Telegram Web
#ከልብ፡የፈለቀ፡ዕንባ...😭

መላ ዘመኗን በኃጢአት የኖረች
የእግዚአብሔርን ሕግ ተላልፋ የሻረች
ሰውን ለማሳት በየመንገዱ የምትቀመጥ
በየ ዕለቱ ገላዋን ለዝሙት የምትሸጥ
በደል የሆነላት ለእርሷ ደስታና ሃሤት
ይህቺ ኃጢአተኛ ይህቺ ዘማይት ሴት

ዛሬ ግን ይህቺው ሴት...
ያላትን ገንዘብ ሁሉ ሰበሰበች
ውድ የሆነ ሽቱ የት እንዳለ አሰበች
በልቧም ጌታዋን መፈለግ አበዛች
በ300 ዲናር ውድ ሽቱ ገዛች
ከዚያም፡ ሮጠች ወደ ስምዖን ቤት
ጌታዋ፣ የናፈቀችው፣ እርሱ ወዳለበት።

ጌታም ትግባ ብሎ እንዳለፈች
ከጌታ እግሮች ሥር ተደፋች
ዓይኗ የሞቀ የዕንባ ጅረት አወረደ 😭
የሚያቃጥል ትኩስ ዕንባ ከቶ ያልበረደ

በዕንባ ያራሰች እግሩን በፀጉሯ ጠረገች
ከእግሮቹ ቀና ማለትን አልፈለገች
የቀድሞ ፈ ውኃ የሚያርስ💦
ምን ብታነባ ነው እስከ ምን ድረስ?

ለምጻሙ ስምዖን እንዳትገባ ቢከለክላት
ይሁዳም ስለ ሽቱው አንድ ነገር ቢላት
እርሷ ዝም ብላለች ጌታ ነውና የሚናገርላት።

እኔስ ዘላለሜን በበደል በኃጢአት ምኖረው
መቼ ነዎ እንደ ማርያም ኃጢአቴን ምሽረው?😔
መች ይሆን ጌታዬን ናፍቄ ካለበት ምገባው?
ከልብ የፈለቀ ዕንባ ከፊቱ ወድቄ ማነባው?😭

ሚያዝያ 23/2016 ዓ/ም
©D.n Johannes7!
@kinexebebe
††† እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† መድኃኔ ዓለም †††

††† ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ በዚሕ ዕለት ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት::
ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::

*ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::

በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት:: በሠለስት (ሦስት ሰዓት ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት::

ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት:: ሰባት ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ::
ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ::

ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በባሕርይ ሥልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ:: በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: አሥራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት::

በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ:: (ማቴ. 27:1, ማር. 15:1, ሉቃ. 23:1, ዮሐ. 19:1)

††† ለእኛ ለኀጥአን ፍጡሮቹ ሲል ይህንን ሁሉ መከራ የታገሰ አምላክ ስለ አሥራ ሦስቱ ኅማማቱ: አምስቱ ቅንዋቱ: ስለ ቅዱስ መስቀሉ: ስለ ድንግል እናቱ ለቅሶና ስለ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስ ብሎ ይማረን::

††† መድኃኔ ዓለም ከወዳጆቹም ጸጋ ክብርን ያድለን:: 

††† "የተጠራችሁለት ለዚህ ነው:: ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና:: እርሱም ኃጢአት አላደረገም:: ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም:: ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም:: መከራንም ሲቀበል አልዛተም . . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ::" †††
(፩ጴጥ. ፪፥፳፩-፳፭)
@kinexebebe
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የልደትሽ ቀን ልደታችን ልጅሽ ደሞ ህይወታችን ነው🙏🙏🙏

እንኳን አደረሳችው ግንቦት 1
ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም

ሃና እና ኢያቄም ፣ ተግተው ቢማልዱ
የአምላክን እናት ድግልን ወለዱ
ጸሐይን የምትወልድ ፣ ጨረቃን አመጡ
ለጨለማው አለም ፣ ብርሃን አወጡ
በአንቺ የልደት ቀን ፣ እኛም ተወልደናል
ተጠምቆ ተሰቅሎ ፣ ልጅሽ አድኖናል
ካለአንቺ እማ ልደት ፣ ይሄ መች ይሆናል
እውነት በልደትሽ ፣ ልደት ተሰቶናል።

እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለአማላጃችን ለቅድስተ ቅዱሳን ለእመቤታችን የልደት በዓል አደረሰችሁ።

ፍቅሯን በልቦኖቻችን ውስጥ ታኑርብን ታጽናብን ❤️❤️

በልደቷ ለዓለም ሁሉ ድኅነትን ያስገኘች እናታችን በስደት በመከራ በጦርነት በርሃብ በስደት እና በእርዛት ላሉት ሁሉ የሰላም ፍቅርን እና አንድነትን ከልጇ አማልዳ ትላክልን። አሜን
@kinexebebe
ልደታ ለማርያም ፩🙏🙏
ከሀና ማህጸን የአዳም ተስፋ ታየች
በኀጢአት የደረቀው የሰው ህይወት በድንግል መወለድ በተስፋ ለመለመ
ጨለማው ዓለም በድንግል መወለድ ብርሃን ሆነ
የሊባኖስ ተራራ በብርሃን ተከበበ
ሊባኖስ የብርሃን መቀነት ታጠቀች
ሊባኖስ በብርሃን አጥር ታጠረች
ኢያቄም የደስታ ካባ ደረበ
ሀና የደስታ አክሊል ደፋች
የብርሃን እናት ድንግል ተወልዳለታለችናችና
የዓለም ሞት በህይወት ተቀየረ
ሰማይ ከሀና ማኅፀን ተወለደች
የሐና ማሕጸን የሰማዯ መውጫ ሆነ
የውርስ ኀጢአት ከድንግል ራቀ
ሰወች ሁሉ በውርስ ኀጢአት በሚወለዱበትን ያለውርስ ኀጢአት ንጹህ ሁና ወላዲተ አምላክ ተወለደች
ከኢያቄም አብራክ ነጭ እንቁ አበራች
ከሀና ማኅጸን ጸአዳ ርግብ ወጣች
የሀና ታሪክ ተቀየረ
ሀና የእግዚአብሔር ወልድ አያቱ ተባለች
ሰማያት ሰለሰማዯ መወለድ ዝማሬ ዘመሩ
ምድር ሰማይን በመሸከሟ እልል አለች
ሰማዯ በምድር ታየች
የአበው ተስፋ መሰረት ተጣለ
አይሁድ አፈሩ
ቤተ ክረርስቲያን የድንግልን መወለድ አበሰረች
በ5485 ዓመተ ዓለም ድንግል ተወለደች
ፀሐይ ሊወጣ ሰማይ ተገኘች
ሰማዯ ከሰው ተወልዳ ፀሐይን ወለደች
እመቤቴ በመወለድሽ የአበው ተስፋ እውን ሆነ።
የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለያችሁ🙏🙏
@kinexebebe
ዳግም ሥራኝ

በሰጠኸኝ ሳላመሰግን ባጣሁት ያማረርኩህ
ዝቅ ብዬ ሳላይ በበላዬ ያስጨነቅኩህ
በሰው ላይ ጣቴን የምቀስር
ወንድሜን በግፍ የማሳስር
አስታራቂ መስዬ የአንዱን ለአንዱ የነገርኩ
በሰላም በፍቅር ፈንታ ፀብ ጥላቻን ያፋፋምኩ
ነጠላዬን አስረዝሜ ማለዳ ከማደሪያ
ማምሻ ከሰኬም የምገኝ
ገና ነው ስል የመሽብኝ
አሥራ አንደኛው ሰዓት ላይ ቆሜ ዛሬም ኃጢአት ያናወዘኝ ሥራዬ ተዘበራርቆ ስባዝን ውዬ ስባዝን ያደርኩኝ
አጎንብሼ የምማትር የኃጢአት ሽክም ያጎበጠኝ
ለኔ ስትል ሰው መሆንክን የረሳሁኝ
ውለታ ግርፋት ሞትህን እንኳን ያላሰብኩኝ
ለአፍታ ዳግም ምጽአትህን ቸል ያልኩህ
የአዳምን ጩኸት ጮኸህ ጎንህን በጦር ተወግተህ የከፈልከውን ዋጋ ከልብ ያላሰብኩኝ
በስም ብቻ የምኖር በደልን የካብኩኝ
ልቤ ከዓለም ሆኖ አገልጋይህ መስዬ
ከጠላት ጋር ውዬ ከእርሱ ጋር ተዋውዬ
በኃጢአት ደምቄ
በቂም አሽብርቄ
ለሰውማ አለሁ ለወጪ ለገቢ በዓይን እታያለሁ
በሰገነት ቆሜ ለክብርህ እዘምራለሁ
ነጠላ ቀሚሴን አስረዝሜዋለሁ ጠዋት እና ማታ እመላለሳለሁ
በጎ እንደሚሠራ ጎንበስ ቀና እላለሁ
የጽድቅ አበባዬ ጠውልጎ የኃጢአት ችግኜ አፈራ
አዝመራው ለምልሞ በለሱም የጎመራ
ለዓለም ሳጎበድድ ጊዜዬን የጨረስኩ
በኃጢአት ብል ተበልቼ ባዶ ሆኜ የቀረሁ
ክርስትናዬን በነጠላ የሽፈንኩ
የራሴ ምሶሶ እያለ ጉድፍ ለማውጣት የሮጥኩ
እኩይ ግብሬ ጸጽቶኝ በንስሐ ያልታጠብኩ
በተሰጠኝ የማልረካ ምስጋና የተሳነኝ
የራሴ ወርቅ ተቀምጦ የሰው ነሐስ የሚያምረኝ
ለሰዎች ያለሁ መስዬ ከእቅፍህ የወጣሁኝ
አካሌ ከመቅደስ ልቤ ከዓለም የሆነብኝ
ጠፋ ብዬ የምፈልግ ለራሴ ፈላጊ የሚያሻኝ
የተሰጠኝ መና ሰልችቶኝ የግብጽን ሽንኩርት የናፈቅኩኝ የሚጠቅመኝን ትቼ የማይጠቅመኝን የፈለግኩ
እንደ ዴማስ ተማርኬ ዓለም ያስቀረችኝ
በውበቷ ገመድ አስራ የሳበችኝ
በቤትህ ውስጥ የጠፋሁ
...ድሪምህን ዳግም ሥራኝ።
@kinexebebe
2024/06/25 23:33:41
Back to Top
HTML Embed Code: