Telegram Web
እግዚአብሔር እረስቶኛል አትበል
ትርጉም ገብረእግዚአብሔር ኪደ
እግዚአብሔር እረስቶኛል አትበል!

ስሙት ታተርፉበታላችሁ...
አሮጌውን ሰው አስወግዱ
ገብረእግዚአብሔር ኪደ
አሮጌውን ሰው አስወግዱ

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Audio
እምነት እንደ ቅቤ

(መንፈሳዊ ትረካ)
+++ድንቅ ልዩነት ተመልከቱ+++

በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ፈርዲናንድ ማጄላን ዓለምን በመርከብ ዞረ።

👉ሐዋርያቱ ደግሞ መርከባቸውን ጥለው ዓለምን ዞሩ!

ዛሬ ይዘንባል እያሉ ትንቢት የሚተነብዩ ሜትሮሎጂስቶች ሞልተዋል።

👉እንደ ኤልያስ ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን የዘጋ ዳግመኛም ዝናብን ያዘነበ ከቶ የለም።

በላብራቶሪው ተመራምሮ ህሙማንን የፈወሰ ሞልቷል።

👉እንደ ጴጥሮስ ጥላው ድውይ የፈወሰ ከቶ አላየሁም።

በዘፈኑ አጋንንትን የጠራ እንደ ማይክል ጃክሰን ሞልቷል።

👉እንደ ዳዊት በበገና መዝሙሩ አጋንንትን ያስወጣ እስከ ዛሬ አልተገኘም።

ከረቫትና ሱፉን ለብሰን የምንጎራደድ ሞልተናል።

👉የልብሱ ቁጨት አጋንንት ያስወጣ እንደ ጳውሎስ ከቶ አልተገኘም።

የግብጽ ነገሥታት አጽማቸው በክብር ይቀመጣል።

👉ዐጥንቱ ሙት ያስነሳ እንደ ኤልሳዕ ከቶ አላየንም።

በአሜሪካ የነገሥታትን ምሥጢር የሚሰልሉ ድርጅቶች ሞልተዋል።

👉እንደ ኤልሳዕ በእስራኤል ሆኖ በሶሪያ ቤተመንግሥት የሚደረገውን ምሥጢር ያወቀ አልተገኘም።

ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃን በእግሩ የረገጠ ዩሪ ጋጋሪ ዛሬ ብዙዎቹ አድርገውታል።

👉እንደ ኢያሱ ፀሐይን ያቆመ ከቶ አልተገኘም።

በነገራችን ላይ በተፈጥሮ ሕግ መሰረት ፀሐይ በመሃል ቆማ መሬት ዙሪያውን ትዞራለች። በፀሐይ ፊት ያለው የመሬት ክፍል ቀን ሲሆን ሌላኛው ጎን ደግሞ ማታ ይሆናል።

እነ ኢያሱ በሚዋጉበት ጊዜ መሬት ከፀሐይ ፊቷን አዙራ ቀኑ ሊጨልም ነበር።

👉ኢያሱ ግን መሬት እንዳትዞር አደረጋት! ፀሐይን በገባኦን አቆመ ተባለ! መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ

ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም።

👉 እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበርና ((እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።))
የዓለም መሪዎች ከአስር በላይ ቋንቋ መናገራቸውን እንጃ፤

👉ሐዋርያቱ ግን 72 ቋንቋ ተገለጠላቸው።

ኃያላን ነገሥታት ድውይ እንኳን መፈወስ አይችሉም።

👉ቅዱሳኑ ግን የ70 የ80 ዘመን ሬሳ አስነሱ።

👉ጠቢባን ነን የሚሉ ጸሐፍት ፈሪሳዊያንን ምላሽ ያሳጣቸው ዘንድ ጥበብ ያልነበራቸውን ዓሳ ወጋሪ የነበሩ ሐዋርያትን መረጠ።

ኃያላን ነገሥታት የመሰሉ መሪ ዳዊትን የመሰሉ ነገሥታትን የወለዱ የከበሩ እናቶች ሞልተዋል።

👉የነገሥታትን ንጉሥ ክርስቶስን የወለደች እናት ግን አንድ ብቻ ናት።

ይህችውም ከሴቶች መካከል ተለይታ የተባረከችው ድንግሊቱ 👉 ማርያም ናት 👈

           
ስብሐት ለእግዚአብሔር!

@kinexebebe
እንኳን አደረሰን!

☞በእንተ #እግዝእትነ #ማርያም ድንግል፤
ወበእንተ #ኢየሱስ #ክርስቶስ ወልዳ ፍቁር፤

☞ዝክሩ ስመ አበዊነ ቅዱሳን #ነቢያት #ሙሴ #ወአሮን #ዳዊት #ወሰሎሞን #ዕዝራ #ወዘካርያስ እለ አውኃዙ ተነብዮ በእንተ አማናዊት #እምነ #ጽዮን፡፡

"" ጸጋ ዘአብ ፥ ኂሩት ዘወልድ ሱታፌ ዘመንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ፡ ወበረከታ ለእምነ #ጽዮን_ማርያም ፡ ተፋቅሮ #ዘነቢያት #ወዘሐዋርያት ወዘአበው ቀደምት ቅዱሳን ፡ ወትረ የኀሉ ምስሌየ ወምስለ ኩልክሙ፡፡ አሜን፡፡ ""

https://www.tgoop.com/kinezebebe
​​እንኳን ለጽዮን ማርያም ማሕደረ አምላክ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በየዓመቱ ኅዳር ፳፩ ቀን በታቦተ ጽዮን የተፈጸሙ ታላላቅ ተአምራት የሚታሰቡበት ቀን ነው፡፡ በዚህ ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የታቦተ ጽዮንን ተአምራት እግዚአብሔር ቃል ቅድስት ድንግል ማርያምን ታቦቱ አድርጎ ከፈጸማቸው ታላላቅ የድኅነት ሥራዎች ጋር በማነጻጸር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በነገረ ድኅነት ውስጥ ያላትን ድርሻ በስፋት ታስተምራለች፡፡

ለምሳሌ እስራኤላውያን ባሕረ ዮርዳኖስን በአቋረጡበት ወቅት ታቦተ ጽዮንን የተሸከሙ ካህናት እግራቸው የዮርዳኖስን ባሕር በመንካቱ ባሕሩ ለሁለት ተከፍሎ ነበር፡፡ ይህንን ታሪክም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ በመወለድና ጥምቀትን በመመሥረት ከሰይጣን ባርነት ወደ እግዚአብሔር ልጅነት እንዳሸጋገረን በማመሥጠር ቤተ ክርስቲያናችን ታስተምርበታለች፡፡ ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤላውያን ጋር ውጊያ በገጠሙበት ወቅት ታቦተ ጽዮንን ከእስራኤላውያን ማርከው ዳጎን በሚባለው ቤተ ጣዖታቸው ውስጥ አኑረዋት በነበረ ጊዜ ታቦቷ የዳጎንን ምስል አንኮታኩታ ጥላው ነበር፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ይህን ታሪክ እንደ ምሳሌ በመጠቀም ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደው በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ከአምልኮ ጣዖት ወጥተን አንድ አምላክን ወደ ማምለክ ስለ መመለሳችንና በእመቤታችን ምክንያት ስለ ተደረገልን የእግዚአብሔር ቸርነት ትምህርት ትሰጥበታለች፡፡

እኛም በዛሬው ዘግጅታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማናዊቷ ታቦተ ጽዮን መኾኗን የሚያስቃኝ ትምህርት ይዘን ቀርበናል፤ እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ካወጣቸው በኋላ የአምልኮ ሥርዐታትን ይፈጽሙበት ዘንድ የምስክሩን ድንኳን፣ የቃል ኪዳኗ ታቦትንና ለአምልኮ ሥርዐቱ ማከናወኛ የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ንዋያተ ቅድሳትን እንዲሠሩ አዝዟቸው ነበር፡፡ ከቃል ኪዳኗ ታቦት ውስጥም በእግዚአብሔር ጣት ዐሥርቱ ትእዛዛት የተጻፉበት የሕጉ ጽላት፤ ዐርባ ዓመት ሙሉ እስራኤላውያን በሲና ምድረ በዳ የተመገቡትን መና የያዘች መሶበ ወርቅ፤ አሮን ለክህነት አገልግሎት ስለ መመረጡ ምስክር የኾነችው፣ ለምልማና ፍሬ አፍርታ የተገኘችው የአሮን በትር ይገኙባታል /ዕብ.፱፥፬/፡፡ ደብተራ ድንኳኗንና በውስጧ የሚገኙ ንዋየተ ቅድሳትን እግዚአብሔር በሙሴ ሲያሠራ ለሰማያዊው ምሥጢር ምሳሌና ጥላ ናቸውና ተጠንቅቆ እንዲሠራቸው አዝዞት ነበር /ዕብ.፰፥፭/፡፡

ቅዱስ ጳውሎስም ይህችን ድንኳን ‹‹የአገልግሎት ሥርዐታት የሚፈጸምባት ፊተኛይቱ ድንኳን›› ብሎ ይጠራታል፡፡ በዚህ መሠረት ደብተራ ድንኳኗና በውስጧ ያሉ ንዋያተ ቅድሳት ለሰማያዊው ምሥጢር ምሳሌና ጥላ እንደ ኾኑ እንረዳለን፡፡ የደብተራ ድንኳኗ ምሳሌ የኾችው ሰማያዊቱ ስፍራም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ በውስጧ አማናዊውና ሰማያዊው ምሥጢረ መለኮት ይፈጸምባታልና፡፡ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካሉ ስለ ኾነች፤ ዘለዓለማዊ ሕይወትን የሚያሰጥ ምሥጢርም በውስጧ ስለሚከናወንባት በእርግጥም ሰማያዊ ስፍራ ናት፡፡ ታቦተ ጽዮን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትመሰላለች፡፡ ይህን ለመረዳት ግን ስለ ታቦተ ጽዮን አሠራርና መንፈሳዊ ትርጉም አስቀድመን ልንረዳ ይገባናል። እግዚአብሔር አምላክ ታቦተ ጽዮንን እንዲሠራ ብልሃትን፣ ጥበብን፣ ማስተዋልን፣ ዕውቀትን ይለይ ዘንድ መንፈሱን ያሳደረበትን ከይሁዳ ወገን የኾነውን ባስልኤልን መረጠ /ዘፀ.፳፭፥፱/፡፡ እርሱም እግዚአብሔር በሰጠው ማስተዋል ከማይነቅዝ እንጨት ርዝመቷ ሁለት ክንድ ተኩል፤ ወርዱዋ አንድ ክንድ ተኩል፤ ቁመቷ አንድ ክንድ ተኩል እንዲኖራት አድርጎ ታቦቷን ሠራት፡፡

በመቀጠል በውስጥም በውጪም በጥሩ ወርቅ ለበጣት፣ ከታቦቷም ዙሪያ የወርቅ አክሊልን አደረገላት፡፡ ካህናት ታቦተ ጽዮንን ለመሸከም እንዲረዳቸውም በአራቱም መዓዘናት በወርቅ የተሠሩ ቀለበቶችንና በእነርሱም ውስጥ የሚገቡ ሁለት መሎጊያዎችን ሠራ፡፡ ከጥሩ ወርቅም የስርየት መክደኛውን በቃል ኪዳን ታቦቷ ላይ በርዝመቷና በወርደዋ ልክ ሠራ፡፡ የስርየት መክደኛውን እንዲጋርዱት አድርጎም ጥሩ ከኾነ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ኪሩቤልን ሥሎ በስርየት መክደኛው ግራና ቀኝ አስቀመጣቸው፡፡ እነዚህ በጥሩ ወርቅ የተሠሩት ሁለቱ ኪሩቤል ፊታቸው ወደ ስርየት መክደኛው ኾኖ እርስ በእርሳቸው እንዲተያዩ ተደርገው የተሠሩ ናቸው፡፡ በዚህ በስርየት መክደኛው በሁለቱ ኪሩቤል መካከል እግዚአብሔር ለሙሴ እየተገለጠ ሰው ከባልንጀራው ጋር እንደሚነጋገር በግልጽ ያነጋግረው ነበር፤ ለሕዝቡም በደመና ዐምድ ይታያቸው ነበር /ዘፀ.፰፥፲፩፤ ፳፭፥፳፪-፴፫/፡፡

ወደ ምሥጢሩ ትርጓሜ ስንመለስም ታቦተ ጽዮን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ስትኾን፣ በውስጧ የያዘችው የሕጉ ጽላትም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቷ ከማይነቅዝ እንጨት መሠራቷ የእመቤታችንን ንጽሕና የሚያመለክት ሲኾን፣ በውጪም በውስጥም በጥሩ ወርቅ መለበጧ ደግሞ ቅድስናዋንና በሁለት ወገን ድንግል መኾኗን የሚያስረዳ ነው፡፡ ታቦተ ጽዮን በግራና በቀኝ በኩል በተዘጋጁ አራት ከወርቅ የተሠሩ ቀለበቶች ነበሯት፤ በእነዚያ የወርቅ ቀለበቶች ውስጥም ሁለት መሎጊያዎች ይገቡባቸው ነበር፡፡ ታቦቷን ለማንቀሳቀስ ባስፈለገ ጊዜ አራት ሌዋውያን ካህናት በመሎጊያዎቹ ይሸከሟታል፡፡

​​ይህ ሥርዐት በሰማያትም የሚታይ እውነታ ነው፡፡ የጌታን መንበር ገጸ ሰብእ፣ ገጸ ንሥር፣ ገጸ ላህምና ገጸ አንበሳ ያላቸው አርባዕቱ እንስሳት ይሸከሙታልና /ኢሳ.፮፥፩-፭፤ ሕዝ.፩፥፩-፲፮/፡፡ ለአማናዊቷ ታቦት ለቅድስት ድንግል ማርያምም ሰላምን የሚያወሩ፣ መልካም የምሥራችንም የሚናገሩ፣ መድኀኒትንም የሚያወሩ፣ ጽዮንንም ‹‹አምላክሽ ነግሦአል›› የሚሉ፣ እግሮቻቸው በተራሮች ላይ እጅግ ያማሩ የእርሷንና የጌታችንን ስም ተሸክመው ወንጌልን ለዓለም የሚሰብኩ ኦርቶዶክሳውያን መምህራን አሏት /ኢሳ.፶፪፥፯/፡፡ የስርየት መክደኛው መቀመጫው የንጹሐን አንስት፣ መክደኛው የንጹሐን አበው፣ ግራና ቀኙ የሐናና የኢያቄም ምሳሌ ነው፡፡ በክንፎቻቸው የጋረዱት  ኪሩቤልም የጠባቂው መልአክ ቅዱስ ሚካኤልና የአብሣሪው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ምሳሌዎች ናቸው፡፡

የስርየት መክደኛው ስርየቱ የሚፈጸምበት ስፍራ ቢኾንም ነገር ግን በዚህ ቦታ ምንም ዓይነት መሥዋዕት አይቀርብም ነበር፡፡ ይህም በጊዜው አማናዊው መሥዋዕት ገና እንዳልተሠዋ ያስገነዝበናል፡፡ ይህ ስፍራ እግዚአብሔር ለሙሴ የሚገለጥበት ቦታ ነው፤ ከእርሱ ውጪ ሌላ ነገር በእዚያ ላይ ማረፍ አይችልም ነበር፡፡

ከዚህም የምናስተውለው አንድ ምሥጢር አለ፤ ይኸውም እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም የገባውን ቃል ኪዳን ሊፈጽም ሰው በኾነ ጊዜ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብበት ልዩ ስፍራ እንዳዘጋጀ ያመላክተናል፡፡ ይህ ስፍራ አማናዊ መሥዋዕት የሚቀርብበት ቦታ እንደሚያስፈልግ የሚያስገነዝብ ስፍራ ነው፡፡ ይህን ለማመልከትም ለኃጢአት ስርየት የቀረበው መሥዋዕት ከታረደ በኋላ ካህኑ ደሙን በጣቱ እየነከረ ሰባት ጊዜ በስርየት መክደኛው አንጻር በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ይረጨው ነበር /ዘሌ.፬፥፮/፡፡ ነገር ግን ይህ ደም ከስርየት መክደኛው ላይ አያርፍም ነበር፤ ምክንያቱም በዚህ ስፍራ መቅረብ የሚገባው አማናዊው መሥዋዕት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነውና፡፡
ይህ የስርየት መክደኛ ለእኛ የሚያስተላልፈው ተጨማሪ መልእክትም አለው፡፡ ይኸውም አማናዊው መሥዋዕት ክርስቶስ መሥዋዕት ኾኖ ዓለምን ማዳኑ እንደማይቀርና መሥዋዕቱ የሚቀርብበት ስፍራም በቅድስተ ቅዱሳኑ (ቤተ መቅደሱ) ውስጥ እግዚአብሔር በምሕረት በሚገለጥበት በቃሉ ማደሪያ በጽላቱ ላይ መኾን እንደሚገባው ያስገነዝበናል /ዕብ.፬፥፲፮/፡፡ ይህም እግዚአብሔር አምላክ በነቢዩ ሚልክያስ ላይ አድሮ ‹‹ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይኾናልና በየስፍራውም ስለ ስሜ ዕጣንን ያጥናሉ፤ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፤›› /ሚል.፩፥፲፩/ በማለት እንደ ተናገረው የስርየት መክደኛው አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሥጢረ ቍርባንን ለምትፈጽምበት ጽላት ወይም ታቦት ምሳሌ መኾኑን ያሳየናል፡፡

የስርየት መክደኛውን የሚጋርዱት በጥሩ ወርቅ የተሠሩት የኪሩቤል ምስሎችም አማናዊው መሥዋዕት በሚሠዋበት ጊዜ በዙሪያው ረበው የሚገኙ የመላእክት ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችን እንዳስተማሩን ሁለቱ ኪሩቤል የተባሉት ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ናቸው፡፡ ይህን ለማስገንዘብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በመንበረ ታቦቱ ላይ ምስለ ፍቁር ወልዳ እንዲቀመጥ ታዝዛለች፡፡ ምስለ ፍቁር ወልዳን  ላስተዋለ ሰው በትክክል የታቦተ ጽዮንን መንፈሳዊ ትርጕም ይረዳል፡፡

ታቦተ ጽዮን ከሌሎች የብሉይ ኪዳን ንዋያተ ቅድሳት በተለየ መልኩ እጅግ ግሩም የኾነ ምሥጢርን በውስጧ ይዛለች፡፡ ይህን ድንቅ ምሥጢር ለመረዳትም አንድ ምሳሌ እንመልከት፤ ንጉሥ ዳዊት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑ ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ጽዮን ከተማ ባስመጣበት ወቅት በታቦቷ ፊት በሙሉ ኃይሉ በደስታ እየዘለለ ለእግዚአብሔር መንፈሳዊ መዝሙርን አቅርቦ ነበር /፪ሳሙ.፮፥፲፪-፲፯/፡፡ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሚኾን ድርጊት በሐዲስ ኪዳንም ተፈጽሟል፡፡ ይኸውም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለቅድስት ኤልሳቤጥ ሰላታ በሰጠቻት ጊዜ የስድስት ወር ፅንስ የነበረው ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የእመቤታችንን የሰላምታ ድምፅ በሰማ ጊዜ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ኾኖ በደስታ ዘሏል (ሰግዷል) /ሉቃ.፩፥፵፬/፡፡ ቅዱስ ዳዊት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት እየተደሰተ ለአምላኩ የምስጋና ቅኔን መቀኘቱም ለሰው ልጆች ዅሉ የመዳናችን ምክንያት የኾነችውን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን በቃል ኪዳኗ ታቦት በኩል አስቀድሞ በዓይነ ሕሊና ስለ ተመለከታቸው ነበር፡፡

ዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@kinexebebe
          #ጎጆ_ቀለስኩልህ

         (በሰመረ ፍስሃ)

በአውላላ ሜዳ በጠራራ ፀሐይ
ከአስፓልቱ አጠገብ ስኖር ጎዳና ላይ
የበጋውን ንፋስ በዙሪያዬ ከቦኝ
እንደ ዥዋዥዌ ወዲያ ሲወስደኝ፡፡
...................ወዲህ ሲመልሰኝ

ዝናቡ በተራው ጉዴን ተመልክቶ
...................ጉድፌን አፅድቶ
ይወደኝ ይመስል ልብሴን ያጥብልኛል
ጎጆዬን አፈራርሶ በብርድ ይገርፈኛል፡፡

ከዚህ የባሰ ግን ሰዉ ነው 'ሚገርመኝ
በነጋ በጠባ መተንፈሻ ያሳጣኝ፡፡

ስለተናገርኩኝ ማጣት መከፋቴ
የእውነት ስለኖርኩኝ ውሸትን ጠልቼ
አፋቸውን ሞልተው እብድ ነው ይሉኛል
አንዳንዴ ሲያሻቸውም ድሃ ነው ይሉኛል፡፡

የሆነው ሆነና ቅር አላለኝም
አጣሁኝ ብዬም አላማረርኩም
ጌታ እንዳስተማረኝ ለበጎ ነው ብዬ
የማይቻል የለም እኖራሎህ ችዬ፡፡

ይሄውልህ ግን ሚካኤል ሆይ...
የሰው ልጅ ሲሸሸኝ ማንነቴን አይቶ
ሰላምታ ሲነፍገኝ ኑሮዬን ተመልክቶ
አንተ ግን አንተ ነህ የአምላክ መልእክተኛ
ሁሌ  'ምትጠብቀኝ መቼም የማተኛ፡፡
ምንም ሳይገድብህ ከቤቴ ገብተሀል
ድሃዋን ጎጆዬ በፍቅር ጎብኝተሀል፡፡

እናም ሚካኤል ሆይ....
ከኔ እንዳትርቅ ስለሳሳሁልህ
በንፁህ ልቤ ውስጥም ጎጆ ቀለስኩልህ፡፡
@kinexebebe
+++እንኳን አደረሰን+++
ዱራ ሜዳ አድምጭ፥ ንጉስ ሆይ ስማ፤
መለከት ቢጮህ፥ አዋጅ ቢሰማ።
እንኳን አድኖን፥ ባያድንንም፣
አንተ ላቆምከው፥ ምስል አንሰግድም።

ፍሙ እየጋለ ፥እጥፍ ቢነድ፤
ገብርኤል መጣ፥ እሳት ሊያበርድ።
እንደ ንጉስ፥ ልጅ ተመላለሱ፤
እሳቱን ውሀ፥ አርጎት ቅዱሱ።

ሰልስቱ ደቂቅ፥ ሞትን ሳፈሩ፤
ነበልባል መሀል፥ በእምነት ዘመሩ።
ለአምላካቸው እጅ እየነሱ፤
በእሳት መካከል ተመላለሱ።

አንዷን ቤታችንን፥ ሊያቃጥል ሊያነዳት፤
ሀገር እንዳልሰራች፥ ጠላት ተነሳባት።
የእሳቱን ነበልባል፥ አብርደው መላኩ፤
በቁጣህ ተመለስ፥ ተዋህዶን ለነኩ።

አመቱን በሰላም፥ እንዳስጀመርከን፤ 
ደሞ የዛሬ አመት፥ ሰላም አድርሰን፤
+++
@kinexebebe
# ስንት ቀን ፈጀብህ?
/መንፈሳዊ መነባንብ /
-----------------✞-------------------
ለአዳም ኪዳን ሰጠህ
እንደምትወለድ ወደ ምድር ወርደህ
እንዴት ነበር ያኔ..?
ወደ እኛ ስትመጣ መላእክትን ትተህ?
………
የሔዋን እርግማን
የባሏም የውርስ ኃጢአት መዘገን
እንዲያ አሳሰበህና
መጣህልን ሁሉን አደረግህ በፅሙና
.........
እንዴት ነበር ያኔ..?
ያችን ንጹሕ ለመፈለግ የወሰደብህ ጊዜ
አድርገህ የሰጠኸንን ፈውስ በበድልን ጊዜ
ግን ምን ያህል ነው ልፋትህ?
ድንግልን ስትፈልግ የፈጀብህ?
.........
ከሰማያት ስትወርድ አጀቡህ መላእክት?
ዓለሙስ ተናወፀ በይባቤ በስብሐት?
ያ ምቀኛ ዲያቢሎስ ግን ምን አለ?
ወደ እኛ ስትመጣ አለ አይደል ኮበለለ?
ነው ሥጋ ለብሶ ጉድ ሠራኝ አለ?
........
እንዴት ነው እርቀቱ
የሰማይ ምጥቀቱ
የምድርስ ሥፋት
ከሷ እስክታርፍባት?
ግን ጌታ...?ሰማያት ምን አሉ
ትትሀቸው መጠህ ባንተ አጉረመረሙ?
ፍጥረታትስ ቢሆን ማሕሌት አቆሙ?
.......
ምሥጢረኛው ጌታ
መንገድህ በየት ነው ወደ እኛ ስትመጣ?
ቤተ ልሔም ስትደርስ
ማን አገለገልህ?ምን አለች ምድሪቱስ
እያቄም ወሐናን እንዴት መረጥሃቸው
አንተ እንድትወለድ ምክንያትህ ናቸው
.......
ሰማዩ ሰፊ ነው
ምድርንም ታውቃለህ
እንዴት እንድትሰፋ ሆና መረገጫህ
ግን እና ጌታ ሆይ ምኑ ነው የቻለህ?
የድንግል ማሕጸን እሳት መሸከሙ
ምድርም መልኮት በእሷ ላይ መቆሙ
..........
እንዴት ነበር ያኔ
በቤተ ልሔም ውስጥ
አንተን የሚያሞቅ ከእንስሶች ስትሰጥ?
........
ዮሴፍ ምን አለ
አንተን በማየቱ እርጅናው ታጎለ?
አንተን የጠበቀህ አዳምስ በግርማህ ምን አለ?
........
እንዴት ነው ስጦታው
የሰብአ ሰገሉ ወርቅ እጣን አምኃው
የእረኞቹ ደስታ
የመላእክት ብሥራት የልደትህማታ
.........
እንዴት ነበር ያኔ
የልደትህ ማታ
የዝማሬው ለታ
የእናትህ ደስታ
የፍጥረት እልልታ
ሚዳቋ ስትዘል ከኢትዮጵያ አይታ
ግን ጌታ እረቂቁ አምላክ
በየትስ መጠህ ነው ከኛ የተወለድክ


✞ስብሐት ለእግዚአብሔር ✞


*ከሮቤል ጌታቸው
@kinexebebe
፨እልል የምስራች ክርስቶስ ተወልዷል፨
በተባረከችው በዚያች በውብ ምሽት
እረኞችም ሁሉ እደጅ ባደሩበት
ህፃን ተወለደ በከብቶች ግርግም ውስጥ
ቤዛ ሊሆን ኋላ ለዓለም ነፍሱን ሊስጥ
ጌታ ተወለደ የእስራኤል ንጉስ
ከአለም እርኩሰት ትውልድን ሊመልስ
እልል..!የምስራች ክርስቶስ ተወልዷል
ከእናቱ ከማርያም ከማህፀኗ ወጥቷል።
በዚያች ቅድስት ለሊት በከብቶች በረት ውስጥ በጨርቅ ተጠቅልሎ
በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን ለሰው ልጅ አድሎ
ሊያኖረን ተወልዷል የሠራዊት አምላክ አልፋና ኦሜጋ
ከእናቱ ከማርያም ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ከስጋዋ ሥጋ
እልል... የምስራች ኢየሱስ ተወልዷል
አለምን ከጥፋት ሊያድን ምድር ወርዷል
ከእግዜር የተላኩት ቅዱሳን መላዕክት ብሥራት አብስረዋል
ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ሲሉም መዝሙር ዘምረዋል።
እኛም እስቲ እንዘምር እናሸብሽብላት በምሥጋና ዜማ
የጌታን መወለድ ያልሰማ እንዲሰማ የሰማ እንዲያሰማ።
እልል... የምስራች ክርስቶስ ተወለዷል
ከእናቱ ከማርያም ከማህፀኗ ወጥቷል።
@kinexebebe
ወልድ ተወለደ 🤲😊
የአብ ቃል ክርስቶስ ወልድ ተወለደ
የፍቅር ባለቤት ወደ ምድር ወረደ
ከአብ ካባቱ ጋር ሊያስታርቀን ወደደ
ቅዱስ እግዚአብሔር ሊታረቀን ወዶ
ከሞት አተረፈን አንድ ልጁን ሰዶ
ዳግም በመንግስቱ እንኖር ዘንድ ፈቅዶ
ይህው ተቀበለን እጆቹን ዘርግቶ
አዳም ምህላውን ቃል ኪዳኑን ሰምቶ
ይጠብቅ ነበረ በተስፋ ተሞልቶ
እሱ በሌለበት ቢመጣም ዘግይቶ
የእስራኤል ንጉስ መወለዱን ሰምቶ
ይዘምር ነበረ በሳት ውስጥ ተውጦ
ከልጆቹ ጋራ በሲኦል ተቀምጦ
ከንፆህይቷ እመቤት ከድንግል ማርያም
ይህው ተወለደ በቤተልሔም ግርግም
በከብቶች በረት ውስጥ ክብሩን በማይመጥን
ራሱን ዝቅ አርጎ ከፍ ሊያረግ እኛን
ከሱ እንማር ዘንድ ፍፁም ትህትናን
ተወለደ እየሱስ የአለሙ ንጉስ
ተወለደ ጌታ የፍጥረት ሁሉ ፈውስ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@kinexebebe
@kinexebebe
@kinexebebe
ምስክር ነኝ አኔ
ምስክር ነኝ አኔስ ሳለሁ በህይወቴ
ኦርቶዶክስ ነችና አንዲቷ እምነቴ
ከጥንት አባቶቼ የዘረስኳት ማንነቴ
ተዋህዶ ነችና የዘለዓለም ቤቴ
ሀጢያትን ሰርቼ ብዙ በድያለሁ
ትዕዛዙንም ጥሼ ሰውንም ንቄያለሁ
አንድ ተስፋ እንዳለኝ አሁን አውቄያለሁ
ስታመም ድኜበት ስቸገር አግኝቼ ሳዝንም ተደስቼ መጥቻለሁና ሁሉንም አግኝቼ
የጎደለው ሞልቷል ወደ አንቺ መጥቼ
ዛሬን መስክሬያለው ሁሉንም አይቼ
ነፅቻለሁና ንስሀ ገብቼ
ለስጋ ወደሙ ክብርም በቃሁኝ
ሰላም የሞላበት ህይወትን አየሁኝ
በተዋህዶ ዕምነቴ ክብር አገኘሁኝ።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@kinexebebe
@kinexebebe
@kinexebebe

የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳን ስለ ጌታችን ጥምቀት

አቤቱ የሰማያት የምድር ጌታ ሆይ አሁንስ እኔን ባርያህን አጥምቀኝ፡፡ በእጅህ የሠራኸውንም አንፃው፡፡ መድኃኒት የሆነች ቀኝህንም ዘርጋ፡፡ ወደ መንግሥትህ በፍጥነት እሄድ ዘንድ ለኃጥአንም የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ብየ እሰብክ ዘንድ በእርሷ ከልለኝ፡፡

አንተም ዮርዳኖስ ሆይ ዛሬ ከኔ ጋር ደስ ይበልህ፡፡ እግዚአብሔር አምላክህ በአንተ ዘንድ ቁሟልና፡፡ እናንተም ተራሮች፣ ኮረብቶች፣ ባሕሮች፤ ወንዞች፤ ፈሳሾች እና የውኃ ምንጮች ሁሉን የቀደሰውን እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ አቤቱ አምላኬ ሆይ ባርከኝ፤ ውኆችንም ሁሉ አክብራቸው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ ለዮሐንስ እንዲህ አለው፡፡ አሁንስ ዝም በል፡፡ ሕጌንና ሥርዐቴን ልፈጽም እፈልጋለሁና፡፡ ልሠራው የወደድሁትንም አትቃወመኝ፡፡ ጠላት ዲያብሎስ ሰምቶ እኔን መጣላቱን እንዳይተው የመለኮቴን ክብር አትናገር፡። ዛሬ ለእኔ እና በእኔ ለሚያምኑ ሁሉ በደስታ ታላቅ ምልክት ይደረጋልና። ጥምቀቱን ለእኔ ፈልጌው አይደለም፡፡ በበደል ኃጢአት የቆሰሉትን እፈውስ ዘንድ ነው እንጂ፡፡

ሙታንን ሳስነሣቸውና ታላላቅ ታምራትን ሳደርግ ባየህ ጊዜ ለሰው ሁሉ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እንደሆንሁ ንገራቸው፡፡ አመስግነኝ ለመንግሥቴም ስገድ። በአባቴ ቀኝ ስቀመጥ ባየህ ጊዜም አምላክነቴን ተናገር፡፡

እነሆ አሁን የመጀመሪያውን ትእዛዝ እፈጽም ዘንድ አዲሱን ሥርዐትም እጀምር ዘንድና በምእመናን ልቡና ውስጥ በደሜ እጽፈው በመንፈሴም አትመው ዘንድ፣ ወደ መስቀልም እወጣና ሕማማትንም እታገሥ ዘንድ፣ በመለኮቴም የቀደመውን በደል አጠፋ ዘንድ ወደ ሲኦል ወርጄ በዚያ የሚኖሩትን እሥረኞችንም አድናቸው ዘንድ፣ በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩትም የሥጋዬን መብራት አበራላቸው ዘንድ፣ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተነሥቼ የሞትን ሥልጣኑን ሽሬ ኃይሉን አጠፋ ዘንድ እወዳለሁ፡፡

በእኔ ለሚያምኑ ሁሉ በሥላሴ ስም ልዩ የሆነች ጥምቀትን እሰጥ ዘንድ እነሆ ዛሬ ይህችን ጥምቀት እጠመቃለሁ፡፡ ስለዚህ ቃሌን ስማኝ፤ ለእኔም ታዘዝ፤ እጅህንም ዘርጋና አጥምቀኝም፡፡

እናቴ ማርያም በመፅነሷና በመውለዷ እንደ ታዘዘችኝ ቀኝህን ዘርጋና በዮርዳኖስ አጥምቀኝ፡፡ እናቴ ማርያም በጨርቅ እንደ ጠቀለለችኝ፣ አንተም ታዘዘኝ፣ አጥምቀኝም፡፡ እናቴ ማርያም በሕፃናት ልማድ ሐሊበ ድንግልናዋን እንደ አጠባችኝ፣ አንተም እጅህን በራሴ ላይ ጫን፡፡ ኪሩቤል የሚፈሩት ሱራፌልም የሚያመሰግኑት በእርሱ ያመነም የማይጠፋ እኔ ነኝና፡፡

ይቀጥላል......

(ድርሳነ ሠለስቱ ሊቃውንት በመምህር ቃለጽድቅ ሕግነህ የተተረጎመ ገጽ 55-67)

@kinexebebe
@kinexebebe
@kinexebebe
+++ የዘመኑ ፈተና... +++

የራስ ጸጉሩን በመጠኑ ለመስተካከል አንድ ሰው ወደ ጸጉር ቤት ያመራል፡፡ የጸጉር ውበት ባለሙያውም ያለመጠን ብቅ ብቅ ያሉ የጸጉር ዘለላዎቹን ከማረም ጋር ጥቂት ጨዋታ ቢጤ ይጀምራሉ፡፡

  ጸጉር ቆራጭ- ወንድሜ በእግዚአብሔር መኖር ታምናለህን ?

  ተቆራጭ- እንዴታ?! ምን ጥርጥር አለው፡፡

  ጸጉር ቆራጭ- እኔ ግን በእግዚአብሔር መኖር አላምንም፡፡ ያንተም እምነት ልክ እንደሆነ አላስብም፡፡ እስኪ አስተውል! ዓለምን እና በውስጧ የሚኖሩትን የፈጠረ በጎ ፣የፍጥረቱንም መጎዳት የማይሻ መልካም አምላክ ቢኖር ኖሮ ዓለም እንዲህ በጥፋት ባልታመሰች፡፡ አሁን ወደ ጎዳናው ብትወጣ አሳዳጊ አጥተው በደዌ ተይዘው በየሜዳው የተበተኑ ሕፃናትን፣ ጧሪ ያጡ አረጋውያንን ትመለከታለህ፡፡ ታዲያ ይህን ሁሉ ነገር እያየህ ፈጣሪ አለ ብለህ ታምናለህ ?

በዚህ ጊዜ ጸጉሩን የሚስተካከለው ሰው በዝምታ ተዋጠ፡፡ የተነሡት ማስረጃዎች ሁሉ የማይካዱ የአደባባይ ሐቆች እንደሆኑ ሲያስብ መልስ አጥቶ ከራሱ ጋር ግብግብ ገጠመ፡፡ ፈጥኖ የእርሱን ሐሳብ መቀበልም አልፈለገም፡፡ የማይጨበጥ ምክንያት ይዞ በጉንጭ አልፋ ክርክር ሊሞግተውም አልወደደም፡፡ ብቻ የመረጠው ዝምታን ነበር፡፡ ዝም አለ!

እንዲህ ዝም እንዳለ ጸጉሩን ተስተካክሎ ጨርሶ ወጣ፡፡ የሚደንቀው ግን ወደ ወጣበት ጸጉር ቤት ድንገት ዘው ብሎ ገባ፡፡ ቀጥሎም ጸጉሩን ወዳስተካከለው ሰው እየጠቆመ ‹‹ጸጉር ቆራጭ የለም!›› አለው፡፡ ጸጉር አስተካካዩም በንግግሩ እየተገረመና በድንጋጤ እያየው ‹‹እንዴት? አንተ ራስህ የት ተቆርጠህ ነው እንዲህ የምትናገረው?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ያም ደንበኛ ጸጉር ቆራጩን እጁን ይዞ ወደ ውጭ እያስወጣው፣ በጎዳናው ላይ የተንጨባረረ እና ያልጸዳ ጸጉር ወደ ነበረው ሰው እየጠቆመ ‹‹ጸጉር ቆራጭማ የለም፡፡ ጸጉር ቆራጭ ቢኖር ኖሮ ይህ ምስኪን በተቆረጠ ነበር›› አለው፡፡ ጸጉር አስተካካዩም እርማት ለመስጠት እየቸኮለ ‹‹ቆይ ቆይ ወንድሜ አትሳሳት፡፡ ጸጉር አስተካካይማ እኔ አለሁ፡፡ ይህ ሰው ጸጉሩ የተንጨባረረው እኔ ባለመኖሬ ሳይሆን እርሱ ወደ እኔ ስላልመጣ ነው›› እያለ መኖሩን ሊያሳምነው ሞከረ፡፡

ያም ጸጉር ተስተካካይ እንዲህ አለው ‹‹አዎ፤ የዚህ ሰው ጸጉር ያለ ልክ አድጎ የተንጨባረረውና አዳፋ የሆነው አንተ ባለሙያው ስለሌለህ ሳይሆን እርሱ ወደ አንተ ስላልመጣ ነው፡፡ ልክ እንደዚህ ደግሞ ዓለም ችግር ውስጥ የምትወድቀውና ክፉ ነገር የሚያጋጥማት ፍጹም በጎ የሆነ አምላክ ሰለሌለ ወይም የሚጠብቃት ቸር እረኛ ስላጣች ሳይሆን ዓለም ወደ ፈጣሪዋ ስላልመጣች፣ በንስሓም ወደ እርሱ ስላልቀረበች ነው።››

@kinexebebe
@kinexebebe
@kinexebebe

‹እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል›
2ኛ ዜና 15፡2

ወደ አምላካችን እንቅረብ!!!
መቅደም  ነበረበት (ርዕስ)      
               ዘሩእጅግ ያማረ ያለዉ  ጥሩ  ቦታ                አበቃቅሉ መልካም  ደስ የሚል ለእይታ  
ዘሪው አዘጋጅቶ ማዳበርያኮምፖስት       
ከብቶች እንዳይገቡ  በአጥረ ከልሉት      
ጥዋት እና ማታ ዘወትር ሲመለከት      
ረስቶ ዋናውን ትልቁን ቁም ነገር         
ኮትኩቶ ማሳደግ  በጥበብ  በፍቅር        
   አረሞችም ወጡ ከበቡት  ዙሪያውን          ሊያደርጉት ፈሬ አልባ ሊያስቀሩት ብቻውን
ገዝግዘው ገዝግዘው ሊቀሙት ርስቱን
      መቅድም ነበረበት ብለህ ከመፀፀት
     መስራት ያለብህን  ቀድመህ አስብበት
  ካላወክም ጠይቅ ካንተ በፌትላሉት ታላላቅ ሠዋችን
ዘር መቸ ተዘርቶ መቸ እደሚያፈራ
ይነግርሁሀል እና ሰርአት አና ስልቱን ሁሉን በየተራ
  ማግኘት ትችላለህ የፈለከውን  ምርት  ከትልቅ ተራራ
    እስኪ አንድ ጥበብ ሠዋች ላስታውሳችሁ
አናጺው ሲሰራ በጥልቅ ካያችሁ
   መሠረቱን ጥሎ ሲጀምር ከቦታው
እስከ ጉልላቱ እንደት እዳሠበው
   አናጺው ጥበበኛ ሊህቅ ነው ለቤቱ
  አስቀድሞ ያውቃል ከመስራቱ በፌትስለ ቤትነቱ
      አናጺው ሲሰራቤቱን ሲጥል መሠረቱን
ቀድሞ አስቦ ነበር ሦስት ነገሮችን
ነፉስ እንደ ሜነፋስ ቀድሞ ስላወቀ
ማገር ግድግዳውን በደንብ አጠበቀ
ነፋስ ከነፈሰ ዝናብ እደሜዘንብ ሲያስብ ይህን ጥምረት
ፀሀይእና ዝናብ የሚከላከልን ድፍን ዳስ
ሠራለት
ዝናብ ከዘነበ ጎርፍ አይቀርም እና
ዉሃ ልክ አስያዘው በዘው እንዲፀና
መቅደም ያለበትን እየተውክ ሄደህ
ለመምሰል ብትሞክር እራስክን አታለህ
አትችልም እና ቀጥ ብልህ መቆም እደጓደኞችህ።

H/Giorgis from wcu.

@kinexebebe
@kinexbebe
ከ20 k በላይ member ያላቸውን መንፈሳዊ ቻናሎች መግዛት የሚፈልግ ካለ
👉 @Yene_mareyam አናግሩን።
Forwarded from ዘ-ተዋሕዶ ቦት
[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱
2025/01/21 01:50:09
Back to Top
HTML Embed Code: