Telegram Web
++ ኪነጥበብ - የደብረታቦር ጭውውት !!

(ደብረ ታቦር ምስጢር)

ትዕይንት አንድ



ወንድሜነህ ፡ ሰውነት ኧረ ሰውነት (በገጠርኛ ዘይቤ )


ሰውነት ፡ ኧረግ ወንድሜነህ ምን ሆነሀል?


ወንድሜነህ ፡ ሰውነት እንኳን አደረሰህ

ሰውነት ፡ እንኳን አብሮ አደረሰን

ወንድሜነህ ፡ ዘንግተኸዋል እንዴ

ሰውነት ፡ ምኑን ነው ወንድሜነህ

ወንድሜነህ ፡ እንዴ ባለፈው ሳምንት የበዓሉን አከባበር ጉዳይ በበዓሉ እለት ይነገራል ይፈረዳል ብለው ደኛው አልሸኙንም፡፡


ሰውነት ፡ ኧረግ ኧረግ ዘንግቼው እኮ ነው ከቢሸው ጋር የተካሰስንበት ጉዳይ ኧረ ለመሆኑ ባለፈው ከተረታ እናያለን ያልነውን ነገር አዘጋጅተሃል?

ወንድሜነህ ፡ ታዲያ ዛሬማ ሳንረታው ንቅንቅ የለም አይ እንዳው ለነገሩ ፍርድ  አይታወቅም ብዬ ነው እንጂ

ሰውነት ፡ በል ወደዚያው እንሒድ (ተያይዘው ይወጣሉ )


ትዕይንት ሁለት


(ሰዎች ተረሰብስበው ዳኛው ተቀምጠው ይታያሉ ተከሳሽ ቆመዋል )

ዳኛ ፡ እንደምን ዋላችሁ ?

#በህብረት ፡ እግዚአብሄር ይመስገን

#ዳኛ ፡ ከሳሽ ወዴት አለ

#ወንድሜነህ ፡ አለሁ እዚህ ነኝ ዳኛ
  እንዳይሆንብኝ ጉበኛ
  ፍርድ የማያጣምሙ እውነተኛ
  የማያዳሉ ትክክለኛ
  እንዲሆኑ እመኛለሁ መለኛ


#ዳኛ  ፡ ተከሳሽ ወዴት አለህ

#ተከሳሽ ፡ በዚህ ነኝ ክቡር ዳኛ
     ልረታ የተዘጋጀው ሐቀኛ
     መሆኔ የታወቀልኝ ለሐገር ተቆርቋሪ
     ባህልና ትውፊት ጠባቂ አስከባሪ


ዳኛ ፡  ተከሳሽ ቀጥል

#ተከሳሽ  ፡  በልሀ ልበልሀ
     ለውሻ የላት ምሳ
     ለቀበሮ የላት ገሳ
     ለዶሮ የላት ግት
     ለፌቆ የላት ባት
     የአንተም ነገር እንዲሁ ነው ተረት

ወንድሜነህ ፡ ለውሻ ባይኖራ ምሳ
                ያንን ሁሉ ጅብ መልሳ
                ለቀበሮ ባይኖራ ገሣ
               ያንን ሁሉ ጉድጓድ ርቃ ምሳ
             ለዶሮ ባይኖራት ግት
             ያንን ሁሉ ጫጩት
              አንተ አሳድግላት
            ለፌቆ ባኖራት ባት
         ያንን ሁሉ ሜዳ አንተ ሮጥክላት
        የኔ ነገር እውነት አንድም        ያልተቀላቀለበት ሐሰት

#ዳኛ  ፡ ከሳሽ ነገሩን አስረዳ

ወንድሜነህ ፡ ነገሩን ሳስረዳ ዘንድ
ዛሬ የምናከብረው በዓል የደብረ ታቦር
በጭፈራ  በልመና ሰውን በማስደንገጥ ነው የሚከበር
  (ሰዎች አይደለም አይደለም እያሉ ይንጫጫሉ )

#ወንድሜነህ ፡ እንግዲህ እንዲ ካልተከበረ
  ባላንታዬ ቢሻው ሊያከብር ትግደረደረ
  የከተማውን ባህልና ትውፊት
  ከቤተክርስቲናችን ሊቀላቅል ልዱልበት

#ተከሳሽ ፡ ምን ክፋት አለው እናንተዬ
     ክብሩ በተገለጸበት ቀን የጌታዬ
     ብንጨፍር ብንዘፍን ብንሸልል

#ወንድሜነህ ፡ አለው እንጂ ክፋት
  ጭፈራይቱን እና ዘፈኑን ማን አመታት
   የዲያብሎስ መሆኑ ተረስቶ
   ሃይማኖታችን ሊሆን አንቱ ፈንቶ

#ዳኛ ፡   ከሳሽ ይበልጥ ነገሩን ግልጥ አድርግ

#ወንድሜነህ፡ እሺ ዳኛ ይበልጥ ነገሩን ለማስረዳት መጽሀፍ ቅዱስ መግለት መመርመር አለበት 
   ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
     በዚህች ምድር ላይ ሲኖር ሲመላለስ
     ይታይ ነበረ ሙታንን ሲያስነሳ በሽተኛ ሲፈውስ
     ታዲያም ጌታችን በምድር ላይ እያለ
    አምላክነቱን ሰዎች አያውቁም ነበረ
    ሰዎች እኔን ማን ይሉኛል
    ብሎ ጠየቀ ሐዋርያቱ ያውቁኛል
    አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ  ነው ይሉሃል
    አንዳንዶች ኤልያስ ነው ይሉሃል
    ብሎ ጠየቀ እናንተስ ማ ትሉኘላቹ
    ጴጥሮስ መለሰ አንተ የሕያው የእግዚብሄር ልጅ
    እግዚአብሄር ገልጦለት ጴጥሮስ ይህን ቢመለስ ቢመሰክር
    ሌሎቹ ሐዋርያት አምላክነቱን ይጠራጠሩ ነበር

#ተከሳሽ
ጌታዬ ይሄ ሰው ነገሩን ማስረዳቱን ትቶ
     ሌላ ሲዘበርቅ ዝም ይሉታል ከቶ

#ዳኛ ፡ ተከሳሽ ትዕግስት ይኑርህ
    ችሎት ፊት መሆንህን ምነው መዘንጋትህን
    በከሳሽነቱ ነገሩን ሲያስረዳ
      ከመጽሐፍ ቅዱስ ማመሳከር ቢዳዳ
     ሊያስቆጣህ አይገባም
     በከሳሽነትህ ትቃወመው የለ
     በል ቀጥል ከሳሽ

#ወንድሜነህ
ጌታችን አምላክነቱን ሊገልጥ
የምስጢርን ቁልፍ ለሶስቱ ሐዋርያት ሊሰጥ
ወደ ታቦር ተራ ይዟቸው ወጣ
ዮሐንስ ያዕቆብ እንዲሁም ጴጥሮስ
ጌታን ተመለከቱ ሲነጋር ከሙሴ ከኤልያስ
 ልብሱ እንደበረዶ ነጣ ፊቱም ተለወጠ
 ብርሃነ መለኮቱን በሰው ፊት ገልጦ

#ዳኛ ፡   ከሳሽ ይብቃ ተከሳሽ ቀጥል

#ተከሳሽ  ፡ እንግዲህ ጌታዬ ወንድሜነህ እንዳለው
  በዓሉ እንደዚህ መሆኑንም አምናለሁ
  የአከባበሩ ሥርዓት ነው እኔን ከእሱ የሚያታላው
     በዓመት በዓሉ የሚደረገውን ሁሉ
  ምሥጢሩ ባይገባኝ የድርጊቱ ቃሉ
  የከተማውን አከባበር ማምጣት መተግበር ችግሩ ምንድን ነው አሉ
    በጅራፍ ፋንታ ሮኬት
    በምስጋና ቦታ ጭፈራ ሁካታ

#ዳኛ ፡ ምስጢሩ ካልተገለጠልህ ካልገባህ
  ከሳሽ ግልጥልጥ አድርጎ ይንገርህ

#ወንድሜነህ ፡ አመሰግናለሁ ዳኛ
  ተከሳሽን የከሰስነው ሁለት ሆነን ነው
  ስለዚህ ለሁለት ምስጢሩን እንድናስረዳው
  ይፍቀድልን ጌታው


#ዳኛ  ፡ ፈቅጃአለሁ

#ወንድሜነህ ፡ ሰውነት በል ተነሳ

#ሰውነት ፡ አመሰግናሁ ዳኛ
  እንግዲህ ምስጢሩን ለመዘርዘር
  ማስረዳቱን ከተራራይቱ እንጀምር
  ጌታችን ይንንን የታቦር ተራራ መምረጡ
  በነቢያት የተነገሩት ትንቢቶች እና ምሳሌዎች እንዲፈጠሙ
  ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ሶስቱን ይዞ መውጣጡ ደግሞ
ከእነዚህ ከአስራ ሁለቱ ያዕቆብና ዮሐንስ
 መስሏቸው ነበረ ጌታ በምድር የሚነግስ
 ስልጣንንም ሽተው በአማላጅነት ቢልኩ በአናታቸው
የሰማይ የምድርም አምላክነቱን በታቦር ተረራ አሳያቸው

#ወንድሜነህ
ጴጥሮስ ደግሞ መምጣቱ
ሞቱን አያውቅም ነበረ እንደ አምላክነቱ
ጌታ እኔ እሞታለሁ ቢላቸው
 ጴጥሮስ በአንተ አይሁንብህ አይፈጸምብህ አለው
ጌታም አምላክ መሆኑን ሊገልጥለት
 ሞቶ ለሰው ልጆች እነደሚሰጥ ሕይወት
 በታቦር ተራራ ሁሉንም ግልጥልጥ

#ሰውነት  ፡ 

በታቦር ተራራ ጌታ ከሁለት አበው ጋር ሲነጋገር
አንደኛው በሕይወት ሌላው ሞቶ ነበር
ማለቴ ኤልያስ ከሰማይ ሙሴ ከመቃብር
 እነዚህ ሁለት አበው የመገኘታቸው
 ዝም ብሎ እንዳይመስለን እንዲህ ነው ምስጢራቸው
 ሙሴ በምድር እያለ አምስት መቶ ሰባ ጊዜ ከአምላኩ ጋር ተነጋግሮ ነበር 
 እንግዲህ እንዲህ ቢነጋረውም ግን ፊቱ ነበር ከእርሱ የተሰወረ
ሙሴም ጠየቀ ሁል ጊዜ አነጋርሃለው መቼ ነው ፊትህን የማው
 የእኔን ፊት አይቶ የሚጸና የለም ግን ሰው ሆኜ በምድር ላይ ስመላለስ ታየኛለህ
ጌታ አምላክቱን ቢገልጥ በጥቂቱ ቢያሳያቸው


#ይቀጥላል

ጸንተው መቆሙ አቃታቸው ሁለቱም ተመለሱ ወደየቦታቸው


#ወንድሜነህ ፡ እንግዲህ በዚህ በዓል ላይ ጅራፍ ማጮህን ጌታ በታቦር ታራራ አምላክነቱን ሲገልጥ አብ በሰማይ ሆኖ የምወደው ልጄ ነውና እርሱን ስሙት ብሎ ተናገረ። በዚህ ንግግሩ ደንግጠው ወደቁ ይህንን የንግግሩን ኃያልነት አስፈሪነት ለማስታወስ ጅራፍ እናጮሐለን፡፡
#ሰውነት ፡ ሙልሙል መጋገሩ እና መመገባችን ጌታ አምላክነቱን በገለጠ ጊዜ ተራራ ተራራው በብርሃን ተሞልቶ ነበር በዛም አካባቢ የነበሩ እረኞች ያልመሸ መስሏቸው በዛ አካባቢ ቆይተው ነበር፡፡ ቤተሰቦቻቸውም ልጆቻቸው በማምሸታቸው ተጨንቀው ለእራት የሚሆን ሙልሙል ዳቦን ይዘውላቸው መምጣታቸውን በማስታወስ ዛሬም 
ሙልሙሉን እንነጋራለን። ችቦው ደግሞ ልጆቻቸውን ለመፈለግ የመጡት ወላጆች ችቦ እያበሩ መምጣታቸውን አንድም ደግሞ የጌታን ብርሃንነት የምናስታውስበት ነው፡፡


#ተከሳሽ  ፡ አሁን ገብቶኛል  ምስጢሩ ካሳ እንዲሆነኝ አንድ ገንቦ ጠላ እና ዳቦ ይዤ መጥቻለው። ማነሽ አለሚቱ ወደዚህ አምጪው ፡፡


#ወንድሜነህ ፡ እኔም እንግዲህ ከበረከቱ ተካፋይ እንድሆን ያመጣሁትን
እሰጣለሁ፡፡

#ተፈፀመ
@kinexebebe
✍🏿ሦስት ዳስ እንስራ✍🏿
ወልደ እጓለምህያው ኢየሱስ ክርስቶስ
ቂሳሪያ ሳለ ሀገረ ፊሊጶስ
በሐዋርያት ልብ ወንጌልን ሊዘራ
ዓለሙ ስለርሱ ምን እንደሚያወራ
ከቶ ምን እያለ እንደሚሰናከል
'ሚመላለሰውን ልባቸው መካከል
እንደ እሩቅ ብእሲ እውቀት እንዳነሰው
መጠየቅ ጀመረ  እንደ አላዋቂ ሰው
"ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ~ ምን ይናገራሉ?"
      ~በማለት ቢጠይቅ~
"ሙሴ ነው ይልሃል ከፊሉ
ኤሊያስ ነው ብለው የሚያስቡም አሉ
ደግሞ ዮሐንስ ብለው የሚሰናከሉ
ቁጥራቸው ብዙ ነው እንደ አሸን የፈሉ
አረ ብዙ ይሉሃል! ምን አለ የቀራቸው?
ኤርሚያስ ወይ ኢሳያስ ተነስተው ከአንዳቸው
መጥተዋል ይላሉ እ'ስ በርስ ሲያወሩ"
በማለት ነገሩት አንዳች ሳያስቀሩ
"ማነው ትላላችሁ? ማነኝ ለእናንተሳ?"
በማለት ቢጠይቅ ጥያቄ ቢያነሳ
የዮና ልጅ ስምኦን በመንፈስ ተሞልቶ
        "አንተ ክርስቶስ ነህ"
በማለት መለሰ አንደበቱን ከፍቶ
"መንፈስ ቅዱስ እንጂ ከቶ ስጋና ደም ይህን ያልነገረህ
ባንተ መሰረት ላይ መቅደሴን የማንጽ አንተ ጴጥሮስ ነህ
የገሃነም ደጆች የማያናውጧት 'ሚፈሯት ክፉኛ
ቤቴን እሰራለሁ በዚህ መሰረት ላይ ለዓለሙ መዳኛ፡፡"
ብሎ ተናገረ የሰላሙ ንጉስ የሰላሙ ዳኛ፡፡
ፈጣሪ መሆኑን ሊያስረግጥላቸው ከቀናት ቦሃላ
ከጴጥሮስ፣ ከያይቆብ ከዮሐንስ ጋራ
ወጣ አስከትሏቸው ታቦር ወደ ሚባል እረጅም ተራራ
ለማመን የሚከብድ ታምር ተፈጠረ ተዚያ እንደደረሱ
በፀአዳ ብርሐን መብለጭለጭ ጀመረ የጌታችን ልብሱ
መልኩም ተለዉጦ እንደ ፃይ ሲያበራ
በብርሐን ተሞላ የታቦር ተራራ፡፡
እረኞች በሙላ ከብት የሚጠብቁ
~ቀሩ ቤት ሳይገቡ ~ በብርሐኑ ሙላት መምሸቱን ሳያውቁ
ከሙታን መኖሪያ ሙሴን አስነስቶ
ከብሔረ ሄዋን ኤልያስን ጠርቶ
በሚያስገርም ግርማ በሚያስደንቅ ክብር
ሁለቱን ነብያት ያዋራቸው ጀመር፡፡
"ያለህ የምትኖር የዘለዓለም ንጉስ አንተ እፁብ ገናና
ፍቅር አገብሮህ ዓለሙን ለማዳን ብትወርድ በትህትና
የባርያን መልክ ይዘህ አብረሐቸው ብትውል ብትኖር ከነርሱጋ
በሚመጥናቸው ተገልፀህ ብትታይ በገዘፈ ስጋ
     ~ ነብይ አሉህን?~
ወልደ እጓለመህያው ወዮ ይቅር በላቸው
አንተን ነብይ ሊል እንዴት ቻለ አፋቸው?
የነብያት ሁሉ አምላክ ሆነህ ሳለ
ዓለም ቢሰናከል ፍጡር ነህ እያለ
አትቀየም ጌታ ሳያውቁት ነዉና
ያንተን አምላክነት ያንተን ልዕልና፡፡
የአማልክት አምላክ ነው ዓለም ሆይ እወቀው"
ብለው መሰከሩ  ከጌታ ስር ወድቀው
ጴጥሮስ ከተኛበት ይሄንን ክብር ሲያይ ተሞልቶ በደስታ
"ሶስት ዳስ እንስራ" ብሎ ተማፀነው ቀርቦ ወደ ጌታ
"አንዱን ለኤሊያስ፣ አንዱንም ለሙሴ፣ አንዱን ደግሞ ላንተ
በዚህ መኖር ጓጓሁ ~ ልቤ እጅጉን ሻተ
አንሂድ ወደ ሌላ ~ ይህ ቦታ መልካም ነው"
እያለ በፍቅር ጌታን ሲማፀነው
ፀአዳና ብሩህ ደመና ጋርዷቸው
"በርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ" እርሱን ስሙ አላቸው
ከታቦር ተራራ ጌታችን መምጣቱ
ከነብያቱ ጋር አንድ ላይ ማውራቱ
ጥልቅ ሚስጥር አለው አንድምታ
በቅዱሳት መፅሐፍት የሚፈታ
    "አንድም"
በዘመነ ብሉይ ሳይገለጥ ጌታ ደካማውን ስጋ ግዙፉን ሳይለብሰው
ሊቀ-ነብይ ሙሴ ቢጠይቀው ግዜ ፊቱን እንዲያሳየው
የባርያን መልክ ይዞ ፊቱ እንደሚገለጽ በገዘፈ ስጋ
ገብቶለት ነበረ የማይሽረውን ቃል ሲና ተራራውጋ
              "አንድም"
ሐሴት ያደርጋሉ ታቦር አርሞንዔም
ብሎ ስለነበር ትንቢቱን ሊፈጽም
             "አንድም"
"ሙሴ ነው ይሉሃል" ብለው ስለነበር
ሙሴን አሳያቸው ጠርቶ ከመቃብር
የነብያት አምላክ ፈጣሪ መሆኑን ስሙ የገነነ
ኤልያስም መጥቶ ምስክር ሆነለት ነብይ እንዳልሆነ፡፡
       ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@kinexebebe
.....ተገለጠ...በግረማ

በስውሮች  አለም  መገለጥ ብርቅ  ነው
ሊያውም በተራራው  በሄርሞን  የሆነው

......ከጊዜያት በፊት

ኢየሱስም  ሲደርስ ወደ ፊሊጲስ ቄሳርያ
ጥያቄን  ጠየቀ አሻሚ  ነበር  ያ
እንዳው  ለመሆኑ  እኔን  ማን  ይሉኛል?
ብሎ ጠየቃቸው  መልስን  ይፈልጋል

ከነብያት  አንዱ...እ...መጥምቁ  ዮሐንስ
ሙሴ ነው ይላሉ  ደግሞም  ኤሊያስ
ሌላም ብዙ  ብዙ  ሲሉ  እንሰማለን
የህዝቡ  ምላሽ  ነው  ይህን  እናውቃለን
..
እናንተስ  ማን  ትሉኛላቹ   ብሎ ቢጠይቀን
በመንፈስ ቅዱስ ሀይል  ይህንን  መለስን
አንተማ ....ክርስቶስ  ነህ  የእግዚአብሔር  ልጅ
ህዝቡን  ከሀጢያት ከመርገም  የምትዋጅ

ብዬ ብመልስ  ቀደም ብዬ  ከሁሉ
አለት  አደረገኝ  የፀናሁ  በቃሉ
ስጋና  ደም  መክሮ  መቼ ይህን ሊያብራራ
የእውነትን ብርሃን.....ለአለም  ሊያበራ
የአባቴ  ሀይል  አግዞ  እረድቶክ
በመንፈስ ቅዱስ ምሪት  ይህንን ተናገርክ

.....መቼ  በእዚህ  በቅቶ

በደብረ ታቦር  በእዛች  ቅድስት  ቀን
ጌታ መድኃኔዓለም  የገለጠው  ክብሩን
ሙሴና ኤሊያስ  ከእርሱ ጋር  ነበሩ
ዮሐንስ  ያዕቆብ  ጴጥሮስ ደቀ መዝሙሩ
በረጅሙ ተራራ  ብቻቸውን  ሆነው
በጣም ያስደንቃል እዛ ላይ  የሆነው

ሙሴን ከመቃብር ኤሊያስን  ከብሄረ ህያዋን
ጴጥሮስን አቁሞ  ያዕቆብ  ዮሐንስን
ፊቱ  አንፀባረቀ  ደመና  ወረሰን
ልብሱ  ፀአዳ  እድፈት  የለበትም
ከፊቱ  ወደቅን ልናየው አልቻልንም

ጌታ ሆይ  በእዚሁ እንሁን ለእኛ መልካም  ነው
ሶስት ዳስ እንስራ  እኛው  እንቀልሰው
ብሎ  ተናግሮ   ጥቄት  ቆመና
ምድር  ተለወጠ  በክብር  ደመና 

ደመናውም መጥቶ  በሀይል  ሲጋረዱ
በጣም  ተንቀጥቅጠው በፍርሃት  ራዱ

.....ድምፅ  መጣ   ከሰማይ .....

የምወደው  ልጄ  በእርሱ  ደስ   የሚለኝ
አንድያዬን  እርሱን  ቃሉን  አድምጡልኝ
ብሎ  መሰከረ  የአባትነት  ቃሉን
በክብር  ገለጠ  አብ  አንድያውን

የሚደመጥ  ጌታ  ሚደመጥ  አዳኙን
በክብር የታየው  ከፍ ብሎ በሔርሞን
ልብሱ  እንደ በረዶ  ፍፁም ነጭ የሆነው
የአብ  አንድያ ልጅ  ኢየሱስ  እኮ  ነው

.....እና  እኔም ......

ከውበትህ  ፀዳል  ከግርማ  ልካፈል
በደብረ   ታቦር   ካንተ   ጋር  ብገኝም
ከፊትህ  የምቆምበት ብርታት  አላገኝም

በቃ ...በቃ...ታቦር  እራሱ  እኔ  ልሁን
የአንተነትህ   ፀዳል  እንዲያንፀባርቅብኝ
አለት ካልከኝ  አይቀር  ታቦርን   አድርገኝ .
.
.
.
.
.,...  ቬሩታዊት  ዮሐንስ
......10/12/2015
.....3:36
.....ሮብ
@kinexebebe
@kinexebebe
@kinexebebe
ምን ብንል ምን ይበቃል?

የበሽታዎቻችን ሁሉ መድሀኒት ፣ የመረበሾቻችን ሁሉ ሰላም ፣
የሁካታዎቻችን ሁሉ እርጋታ ፣
የሀዘኖቻችን ሁሉ ደስታ፣
የሰው ዘር ሁሉ ዘር፣
የአይምሮአችን ሁሉ አይምሮ፣
የውዳሴዎቻችን ሁሉ ውዳሴ፣
የንፅህናዎች ሁሉ ንፅህና፣
የቅድስናዎች ሁሉ ቅድስና፣
የመልካሞች ሁሉ መልካም ፣

የሆንሽ እመቤቴ ሆይ ምን ብናገር የክብርሽን ጠብታ ታክል መናገር እችል ይሆን?

ድንግል ሆይ
የብርሀናት ሁሉ ብርሀን እናት
የጊዜን ፈጣሪ የወለድሽ ክብርት
አለማትን በእጆቹ መዳፍ የያዘውን  የያዝሽ
ህፃናትን የሚያሳድገውን ያሳደግሽ
የፍጥረትን ሁሉ ፈጣሪ ፣ የፈጠረሽን   እርሱን የወለድሽ ፣

ወለላይቱ ሆይ እንደምን ያለሽ ነሽ ?

ድንግል ሆይ ልቦናዬን አጨልሜ ለሰው፣ ለፈጣሪ ና ለተፈጥሮ አልስማማ ብዬ ሀጢያቴ ከሩቅ እየሸተተ ባያስቀርብም ፣ አዛኚቱ ሆይ የልቤን ጨለማ በብረሀንሽ አንፅተሽ ትቀርቢኝ ዘንድ እማፀንሻለሁ።

እመቤቴ ሆይ  የእኔ ባልሆነ አለኝ ብዬ በማስበው ትንሽ ነገር ተመፃድቄ የነፍሴን ልብ በትዕቢት ላፈርጣት ነውና ፤  ታላቁ መልዐክ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ አምላክን ትወልጃለሽ ሲልሽ እነሆኝ የጌታ ባርያ እንደ ቃልህ ይደረግልኝ ባልሽበት ትሁት ልቦናሽ  ነፍሴ ላይ የተጣበቀውን የልቦና ትዕቢት ቆርጠሽ ጣይሊኝ።

እመብዙኃን ሆይ   የፀጋዎች ሁሉ መገኛ(ግምጃ ቤቱ) የሆንሽ ክብርት ሆይ ከልጅሽ ከጌታችን ከመድሀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የበራችልኝን ትንሽ የፀጋ ሻማ ላጠፉ እታገላለሁና፤ ወድጄ ፈቅጄ በሀጢያቴ ጎርፍ እኔኑ ላጠፋ የምፍገመገመውን ከርታታ ልጅሽን ከተሸከምኩት የኃጢያት ክምር አሳርፈሽ የተወደደ ልጅሽ ታደርጊኝ ዘንድ እለምንሻለሁ ።

እመብርሃን ሆይ  በመጠመቅ  በህይወቴ የተሰጠኝን የተወደደ ልጅሽን  አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን በጨለሙ ሀሳብ፣ ቃልና ተግባሮቼ ለማስወጣት እየታተርኩ ነውና ወደ ሞት የሚፋጠኑትን አካለ ስጋና ነፍሴ  በብርሃን እናትነትሽ በብርሃናዊ አካሎች ቀይሪልኝ።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ምን ብንል ምን ይበቃል ?  የቱ ፊደል፣ የትኛውስ ቃል ያንቺን ክብር ይገልጠዋል? 

ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን ሁሉ በላይ የሆንሽ ክብርት ሆይ በአዳፋ ነፍስና ስጋዬ ፣ በተዳደፈ ማንነቴ  ስላንቼ ለማሰብ ፣ ለመፃፍ ስለሞከርኩም   ይቅር በዪኝ ።

                              እናቴ ሆይ

በፅንሰትሽ እንደአዲስ አፍርሰሽ ትሰሪኝ ዘንድ ፣ ፈርሼም እንደምትፈልጊው እፀነስ ዘንድ ከተወደደ ልጅሽ ከጌታችን ከመድሀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ለምኚልን ።

  አዕምሮውን ልቡን ሳይብን አሳድሪብን
  ፀጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን

አንቺን የፀነሰች ማህፀን የተመሰገነች ናት።
   @kinexebebe
በዚህ መሆን ለኛ መልካም ነው
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ሰላም ላንተ ይሁን ፥ የታቦር ተራራ
የተገለጠብህ ፥ የአምላክ ድንቅ ስራ
ቅዱሱ ተራራ ፥ የምስጢራት ደብር
ግርማው የታየብህ ፥ በገናና ክብር
ልብሱ ነ....ጭ ሆነ ፥ ድንገት ተለወጠ
አንደ ፀሐይ በራ ፥ ምስጢር ተገለጠ

ቡሄ ቡሄ በሉ ፥ ሰዎች ተደሰቱ
ጨለማ ሲገፈፍ ፥ ሲነጋ ሌሊቱ
ከክህደት የሚያድን፥ ከጥርጥር መንፈስ
እውነት በዚያ ታይቷል፥ ልብን ሞልቶ ሚፈስ

ለፈሪሳውያን ፥ ለአዋቂ ነን ባዮች
በሙሴ ህግ አለን ፥ ተከራካሪዎች
እነሙሴ መጥተው ፥ ለርሱ መሰከሩ
ኋላ መገለጡን ፥ ቀድመው እንዳወሩ

አንድም ስለሰው ልጅ፥ ስለ ማንነቱ
ልባቸው ለሚስት ፥ ስለ አምላክነቱ
ኤልያስ ነህ ለሚሉት፥ ኤልያስ መጣላቸው
ሙሴ ለሚሉትም ፥ ሙሴን ጠራላቸው
የሚያነሳ የሚያኖር ፥ ፈጣሪ አምላካቸው
ከያሉበት ጠርቶ ፥ በዚያ አስቆመላቸው

ኤልያስም አለ..............
ዮርዳኖስን ብከፍል፥ ሰማይን ብለጉም
ምልክትን ባደርግ ፥ እሳትን ባወርድም
ኃይልን ብጎናፀፍ ፥ ጠላትን ባርድም
አምላኬን በኔ ስም ፥ ሲጠሩት አልድም
ብሎ መሰከረ ፥ ልቡ እየተነካ
ጌታው በርሱ መጠን ፥ ስለማይለካ

ሙሴም እንዲህ አለ ...........
በሲና በረሃ ፥ ከላይ መና ባወርድ
ከአለት ውሃ ባፈልቅ ፥ ደመናን ብጋርድ
ታምራትን ባደርግ ፥ ባህርን ብከፍልም
የአባቶቼን አምላክ ፥ ጌታን አላኽልም
የአብርሐምን አምላክ ፥ በርሱ ልክ አሎንም !!
አንኳን መሆን ቀርቶ ፥ ያሰቡት ለምን ነው ?
ጌታን #ማየት እንኳን ፥ እጅግ መታደል ነው
ብሎ ተናገረ...... ፥ ስለ አማኑኤል ክብር
በአምሳለ ተዋህዶ ፥ በምጢሩ ደብር

አንድም አሮን እና ፥ ማርያም እህቱ
በሲፓራ ዮቶር ፥ በኢትዮጵያዊቱ
ሙሴን ቢያቆጣቸው፥ ጥቁሯን በማግባቱ
እግዚአብሔር አለ.........
ባርያዬን በቤቴ ፥ እኔ ሹሜዋለሁ
ነብያት ባስነሳ ፥ ምሳሌ እሰጣለሁ
አልያም በራእይ ፥ ሆኘ አገለጣለሁ
ሙሴን ግን ዝምበሉት ፥ እኔ እታየዋለሁ
አፍለአፍ በግልጥ ሆኜ፥ አናግረዋለሁ
ብሎ ስለነበር ፥ ትንቢት ተፈጸመ
አፍለአፍ ተናገሩ ፥ በግልፅ አብሮት ቆመ

አንድም የህያዋን ፥ የሙታን አምላክ ሲል
ኤልያስ ከህያዋን፥ ሙሴን ከመቃብር
የነብያት እና ፥ የሐዋርያት ጭምር
ጥንት የነበረና፥ ዘለዓለም የሚኖር
በአልፋና ኦሜጋ ፥ በ'ውነተኛው ባ'ንዱ
ብሉይና ሐድስ ፥ እዚያው ተዋሐዱ
በአንድ እምነት ሆነው፥ በፊቱ ሰገዱ

አንድም የስላሴ ፥ ምስጢር ተገለጠ
በብሩህ ደመና ፥ አብ ድምፁን ሰጠ
እኛም ከወልድ ጋር፥ ባንድ ቆመን ሳለን
የምወደው ልጄን ፥ እርሱን ስሙት አለን
በብርሃን አምሳል ፥ መንፈስ ቅዱስ ታየን
ልጅም በአባቱ ዘንድ፥ ያለውን ክብር አየን
ለማይጠፋ እርስቱ ፥ ለመንግሥቱ ለየን

አንድም ነገረ ጾም ፥ ለሚጠራጠሩ
አርባ ቀንና ሌት ፥ በጾም የከበሩ
ሙሴና ኤልያስ ፥ ሁለቱ ተጠሩ
የተራራው ምስጢር ፥ ተገልጦ ያየነው
ቢቀኙት አያልቅም ፥ እጅግ የበዛ ነው
ቢነገር > > >> >> >> !

ከአለም ተረት ተረት፥
ከሌለው መሰረት
ከይሆናል ግምት ፥
ውልየለሽ መላ-ምት
ከይምሰል ብልሃት ፥ ከልብ-ወለድ ትርክት

ኑ በዚህ ተራራ.........!!
ኑ ቃሉን እንስማ ፥ እንኑር በርሱ እቅፍ
ከወጀብ ማዕበሉ ፥ ከነፋስ እና ጎርፍ
በአለም ከምናየው.. ..
ከጥፋት ርኩሰት ፥ እንሽሽ እንትረፍ
ከሚጋየው መቅሰፍት ፥ እናምልጥ እንለፍ
በማደሪያው ገብተን ፥ በቅዱሱ መቅደስ
ከዘርፋፋው ልብሱ ፥ ዳስሰን እንፈወስ

ኑ በዚህ ተራራ.... ...
ከቅዱሳን ጋራ ፥ አንቁም በኅብረት
ቤተ ክርስቲያንን ፥ ቅጥሯን እንሙላት
ለጥያቄያችን መልስ፥ ወደ የሚገኝባት
የሚያለቅሱት እምባ ፥ የሚታበስባት
የታመሙት ሁሉ ፥ የሚፈወሱባት
ያቀረቀሩትም ፥ ቀና የሚሉባት
ጥላቻ ያይደለ ፥ ፍቅር የነገሠባት
ከሁከት የራቀች ፥ ሰላም የበዛበት
በዚች መሆን ለኛ ፥ መኖሩ መልካም ነው
አምባ መጠጊያችን ፥ክርስቶስ በርሷ ነው

ኑ በዚች ተራራ........
ልባችሁ አይፍራ!
ከሊቅ እስከ ደቂቅ
ትንሽ እስከ ትልቅ ፥ ከእቅልፍ ተነሱ
የእምነት ጋሻችሁን ፥ ሰይፋችሁን አንሱ
ተቃዋሚው በዝቷል ፥
ፍቅር ከአለም ጠፍቷል
ገንዘብ አምላኪና ፥ ርኩሰቱም ታይቷል
አሳዳጃችንም ፥ ጠላት አፉን ከፍቷል

ኑ በዚች ተራራ ...........
ልባችሁ አይኩራ
ለሰላሟ መርከብ ~ ለዚች ላ'ማናዊት
ካባችሁ እስኪወድቅ ~ እንደ ቅዱስ ዳዊት
እንዘምር ለጽዮን~ለመአምላክ ለእናቱ
አድስ ቅኔ እንቀኝ ~ እንውደቅ በፊቱ
ማደርያውን እና ~ ስሙን እናወድስ
የጠላትን ቅጥር ~ በእልልታ እንደርምስ

እምዬ ኦርቶዶክስ ፥ እናት ተደፍራለች
በጠላት እጅ ወድቃ ፥ ልጆቼን ትላለች
ንፁሐን ልጆቿ ፥ እምነቴን ስላሉ
ደማቸው ፈሰሰ ፥ በገፍ ተገደሉ
የቀጥተኛዋን ፥ መንገድ የሚያፈርሱ
የዳቢሎስ ልጆች ፥ አጥፊዎች ተነሱ
በግፍ የሚጠሏት ፥ አሳዳጆች በዙ!

የገዛ ልጆቿም ፥ እንደ እርብቃ ማህፀን
እኔ'በልጥ እኔ'በልጥ፥ ብኩርና ሽተን
ባ'ንድ እትብቷ ታስረን ፥ በሆዷ ተኝተን
ለማያልፈው መንግሥት ....
ህዝብ የምንሆነውን ፥ ዓላማ ዘንግተን
ለዚያውም ትልቁን ...
የሰማይ አርማውን ፥ መስቀሏን አንግተን
በምድራዊ ሀሳብ ፥ ክልል እና ወሰን
ላላፊ እና ጠፊ ፥ ለማትረባዋ አለም
በቅድስቲቱ ምድር ፥ በዳግማዊት ሳሌም
ያልተሰማ ሮሮ ፥ ያልታየ ጉድ የለም

አቤቱ ዝም አትበል!!
ጌታ ሆይ ዝም አትበል ፥ ይህ እስከመቼ ነው ?
የቀድሞ ምህረትህ፥ ይቅርታህ ወደትነው?

ለያህዌ ለአዶናይ......
ለእግዚአብሔር ኤልሻዳይ፥ ሁሉ ለሚቻለው
እባክህ አሁን አድን ፥
አሁን አቅና እያልን ፥ እንድንማፀነው
በአንድ ልብ ሆነን ፥ እንድንለምነው
በዚህ መሆን ለኛ ፥ መኖሩ መልካም ነው።
@kinexebebe
ሰላም ውድ የኪነ ጥበብ ቻናል ተከታዮች ዛሬ ለየት ያለ የስጦታ መርሐ ግብር አዘጋጅተንላችኋል።
የቻናላችን መወያያ ግሩፕ ላይ በመግባት ሰው add በማድረግ ከ5 _ 25 ብር ካርድ ይሸለሙ።
እንዳያመልጣቹ
https://www.tgoop.com/+hqpdBAh-vTZhMTA0
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
☃️ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ
መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ:
ሰላም ውድ የኪነ ጥበብ ቻናል ተከታዮች ዛሬ ለየት ያለ የስጦታ መርሐ ግብር አዘጋጅተንላችኋል።
   የቻናላችን መወያያ ግሩፕ ላይ በመግባት ሰው add በማድረግ ከ5 _ 25 ብር ካርድ ይሸለሙ።
               እንዳያመልጣቹ
https://www.tgoop.com/+hqpdBAh-vTZhMTA0

ግሩፑ ያሉንን ኪነጥበቦች ተጠያይቀን ለመለዋወጥ ስለምንጠቀመው add ማድረግም join ማረግም ተጠቃሚ ያረጋል እያረጋቹ

https://www.tgoop.com/+hqpdBAh-vTZhMTA0
  ደብረ ታቦር 

➣ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው?
➣ችቦ በቤተ ክርስቲያን እይታ ?  
➣ጅራፍ ማጮህ ምስጢሩ ምንድን ነው ?
➣ሙልሙል በቤተክርስቲያን አንድምታ እንዴት ይታደላል?

  🕯... እግዚአብሔር አምላክ ምስጢሩን ጥበቡን ይግለጥልን !!!

➣ ቡሄ

ቡሄ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን እና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን በደብረ ታቦር የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል ይሰኛል ፡፡ አንድም ደግሞ ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚገለጥበት ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡
አበው እንዲህ ሲሉ ወቅቱን ያመላሉ......
“ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡

➣ ጅራፍ 

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው ...

1ኛ... ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡
2ኛ.... አንድም ደግሞ ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡

➣ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡  በምሽት ለምን ይበራል ቢሉ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ አንድም ደግሞ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን መከራ እየተቀበለም አርአያ አንድም ምሳሌ ብርሃን መሆኑን አንድም በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡  ችቦውም በ12 ምሽት ይበራል ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡

➣ ሙልሙል

በዚህች እለት በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን * ቡሄ * እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ይህን ማድረጉ ትውፊታዊ ብቻ አይደለም እንደ መጽሐፈ ቅዱስ  ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው መርቀው ይሄዳሉና የዚህ ምሳሌ ነው።

፨፨፨አነሳስቶ ያስጀመረን አስጀምሮ ያስፈጸመን ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን!!!!፨
  @kinexebebe
Forwarded from ተዋህዶ
የበገና መዝሙሮችና ቁጥሮቹን እንዴት ላግኝ?🤔
በገና ምንድነው?🤔
አገልግሎቱስ?🤔
ከበገና ደርዳሪ ምን ይጠበቃል?🤔
መንፈሳዊ ጥቅሙስ ምንድነው ?🤔
ሁሉኑም በአንድ ያገኛሉ ይቀላቀሉ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#እንኳን_ለእመቤታችን_ትንሣኤና_ዕርገት_በዓል_አደረሳችሁ
ሸምሸርሸጢን ከሚባለው ከግራር እንጨት የተቀረጸው ታቦት አይነቅዝም አይበላሽም
እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ  ያደረባት የጌታ ዙፋን የሆነች የወላዲተ አምላክ  የታቦተ መቅደስ የድንግል ማርያም ሥጋዋ በምድር አይኖርም ተነሥታለች ዐርጋለች!

ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኵለሄ ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይነቅዝ እንዲል ቅዱስ ኤፍሬም

ታቦቱ 👇
1. እግር አለው 👉የንጹሐን አበው ምሳሌ ነው
2. መያዣ አለው 👉 የንጹሐን ምእመናን ምሳሌ ነው
3. በውስጥና በውጪ በወርቅ የተለበጠ ነው 👉 አመቤታችን በነፍሷም በሥጋዋም ንጹሕ የመሆኗ ምሳሌ ነው
4. ፈለግ አለው 👉 የልቡናዋ ምሳሌ ነው
5. ብጽብጽ ወርቅ አለው 👉ሁከት መንፈሳዊ ነው እመቤታችን በጸጋ መንፈስ  ቅዱስ ምሥጢራት  በልቡናዋ ይወጣሉ ይወርዳሉና
6. አራት ቀለበት አለው 👉 አመቤታችን በአራት ወገን (ከርእይ ከሰሚእ ከአጼንዎ ከገሢሥ) ንጽሕት ናትና
7. ሁለት መሎጊያ አለው 👉 የአዳምና የሔዋን አንድም የዮሴፍና የሰሎሜ ምሳሌ ነው
8. ታቦቱ ርዝመቱ 2 ከንድ ተኩል ፣ ቁመቱ 1 ክንድ ተኩል ፣ ወርዱ 1 ክንድ ተኩል ነው ። ይህ ሲደመር  5 ክንድ ተኩል ነው ይኸውም 5500 ዘመንን የሚያሳይ ነው
የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ ከአማናዊት ታቦት እመቤታችን ጽላት ጌታ ተገኘ።

እመቤታችን 👇
• ሕሊናዋ ልቡናዋና አእምሮዋ በመንፈስ ቅዱሰ የተሞላ ነው
• ሕይወቷ ለጽድቅ የተሰጠ ነው
• አካሏ ለቅድስና የተሠዋ ነው
• እጆቿ አካለ መለኮትን የዳሠሡ ናቸው
•  እግሮቿ ለእኛ መዳን እንዲሆንልን እንዲደረግልን የተንከራተቱ ናቸው
• አንደበቷ ምስጋናን ብቻ ያውቃል
• ፍቅር እና ትሕትና ቋንቋዋ ነው
• በአጠቃላይ ቀድማ ትነሣኤ ልቡናን የተነሣች በመሆኗ የጌታ እናት የዓለም ሁሉ እናት ሆናለች
• ስለዚህም ከጌታ ቀጥላ ከእኛ አስቀድማ ተነሥታለች ዐርጋለች!!!
አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት" ብሎ ዳዊት እንደተናገረ (መዝ 131፥8)
እርሱ የመቅደሱ ታቦት ተነሥተዋል!!!

“ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው.....”
  — 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥23

በረከቷ አማላጅነቷ
ልጅዋ የሚቀበለው ጸሎቷ በሁላችንም ላይ ይደርብን🙏🙏🙏
ለዓመቱ በሰላም ያድርሰን🙏

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
@kinexebebe
Forwarded from መዝሙር ግጥሞች ቤት🛎EOC🔔✝️ (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
#ከ አየር ጤናም መነሻ አለ
#ከአያት ጣፎ ቅዱስ ገብርኤል
# ከ አያት አደባባይ
# የካ ሚካኤል ና መገናኛ
#አዲሱ ገቢያ

0953125078 እደዉሉ
@DA121922 አናግሩኝ
የመስቀል ጭውውት ለጠየቃችሁን
ርዕስ ፦ መስቀል

ሰብለ ፦ ሠላም ላንች ይሁን እህቴ  ኤደን እንዴት ነሽልኝ?
ኤደን ፦ እግዚአብሔር ይመስገን በuጣም ሰላም ነኝ ሰብልየ አንች እንዴት ነሽ የመስቀል በዓል እንዴት ነበር?
ሰብለ ፦ ሰላምሽ ይብዛልሽ እህቴ ኤደን እኔም በጣም ሰላም ነኝ የመስቀል በዓል በጣም አሪፍ ነበር አንች ጋስ?
ኤደን ፦ እሽ እህቴ ሰብለ በዓል እኔጋም በጣም አሪፍ ነበር።
ሰብለ ፦ መልካም  እህቴ ኤደን ስለ መስቀል እንድታስረጅኝ ብለሽኝ ነበር አይደል?

ኤደን ፦ አወ  እህቴ ሰብለ መስቀል ምን እንደሆነ አላውቅም ዝም በይ በየ አመቱ መስቀል እየተባለ ሲከበር አብሬ አከብራለሁ ግን ትርጉም ምን እንደሆነ አላውቅ እና አንች መንፈሳዊ ግሩብ ስላለሽ ብዙ ታውቂአለሽ እና ስለመስቀል ብዙ ጥያቂዎች አሉኝ ደስተኛ ከሆንሽ ብታስረጅ።
ሰብለ ፦ እሽ ኤደንየ ችግር የለውም ጠይቂኝ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከተረዳሁትና ከተማርኩት ከብዙ በጥቂቱ እመልስልሻለሁ።
ኤደን ፦ እሽ ሰብልየ ጥያቂውን እንድጠይቅሽ እድል ስለሰጠሽኝ በጣም አመሰግናለሁ።
ሰብለ ፦ እሽ ኤደንየ  ችግር የለውም ስዓት እየሔደ ስለሆነ ቶሎ ተሎ ጠይቂኝ።

ኤደን ፦ እሽ እህቴ የመጀመሪያው ጥያቂ መስቀል ማለት ትርጉሙ ምን ማለት ነው?
ሰብለ ፦ ቃለ ህይወትን ያሰማልን አረፍ ጥያቂ ነው። መስቀል ማለት ሰቀለ አመሳቀለ ትምህረተ መስቀል (የመስቀል አድራጊ) ካለው የግዕዝ ቃል የመጣ ሲሆን   ትርጉሙም የተመሳቀለ እንጨት ማለለት ነው።
ኤደን ፦ በእውነት ሰብልየ ቃለ ህይወትን ያሰማልን   ፀጋውን ያብዛልሽ።

ሰብለ ፦ አሜን እህቴ ኤደን አብሮ ያሰማልን  እሽ ቀጥይ ጥያቂሽን።
ኤደን ፦ እሽ እህቴ ሰብለ እየሱስ ክርስቶስ በመስቀለይ የተሰቀለበት ምክንያት ምንድን ነው ?
ሰብለ ፦ መልካም እህቴ ኤደን ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተሰቀለበት ምክንያት አዳምን በሞተበት ለማዳን ዳቢሎስን በገደለበት ለመግደል ነው።

ኤደን ፦ እሸ እህቴ ሰብለ ቃለ ህይወትን ያሰማልን አዳም የሞተው እንዴት ነው ዳቢሎስስ አዳምን የገደለው ምን ብሎ ነው?
ሰብለ ፦ እሽ እህቴ ኤደን ጥሩ ጥየቄ ነው አዳም የሞተው ዕፀ በለስ በልቶ ነው ዳቢሎስ ደግሞ አዳምን የገደለው ዕፀ በለስ ብትበላ አምላክ ትህናለህ ብሎ ነው።
ሔደን ፦ እሽ እህቴ ሰብለ ቃለ ህይወትን ያሰማልኝ  መስቀል ባይኖር ክርስትና ምን ይሆናል?

ሰብለ ፦ አሜን እህቴ ኤደን አብሮ ያሰማልን መስቀል ባይኖር ክርስትና ትርጉም የለውም ምክንያቱም አባታችን ቅዱስ ያሬድ እንደተናገረው መስቀል የሰላም ምልእክት ነው ዳቢሎስ ሞቶበታል እኛ ድነንበታል ሲል ተናግሮታል ስለ ዚህ መስቀል ምልእክት ነው፣ መድኃኒት ነው፤ መስቀል ደህንነት የተፈፀመበት ነው። እንዲሁም ድንግል ማርያምና መስቀል ለነገረ ድህነት ትለቅ ቦታ አላቸው በተጠማሪም ድንግል ማርያመና መስቀል ለአዳም የተሰጡት የተስፋ ቃል ናቸው።

ኤደን ፦ በእውነት እህቴ ሰብለ ቃለ ህይወትን ያሰማልን ፀጋውን ያብዛልሽ ካልሰለቸሽና ካለደከመሽ አሁንም ጥያቄ አለኝ።
ሰብለ ፦ አሜን እህቴ ኤደን የእግዚአብሔር ቃል መቼም አይሰለችም አያደክምም ጠይቂኝ።
ኤደን ፦ እሽ እህቴ ሰብለ መስቀልን ለምን እናከብራለን?
ሰብለ ፦ እሽ እህቴ ኤደን መስቀልን የምናከብረው ጌታችን እየሱስ ክረስቶስ የተሰቀለበት ዳቢሎስን ድል የነሳበት እኛ የዳንበት ስለሆነ ነው። እንዲሁም መስቀል የሚገድልና የሚያድን ነው።

ኤደን ፦ እሽ እህቴ ሰብለ መስቀል የሚገድል እና የሚያድን ነው ስትይ ምን ማለትሽ ነው?
ሰብለ ፦ እሽ እህቴ ኤደን መስቀል የሚያድን ነው ስል እኛ ድነንበታል መስቀል ገዳይ ነው ስል ደግሞ ዳቢሎስ ሞቶበታል ማለቴ ነው:: አባታችን ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንዲህ ብሎል ክርስቶስ በመስቀሉ ዳቢሎስን ገደለው ስለዚህ መስቀል ዳቢሎስ የሞተበት እኛ የዳንበት ነው ማለት ነው እህቴ ኤደን አሁንስ ግልፅ ሆነልሽ?

ኤደን ፦ አወ እህቴ ሰበለ ግልፅ ሆኖልኛል ቃለ ህይወትን ያሰማልኝ እሽ የመጨረሻ ጠያቄ ልጠይቅሽና ይበቃናል እህቴ ሰብለ አንድ መፅሐፍ ቅዱስ ሳነብ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ከሰባት እንጨት የተዘጋጀ ነው ይላል ሰባት የሆነበት ምክነንያት ምነድን ነው?

ሰብለ ፦ እሽ እህቴ ኤደን እኔም ስራ አለኝ የመጨረሻሽን ጥያቄ ልመልስልሽና እንሰነባበታለን። ክርስቶስ  የተሰቀለበት መስቀል  እንጨት 7 የሆነበት ምክንያ 7ቁጥር በእብራዊያን ፍፁም ቁጥር ማለት ነው እንዲሁም የሰው ልጅ የተፈጠረው ከ7 ባህሪያት ነው ማለትም ከአራቱ ባህርያተ ስጋና ከሶስቱ ባህርያተ ነፍስ ነው።

ኤደን ፦ እሽ እህቴ ሰብለ  ቃለ ህይወትን  ያሰማልኝ ፀጋውን ያብዛለልሽ በዙ ነገር አሳወቅሽኝ በእውነት ከለብ አመሰግናለሁ።
ሰብለ ፦ አሜን ኤደንየ ችግር የለውም እንዲህ የጠፋሽን ነገር ጠይቂኝ እኔም የቻልኩትን እመልስልሻለሁ አሁን ስአት እየሔደ ስለሆነ ወደ  ቤቴ  ልሔድ ቻው እሽ ኤደየ የኔ ቆንጀ።
ኤደን ፦ እሽ ሰብልየ ቻው  መልካም ቀን ይሁንልሸ።
ሰብለ አሜን ኤደንየ ለሁላችን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን !!
@kinexebebe
2025/06/26 16:36:39
Back to Top
HTML Embed Code: