጎተራ ሆኛለሁ፤
እንዴት አባቴ ቀና ብዬ መንበረ ጸባኦትን አያለሁ።
እባክሽን እናቴ ወለላይቱ ተማለጂኝ፤
እንደቃና ዘገሊላ ባዶ ማድጋዬን ሙዪልኝ።
ከፊቱ እንዳላፍር ከአማኑኤል ጋር አስታርቂኝ፤
ለተጠማ ውሻ እንዳዘንሽ ለመጻተኛው እዘኚልኝ።
አንቺ የትሁታን ትሁት ርህሪይተ ልብ እናቴ፤
ከልጅሽ ከኢየሱስ አማልጂኝ እዘኚ ለእኔም እመቤቴ።
አንቺ ውዳሴሽ የነፍስ ስንቅ ስምሽ ከማር የጣፈጠ፤
በላኤሰብዕ በእፍኝ ውሃ በምልጃሽ ከሞት ያመለጠ።
አንቺ መላእክት የሚጎበኙሽ የካህናት አለቆች ምስጋናቸው፤
በመወሰን የማይወሰን እሳተ መለኮትን የቻልሽው።
አንቺ ከገነት በተሰደደ ጊዜ ለአዳም ተስፋ የሆንሺው፤
ዛሬም ለእኔም ተስፋ ሁኚኝ ለነፍሴ ስለነፍሴ ተዋሺው።
እንጂ እኔማ አልቻልኩም የልቤ ንጽህና ጠፍቷል፤
ለጸሎት እንኳን ስቆም ልቤ ለሁለት ተከፍሏል፡፡
ኧረ አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ፡፡
የጭንቅ አማላጂቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?
እምቢ አለኝ ፆም ጸሎት እምቢኝ አለኝ ንስሐ፤
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኘ ከዓለም ውሃ።
የልቤን መወላወል የነፍሴን ድካም አበርቺ፤
በአማላጅነትሽ ስር ነኝ እና ከልጅሽ አስታርቂኝ አንቺ።
ለሰው ዓይን ባይገለጥም ሰውሬ የሰራሁት ኃጢአት፤
አምላክን አሳዝኖታል የምኖርበት ሕይወት፤
ይኸው የምናገረው አይሰምር የወረወረኩት አይመታም፤
ስጋዬ አልተቀደሰ ገበታዬ በረከት የለውም፤
ዕውቀት ምርምር አይዘልቀኝም ህሊናዬ ፍሬ አይቋጥር፤
ዝርው ሆኖብኝ ቀርቶ የነፍስ የስጋዬ ምስጢር።
ይኸው የማወራው ለሰው አይጥም ፍቅር ከእኔ ቤት ርቋል፤
መቆም መቀመጤ አያምርም ሰው በስራዬ ይማረራል፤
የኃጢአት ምንዳዬ ይኸው የኃጢአት ደሞዜ ይኸው ስቃዬ ውስጤን በልቶታል፤
ለአንድነት የተናገርኩት ዛሬም ጉባኤ ይበትናል።
እና አዛኝቱ ታረቂኝ ከልጅሽ ከአማኑኤል አማልጂኝ፤
ከሰው የሸሸግኩት ኃጢአት ጨርሶ በልቶ ሳይውጠኝ።
የበላኤሰብዕ እመቤት እባክሽን ተማለጂኝ፤
አንቺ ሕይወቴን ዳብሺው ነፍሴ ዕረፍት እንድታገኝ።
ኧረ አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ፤
የጭንቅ አማላጅቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?
ጸሎት ምህላ አቃተኝ መንፈሴ ለንሰሐ ሸፈተ፤
መንጸፈ ደይን ወደቅኩኝ ስጋዬ ነፍሴ ሸተተ።
እምቢ አለኝ ፆም ጸሎት እምቢኝ አለኝ ንስሐ፤
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኘ ከዓለም ውሃ።
ኧረ አንድ በይኝ እመቤቴ ወለላይቱ ተማለጂኝ ጨርሶ አለም ሳይነጥቀኝ ከወደኩበት አንሺኝ።
እባክሽን ተማለጂኝ እናቴ ኪድሀነ ምህረት
ተስፋ ክብራችን አንቺ ነሽ
#ሰአሊለነ_ቅድስት 😭🤲🤲🤲
#ሰአሊለነ_ቅድስት 😭🤲🤲🤲
#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
@kinexebebe

፨ጨረስኩ ሳልጀምረው፨ 📝✏️
ከፊደላት ተራ ከሆህያት ገብቼ
ክብርሽን ለመግለጽ አሙልቼ አስፍቼ
አበው ሲናገሩ ስላንቺ ሰምቼ
ቃላትን ከቃላት መርጬ አሳክቼ።
<ሀ>ብዬ ጀመርኩኝ ልናገር ጸጋሽን
መጽሐፍ ከሚለው በልቢም ያለውን
አባቶች ቅዱሳት ያስተላለፉትን
በሕይወት ከነሱ የተቀበልኩትን።
ከነ<ሀ> ነጎርቤት ከነ <ለ> አዝማዳት
በሰባት በሰባት ከተከፋፈሉት
ከላይ እስከታች የተደረደሩት
እስከነ <ፐ >ድረስ ከተሰበሰቡት።
ያንንም ሳወጣው ይንንም ስመዘው
ጥንት የመረጥኩትን መልሼ ስተወው
ፊት ያስገባሁትን ኃላ ስመልሰው
አንዱን አስገብቼ ሌላውን ሳወጣው
ፈጽሜአለሁ ብዬ የፃፍኩትን ሳየው
ድንግል ውዳሴሽን ጨረስኩ ሳልጀምረው
@kinexebebe
ከፊደላት ተራ ከሆህያት ገብቼ
ክብርሽን ለመግለጽ አሙልቼ አስፍቼ
አበው ሲናገሩ ስላንቺ ሰምቼ
ቃላትን ከቃላት መርጬ አሳክቼ።
<ሀ>ብዬ ጀመርኩኝ ልናገር ጸጋሽን
መጽሐፍ ከሚለው በልቢም ያለውን
አባቶች ቅዱሳት ያስተላለፉትን
በሕይወት ከነሱ የተቀበልኩትን።
ከነ<ሀ> ነጎርቤት ከነ <ለ> አዝማዳት
በሰባት በሰባት ከተከፋፈሉት
ከላይ እስከታች የተደረደሩት
እስከነ <ፐ >ድረስ ከተሰበሰቡት።
ያንንም ሳወጣው ይንንም ስመዘው
ጥንት የመረጥኩትን መልሼ ስተወው
ፊት ያስገባሁትን ኃላ ስመልሰው
አንዱን አስገብቼ ሌላውን ሳወጣው
ፈጽሜአለሁ ብዬ የፃፍኩትን ሳየው
ድንግል ውዳሴሽን ጨረስኩ ሳልጀምረው
@kinexebebe
#እናስተዋውቃቹ
#ቅዱስ_ሚናስ (#ማር_ሚና)
ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) በምድረ ግብጽ ተወዳጅ ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው። በግብጻውያን ልዩ ቦታ አለው ማር ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም። ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ ነው። በተለይ ለታመመ ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ ደራሽ ባለ በጎ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው።
ቅዱስ ሚናስ ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው። በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች ልጅ፣ በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ፣ በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ፣ ሃብትን ክብርን ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት የተወሰነ፣ በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ በአላውያን ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ ህዳር 15 በሰማዕትነት ያረፈበት ሲሆን ሰኔ 15 ደግሞ ቤተ ክርስቲያኑ መርዩጥ በተባለ አገር የከበረችበት ነው።
#በአንድ_ወቅት፦
ዐሥራ ስምንት ቀሳውስት በሥራ ጉዳይ አቡነ ቄርሎስ ፮ኛን ለማነጋገር መርዩጥ ወደ ሚገኘው የቅዱስ ሚናስ ገዳም ጉዞ ጀመሩ። ቀሳውስቱ በጉዞአቸው መንገድ ስተው ሲባዝኑ ከአንድ የበረሓ ሰው ጋር ተገናኙ።
የበረሓው ሰው መርዩጥ የሚገኘው የቅዱስ ሚናስ ገዳም ለመሄድ መንገድ እንደሳቱ ቀድሞ ተረድቶ ነበርና "የማር ሚናስን ገዳም ነው የምትፈልጉት? በማለት ይጠይቃቸዋል። እነርሱም ችግራቸውን እንዴት እንዳወቀ በልባቸው እያደነቁ "አዎን" አሉት። የበረሓው ሰውም እየመራ ከገዳሙ አደረሳቸው አቡነ ቄርሎስ ፮ኛም ወደ በር ወጥተው ተቀበሏቸው።
ከዚያም "ምነው ዘገያችሁ? መንገድ ሳታችሁ እንዴ?" ብለው እንደ ቀልድ ጠየቋቸው። እነርሱም "አዎን! በጣም ተቸግረን ሳለን ይህ የበረሓ ሰው ደርሶልን መንገዱን አሳየን" ብለው ወደ ሰውየው ለማመልከት ዘወር ሲሉ እርሱ በአካባቢው የለም። አቡነ ቄርሎስም "መንገድ እንደጠፋችሁ ስለተረዳሁ ሚናስን ልኬላችሁ ይዟችሁ የመጣው እርሱ ነው" አሏቸው።
አምላካችን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከትን ይክፈለን!!

እግዚአብሔር እረስቶኛል አትበል
ትርጉም ገብረእግዚአብሔር ኪደ
እግዚአብሔር እረስቶኛል አትበል!
ስሙት ታተርፉበታላችሁ...
ስሙት ታተርፉበታላችሁ...
አሮጌውን ሰው አስወግዱ
ገብረእግዚአብሔር ኪደ
አሮጌውን ሰው አስወግዱ
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Audio
➕እምነት እንደ ቅቤ➕
(መንፈሳዊ ትረካ)
(መንፈሳዊ ትረካ)
+++ድንቅ ልዩነት ተመልከቱ+++
በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ፈርዲናንድ ማጄላን ዓለምን በመርከብ ዞረ።
👉ሐዋርያቱ ደግሞ መርከባቸውን ጥለው ዓለምን ዞሩ!
ዛሬ ይዘንባል እያሉ ትንቢት የሚተነብዩ ሜትሮሎጂስቶች ሞልተዋል።
👉እንደ ኤልያስ ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን የዘጋ ዳግመኛም ዝናብን ያዘነበ ከቶ የለም።
በላብራቶሪው ተመራምሮ ህሙማንን የፈወሰ ሞልቷል።
👉እንደ ጴጥሮስ ጥላው ድውይ የፈወሰ ከቶ አላየሁም።
በዘፈኑ አጋንንትን የጠራ እንደ ማይክል ጃክሰን ሞልቷል።
👉እንደ ዳዊት በበገና መዝሙሩ አጋንንትን ያስወጣ እስከ ዛሬ አልተገኘም።
ከረቫትና ሱፉን ለብሰን የምንጎራደድ ሞልተናል።
👉የልብሱ ቁጨት አጋንንት ያስወጣ እንደ ጳውሎስ ከቶ አልተገኘም።
የግብጽ ነገሥታት አጽማቸው በክብር ይቀመጣል።
👉ዐጥንቱ ሙት ያስነሳ እንደ ኤልሳዕ ከቶ አላየንም።
በአሜሪካ የነገሥታትን ምሥጢር የሚሰልሉ ድርጅቶች ሞልተዋል።
👉እንደ ኤልሳዕ በእስራኤል ሆኖ በሶሪያ ቤተመንግሥት የሚደረገውን ምሥጢር ያወቀ አልተገኘም።
ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃን በእግሩ የረገጠ ዩሪ ጋጋሪ ዛሬ ብዙዎቹ አድርገውታል።
👉እንደ ኢያሱ ፀሐይን ያቆመ ከቶ አልተገኘም።
በነገራችን ላይ በተፈጥሮ ሕግ መሰረት ፀሐይ በመሃል ቆማ መሬት ዙሪያውን ትዞራለች። በፀሐይ ፊት ያለው የመሬት ክፍል ቀን ሲሆን ሌላኛው ጎን ደግሞ ማታ ይሆናል።
እነ ኢያሱ በሚዋጉበት ጊዜ መሬት ከፀሐይ ፊቷን አዙራ ቀኑ ሊጨልም ነበር።
👉ኢያሱ ግን መሬት እንዳትዞር አደረጋት! ፀሐይን በገባኦን አቆመ ተባለ! መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ
ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም።
👉 እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበርና ((እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።))
የዓለም መሪዎች ከአስር በላይ ቋንቋ መናገራቸውን እንጃ፤
👉ሐዋርያቱ ግን 72 ቋንቋ ተገለጠላቸው።
ኃያላን ነገሥታት ድውይ እንኳን መፈወስ አይችሉም።
👉ቅዱሳኑ ግን የ70 የ80 ዘመን ሬሳ አስነሱ።
👉ጠቢባን ነን የሚሉ ጸሐፍት ፈሪሳዊያንን ምላሽ ያሳጣቸው ዘንድ ጥበብ ያልነበራቸውን ዓሳ ወጋሪ የነበሩ ሐዋርያትን መረጠ።
ኃያላን ነገሥታት የመሰሉ መሪ ዳዊትን የመሰሉ ነገሥታትን የወለዱ የከበሩ እናቶች ሞልተዋል።
👉የነገሥታትን ንጉሥ ክርስቶስን የወለደች እናት ግን አንድ ብቻ ናት።
ይህችውም ከሴቶች መካከል ተለይታ የተባረከችው ድንግሊቱ 👉 ማርያም ናት 👈
ስብሐት ለእግዚአብሔር!

✝እንኳን አደረሰን!✝
☞በእንተ #እግዝእትነ #ማርያም ድንግል፤
ወበእንተ #ኢየሱስ #ክርስቶስ ወልዳ ፍቁር፤
☞ዝክሩ ስመ አበዊነ ቅዱሳን #ነቢያት #ሙሴ #ወአሮን #ዳዊት #ወሰሎሞን #ዕዝራ #ወዘካርያስ እለ አውኃዙ ተነብዮ በእንተ አማናዊት #እምነ #ጽዮን፡፡
"" ጸጋ ዘአብ ፥ ኂሩት ዘወልድ ሱታፌ ዘመንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ፡ ወበረከታ ለእምነ #ጽዮን_ማርያም ፡ ተፋቅሮ #ዘነቢያት #ወዘሐዋርያት ወዘአበው ቀደምት ቅዱሳን ፡ ወትረ የኀሉ ምስሌየ ወምስለ ኩልክሙ፡፡ አሜን፡፡ ""
https://www.tgoop.com/kinezebebe

እንኳን ለጽዮን ማርያም ማሕደረ አምላክ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በየዓመቱ ኅዳር ፳፩ ቀን በታቦተ ጽዮን የተፈጸሙ ታላላቅ ተአምራት የሚታሰቡበት ቀን ነው፡፡ በዚህ ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የታቦተ ጽዮንን ተአምራት እግዚአብሔር ቃል ቅድስት ድንግል ማርያምን ታቦቱ አድርጎ ከፈጸማቸው ታላላቅ የድኅነት ሥራዎች ጋር በማነጻጸር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በነገረ ድኅነት ውስጥ ያላትን ድርሻ በስፋት ታስተምራለች፡፡
ለምሳሌ እስራኤላውያን ባሕረ ዮርዳኖስን በአቋረጡበት ወቅት ታቦተ ጽዮንን የተሸከሙ ካህናት እግራቸው የዮርዳኖስን ባሕር በመንካቱ ባሕሩ ለሁለት ተከፍሎ ነበር፡፡ ይህንን ታሪክም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ በመወለድና ጥምቀትን በመመሥረት ከሰይጣን ባርነት ወደ እግዚአብሔር ልጅነት እንዳሸጋገረን በማመሥጠር ቤተ ክርስቲያናችን ታስተምርበታለች፡፡ ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤላውያን ጋር ውጊያ በገጠሙበት ወቅት ታቦተ ጽዮንን ከእስራኤላውያን ማርከው ዳጎን በሚባለው ቤተ ጣዖታቸው ውስጥ አኑረዋት በነበረ ጊዜ ታቦቷ የዳጎንን ምስል አንኮታኩታ ጥላው ነበር፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ይህን ታሪክ እንደ ምሳሌ በመጠቀም ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደው በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ከአምልኮ ጣዖት ወጥተን አንድ አምላክን ወደ ማምለክ ስለ መመለሳችንና በእመቤታችን ምክንያት ስለ ተደረገልን የእግዚአብሔር ቸርነት ትምህርት ትሰጥበታለች፡፡
እኛም በዛሬው ዘግጅታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማናዊቷ ታቦተ ጽዮን መኾኗን የሚያስቃኝ ትምህርት ይዘን ቀርበናል፤ እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ካወጣቸው በኋላ የአምልኮ ሥርዐታትን ይፈጽሙበት ዘንድ የምስክሩን ድንኳን፣ የቃል ኪዳኗ ታቦትንና ለአምልኮ ሥርዐቱ ማከናወኛ የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ንዋያተ ቅድሳትን እንዲሠሩ አዝዟቸው ነበር፡፡ ከቃል ኪዳኗ ታቦት ውስጥም በእግዚአብሔር ጣት ዐሥርቱ ትእዛዛት የተጻፉበት የሕጉ ጽላት፤ ዐርባ ዓመት ሙሉ እስራኤላውያን በሲና ምድረ በዳ የተመገቡትን መና የያዘች መሶበ ወርቅ፤ አሮን ለክህነት አገልግሎት ስለ መመረጡ ምስክር የኾነችው፣ ለምልማና ፍሬ አፍርታ የተገኘችው የአሮን በትር ይገኙባታል /ዕብ.፱፥፬/፡፡ ደብተራ ድንኳኗንና በውስጧ የሚገኙ ንዋየተ ቅድሳትን እግዚአብሔር በሙሴ ሲያሠራ ለሰማያዊው ምሥጢር ምሳሌና ጥላ ናቸውና ተጠንቅቆ እንዲሠራቸው አዝዞት ነበር /ዕብ.፰፥፭/፡፡
ቅዱስ ጳውሎስም ይህችን ድንኳን ‹‹የአገልግሎት ሥርዐታት የሚፈጸምባት ፊተኛይቱ ድንኳን›› ብሎ ይጠራታል፡፡ በዚህ መሠረት ደብተራ ድንኳኗና በውስጧ ያሉ ንዋያተ ቅድሳት ለሰማያዊው ምሥጢር ምሳሌና ጥላ እንደ ኾኑ እንረዳለን፡፡ የደብተራ ድንኳኗ ምሳሌ የኾችው ሰማያዊቱ ስፍራም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ በውስጧ አማናዊውና ሰማያዊው ምሥጢረ መለኮት ይፈጸምባታልና፡፡ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካሉ ስለ ኾነች፤ ዘለዓለማዊ ሕይወትን የሚያሰጥ ምሥጢርም በውስጧ ስለሚከናወንባት በእርግጥም ሰማያዊ ስፍራ ናት፡፡ ታቦተ ጽዮን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትመሰላለች፡፡ ይህን ለመረዳት ግን ስለ ታቦተ ጽዮን አሠራርና መንፈሳዊ ትርጉም አስቀድመን ልንረዳ ይገባናል። እግዚአብሔር አምላክ ታቦተ ጽዮንን እንዲሠራ ብልሃትን፣ ጥበብን፣ ማስተዋልን፣ ዕውቀትን ይለይ ዘንድ መንፈሱን ያሳደረበትን ከይሁዳ ወገን የኾነውን ባስልኤልን መረጠ /ዘፀ.፳፭፥፱/፡፡ እርሱም እግዚአብሔር በሰጠው ማስተዋል ከማይነቅዝ እንጨት ርዝመቷ ሁለት ክንድ ተኩል፤ ወርዱዋ አንድ ክንድ ተኩል፤ ቁመቷ አንድ ክንድ ተኩል እንዲኖራት አድርጎ ታቦቷን ሠራት፡፡
በመቀጠል በውስጥም በውጪም በጥሩ ወርቅ ለበጣት፣ ከታቦቷም ዙሪያ የወርቅ አክሊልን አደረገላት፡፡ ካህናት ታቦተ ጽዮንን ለመሸከም እንዲረዳቸውም በአራቱም መዓዘናት በወርቅ የተሠሩ ቀለበቶችንና በእነርሱም ውስጥ የሚገቡ ሁለት መሎጊያዎችን ሠራ፡፡ ከጥሩ ወርቅም የስርየት መክደኛውን በቃል ኪዳን ታቦቷ ላይ በርዝመቷና በወርደዋ ልክ ሠራ፡፡ የስርየት መክደኛውን እንዲጋርዱት አድርጎም ጥሩ ከኾነ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ኪሩቤልን ሥሎ በስርየት መክደኛው ግራና ቀኝ አስቀመጣቸው፡፡ እነዚህ በጥሩ ወርቅ የተሠሩት ሁለቱ ኪሩቤል ፊታቸው ወደ ስርየት መክደኛው ኾኖ እርስ በእርሳቸው እንዲተያዩ ተደርገው የተሠሩ ናቸው፡፡ በዚህ በስርየት መክደኛው በሁለቱ ኪሩቤል መካከል እግዚአብሔር ለሙሴ እየተገለጠ ሰው ከባልንጀራው ጋር እንደሚነጋገር በግልጽ ያነጋግረው ነበር፤ ለሕዝቡም በደመና ዐምድ ይታያቸው ነበር /ዘፀ.፰፥፲፩፤ ፳፭፥፳፪-፴፫/፡፡
ወደ ምሥጢሩ ትርጓሜ ስንመለስም ታቦተ ጽዮን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ስትኾን፣ በውስጧ የያዘችው የሕጉ ጽላትም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቷ ከማይነቅዝ እንጨት መሠራቷ የእመቤታችንን ንጽሕና የሚያመለክት ሲኾን፣ በውጪም በውስጥም በጥሩ ወርቅ መለበጧ ደግሞ ቅድስናዋንና በሁለት ወገን ድንግል መኾኗን የሚያስረዳ ነው፡፡ ታቦተ ጽዮን በግራና በቀኝ በኩል በተዘጋጁ አራት ከወርቅ የተሠሩ ቀለበቶች ነበሯት፤ በእነዚያ የወርቅ ቀለበቶች ውስጥም ሁለት መሎጊያዎች ይገቡባቸው ነበር፡፡ ታቦቷን ለማንቀሳቀስ ባስፈለገ ጊዜ አራት ሌዋውያን ካህናት በመሎጊያዎቹ ይሸከሟታል፡፡
ይህ ሥርዐት በሰማያትም የሚታይ እውነታ ነው፡፡ የጌታን መንበር ገጸ ሰብእ፣ ገጸ ንሥር፣ ገጸ ላህምና ገጸ አንበሳ ያላቸው አርባዕቱ እንስሳት ይሸከሙታልና /ኢሳ.፮፥፩-፭፤ ሕዝ.፩፥፩-፲፮/፡፡ ለአማናዊቷ ታቦት ለቅድስት ድንግል ማርያምም ሰላምን የሚያወሩ፣ መልካም የምሥራችንም የሚናገሩ፣ መድኀኒትንም የሚያወሩ፣ ጽዮንንም ‹‹አምላክሽ ነግሦአል›› የሚሉ፣ እግሮቻቸው በተራሮች ላይ እጅግ ያማሩ የእርሷንና የጌታችንን ስም ተሸክመው ወንጌልን ለዓለም የሚሰብኩ ኦርቶዶክሳውያን መምህራን አሏት /ኢሳ.፶፪፥፯/፡፡ የስርየት መክደኛው መቀመጫው የንጹሐን አንስት፣ መክደኛው የንጹሐን አበው፣ ግራና ቀኙ የሐናና የኢያቄም ምሳሌ ነው፡፡ በክንፎቻቸው የጋረዱት ኪሩቤልም የጠባቂው መልአክ ቅዱስ ሚካኤልና የአብሣሪው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ምሳሌዎች ናቸው፡፡
የስርየት መክደኛው ስርየቱ የሚፈጸምበት ስፍራ ቢኾንም ነገር ግን በዚህ ቦታ ምንም ዓይነት መሥዋዕት አይቀርብም ነበር፡፡ ይህም በጊዜው አማናዊው መሥዋዕት ገና እንዳልተሠዋ ያስገነዝበናል፡፡ ይህ ስፍራ እግዚአብሔር ለሙሴ የሚገለጥበት ቦታ ነው፤ ከእርሱ ውጪ ሌላ ነገር በእዚያ ላይ ማረፍ አይችልም ነበር፡፡
ከዚህም የምናስተውለው አንድ ምሥጢር አለ፤ ይኸውም እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም የገባውን ቃል ኪዳን ሊፈጽም ሰው በኾነ ጊዜ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብበት ልዩ ስፍራ እንዳዘጋጀ ያመላክተናል፡፡ ይህ ስፍራ አማናዊ መሥዋዕት የሚቀርብበት ቦታ እንደሚያስፈልግ የሚያስገነዝብ ስፍራ ነው፡፡ ይህን ለማመልከትም ለኃጢአት ስርየት የቀረበው መሥዋዕት ከታረደ በኋላ ካህኑ ደሙን በጣቱ እየነከረ ሰባት ጊዜ በስርየት መክደኛው አንጻር በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ይረጨው ነበር /ዘሌ.፬፥፮/፡፡ ነገር ግን ይህ ደም ከስርየት መክደኛው ላይ አያርፍም ነበር፤ ምክንያቱም በዚህ ስፍራ መቅረብ የሚገባው አማናዊው መሥዋዕት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነውና፡፡

ይህ የስርየት መክደኛ ለእኛ የሚያስተላልፈው ተጨማሪ መልእክትም አለው፡፡ ይኸውም አማናዊው መሥዋዕት ክርስቶስ መሥዋዕት ኾኖ ዓለምን ማዳኑ እንደማይቀርና መሥዋዕቱ የሚቀርብበት ስፍራም በቅድስተ ቅዱሳኑ (ቤተ መቅደሱ) ውስጥ እግዚአብሔር በምሕረት በሚገለጥበት በቃሉ ማደሪያ በጽላቱ ላይ መኾን እንደሚገባው ያስገነዝበናል /ዕብ.፬፥፲፮/፡፡ ይህም እግዚአብሔር አምላክ በነቢዩ ሚልክያስ ላይ አድሮ ‹‹ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይኾናልና በየስፍራውም ስለ ስሜ ዕጣንን ያጥናሉ፤ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፤›› /ሚል.፩፥፲፩/ በማለት እንደ ተናገረው የስርየት መክደኛው አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሥጢረ ቍርባንን ለምትፈጽምበት ጽላት ወይም ታቦት ምሳሌ መኾኑን ያሳየናል፡፡
የስርየት መክደኛውን የሚጋርዱት በጥሩ ወርቅ የተሠሩት የኪሩቤል ምስሎችም አማናዊው መሥዋዕት በሚሠዋበት ጊዜ በዙሪያው ረበው የሚገኙ የመላእክት ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችን እንዳስተማሩን ሁለቱ ኪሩቤል የተባሉት ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ናቸው፡፡ ይህን ለማስገንዘብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በመንበረ ታቦቱ ላይ ምስለ ፍቁር ወልዳ እንዲቀመጥ ታዝዛለች፡፡ ምስለ ፍቁር ወልዳን ላስተዋለ ሰው በትክክል የታቦተ ጽዮንን መንፈሳዊ ትርጕም ይረዳል፡፡
ታቦተ ጽዮን ከሌሎች የብሉይ ኪዳን ንዋያተ ቅድሳት በተለየ መልኩ እጅግ ግሩም የኾነ ምሥጢርን በውስጧ ይዛለች፡፡ ይህን ድንቅ ምሥጢር ለመረዳትም አንድ ምሳሌ እንመልከት፤ ንጉሥ ዳዊት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑ ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ጽዮን ከተማ ባስመጣበት ወቅት በታቦቷ ፊት በሙሉ ኃይሉ በደስታ እየዘለለ ለእግዚአብሔር መንፈሳዊ መዝሙርን አቅርቦ ነበር /፪ሳሙ.፮፥፲፪-፲፯/፡፡ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሚኾን ድርጊት በሐዲስ ኪዳንም ተፈጽሟል፡፡ ይኸውም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለቅድስት ኤልሳቤጥ ሰላታ በሰጠቻት ጊዜ የስድስት ወር ፅንስ የነበረው ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የእመቤታችንን የሰላምታ ድምፅ በሰማ ጊዜ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ኾኖ በደስታ ዘሏል (ሰግዷል) /ሉቃ.፩፥፵፬/፡፡ ቅዱስ ዳዊት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት እየተደሰተ ለአምላኩ የምስጋና ቅኔን መቀኘቱም ለሰው ልጆች ዅሉ የመዳናችን ምክንያት የኾነችውን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን በቃል ኪዳኗ ታቦት በኩል አስቀድሞ በዓይነ ሕሊና ስለ ተመለከታቸው ነበር፡፡
ዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

#ጎጆ_ቀለስኩልህ
(በሰመረ ፍስሃ)
በአውላላ ሜዳ በጠራራ ፀሐይ
ከአስፓልቱ አጠገብ ስኖር ጎዳና ላይ
የበጋውን ንፋስ በዙሪያዬ ከቦኝ
እንደ ዥዋዥዌ ወዲያ ሲወስደኝ፡፡
...................ወዲህ ሲመልሰኝ
ዝናቡ በተራው ጉዴን ተመልክቶ
...................ጉድፌን አፅድቶ
ይወደኝ ይመስል ልብሴን ያጥብልኛል
ጎጆዬን አፈራርሶ በብርድ ይገርፈኛል፡፡
ከዚህ የባሰ ግን ሰዉ ነው 'ሚገርመኝ
በነጋ በጠባ መተንፈሻ ያሳጣኝ፡፡
ስለተናገርኩኝ ማጣት መከፋቴ
የእውነት ስለኖርኩኝ ውሸትን ጠልቼ
አፋቸውን ሞልተው እብድ ነው ይሉኛል
አንዳንዴ ሲያሻቸውም ድሃ ነው ይሉኛል፡፡
የሆነው ሆነና ቅር አላለኝም
አጣሁኝ ብዬም አላማረርኩም
ጌታ እንዳስተማረኝ ለበጎ ነው ብዬ
የማይቻል የለም እኖራሎህ ችዬ፡፡
ይሄውልህ ግን ሚካኤል ሆይ...
የሰው ልጅ ሲሸሸኝ ማንነቴን አይቶ
ሰላምታ ሲነፍገኝ ኑሮዬን ተመልክቶ
አንተ ግን አንተ ነህ የአምላክ መልእክተኛ
ሁሌ 'ምትጠብቀኝ መቼም የማተኛ፡፡
ምንም ሳይገድብህ ከቤቴ ገብተሀል
ድሃዋን ጎጆዬ በፍቅር ጎብኝተሀል፡፡
እናም ሚካኤል ሆይ....
ከኔ እንዳትርቅ ስለሳሳሁልህ
በንፁህ ልቤ ውስጥም ጎጆ ቀለስኩልህ፡፡
@kinexebebe
(በሰመረ ፍስሃ)
በአውላላ ሜዳ በጠራራ ፀሐይ
ከአስፓልቱ አጠገብ ስኖር ጎዳና ላይ
የበጋውን ንፋስ በዙሪያዬ ከቦኝ
እንደ ዥዋዥዌ ወዲያ ሲወስደኝ፡፡
...................ወዲህ ሲመልሰኝ
ዝናቡ በተራው ጉዴን ተመልክቶ
...................ጉድፌን አፅድቶ
ይወደኝ ይመስል ልብሴን ያጥብልኛል
ጎጆዬን አፈራርሶ በብርድ ይገርፈኛል፡፡
ከዚህ የባሰ ግን ሰዉ ነው 'ሚገርመኝ
በነጋ በጠባ መተንፈሻ ያሳጣኝ፡፡
ስለተናገርኩኝ ማጣት መከፋቴ
የእውነት ስለኖርኩኝ ውሸትን ጠልቼ
አፋቸውን ሞልተው እብድ ነው ይሉኛል
አንዳንዴ ሲያሻቸውም ድሃ ነው ይሉኛል፡፡
የሆነው ሆነና ቅር አላለኝም
አጣሁኝ ብዬም አላማረርኩም
ጌታ እንዳስተማረኝ ለበጎ ነው ብዬ
የማይቻል የለም እኖራሎህ ችዬ፡፡
ይሄውልህ ግን ሚካኤል ሆይ...
የሰው ልጅ ሲሸሸኝ ማንነቴን አይቶ
ሰላምታ ሲነፍገኝ ኑሮዬን ተመልክቶ
አንተ ግን አንተ ነህ የአምላክ መልእክተኛ
ሁሌ 'ምትጠብቀኝ መቼም የማተኛ፡፡
ምንም ሳይገድብህ ከቤቴ ገብተሀል
ድሃዋን ጎጆዬ በፍቅር ጎብኝተሀል፡፡
እናም ሚካኤል ሆይ....
ከኔ እንዳትርቅ ስለሳሳሁልህ
በንፁህ ልቤ ውስጥም ጎጆ ቀለስኩልህ፡፡
@kinexebebe
+++እንኳን አደረሰን+++
ዱራ ሜዳ አድምጭ፥ ንጉስ ሆይ ስማ፤
መለከት ቢጮህ፥ አዋጅ ቢሰማ።
እንኳን አድኖን፥ ባያድንንም፣
አንተ ላቆምከው፥ ምስል አንሰግድም።
፡
ፍሙ እየጋለ ፥እጥፍ ቢነድ፤
ገብርኤል መጣ፥ እሳት ሊያበርድ።
እንደ ንጉስ፥ ልጅ ተመላለሱ፤
እሳቱን ውሀ፥ አርጎት ቅዱሱ።
፡
ሰልስቱ ደቂቅ፥ ሞትን ሳፈሩ፤
ነበልባል መሀል፥ በእምነት ዘመሩ።
ለአምላካቸው እጅ እየነሱ፤
በእሳት መካከል ተመላለሱ።
፡
አንዷን ቤታችንን፥ ሊያቃጥል ሊያነዳት፤
ሀገር እንዳልሰራች፥ ጠላት ተነሳባት።
የእሳቱን ነበልባል፥ አብርደው መላኩ፤
በቁጣህ ተመለስ፥ ተዋህዶን ለነኩ።
፡
አመቱን በሰላም፥ እንዳስጀመርከን፤
ደሞ የዛሬ አመት፥ ሰላም አድርሰን፤
+++
@kinexebebe
ዱራ ሜዳ አድምጭ፥ ንጉስ ሆይ ስማ፤
መለከት ቢጮህ፥ አዋጅ ቢሰማ።
እንኳን አድኖን፥ ባያድንንም፣
አንተ ላቆምከው፥ ምስል አንሰግድም።
፡
ፍሙ እየጋለ ፥እጥፍ ቢነድ፤
ገብርኤል መጣ፥ እሳት ሊያበርድ።
እንደ ንጉስ፥ ልጅ ተመላለሱ፤
እሳቱን ውሀ፥ አርጎት ቅዱሱ።
፡
ሰልስቱ ደቂቅ፥ ሞትን ሳፈሩ፤
ነበልባል መሀል፥ በእምነት ዘመሩ።
ለአምላካቸው እጅ እየነሱ፤
በእሳት መካከል ተመላለሱ።
፡
አንዷን ቤታችንን፥ ሊያቃጥል ሊያነዳት፤
ሀገር እንዳልሰራች፥ ጠላት ተነሳባት።
የእሳቱን ነበልባል፥ አብርደው መላኩ፤
በቁጣህ ተመለስ፥ ተዋህዶን ለነኩ።
፡
አመቱን በሰላም፥ እንዳስጀመርከን፤
ደሞ የዛሬ አመት፥ ሰላም አድርሰን፤
+++
@kinexebebe
faaruu haraa Glataan Dhiyeessaa f/taa Yoobsan mokoonon (@FaaruuTube400 ...
https://youtube.com/watch?v=FBx4zl28ayc&si=lxcD8YWj4moW5sWu

YouTube
faaruu haraa Glataan Dhiyeessaa f/taa Yoobsan mokoonon (@FaaruuTube400 @Faaruu @FaaruuDaawit
#oromo #faarfannaa_afaan_oromoo #faaruuortodoksii #ማህቶት #ethiopia #ተዋህዶ #ሰይፉ_ሾው #ሰይፉ_ፋንታሁን #ዶንኪቲውብ
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢