Telegram Web
🤔🤔🤔🤔
ወ/ሮ እመቤት ብዙ ጊዜ በመስኮት ወደ ውጪ የማየት ልምድ ያላት ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ  የምታየው ነገር ጥያቄ ይሆንባታል። ነገሩ እንዲህ ነው በመስኮት ሆና ወደ ውጪ ስታይ ጎረቤቶቿ  አጥበው የሰቀሉት ልብሶች በሙሉ የቆሸሹ ናቸው ። በዚህም ጎረቤቶቿ "አጥበው የሰቀሉት ልብስ እኮ የቆሸሸ ነው፤ ለምን በደምብ አያጥቡም?" ብላ ባለቤቷ የሆነውን ሰለሞንን ትጠይቀዋለች።
ሰለሞንም ነገሩን ያይና ዝም ይላታል።
እመቤት ተደጋጋሚ በምታየው ነገር ደጋግማ ሰለሞንን በጥያቄ ማሰልቸት ጀመረች።
አንድ ቀን ግን እመቤት እንደ ልማዷ በመስኮት ስታይ ንፁህ የሆነ የታጠበ ልብስ ታያለች በዚህም እጅግ ደስ ብሏት ዛሬ ጥሩ አድርገዋል ልብሳቸውን በደምብ አጥበው ነው ያሰጡት ብላ ለሰለሞን ስትነግረው ጊዜ ሰለሞንም "አይ በፊትም እኮ ያንቺው ስህተት ነው፤እኔ በጠዋት ተነስቼ የመስኮቱን መስታወት  ስለ ወለወልኩት ነው ዛሬ ጥርት ብሎ የታየሽ "ብሎ ነገራት።

@kinexebebe
ያረገው ከሰማይ የወረደው ከድንግል ማርያም የተወለደው የፍጥረት   
       አስገኚ የዓለም ሠራኢ መጋቢ እግዚአብሔር ነው ።
◉❖═───◉●◉♰♰♰◉●◉────❖◉༻

#በዓለ_ዕርገትን ስናከብር አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በዚህ ዓለም ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ኖሮ ከማኅበረ መላእክት ተለይቶ ይኖር ለነበረ ለአዳም ጽንዐ ነፍስ ልጅነት ስጥቶ ከማኅበረ መላእክት ጋር አንድ አድርጎ ዐረገ ስንል ነው ።

ስለዚህ ያረገው #ቅዱስ_ቅዱስ_ቅዱስ ተብለው ከሚመስገኑ ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ መውደቃችንን በግብረ ዲያብሎስ መያዛችንን በእግረ አጋንንት መጠቅጠቃችንን አይቶ ልዑል ባሕርዩን ዝቅ አድርጎ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው ስለሰው ልጅ ፍቅር ሲል መከራ የተቀበለው በሞቱ ሞታችንን በቁስሉ ቁስላችንን ያደረቀ የሰውን ልጅ ከዲያብሎስ አገዛዝ ያላቀቀ የባርነት መዝገባችንን የፋቀ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።

#ነቢዩ_ዳዊት ያረገው የፍጥረታት አስገኚ እግዚአብሔር እንደኾነ ሲዘምር (እግዚአብሔር በዕልልታና በመለኸት ድምፅ ወደ ሰማይ ዐረገ ) ዐረሲል ያረገው ከሰማይ የወረደው ከድንግል ማርያም የተወ ለደው የፍጥረታት አስገኚ የዓለም ሠራኢ መጋቢ እግዚአብሔር እንደኾነ ነግሮናል (መዝ46፥5)

ጌታችን ወደ ሰማይ ሲያርግ የነበረውን ድባብ ምን ይመስላል ቢሉ ፦ ቢታንያ ሲደርስ መሄዱን ትቶ ቆመ ደቀ መዛሙርቱም ከበውት ቆሙ ጌታም በፍቅር ዐይን አያቸው እጆቹንም አንሥቶ ሲባርካቸው ከማንኛውም ምድራዊ ስበት በበለጠ ኀይል ከመካከላቸው ተነሥቶ ወደ ሰማይ ዐረገ « ወደ አባቴ ወደ አባታችሁ ዐርጋለሁ » ይህን እየተናገረ ሳለ ደመና ነጠቀው ከዐይኖቻቸውም ሠወረው ።

ዳግመኛ መብረቅ የለበሱ ሁለት ሰዎች ታይዋቸው እናንት የገሊላ ሰዎች ቆማችሁ ሰማይ ሰማይን ለምን ትመለከታላችሁ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያርግ እንዳያችሁ ዳግመኛም በክብር ወደ እናንተ ይመጣል ። « ሞቱን እየተናገርን ትንሣኤውንና ወደ ሰማያት ማረጉን አምነን ዳግመኛ በክብር መምጣቱን ተስፋ እናደርጋለን ። » እንዲል ( ድጓ ዘጰራቅለጦስ )

ደቀ መዛሙርቱም ጌታቸውን ከዐይናቸው እስኪሰወርና አይኖቻቸው እስኪፈዙ ድረስ በአድናቆትና በፍቅር ወደ ላይ ተመለከቱ ወዲያውኑ የክብር ደመና ከዐይናቸው ሰወረው ።

የጌታ ዕርገት #የርቀት_ያይደለ_የርሕቀት_ነው ይህ ማለት መርቀቅ ሳይሆን መራቅ ነው ለምሳሌ አውሮፕላን ከምድር ሲነሣ ቀስ እያለ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ አካሉ እያነሰ እያነሰ ይሄዳል በመጨረሻም ወፍ እስኪመስለን ድረስ ለዐይናችን ይርቃል አምላካችንም ልክ እንደዚያ የሐዋርያት ዐይን ማየት እስከቻለበት መጠን ድረስ ከፍ ከፍ እያለ ወደ ሰማይ ዐርጓል ።

መላእክትም የደመና ሰረገላም መስለው በተቀበሉት ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ጥዑም የሆነውን የመላእክትን ዝማሬ ሰምተዋል መላእክትም ትኩር ብለው የጌታን ዕርገት ለሚመለከቱ ሐዋርያት « እናንተ የገሊላ ሰዎች ወደ ሰማይ ሲወጣ ያያችሁት ተመልሶ ይመጣል » የሚል ተስፋ አበሠሩአቸው።

ደቀ መዛሙርቱም « እነሆ እኔ እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ » ሲል የሰጣቸውን ተስፋ እያስታወሱ ከቢታንያ ተመለሱ።
@kinexebebe
#ኧረ_አልሆንልኝም_አለ

/ድንቅ የንስሐ መነባንብ/

ኧር አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ፤
የጭንቅ አማላጅቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?

ጸሎት ምህላ አቃተኝ መንፈሴ ለንሰሐ ሸፈተ፤
መንጸፈ ደይን ወደቅኩኝ ነፍሴ በኃጢአት ሸፈተ።
እምቢ አለኝ ፆም ጸሎት እምቢኝ አለኝ ንስሐ፤
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኘ ከዓለም ውሃ።

ኧር አንድ በይኝ እመቤቴ ወለላይቱ ተማለጂኝ፤
ጨርሶ ዓለም ሳይነጥቀኝ ከወደኩበት አንሺኝ።

ነጭ ነጠላ አጣፍቼ ከቤተ መቅደስ ስወጣ፤
መጽሐፍ ቅዱስ ዘርግቼ ለስብከት መድረክ ስወጣ፤
ልብሰ ተክህኖ ለብሼ ንፍቅ ገባሬ ሰናይ ስሆን፤
ጥቅስ በቃሌ ስደረድር ለዜማ ቅኔ ስቀኝ፤
አካሌ እዚህ ሆኖ መንፈሴ እየሸፈተ፤
ነፍሴን በኃጢአት ገንዞ ስጋዬ ነፍሴን ጎተተ።

ኧር አንድ በይኝ እመብርሃን ወለላይቱ ተማለጂኝ፤
ጨርሶ ዓለም ሳይነጥቀኝ ከወደኩበት አንሺኝ።

ማለዳ ኪዳን አድርሼ ቅዳሴ ጸሎት ጨርሼ፤
ከቤተክርስቲያን ወጥቼ ወደ ስጋ ገቢያ ተመልሼ፤
በኃጢአት ባህር ስዋኝ የግፍ ዳንኪራ ስረግጥ እውላለሁ፤
የልጅነት ፀጋዬን አውጥቼ ብኩርናዬን እሸጣለሁ።
እዚህ መልአክ መስዬ ላዬ በቅድስና በርቶ፤
ውጪ ከክፋት ከፍቼ ኃጢአት በጽድቄ ተተክቶ፤

በሀሜት የሰው ስጋ ስበላ በወንድሜ ሸር ስሸርብ፤
ስዋሽ ስቀጥፍ ውዬ ስሰርቅ ሳሽሟጥጥ ስሳደብ፤
ነጠላ ስለብስ ግን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ስገባ፤
ሰዓሊለነ ቅድስት ስል ያለ ንስሐ እንባ፤
የመውደቂያዬ ጉድጓድ ጥልቀቱ ወሰን ዳርቻ የለውም፤
እዝነ ህሊናዬ ለዓለም እንጂ ለጽድቅ ቦታ የለውም፤

መሃረነ ክርስቶስ እንዳልል ተዘከረነ ፈጣሪዬ፤
ኃጢአት በደሌ አፈነኝ በሀፍረት ነደደ ህሊናዬ፤
ምን ብዬ ልጥራው ጌታዬን ተዘከረነ ብዬ።
ስለእኔ መገረፉን የመስቀሉን ፍቅር አቃልዬ፤
እንዴት ማረኝ ልበለው ስለ ስጋ ጣዕም ተቃጥዬ።

ምን ብዬ ልጥራው ጌታዬን?

ዓይኔን ወደ ፀፍፀፈ ሰማይ ወደ ሥላሴ መንበር፤
አንስቼ ማየት አቃተኝ ማረኝ ብዬ ለመናገር።
ለሰው ጻድቅ መስዬ የኃጢአት ጎተራ ሆኛለሁ፤
እንዴት አባቴ ቀና ብዬ መንበረ ጸባኦትን አያለሁ።
እባክሽን እናቴ ወለላይቱ ተማለጂኝ፤
እንደቃና ዘገሊላ ባዶ ማድጋዬን ሙዪልኝ።
ከፊቱ እንዳላፍር ከአማኑኤል ጋር አስታርቂኝ፤
ለተጠማ ውሻ እንዳዘንሽ ለመጻተኛው እዘኚልኝ።

አንቺ የትሁታን ትሁት ርህሪይተ ልብ እናቴ፤
ከልጅሽ ከኢየሱስ አማልጂኝ እዘኚ ለእኔም እመቤቴ።
አንቺ ውዳሴሽ የነፍስ ስንቅ ስምሽ ከማር የጣፈጠ፤
በላኤሰብዕ በእፍኝ ውሃ በምልጃሽ ከሞት ያመለጠ።

አንቺ መላእክት የሚጎበኙሽ የካህናት አለቆች ምስጋናቸው፤
በመወሰን የማይወሰን እሳተ መለኮትን የቻልሽው።
አንቺ ከገነት በተሰደደ ጊዜ ለአዳም ተስፋ የሆንሺው፤
ዛሬም ለእኔም ተስፋ ሁኚኝ ለነፍሴ ስለነፍሴ ተዋሺው።

እንጂ እኔማ አልቻልኩም የልቤ ንጽህና ጠፍቷል፤
ለጸሎት እንኳን ስቆም ልቤ ለሁለት ተከፍሏል፡፡

ኧረ አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ፡፡
የጭንቅ አማላጂቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?
እምቢ አለኝ ፆም ጸሎት እምቢኝ አለኝ ንስሐ፤
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኘ ከዓለም ውሃ።

የልቤን መወላወል የነፍሴን ድካም አበርቺ፤
በአማላጅነትሽ ስር ነኝ እና ከልጅሽ አስታርቂኝ አንቺ።
ለሰው ዓይን ባይገለጥም ሰውሬ የሰራሁት ኃጢአት፤
አምላክን አሳዝኖታል የምኖርበት ሕይወት፤
ይኸው የምናገረው አይሰምር የወረወረኩት አይመታም፤
ስጋዬ አልተቀደሰ ገበታዬ በረከት የለውም፤
ዕውቀት ምርምር አይዘልቀኝም ህሊናዬ ፍሬ አይቋጥር፤
ዝርው ሆኖብኝ ቀርቶ የነፍስ የስጋዬ ምስጢር።

ይኸው የማወራው ለሰው አይጥም ፍቅር ከእኔ ቤት ርቋል፤
መቆም መቀመጤ አያምርም ሰው በስራዬ ይማረራል፤

የኃጢአት ምንዳዬ ይኸው የኃጢአት ደሞዜ ይኸው ስቃዬ ውስጤን በልቶታል፤
ለአንድነት የተናገርኩት ዛሬም ጉባኤ ይበትናል።

እና አዛኝቱ ታረቂኝ ከልጅሽ ከአማኑኤል አማልጂኝ፤
ከሰው የሸሸግኩት ኃጢአት ጨርሶ በልቶ ሳይውጠኝ።
የበላኤሰብዕ እመቤት እባክሽን ተማለጂኝ፤
አንቺ ሕይወቴን ዳብሺው ነፍሴ ዕረፍት እንድታገኝ።

ኧረ አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ፤
የጭንቅ አማላጅቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?

መልካም ቀን
@kinexebebe
ጠፍቼ_እንዳልቀር_መንፈሳዊ_ግጥም📍በኪነ_ጥበብ.pdf
10.2 MB
👉 ጠፍቼ እንዳልቀር_መንፈሳዊ ግጥም📍በኪነ-ጥበብ.pdf
.
➥በፍቅሩ በቀለ
@kinexebebe
#ሰበር_ዜና_ከጠቅላይ_ፍርድ_ቤት

አቶ #ሥጋ የተባሉ የከተማችን ነዋሪ በወ/ሮ #ነፍስ በፈፀመው ወንጀል #ሰኔ_01ቀን 2017 ዓ/ም  ለተከታታይ 34 ቀናት በፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን  ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰሞኑን በሰጠዉ መግለጫ አስታውቋል።

እኚህ አቶ #ሥጋ ከአባታቸው ከአቶ እንብላ ሁሉንም እና ከእናታቸው  ከወ/ሮ እንጠጣ አማርጠን  #ሰዉ በተባለ ሀገራችን በምትገኘው #ሆድ በምትባል ከተማ የተወለዱ ሲሆን በከተማዋ መኖር ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ  ከወ/ሮ ነፍስ ጋር ስምምነት እንዳልነበራቸው  ሪፖርታቸው #ራስን_መግዛት ገልጿል።

በዘገባዉ እንደተገለጠዉ ወ/ሮ ነፍስ  በአቶ ሥጋ ላይ ያቀረቡትም #ክስ  እንደሚከተለው ነበር።

"እኔ ወ/ሮ ነፍስ ዘለዓለማዊ  የተባልኩኝ የከተማው  ነዋሪ እንዲሁም የድርጅታችን ቋሚ ሠራተኛ ስሆን  #በአቶ_ሥጋ_እንብላ የተባሉ የድርጅታችን ኮንትራት ሠራተኛ እየደረሰብኝ ያለው  የመብት  #መጋፋትና #ጭቆና ስለበረታብኝ መጎዳቴን ተመልክታቹሁ  ትክክለኛ እና ቅን የሆነ መፍትሄ እንድትሰጡኝ ስል በትሕትና እጠይቃለሁ። ምክንያቱም በድርጅታችን ያለውን የሥራ ኀላፊነት በአግባቡ  እንዳልወጣ  ብዙ ተፅዕኖዎችና ፈተናዎች እየደረሰብኝ እገኛለሁ።
#ለምሳሌ #እንዳልፆም #እንዳልፀልይ #እንዳላስቀድስ #እንዳላገለግል እንዱሁም በገላ፡ 5፥22 በተሰጠኝ የአሠራር ሒደት  መሠረት  እንዳልሠራ ጣልቃ እየገባ የተሰጠኝ የሥራ ኀላፊነት በአግባቡ ተወጥቼ #የአክሊሉ ተሸላሚ እንዳልሆን
በምቀኝነት ስኬት እንዳላከኝ እያደረገኝ ነው።"  ሲሉ ገልፀዋል።

የአቶ_ሥጋ_እንብላ ጠበቃ  የሆነው #አቶ_ሥርአት_አልባ_ተሃድሶ  በበኩላቸው ያቀረቡት መከራከርያ "እንበለ ሥጋ ኢትቀውም ነፍስ" (ያለ ሥጋ ነፍስ መኖር አትችልም) የሚል የጥቅስ ነጠቅ  ጥያቄ ቢሆንም "ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን" በሚል አንቀጽ መብታቸው ተከብሮላቸው እያለ ነገር ግን የወ/ሮ #ነፍስን መብት የማክበር ግዴታቸውን እንዳልተወጡ የየከሳሽ ጠበቃ #ቀኖና ተከራክረዋል።

#ክቡር_ዳኛ_የሆኑት_ዳኛ_በጎ_ኅሊናም የግራ ቀኝ ክርክርን በሚገባ ካደመጡ በኋላ #አቶ_ሥጋ_በ34_ቀን_ፅኑ_እስራት_እንዲቀጣ_ብይን_ሰጥተዋል

ውሳኔዉን ተከትሎ ኬዙን ይዘዉት የነበሩት ኢንስፔክተር #ንሥሓ  እና ሻለቃ #ስግደት(ዶ/ር)   #በአቶ_ሥጋ ላይ የተሰጠዉን የ34_ቀን_ፅኑ_እስራት_ቅጣት_ብይን በተመለከተ ሓሳባቸዉን የሰጡ ሲሆን የነበረዉን ሁኔታ እንዲህ አብራርተዋል፡

በተከሳሽ #አቶ_ሥጋ_እንብላ እና በወ/ሮ #ነፍስ_ዘለዓለም መካከል የተፈጠረዉን  አለመግባባት በእርቅ ለመፍታትና በሽማግሌ እልባት እንዲያገኝ ለማድረግ የተሞከረ እንደነበር የገለጹ ሲሆን ነገር ግን በቀረበዉ የእርቅና የሽማግሌ ምክር ፕሮግራም ላይ ምንም እንኳን
ወ/ሮ #ነፍስ ፍቃደኛ ሆነዉ ጉዳዩን በይቅርታ ለማለፍ ቢስማሙም #አቶ_ሥጋ_እንብላ ግን አሻፈረኝ በማለት ለሽማግሌዎቹና ለይቅርታ ያላቸዉን ንቀት አሳይተዋል። ስለዚህ ጉዳዩ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቀርቦ ለሃምሳ ቀናት ክርክር ከተደረገ በኋላም እንደሰማችሁት  #አቶ_ሥጋ_በ34_ቀን_ፅኑ_እስራት_እንዲቀጡ_ብይን_ተሰጥቷል ሲሉ ገልጠዋል። አያይዘዉም የተወሰነዉ  ውሳኔ ትክክለኛና ሕግን ያማከለ እውነተኛና ቅን ውሳኔ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ዜናዉን_ከቲክቫ_ቤተ_ክርስቲያን አግኝተነዋል።
@kinexebebe
በመንፈሳዊ ሕይወት ለመለወጥ

#1ኛ የፀሎትን ህይወት ተለማመድ ተጠቀምበትም፣
#2ኛ ከመንፈሳዊ አባቶችና ሊቃውንት መ/ራን ምክርና ትምህርት አትራቅ
#3ኛ ከቅዱሳት መፃህፍት ጋር ያለህን ግንኙነት አዘውትር፣
#4ኛ የምትውልባቸውን ቦታዎች ፥የምታነባቸውን መፃህፍት፥ የምትመርጣቸውን ባልጀሮችህን ምረጥ፤ለመንፈሳዊ ህይወትህና ለሌሎች ወንድሞችህና እህቶችህ የሚያሰናክሉ እንዳይሆኑ ተጠንቀቅ፣
#5ኛ የእግዚአብሄር ቤተመቅደስ መሆንህን ዘወትር አትዘንጋ፣
#6ኛ ሃፍረትንና ፍርሃትን አስወግድ፥በራስህ ማስተዋልም አትደገፍ፣
#7ኛ አላዋቂነትህን ተቀበል 'እኔ ብቻ'፦ አትበል ውዳሴ ከንቱንም አትፈልግ፣
#8ኛ ለሰራሃው ሃጢአት ሳትዘገይ ንስሃ ግባ፣
#9ኛ ልበ ደንዳናነትንና አመፀኛነትን ከአንተ አርቃቸው፣
#10ኛ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ለመኖርና የቃሉ ሙላት በውስጥህ ኖሮ ከክርስቶስ ጋር መኖርን ተለማመድ በቃሉም ፀንተህ ተገኝ፣
#11ኛ የቅዱሳንን ተጋድሎና ፍቅር በመመልከት እነርሱን ለመምሰል ትጋ፣
#12ኛ ከዚህ በፊት የነበርክበትን የሃጢአት ህይወት ኮንነው
#13ኛ ሰዎችን/ባልንጀራህን አፍቅር ከጥላቻም ራቅ፣
#14ኛ ነገርን ሁሉ ለበጎነው ብለህ ተቀበል። ጌታ ሆይ ይህን እንድናደርግ እርዳን አሜን ይቆየን።
@kinexebebe
🚹ስማኝ ልጄ

1.ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!!
2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!!

3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!!

4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!!

5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!!

6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!!

7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!!

8. ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!!

9. ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!!

10. ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ስትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!!

11. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ግዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!!

12. እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነትተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!!

13. አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!!

14. ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!!

15. ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!!!

16. አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!!!!

ማስተዋሉንያድለን አሜን።

@kinexebebe
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
👉ሲያስተምር እንባ ከአይኖቹ ይቀድሙታል ተስፋ የቆረጠውን ወጣት ተስፋ ይሰጠዋል በእግዚአብሔር ቃል ተስፋውን ያለመልማል የመምህር እዮብ ይመኑ ቻናል ይቀላቀሉ 👇👇👇

የመምህር እዮብ ይመኑ ትምህርት
የመምህር እዮብ ይመኑ ትምህርት
የመምህር እዮብ ይመኑ ትምህርት
Forwarded from ኦርቶዶክሳዊ ቻናል
የ1000 ብር ካርድ ሊለቀቅ ነው 9 ደቂቃ ብቻ ነው የቀራው። ቶሎ ከስር JOIN ሚለውን ነክታቹ JOIN REQUEST ላኩ 🏃‍♀️🏃‍♂️

20 ሰዎች ብቻ ፍጠኑኑኑኑኑ🏃‍♀‍➡️🏃‍♀‍➡️🏃‍♀‍➡️
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛


🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
👉በሚሊኒየም አዳራሽ ማዕዶት ለኢትዮጵያ መምህራችን ዲያቆን ሔኖክ ሀይሌ አስተምሮ ሲጨርስ እንዲህ ብሎ ቃል አስገባን።
"ነጠላ ለብሳችሁ የመጣችሁበት ይህን አዳራሽ ነገ ልብስ ቀይራችሁ [ለዘፈን፥ ለጭፈራ] እንዳትመጡበት።"
ምዕመኑም በጭብጨባ ቃል ገብቷል።
 
ኦሮሞኛ መዝሙሮችን ማጥናት ለምትፈልጉ ምርጥ ቻናል ልጠቁማችሁ linkun በመንካት ተቀላቀሉ።
https://www.tgoop.com/tawahiidoo
#ለደጉ እና ለሩሩህ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ በዓል እንኳን አደረሳቹ።

"ቅዱስ ሚካኤል ኾይ"

እንደ ፀሐይ ሥነ ጸዳል የሚያንጸባርቁ በሰማይ ላይ ለሚንበለበሉ አክናፎችኽ ሰላም እላለኹ

የእግዚአብሔር ልዩ መልእክተኛ ሚካኤል ኾይ ከላይ ከሰማይ ተመልክተኽ በምትመጣበት ጊዜ ኹሉ በሲዖል የሚኖሩ ግዞተኞች ሚካኤል ኾይ መጣኽልን ደረስክልን እያሉ ደስታቸውን ይገልጻሉ።"

#መልክአ ቅዱስ ሚካኤል

" የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።"

#መዝሙረ ዳዊት 34:7፤)

"በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል። "

#ትንቢተ ዳንኤል 12:1

" የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት። "

   #ትንቢተ ዳንኤል 10:13

" ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።
"
#ትንቢተ ዳንኤል 10:21፤)ዐ

"የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር። ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።"

#የይሁዳ መልእክት 1:9፤

"ቅዱስ ሚካኤል ኾይ
እንደ ፀሐይ ሥነ ጸዳል የሚያንጸባርቁ በሰማይ ላይ ለሚንበለበሉ አክናፎችኽ ሰላም እላለኹ

የእግዚአብሔር ልዩ መልእክተኛ ሚካኤል ኾይ ከላይ ከሰማይ ተመልክተኽ በምትመጣበት ጊዜ ኹሉ በሲዖል የሚኖሩ ግዞተኞች ሚካኤል ኾይ መጣኽልን ደረስክልን እያሉ ደስታቸውን ይገልጻሉ።"

    #መልክአ ቅዱስ ሚካኤል.

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
@kinexebebe
#ሰኔ_21_እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ለሕንጸተ ቤተ ክርስቲያን ዘእግዝእትነ ማርያም እና ሰኔ ጐልጐታ እንኳን አደረሰን! የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነቷ ረድኤቷ በረከቷ ጥበቃዋ አይለየን እመ ብዙኃን የብዙኃን እናት ድንግል ማርያም ሆይ ሳይነግሩሽ የሰውን ችግር ጭንቀት የምታውቂ እሩህሩህ እናት ነሽና የጎደለንን ሙይልን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው አማላጅነትሽ ፍፁም ረድኤትሽ አይለየን፤ የቃል ኪዳን ሀገርሽን ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያን በምልጃሽ አስቢያት! አሜን፡፡

''በዕንቊ ሰንፔር ትትሐነጽ ወበመረግድ
ሃሌ ሉያ ለአብ ሐጹር የዓውዳ ትበርህ እምከዋክብት
ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ
ጽዮን ቅድስት ቤተ ክርስትያን ደብተራ ፍጽምት''
ዚቅ ዘቅዱስ ያሬድ

እንኳን ለእናታችን ለቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችው
ባህር ሙሉ ቀለም...
ሰማይ ያህል ብራና ተዘርግቶላቸው
ክብርሽን ለመፃፍ
ከምስጋናሽ ባህር እፍኝ  ለመጨለፍ
አንችልም ካሉ፤ አበው  በትህትና
ስላንቺ የምፅፍ  እኔ ማነኝና

ኦ ማርያም ምልአተ ውዳሴ
በመኑ
ወበ አምሳለ መኑ ናስተማስለኪ
                  ካሉሽ በቅድስና
ስለ አንቺ ምራቀቅ እኔ ማነኝና

ገብርኤል መልአክ ፤
ምስራች ሊያበስርሽ ከተርበተበተ 
ከክብሩ በልጦበት ያንቺ ልዕልና
ስለንቺ የምገጠም እኔ ማነኝና

ያልተወለደው ባለ ቅኔ
ነባቤ መለኮት በማህፀን ሳለ
ቅኔ ከዘረፈ ለ15 አመቷ ገሊላዊት ብላቴና
ስለእሷ የምቀኝ እኔ ማነኝና

እኔ ማነኝና....
@kinexebebe


From @MekuanenetM
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
❤️በማርያም ይሄን ቻናል ሳታዩት እንዳታልፋ
በቻናሉ ቀን በቀን አዳዲስ መንፈሳዊ ጥያቄዎች ይለቀቃል በማግስቱም
የቻናሉ አባላት ድምፅ ከሰጡ በኋላ
መልሱ ይለቀቃል።
በጣም አስተማሪ የሆነ መንፈሳዊ ቻናል ቻናሉን ለመቀላቀል
ከስር ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ።

         👇👇👇
@metehafe_kedusawi_teyake
@metehafe_kedusawi_teyake
@metehafe_kedusawi_teyake
2025/07/07 08:19:06
Back to Top
HTML Embed Code: