Telegram Web
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 65)
----------
11፤ በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።

12፤ የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ


#እንካን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም በጤና በፍቅር አደረሳችሁ/አደረሰን
#በዓሉ የሰላም የፍቅር የጤና እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴ ነው

#መልካም #አዲስ #አመት

😊😊😊
የተሰቀለውን እንጂ የተሰቀለበትን አንሰብክም ለሚሉ ሀሰተኞች ወንድሞቻችን የተሰጠ ድንቅ ምላሽ!
'' የተሰቀለውን ነው የተሰቀለበት ነው የሚያድነው ? ''

ጌታ በቀራንዮ እናቱን በቅዱስ ዮሐንስ አማካኝነት ለሁላችን እናት አድርጎ አንደሰጠን መስቀሉንም ትዕምርት አድርጎ ለሁላችን ሰጥቶናል :: የመስቀሉ ነገር ሲነሳ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስ ከተሰቀለበት መስቀል ለመለየት አዳኙ ክርስቶስ እያለ የምን መስቀል መስቀል ማለት የሚሉ አሉ ::

እንደነዚህ ያለው አመለካከት ''ሐኪሙ እያለ የምን መድሐኒት መድሐኒት ማለት ነው ? '' ክርስቶስ ነው ወይስ የሰበከው ወንጌል ነው የሚያድነው
ብሎ እንደመጠየቅ ነው !

ይህን ጥያቄ የሚጠይቁ ሰዎች ጥያቄያቸው እኛን ብቻ ሳይሆን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስንም ይመለከታልና ስለምን ክርስቶስ ጥልን በኃይሉ ወይም በአምላክነቱ ገደለ ከማለት ይልቅ "ጥልንም በመስቀሉ ገድለ" (ኤፌሶን ሰዎች 2: 16) እንዲሁም የሚቃወመንን ዲያቢሎስ ከመንገድ አስወገደው ከማለት ይልቅ "በመስቀል ጠርቆ
ከመንገድ አስወግዶታል" (ቆላስይስ ሰዎች 2: 14 ) ብሎ እንደጻፈ ይጠይቁልን !

መጽሐፍ ቅዱስ ታቦትን "የእግዚአብሔር የቃልኪዳኑ ታቦት" እያለ ይገልጸዋል ስለ ቅዱሳን መላእክትም በተነገረበት ሥፍራ ሁሉ ደግሞ "የእግዚአብሔር መልአክ" እያለ የቃልኪዳኑ ታቦትም ይሁን ቅዱሳን መላእክት የእግዚአብሔር እንጂ የሌላ የማንም ስላልሆኑ ማንም ከእግዚአብሔር እንዳይለያቸው አንባቢ ያስተውል ዘንድ መጽሐፍ በግልጥ ያብራራል ::

የሐዲስ ኪዳን ልዩ የደሙ ምልክት የሆነው የምንመካበት መስቀልንም የክርስቶስ ነውና ማንም ከመድሃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ
እንዳይለየን መጽሐፉ ያስጠነቅቀናል " ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።" (ገላትያ ሰዎች 6: 14)

ብዙዎች ጌታችንን በመስቀሉ ላይ በቀራኒዮ ተሰቅሎ ባዩት ጊዜ ደጋግመው እናምንብህ ዘንድ "ከመስቀሉ ውረድ.... " ሲሉት ነበር (የማርቆስ ወንጌል 15: 30) መድኃኔዓለም ክርስቶስ ግን
ያምኑበት ዘንድ አምላክነቱም ይገለጥም ዘንድ ከመስቀሉ ላይ መውረድን እንቢ አለ ! ይልቁንም በመስቀሉ ላይ ሞቶ ሕይወትን ሰጠን !

በአምላካዊ ደሙ መፍሰስም መስቀሉን እንድንበት ዘንድ ቀደሰው ! ከዚያች ሰዓትም ጀምሮ ክርስቶስን ለሚያምኑ ሁሉ የሕይወት ዕፅ ሆነ ::

ዛሬም ክርስቶስን ለመምሰል ለምንጋደል ሁላችን መስቀሉን ከአንገታቹ አውልቁ ወደ መስቀሉ አትመልከቱ ስለ መስቀሉ አትተንፍሱ እያሉ ከመስቀሉ ላይ ሊያወርዱን የሚጥሩ ቢበዙም
ከመሰቀሉ ላይ ለቅጽበት ዓይናችንን ዞር አናደርግም ! በመስቀሉ የተከፈለልንን የደም ዋጋ ስለምናውቅ ከመስቀሉ ለአፍታም ቢሆን አንወርድም !

ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረ እኛ ግን በመስቀል
ላይ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአዲስ ኪዳን አይሁዶች ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1: 23)
"እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።" (የማቴዎስ ወንጌል 16: 24)

የሚለውን ጥቅስ ቤተክርስቲያናችን ምስጢራዊ ፍቺውን አጉልታ የምታስተምር ቢሆንም እጅግ በሚደንቀው ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱስ መተርጎም የለበትም በቀጥታ እንደወረደ ነው ማንበብ ያለብን
ምንም ምስጢራዊ ፍቺ የለውም ግልጽ (ቀላል ልሳን) ነው የሚሉን መስቀልን የተመለከተ ጉዳይ ሲሆን ግን የአንድምታ መተርጉማን ሆነው
አንድም እንዲ ነው አንድም እንዲያ ነው እያሉ ጉባኤ ቤት ሲቀመጡ ለተመለከተ በስሙ እያመኑ ቅዱስ ጳውሎስ "ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ሆነው ይመላለሳሉ" (ፊልጵስዩስ
ሰዎች 3:18) ብሎ አንደተናገረ ።

ነገረ መስቀሉን ለመቃወም ዶግማቸውን እስከ መቀየር ያደረሳቸው ምን እንደሆነ ለመረዳት
አስቸጋሪ ነው :: ራሷ ክርስቶስ የሆነላት ቅድስት ቤተክርስቲያን ግን ዓይኖቿ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ስለተሣለባት ዘወትር አካላቷ
የሆንን ምእመናን ልብ ውስጥ መስቀሉ እስኪተከል ድረስ ስለ መስቀል ትሰብካለች ፣ ትዘምራለች ፣በመስቀል ትቀድሳለች ፣ በመስቀል
ትባርካለች ፣ ልጅነትን ትሰጣለች ፣ አገልግሎቷንም ሁሉ በመስቀል ጀምራ በመስቀል ትፈጽማለች !

ዲ/ን ዶ/ር ዳዊት ከበደ
ምንጭ:-
መስከረም 15/1/2015 ዓ.ም
😊መስቀል


መስቀል ዕፀ ሕይወት ነው። መስቀል ዕፀ መድኃኒት ነው። መስቀል ዕፀ ትንቢት ነው። መስቀል ዕፀ ዕረፍት ነው።

መስቀል ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው። የአጋንንትንም ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው።

መስቀል ርኵሳን መናፍስትን የሚወጋቸው የእሳት ዘገር ነው። የአመስቴ ማውያንንም ሠራዊት የሚመታ የመብረቅ ጦር ነው።

መስቀል ማኅተመ ሥላሴየሌለው ሰው ወደእርሱ ሊቀር በው የማይቻለው አምባ መጠጊያ ነው። መስቀል ከግራም ከቀኝም ለሚመጣ ጠላት የጽድቅ ጋሻ ነው። ጳውሎስ ውጊያችሁ ከሥጋና ከደም ጋር አይደለምን እንዳለው መስቀል የጦር መሣርያ ነው።

መስቀል የጦር ውጋት ሊቀድደው፣ የቀስትና የዘንግም ጫፍ ሊበላው የማይችል የሃይማኖት ጥሩር ነው።

መስቀል አማሌቃውያንን ለመዋጋት በራፊድ በረሐ በተዘረጋው ስሙሴ እጅ አምሳል የተሠራ ነው።

መስቀል ሰሙሴ እጅ ወደ ውስጥ በተጨመረ ጊዜ መራውን ውኃ በቀር በረሐ ያጣፈጠ ነው። መስቀል የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም ነው።

መስቀል ለሚጋደሉ የድል አክሊል፤ ወደ በጉ ሰርግ ለተጠሩትም የሰርግ ልብሳቸው ነው። መስቀል የማይነጥፍ ምንጭ፣ በቁዔትም ጥቅምም የሞላበት የክብር ጉድጓድ ነው።

(ውዳሴ መስቀል በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

@linkortodoxe21
ተማሪዎች ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ምን ብለው ይጸልዩ?

የግብፅ ቤተክርስቲያን በቅርቡ ማዕረገ ቅድስና የሠጠቻቸው ቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡ ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡) በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡

ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡

+++ ጸሎት +++

‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ

‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ!

አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡

ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡

ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡

ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!"

ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን!

#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ
"እገድልሐለሁ ያልከኝ እውነትም ገደልከኝ።"

.በአንድ ወቅት ከቤ/ክን አገልጋይ ከነበረ ሰባኪ ሲመሰከር ከሰማሁት እውነተኛ ታሪክ ላካፍላችሁ። አንድ እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚያገለግል ዲያቆን
ነበር። የዚህ ዲያቆን ጎረቤት የሆነ ሠውም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ይህን ዲያቆን በጣም ጠምዶ ይዞት ነበር። በመንገድ ላይ ባገኘው ቁጥር በጣም አስጸያፊ ስድብ ከመስደብ ጀምሮ ቆሻሻ ውሐ በላዩ ላይ እስከመድፋት እንዲሁም ካልደበደብኩት እያለ በገላጋይ ነበር የሚለመነው ዲያቆኑ ግን ይህ ሁሉ ሲሆን "እግዚአብሔር ይባርክህ ያስብህ" ከማለት ውጪ ምንም የክፋት ቃል ከአንደበቱ አይወጣም ነበር። ከእለታት በአንዱ ቀን ግን ዲያቆኑ ምርር ብሎት ሠውየውን "እገድልሐለሁ።" ብሎት ይሄዳል። ሠውየውም ይሄ ዲያቆን እገድልሐለሁ ያለኝ ምን ገዝቶ ነው ቦንብ ነው? ሽጉጥ ነው? ዱርየ ነው? በማለት መጨናነቅ ይጀምራል።

. ከእለታት በአንዱ ቀን ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ ዲያቆኑ ከቅዳሴ ወጥቶ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲሔድ መንገድ ላይ ሕዝብ ተሰብስቦ ያያል። ጠጋ ብሎ ምን እንደተፈጠረ ይጠይቃል። ሠዎቹም አንድ ተሽከርካሪ አንድ ሕጻን ልጅ
ገጭቶ እንዳመለጠ ይነግሩታል። ጠጋ ብሎ ሲያይም የተገጨው የዚያ እርሱን የሚሰድበውና የሚያዋርደው
ሠውየ ልጅ መሆኑን ይረዳል። በኋላም ልጁን ከነደሙ ይሸከምና ኮንትራት ታክሲ ጠርቶ ልጁን ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ይወስድና ያሳክመዋል። የልጁ አባትም ሥራ ቦታ ነበርና ልጁ ተገጭቶ ወደ
ዘውዲቱ ሆስፒታል መወሰዱ ተደውሎ ይነገረዋል። ሠውየውም ዘውዲቱ ሆስፒታል ሔዶ ልጁ የተኛበት ክፍል
ሲገባ ልጁ ጉሉኮስ ተሰክቶበት ተኝቶ አጠገቡ ደግሞ ያ አልወደውም ጠላቴ እያለ የሚሰድበው ዲያቆን ? ሲያስታምመው ያያል። በአካባቢው የነበሩ ጎረቤቶቹም ልጁ በመኪና እንደተገጨና ያ ጠላቴ የሚለው ዲያቆን
አምጥቶ እያሳከመው እንደሆነና እሱ ባያሳክመው ልጁ ሊሞት ይችል እንደነበር ነገሩት። ሠውየውም ዲያቆኑን ጠርቶ "እገድልሐለሁ ያልከኝ
እውነትም ገደልከኝ። አሁን ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ? " ሲለው
ዲያቆኑም "እኔ ምንም አልፈልግም ከነ ቤተሰቦችህ ንስሐ ግባ ሥጋ ወደሙ ተቀበል። እኔ የምመኝልህ ይህን ብቻ
ነው።" ብሎ አለው።

.በኋላም ዲያቆኑን የሚያውቁት ሰዎች "ለመሆኑ ሠውየዉን እገድልሐለሁ ያልከው ለምንድን ነው? " ብለው
ሲጠይቁት ዲያቆኑም "እኔ እኮ እገድልሐለሁ ያልኩት ሠውየውን
አይደለም እኔ እገድልሐለሁ ያልኩት በሰውየው ላይ አድሮ የሚረብሸኝን ዲያብሎስን ነው። እግዚአብሔርም
ዲያብሎስን መግደያ ምክንያትና ጥበብ እንዲሰጠኝ ስጸልይ ነበር። ልጁ የተገጨውም እግዚአብሔር ለእኔ
ዲያብሎስን መግደያ ምክንያት ሊሰጠኝ ነው። እኔም የሰጠኝን ምክንያት ተጠቀምኩና እንደዛትኩት ዲያብሎስን
ገደልኩት።" ብሎ አላቸው። ግሩምና በጣም ጣፋጭ ትምህርት ነው። እኔ እራሴን ታዘብኩት እናንተስ? ከዲያቆኑ ምን ተማራችሁ?

(ይሄን ፁሑፍ የትም ልታነቡት ትችላላችሁ ዋናው አንብባችሁ መማር መቻላችሁ ነው)
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟ (✟Mentesenhot✟)
#ደብረ_ታቦር (ነሐሴ 13)

ነሐሴ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅና ክቡር በዓል ነው።

በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ። ስለ እነርሱም ጌታችን የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ አለ።

ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ።
ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ላንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ።

በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት። ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና ራሱን የሚሠውርበትን ቤት ይሠራለት ዘንድ የተናገረው ነው። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልንጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው። ራሱንና ባልንጀሮቹ ሐዋርያትን እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና።

ሰለ ሐዋርያትም የእውቀት ማነስ አታድንቅ በዚያን ጊዜ ፍጹማን አልሆኑምና። እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ እነሆ ደመና ጋረዳቸው።

የጌታችንን ጌትነቱን የሚገልጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ። ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱንም ስሙት።

ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋራ ሲነጋገሩ ተሰሙ ስለ ርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነቢያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው።

ሁለተኛም የአብን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእነርሱ ሥውር የነበረ የወልድ ዋሕድን በእውነት ሰው መሆን በዚያን ጊዜ ተረዱ ያን ጊዜ የጌትነቱ ክብር ተገልጦአልና። ሐዋርያትም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሣው ኤልያስንም ያሳረገው አውርዶም ያመጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና። በሰማይና በምድር ሥልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ሊአስነሣቸው ማንም አይችልም።

ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች ከብሉይና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና። የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግምባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ እንደ ሙታንም ሆኑ። ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስም ወደ ቦታው ተመለሱ።

ሐዋርያትንም በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም። ከባሕርያችን የተዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ።

እንግዲህ እናስተውል ሰው ካልሆነ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታቸንን ድንግል ማርያምን በአበሠራት ጊዜ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው እንዴት አላት። አምላክ ካልሆነስ ለመንግሥቱ ፍጻሜ የለውም እንዴት አላት። ሰው ካልሆነ በበረት እንዴት አስተኙት። አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው እያሉ እንዴት አመሰገኑ።

ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውኃ እንዴት አጠመቀው አምላክስ ካልሆነ አልዓዛርን ከመቃብር እንዴት ሊያስነሣው ቻለ። ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው እንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለ መለየት አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ሁል ጊዜ አንድ ህላዌ ነው ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።🙏🙏🙏

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ነሐሴ)

#join or #share
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19 @Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
በፍልሰታ ምጽዋት😍
@linkortodoxe21
📚በደብረ ታቦር ላይ ሙሴና ኤልያስ ለምን ተገኙ???



ሁላችሁም በ comment ላይ ተሳተፉ 👇👇👇

መልሱን አየዋለሁ
https://www.tgoop.com/Ortodoxe21

ሁላችንም እንሳተፍ
እንካን አደረሳችሁ 🙏🙏🙏
@linkortodoxe21
መልካም የቡሄ በዓል እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴ ነው
#አማን_በአማን

አማን በአማን /2/ ተሰብሐ
አማን በአማን /2/ ተሰብሐ
በደብረ ታቦር /2/


@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
#ቡሄ_በሉ

ቡሄ በሉ (2) ልጆች ሁሉ የኛማ ጌታ   
የዓለም ፈጣሪ የሰላም አምላክ
ትሁት መሀሪ በደብረ ታቦር የተገለጠው
ፊቱ እንደ ፀሐይ በርቶ የታየው
ልብሱ እንደብርሃን ያንፀባረቀው

ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን(2)

ያዕቆብ ዮሐንስ እንዲሁም ጴጥሮስ
አምላክን አዩት ሙሴ ኤልያስ
አባቱም አለ ልጄን ስሙት
ቃሌ ነውና የወለድኩት
     
ታቦር አርሞንኤም ብርሃን ታየባቸው
ከቅዱስ ተራራ ስምህ ደስ አላቸው
ሰላም ሰላም የታቦር ተራራ
ብርሀነ መለኮት ባንቺ ላይ አበራ
     
በተዋህዶ ወልድ የከበረው
የእግዚአብሔር አብ ልጅ
ወልደማርያም ነው
ቡሄ በሉ/2/ የአዳም ልጆች
ብርሃንን  ተቀበሉ
     
አባቴ ቤት አለኝ ለከት
እናቴ ቤት አለኝ ለከት
አጎቴም ቤት አለኝ ለከት
ተከምሯል እንደ ኩበት
     
የዓመት ልምዳችን ከጥንት የመጣው
ከተከመረው ከመሶቡ ይውጣ
ከደብረ ታቦር  ጌታ ሰለመጣ
የተጋገረው  ሙልሙሉ ይምጣ
     
ኢትዮጵያውያን ታሪክ  ያላችሁ
ባህላችሁን ያዙ አጥብቃችሁ
ችቦውን አብሩት እንዳባቶቻችሁ
ምስጢር ስላለው ደስ ይበላችሁ
     
አባቶቻችን ያወረሱን
የቡሄን ትርጉም ያሳወቁን
እንድንጠብቀው ለእኛ የሰጡን
ይህን ነውና  ያስረከቡን
     
ለድንግል ማርያም  አሥራት የሆንሽ
ቅዱሳን ጻድቃን የሞሉብሽ
በረከታቸው ያደረብሽ
ሁሌም እንግዶች የሚያርፉብሽ
ሀገረ እግዚአብሔር  ኢትዮጵያ ነሽ
     
ለሐዋርያት የላከ መንፈስ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ጸጋውን ያፍስስ
በበጎ ምግባር እንድንታነጽ
በቅን ልቦና በጥሩ መንፈስ
በረከተ ቡሄ  ለሁላችን ይድረስ
     
ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በጋሽዬ ቤ   ድገም እና ዓመት ድገም እና
ያውርድ በረከት  ድገም እና ዓመት ድገም እና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና

በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና
     

እንዲሁ እንዳላችሁ በፍቅር  አይለያችሁ
ላመቱ በሰላም በፍቅር  ያድርሳችሁ
ክርስቶስ በቀኙ በፍቅር  ያቁማችሁ
የመንግስቱ ወራሽ በፍቅር  ያድርጋችሁ
እንዲሁ እንዳለን በፍቅር  አይለየን
ለዓመቱ በሰላም በፍቅር ያድርሰን
አማኑኤል በቀኙ በፍቅር ያቁመን 
የመንግስቱ ወራሽ በፍቅር ያድርገን


የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት(2) ይግባ በረከት(2)

እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት
የአስራት አገር የአበው ቀደምት
የቅዱሳን አባቶች ትውፊት
ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት
ባህላችንን የአባቶች ትውፊት (3)

#join #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
2025/06/29 07:49:46
Back to Top
HTML Embed Code: