Telegram Web
Forwarded from ሲልዐቱላህ(سلعة الله) (miqbas(፪), miqbasudin(፪))
ሰሞኑን ሳይንቲስቶች በ2050 ዘላለም ለመኖር የሚያስችለንን ጥናት እያደረግን ነው ብለዋል።

ይህ ጉዳይ አደም ገና በጀነት እያለ ሞክሮት የተባረረበት ነው።

አላህ አደምን እንደፈጠረው ሟች መሆኑን ነግሮት ነበረ። ከዚያም ለመፈተኛ አንዲት ዛፍ ተከለና ከዚች እንዳትበላ አለው።

አደምና ሀረዋ የጀነት ኑሮ ስለጣማቸው ዘላለም መኖርን ፈለጉ። ሸይጧንም ይህቺን አጋጣሚ በመጠቀም ወደ እነሱ መጥቶ፦

«ጌታችሁም መልአኮች እንዳትሆኑ ወይም ከዘላለም ነዋሪዎች እንዳትሆኑ እንጂ ከዚች ዛፍ እንዳትበሉ አልከለከላችሁም አላቸው።»
(አዕራፍ 20)

እነሱም ዘላለም መኖርን በጣም ተመኝተው ነበርና ከዛፊቱ በሉ። ነገርግን የሸይጧን ቃል ውሸት ሆነና መሸፈኛቸው ከላያቸው ላይ ተገፍፎ ራቁታቸው ቀሩ። አላህም በሰሩት ጥፋት ምክንያት ወደ ምድር ጣላቸው።

አሁን ከብዙ ዘመናት በኋላ ሳይንቲስቶች እንደገና ዘላለም ለመኖር እየሰራን ነው ይላሉ። በእርግጥ ዘላለም መኖርን መመኘት ተፈጥሯዊ ነው። ነገርግን የአላህ ቀደር ቀድሞ ተፅፏልና የሚቻል አይደለም።

አላህ እንዲህ ብሏልና፦

«ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት። ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሳዔ ቀን ብቻ ነው። ከእሳትም የተራቀና ገነትን የተገባ ሰው በእርግጥ ምኞቱን አገኘ። ቅርቢቱም ህይወት የመታለያ መሳሪያ እንጅ ሌላ አይደለችም።»
(አል-ኢምራን 185)
==========
ربنا لا تأخذنا بما فعل السفهاء منا...
=========

www.tgoop.com/silatullah_4u
ስለ ወሎ — ከሚሴ አንድ ልበል
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
(የከሚሴ ህዝብ በእምነቱና በወሎዬነቱ የማይደራደር፤ በፍቅር፣ በመከባበርና በመቻቻል በአብሮነት እሴት እንዲሁም ለሃገሩ ባለው ፍቅር የማይታማ፣ እንግዳ አክባሪና ጀግና ህዝብ ነው።)
||
ብዙዎች የወሎዋ ፈርጥ—የወሎዬወች መድመቂያ ይሏታል!

ከሚሴ ከተማ በሰሜናዊው ምስራቅ ኢትዮጵያ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የታቀፈች የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር ስር የምትገኝ የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር ዋና ከተማ ስትሆን ከመዲናችን —አዲስ አበባ በ 325Km ርቀት ላይ ያረፈች፤ ከወሎዋ ደሴ ከተማ ደግማ በ 74Km ርቀት ላይ የምትገኝ እንዲሁም ከባህር ጠለል በላይ 1424m ከፍታ ላይ ያረፈች፤ "ከወንዝም ወሎ ቦርከና ይፈሳል ሞልቶ ቁንጅና" የተባለለትን የቦርከናን ወንዝ እንደ መቀነት የታጠቀች፣ በተፈጥሯዊ መልከዓ-ምድር ገፅታዋ የተስተካከለች በሰሜናዊው ምሥራቅ ኢትዮጵያ በቀድሞው የወሎ ክፍለ-ሀገር ውስጥ የምትገኝ ከተማ ናት።
*
በእርግጥ "ከሚሴ" የሚለው ስም የመጣው ከዓረብኛ ቃል እንደሆነ ይታመናል፤ "ኻሚስ" ማለትም "አምስት የሳምንቱ አምስተኛ ቀን ወይም "ሐሙስ" ማለት ሲሆን ትንሽ የመንደሩ ሰዎችና እዛውንቶች ሐሙስ ቀን ይሰባሰቡበት ከነበረው ዛፍ ስር ገበያ እንደጀመሩ ታሪካናት ያስረዳሉ። ሐሙስ ቀን ገበያው የተደረገበት የሳምንቱ ቀን ነው።
:
ይህም ማለት የከተማው ትልቅ ገበያ ሐሙስ ቀን ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በኦሮምኛም ሆነ በዓረብኛ "ሀሙስ—ኸሚስ" ስለሚባል ከዚህ በመነሳት 1935 E.C "ከሚሴ" የሚለውን ስያሜ እንዳገኘች ይነገርላታል።
*
ከሚሴ የተቆረቆረችው የኢጣሊያ መንግስት ሁለተኛውን ወረራ ከኤርትራ በመነሳት ድንገተኛ ወረራዉን ከጀመረ በኋላም ነበር። በ2ኛው የጣሊያን ወረራ ወቅት መስራቾቿ ከአዲስ አበባ በወሎ አስመራ በመዘርጋት ላይ በነበረው የጥቁር—አስፓልት መንገድ ስራ ላይ ተሳታፊ የነበሩት ሁለት ሱዳናዊ ወንድማማቾች እንደሆኑ የእድሜ ባለቤቶች ይናገራሉ፤ ይሁን እንጅ በከብት ጥበቃ ስራ ላይ ያሉ ሰዎች እና ደረሳዎች ማረፊያ ሰርተው የሚያርፉበት አከባቢ እንደነበረም ይነገራል።
:
በአሁን ሰአት ላይ ከሚሴ በልማት ጎዳና፣ በኢኮኖሚ ፍሠት፣ በኢንቨስትመንት መዳረሻነት ራሷን በማነቃቃት ላይ የምትገኝ እንደ ብርሀን ጮራ እየፈነጠቀች፣ እንደ አበባ እየፈካች ያለች ከተማ ናት!
*
የከሚሴ ህዝብ በእምነቱና በወሎዬነቱ የማይደራደር፤ በፍቅር፣ በመከባበርና በመቻቻል በአብሮነት እሴት እንዲሁም ለሃገሩ ባለው ፍቅር የማይታማ፣ እንግዳ አክባሪና ጀግና ህዝብ ነው።
:
ለዚያም ነው ከሚሴን ብዙዎች እንዲህ በማለት የሚገልፆት:- የቆንጆወቹ መፍለቂያ፣ የውቦቹ መንደር፣ የዑለሞች ሀገር፣ የጀግኖቹ መብቀያ፣ የፍቅር ማምረቻ፣ የኢትዮጵያዊን ተምሳሌት፤ በመቻቻል፣ በፍቅር፣ በመከባበር ላይ የተመሰረተች ከተማ ነች።
*
✔️ በጥቅሉ የወሎ ህዝብ ማለት ስምህን ሳያቆላምጥ ለመጥራት የሚከብደው፣ የዋህ፣ ከሰው ጋር በቀላሉ ተግባቢ፣ እንግዳ አክባሪ፤ ለሀገሩ ጥልቅ ፍቅር ያለው ህዝብ ነው።

Photo Credit: 📷Ashu Habesha
*
ነሐሴ 13, 2014 E.C
August 19, 2022 G.C
||
Anu
Forwarded from ሲልዐቱላህ(سلعة الله) (miqbas(፪), miqbasudin(፪))
المتنقبة!
هي الملكة....
في كل وقت، ومكان وزمان
መተነቁብ ሴት!

በማንኛው ጊዜ በየትኛውም ቦታና በማንኛውም ዘመን።
ንግስቲቷ እሷ ብቻ ናት!
Forwarded from ̶N̶a̶s̶_̶w̶i̶t̶h̶_̶P̶a̶l̶e̶s̶t̶i̶n̶e̶ 🇵🇸✌️ (N̴A̴s̴ ̴a̴l̴i̴ 🇵🇸🤴) via @like
Name-Miqbas
From-jima
Code 12

የኔ ልዩ ጓደኞች እኔ ከሁሉም በፊት  እንኳን ለኢደል ፊጥር በሰላም አደረሳችሁ ለማለት መጀመሪያ መሆን እፈልጋለሁ  🥰🥰

#EID_MUBAREK
እንዳሸንፍ Like አድርጉኝ 🙏🙏

Like ለማድረግ @nas_with_Palestine

photo ለመላክ @nas_ali_af
🍃አሰላሙአለይኩም🍃
🍃ወራህመቱላሂ🍃
🍃ወበረካቱህ🍃

እንዴት ናችሁ ውድ የሀገሬ ልጆች?
ቁርአን አልቀራችሁም?  ወይም ጀምራችሁ አቋርጣችኋል? ወይ ከአካቴው ቃኢዳ አልቀራችሁም?  ቁርአን አኽተመዋል!? ግን ኪታብስ ቀርተው ይሆን?  ለነዚህ ሁሉ ጥያቄ
ኢንሻአላህ በአይነቱ ከየት ያለና ሁሉን አቃፊ የሆነ የ online  ቂርአት በአያህ ኦንላይን የቂርአት ማእከል እንጀምራለን።

የምንሰጣቸው የቂርአት አገልግሎቶች፦
➾ቃኢዳ ነውራኒያ
➾ቁርአን ነዘር
➾ቁርአን ሂፍዝ
➾ተጅዊት ቂርአት አጠር ባለች ኮርስ
➾የአጫጭር ኪታቦች ደርስ
➾የተለያዩ ምክሮች


ወደ ግሩፓችን ጎራ በማለት መመዝገብና ቂርአቱን በቀጥታ ኦላይን መጀመር ይችላሉ።

ይፍጠኑ፣ ጊዜው የመሽቀዳደሚያ ጊዜ ነው።

ወርሀዊ ክፍያ፦
ዱባይ ላላችሁ 40 ዲርሃም
👉ከዱባይ ውጭ ያላችሁም በዚሁ ትከፍላላችሁ
ኢትዩ ላላችሁ ከ300-400
=========
ለመመዝገብ
  👇👇👇
@Minayatih_bot
90% ፐርሰንት ሚሆኑ ሚስሊም ሴቶች
===============
||

➾ መገላለጥ ሀራም እንደሆነ ያውቃሉ!
➾ለአጅነብይ ወንድ ምትገላለጥ ሴት ጀነት እንደማትገባም ያውቃሉ!
➾አረ ከነጭራሹም የጀነትን ሽታ እንደማያገኙም ያውቃሉ!
     ➾ግና ከዚሁ ጋር ይገላለጣሉ በምንገዶችም ላይ ይሄዳሉ። 
          
               ➾ትክክል ነው/ ወይስ አይደለም

90% ፐርሰንት ሚሆኑ ሚስሊም ሴቶች
========
||
➾ሽቶ ተቀብቶ ወደ ውጭ መውጣት ሀራም እንሆነ ያውቃሉ!
➾ከማወቃቸው ጋር ሽቶ ተቀብተው ይወጣሉ፣ የወጣት ወንዶችንም አፍንጫ በሽታው ያውዳል!


      ➾ትክክል ነው/ ወይስ አይደለም

90% ፐርሰንት ሚሆኑ ሙስሊም ሴቶች
==============
||

➾ቅንድብ ማስቀንደብ ሀራም እንደሆነ ያውቃሉ!
    ➾ይሄን ከማወቃቸው ጋር ቅንድባቸው ይቆረጣሉ(ይቀነሳሉ)!

90% ፐርሰንት ሚሆኑ ሙስሊም ሴቶች
===========
||
➾ዚና መስራት ሀራም እንደሆነና የባሎቻቸውም ሀቅ እንደሆነ ያውቃሉ!

   ➾ይሄን ከማወቃቸው ጋር ዚና ለመስራት ብለው ከቤታቸው ይወጣሉ።

እስኪ ጥያቄ ልጠይቃችሁ.....!?

  ➼የአላህ(ዓዘ ወጀል) ጀነት እዚህ ደረጃ ላይ እስኪደርሱ ድረስ የረከሰች ሁና ነው!¿
        ወይስ ከነጭራሹም ጀነት መግባትን ማይፈልጉ ሁነው ነው!¿
==========
ይድረስ ከሰፈሯ ልጆች አልፋ በየ social mediaውም ፎቶዋን በመለጣጠፍ ፊትና ለሆነቺው ለሚስኪኗ እህቴ...!

https://www.tgoop.com/tuaifetumensurah

https://www.tgoop.com/tuaifetumensurah
Forwarded from ሲልዐቱላህ(سلعة الله) (Hidayan nafaki ....)
~ሂጃብ (ኒቃብ)ሱና ነዉ ለምትሉ ....!

🔖 ሸህ ሷሊህ አልፈውዛን "አላህ ይጠብቃቸው" እንዲህ አሉ።

ሴት ልጅ ፊቷን ገልጣ የምትወጣ ቢሆን ኖሮ ሊያጫት ለሚፈልግ ሰው ሂድና ተመልከታት የሚል ፍቃድ ባላስፈለገ ነበር።
📓اتحاف الطلاب | ٣٨٥
Forwarded from ጧኢፈቱል-መንሱራህ (ابو عبد الملك ابن سعيد ان شاء الله)
📵👉 ስለዚህ ወንድሞችና እህቶች ከዚህ አስቀያሚ፣አውዳሚ፣ቆሻሻ  ከሆነ ቲክ ቶክ ከመመልከት እራሳችንን፣ቤተሰቦቻችንን፣ወንድሞቻችንን፣እህቶቻችንን እንምከር እናስተምር⁉️⁉️

በተለይ እኛ ተማሪዎች በዚህ ነገር ላይ ቢዚ ሁነለናል ።

ኢሻ አላህ አላህን ልንፈራ ይገባል
ለአላህ ብለን ልንተው ይገባል አለበለዚያ ጊዚያቺን ይባክናል፣ ከቂረዐት እንስተጓጎላለን /ወደ ሇላ እንቀራለን።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇

@tuaifetumensurah

   ╭─┅───══───┅─╮
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላህ
ቲክቶክ አካውንቴን follow  አድርጉኝ  ኢንሻአላህ  በቅርቡ አዳዲስ ነገር እለቅበታለሁ 

https://www.tiktok.com/@one.person230?_t=8kzxgTn1l7l&_r=1
Forwarded from Human and Humanity
1,እንኳን ተኝተህ ነቅተህም ትሔዳለህ

«أَلَيْسَ الصُّبْحُ بِقَرِيبٍ»
«ንጋቱ ቅርብ አይደለምን?» [ሁድ:81]

አንዲት በዕድሜዋ ጫፍ የደረሰች እንስት በሕይወቷ ያለፈችበትን በጸጸት ስሜት  በማስተወሻ ደብተሯ ላይ እንዲህ ስልት አስፍራለች፦
     «ልጅ እያለሁ 'እንደ ጓደኞቼ ትልቅ ሆኜ መች ይሆን የምገባው!' እያልኩ እጓጓ ነበር።  እንደተመኘሁትም ጊዜው ደርሶ ትምህርት ቤት ገብቼ የልጅነት ጊዜዬን አሳለፍኩ። ከዚያ ብዙ መቆየቴ ስላሰለቸኝ፣ 'መቼ ይሆን ዩኒቨርስቲ መግባት የምችለው!' ብዬ አስብ ነበር። እንደተመኘሁትም በተግባር ገባሁ።  ነገር ግን ከሱም ቢሆን በመሰላቸቴ ተመርቄ የምወጣበትን ዕለት በናፍቆት እጠብቅ ጀመርኩ።  ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ተመርቄ ወጣሁ። ወደ ቤት ስገባ ነጠላነቴ ተሰማኝ።  ስለዚህም ማግባት እንዳለብኝ ወሰንኩ። ብዙም ሳልቆይ አገባሁ። ነገር ግን ቤቱ በጭርታ የተሞላ ሆነብኝ። አላህ ልጆች በሰጠኝ ብዬ ተመኘሁ። ብዙም ሳልቆይ የልጆች እናት ለመሆን በቃሁ። ነገር ግን በቤት ውስጥ መዋል በጣም አስጠላኝ። እናም በተማርኩት ዘርፍ ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩ። ከዚያም የራሴ ቤት እንዲኖረኝ ተመኘሁ። ምኞቴም ተሳካ። ነገር ግን ልጆቼ ያደጉ በመሆኑ ሁሉም እያገቡ አንድ ባንድ እያገቡ ወጡ። ከጊዜ ቡሀላ በተቀጠርኩበት ስራ ተሰላቸሁና ጡረታ ወጣሁ። ከዚያም በቤት ውስጥ መዋል ስጀምር ከተመረኩ በኋላ እንደነበረው ህይወቴ ብቸኝነት ዳግም ያሳድደኝ ጀመር። ነገር ግን ያን ጊዜ ፊቴን ለሕይወት ያዞርኩ ወጣት ነበርኩ። አሁን ግን ዕድሜዬ ወደ አመሻሹ ላይ በመሆኑ ለሕይወት ጀርባ ሰጥቻለሁ። ያለፈው ሕይወቴን እንዴት በፍጥነት እንዳለፈ ከአንዱ የሕይወት እርከን ወደ ሌላው እየተሸጋገርኩበት ከመሆኑ በስተቀር ትርጉም ያለው ነገር አይሰማኝም። ይሁንና አሁንም ቢሆን ሙጣጭ ጊዜና ተስፋ አለኝ። እናም ቁርአንን በቃል ለማጥናት ተመኘሁ፤ ነገር ግን በዕድሜዬ ሳቢያ የማስታወስ ችሎታዬ ከድቶኝ አገኘሁት። ለአላህ መጾም ፈለግኩኝ፤ ሆኖም ግን ጤንነቴ እንደማይፈቅድልኝ ተረዳሁ። የሌሊት ሰላት መስገድ ፈለግኩ፤ ይሁንና እግሮቼ ሊሸከሙኝ አልቻሉም። ጊዜ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የገባኝ በጣም ዘግይቴ ነበር!....» (ቂሰቱን ወሒካያ/141/)

ታሪኩ የሚነግረን በጊዜ ውስጥ የምናልፈው አንድ ጊዜ ብቻ መሆኑንና ዳግም እድል የማይሰጠን መሆኑን ነው።
.
.
.
ይቀጥላል
=======
ምንጭ፦ የማር ጠብታ ከሚለው መፅሀፍ
========

join our telegram channel for more topic

https://www.tgoop.com/Humanity02H
Forwarded from Human and Humanity
1,እንኳን ተኝተህ ነቅተሕም ትሄዳለህ
.
.
ከባለፈው የቀጠለ
=======

«ዛሬ ብቅ ብላ የሄደችው ፀሀይ ነገ ብቅ ማለቷ ተመሳሳይ የሰዓት አቆጣጠር እንድንቆጥር ትፈቅድልናለች እንጂ ያንኑ ጊዜና እድል ይዛልን አትመጣም።»

ጊዜ ሁሉም ነገር የሕልውና እስትንፋሱን  የሚያኝበት ነው። ያለ ጊዜ ምንም ነገር ምንም ነው። ይሁንና ሳውቀው የምናብክነው ቁጥር አንድ ነገር ደሞ ጊዜ ነው። ከላይ የተመለከትናት ባለ ታሪካችን ስትኳትን ኖራ ነበር። ነገር ግን የሕይወቷ ድምር ውጤት ከመጸጸት አላዳናትም። ምክንያቱም ልፋቷ በሙሉ ያውጠነጥን የነበረው ተለምዷዊና ለኑሮ በሚሆኑ ነገሮች ላይ ብቻ ነበር። ሌሎቹን የህይወቷን ጉዳዮች ሳታስገባቸው ጀርባ ሰጥታቸው ኖራለች። ከረፈደ በኋላ ብትባንንም አቀበት ሆነው አገኘቻቸው። ከዚህ የበለጠ የሚያስገርመው ደግሞ እኛም የእርሷኑ ዓይነት  ታሪክ መድገማችን ነው።
ምክንያቱም ቤተሰቦቻችን፤ ትምህርቶቻችን፤ ባሕሎቻችን ስለ ጊዜ ዋጋ የሚገባውን ያህል አላሰረጹብንም።

በርካታ ምሁራን ከሁሉም በፊት ስለ ጊዜ እውነታዎች ማወቅ አስፈላጊ መሆኑን ያሳስባሉ።

አንደኛ፦ ጊዜ እንደ ወንዝ ውሃ አንድ ጊዜ ብቻ የሚረገጥ ነው።  አላህን የሰጠንን የመጀመሪያዋን ደቂቃ ሳይወስድብን በፊት ሌላ ተጨማሪ ደቂቃ አይሰጠንም፤
ሁለተኛ፦ በጊዜ ላይ ስልጣን ያለው አንድም ሰው የለም፤
ሦስተኛ፦ ሁሉም ነገር የኛ የሚሆነውና ወደ መሆን የሚመጣው በጊዜ ውስጥ አልፎ ነው፤
አራተኛ፦ ጊዜ ለሁሉም በእኩል ተሰፍሮ የተሰጠ የሃያ አራት(24) ሰአት እርዝማኔ ያለው ነው፤
አምስተኛ፦ በሕይወታችን ላይ ለውጥ የሚያመጣው እንደ አጠቃቀማችን እንጂ እጃችን በመግባቱ አይደለም፤
ስድስተኛ፦ ሁሉም ሰው በመጭው ዓለም የተሰጠውን ዕድሜ ዘመን እንዴት እንዳሳለፈው አላህ ዘንድ ተጠያቂ ነው፤
ሰባተኛ፦ ጊዜ ከምንገምተው በላይ በጣም ፈጥኖ የሚያልፍ ነው፤
ስምንተኛ፦ ሁሉንም ነገር ማሳካት አንችልም፤
ዘጠነኛ፦ በወቅቱ እንደምናልፍበት የስሜት ጠለል የማጠርና የመርዘም ስሜቱ የሚለያይ ነው፤
አሥረኛ፦ በጥንቃቄ የሚጠቀምበትን ሰው ብቻ ነው ትርፋማ ሊያደርግ የሚችለው በማለት የጊዜ እውነታዎችን ሙሁራኖች አድረድተዋል።

ጊዜን የሚያባክኑ አሥራ አምስት(15) ነገሮችንም በጥናታቸው ዘርዝረዋል፤
.
.
.
.
ይቀጥላል
=======
ምንጭ፦ የማር ጠብታ ከሚለው መጸሀፍ
=======

Join our telegram channel for more topic፦
https://www.tgoop.com/Humanity02H
Forwarded from ሲልዐቱላህ(سلعة الله) (miqbas(፪), miqbasudin(፪))
ምሰሶ አልባው መስጂድ በሃገረ ስዑዲ
===========================
በሳዑዲ ዓረቢያው ተቡክ ዩኒቨርስቲ ስለተገነባው ምሰሶ አልባ ዘመናዊ መስጂድ በጥቂቱ፦

√ የመስጂዱ አጠቃላይ ስፋት 8,000 ካሬ ሜትር ሲሆን፤ 3,500 ሰጋጆችንም ያስተናግዳል።
*
√ እያንዳንዳቸው 50 ሜትር ቁመት ያላቸው ሁለት ሚናሮች አሉት። ጣራው በ 5,887 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ በሞዛይክ ያጌጠ የጉልላት ቅርጽ አለው።
*
√ የመስጂዱ የፊት ለፊት ገፅታዎች በከፍተኛ ደረጃ የብርሃን ማስተላለፊያ ድርብ መስታወት ያላቸው ሲሆን ግድግዳዎቹ እና ወለሎቹ በግራናይት እና በእብነ በረድ ተሸፍነዋል።
*
√ የመስጂዱ የውጪ አደባባዮች እና የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች አጠቃላይ ስፋት 30,300 ካሬ ሜትር ሲሆን የመኪና ማቆሚያዎቹ 380 ተሽከርካሪዎችን የመያዝ አቅም አላቸው።
*
√ መስጂዱ በተፈጥሮው የብርሃን ስርዓት በጉልላቱ እና በመስታወት ግድግዳዎች፣ በማዕከላዊ አየር ማቀዝቀዣ፣ ​​በቢኤምኤስ አስተዳደር እና ቁጥጥር ስርዓት፣ በእሳት አደጋ ጊዜ የማንቂያ ስርዓት ያለው ነው።
*
√ መግቢያዎቹ በግራናይት አደባባዮች የተሸፈኑ ሲሆን የመስጂዱ ግቢ ወለል የእብነ በረድ ንጣፎች እና የመስታወት ግድግዳዎች አሉት።


©: ሀሩን ሚድያ
Forwarded from Human and Humanity
1,እንኳን ተኝተህ ነቅተህም ትሄዳለህ
.
.
.
.
ከባለፈው የቀጠለ
===========

ጊዜን የሚያባክኑ አሥራ አምስት(15) ነገሮችንም በጥናታቸው ዘርዝረዋል፤

አንደኛ፦ ስለ ሕይወት ያለን የተዛነፈ አረዳድ፣
ሁለተኛ፦ ጥርት ያለ የሕይወት ግብ አለመኖር
ሶስተኛ፦ በነገሮች ላይ መወሰን አለመቻል፣
አራተኛ፦ የስሜት መዘበራረቅ መፈጠር፣ አምስተኛ፦ ስንፍና፣
ስድስተኛ፦ ትኩረት ማጣት፣
ሰባተኛ፦ የሚመች ጊዜ መጠበቅ፣
ስምንተኛ፦ ሱስኝነት፣
ዘጠነኛ፦ እንቅልፍ ማብዛት፣
አስረኛ፦ የዝቅተኝነት ስሜት፣
አስራ አንደኛ፦ ብዙ በማይጠቅሙ ነገራቶች ላይ ማተኮር፣
አስራ ሁለተኛ፦ የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም፣
አስራ ሶስተኛ፦ ትኩረት ፈላጊ ባሕልና ቤተሰብ ውስጥ መሆን፣
አስራ አራተኛ፦ ፍጹማዊነትን መጠበቅ፣
አስራ አምስተኛ፦ የመዝናናት ትርጉም መሆናቸውን ገልጸዋል። እዚህ ያልተጠቀሱ ነገር ግን እንደግል የሚመለከቱንን ነገሮች ደግሞ ነቅሶ የማስወገድ ጉዳይ የሚመለከተው እኛኑ መሆኑ መረሳት የለበትም።

ምሁራኑ ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም የሚከተሉትን አሥር ነገሮች ማድረግ ወሳኝ መሆኑንም አስፍረዋል፤
አንደኛ፦ ሕይወትን ከዓላማ ጋር ማሰር።
ሁለተኛ፦ ጊዜ ገዳይ ነገሮችን የተቻለውን ያህል ማስወድ።
ሦስተኛ፦ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ለይቶ ቅድሚያ መስጠት።
አራተኛ፦ አሉታዊ ልማዶችን መንቀልና አዎንታዊ ልማዶችን መከተል።
አምስተኛ፦ ተግባርን በትናንሹ መከፋፈል።
ስድስተኛ፦በአስፈላጊው ቦታ እምቢ ማለትን መልመድ።
ሰባተኛ፦ ጥርት ያለ ግልፅ የህይወት ግብ መከተል።
ስምንተኛ፦ አእምሮን የሚያነቃቁና የሚያድሱ ነገሮችን ማድረግ።
ዘጠነኛ፦ በተመረጠ ሰአት የተመረጠ ነገር ማድረግ።
አስረኛ፦ ስሜትን ማደስ ናቸው። (በዋናነት ከዶ/ር ኢሃብ ፊክር እና ከዶ/ር ዐሊይ ዐባስ የድምፅ ትምህርቶች ላይ የተቀነጨቡ ናቸው)

ታላቁ ቁርአንም ስለ ጊዜ በተለያዩ አንቀጾቹ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል። ለምሥሌ የሚከተሉትን አንቀጾች እንመልከት፤
.
.
.
.
.
ይቀጥላል.....
============
ምንጭ፦ የማር ጠብታ ከሚለው መጽሓፍ
============

Join our telegram channel for,more topic፦

https://www.tgoop.com/Humanity02H
Forwarded from ሲልዐቱላህ(سلعة الله) (miqbas(፪), miqbasudin(፪))
.    አስደሳች ዜና
.   بشرى سارة
جمعية الدعوة والإرشاد وتوعية الجاليات بحي الصحافة (مشكاة) - الرياض
በሳዑዲ ሪያድ (ሐይ ሰሓፋ) የሚገኘው የደዕዋና የማህበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ማህበር ( ሚሽካህ ) ዘርፈ ብዙ የሆኑ የተለያዩ ኢስላማዊ ዕውቀቶችን በነፃ በርቀት (online) ለማስተማር ዝግጅቱን ጨርሶ እርስዎን እየተጠባበቀ መሆኑን ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው፡፡
.
በማህበሩ የሚሰጡ ፕሮግራሞች፦
•  አዲስ ወደ ኢስላም ለተመለሱ ሰለምቴዎች የቁርኣን እና ሌሎች ት/ቶች፣
•  ለጀማሪዎች ቃዒደቱ ኑራኒያ፣
•  ቁርኣን ማስተካከል ( ተስሒሑል ቁራኣን)፣
•  መሰረታዊ የኪታብ ትምህርት፣
•  የደዕዋና ምክር አገልግሎት፣
ፕሮግራሙ የሚሰጥበት፦
•  ቀን፦ ከዕሁድ - ሀሙስ ( ጁሙዓና ቅዳሜ ሲቀር)
•  ሰዓት፦ በሳዑዲ አቆጣጠር ከ4፡00 – 8፡00 pm(ከዐስር ሰላት -ዒሻ ሰላት)

ልብ ይበሉ! ፕሮግራሙ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውስጥ ለርስዎ በሚመች ቀንና ሰዓት ማድረግ ይችላሉ።
.
ለበለጠ መረጃ፦ +966597832809
  whatsapp https://wa.me/qr/NPBHH5AKWC56P1
  telegram  www.tgoop.com/StudentImamuUniversity

جمعية الدعوة والإرشاد وتوعية الجاليات بحي الصحافة (مشكاة) - الرياض
2025/02/06 20:28:12
Back to Top
HTML Embed Code: